ዓርብ 31 ጃንዋሪ 2014

የአማራው ክልል መሪ በአማራው ህዝብ ላይ ተሳለቁ

-የአማራ ክልል ም/ ፕሬዚዳንት እና የብአዴን ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን “የአማራው ህዝብ ሰንፋጭ የሆነ ትምክተኝነት የተጠናወተው በመሆኑ በቤንሻንጉልና በሌሎችም ቦታዎች ለመሰደዱ ምክንያት ሆኖታል” በማለት፣ ለብአዴን ነባርና አዳዲስ ካድሬዎች ተናግረዋል።
ካድሬዎቹ “የአማራው ህዝብ ለምን ይሰደዳል? ለምን በእየክልሉ ጥቃት ይደርስበታል? አማራውን ከጥቃት ለመከላከል ለምን ሙከራ አይደረግም በማለት ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን፣ ም/ል ፕሬዚዳንቱ የአማራው ህዝብ በቅድሚያ እንዳይሰደድ ለማድረግ ስራ እየተሰራ ነው፣ ነገር ግን ከተሰደደ በሁዋላም ቢሆንም ሰንፋጭ የሆነውን ትምክህተኝነቱን በመተው ከሌላው ጋር ለመኖር መልመድ አለበት ብለዋል።
አማራው “በባዶ እግሩ እየሄደ የሚናገረው ንግግር ግን መርዝ ነው” ያሉት ምክትል አስተዳዳሪውና የብአዴን የጽህፈት ቤት ሃላፊው፣ ይሄ መርዝ ንግግሩ አንድ የሚያደርግ አይደለም ሲሉ አክለዋል።
ከኢትዮጵያውያን ጋር አብሮ ለመኖር አማራው  የትምክህት ለሃጩን ማራገፍ አለበት ያሉት አቶ አለምነው፣ ይሄ ለሃጭ ሳይራገፍ በጋራ መኖር አይቻልም ሲሉ ድምድመዋል።
ማንኛውም ስም ያወጣ ሙትቻ ፓርቲ ሁሉ መንገሻው አማራ ክልል ነው ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ፣ ምክንያቱንም ሲገልጹ ትምክህትን እንደ ምግብ ስለሚመገበው ነው ብለዋል። ያንን ምግብ እየተመገበ እንደሚያቅራራም ገልጸዋል።
አንዳንድ የብአዴን አባላት የምክትል ፕሬዚዳንቱ ንግግር እጅግ እንዳበሳጫቸው ለኢሳት ተናግረዋል።
የብአዴን ካድሬዎች አንቀጽ 39 ለምን አይወጣም በማለት ላነሱት ጥያቄ፣ እኝሁ ፕሬዚዳንት ሲመልሱ አንቀጽ 39 ባይኖር ኖሮ ኢትዮጵያ  ደቡብ ሱዳን እንደሆነቸው ትሆን ነበር በማለት መልሰዋል ። አንቀጽ 39 በህዝቦች ዘንድ መተማመን መፍጠሩን፣ አቶ መለስ ዜናዊ በሞቱበት ጊዜ በገሃድ መታየቱን ም/ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል
የድምጽ ማስረጃውን ቀርጸው ለላኩለን በስብሰባው ላይ የተካፈሉ የህክምና ባለሙያዎችን ለማመስገን እንወዳለን።

የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ጎንደር ላይ ታሰሩ

ድንበር ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ እና በሱዳን መንግስታት መካከል ያለው ንግግር ለህዝብ ግልጽ እንዲሆን ለመጠየቅ በመጪው እሁድ በጎንደር ከተማ ለማካሄድ የታቀደውን ሰልፍ ለማስተባበር ወደ ጎንደር ያቀኑት የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ፣ ሌሊት ከተማዋ ደርሰው በማግስቱ የቅስቀሳ ስራ ሲጀምሩ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል።
አመራሮቹ ሲታሰሩ የተመለከተ አንድ ታዛቢ ከኢሳት ጋር ባደረገው አጭር ቆይታ እንደገለጸው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው ወጣት ብርሃኑ ተክለያሬድ፣   ዮናታን ተስፋየ፣ ወይንሸት ሞላ፣ አቤል ኤፍሬምና ጌታነህ ባልቻ ታስረዋል።
ሰማያዊ ፓርቲ በመጪው እሁድ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ የቅስቀሳ ስራ በመስራት ላይ ይገኛል። ሰሜን ጎንደር ፖሊስ አዛዥን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።
ባለፈው አርብ በትግራይ አዲግራት ከተማ ከህዝብ ጋር ለመወያየት ለቅስቀሳ ስራ ሄደው የነበሩት አቶ አስገደ ገብረስላሴ፣ መምህር አብርሃ ደስታና አቶ አምዶም ገብረስላሴ መደብደባቸው ይታወቃል።

እሑድ 26 ጃንዋሪ 2014

Prof Mesfin on Ethio Sudan border dispute



Prof. MesfinAwramba
Times (Addis Ababa) – Professor Mesfin Woldemariam Speaks out on recent
controversy of Ethio-Sudan border demarcation Issue and its historical
context. The event was organized by Semayawi Party. Please watch





ዓርብ 24 ጃንዋሪ 2014

Yegna Temnet New Ethiopian Music 2014

“የአዲስ አበባ ተማሪዎች ለከፍተኛ የስነ ምግባር ጉድለት ተጋልጠዋል”

ተማሪዎች ያለዕድሜያቸው ጫት፣ ሲጋራና ልቅ ወሲብ ይጀምራሉ
ሴት የቢሮ ሠራተኛ ሴቶች በወሲብ ንግድ ኑሮአቸውን ይደጉማሉ

በአዲስ አበባ ከአንደኛ ደረጃ እስከ ከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች፤ ለከፍተኛ የስነ ምግባር ጉድለቶች እንደተጋለጡ ጥናቶች አመለከቱ፡፡ ሰሞኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ከባለድርሻ አካላት ጋር “ስነምግባር ለእድገት ሁሉ መሠረት ነው” በሚል ርዕስ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ በቀረቡት ጥናቶች በተለይ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፤ በየትምህርት ቤቶቹ አካባቢ ባሉ ህገወጥ የአልኮል፣ የአደንዛዥ እጽ መጠቀሚያ እና የወሲብ ፊልሞች ማሣያ ቤቶች መበራከት የተነሣ ለችግሩ ተጋላጭነታቸው በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩ ተጠቁሟል፡፡ አብዛኞቹ ተማሪዎች ወሲብ መፈፀም የሚጀምሩት በዚሁ የትምህርት ደረጃ ላይ እያሉ ነው ተብሏል፡፡ ከጥናት አቅራቢዎቹ አንዷ የሆኑት ወ/ሮ ጽዮን አክሊሉ በጥናታቸው እንዳመለከቱት፤ ተማሪዎች ሲጋራ፣ የአልኮል መጠጥ፣ ጫት እና ልቅ ወሲብ የሚጀምሩት በአብዛኛው ሁለተኛ ደረጃ ከገቡ በኋላ ሲሆን 41.5 በመቶ የሚሆኑት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያሉ ሲጋራ ማጨስ እንደሚጀምሩ ጠቅሰው፤ 67.1 በመቶ ያህሉ ደግሞ በዚህ የትምህርት ደረጃ ወሲብ መፈፀም ይጀምራሉ ብለዋል፡፡
18.1 በመቶ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎችም ያለ እድሜያቸው በሲጋራ ሱስ የሚጠመዱ ሲሆን 20.6 በመቶዎቹም በዚህ የእድሜ እርከን ውስጥ ወሲብ መፈፀም እንደሚጀምሩ ተጠቁሟል፡፡ የአልኮል መጠጥ እና የጫት ተጠቃሚነትን መጠን በተመለከተ ከሌሎች የትምህርት ደረጃዎች ይልቅ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በከፍተኛ ደረጃ የድርጊቱ ጀማሪዎችና አዘውታሪዎች እንደሆኑ ጥናቱ ይገልፃል፡፡ በጥናቱ ከተካተቱ ተማሪዎች መካከል 51.4 በመቶዎቹ የአልኮል ተጠቃሚነትን የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያሉ የጀመሩ ሲሆን፤ 27.2 በመቶዎቹ ደግሞ የአንደኛ ደረጃ ተማሪ እያሉ ጀምረዋል፡፡ 44.6 በመቶ የሚሆኑት ጫት የጀመሩት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያሉ ሲሆን፤ 15.1 በመቶዎቹ ደግሞ የ1ኛ ደረጃ ተማሪ እያሉ መጀመራቸው ታውቋል፡፡ በተለይ የአንደኛ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በከፍተኛ መጠን ያለእድሜያቸው ለአጓጉል ድርጊቶች መጋለጣቸው፣ በስነምግባር የታነፁ ዜጐችን በማፍራት ረገድ አገሪቱ ፈታኝ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ አመላካች ነው ብለዋል - ጥናት አቅራቢዋ፡፡ እጽና አልኮል መጠቀም፣ ልቅ ወሲብ ከመፈፀም ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለው ያመላከቱት አጥኚዋ፤ በተለይ ለችግሩ ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑት የከተማ ልጆች ሲሆኑ ወላጆቻቸው የተማሩ የሚባሉና ከፍ ያለ የገንዘብ አቅም ያላቸው እንደሆኑ ጠቅሰዋል። ከገጠር አካባቢ የሚመጡ ተማሪዎች በአንፃሩ የገንዘብ አቅማቸው አነስተኛ በመሆኑ፣ አልኮልና እፆችን እንዲሁም የወሲብ ተግባራትን እንደልባቸው ለመፈፀም እንደሚቸገሩ ተጠቁሟል፡፡
በእነዚህ የትምህርት ደረጃዎች ያሉና የአቻ ግፊት ሳይበግራቸው ከእነዚህ ሁሉ ሱሶች ነፃ ሆነው የተገኙት ለስነ ምግባራቸው መታነጽ ምክንያቱ፣ በወላጅ ምክር ያደጉና የሃይማኖት ጥንካሬ ያላቸው መሆኑን ያመለከቱት ጥናት አቅራቢዋ፤ የሃይማኖት ተቋማት በዚህ ረገድ ጠንካራ ስራ ለመስራት ቢሞክሩ የበለጠ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል ጠቁመዋል፡፡ በእኚሁ ጥናት አቅራቢ የቀረበው ሌላው ርዕሰ ጉዳይ በጐልማሶች ላይ ያተኮረ ሲሆን በሀገራችን ከ150ሺህ በላይ ሴተኛ አዳሪዎች እንዳሉ ቢገመትም በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ደረጃ ሴት የቢሮ ሠራተኞች እና ተማሪዎች በወሲብ ንግድ ተሰማርተው በአቋራጭ ተጨማሪ ገቢ እያገኙ ኑሮአቸውን እየደጐሙ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ለዚህ ልማድ መስፋፋት ደግሞ ባለሃብቶችና በእድሜ የገፉ ሰዎች አማጋጭ እየሆኑ መምት፣ የመዲናዋ የቱሪስቶችና ዓለማቀፍ ክንውኖች ማዕከልነቷ ማደጉና የጥበብ ውጤቶች ስለ ወሲብ የተዛባ አመለካከት ይዘው ብቅ ማለታቸው በምክንያትነት ተቀምጧል፡፡ ማሣጅ ቤቶችና ራቁት የዳንስ ቤቶች ወሲብ ንግድ መስፋፋቱ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውም በጥናቱ ተጠቅሷል፡፡
ለእነዚህ ሁሉ የስነምግባር ጉድለቶችና ማህበረሰባዊ እሴቶች ውድቀት የህግ ክፍተት መኖሩ ትልቅ ሚና እንዳለው ባይካድም፣ በመንግስት ሚዲያዎች ሳይቀር የሚተላለፉ የማስታወቂያ መልዕክቶች፣ የቃላት አመራረጥና የፕሮግራም አቅራቢዎቹ አለባበስ፣ የመረጃዎች ፍሬ ሃሳብ እና ስነ ምግባር የጐደላቸው ጽሑፎች በስፋት መስተናገድ አስተዋጽኦ አበርክተዋል ተብሏል፡፡ ሌላው ጥናት አቅራቢ አባ በአማን ግሩም የተባሉ የሃይማኖት አባት በበኩላቸው፤ ከቤተሰብ እስከ አገር አቀፍ ደረጃ የመከባበር እሴት መጥፋት፣ ማታለልና ሙስና መስፋፋት ለትውልዱ በስነምግባር አለመታነጽ እንደምክንያት ካቀረቧቸው መካከል ይጠቀሳሉ፡፡ ይሄን ለመቀየር ከሃይማኖት መሪዎችም ሆነ ከመንግስት የስራ ሃላፊዎች የአርአያነት ተግባር እንደሚያስፈልግ የጠቆሙት አባ በአማን፤ እነዚህ አካላት የትውልዱን ስነምግባር በማነጽ ረገድ ያላቸው ሚና እንዲጐላ ቢደረግ መልካም ነው ብለዋል፡፡ ምቀኝነት፣ ውሸት፣ ሃሜት፣ ስርቆት፣ ሙስና፣ የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ፣ አስገድዶ መድፈር፣ የአደንዛዥ እፅ ዝውውርና ተጠቃሚነት እንዲሁም ሽብርና ጦርነት በዓለም ላይ መበራከታቸው ለስነምግባር እሴቶች መጓደል ምክንያት መሆኑን የዘረዘሩት ሌላው ጥናት አቅራቢ ሐጂ አብዱልሃማድ አቡበከር፤ መንግስት እና የሃይማኖት ተቋማት እንዲሁም ማህበረሰቡ በጋራ ኢትዮጵያውያን ወጣት ተማሪዎች ከእነዚህ የስነምግባር ጉድለቶች የሚርቁበትን አቅጣጫ ማሳየት እንደሚገባቸው አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ የከተማው የትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ዲሳሞ ኦቶሬ በበኩላቸው፤ ተማሪዎችን ከአልኮል፣ አደገኛ እጽ፣ ጫት እና ከወሲብ ሱስ ተጋላጭነት የራቁ ለማድረግ ቢሮአቸው የተለያዩ የድርጊት መርሃ ግብሮችን ቀርፆ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ ከተለያዩ የባለድርሻ አካላት ጋር በመሆንም፣ ለእነዚህ መጤ ልማዶች መስፋፋት ምክንያት የሆኑ የንግድ ቤቶች ከትምህርት ቤቶች አካባቢ የሚርቁበትን የወሰን መጠን የሚያስቀምጥና ህጋዊ ክልከላ የሚያደርግ ህግ እየተረቀቀ እንደሆነ በቢሮው ሃላፊዎች ተገልጿል፡፡

source: Addisadmas

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ከፓርቲ ፖለቲካ ራሣቸውን አገለሉ

ከአንድነት ፓርቲ በአመለካከት ልዩነት ለቀዋል
       
 የኢፌዴሪ ኘሬዚዳንት፤ ኋላም የተቃዋሚው አንድነት ለፍትህ እና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፤ ከእንግዲህ የፓርቲ ፖለቲካ በቃኝ በማለት አንድነትን ጨምሮ ከማንኛውም ፓርቲ ራሣቸውን እንግዳገለሉ ለአዲስ አድማስ ገለጹ፡፡ ዶ/ር ነጋሶ ራሣቸውን ከፓርቲ ፖለቲካ ያገለሉት በጤና መታወክ እና በእድሜ መግፋት ምክንያት መሆኑን ገልፀው፤ በቀጣይ በሀገሪቱ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ አስተያየቶችንና ገንቢ ትችቶችን በመስጠት ብቻ ተወስነው እንደሚቆዩ አስታውቀዋል፡፡ በቅርቡ አንድነት ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ በኢ/ር ግዛው ሽፈራው የተተኩት ዶ/ር ነጋሶ፤ ባለፈው ዓመት ሚያዚያ ወር ላይ አንድነት መድረክን ከመገምገሙ ጋር በተያያዘ በተፈጠሩ የሃሣብና እና በአጠቃላይ የአመለካከትና የአቅጣጫ ልዩነቶች ከአንድነት ለመልቀቅ መገደዳቸውን ለአዲስ አድማስ ገልጸዋል፡፡ ዶ/ር ነጋሶ ራሣቸውን ከፓርቲ ፖለቲካ ቢያገለግሉም በአገሪቱ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ግን በግል መሳተፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡

source: Addisadmas

ማክሰኞ 21 ጃንዋሪ 2014

አፈንዲ፣ ጃዋር መሐመድ እና የቴዲ አፍሮ ጉዳይ


teddy and jawar
የሰሞኑ የነ ጃዋር ሲራጅ ግርግር ለኛም ስም አትርፏል፡፡ እንደፈቀደው ይሁን፡፡ እኛ ጉዳያችን ሞልቶልናል፡፡ የታቀደው የቴዲ ኮንሰርት በመሰረዙ በጣም ደስተኞች ነን፡፡ በኮንሰርቱ ታክኮ ሊከሰት የሚችለው የህዝብ መተላለቅ በመቅረቱ እሰየው ነው፡፡ ብርና ዝና ብቻ እያሰቡ የህዝብ መጨራረስን ሊጋብዙ የነበሩ ሰዎች ተንኮላቸው ስለከሸፈባቸው አላህን በጣም ነው የምናመሰግነው፡፡
ታዲያ ያስገረመኝ ነገር ስሜት እውነትን ለመሸፈን ምን ያህል ጉልበት እንዳለው መረዳቴ ነው፡፡ አጃኢብ ነው! ግጭትና ትርምስ ሲሰበክ የነበረው በውሸት የተፈጠረውን ወሬ እንደ ሰበብ በማድረግ ነው፡፡ ውሸቱን ለማዳመቅ በግርግሩ ውስጥ የገቡ ሀይሎች አበዛዝም ያስገርማል፡፡ ከአሜሪካ እስከ ኖርዌይ፣ ከለንደን እስከ ሸገር እየተጠራሩ ሽብሩን ለማጋጋል የተደረገው ጥረት አስደናቂ ነበር፡፡ ለወትሮው በአንድ ብሄር ላይ የሚደረግ ዘረኛ ቅስቀሳን እንቃወማለን ሲሉ የነበሩ አንዳንድ ምሁራን ደግሞ ከኛ ጋር ተባብረው ግጭት እንዳይከሰት ጥረት ያደርጋሉ ብለን ስንጠብቅ የኛ ተቃራኒ መሆናቸው አስገርሞናል፡፡ ለምሳሌ እነ ዳንኤል ብርሃኔ “ቀኝ አክራሪዎች እንዲህ አደረጉ” እያሉ ሲጽፉት የነበረው ነገር በእጅጉ የሚያሳዝን ነው፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ሰዎች ነገሮችን በስሜት በመቀበል እውነትን ከውሸት ለመለየት ጥረት አለማድረጋቸው አስቂኝ ብቻ ሳይሆን አሳፋሪ ሆኖ ነው ያለፈው፡፡ ለምሳሌ በግርግሩ መጀመሪያ ሰሞን “መጽሔቱ ቃለ-ምልልሱን አትሞ አውጥቶታል” ሲባል ከርሞ “ሁለት ዓይነት መጽሔት ነው የታተመው” የሚል ነጠላ ዜማ ተለቀቀ፡፡ ከዚያ ለጥቆም “መጽሔቱ አከራካሪውን ቃለ-ምልልስ ቆርጦ አስቀርቶታል” ተብሎ ተወራ፡፡ “የተቆረጠው ክፍልም ይኸውላችሁ” ተብሎ በአንዳንድ ዌብሳይቶች ላይ ተለጠፈ፡፡ በመጨረሻው ላይ ጭራሽ የቴዲ አፍሮ ቃለ-ምልልስ በኦዲዮ ተቀርጾ በእጃችን ገብቷል የሚል ማስመሰያ ተፈጠረ፡፡ ይህ ሁሉ የውሸት ወሬ ነው፡፡ በግርግሩ የተሳተፉት ግን አንዱንም ለማጣራት አልሞከሩም፡፡ “ጀዋር የተናገረው ነገር ምንጊዜም እውነት ነው” የሚል መመሪያ ያላቸው ነው የሚመስለው፡፡ (ያሳቀኝ ነገር ቴዲ አፍሮ ራሱ መጽሔቱ “ቅዱስ ጦርነት” በሚለው ርዕስ አለመታተሙን ያላወቀ መሆኑ ነው፤ እንደዚያ ዓይነት ርዕስ ያለው መጽሔት በጭራሽ አልታተመም)፡፡
እኛ ለቴዲ አፍሮ አልነበረም የተከራከርነው፡፡ ቴዲ ተናገረ የተባለው ቃል ትክክል ነው ያለ ሰው የለም፡፡ በደሌ መጠጣትን አቁሙ መባሉንም የተቃወመ ሰው የለም (እኛ እንዲያውም አስካሪ መጠጥ የተባለ በሙሉ ቢወገድ ነው የምንፈልገው)፡፡ እኛ ያልነው በሀሰተኛ ወሬ ሰውን ለማጨራረስ አትሞክሩ ነው፡፡ ይህንን ሀሰተኛ ወሬ የሚያራግቡ ሀይሎች ድብቅ አጀንዳ አላቸው ነው ያልነው፡፡ ይኸው ነው መልዕክታችን፡፡
ከዚህ በፊት እንደገለጽኩት ቴዲ አፍሮ በትክክል “ቅዱስ ጦርነት” የሚለውን ቃል ተናግሮ ቢሆን እንኳ መደረግ የነበረበት በፍትሕ መንገድ መፋረድ ነው፡፡ ሆኖም የግርግሩ አድማቂዎች በቀጥታ ወደ ዘረኝነት ቅሰቀሳ ነው የገቡት፡፡ ያሳዝናል! የኦሮሞ ህዝብ ባህልና ወግ ይህ አልነበረም፡፡ የህዝቡ ትግልም ከስርዓቶች ጋር ነው እንጂ ከሰፊው የአማራ ህዝብ ጋር አይደለም፡፡
በኔ በኩል የምችለውን አድርጌአለሁ፡፡ በአላህ እርዳታ የምፈልገውን ውጤት አግኝቼበታለሁ፡፡ ህዝቦቻችን አልተገዳደሉም፡፡ አልተፋጁም፡፡ እነርሱ እንደተመኙት አልተጨራረሱም፡፡ ስለዚህ ባደረግኩት ነገር ደስተኛ ነኝ፡፡ በዚህ ጉዳይ ቅንጣት ታክል ጸጸት አይሰማኝም፡፡ ወደፊትም እንዲሁ ማድረጌን እቀጥላለሁ፡፡
===መነሻው===
ይህንን ሁሉ ትርምስምስ በአጋፋሪነት የመሩትን እናውቃቸዋለን፡፡ ሁሉም በውጪ ሀገር ተቀማጭ ሆነው ነበር እሳቱን ሲያጋግሉት የነበረው፡፡ ዓላማቸው ሰሞኑን የፈጠሩት የሰንበቴ ማህበር ግዙፍ ስኬት እያስመዘገበ እንደሆነ እንደ መጠቆሚያ አድርጎ መጠቀም ነው፡፡ ህዝብ ቢጨራረስ ባይጨራረስ ጉዳያቸው አይደለም፡፡
የግርግሩ ዋና አቀናባሪ ማን እንደሆነ አላውቅም፡፡ እንደ ቃል አቀባይ ሆኖ ሲያገለግል የነበረው ግን ጀዋር መሐመድ ነው፡፡ ጀዋር በቅድሚያ ስለጉዳዩ በኔ ኢንቦክስ ሲነግረኝ “የእንቁ መጽሔት ባለቤቶች ጎል ሊያስገቡን የውሸት ሽፋን በፎቶሾፕ ሰርተው በትነዋል” ነው ያለኝ፡፡ እናም “ይህንን መጽሔት መበቀል አለብን” በማለት ሊቀሰቅሰኝ ሞከረ፡፡ “እንቁ ማለት የማይታወቅ መጽሔት ነው፤ ነገሩን ባናጋግለው ይሻላል” አልኩት፡፡ እርሱ ግን “አይደለም! በጣም ግዙፍ የሆኑ ነፍጠኞች ናቸው በገንዘብ የሚደጉሙት” ብሎ ሊያነሳሳኝ ሞከረ፡፡ እኔ በበኩሌ የሰውዬው አጉል ብልጠት ስለሚደብረኝ ግድ አልሰጠሁትም (እርሱ የሚያወራውን ነገር ሁልጊዜ በጥርጣሬ ነው የማየው)፡፡ ከዚያ በኋላ እርሱን ላለመገናኘት ስሸሸው ቆየሁ፡፡ በዚህ መሀል ቴዲ ሰጠ ስለተባለው ቃለ-ምልልስ ሐቁን ለማወቅ ጥረት አድርጌ ነበር፡፡ እናም ውሸት መሆኑን አረጋገጥኩ፡፡
ታህሳስ 14/2006 ከጀዋር ጋር በሌላ ጉዳይ ስንገናኝ ግን ቀደም ሲል ውሸት ነው ሲለው የነበረውን ነገር “እውነት ነው! የኦዲዮ ማስረጃ ጭምር አለን፤ የመጽሔቱ አዘጋጅ ማረጋገጫ ሰጥቶኛል” የሚል ማሻሻያ ሰጥቶት ከርሱ ጋር እንድሳተፍበት ይጨቀጭቀኝ ጀመር፡፡ ነገሩ ውሸት ነው ሳልለው “ይህንን ነገር ከማጋጋል መቆጠቡ ይመረጣል” ብዬ ላቀዘቅዝ ሞከርኩ፡፡ እርሱ ግን “እምቢ! ቴዲን አፈር አባቱን ሳናበላው አንተወውም፤ አንተ ደስ ካለህ እንደ ፈለግክ ሁን” እያለ ይፎክርብኝ ገባ፡፡ ለፉከራው ግድ ባይኖረኝም ለራሱ ዝና ሲል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኦሮሞ ወጣቶች ዘንድ ያገኘውን ተቀባይነት በመጠቀም ስለሜንጫው የፎከረውን ቃል ተግባራዊ ሊያደርግ ይችላል ብዬ ፈራሁ፡፡ እና የርሱን እንቅስቃሴ የሚያኮላሽ እርምጃ መውሰድ አለብኝ በማለት ወሰንኩኝ (በወቅቱ እኔም እንደርሱ በቢራ የምንቦጫረቅ መስሎት “በደሌ መጠጣት አቁም” ሲለኝ ለጥቂት ነበር ከመሳደብ ራሴን የተቆጣጠርኩት!)፡፡
***** ***** *****
ይህ ሰው በጣም አጭበርባሪ ነው፡፡ የውሸት ወሬ መፈብረክ ይችልበታል፡፡ ደግነቱ የሚፈበርካቸውን ወሬዎች ሀሠትነት ለማረጋገጥ ረጅም ጊዜ አይፈጅም፡፡ የዚህ ሰው ሌላኛው ባህሪ ደግሞ ለሁሉም የፖለቲካ ቡድኖችና ፓርቲዎች የሚሰራ መሆኑ ነው፡፡ ሰውዬው ከላይ ሲታይ የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚ ይመስላል፡፡ ሆኖም አብዛኛው ሰው እንደሚያውቀው ከኦፒዲኦ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋርም የጠበቀ ግንኙነት አለው፡፡ አንድ ቀን ሳያስበው ይህንን ግንኙነቱን ግልጽ ያደረገበትን ጥያቄ ጠየቀኝ፡፡ እኔ በሰጠሁት ምላሽ ሳስደነግጠው ትንሽ እንደማፈር ብሎ ዘጋው (በወቅቱ የጠየቀኝን ጥያቄ ሌላ ጊዜ ብነግራችሁ ይሻላል)፡፡ በርሱ ቤት ነገሩን የማላውቅ መስሎታል፡፡ ይሁንና በፌስቡክም ጭምር በሰፊው ሲባል የነበረ ነገር በመሆኑ ብዙም አልደነቀኝም፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ይህ ሰው ከኦነግ-ቀመስ ቡድኖችም ጋር በትክክል እንደሚሰራ መረጃው አለን፡፡ ከሻዕቢያ ጋር እንደሚሰራም ውስጥ ውስጡን ይወራል፡፡ እነዚህ ግንኙነቶቹ ቀደም ብዬ የሰማኋቸው በመሆኑ ብዙም አላስገረሙኝም፡፡ በጣም የተደነቅኩት ግን “ነፍጠኛ” እያለ ቀን ከሌሊት ከሚሰድባቸው ቡድኖችም ጋር የሚሰራ መሆኑን እራሱ በነገረኝ ጊዜ ነው፡፡ የዚያን ቀን በጣም ነበር የደነገጥኩት (ዕለቱ ህዳር 7/2006 ነው)፡፡ “ይህ ሰው ጥቅም ካገኘ ለሰይጣንም ይሰራል ማለት ነው ለካ!” በማለት ተደመምኩበት፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ከዚህ ሰው ጋር የማደርገውን የመልዕክት ግንኙነት ገታ ማድረግ ጀመርኩ (እንግዲህ ለዚህ ሁሉ ማስረጃው በእጄ ነው ያለው)፡፡
ሰውዬው ከነዚህ ሁሉ ቡድኖች ጋር የሚሰራበት ዓላማ ገንዘብና ዝና ማግኘት ይመስለኛል፡፡ በየሀገሩ እየዞረ ብር እንደሚለቅምም ይታወቃል፡፡ እኔ በበኩሌ በግርግሩና በጉዞው ብር ቢያገኝበት ጉዳይ የለኝም፡፡ ብር አገኝበታለሁ ብሎ የማይገባ ድራማ ሲጫወት ግን ዝም ብዬ ላልፈው አልፈቀድኩም፡፡ የጸረ-በደሌውን ዘመቻ በጎን በኩል የተጋፈጥኩት በዚሁ ምክንያት ነው፡፡ አስቡት እስቲ! የቴዲ አፍሮን ኮንሰርት ለመታደም ድሬዳዋ ስቴድየም በተገኘው ህዝብና እርሱን በሚቃወመው ህዝብ መካከል ግጭት ቢፈጠር ውጤቱ ምን ሊሆን ነው? በዚያ ውጤትስ ተጠቃሚ የሚሆነው ማን ነው? አማራው ነው? ኦሮሞው ነው? ወይንስ ማን ነው? እስኪ እናንተው መልሱት፡፡ … የጃዋር የፖለቲካ ተንታኝነት ይህ ነው እንግዲህ!…(እንኳንም ኮንሰርቱ ቀረ! እሰይ!)
ከዚህ ሰው ጋር የተዋወቅኩት በኢንተርኔት ነው፡፡ የምጽፋቸውን ጽሑፎች በዌብሳይቱ ለመጠቀም በፈለገበት ጊዜ ሲያነጋግረኝ ነው ያወቅኩት፡፡ ከዚያ ውጪ ሌላ ትውውቅ የለንም፡፡ ለአንድም ቀን አይቼው አላውቅም፡፡ እኔ የጻፍኳቸውን ጽሑፎች ከኔ የፌስቡክ ፔጅ ላይ እየወሰደ ዌብሳይቱ ላይ ይለጥፋል፡፡ በቃ ይኸው ነው፡፡ ባለፈው ክረምት ደግሞ “ያንተን መጽሐፍ እናሳትማለን” የሚል ቃል ሰጠኝ፡፡ በጥቅምት ወር መጨረሻ ገደማ ግን የመጽሐፉ ጉዳይ ቀረና መጽሔት እንጀምራለን ብሎ መጣ፡፡ የመጽሐፉ ጉዳይ መቅረቱ ሆዴን እየበላኝ ብቸገርም እስቲ ትንሽ ልመርምረው ብዬ አብሬው ሰነበትኩ፡፡ ይሁንና ከህዳር ወር 10/2006 ወዲህ የመጽሔቱም ነገር የውሃ ሽታ ሆኖ ቀረ፡፡ (የማያደርገውን ነገር በስሜት የሚያወራው እንዲህ ዓይነቱ ቀጣፊ ሰው በድሬዳዋ ልጆች ቋንቋ “ሐጂ ቅደደው” ወይንም “ሐጂ ቦንባ” ነው የሚባለው)፡፡
የሆነ ሆኖ የአሁኑ ግርግር ከዚህ ጉዳይ ጋር አይገናኝም፡፡ መጽሔት እናዘጋጃለን ብዬ የለፋሁበትን ድካም መና ስላስቀረብኝ ቂም ቋጥሬ አይደለም ልጋፈጠው የወሰንኩት፡፡ እርሱ ያመጣው ሎጂክ እጅግ አደገኛና ህዝቦችን የሚያጨራርስ በመሆኑ ነው ዝም ማለቱን ትቼ በቀጥታ የገባሁበት (መጽሔቱን በራሴ ወጪ ይፋ አደርገዋለሁ)፡፡
===ታሪክ ====
እኔ የታሪክ ምሁር አይደለሁም፡፡ ግን ስለታሪክ አንብቤአለሁ፡፡ በተለይ ስለ20ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ታሪክ በደንብ ነው ያነበብኩት፡፡ ከሰሞኑ ግርግር ጋር ተያይዞ የሚነሳውን የአጼ ምኒልክንም ታሪክ አንብቤአለሁ፡፡ ነገር ግን ግርግሩ በተጋጋለበት ወቅት ስለርሱ ትንፍሽ አላልኩም፡፡ ወደፊትም እንዲህ አይነት አደገኛ አሻጥር የተመላበት ሁኔታ በሚፈጠርበት ወቅት ግጭትን የሚያጋግሉ ታሪኮችን አልቆሰቁስም፡፡ ግጭት ሲቀሰቀስ ተጠቃሚው ህዝብ ሳይሆን የህዝብ ጠላት ነው፡፡
አጼ ምኒልክ ደቡብና ምስራቅ ኢትዮጵያን ከግዛተ መንግሥታቸው ጋር ለመቀላቀል ያደረጉት ጦርነት ከፍተኛ እልቂትና ፍጅት የተፈጸመበት ነው፡፡ በዚህ ዘመን ሊታሰቡ የማይገባቸው አጸያፊ ድርጊቶች ተፈጽመዋል፡፡ ህዝቦች የገዛ መሬታቸውን ተነጥቀው በትውልድ ቀዬአቸው ጭሰኛ ለመሆን ተገደዋል፡፡ ይህንን ታሪክ የምኒልክ ጸሐፊ ከነበሩት ጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረ-ሥላሴ ጀምሮ በርካቶች በድርሳናቸው ጽፈውታል፡፡
ታዲያ የአጼ ምኒልክ ጦር ያኔ ለፈጸመው ጥፋት የአሁኑ ትውልድ ዕዳ ከፋይ የሚሆንበት ምክንያት የለም፡፡ በዚህ ዘመን ያለው ትውልድ ያለበት ሃላፊነት ከታሪክ ተምሮ የያኔው ጥፋት እንዳይደገም መከላከልና የህዝቦች የመብት ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ እንዲያገኝ አብሮ መታገል ነው፡፡ ታሪክን የፕሮፓጋንዳ መጠቀሚያ እያደረጉ እልቂትና ሁከትን መቀስቀስ የህዝቦችን ትግል ወደኋላ ማስቀረት እንጂ ለህዝቦች የመብት ጥያቄ አንዳች መፍትሄ አያመጣም፡፡
የዛሬ ሶስት ሳምንት ገደማ ስለ አጼ ምኒልክ አልጽፍም ያልኩት አንደኛ ወቅቱን ያልጠበቀ በመሆኑ ነው፡፡ ስውር ዓላማ ያነገቡ ግለሰቦችና ቡድኖች ህዝቦችን ለማጨራረስ ስለአጼ ምኒልክ በሚነዘንዙበት በዚህ ወቅት እንዲህ ዓይነት ታሪኮችን መጻፍ እነርሱ በሚፈልጉት ወጥመድ ውስጥ ራስን ማስገባት ነው፡፡ ሁለተኛ እንዲህ ዓይነት ታሪኮች በአብዛኛው የሚያወዛግቡን በመሆናቸው ታሪኮቹን በሶሻል ሚዲያ ላይ እያመጡ መለጠፍ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ የአዲስ ነገር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረው ታምራት ነገራ እንደጻፈው እንዲህ ዓይነት የሚያነታርኩ ታሪኮችን በፌስቡክ ላይ መለጠፍ ሌሎች ታላላቅ ህዝባዊ አጀንዳዎች እንዲረሱ መንገድ መክፈት ነው፡፡ ታሪኩን ማወቅ የሚፈልግ ሰው በታሪክ ምሁራን የተጻፉ ድርሳኖችን ቢያገላብጥ ነው የሚሻለው፡፡ ሶስተኛ ደግሞ እንዲህ ዓይነት ታሪኮችን መጻፍ እኔ ፌስቡክን ከምጠቀምበት ዓላማ ጋር በጭራሽ የማይሄድልኝ በመሆኑ ነው፡፡
===ትምህርት===
ይህ ግርግር ከተጀመረ ወዲህ ብዙ ተብዬአለሁ፡፡ በወረዱ ቃላት ተሰድቤአለሁ፡፡ አብዛኛው ተሳዳቢ የማያውቀኝ ስለሆነ ምንም አልተሰማኝም፡፡ አንዳንድ ሰዎች የሚንጫጩበት ግለት ግን በጣም አስደንቆኛል፡፡ ይገርማል! አንድ ነገር ልንገራችሁ፡፡
ወላጅ አባቴ ለኦሮሞ ህዝብ በተደጋጋሚ ጊዜአት ታስሮ፣ ተደብድቦ፣ በሚሊዮን የሚቆጠር ንብረቱን አጥቷል፡፡ ትግሉ ሲጀመር ጳጉሜ 5/1966 ቀን የመጀመሪያ ሰማዕት ሆኖ የወደቀውና ሬሳው ረጅም ርቀት የተጎተተው ሰው አሕመድ ተቂ (ሁንዴ) የተሰኘው አጎቴ ነው (ጓደኛው ኤለሞ ቂልጡ በዚያው ቀን ነው የሞተው፤ ሆኖም በወቅቱ የአካባቢው ጸጥታ ሀይሎች ስላላወቁት እዚያው የወደቀበት ቦታ ላይ ትተውት ሄደዋል፤ እስከዛሬ ድረስ ያንን የመሰለ ጀግና ገበሬዎች በአንድ ገደል ጥግ በቆፈሩት ጉድጓድ ውስጥ ራቅ ብሎ ተኝቷል፤ እነ ጀዋርን የመሳሰሉ ሰዎች ግን ሬሳውን እንኳ ደህና ቦታ ስለመቅበር ጉዳይ ላይ ሳይመካከሩ በየስርቻውና በየፓርቲው “ኤለሞ” እያሉ ቱሪናፋ ይነዛሉ… ሐፍረተ ቢስ! አዳማ ውስጥ ደግሞ በርሱ ስም ትልቅ ግንብ አቁመዋል፤ ሬሳውን እንቅበር ብሎ የጠየቀ ሰው ግን እስከ አሁን ድረስ የለም፤ እኛ ከጠየቅን “ሌላ ተልዕኮ አላችሁ” እንባላለን፤ ጉድ እኮ ነው)፡፡
አባቴ የታናሽ ወንድሙን ሬሳ ካየበት ደቂቃ ጀምሮ አዕምሮው ተነክቷል፡፡ ኑሮው የቀን ጭለማ ሆኖበት ከሰው ተለይቶ በራሱ መንገድ ለብቻው ነው የኖረው፡፡ ደርግ ሲወድቅ ያለ አዋጅ የተወረሰበትን አንድ ክፍል ቤቱን እንዲመልሱለት ጥረት አድርጎ ተከልክሏል፡፡ በዚያው ከተማ ውስጥ ግን እስከ አምስት ክፍል ቤት ያላቸው ሰዎች (ለዚያውም በአዋጅ የተወረሱ) ተመልሶላቸዋል፡፡ በዚህ ረጅም ዓመታት ውስጥ አባቴን የት ነህ ብሎ የጠየቀው ሰው የለም፡፡ ከርሱ ጋር የምንቸገረው እኛ ልጆቹ ነን፡፡ አሁንም የድሮው ግርፋት አገርሽቶ እግሩን ፓራላይዝ አድርጎት ሲያስቀምጠው ከርሱ ጋር እየተቸገሩ ያሉት ልጆቹ (በተለይ ሴት ልጁ) ብቻ ናቸው፡፡ እነዚህ “እናውቅሃለን፤ ዘመድህ ነን” ባይ ወገኖች “አባትህ የት ደረሰ” ብለው ጠይቀውኝ እንኳ አያውቁም፡፡ እኔም ነገ ብቸገር የሚገጥመኝ ዕድል ይኸው ነው፡፡ እነዚህ ቱሪናፋ የሚነፉት ወሽከሬዎች ጉዳይ ኖሮኝ እገዛ ብጠይቃቸው አካውንት ዲአክቲቬት እስከማድረግ ይደርሳሉ፡፡ በተለይ ዘላለም ወዬሳ የሚባለው የኦነግን ማሊያ የለበሰ የኦፒዲኦ አገልጋይ “በኦሮሞ እጅ አድገህ፣ የኦሮሞን እንጀራ በልተህ፣ የኦሮሞን ልብስ ለብሰህ፤ ዛሬ ኦሮሞን ከዳህ”… እያለ ሲዘባርቅ ከቤታቸው ኩሽና በየቀኑ እንጀራ በወጥ ሲያቀብለኝ የኖረ ነበር የሚመስለው፡፡
ምሁራን ነን ተብዬዎቹም ኤለሞ ቂልጡን ሲያወድሱት ሳት ብሎአቸው እንኳ በዚያው ቀን በዚያው ሜዳ ላይ ከኤሌሞ ቀድሞ የሞተውንና በርሱ ሰበብ መላው የሀረርጌ ክፍለ ሀገር የታመሰበትን የሰማዕት አጎቴን ታሪክ በአንድም መጽሔትና መጽሐፍት ሲያነሱት አይቼ አላውቅም (እርግጥ አንድ ጊዜ የድሮው የኦነግ ሊቀመንበር አቶ ገላሳ ዲልቦ ገለምሶ ከተማ መጥተው የአጎቴን ስም ሲያነሱት ሰምቻለሁ፤ ”ግዝትና ግዞት” በተሰኘው መጽሐፍ ውስጥም ስሙን አይቼዋለሁ፤ ቴዎድሮስ ሙላቱ በጻፈው አኬል ዳማ ውስጥም ታሪኩ በጥቂቱ ተጠቅሷል፤ ፕሮፌሰር ሙሐመድ ሐሰንም በኢንሳይክሎፒዲያ ኢትዮፒካ ውስጥ አንዴ ስሙን የጠቀሰው ይመስለኛል፤ እነዚህን አራቱን ብቻ በቤተሰቤ ስም አመሰግናቸዋለሁ፤ ከዚህ የተቀረው ሁሉ አስመሳይ ነው)፡፡
ለረጅም ገዜ የዚህ አጎቴ ታሪክ መረሳት በጣም ያንገበግበኝ ነበር፡፡ እናም ታሪኩ መጻፍ አለበት ብዬ ለመጀመሪያ ጊዜ አንድ መለስተኛ ጽሑፍ በዊኪፒዲያ ውስጥ ያስቀመጥኩት እኔ ነኝ፡፡ ከዚያ በኋላ ነው እርሱን ለማወቅ በሚል መጠነኛ ግርግር የተጀመረው፡፡ ከማንም በፊት አጎቴን ያስታወሰው ግን ዓሊ ቢራ ነው፡፡ ገጣሚው አቡበከር ሙሳ እና ዓሊ ቢራ በጋራ ምስጋና ሊደርሳቸው ይገባል፡፡ “ያ ሁንዴ በሬዳ” የተሰኘው ዜማ የተጻፈው ለአጎቴ ለአሕመድ ተቂ ሼኽ ሙሐመድ-ረሺድ ነው (በነገራችን ላይ ዓሊ ቢራንም ለመጀመሪያ ጊዜ በዊኪፒዲያ ያስገባሁት እኔ ነኝ፤ ዓሊ ቢራ ለአጎቴ ማስታወሻ የሰራውን ስራ ለማክበር ይሆን ዘንድ ነው ታሪኩን በዊኪፒዲያ የጻፍኩት)፡፡
ታዲያ የአጎቴ ስም አለመነሳቱ አንዳንዴ ለበጎ ነው ያሰኘኛል፡፡ በርሱ ጦስ የአባታችን ህሊና ተቃውሶ የአባት ፍቅር በደንብ ሳይገባን ነው ያደግነው፡፡ አባቴ በ1975 ከእስራት ወጥቶ ከዝርፊያ የተረፈውን ገንዘብ ዝም ብሎ ሲበትን ጸባዩን ማስተው ያቃታት እናቴ እኛን ለማሳደግ ያሳለፈችው ስቃይ እስከ አሁን ድረስ ውስጤን ያነደኛል፡፡ በተገደለው አጎቴ ሰበብ ሌላኛው አጎቴም (ኢስራፊል ይባላል) አዕምሮው ተነክቷል፡፡ ሟች እናታቸው መርየም “ልጄ አህመድ ተቂ” እንዳለች ነው ህይወቷ ያለፈው፡፡ ወላጅ አባቱ ሼኽ ሙሐመድ ረሺድ ግን የአላህ ሰው ስለሆኑ ትዕግስቱ ነበራቸው፡፡ የአጎቴ ጓደኞች የነበሩት እነ ነጃሽ ዒስማኢል፣ ሙሐመድ በከር፣ ዒስማኢል አሕመዩ፣ ሙሐመድ አብዶ (ሉንጎ) የመሳሰሉት ድንቅ ነጋዴዎች ፣ በግርፋትና ቶርች ብዛት ናላቸው ዞሮ ያለ ጊዜአቸው ከስራው ዓለም ተሰናብተው የሰው ጡረተኛ ለመሆን ተገደዋል (ሉንጎ ከድብደባ ብዛት ዐይኑን አጥቷል)፡፡ የአጎቴን ታሪክ ማንሳት የሚችሉት በርሱ ሰበብ እውነተኛውን ስቃይ ያዩት እነዚህ ሰለባዎችና ቤተሰቦቻቸው ናቸው፡፡ ምድረ አጭበርባሪ መንገደኛ ሁሉ ስሙን እየጠራ መነገጃ እንዲያደርገው አንፈቅድም፡፡
የኔ አጎት የሞተው ለኦሮሞ መብትና ነጻነት ሲል ነው፡፡ አጎቴ አማራን ለመጨፍጨፍ አይደለም ጫካ የገባው፡፡ ከአማራዎች ጋር በጉርብትና ሲኖርና በጋራ ሲሰራ የነበረ ሰው ነው፡፡ እርሱ የታገለው ጨቋኙን ስርዓት ነው እንጂ የአማራ ተወላጆችን አይደለም፡፡ የርሱን ታሪክ ከበደሌ ቢራ ጋር እያገናኛችሁ ማስጠንቀቂያ ልትሰጡኝ የምትሞክሩት ሀይሎች ህልመኞች መሆናችሁን እወቁ፡፡ ለራሳችሁ ሰው የመጨፍጨፍ ዓላማ ካላችሁ በግልጽ አሳውቁን፡፡ የአጎቴን ስም ግን አለቦታው አታንሱት፡፡ እዚያው መቃብሩ ውስጥ በሰላም ይተኛበት፡፡
*****
እንግዲህ አፈንዲ ማለት ይህንን ሁሉ ታግሶ ዝም ያለ ሰው ነው፡፡ ዛሬ “አፈንዲ ጉራጌ ነው፣ አደሬ ነው፣ ጎበና ነው ጂንኒ ጀቡቲ” እያሉ የሚጯጯኹት ታሪክን መሸጥ የለመዱ አስመሳዮች ናቸው፡፡ “ህዝብን ማጋጨት አቁሙ” ማለት ጎበና ከሆነ በእርግጥም ጎበና ነኝ (አንዳንዶች ጭራሽ የጻፍኩትን ሳያገናዝቡት “አባት ማር ስለበላ የልጅ አፍ ጣፋጭ አይሆንም” እያሉ ሊተርቱ ይፈልጋሉ)፡፡
ሰማችሁ ወይ! እኔ ልረዳችሁ ብዬ ነው እንጂ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል፡፡ አንድም ነገር የመጻፍ ግዴታ የለብኝም፡፡ በአባቴ ላይ የደረሰውን ስቃይ እያየሁ ያደግኩ በመሆኔ ከርሱ ህይወት በቂ ትምህርት ወስጄአለሁ፡፡ የሚያሳዝነኝ እንዲህ የሚነገድበት ህዝብ ለሁሉም ነገር ባይተዋር መሆኑ ነው፡፡ ለሁሉም ትምህርት ወስጄበታለሁ፡፡
===የኔ ዓላማ===
ከዚህ ቀደም እንደጻፍኩት እኔ የፖለቲካ ዓላማ የለኝም፡፡ የኔ ጉዳይ ያለው ከህዝብ ዘንድ ነው፡፡ የማንኛውም ህዝብ መብትና ነጻነት እንዲከበር ጽኑ ፍላጎቴ ነው፡፡ የአንዱን ህዝብ መብት ለማስከበር ሌላውን መንካት ትክክለኛ ነገር አይደለም፡፡ እኔ የወጣሁበት የኦሮሞ ህዝብ መብት የሚከበረው የአማራን ህዝብ በመጨቆን አይደለም፡፡ የአማራውንም መብት ማስከበር የሚቻለው ኦሮሞን በመጨቆን አይደለም፡፡ የጭቆናው ደረጃና ስልት ቢለያይም ሁሉም ህዝብ መብቱን ፈላጊ ነው፡፡ ስለዚህ ለህዝቦች መብት የሚታገሉ ወገኖችና ቡድኖች ይኑሩ፡፡ እኛ ደግሞ ይህ የመብት ትግልና በርሱ ምክንያት ከሌላ አቅጣጫ የሚሰነዘረው ግብረ-መልስ ውላቸውን ስተው ሌላ አቧራ እንዳይቀሰቅሱ የመከላከሉን ስራ እንስራ፡፡ በህዝቦች መካከል ፍቅርና ወንድማማችነትን እናጎልብት፡፡
የኔ የምንጊዜም ፍላጎትና ዓላማ ይህ ነው፡፡ ከተወለድኩበት የኦሮሞ ህዝብ በፊት በሀረሪ ህዝብ ላይ ያተኮረ መጽሐፍ የጻፍኩት በዚህ መንፈስ ነው፡፡ ከገለምሶ የተገኙትን የመምሬ ሙላቱ እና የሼኽ ዑመር ገለምሲይ አስደሳች ታሪኮችን ጽፌ በፌስቡክ እና በድረ-ገጾች ላይ የለጠፍኩት ለዓላማችን መሳካት ያግዘናል በሚል ነው፡፡ ሰዎች የፖለቲካ ታጋይ መስዬአቸው በተሳሳተ መንገድ እንዳይረዱኝ በሚል ልዩ ልዩ ማስታወሻዎችን ለጥፌ ያስነበብኩት “ፖለቲካው አይመለከተኝም” ብዬ ሳይሆን በዚህ ገጽ ላይ ፖለቲካ እንደማላካሄድ ለማሳወቅ በሚል ነው፡፡


አፈንዲ ሙተቂ
http://www.goolgule.com/afendi-jawar-mohammad-and-the-issue-of-teddy-afro/
 

የወያኔ ነፍስ በበረከት ስምዖን በኩል ስትቃዥ

አንደኛው መስከረም ጠብቶ ሌላኛው መስከረም እስኪጠባ ድረስ ባሉት የ365.25 ቀናት ውስጥ ስንት ጉድ መስማት እንዳለብን የሚጠቁም አሃዛዊ መረጃ ሊኖር እንደማይችል መቼም ግልጥ ነው፤ ነገር ግን የዘመናችን ኢትዮጵያ የታሪክ ጎርፍ ያመጣብን ከወያኔና መሰሎቹ በስተቀር ሌሎቻችን ያልጠበቅነው ዱብዕዳ ክስተት ምሥጋና ይንሳውና በዬቀኑ የማንሰማውና የማናየው ዕንቆቅልሽ እንዳይኖረን ሆነናል፡፡ በዚህ መልክ በተለይ ባለፉት 22.8 ዓመታት ውስጥ የታዘብነው የታሪክ ምፀትና ወኔያዊ የውሸት ስንክሳር በረጂሙ ታሪካችን ታይቶም ሆነ ተሰምቶ እንደማያውቅ ማንም ጤናማ ኅሊና ያለው ዜጋ የሚመሰክረው ይመስለኛል፡፡ ለዛሬ አንዱን የወያኔ ነጭ ውሸት እንመለከታለን፡፡
በነገራችን ላይ ወያኔና እውነት ዐይንና ናጫ መሆናቸውን የማይረዳ ወገን እንደማይኖር እገምታለሁ፡፡ የወያኔን ተፈጥሮ ወያኔ ራሱን ጨምሮ ሁሉም ያውቃል፤ የወያኔ እውነት፣ የእውነት ግልባጭ የሆነችው ሀሰት ናት፡፡ ለወያኔ ውሸት ማለት እውነት ናት፡፡ ለወያኔ እንደእውነት የሚመርና የሚያቅር ነገር የለም፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ለወያኔ እንደሀሰት የሚጣፍጥ ምንም ነገር የለም፡፡ ወያኔና እውነት በሂሳባዊ አገላለጽ ‘asymptote’ ናቸው – መቼም ሊገናኙ የማይችሉ ተጻራሪ ኑባሬያት በመሆናቸው፡፡ ወያኔ የሀሰት የህግ ባል ነው፤ የሚለያዩት ወይም የሚፋቱት ከሁለት አንድኛቸው ወይም ሁለቱም ሲሞቱ ብቻ ነው፡፡ ሀሰት ግን እስከዓለም ፍጻሜ ስለምትኖር ወያኔ ካልጠፋ ከውሸታምነቱና ከሀገር አጥፊነቱ ተፈጥሯዊ ባሕርይው ሊፋታ አይቻለውም፡፡ ታሪክ ግን ሥራውን የማይረሣ ቆፍጣና ገበሬ በመሆኑ ጊዜውን ጠብቆ እነዚህን ጉግማንጉጎች ወደማይቀረው መቃብራቸው እንደሚሰዳቸው የታመነ ነውና መፍረስ የጀመረው የበሰበሰ ሥርዓታቸው ከነሰንኮፉ ተገርስሶ ሀገራችን በቅርቡ ነጻ እንደምትወጣ በሙሉ ልብ አምናለሁ፡፡ በዚህች መንደርደሪያ ወደሰሞነኛው የበረከት ስምዖን ውሽከታ እንለፍ፡፡
“የኢትዮጵያ አርሶ አደር እስካሁን በተደረገለት ሥራ በሚገባ የረካ ስለሆነ ‹መንግሥት ሰልፍ ውጣ ቢለው ይወጣል፤ መንግሥት ተኛ ቢለው ይተኛል፤ ግፍ ብንፈጽም እንኳን አርሶ አደሩ ይህንን መንግሥት ይሸከመዋል እንጂ ምንም አይለውም፡፡”
ይህን የብፃይ በረከት ንግግር በዓይነቱ ልዩ የሚያደርገው የተባበሩት መንግሥታት ሰሞኑን ባወጣው አንድ ጥናታዊ ዘገባ ላይ በአፍሪካ ፈጣን ዕድገት ከሚያሳዩ አሥር ሀገሮች ውስጥ ኢትዮጵያ አለመካተቷና በተጓዳኝም ይህቺው ኢትዮጵያ – ይህቺው ወያኔን በጫንቃዋ እንደምትሸከም በረከት አፉን ሞልቶ የመሰከረላት ጉደኛዋ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ጠኔ ጓዙን ጠቅልሎ ከመሸገባቸው አምስት የመጨረሻ ድሃ ሀገራት ውስጥ መመደቧ ነው – (በረከት ይህን ሪፖርት ሳያነብ መሆን አለበት ያን በህልሙ የደረሰውን ጅሎችን የማሞኛ ተምኔታዊ(utopian) ቧልታይና ድንቃይ ድርሰቱን የደሰኮረው!)፡፡ በነገራችን ላይ በአምባገነንነትና በድህነት በወያኔ መንግሥት ሳይቀር የምትታማዋ ኤርትራ በነዚህ ዘገባዎች አልተካተተችም(እንዲያውም ዘገባው ኢትዮጵያን ይግረማት ብሎ ከአሥሩ በፍጥነት እያደጉ ካሉ የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ አንዷ ኤርትራ እንደሆነች የገለጠ መሰለኝ)፡፡ ኢትዮጵያ ቻድን ብቻ በልጣ በአፍሪካ በርሀብተኝነት ሁለተኛ ስትወጣ ኤርትራ ከአምስቱ የባሰባቸው ሀገራት ውስጥ አልገባችም፡፡ የርሷ መግባት አለመግባት የኔ ራስ ምታት አይደለም፡፡ ነገር ግን ይህች በማዕቀብና በልዩ ልዩ የማሰቃያ መንገዶች የተወጠረች የቀድሞ የኢትዮጵያ ግዛት ከኢትዮጵያ የተሻለች መሆንዋን በመረጃ በተደገፈ ዘገባ የሚረዳ ጤናማ ሰው የወያኔን ሚዲያ አስችሎት እንዴት ሊከታተል እንደሚችል ይታያችሁ፡፡ ክርስቶስ ‹አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ› አለ፡፡ ወያኔም ይህችን የክርስቶስ አባባል ቀምቶ በማንሻፈፍ ‹አፌን በሀሰትና ዕብለት እከፍታለሁ› አለና ነጋ ጠባ የማያቅመን የሀሰት ወሬ የማይነጥፍበት አስገራሚ ፍጡር ሆነ፡፡
መዋሸት የማይሰለቸው ‹ልማታዊው መንግሥታችን› በሚዲያው የሚያሳየን ኢትዮጵያና እኛ በግልጥ የምናያት ኢትዮጵያ ተለያይተውብን ተቸግረናል፡፡ እነሱ ‹ኢትዮጵያ በልማት ጎዳና እየተመመች ናት፤ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ራዕይ ለማሳካት በየፈርጁ የምናካሂደው የልማት ግስጋሴ ግቡን እየመታ ነው፤ የኢትዮጵያ ልማት ማንም በማይወዳደረው ሁኔታ ወደፊት እየተምዘገዘገ ነው፡፡ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓታችንን በማይነቃነቅ ዓለት ላይ ገምብተናል፤ የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መብት ሳይሸራረፍ የተከበረባትና በሕዝቦች መፈቃቀድ ላይ የተመሠረተ አንድነት እውን የሆነባት አዲሲቷ ኢትዮጵያ ተፈጥራለች፡፡ አሁን ዋናው ጠላታችን ድህነት ነው፡፡ እሱንም እየተዋጋነው ነው…›እያሉ በቲቪያቸው እያላገጡብን ነው – ድህነትን ለመዋጋትና ለማሸነፍ ደግሞ ስንት አሥር ዓመቶች እንደሚያስፈልጉን እነሱው ናቸው የሚያውቁት፤ ለመልካም አስተዳደር እኮ አንድ የመኸር ወቅትም ትልቅ ጊዜ ነው – እንኳንስ 23 ዓመታት፡፡ ወያኔዎች ግን በድህነት ላይ እንደዛቱና ወደታሪክነት እንለውጠዋለን እንዳሉ ሦስት ዐሠርት ዓመታትን ሊደፍኑ ነው፤ አያፍሩም፡፡ በማከያው ግን ዕድሜ ለወያኔው ጉጅሌ በምግብ “ሞልቶ መትረፍረፍ” ከአፍሪካ አንዲት ሀገር ብቻ በልጠን በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎቻችን የተንጣለሉ የአስፋልት መንገዶችንና በአብዛኛው የትግራይ ተወላጆች የሆኑ ኢንቬስተሮች የገነቧቸውን ሕንፃዎች “እየተመገቡና እየጠገቡ” መሆናቸው እየተነገረን ነው፤ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ያጡ የነጡ ዜጎቻችንም ከዬቆሻሻ ገንዳዎች የሀብታም ፍርፋሪና የሙዝ ልጣጭ ለመሻማት ቀን ከሌሊት ሲራኮቱ ይታያሉ፡፡ የወያኔ ዕድገት ይህ ነው፡፡ የወያኔ ‹ልማታዊ ጋዜጠኞች›ም በበኩላቸው የሕዝቡን ሰቆቃ እንዳይመለከቱና እንዳይዘግቡ እንደአቃቂ ፈረስ ዐይኖቻቸውን በወያኔ ተከልለው በብድርና በዕርዳታ በተገነቡ መንገዶችና ድልድዮች ላይ ካሜራዎቻቸውን በመደቀን ሌት ከቀን በተመሳሳይ ዜናዎችና ሀተታዎች ማደንቆራቸውን ተያይዘውታል፡፡ እኛን እሚያሳክከን ሆዳችን ላይ እነሱ እሚያኩልን እግራችንን፡፡ የሚገርሙ ጋዜጠኞችና የሚገርም የማፊያዎች መንግሥት፡፡
ወደበረከት ንግግር እንመለስ፡፡ እንደእውነቱ በረከት ከፍ ሲል የተናገረውን ነገር ለምን እንደተናገረው አልገባኝም፡፡ ምን ማለት እንደፈለገ ለመረዳት አስተርጓሚ ሳያስፈልግ አይቀርም፡፡  አማርኛ ቋንቋን አውቃለሁ ብዬ ደረቴን ነፍቼ እናገራለሁ፡፡ ነገር ግን ይህንን የበረከትን ንግግር እንደመሰለኝ ተርጉሜ እንዲገባኝ ጥረት አደረግሁ እንጂ በቅጡ ልረዳው አልተቻለኝም፤ እርሱም ቢሆን ጎንደር ውስጥ ብዙ ዓመታትን ስለኖረ አማርኛን ከአፍ መፍቻው ባልተናነሰ ያውቃል ብዬ እገምታለሁና ‹ምን ማለት እንደፈለገ ሳይገባው እንዲህ ያለ የተወነዣበረ ንግግር በአደባባይ ተናግሮ የሰው መሣቂያ ለመሆን አይደፍርም› ብዬ ለማመንም በጣም ተቸገርኩ፡፡
ይህን ንግግር በብዙ መልኩ መገንዘብ እንደሚቻል አምናለሁ፤ በአማርኛው “የጊዮርጊስን ግብር የበላ ሳይነኩት ይለፈልፋል” ወይም በሌላ ፈሊጣዊ አገላለጽ “የምላስ ወለምታ” የምንላቸው ምሥል ከሳች አባባሎች አሉ፡፡ በፈረንጅኛው “Fruedian slip” የሚባል በሥነ ልቦና የትምህርት ዘርፍ የሚጠቀስ ሐረግ አለ፡፡ ይህ ሰው የተናገረውን ከነዚህ ጽንሰ ሃሳባዊ ዕይታዎች አንጻር ብንመለከተው ወያኔ ከመጃጀቱና በወንጀል ድርጊቶች ከመጨመላለቁ የተነሣ ነፍሱ እየቃዠች መሆኗን መረዳት አያዳግተንም፡፡ አለበለዚያ ግፍ በመሥራት ላይ የቆመ የወሮበሎች መንግሥት  “ገበሬው ግፍ ብንፈጽምበትም ይሸከመናል” ብሎ መናገሩ ምን ትርጉም ይኖረዋል? አንድ ጤነኛ ሰው ከመሬት ተነስቶ “በጥፊ ባጮልህና ዐይንህን በጉጠት ባወጣውም እንደማትቀየመኝ አውቃለሁ! ከኔ በበለጠ ሊያሰቃይህ የሚችል ወገን እንደሌለ ስለማውቅ ለስቃይ ለስቃይ እኔው እሻልሃለሁና ምርጫህ እኔው ብቻ ልሆን ይገባኛል” ብሎ እንዴት ሊናገር ይችላል? እንዲህ ብሎ የሚናገር ሰው ካለ ደግሞ እንደበረከት የለዬለት በሽተኛ እንጂ ጤናማ ሰው ሊሆን አይችልም፡፡ ከወፈፌና በሽተኞች ንግግር ይሠውረን፡፡ “ዱባ ካላበደ ቅል አይጥልም” አሉ? የሚገርም በረከት ነው የሆነብኝ እባካችሁን፡፡
ይህን ንግግር በቁሙ መረዳት እንደሚቻለው በረከት ማለት ቅል ራስና እሚናገረውን እንኳን የማያውቅ ገልቱ ሰው ነው፡፡ ለመደዴ የቃላት አጠቃቀሜ ይቅርታ ይደረግልኝና እንደዚህ ያለ ድፍን ቅልና ባልጩት ራስ የኢትዮጵያ አንዱ ባለሥልጣን እንደነበረ በነገው የታሪክ መዝገባችን ሠፍሮ ሲታይ በቀጣይ ትውልዶቻችን ዘንድ በእጅጉ ከምናፍርባቸው የታሪክ ስብራቶቻችን መካከል አንዱና ትልቁ ነው፡፡ ሰው ምን ቢጃጃል እንደዚህ አይናገርም ወይም አይጽፍም፤ አለበለዚያም አብዷል ማለት ነው፡፡ “አፍ ሲከፈት ጭንቅላት ይታያል” የሚባለው እኮ እንደዚህ ያለ በደናቁርት አስተሳሰብ የተለወሰ የአነጋገር ጭቅቅት ሲያጋጥም ነው፡፡ ተመልከቱልኝ፡-
“መንግሥት ሠልፍ ውጣ ቢለው ይወጣል፤ ተኛ ቢለው ይተኛል፡፡”
ምን ማለት ነው? ገበሬውን በማስገደድም ይሁን በማታለል ሠልፍ ማስወጣት ይቻል ይሆናል፡፡ ነገር ግን እንዴት ነው እንደሕጻን ልጅ ገበሬውን በትዕዛዝ አባብሎ ማስተኛት የሚቻለው? ምን ዓይነት ዕብሪትና ትምክህት ነው? ምን ዓይነት የድንቁርና አነጋገር ነው? ለነገሩ ወያኔዎች ከአለቃቸው ከመለስ ጀምሮ ለአነጋገራቸው ደንታ የላቸውም፤ የሚያስቡት እንደጤናማ ሰው በጭንቅላት ሣይሆን እንደ አውሬ በጡንቻ ሣይሆን አይቀርም – አውሬ በጡንቻው ካሰበ፡፡ ሀገር፣ ታሪክና ወገን አለን ብለው ራሳቸው ስለራሳቸው የሚያምኑ አይደሉም፤ ባህል የላቸውም፤ ሞራል ወይም ‘ethical values’  ብሎ ነገር አያውቁም፤ ምናልባት ከሴቴኒዝም በስተቀር ሁነኛ ሃይማኖትም ያላቸው አይመስሉም (ለዚህም ይመስላል ወንጀለኝነት የሚያዝናናቸውና በሰዎች ስቃይ የሚደሰቱት)፤ በትውፊትና በወግ ልማድ አያምኑም፤ ባጭሩ ወፍዘራሽ የመርገምት ውጤቶች ናቸው፡፡ ከሁሉም ነገር የወጡና ከዜሮ መጀመር የሚወዱ በፈረንጅኛው አገላለጽ nihilists ናቸው – hedonist የሚል ምርቃትም ማከል ይቻላል፡፡ ታሪክን ማጥፋትና ነባር ባህልን ማውደም ያረካቸዋልና፡፡
ወያኔዎች ማለት ባጭሩ ማሊ በምትባለዋ አፍሪካዊት ሀገር ‹አዛዋድ› በሚል ራሳቸው በፈጠሩት አዲስ ግዛት ውስጥ ፈረንሣይ ድምጥማጣቸውን እስክታጠፋቸው ድረስ ለተወሰነ ጊዜ በሼሪዓ ህግ የሚተዳደር እስላማዊ መንግሥት መሥርተው እንደነበሩት የቱዋሬግ አማፅያን  የሚመሰሉ ናቸው – ወያኔዎች እንደሶማሊያው አልሻባብ ዓይነትም ናቸው – ነገር ግን መንግሥት ስለያዙ ደፍሮ በአሸባሪነት የፈረጃቸው ዓለም አቀፍ ኃይል ሊገኝ አልቻለም፡፡ ለነገሩ ወያኔዎች ሀገራዊ አጀንዳ ስለሌላቸውና የማንንም ፀረ-ኢትዮጵያ የሆነ አጀንዳ አንከርፍፈው በተባባሪነት ስለሚጓዙ ለዓለም አቀፍ ታዋቂ ኃይሎች እስትራቴጃዊ ጠቀሜታ እስከሰጡ ድረስ በአጋርነት የሚያስጠጋቸውና ሙሉ ድጋፍ የሚሰጣቸው አያጡም(ኢትዮጵያውያንን ለጊዜውም ቢሆን እያስቸገረን ያለው ይህን መሰሉ የወያኔ እስስታዊ ተፈጥሮ ነው)፡፡ እነዚያ የአልቃኢዳ የአፍሪካ ክንፍ የሆኑ አማጽያን በቲምቡክቱ ውስጥ የነበሩ ዕድሜያቸው በሺዎች ዓመታት የሚገመት የታሪክ ቅርሶችን በዶማና አካፋ እንዲሁም በግሬደር በአጭር ጊዜ የሥልጣን ቆይታቸው ውስጥ ድራሻቸውን ማጥፋታቸውን የቅርብ ጊዜ ትዝታ በመሆኑ ከዐይነ ልቦናችን ገና አልተሰወረም፡፡ ወያኔዎችም እያዋዙ በእስከዛሬው የኃይል አገዛዛቸው እጅግ በርካታ የኢትዮጵያ ቅርሶችንና ታሪኮችን አጥፍተዋል – ከሁሉም የሚብስ ጥፋታቸው ግን ከቁሣዊው ይልቅ ሥነ ልቦናዊውና  ኅሊናዊ ወመንፈሣዊው አጠቃላይ ውድመት የበለጠ ኪሣራ ያደረሰብንና ለማገገምም ብዙ ጊዜ የሚወስድብን ከባዱ ጥፋት ይመስለኛል፡፡ እነዚህ ናቸው እንግዲህ ጅብ እማያውቁት ሀገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ እንደሚል በምናውቃቸው ምሥኪን ዜጎች መሀል ሆነው ገበሬው የነሱ እንደሆነ የሚሰብኩን፡፡ ለነገሩ ጅብ እንኳን በማያውቁት ሀገር ነበር ተናገረው የተባለውን የተናገረው፡፡ ወያኔዎች ግን ዐይናቸውን በጨው አጥበው እኛው ፊት ሸፍጣቸውንና የሀሰት ቱሪናፋቸውን ካለተቀናቃኝ ለብቻቸው በተቆጣጠሩት ሚዲያቸው ያናፉብናል፡፡
የኢትዮጵያ ገበሬ ኑሮው ምን ይመስላል?
በአሁኑ ወቅት በወያኔ ሥርዓት እንደገበሬው የሚማረር የለም፡፡ የወያኔን የውሸት ፕሮፓጋንዳ ለወያኔና ወያኔያውያን ትተን እውነቱን ብቻ እናውራ ካልን የገበሬው ኑሮም ሆነ የአጠቃላዩ የሀገሪቱ ሕዝብ ሕይወት ያሳዝናል ብቻ ሳይሆን ያስለቅሳል፡፡ እኔ ይህን መልእክት የምጽፍላችሁ ዜጋ በሀገር ቤት የምኖርና አልፎ አልፎ ወደገጠር ለሥራ ጉዳይ ወጣ የምል በዚያም ምክንያት የብዙ አካባቢዎችን ነዋሪዎች ሰቆቃና የዕለት ከለት ውጣ ውረድ የምታዘብ ሰው ነኝ፡፡ ስለዚህም የምለው ነገር በስማ በለው የተገኘ ሳይሆን በራሴም ሕይወት እየደረሰ ያለ እውነተኛ ሰቆቃ መሆኑን ላስታውስ እፈልጋለሁ፡፡ የገበሬው ኑሮ ከእኛ ከከተሜዎቹ የባሰ እንጂ የተሻለ እንዳልሆነ በውነት እመሰክራለሁ፡፡
የአንድ አምባገነን መንግሥት ትልቁ ሕዝብን የመግዣ መሣሪያ ሌላ ሳይሆን በማይምነትና በድንቁርና ሸብቦ በማስፈራራትና በማስራብ አንቀጥቅጦ ወደተናጋሪ እንስሳነት መለወጥ ነው፡፡ ወያኔም እያደረገ ያለው ይህንኑ ነው፡፡ በየትኛውም የኢትዮጵያ አካባቢ ብትሄዱ ለይስሙላ ትምህርት ቤቶች ይሠሩ እንጂ ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት ባለመኖሩ መማር ካለመማር የሚለይበትን መሠረታዊ ነጥብ ፈልጋችሁ ልታገኙ አትችሉም፡፡ በመሆኑም ገበሬው ከትምህርት ርቋል፤ የጨለማ አዘቅት ውስጥም ከገባ ቆይቷል፡፡ በማይምነት አለንጋ እየተገረፈ፣ በብጥቅጣቂ እርሻ ላይ በሚዘራት አነስተኛ ሰብል እየተሰቃዬ፣ ከዚያችም ሰብል ላይ ከፍተኛ ግብር እንዲከፍል እየተገደደና ከብቱንና ንብረቱን ሸጦ ግብር እንዲያስገባ እየተጠየቀ የሚገኝ ገበሬ ወያኔን ጣዕረሞት ሲይዘው “በፍቅርና በትግስት ይሸከመዋል” ሳይሆን “የወያኔን ሬሣ ተሸክሞ ወደመቃብሩ ይሸኘዋል” ቢባል ነው ትክክለኛው፡፡  ገበሬው በቀን አንድ ጊዜም የሚቀምሰው በሌለበት ሁኔታ፣ ገበሬው የልጁን ወስፋት የሚሸነግልበት አንዳችም እህልና ጥሪት አልባ በሆነበት ሁኔታ፣ ገበሬው ከገጠር እየፈለሰ ወደከተሞች በመግባት ለወያኔ ሕንጻና ፋብሪካ ግንባታዎች የቀን ሠራተኛ እየሆነ ባለበት ሁኔታ፣ ገበሬው ልጆቹ ወደዐረብ ሀገር እየተሰደዱ ለዐረብ ጀማላ የሠይፍ እራትና የአስገድዶ መድፈር ሲሳይ እየሆኑ ባሉበት ሁኔታ፣ ገበሬው በማዳበሪያ ዕዳ የስንግ ተይዞ ኤሎሄ እያለ በሚገኝበት ሁኔታ፣ ገበሬው በአድሎኣዊ የመሬት ሥሪት ምክንያት መድሎ እየተሠራበት ማለፊያው የውሃ መሬት ለካድሬዎችና ለወያኔዎች እየተሰጠ ጭንጫውና መናኛው መሬት ግን ለድሃ ገበሬ እየተሸነሸነ ባለበት ሁኔታ፣ገበሬው ከማሳውና ከመኖሪያው እየተፈናቀለ መሬቱ በልማት ስም ለወያኔ ከበርቴዎች እየተቃረጠ ባለበት ሁኔታ፣ አህያ የተጫነችውን እንደማትበላ ሁሉ ገበሬውም ያመረተውን ምርት ለዕዳ ክፍያ ሲል ለጠገቡ የወያኔ ‹ልማታዊ ባለሀብቶች› በርካሽ እንዲሸጥና ጨርቁ በላዩ ላይ አልቆ በባዶ እግሩ እየሄደ በእሾህና በእንቅፋት አሣሩን እንዲበላ ተፈርዶበት ባለበት ሁኔታ፣ … በረከት የተናገረውን መስማት በርግጥም ተዓምር እንጂ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል? በቀደመው ዘመን “እስመ አልቦ ነገር ዘይሰአኖ ለእግዚአብሔር” ነበር ሲባል እምንሰማ፡፡ አሁን ደግሞ “እስመአልቦ ነገር ዘይሰኣኖ ለወያኔ”ብንል እንሳሳት ይሆን? ወያኔ ጥቁሩን ነጭ፣ ነጩን ጥቁር፤ ልቅሶን ሠርግ፣ መርዶን ብሥራት ማድረግ የሚችል ልዩ ምትሃት ያለውና በአፍ ጤፍ የሚቆላ ፍጡር ነው፡፡ ወያኔን ለሚያውቅ የወያኔ ዲስኩርና ፕሮፓጋንዳ  ችግር የለውም – በወያኔ ፕሮፓጋንዳ የሚጃጃል ወያኔን የማያውቅ ወይም ማወቅ የማይፈልግ ብቻ ነው፡፡ ‹ብታምኑም ባታምኑም የኢትዮጵያ ሕዝብ ወያኔን ከእግር እስከራሱ ጠንቅቆ ያውቀዋል!›፡፡ እናም በተለይ በአሁኑ ወቅት ወያኔ ማንንም ሊያታልል በማይችልበት ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ሞቶ በሞቶ እርግጠኛ ሆኜ እናገራችኋለሁኝ፡፡
እናም ወያኔ ስለገበሬው የሚያወራውና እኛ ስለገበሬው የምናውኧው፣ ገበሬውም ስለወያኔ የሚለውና ስለራሱም ከራሱ ኑሮ የሚስተዋለው ለዬቅል መሆናቸውን ልብ ማለት ይገባል፡፡ ‹ይሉሽን በሰማሽ ገበያ ባልወጣሽ› ይባላል፡፡ በረከት የሚናገረው ለሌሎች ብቻም ሳይሆን ለራሱም ሀሰት መሆኑን ማንም አያጣውም፡፡ በረከትን በማታው ‹ክብ ጠረጴዛ› አግኝተን “ምነው ወዲ ስምዖን፣ እንደዚያ ያለ ነጭ ውሸት ማናፈስ ደግ ነው እንዴ ? ለመሆኑ አንተስ ታምንበታለህ? ኅሊናስ የሚባል ነገር የለ(ህ)ም እንዴ?” ብንለው መልሱ ቀላል ነው፡፡ “ወንድሜ፣ በፖለቲካ ኅሊና ብሎ ነገር የለም፡፡ ዋናው ማምለጥ ነው፡፡ የምታደርገውን አድርገህ፣ የምትናገረውን ተናግረህ በፊትህ ከተደቀነብህ ችግር ማፈትለክ እንጂ ስለምትናገረው ነገር እውነትነት ከተጨነቅህ ፖለቲካ ውስጥ ቀድሞውን መግባት የለብህም፡፡ በተለይ እንደኛ ዓይነቱን ችግር ለጠላትም አይስጥ ወንድሜ፡፡ የገባንበት አጣብቂኝ በቀላሉ የሚወጡት አይደለም፡፡ መጥኖ መደቆስ አስቀድሞ ነበር ወዳጄ፡፡ በደም ጨቅይተናል፤ በሙስና በክተናል፤ በዘረኝነቱም ረገድ ያጠፋነውን ጥፋትም ቆም ብለው ሲያስተነትኑት የአንጎልን ሚዛን የሚያዛባና የሚያሳብድ ነው፤ ወደትግል ከገባንበት ጊዜ ጀምሮ የገደልነውና ለስደትና ለእሥራት የዳረግነው ዜጋ የኅሊና ዕረፍት እያሳጣ መቆሚያ መቀመጫ ያሳጣናል፤ ለዚህም ነው ብዙዎቻችን ቢሯችን ውስጥ ሣይቀር በብርጭቆ ውስጥ መደበቅን የምንመርጠው፡፡ ሰው ወዶና ፈቅዶ ጉበቱን በመጠጥ ቦጫጭቆ ሞትን በራሱ አይጋብዝም፡፡ ታዲያ አሁን ምን እናድርግ? ነገር የተበላሸው ዱሮ ነው፤ አሁን ሁሉም ነገር ጠርዝ ከለቀቀ በኋላ ከመዋሸትና ከማምታታት ውጪ ምን አማራጭ አለን? አንድ ነገር ሲገቡበት ቀላል ነው፤ ለመውጣት ግን ከባድ ነው፡፡ የኛ ወደዚህ ሥፍራ መምጣትና አንድ ሰው ወደአደንዛዥ ዕፅ ሱስ መግባት ሂደቱ ተመሳሳይ ነው፤ ሁለታችንም እንደዋዛ እንገባለን – እንደዋዛ መውጣት ግን ለሁለታችንም ከባድ ነው፡፡…” አዎ፣ በረከት በዊስኪ ጨዋታው ለሁነኛው ልክ እንደዚህ እንደሚያጫውተው ‘subconscious’-ኡን በርቀት በማንበብ መረዳት ይቻላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ለወደቀም ማዘን ተገቢ ነው፤ ‹ለሚወድቅ› ብላችሁ ልታሻሽሉትም ትችላላችሁ፡፡ እንደኔ ግን ወያኔዎች ሲነሱ ነው የወደቁት፡፡ ሰው ሲወለድ ነው የሞተው እንደምንል መሆኑ ነው፡፡ ወያኔዎችም ክፋትን መሥራት ሲጀምሩ፣ በቂም በቀል የተቃኘ የጥላቻ አገዛዛቸውን በስፋት ሲያጧጡፉ፣ ሀገርን ሲሸጡና ሲለውጡ፣ ምድርን በደም ረግረግ ሲሞሉ፣ አማራን ከትግሬ፣ ትግሬን ከኦሮሞ እዬለዩ አንዱን መጥቀምን ሌላውን መጉዳትን ባህላቸው ሲያደርጉ፣ ዳር ድንበርን እንዳወጣ ለባዕድ ሀገራት ሲቸበችቡ፣ ሀገርን ካለመውጫ በር ዘግተው የሚሊዮኖችን እስትንፋስ ሲዘጉ፣ … ያኔ ነው ወያኔዎች ገና በጧት ሳይወለዱ የሞቱት፡፡ እዚህ ላይ የሞት ዓይነት ብዙ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ እንጂ የአሁኑ እስትንፋሳቸውማ በ“ሥልጣን” ካሳለፉት ጊዜ አንጻር ሲታይ የደቂቃዎች ያህል ጊዜ ብቻ የቀራቸው ጉድጓዳቸው የተማሰ ልጣቸውም የተራሰ ስለመሆኑ ጨረቃና ፀሐያቸውን በማየት ብቻ የምንረዳው ነው – ዘመናቸው አልቋል፡፡ … የኔ አይደለም …የርሱ እንጂ፡፡ የፍርድ ሂደቱና ብያኔው ከታች አይደለም – ከላይ እንጂ፡፡
የኢትዮጵያን ገበሬ ኑሮ በረከት አያውቀውም ማለት ዘበት ነው፡፡ የኢትዮጵያን ገበሬ ወያኔ አያውቀውም ብሎ በዚህ ሰውዬ ንግግር መደመምም ከንቱ ነው፡፡ በገበሬው መቀለድ አምሯቸው እንጂ የሚናገሩት ነገር እውነቱ የተገላቢጦሽ መሆኑን አጥተውት አይደለም፡፡
ስለሆነም በረከት የሚለው ነገር “አይሰማም!” እንላቸዋለን ፡፡ በረከት ልፋ ብሎት ተናገረ የተባለውን ይናገር እንጂ የራሱ ስብሰባ አባላት ሳይቀሩ ሲችሉ በግልጥ ሳይችሉ ደግሞ በውስጣቸው ይስቁበታል፡፡ ለዚያውም ከትከት ብለው ነው እሚስቁበት – እንደጅል በመቁጠር፡፡ እርግጥ ነው – በረከት ጅል አይደለም፡፡ ጅል ለመምሰል የቆረጠው ግን ምርጫ በማጣት ይመስለኛል፡፡ አንድ ሰው ፀሐይ የሞቀውን እውነት ለመሸፈን በመሞከር በግልባጩ ለማውራት ከተገደደ አንድም ያስጨነቀው ነገር አለ ማለት ነው፤ አለበለዚያም የመዋሸት ተፈጥሯዊ ጠባይ  አለበት ማለት ነው – ልክ እንደመለስ ዜናዊ፡፡ መለስ ዜናዊ በሣይንስ የተረጋገጠ ላይሆን ይችላል እንጂ በእንግሊዝኛው ‘pathological liar’  የሚባል ዓይነት ግለሰብ እንደነበር መረዳት አይቸግርም፡፡ እርሱ በቲቪ ቀርቦ የሚናገራቸውን ንግግሮችና መሬት ላይ ይታይ የነበረውን እውነት በማስተያየት የዚህን ሰው ውሸት በመናገር የመርካት ጠባይ ወይም የተዛባ ተፈጥሯዊ ባሕርይ በቀላሉ መገንዘብ ይቻል ነበር፡፡ በዚህ መልክ ይህ ተጋቦታዊ ደዌ በትግል አጋርነትና በጥቅም ተጋሪነት ምክንያት ለበረከትም ተርፎ ይሄውና በረከትም አንድም ሰው ላያምነው – አንድም የራሱ ሰው ሳይቀር አምኖ ላይቀበለው – እንዲሁ ድከም ብሎት ሲወሻክት እናደምጠዋለን፡፡ እስከመቼ እየወሻከተ በሰው ስቃይ ሲደሰትና የሰውን ስቃይ ለሚዲያ ፍጆታ ያህል ለከንቱዎች በመሸጥ እንደሚኖር ገና የምናየው ይሆናል፡፡ ወደኅሊናው የሚመለስ አይመስለኝም እንጂ ከተመለሰ ግን የገበሬውም ሆነ የአጠቃላዩ የኢትዮጵያ ሕዝብ ካሉት በታች ከሞቱት በላይ የሆነ የሰቆቃ ሕይወት በሚያሳድርበት የእርግማን መዘዝ እንደይሁዳ ራሱን ሰቅሎ እንደሚገድል አምናለሁ፡፡ ያ ቀን ደግሞ በጣም ቀርቧል፤ ምን አለ በሉኝ እነዚህ ጉዶች የሥራቸውን የሚከፈሉበት ጊዜ በብርሃን ፍጥነት እየገሰገሰ በመምጣት ላይ መሆኑ ይሰማኛል፡፡ ቋቱ ሞልቷል፤ የሚቀረው የሚጠራርጋቸውን ማዕበል የሚያስነሣው የፈጣሪ ፊሽካ ብቻ ነው፡፡
የኃጢኣት ትንሽና ትልቅ ባይኖረውም አንድ ሰው ሰርቆ ቢበላ እርቦት ሊሆን ይችላልና ምንም አይደለም ሊባል ይችላል፤ ቢሳደብ ተናድዶ ሊሆን ይችላል በሚል ይቅርታ ሊደረግለት ቢችል ምንም አይደለም፡፡ ነገር ግን በመንግሥት ሠራሽ ርሀብና በግፈኛ አገዛዝ እያለቀሰ የሚኖርን ገበሬ በሚያስለቅሰው ዘረኛ ሥርዓት ተደስቶና ደልቶት እንደሚኖር በሚያስገርም አነጋገር ሰይጣናዊ ስብከትን በመገናኛ ብዙኃን መልቀቅ ከይቅርታ በላይ ነው፡፡ ብሶቱን ችሎ፣ የሚደርስበትን ግፍና መከራ ተቋቁሞ በሞትና በሕይወት እየተንጠራወዘ በሚኖር ሕዝብ ላይ ይህን የመሰለ ቀልድና ድራማ እየሠሩ መሣለቅ ለዘር የሚተርፍ መራራ ቅጣት ሊያስከትል እንደሚችል በረከትም ሆነ ግብረ አበሮቹ መረዳት አለባቸው፡፡ ይህ መሪር ቀልዳቸው ዛሬና ለነሱ ምንም ላይመስል ይችላል፡፡ ይሁንና እያንዳንዷ የምናደርጋት መጥፎ ነገር ሁሉ ትልቅ ዋጋ ሳታስከፍል እንዲሁ የምትቀር እንዳልሆነች ቀልደኞቹና በኢቲቪ የሚገኙ ሆዳም ወናፎች ሁሉ ሊገነዘቡት ይገባል፡፡ ዛሬ ገበሬውም ሆነ ከተሜው አንደበቱ ተለጉሟል፤ አይናገርም፤ ሊናገርም አይፈልግም፡፡ ሰሚ ስለሌለውና ፈጣሪው ፊቱን እንዳዞረበት ስለተረዳ ሁሉም በዝምታ  ተቀምጧል፡፡ ይህ ማለት ግን ዘመን አይለወጥም፣ ዝም ያለም ሁሉ ደንቆሮና አላዋቂ ነው  ማለት አይደለም፡፡ ወያኔ እንዳልነበር ሁሉ የማይኖርበት ጊዜ ሲመጣ ሊከሰት የሚችለውን ትዕይንት አለማየት ነው፡፡ ያኔ እንደዛሬው እዩኝ እዩኝ እንደተባለ ሁሉ ደብቁኝ ደብቁኝ የሚባልበት ጊዜ መድረኩን ይረከባል፡፡ ጥጋብ ደግሞ ወደራብ መንዳቱ ያለና የነበረ ነው፡፡ የጠገበ የሚራብ የማይመስለው የመሆኑ መጥፎ አጋጣሚ ግን አሳዛኝ የታሪክ ግጥምጥሞሽ እንደሆነ እስካሁን አለ – ሲገርም፡፡ አንዱ ከአንዱ ገመና ትምህርት ቢገበይ፣ የሚነሣው ከሚወድቀው ቢማር ግና የችግሮቻችን መንስኤዎች እንደጤዛ በረገፉ፣ እንደጉምም በበነኑ ነበር፡፡ ይህ አለመታደል እስከመቼ እንደሕግ ሆኖ እንደሚበጠብጠን አላውቅም፤ እስኪ የመጨረሻችን ያድርግልን፡፡
በማጠቃለያዬ ማሳሰብ የምፈልገው ነገር አለኝ፡፡ በረከትም ሆንክ ሌላ ጊዜ ሰጠኝ የምትል ባለሥልጣን ሁሉ ካለፈው ታሪክ ተማር፡፡ የሚያሳዝነኝ ነገር አፄዎቹ ከቀደሙት አፄዎች መማር ሳይፈልጉ ቀሩ፤ ቀሩናም ሕዝብን ሲንቁ ሲንቁ ቆይተው በናቁት ሕዝብ እርግማንና አመፅ ምክንያት እንዳልሆኑ ሆኑ – ዘር እንኳን አልወጣላቸውም፡፡ ደርግም ፈጣሪን ሣይቀር ከድቶና አስከድቶ ራሱን የፈጣሪን ያህል በመቁጠር ሕዝብን ሲንቅና ሲያዋርድ ቆይቶ በናቀውና ባዋረደው ሕዝብ እርግማንና ሁለንተናዊ የእምቢታ አመፅ ሰበብ እንደባቢሎን አይሆኑ ሆኖ ተንኮታኮተ – ስንትና ስንት ዘመናዊ ትጥቅ እያለው አንዱም አላዳነውም፤ ይንቃቸው በነበሩ መናኛ የጫካ ወሮበሎች በቀላሉ ተገፍትሮ ወደቀ፡- መጽሐፉ ‹ንጉሥ በሠራዊቱ ብዛት አይድንም› እንደሚል መዘንጋት አይገባም፡፡ እነዚህኞቹ ፀረ-ኢትዮጵያ ጉጂሌዎችም አይነጋ መስሏቸው የኢትዮጵያ ታሪክ መዝገብና ሕዝቡ ሊሸከሙት ያልተቻላቸው ግፍና በደል በሀገርና በሕዝብ ሠሩ፤ ዋናዎቹ የአገዛዙ ቁንጮዎች በሣምንታት ልዩነት ወደማይቀሩበት የሲዖል ሥፍራቸው ተጓዙ፤ ቀሪዎቹም በመኖርና ባለመኖር አጣብቂኝ ውስጥ ተሰንቅረው ያደርጉትን በማጣት ፈጣሪ ሩህያቸውን ጨርሶ እስኪወስዳት እየተንጠራወዙ ይገኛሉ – ይህን እውነት ማስተሃቀር ፈጽሞውን የሚቻል አይደለም፡፡ ለውስጥ አዋቂዎች ወያኔዎች በሕይወት እንደሌሉ ከገባን ቆይተናል፡፡ በሕይወት ያሉ እንዲመስሉ የሆነው ምናልባት ለበጎ ነው፡፡ እንጂ እንደእውነቱ ወያኔ አከርካሪው የተመታው ዋናውን የሥርዓቱን መሃንዲስ መለስ ዜናዊን ፈጣሪ ባልተጠበቀ ወቅት ገና በ‹ማለዳ ዕድሜ›ው ሲጠራው ነው፡፡ ልብ ከተገኘ “ሁሉም ከእያንዳንዱ፣ እያንዳንዱም ከሁሉም እንዲማር ጊዜ ለመስጠት ተብሎ ነው የወያኔ የማይቀር ኅልፈት አዝጋሚ እንዲሆን የተደረገው” ብሎ ማሰብም ይቻላል – ምንም ነገር ማሰብ በማንም አልተከለከለምና (ወያኔዎች ግን ይህንንም ተፈጥሯዊ መብት ሊነፍጉን ይቃጣቸዋል፤ ኢትዮጵያ ውስጥ እየኖርክ ወያኔን ስለመጣል ወይም በሀገሪቷና በሕዝቡ ላይ የጣሉትን ግፈኛ የአገዛዝ ቀምበር ስለመቃወም “ማሰብ”ም አትችልም – ማሰብህ በዐይነ ውኃህ የፊት-ንባብ ከተደረሰበት በአሸባሪነት ተጠርንፈህ ዘብጥያ ትወርዳለህ)፡፡ ማሰብ በቻልንበት ሃሳብ ውስጥ በጊዜ ሰጪነት የምንጠረጥረውን አካል ደግሞ ለሁላችንም እኩል በሚገባን ቋንቋ አቶ ታሪክ ልንለው እንችላለን፡፡ ታሪክ የሚያዳላ ይመስለናል እንጂ ለማንምና ለምንም በጭራሽ አያዳላም – የራሱ የጊዜ ቀመር እንዳለው ግን ማጤን ተገቢ ነው (እርግጥ ነው – ‹መብሰሉ ለማይቀረው ጭንቅላት እንጨት ይፈጃል› እንደሚባለው አንድ ታሪካዊ ኹነት ተከናውኖ ቀጣዩ ሌላ ኹነት እስኪከናወን የሚኖረው የጊዜ እርዝማኔ በትግስታችንና በሃይማኖታችን ጭምር አሉታዊ ጥላውን ማጥላቱ የማናልፈው የዘመን ቅጣት ይመስላል፤ ማን ነበረች – አዎ፣ ሜሪ አርምዴ – “ፍቅር ያዘኝ ብለሽ አትበይ ደንበር ገተር፤ እኛም አንድ ሰሞን እንደሱ አ’ርጎን ነበር፤› ያለችውን የዘፈን ግጥም አለመዘንጋት የአጽናኝነት ጠቀሜታ አለውና እናስታውሰው፡፡) ዕድሜ ይስጠን ሁሉን እናያለን፡፡ ሌላ ዘፋኝም “እናያለን ገና” ብሏል፡፡ ይህንኑ ዘፈን ልጋብዛችሁና እንለያይ፡፡ ጣሊያኖች ሲለያዩ “አሪቬዴርቺ” ይላሉ – በ“ሰላም ያገናኘን” ለማለት፡፡
ሰበር መርዶ!
ይህን ጦማር ጽፌ የጨረስኩት ሌሊት ነው፡፡ ጧት ወደሥራ ልሄድ ስነሳ እንደወትሮው ሁሉ ቤቴ አጠገብ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸውን ወደዬክፍላቸውን ከማስገባታቸው በፊት ሰንደቁ አጠገብ አሠልፈው ብሔራዊ መዝሙር በቴፕ ከፍተው ሲያጮኹ ሰማሁ፡፡ ይሄኔ ኮምፒውተሬን ከፍቼ ይህችን ሃሳብ በሰበር መርዶነት ለመሰንቀር ወደድኩ፡፡ የሀገር ሞት ከዚህ በላይ የለም፡፡ በጥንት ጊዜ ብሔራዊ መዝሙር ተማሪው ነበር በስሜት ተውጦ በመዘመር ወደክፍሉ የሚገባው፡፡ አሁን ዕድሜ ለወያኔ አዲሱ መዝሙር ሊያውም በመሣሪያ ብቻ የተቀነባበረው በቴፕ ይዘፈንና ወደክፍል ይገባል፡፡ ዛሬ ዛሬ የኢትዮጵያን ብሔራዊ መዝሙርና ባንዴራ የሚያውቅ ትውልድ እየጠፋ ነው፡፡ ራሱ መለስ ዜናዊ (በሕይወት ኖሮ) ይህን መዝሙር ውጣው ቢባል የሚችለው አይመስለኝም፡፡ ሌሎቹ የወያኔ ባለሥልጣናት ቢጠየቁም የሚያውቁት ስለመሆናቸው እርግጠኛ መሆን አይቻልም – ብቸኛ ዘመዳቸው ሆዳቸው በመሆኑ ስለሀገር ምንነት የሚያውቁት ነገር የለም ማለት ይቻላል፡፡ የሚሰቀለው ባንዴራ ደግሞ የተቀዳደደ፣ የነተበ፣ ቀለሙን የለወጠ፣ ከተሰቀለ የማይወርድና ተበጣጥሶ እስኪያልቅ 24 ሰዓት የሚውለበለብ የማን ሀገር ባንዴራ መሆኑም የማይታወቅ ነው፤ የጥንቱን የባንዴራ አሰቃቀልና አወራረድ ሥርዓት የሚያስታውስ ዜጋ የአሁኑን ሲያይ ያለቅሳል፡፡ ከአዲስ አበባ ወጣ በሚል ቦታ ደግሞ የኦሮሚያ ባንዴራና የኦሮሚያ ብሔራዊ መዝሙር በትምህርት ቤቶች እንደዚሁ በቴፕ ሲዘመር ወይም ልጆች በግዴታ አጥንተው እንዲዘምሩት ሲደረግ ታያላችሁ፡፡ ይህችን የነፃነት ምኩራብ የሆነች የታሪክ አምባ ሀገራችንን እንዲህ ባለቤት ያሳጧት የሰይጣን ልጆች ዋጋቸውን ሳያገኙ ከቀሩ በርግጥም ኢትዮጵያ ፈጣሪ የላትም፡፡ አላስችል ብሎኝ አሁን በእግረ መንገድ ትንሽ ለመናገር ፈለግሁ እንጂ ይህ ጉዳይ ብዙ የሚያናግር ነው – የጋራ የሚባለል አንዳችም ነገር እንዳይኖረን ከፍተኛ የጥፋት ሥራዎች በመሠራታቸው አሁንና ለጊዜው ጠፍተናል፤ አለን እንላለን እንጂ በርግጥም በወኔያዎች ደባና ሤራ የአብሮነት ኅልውናችን አደጋ ላይ ወድቋል – ብዙ የትስስር ገመዶች ተበጣጥሰዋል፡- የጋራ ቋንቋ፣ የጋራ መሪ(ዎች)፣ የጋራ የመከላከያ ጦር፣ የጋራ የፖሊስ ሠራዊት፣ የጋራ ድንበር፣ የጋራ ባህል፣ የጋራ ትውፊት፣ የጋራ ሥነቃልና ሥነ ጽሑፍ፣ የጋራ ቤተ መንግሥት፣ የጋራ መንግሥታዊ መዋቅር፣ የጋራ… የጋራ… የጋራ… የምንለው ነገር እንዳይኖረን ተደርገን አንዳችን አንዳችንን የጎሪጥ እንድናይና እንድንፈራራ ተደርገናል፡፡ ሌላው ሁሉ ቀርቶ የጋራ ስብዕና ወይም የሰውነት ደረጃ እንኳን የለንም፤ አንዱ ከሌላው የበለጠ ሰው ነው – ሌላውም ከአንዱ ያነሰ ሰው ነው፡፡ አንዱ የሰው ዘር ከሌላው በተለዬ ምርጥ ነው – ሌላው ደግሞ ውዳቂና ቢገድሉት የበቃ ነፍሱ ከእንስሳት ነፍስም ሳይቀር ያነሰ ዋጋ ያለው ነው – ሩቅ ተመልካቹ ጆርጅ ኦርዌል ጨርሶታል – “All animals are equal, but some are more equal than the others.”፡፡ በዚህ መልክ በፈረጁን ሰዎች ነው እንግዲህ አጥንታችን ድረስ ዘልቆ በሚጠዘጥዝ መሪር ፈረዖናዊ አገዛዝ እየተቀጠቀጥን የምንገኘው፡፡
ያን ደገኛ ኢትዮጵያዊ የአንድነት መንፈስ ለማምጣት እነቴዲ አፍሮን የመሰሉ የቁርጥ ቀን ልጆች ብቻ ሣይሆኑ ሁላችንም የየበኩላችንን ጥረት ማድረግ ይኖርብናል – ለራሳችንና ለልጆቻችን ስንል፡፡ ከራስ ወዳድነትና ከአህያይቷ የ‹እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል› ያረጀ ያፈጀ አስተሳሰብም ባፋጣኝ እንውጣ፡፡ አርቀን መመልከትን ባህላችን እናድርግ፡፡ ጎርፉ ሳይደርስብን ራሳችንን በኅሊና ጸጸት አጥበን ለመጪው መልካም ኢትዮጵያዊ ዘመን ዝግጁ ሆነን ለመጠበቅ እንሞክር፡፡ በየድረ ገጹ የሚታዬው ዘረኝነት ላይ የተመሠረተ ወያኔያዊ የዱባ ጥጋብ መሰል ቡራከረዩና ወንዝ የማያሻግር ከፋፋይ ፕሮፓጋንዳ ዘመኑን እያገባደደ በመሆኑ የአንዲት እናት ልጆች ነንና እንሶብር፡፡ ወያኔ የጋተንን ብርብራና መቅመቆ ማርከሻ እንፈልግለት፤ “ስሜት-ወለድ” ማስጠንቀቂያየን እዚህም ላይ ልድገመው – “እዩዩኝ ያለ ደብቁኝ ደብቁኝ ይላል”፡፡

በደምና በአጥንት መስዋዕትነት ተከብሮ የቆየ የሃገራችንን ዳር ድንበር ለባዕድ አሳልፈን አንሰጥም!

ሀገራችን ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሃብቷ የታደለች ፣መልካም የአየር ፀባይ ያላት፣ህዝቦቿ የራሳችን አኩሪባህልና ወግያለን፣የራሳችን መልካም መልክዓ ምድራዊና አሰፋፈር ያለን በጋራ ተሳስረን አብረን የኖርንባትና የምንኖርባት በየትኛውም ዘመን ሉአላዊነቷ ያልተደፈረ ለአፍሪካ ተምሳሌት የሆነች ሀገር ናት። በተለያየ ወቅት የተፈጥሮ ሃብቷን ለመቀራመትና ሉአላዊነቷን ለመዳፈር የሞከሩ ሃገራት ሁሉ፣በውድ ልጆቿ የተባበረ ክንድ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥተው ኢትዮጵያን ዳግም እንዳይመኟት የተባረሩበትና የኢትዮጵያን አይበገሬነት በአፍሪካም ሆነ በአለም መድረክ ያስመሰከረች፣ አንድነቷንና ሉዓላዊነቷን ጠብቃ በማቆየት በአለም ታሪካዊ ስፍራ ያላት፣ በቀደምት ውድ ልጆቿ የደም መስዋዕትነት ሀገራችን ሉአላዊነቷ ሳይደፈር ለብዙ ሺ አመታት ቆይታለች።
በአሁኑ ስዓት ኢህአዴግ/ህወሃት ለግልና ለግዚያዊ የፖለቲካ ጥቅም ሲል የኢትዮጵያን አንድነት በማደብዘዝ እንሆ በእኛ ዘመን ለዘመናትተደፍሮ የማያውቀውን የኢትዮጵያን ሉአላዊነት በመጋፋት የኢትዮጵያ የሉአላዊነት ባለቤት የሆኑት ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ሳይወያዩበትና ሳያፀድቁት በጓሮ በር የኢትዮጵያን መሬት ለባዕድ ሃገር/ሱዳን ቆርሶ ለመስጠት ሽርጉዱን ተያይዞታል። ከአመታት በፊት በምዕራቡ የሃገራችን ክፍል /ድንበር በኩል/ በመሸራረፍ ለም የሰሊጥ ምርት የሚሰጥ መሬት ለሱዳን ሲሰጥ ዝም በማለታችን  እንሆ ዛሬ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት የሚጋፋ ፣ የኢትዮጵያን ቅርጽ የሚያጠፋ ረጅም ርዝመት ያለው ለም መሬት ለሱዳን ለመስጠት ዝግጅቱ መጠናቀቁን ሰማን።
ዛሬ ላይ ሆነን ይህንን መሰሪ ተግባር አንድነታችንን አጠናክረን መግታት ካልቻልን ነገ ደግሞ በሌላኛው የኢትዮጵያ ጫፍ በኩል የኢትዮጵያ መሬትተቆርሶ ለሌሎች አጎራባች ሀገራት ላይሰጥ ምን ዋስትና አለን?
አያቶቻችንና አባቶቻችን ደማቸውን ገብረው ፣አጥንታቸውን ከስክሰው ያስረከቡንን የሀገር ሉአላዊነት ሳይሸራረፍ ለመጭው ትውልድ ማስተላለፍ የእኛ የአሁኑ ትውልድ የታሪክ  ግዴታ ነው። ይህን የታሪክ ግዴታችንን ሳንወጣ/ችል በማለት/ በመሰሪው የህወሃት/ ኢህአዴግ አመራር የሃገራችን ሉአላዊነት እየተሸራረፈ ለባዕድ ሀገራት ሲሰጥ በምን አገባኝ ስሜትዝም ብለን ብንመለከት በ– ዚ–ያ ዘመን ዘመናዊ መሳሪያ ከታጠቀ የውጭ ጠላትጋር የሀገሬን ሉአላዊነት አላስደፍርም በማለት በዱላ፣ በጦርና ጋሻ፣ ዘመናዊ ባልሆነ  የጦር መሳሪያ ፣በባዶ እግራቸው በመዝመት ደማቸውን አፍስሰው አጥንታቸውን ከስክሰው የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ሳያስደፍሩ ያስረከቡን የአባቶቻችን አጥንት እሾህ ሆኖ ይወጋናል።
“የኢትዮጵያ ድንበሮች በኢትዮጵያውያን ደም የራሱ፣ በኢትዮጵያውያን አጥንት የተገነቡ ሲሆኑ ድንበሮቻችንን ለማስከበር ከሁልቆ መሣፍርት፣ ተራ ዜጐች አንስቶ እስከ አንድ ታላቅ ንጉሠ ነገሥት አጼ ዮሐንስ አንገታቸው ሰጥተዋል፡፡ በዶጋሊ፣ በጉራዓ፣ በጉንዲት፣ በመተማ፣ በአድዋ፣ በወልወል በቅርብ ጊዜያት ደግሞ በሶማሊያና በኤርትራ የፈሰሰው የኢትዮጵያውያን ደም የሌላውን ግዛት በመቋመጥ ሳይሆን ድንበሬን አላስነካም በሚል ነበር፡፡ እንደዛሬው መኪና ወይንም ባቡር ባልኖረበት የቀደምት ኢትዮጵያውያን ከመሃል አገር ተነስተው በእግር ለወራት በረሃውን አቋርጠው፣ ተራራውን ወጥተው፣ ንዳዱን ተቋቁመው፣ ወባውን ደፍረው ከሙስታሂል እስከ ጋምቤላ፣ ከራስ ካሣር እስከ ሞያሌ ዘልቀው ድንበሩን ሰፍረው ኢትዮጵያን ለዚህ ትውልድ አስረክበው ሄዱ፡፡ ይህ ተረካቢ ትውልድ የተረከበውን መሬት ሳይቀነስ ለቀጣዩ ትውልድ ያስተላልፋል ይሆን—-” ከያዕቆብ ኃይለማሪያም/20 July 2008/።
ይህ ትውልድ ከአባቶቹ የወረሰውን አደራ ጠብቆ የሀገሩን ሉአላዊነት ሳይሸራረፍ በማስከበር ለመጭው ትውልድ የማስተላለፍ ግዴታ ያለበት መሆኑን ለአፍታ መዘንጋት የለበትም ። ህወሃት/ኢህአዴግ ከኢትዮጵያ ህዝብ እውቅና ውጭ በሚስጥር የኢትዮጵያን ሉአላዊነት በመጋፋት ዳር ድንበራችንን ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት የተደረገውን የውል ስምምነት የፖለቲካ ልዩነት፣ ብሄር፣ ሃይማኖት፣አመለካከት ሳይለያየን  የፖለቲካፓርቲዎች ፣ ድርጅቶች፣ ሲቪክስማህበራትና ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል በጋራ ተንቀሳቅሰን አሁኑኑ ማስቆም ካልቻልን የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ከማስደፈርም አልፎ እስከ ወዳኛው ትውልድ ድረስ ብጥብጥና ትርምስን የሚያወርስ ስውር ደባ ነው።
በመሆኑም የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትና ሉአላዊነት በመጋፋት ለም መሬታችንን ለሱዳን አሳልፎ የሚሰጠውን ስምምነት አገር ወዳድ የሆንን ኢትዮጵያዊያን ሁሉ በጋራ በመንቀሳቀስ በደምና በአጥንት መስዋዕትነት ተከብሮ የቆየ የሃገራችንን ዳር ድንበር ለባዕድ አሳልፈን አንሰጥም!  በሚል መርህ ተግባብተን ይህንን እኩይ ተግባር ለማስቆም ግዜ ሳንወስድ በያለንበት ፈጥነን መንቀሳቀስ ይጠበቅብናል።
የሀገራችንን ዳር ድንበር ለባዕድ ሀገር አሳልፎ የመስጠት ታሪክ አልወረስንም!

source: www.ecadforum.com 

የደህንነት ሰራተኞች ሃላፊነታችን ለአገር ወይስ ለፖለቲካ ስርአቱ ነው የሚል ጥያቄ አነሱ

መንግስት በመረጃዎች አያያዝ ዝርክርክነት ፣ በሳይበር በሚደረጉ ስለላዎች እና ከውስጥ ባሉ የመንግስት አካላት እየሾለኩ በሚወጡ መረጃዎች ህልውናየ አደጋ ላይ ወድቋል በማለት ግመገማ ማድረጉን ተከትሎ  ”የደህንነት ሰራተኞች ሃላፊነታችን ለማን ነው?” የሚል ጥያቄ ማንሳታቸውን  ከደህንነት መስሪያ ቤት ለኢሳት የደረሰው በድምጽ የተደገፈ መረጃ አመለከተ። በስብሰባው ላይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና የመንግስት ሹሞችም ተገኝተው ነበር።
ጥያቄውን ያነሱት በፌደራል ስር የሚገኙ የደህንነት ስራተኞች እና ቀደም ብሎ በአቶ መለስ ዜናዊ ዘመን በትግራይ ውስጥ በመቀሌ ዩኒቨርስቲ ሽፋን የተቋቋመው ኤም አይ ቲ እየተባለ በሚጠራው ከመቀሌ ከተማ 9 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በተገነባው ተቋም ውስጥ ተመርቀው የወጡት የደህንነት ሰራተኞች ናቸው።
የደህንነት ሰራተኞቹ “የእኛ ሃለፊነት የአገር ደህንነትን ማስጠበቅ ነው የፖለቲካ ስርአቱን ?” በሚል  ጥያቄ ያነሱ ሲሆን፣ አንድ  የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን  ” የፖለቲካ ስራ የማይሰራ ደህንነት የለም፣ የደህንነት ስራ ሲጀመር ስርአት የማቆየት ስራ ነው፤ ስርአቱን የምናቆይበት ደግሞ ፕሮፌሽናል ነው፣ በስርአቱ ላይ እምነት ማሳደር የሚጠይቅ ተግባር ነው፣ የግንቦት7ትን አስተሳሰብ የሚያቀነቅንና ስርአቱ በጉልበት መፍረስ አለበት ብሎ የሚያስብ ሰው፣ የተስፋየ ወልደ ስላሴ አይነት የደህንነት ብቃት አለው ቢባል፣ ሞሳድ 20 አመታት አሰልጥኖታል ቢባል ስርአቱን ከማፍረስ ውጭ ደህንነቱን ሊያስጠብቅ አይችልም” ፣ ስለዚህ የደህንነት ስራ ለሚሰሩ ወገኖች የፖለቲካ ወገንተኝነታቸው ወሳኝ ነው የሚል መልስ ሰጥተዋል ።
“የደህንነት ተቋሙ ፣ ሰራዊቱና ሚዲያው በተቃዋሚዎች ዘንድ መቼውንም ቢሆን ገለልተኛ ተደርጎ አይቆጠርም” ያሉት እኝህ ከፍተኛ ባለስልጣን ፣ ገለልተኛ ማድረግ የሚባል አስተሳሰብ ያለው ካለ እንደዛ ሊሆን አይችልም፣ ሊሆን የሚችለው የተቃዋሚዎችን ሰዎች ደህንነት ውስጥ ማስገባት ነው ብለዋል። ” በተለይም በተቋም ደረጃ ፤በምህጻረ ቃል ኢንሳ እየተባለ የሚጠራው የመረጃ ደህንነት መስሪያ ቤት፤ የዜግነት እና ኤምግሬሺን ፤የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤በጀኔራል ሳሞራ የኑስ የሚመራው የመከላከያ ደህንነት ፤የአስተዳደር እና ፀጥታ ፤ የፌደራል ፖሊስ ፤ የፀረ ሽብር ግብረ ሃይል በእዝ ሰንሰለት በሚፈጠር ልዩነት እርስ በርስ እየተወዛገቡ ሲሆን፣ ተቋሞቹን በትክክል የሚመሩትን አካላት  ለመለየት አስቸጋሪ ሆኖ መገኘቱና እርስ በርስ በሚፈጥሩት  እሰጥ አገባ  አንዱ አንዱ የሚሰራውን የማጠፋፋት እርምጃ እየወሰዱ መሆኑ በግምገማው ላይ ተነስቷል፡፡
የመንግስት ሚስጥሮች ለሶስተኛ ወገኖች ተላልፈው እየተሰጡ በመሆኑ ሚስጢሮችን  መደበቅ የማይቻልበት ደረጃ ላይ ተደርሷል ሲሉ አንዳንድ ባለስልጣኖች አስተያየቶችን ሰጥተዋል።
ለተነሱት አስተያየቶች መልስ የሰጡት ባለስልጣኑ፣ ኢንሳ የተቋቋመውም ይህን ለመስራት መሆኑን  ገልጸው፣ “አገሮች ሙሉ በሙሉ ከሳይበር ስለላ ነጻ ባለመሆናቸው አቶ ሃይለማርያምም ነጻ ናቸው ብየ አላስብም” ብለዋል። “አሜሪካኖች የምንናገረውን ሁሉ ከፈለጉ ይሰሙታል” የሚሉት እኝሁ ባለስልጣን፣ “እኛም የአቅማችንን ያክል አሜሪካኖች የሚናገሩትን ለማዳመጥ እንሞክራለን” ብለዋል። የሳይበር ስለላ ለማካሄድ ጥሩ ጅምሮች ቢኖሩም፣ ያን ያክል የምንኩራራበት ግን አይደለም በማለት ኢነሳ ያለበትን ደረጃ አመላክተዋል
ከኦሮሚያና ከደቡብ የመጡ የደህንነት ሹሞች ደግሞ “በመከላከያ የደህንነት ተቋሞች ውስጥ የአንድ ብሄር የበላይነት ጎልቶ ይታያል” በሚል ቅሬታ ያነሱ ሲሆን ፣ ባለስልጣኑም “የሰራዊት ማመጣጠን ስራ በረጅም ጊዜ የሚሰራ ስራ  ነው ” በማለት ለመመለስ ሞክረዋል።
” ትግሉን መርተው እዚህ ድረስ የመጡ ሰዎችና በመከላከያ ውስጥ ያለውን የመኮንኖች ቦታ የያዙት ከአንድ አካባቢ የመጡ መሆናቸው ግልጽ ነው የሚሉት ባለስልጣኑ፣ ያም ሆኖ ከትግራይ የመጡ በርካታ ጄኔራሎች ጡረታ እንዲወጡ ቢደረግም ሂደቱ ግን ረጅም ጊዜ የሚወሰድ ነው ሲሉ አክለዋል።
“የብሄር ተዋጽኦ ብቻ የአንድን ሰራዊት ጠንካራና ደካማ ጎን መገለጫ ተደርጎ መወሰድ ካለበት አደጋ አለው ” ያሉት ባለስልጣኑ፣ የአንድ ብሄር የበላይነት አለ ተብሎ በአጭር ጊዜ ለማመጣጠን ብቻ በአንድ አዳር ሁሉንም ነገር መቀየር እንደማይቻል መንግስት ያምናል ሲሉ ተናግረዋል
አቶ መለስ ዜናዊ በውጭ ሃይሎች ተገድለዋል ይባላልና በምን እንደሞቱ በትክክል ይነገረን በሚል ባለስልጣናት ላነሱት ጥያቄም የደህንነት ባለስልጣኑ፣ “አቶ መለስ በውጭ ሃይሎች ተገድለዋል የሚል ትክክለኛ ማስረጃ የለም በማለት መመለስ የጀመሩት ባለስልጣኑ፣ እርሳቸው የሞቱት በስራ ብዛት ተዳክመው እና ህክምናውን መቋቋም ባለመቻላቸው ነው ሲሉ ደምድመዋል።
በተያያዘ ዜናም የሃገሪቱን ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል ከኢሳት ጋር በመሆን እየሰራችሁ ነው፣ ለኢሳትም መረጃ ታቀብላላችሁ  ተብለው የተጠረጠሩ  5 የደህንነት አባላት በቁጥጥር ስር ውለዋል።  ወጣት መብራቴ ታምራት ፤ወጣት ጀማል አወል ፤ወጣት ደጀኔ አድማስ ፤ ወጣት ሃይሉ ጨርቆስ ፤መቶ አለቃ አሰፋ አብርሃ ሰሞኑን በደህንነቶች ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኢሳት የደህንነት ምንጮች ገልጸዋል።
በተመሳሳይ ዜናም በሃገሪቱ በ28ቱ ዩኒቨርስቲዎች የሚገኙ የህወሃት አባላት ተማሪዎች እና የደህንነቶች ሃለፊዎች ግምገማ መጀመራቸውን ለማወቅ ተችሎአል።
በግምገማው ወቅት የኦህዴድ እና የብአዴን መሪዎች የተማሪዎችን እንቅስቃሴ በመከታተል ባሰዩት ውጤት የተገመገሙ ሲሆን፣ ባለፉት ስድስት ወራት የአክሱም ፤ ደብረ ታቦር እና ደብረ ብርሃን የኒቨርስቲዎች ከፍተኛ የአመጽ እንቅስቃሴ የታየባቸው በመሆኑ ልዩ የደህንነት ክትትል እንደሚያስፈልጋቸው ተወስቷል።

ሐሙስ 16 ጃንዋሪ 2014

ለሕዝብ ግልፅ ያልሆነው የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጉዳይ

በቅርቡ ከኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጋር በተያያዘ የተለያዩ ኀሳቦች እየተነሱ ነው። በተለይ ከሰሞኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ካርቱምን ከጎበኙ በኋላ ከሌሎች ጉዳዮች በበለጠ የድንበሩ ጉዳይ መነጋገሪያ ሆኗል።

የካርቱም አንዳንድ መገናኛ ብዙሃንም በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው የድንበር ማካለል አለመግባባት (Demarcation disputes) በቅርቡ መፍትሄ እንደሚያገኝ ዘግበዋል። የሱዳኑ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዓሊ ከርቲ ሁለቱ አገሮች የድንበር ማካለል ችግራቸውን ለመፍታት መስማማታቸውን ገልፀዋል። ሱዳኖቹ “ፍሻጋ” በማለት በሚጠሩት አካባቢ ያለው የድንበር ችግር ይፈታል ብለው እንደሚያስቡ እየገለፁ ነው። በሌላ ወገን በርካታ ኢትዮጵያውያን መሬት ከኢትዮጵያ ተቆርጦ ለሱዳን ሊሰጥ ነው በሚል ቅሬታ እያሰሙ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት ጉዳዩን በተመለከተ እስካሁን የሰጠው መረጃ የለም። በቅርቡ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ሁለቱም አገሮች ሰላማዊ የድንበር ቀጠና እንዲኖራቸው እየሰሩ ነው ከማለታቸው ባለፈ፤ በጉዳዩ ላይ ዝርዝር መረጃ አልሰጡም። በቀጣይም በሀገር ውስጥና በውጪ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እውነታውን ይገልፃሉ ተብሎም ይጠበቃል። ከዚህ ቀደም የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ይሄው ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረት በመሳቡ በፓርላማው ቀርበው ማብራሪያ መስጠታቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሁለቱ ሀገሮች ድንበር ችግር ያለበት መሆኑን በመጥቀስ የማካለል ስራው እንደሚከናወን መግለፃቸው አይዘነጋም። ይኼው የድንበር ማካለል ከጥቂት ወራት በኋላ ሊከናወን እንደሚችል እየተነገረ ነው። ነገር ግን የማካለል ሂደቱ በምን መልኩ እንደሚፈፀም የታወቀ ነገር የለም።

በሀገሪቱ የሚገኙ ተቃዋሚዎች ግን የድንበር ማካለሉ ሂደት ግልፅነት የሌለው መሆኑን በመጥቀስ በመንግስት ላይ ጥያቄ አንስተዋል። ኢዴፓ፣ መኢአድ፣ አረናም ሆነ አንድነት ቅሬታቸውን ገልፀዋል።

የአረና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አብርሃ ደስታ ጉዳዩን በተመለከተ ፓርቲው እንደ ፓርቲ መረጃ እንደሌለው ገልፀዋል። ነገር ግን በግል በሁመራ ከሚገኙ ነዋሪዎች መረጃውን ለማጣራት ጥረት ማድረጋቸውን ገልፀዋል። በሁመራ የሚኖሩ አንዳንድ ግለሰብ ነዋሪዎች “መሬቱ ለሱዳን ይሰጣል” ተብሎ እየተወራ መሆኑን ደርሰንበታል ብለዋል። በተጨማሪም የአካባቢው ባለስልጣናትን ስለጉዳዩ ለመጠየቅ ሙከራ ማድረጋቸውንም የሚገልፁት አቶ አብርሃ ባለስልጣናቱም “የምናውቀው ነገር የለም” እንዷላቸውም ነው የገለፁት።

ፓርቲው ጉዳዩ የሀገር ጉዳይ እንደመሆኑ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶት እያጣራ መሆኑን የገለፁት አቶ አብርሃ፤ ከስርዓቱ ባህሪ በመነሳት በድንበር ማካለሉ ላይ እምነት መያዙ አስቸጋሪ ነው ይላሉ። “ሥርዓቱ ለስልጣን ብሎ እንጂ የሀገር ድንበር ለመጠበቅ አይደለም። ከዚህ ጉዳይ ተነስቶ የኤርትራን ጉዳይ እንዳለ ሆኖ የሱዳንም ጉዳይ ሊያጠራጥር ይችላል። ምክንያቱም ሥርዓቱ ለኢትዮጵያ ያለው ተአማኒነት ላይ ጥርጣሬ አለን። ሥርዓቱ ዳርድንበር ከመጠበቅ ባለፈ፤ የውጪ ኃይሎችም ጋር ቢሆን በስልጣን የሚቆይበትን መንገድ ሊያፈላልግ ይችላል” በማለት ጥርጣሬአቸውን ገልፀዋል።

የሱዳን መንግስት የአባይን ግድብ በመደገፉ በምትኩ ከኢትዮጵያ መሬት ተቆርሶ ተሰጥቶት ሊሆን ይችላል የሚለውን ጥርጣሬም በተመለከተ አቶ አብርሃ ሲመልሱ፤ “የሱዳን መንግስት የአባይን ግድብ መደገፉ ጥሩ ነው። ነገር ግን የሱዳን መንግስት የአባይን ግድብ ቢደግፈውም፣ ባይደግፈውም የእኛ ግድብ ነው። የሱዳን መንግስት የአባይን ግድብ መደገፉ ጥሩና የምንፈልገው ቢሆንም፤ ስለደገፈ ተብሎ የሚሰጥ መሬት ሊኖር አይገባም። ከአባት፣ አያቶቻችን የተረከብነው መሬት ለሌላ አካል ሊሰጥ አይገባም። ድርጊቱ ተፈፅሞ ከሆነ እንታገለዋለን” ሲሉ መልሰዋል።

“መንግስት በጉዳዩ ላይ ግልፅ መሆን አለበት” የሚሉት አቶ አብርሃ፤ በጉዳዩ ላይ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ግልፅ መደረግ አለበት ብለዋል። ድንበሩ ሲካለልም የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች መሳተፍ አለባቸው ብለዋል።

“የድንበር ጉዳይ የአንድ ፓርቲ ጉዳይ አይደለም። ኢህአዴግ በመንግስትነቱ ሳይሆን በፓርቲነቱ ስለሚሰራ ጥርጣሬ አለን” የሚሉት አቶ አብርሃ ስለሆነም ለጉዳዩ ማረጋገጫ የሚሆን ግልፅ መረጃ ሊሰጥ ይገባል ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት ቀጠናው የተረጋጋ ባለመሆኑ የድንበር መካለል እንደሌለበት የጠቀሱት አቶ አብርሃ የድንበር ማካለሉ ሂደት ተጀምሮም ከሆነ መቆም አለበት ብለዋል። በደቡብ ሱዳንና በሰሜን ሱዳን አንዳንድ አካባቢዎች መረጋጋት በሌለበት በድብብቆሽ ወደ ድንበር መካከል መገባት የለበትም ሲሉም አሳስበዋል።

የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ጫኔ ታደሰም እንደ አቶ አብርሃ በጉዳዩ ላይ ከመንግስት ግልፅ የሆነ መረጃ ማግኘት እንዳልቻሉ ገልፀው፤ ነገር ግን መንግስት በውጪ ግንኙነትና የዲፕሎማሲ ዙሪያ ላይ ጠንከር ያለና ኢትዮጵያውያንን ለሚጠቅም ተግባር ቅድሚያ መስጠት እንዳለበት አስገንዝበዋል። ለዚህ ደግሞ የድንበር ጉዳይ የሕዝብ ጉዳይ እንደመሆኑ ግልፅ አሰራርን መከተል አለበት ብለዋል። ከመንግስት ባለፈ ሚዲያውም ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበዋል።

አቶ ጫኔ በመንግስት በኩል የሀገር ድንበርን በተመለከተ የመድበስበስ አካሄድ መኖር የራሱ አደጋ እንዳለው ይገልፃሉ። ፓርቲያቸውም እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊና እንደ ተቃዋሚ ፓርቲ የሚያሳስበው እንደሆነና በጉዳዩም ላይ ተጨባጭ መረጃ ለማግኘት እየጣረ መሆኑን አስረድተዋል። እንደ ፓርቲም በአካባቢው ከሚገኙ አባሎቹም መረጃ የማሰባሰብ ስራም እያከናወነ እንደሆነም ጠቅሰዋል።

ኢዴፓ ከኢህአዴግ ጋር የውጪ ግንኙነት ፖሊሲ ልዩነት እንዳለውም ጠቅሰዋል። ከድንበር ማካለል ጋር በተያያዘም ያሉ ችግሮች የኢህአዴግ የውጪ ፖሊሲ ችግሮች የሚመነጭ መሆኑን ጠቅሰው አሁንም በመንግስት በኩል የኢትዮ ሱዳንን ድንበር ማካለል ላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሚጎዳ መልኩ የሚፈፀም ከሆነ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን ቆመን የማጋለጥና የመቃወም ስራ እንሰራለን ብለዋል።

የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ስለሺ ፈይሳ በበኩላቸው ፓርቲያቸው በጉዳዩ ላይ አቋም መወሰዱን ይናገራሉ። ፓርቲው የወሰደው አቋም፤ ጉዳዩን የማጋለጥና ሕዝቡ እንዲያውቀው የማድረግ መሆኑን ገልፀዋል።

“የኢትዮጵያ መንግስት ከሕዝቡ ጀርባ ሆኖ ድንበር የማካለል ስራ እየተሰራ በመሆኑ እንቃወመዋለን። ጉዳዩን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚያውቀው አይመስለንም። ምን ያህል መሬት ለሱዳን ይሰጣል? ለምንስ ይሰጣል? ታሪካዊ ባለቤትነቱ የማነው? የሚለው መታየት አለበት የሚሉት አቶ ስለሺ፤ ድንበሩን በድብብቆሽ የማካለሉ ተግባር ተቀባይነት የለውም ብለዋል።

ፓርቲው ከልዩ ልዩ ምሁራንና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ሰዎች እንደተረዳው የኢትዮ ሱዳን የድንበር ማካለል ባለፉት ሰርዓቶች ቢነሳም ጉዳዩ ሳያስተናግዱት መቆየታቸውን አስታውሰው ኢህአዴግ ግን መነሻው ግልፅ ባልሆነ መንገድ የድንበር ማካለል ጥያቄውን አሁን ማንሳቱን ጠቅሰዋል። ያም ሆኖ ኢህአዴግ በሱዳን ድንበር አሸባሪ የሚላቸው ወገኖች ተደራጅተው እንዳይመጡበት ገዢ መሬት ለማሳጣት ድንበሩን ለድርድር አቅርቦ እንደሚሆንም እንገምታለን ብለዋል።

ፓርቲውም ይሄንኑ ጉዳይ እንደ አጀንዳ በመያዝ የፓናል ውይይት በማዘጋጀት ከፓናል ውይይቱ በሚነሳው ኀሳብ ደግሞ ሕዝቡ አቋም እንዲይዝና እንዲሁም በጉዳዩ ላይ ወደ አካባቢው በማቅናት በጎንደር ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እቅድ መያዙንም ተናግረዋል።

“በአሁኑ ወቅት መሬቱ በእርግጥም ለሱዳን አልተሰጠም” ያሉት አቶ ስለሺ፤ ሆኖም ግን በድንበር ማካለሉ ላይ ድርድር ተካሂዶ በወረቀት ደረጃ ሁለቱ አገሮች መስማማታቸውን የኢትዮጵያ መንግስትም በኀሳብ ደረጃ ተስማምቶ በመጪው መጋቢት የመሬት ርክክብ እንደሚፈፀም የሱዳን የመገናኛ ብዙሃንና ሌሎች ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች እየዘገቡት እንደሆነም ተናግረዋል።

“ጉዳዩን እየደበቀው ያለው ኢህአዴግ ብቻ ነው” የሚሉት አቶ ስለሺ፤ “ነገሩ ግመል ሰርቆ አጎንብሶ ነው” ብለውታል። የድንበር ማካለል ጉዳይ የሉአላዊነት በመሆኑ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ ሊፈፀም አይገባም ሲሉ ተቃውመዋል። ኢህአዴግ ለሀገሪቱ ታሪካዊ ሉአላዊነት ደንታቢስ በመሆኑም የድንበር ማካለሉን ለስልጣኑ ብሎ ከመፈፀም ወደኋላ አይልም ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል። ፓርቲያቸው ሕዝቡ ጉዳዩን እንዲያውቀው ከማድረግ ባለፈ ኢህአዴግ በድርድር የተስማማባቸው ስምምነቶች በመጪው ትውልድ ተቀባይነት እንዳይኖረው ለማድረግ አበክሮ እንደሚሰራ ነው ጨምረው የገለፁት።

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ሊቀመንበር አቶ አበባው መሐሪም እንደሌሎቹ የፓርቲ አመራሮች ጉዳይ የሚያሳስበው መሆኑን በመግለፅ ጉዳዩን የሚያጣራ ቡድን ወደ ስፍራው መላኩን ተናግረዋል። አጣሪ ቡድኑ በሚያመጣው መረጃ ላይ መግለጫ እንደሚሰጥ ገልፀዋል።

ይሁን እንጂ መኢአድ እንደ ፓርቲ ድንበሩ በቅድመ አያቶቻችን አባቶቻችን የተካለለ በመሆኑ እንደገና መከለል የለበትም የሚል አቋም እንዳለው ገልፀዋል። የፓርቲው አቋም የአከላለል ሂደቱ ግልፅ ይሁን አይሁን ከማለት ባለፈ ድንበሩ እንደገና መከለል አይገባውም የሚል እንደሆነ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ድንበር ማካለል ቀደም ሲል በነበሩ ስርዓቶች ሳይነሳ አሁን የተነሳበት ምክንያት የአማራውን ብሔር በመልከአምድር እና በቁጥር ለማሳነስ የሚደረግ ሴራ ነው የሚሉት አቶ አበባው፤ ፍትህና ዴሞክራሲ እንዲሁም በሕዝብ እኩልነት የሚያምን ሁሉ ሊቃወመው ይገባል ብለዋል።

በመንግስት በኩል የድንበር ማካለሉን ሂደት ለሕዝብ ግልፅ ማድረግ በተለይ ጎንደር አካባቢ ሱዳኖች ይገባናል ስለሚሉት መሬት ግልፅ አቋም መያዝ አለበት የሚሉት አቶ አበባው፤ “ሕዝቡ ድምፁ ሊሰማና የታሪክ አዋቂዎችና አባቶች በጉዳዩ ሊጠየቁ ይገባል። ሽፍንፍን ባለ ሁኔታ ድንበር ማካለል ተገቢ አይደለም። ይህ አካሄድ ለሱዳንም ሆነ ለኢህአዴግ አይጠቅምም” ሲሉ አስረድተዋል። የኢትዮጵያ መንግስትም ይህንን አድርጎ እና እያደረገ ከሆነም እንደገና ነገሩን እንዲያጤነው” ሲሉ አሳስበዋል።

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው በበኩላቸው የፓርቲው አዲሱ የስራ አስፈፃሚ እየተወያየባቸው ካሉ ሦስት አስቸኳይ ዋና ርዕሰ ጉዳዮች የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ማከለል ጉዳይ አንዱ መሆኑን ገልፀዋል።

ኢህአዴግ በሉአላዊ ግዛት ማስከበር ጉዳይ የላላ አመለካከት ያለው በመሆኑ ብሔራዊ ጥቅማችንን ሊጐዳ የሚችል እርምጃ ሲወስድ በመቆየቱ አሁንም በዚህ ተግባሩ ሊቀጥል እንደሚችል የጠቀሱት አቶ ሀብታሙ ከዚህ በፊትም የሀገሪቱን ታሪካዊ ባለቤትነት በጣሰ መንገድ ኢትዮጵያ ወደብ አልባ መደረጓን አቶ ሀብታሙ አስታውሰዋል። አሁንም የኢትዮ-ሱዳን ድንበር የኢትዮጵያን ጥቅም ባላስጠበቀ መንገድ ሊፈፀም ስለሚችል ከፍተኛ ሰጋት አድሮብናል ብለዋል።

“በሱዳን በኩል እየተጠየቀ ያለው መሬት የኢትዮጵያ ነው” የሚሉት አቶ ሀብታሙ፤ ይሄንን ሉአላዊ ግዛት ለሱዳን መስጠት ተገቢ አይደለም ብለዋል። ኢህአዴግ በኢትዮጵያ ግዛት ላይ እንደገና ከተደራደረበት ከሕዝብ ጋር በመሆን የምንታገለው ነው ብለዋል።

እስካሁን በመንግስት በኩል ግልፅ መረጃ እንዲሰጥ ፓርቲያቸው ደጋግሞ እያሳሰበ መሆኑን የጠቀሱት ህዝብ ግንኙነቱ የድርድሩ ውጤት ብቻ ሳይሆን ሂደቱም ለህዝቡ ግልፅ መደረግ እንዳለበትም አሳስበዋል።

“ከዚህ በፊት ከ60ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን የረገፉበት የባድመ ጉዳይ መፍትሄ አላገኘም። የአሰብ ወደብን በተመለከተም ኢህአዴግ ቸልተኛ አቋም በመከተሉ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ጎድቷል” የሚሉት አቶ ሀብታሙ አሁንም በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ማካለል በተመለከተ ኢህአዴግን እንድንጠራጠረው አድርጎናል ብለዋል።

ኢህአዴግ በተፈጥሮአዊ ባህሪውን እና ከቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሚመነጭ አስተሳሰብ መረዳት እንደሚቻለው ግንባሩ በሉአላዊነት ላይ የተዛባ አቋም ያለው በመሆኑ አሁንም የሀገሪቱን ሉአላዊነት በመጠበቅ ላይ ስጋት አለን ሲሉ አቶ ሀብታሙ ገልፀዋል።

“ሀገር ማለት ሕዝብ ነው ነው ብለው ለኢትዮ-ኤርትራ ድንበር 60 ሺህ ሰው አስጨርሰዋል” የሚሉት አቶ ሀብታሙ ከሱዳን ጋር ያለውን ግንኙነት ጤናማ ለማድረግና የአባይን ግድብ መደገፉን ተከትሎ መሬት ቆርጦ ለመስጠት ከታሰበ ተገቢም፣ ትክክል አይደለም ብለዋል። ድንበር እየሰጡ ግድብ መገደብ ሰጥቶ መቀበል አይደለም በማለት ተቃውመውታል። ግድብ መገደብ የሀገሪቱ መብት እንደሆነም መታወቅ አለበት ሲሉ አጠቃለዋል።

በዚሁ አወዛጋቢ ጉዳይ ላይ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲን ለማነጋገር ጥረት አድርገናል። ነገር ግን ከጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ኦፊሴላዊ ጉብኝት ጋር በተያያዘ ስራ ስለበዛባቸው ልናገኛቸው አልቻልንም። በተመሳሳይ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪካ ጉዳዮች በኩልም መረጃ ለማግኘት ጥረት አድርገናል። በመስሪያ ቤቱ አሰራር በቃል አቀባዩ በኩል መረጃ ስለሚሰጥ ሊሳካልን አልቻለም።

በተጨማሪም የመንግስት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ሽመልስ ከማልን ለማነጋገር ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት ቴሌፎናቸው ስለማይሰራ ልናገኛቸው አልቻልንም። በጠቅላይ ሚኒስትር የሕዝብ ግንኙነት አማካሪ አቶ ደስታ ተስፋውን አነጋግረን አቶ ሽመልስን ወይም አምባሳደር ዲናን ብቻ ማነጋገር እንደምንችል ገልፀውልናል። በቀጣይ ሳምንት የመንግሥትን ምላሽ ይዘን ለመመለስ ጥረት እናደርጋለን።

ረቡዕ 15 ጃንዋሪ 2014

ኢህአዴግ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ መመሪያን መተውን አስታወቀ

የጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ አማካሪ የሆኑት አቶ በረከት ስምዖን በቅርቡ ከሚኒስትሮች እና ከኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ባደረጉት ውይይትና ግምገማ ላይ ” ህዝቡን ለመምራት የሚነደፉ ንድፈ ሀሳቦች ( ቲዮሪዎች) በየጊዜው ካልተሻሻሉ የሚዝጉ በመሆናቸው አብዮታዊ ዲሞክራሲ በልማታዊ ዲሞክራሲ እንዲተካ ተደርጓል ብለዋል። የኢህአዴግ መንግስት ይበልጥ የሚገለጸው በአብዮታዊ ዲሞክራሲ አስተሳሰብ ሳይሆን በልማታዊ ዲሞክራሲ አስተሳሰብ ነው በማለት አቶ በረከት ገለጽዋል
አቶ በረከት አብዮታዊ ዲሞክራሲ በልማታዊ ዲሞክራሲያዊ መንግስት ከመተካቱ በፊት ፣ ግንባሩ ለ3 ተከፍሎ እንደነበር ገልጸዋል። አንደኛው የአመራር ወገን “ችግራችን የውስጥ ነው እና በቅድሚያ የውስጥ ችግራችንን እንፈትሽ የሚል” አቋም ሲይዝ ፣ ሌላው ወገን ደግሞ ዋናው ችግራችን ሻዕቢያ በመሆኑ በቅድሚያ ሻዕቢያን እንውጋ የሚል አቋም ይዞ እንደነበር፣ እና ሻእቢያን ከወጋን በሁዋላ ወደ ውስጥ ችግራችን እንመልከት የሚለው ሶስተኛው አማራጭ አሸንፎ መውጣቱን ገልጸዋል
በ1997 ዓም ዋናው የአመጽ ሀይል የነበረው ስራ ያጣውና ተስፋ የቆረጠው ወጣት ነው በማለት የገለጹት አቶ በረከት ለወጣቱ ስራ ካልተፈጠረለት በመንግስት እና በአገር ላይ እንደሚያምጽ ገልጸዋል። መንግስት የምርጫ 97ትን አመጽ ያስነሱት ተቃዋሚዎች ናቸው ብሎ ሲከስ መቆየቱ ይታወቃል።
ኢህአዴግ ከባላሀብቱ ነጻ የሆነ መንግስት ለመመስረት መነሳቱን የገለጹት አቶ በረከት፣ ስልጣን ላይ የሚያመጣን አርሶአደሩና በከተማ ያለው ጭቁኑ ህዝብ ነው እንጅ ባለሀብቱ  አይደለም ብለዋል። የኢትዮጵያ መንግስት በባለሀብቱ ገንዘብ የሚተዳደር አይደለም ያሉት አቶ በረከት፣ ገንዘብ ከፈለገ ከባላሀብቱ በግብር መልክ መውሰድ እንደሚችል ተናግረዋል። ይህ መንግስት ለህልውናው የራሱ የገቢ ምንጭ እንዳሉት የጠቀሱት አቶ በረከት፣ አየር መንገድን ባንኮችን እና መብራት ሀይልን በምሳሌነት አንስተዋል። የመንግስትን አስተዳደር ያለምንም ችግር ለማስኬድ የባለሀብቱም የውጭ ድጋፍም እንደማያስፈልግ አቶ በረከት አክለዋል።
አቶ በረከት፣  ኢህአዴግ ምርጫውን ያለባለሀብቶች ድጋፍ ማሸነፍ እንደሚችል እየገለጹ ባለበት ጊዜ በድንገት የመንግስት ተቋሞችን በመግለጽ በቂ ገንዘብ አለን ማለታቸው ተሰብሳቢዎችን ማስገረሙን ስብሰባውን የተከታተሉት አንድ ከፍተኛ የኢህአዴግ  አመራር ገልጸዋል። አመራሩ እንዳሉት ኢህአዴግ ለምርጫ ማስኬጃ ከመንግስት ገንዘብ እንደሚወሰድ የ  አቶ በረከት ንግግር በቂ ማሳያ ነው ።
መንግስት የራሱ ገንዘብ ከሌለው እንደምእራብ የአፍሪካ አገራት ይሆናል ያሉት አቶ በረከት፣ የኮትዲቩዋር ሚኒስትሮች ደሞዛቸውን የሚወስዱት ኮትዲቯር ከሚገኘው የፈረንሳይ ኢምባሲ ነው ይላሉ። በኬንያም ሁኔታው ተመሳሳይ መሆኑን አቶ በረከት አክለዋል
ኢህአዴግ በ2002 በተደረገው ምርጫ ከግል ባለሀብቶች ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡ ይታወቃል።
በባቡር ግንባታ፣ በመንገድ ቁፋሮና በትራንሰፖርትና እጥረት የተነሳ በአዲስ አበባ መኖር ያስጠላል ያሉት አቶ በረከት ያም ቢሆን ግን ህዝቡ ልማት ነው በሚል እንደሚቀበለው ገልጸዋል ።

ኢትዮጵያ በአለም የምግብ እጥረትና ባልተመጣጠነ ምግብ የመጨረሻውን ደረጃ ያዘች

የኦክስፋምን ጥናት መነሻ በማድረግ ረዩተርስ እንደዘገበው በምግብ አቅርቦት፣ በምግብ ጥራትና በምግብ ዋጋ ኢትዮጵያ ከ125 አገራት ከቻድ በመቀጠል የመጨረሻውን ደረጃ ይዛለች።በአለም ላይ የተመጣጠነ ምግብ በማቅረብ፣ በምግብ ዋጋና በጥራት ሆላንድ አንደኛ ሆና ስትመረጥ ፈረንሳይና ስዊዝርላንድ ይከተላሉ። አሜሪካ 21ኛ ደረጃ ስትይዝ ከአንድ እስከ 10 ያሉትን ደረጃዎች የአውሮፓ አገራት ይዘውታል።

የኦክስፋም ጥናት ላለፉት 23 አመታት ኢትዮጵያን በምግብ እራሱዋን እናስችላለን፣ ግብርናው በከፍተኛ ደረጃ እያደገ ነው በማለት ለሚናገረው ለኢትዮጵያ መንግስት ትልቅ መርዶ ነው በማለት አንድ ኢኮኖሚስት ተናግረዋል ። ከአፍሪካ አገራት በምግብ አቅርቦትና ጥራት ከኢትዮጵያ በባሰ ሁኔታ ውስጥ መገኘቷ፣ እስከ ዛሬ ድረስ ለግብርናው ዘርፍ የዋለውን ኢንቨስትመንት ጥያቄ ውስጥ የሚከት ብቻ ሳይሆን የገዢውን ፓርቲ ግብርና መር ፖሊሲ ውድቀትን የሚያመላክት መሆኑን አስተያየት ሰጪው ይናገራሉ።

አርሶ አደሩን እንደፈለገ ብናደርገው በኢህአዴግ ላይ አይነሳም ሲሉ አቶ በረከት ተናገሩ

ር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ አማካሪ የሆኑት አቶ በረከት ስምኦን ለመንግስት ሚኒስትሮችና ለከፍተኛ የኢህአዴግ አመራሮች በተዘጋጀው የምርጫ ውይይትና ግምገማ ላይ ባቀረቡት ንግግር ላይ እንደገለጹት አርሶ አደሩ እስካሁን በተሰረላት ስራ በመርካቱ ” መንግስት ሰላማዊ ሰልፍ ውጣ ቢለው ይወጣል፣ መንግስት ተኛ ቢለው ይተኛል፣ ግፍ ብንፈጽም አርሶአደሩ ይህን መንግስት ምንም አይለውም፣ ይሸከመዋል” ብለዋል።
30 በመቶ የሚሆነውን ወጪ የምንሸፍነው በውጭ እርዳታ በመሆኑ፣ ከውጭ ተጽእኖ ለመላቀቅ ወጪያችንን የሚሸፍን ገቢ ማግኘት አለብን ያሉት አቶ በረከት፣ “በ1997 ምርጫ ወቅት የውጭ ሃይሎች ጥፋት ያጠፉትን መሪዎችን ወደ ፍርድ ቤት የምትወስዱዋቸው ከሆነ እርዳታ እናቆማለን ባሉት መሰረት እርዳታ አቁመውብን ነበር” ሲሉ ለራሳቸው ባለስልጣኖች ተናግረዋል።
አቶ በረከት  ”በ1884ቱ ድርቅ ጊዜ የአሜሪካ የእርዳታ ድርጅት ሃላፊው የመሬት ፖሊሲያችሁን ካልቀየራችሁ እርዳታ አንሰጥም” ብለዋቸው እንደነበር ተናግረዋል።
ኢህአዴግ ከዋናዎቹ አመራሮች ጀምሮ በተዋረድ ለሌሎች አመራሮችም ምርጫውን ስለሚያሸንፉበት ሁኔታ ስልጠና እየሰጠ ነው። ኢህአዴግ የገጠሩን ድምጽ ሙሉ በሙሉ እንደሚያገኝ አቶ በረከትና ኢህአዴግ ሙሉ በሙሉ ተማምነዋል። ይሁን እንጅ የኢህአዴግ ካድሬዎች  በየገጠሩ በመዞር ያልተደራጀውን አርሶአደር በአንድ ለአምስት በማደራጀት፣ በመሬት እጥረት የተከፋውን ወጣት የወል መሬት እየሸነሸኑ በመስጠት ላይ መሰማራታቸውን የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።

ዓርብ 10 ጃንዋሪ 2014

አዋሳ አየር ማረፊያ ሊሰራላት ነው





 
ፋና እንደዘገበው ከተማዋን የሚጎበኙ ቱሪስቶች መጨመራቸውን ተከትሎ በከተማዋ አውሮፕላን ማረፊያ ለማሰራት እድቅ ተይዟል። የኤርፖርቶች ድርጅት የግንባታ መሬት ከአዋሳ መስተዳደር መረከቡን በመግለጽ በአንድ ሚሊዮን ብር የዲዛይን ስራው እንደሚሰራና በአራት ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ገልጿል።
አዋሳ ከአዲስ አበባ በ270 ኪሜ ርቀት ላይ የምትገኝ ሲሆን በአለፈው የፈረንጆች አመት ከ600 ሺ የአገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶች ጎብኝተዋታል።

Emperor Menelik's audio message to Queen Victoria

(ሰበር ዜና) እነ ሌንጮ ለታ ኢትዮጵያ ሊገቡ ነው

(በአንድ ወቅት በዘ-ሐበሻ ድረገጽ ወጥቶ የነበረው ሌንጮን እና ፕሮፌስር ይስሃቅን በሚኒያፖሊስ በድርድር ስብሰባ በኋላ የተነሱትን ፎቶ የሚያሳይ ምስል)
(በአንድ ወቅት በዘ-ሐበሻ ድረገጽ ወጥቶ የነበረው ሌንጮን እና ፕሮፌስር ይስሃቅን በሚኒያፖሊስ በድርድር ስብሰባ በኋላ የተነሱትን ፎቶ የሚያሳይ ምስል)

(ዘ-ሐበሻ) “ከእንግዲህ የቀድሞው መንገድ አይሰራም” በሚል የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባርን የመሰረቱት የቀድሞ የኦነግ አመራሮች እነኦቦ ሌንጮ ለታ ኢትዮጵያ ሊገቡ መሆኑ ተሰማ፡፡ የዘ-ሐበሻ የሚኒያፖሊስ ምንጮች እንዳስታወቁት ከዚህ ቀደም ኦሮሚያ ክልልን ለማስገንጠል ይንቀሳቀሱ ከነበሩ ሃይሎች ጋር የነበሩት እነ ኦቦ ሌንጮ ለታ የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባርን በሚኒሶታ ከመሰረቱ በኋላ በሃገር ቤት ገብተው ለመታገል መወሰናቸውን አስታውቀዋል።
ከጥቂት አመታት ወዲህ ፕሮፌሰር ኤፍሬም ኢስሃቅ እነ ሌንጮ ለታን ለማስማማት ወደሚኒያፖሊስ ከ2008 ጀምሮ በተደጋጋሚ ሲመላለሱ እንደነበር የዘ-ሐበሻ ምንጮች በፎቶ ግራፍ ጭምር የተደገፈ መረጃ ያቀረቡ ሲሆን “ከ እንግዲህ የቀድሞው መንገድ አይሰራም” የሚል አቋም የያዘው ይኸው የሌንጮ ለታ ግሩፕ የፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅን ምልጃ ተቀብሎ ወደ ኢትዮጵያ በመግባት በቀጣዩ ምርጫ ለመወዳደር እንደሚዘጋጅ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገልጸዋል።
የሌንጮ ለታ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ወደ ኢትዮጵያ በቅርብ ቀን እንደሚገባ ያስታወቁት እነዚሁ ምንጮች፤ በተለይ በአሁኑ ወቅት በርካታ የኦሮሞ ምሁራን፣ የሰብ አዊ መብት ተከራካሪዎች የመብት ጥያቄ አንስተው በአሸባሪነት በታሰሩበት ወቅት በዴሞክራሲያዊ መንገድ ኢሕ አዴግን እንታገላለን ብለው መወሰናቸው በሚኒሶታ የሚገኙ በርካታ ኦሮሞ ኢትዮጵያውያንን እያነጋገረ እንደሚገኝ በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል።
ለትውስታ እነዚህን ታሪካዊ ፎቶዎች እንጋብዝዎ

olf 2
olf 3
olf 4
olf 5
olf 6



Olf

ሐሙስ 9 ጃንዋሪ 2014

Breaking News: Teddy Afro with renowned African artist released a new single


January 9, 2014
Teddy Afro in collaboration with renowned African artist has released a new single from Coke studio. The song entitled “Togetherness” aims to bring friendship and brotherhood among Africans!
Meanwhile Teddy’s world cup song is to be released very soon. Africa Unite! One Love!


In celebrating Coke Studio Africa, the artists come together with a musical message for Africa, calling for unity amongst Africans on the Season 1 Finale.
Coke Studio Africa is convergence of a diverse number of prominent African artists coming together to combine various genres of music from all over Africa.

ዓርብ 3 ጃንዋሪ 2014

በሞያሌ ከተማ የኦነግ ታጣቂዎች የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ ከተማዋ በመከላከያ ሰራዊት ስትታመስ ዋለች

ለፈው ረቡእ ታጣቂዎቹ ከቀኑ 10 ሰአት ገደማ ወደ ከተማዋ በመግባት 3 ጠባቂዎችን በመግደልና አንደኛውን ታጣቂ መሳሪያውን በመቀማትና ልብሱን በማስወለቅ " ሂድና ለአለቆችህ ንገር" በማለት ጉዳት ሳያደርሱበት መልቀቃቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጸዋል። ታጣቂዎቹ አንድ ድግን መትረጊስ፣ አንድ ላውንቸርና አንድ ባዙቃ ማርከው ወስደዋል። ይህንን ተከትሎ በአካባቢው የደረሱት የመከላከያ ሰራዊት አባላት አንዳንድ የከተማ ነዋሪዎችን እየደበደቡ ሲያሰቃዩ መቆየታቸውን ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ለኢሳት ገልጸዋል።
 

አንድ ሹፌር ለኢሳት እንደገለጹት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተሳፋሪዎች ከመኪና ላይ በመሳወረድ ድብደባ እንደፈጸሙባቸውና እርሳቸውም በጥፊ እንደተመቱ ተናግረዋል "እኛ ለምን እንደተደበደብን አልገባንም" የሚሉት ነዋሪዎች፣ ሁኔታው እስከትናንት ድረስ ውጥረት የነበረበት እንደነበርና ፍተሻው በእየጫካው እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል። ታጣቂዎቹ በነዋሪዎች ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለማድረሳቸውም ተገልጿል።በጉዳዩ ዙሪያ የሞያሌን አስተዳደር ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም። መንግስትም በጉዳዩ ላይ የሰጠው አስተያየት የለም።ኦነግ ገዢውን ሀይል በትጥቅ ትግል ለማስወገድ ከሚንቀሳቀሱት ድርጅቶች መካከል አንዱ ነው።ይህ በእንዲህ እንዳለ የመንግስት ታጣቂዎች በኦጋዴን ውስጥ በሚኖሩ ዜጎች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ኦጋዴን ፕሬስ ዘግቧል።ልዩ ሚሊሺያ የሚባሉት ሀይሎች ከመከላከያ ሰራዊት አባላት ጋር በወሰዱት እርምጃ ፍሪህ ደሃግ አዳር የተባለው ሰው ሲገደል ሌሎች ደግሞ ቆስለዋል።"እኛ ለምን እንደተደበደብን አልገባንም" የሚሉት ነዋሪዎች፣ ሁኔታው እስከትናንት ድረስ ውጥረት የነበረበት እንደነበርና ፍተሻው በእየጫካው እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል።ታጣቂዎቹ በነዋሪዎች ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለማድረሳቸውም ተገልጿል።በጉዳዩ ዙሪያ የሞያሌን አስተዳደር ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም። መንግስትም በጉዳዩ ላይ የሰጠው አስተያየት የለም። ኦነግ ገዢውን ሀይል በትጥቅ ትግል ለማስወገድ ከሚንቀሳቀሱት ድርጅቶች መካከል አንዱ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ የመንግስት ታጣቂዎች በኦጋዴን ውስጥ በሚኖሩ ዜጎች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ኦጋዴን ፕሬስ ዘግቧል። ልዩ ሚሊሺያ የሚባሉት ሀይሎች ከመከላከያ ሰራዊት አባላት ጋር በወሰዱት እርምጃ ፍሪህ ደሃግ አዳር የተባለው ሰው ሲገደል ሌሎች ደግሞ ቆስለዋል።

ሐሙስ 2 ጃንዋሪ 2014

በደቡብ ክልል የይርጋ ጨፌ መምህራን የስራ ማቆም አድማ አደረጉ

መምህራኑ አድማውን የጀመሩት ያለፍላጎታችን ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ደሞዛችን እየተቆረጠብን ነው በሚል ነው። መምህራኑ ለይርጋ ጨፌ ከተማ አስተዳደር፣ ለጌዲዮ ዞንና ልክልሉ ትምህርት ቢሮ በጻፉት ደብዳቤ ላይ ” ከ ሀምሌ 2005 ዓም ጀምሮ ለህዳሴ ግድብ የሚቆረጠው ገንዘባችን እኛ ያለፈቀድነውና ያልተስማማንበት በመሆኑ ጥቅምት 28፣ 2006 ጀምሮ  ስራችንን በአግባቡ እየሰራን የመብት ጥያቄያችንን ለሚመለከተው ሁሉ ስናቀርብ በመቆየታችን ታህሳስ አንድ በዞን መምህራን ማህበር ሰብሳቢነት የከተማው ከንቲባ ፣ የከተማው ትምህርት ዩኒት ሃላፊ በተገኙበት አቆራረጡ አግባብነት የሌለውና የመምህራንን መብት የጣሰ መሆኑን በውይይቱ ተረጋግጦ ከታህሳስ ጀምሮ የሚቆረጠው ገንዘብ እንዲቆም፣ መወሰኑን” አስታውሷል። ድብዳቤው “ነገር ግን የከተማው አመራር እንደተለመደው በመዋሸት እንዲቆም የተወሰነው ገንዘባችን እንዲቆረጥብን አድርጓል” ይላል።
ድብዳቤው አያይዞም ” የታህሳስ ወር የተቆረጠበን ተስተካክሎ እንዲከፈለን፣ ከሀምሌ 30 ፣ 2005 ዓም ጀምሮ ለተከታታይ 5 ወራት የተቆረጠብን ገንዘብ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲመለስልን፣ ከዚህ ቀደምም ያለፈቃዳችን እየተቆረጠብን ያለው የኢች አይ ቪ መዋጮ እንዲቆም እየጠየቅን ከዛሬ ማለትም ከታህሳስ 22 ቀን 2006 ዓም ጀምሮ ስራ ማቆማችንን እንገልጻለን፤ የታህሳስ ወር የሚመለስልን ከሆነ ግን ወደ ስራ ገበታችን ተመልሰን እየሰራን ከዚህ ቀደም የተቆረጠውን  የ5 ወር ገንዘባችንን ደግሞ እስከ ታህሳስ 25 2006ዓም በትእግስት የምንጠብቅ ሲሆን ይህ ሳይሆን ቢቀር ግን አሁንም ስራችንን ለማቆም የምንገደድ እና ለሚመለከተው የበላይ አካል የምንሄድ መሆናችንን ከወዲሁ እናሳውቃለን” ብሎአል።  በትምህርት ቤቱም  ይሁን ከትምህርት ቤት ውጭ ለሚፈጠሩ ችግሮች  መምህራኑ ተጠያቂዎች ያለመሆናቸውን ገልጸዋል።
ደብዳቤውን ተከትሎ መምህራኑ ያስራ ማቆም አድማውን ተማሪዎችን በማሰናበት መጀመራቸውን ተከትሎ መስተዳድሩ ዛሬ የታህሳስን ወር ለመክፈል መገደዱን ዘግይቶ የደረሰን ዜና ያመለክታል።
በደቡብ ክልል በሚገኙ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራን ያለፈቃዳቸው የሚቆረጥባቸውን ገንዘብ በመቃወም የስራ ማቆም አድማ ሲያደርጉ ሰንብተዋል።
ታህሳስ ፳፫( ሃያ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-