የማሙሸት አማረ ክስ
ሚያዝያ 14/2007 ዓም በisis የታረዱ ወገኖቻችን ላይ የተደረገውን አሰቃቂ ግድያ ለማውገዝ የተጠራውን የተቁውሞ ሠልፍ አመጽ እንዲነሳ አቀነባብረሀል ፣ድንጋይ በመወርወር ሌሎች እንዲወረውሩ አነሳስተሀል፣ ምርጫው ሠላማዊ እንዳይሆን ሁከት ለማስነሳት በመኖሪያ ቤትህ ወጣቶችን በመሠብሰብ አደራጅተሀል ፣ ወዘተ የሚል ነው ግንቦት 05/2007 ዓም ከቤት ወደ ት / ቤት በመጓዝ ላይ እያለ ቦሌ ሚካኤል አካባቢ ታፍኖ የተወሰደው ቦሌ ፓሊስ መምሪያ ከተወሰደ በኋላ ከጥቂት ሰአት በኋላ ሲኤም ሲ አካባቢ ፍርድ ቤት አቅርበው ከተያዘ በኋላ የመያዣ እና ቤት የመበርበሪያ ትዕዛዝ አውጥተው በርብረዋል ።
በማግስቱ በ06/2007 ዓም ሲኤምሲ ፍርድ ቤት 4:30 አካባቢ አቅርበውታል ፍርድ ቤት ያቀረበው ፓሊስ የሱ መርማሪ ያልሆነ ነበር በእለቱ ማሙሸትን የመረመረ መርማሪ ምርመራውን እንዳጠናቀቀና 4 ሠውም እንደመሠከረበት ነግሮት ነበር ፍርድ ቤት ያቀረበው ፓሊስ ግን ምርመራውን እንዳልጨረሰና ምስክሮችም አስመስክሮ እንዳልጨረሰ ገልጾ በተጨማሪም ግብረአበሮቹ ገና እንዳልተያዙ በማስረዳት የ14 ቀን ቀጠሮ ጠይቆበት ነበር ዳኛው እሱ በእራሱ ወንጀል ይጠየቃል ሌሎቹም በስራቸው ይጠየቃሉ የጠየቃችሁት የ14 ቀን ጊዜ ብዙ ነው 4 ቀን በቂ ነው በማለት ወሰነ ።

የማሙሸት አቤቱታ
ማሙሸት መርማሪየ ምርመራ ጨርሰሀል ምስክር ተመስክሮብሀል ብሎኛል ይህ ፓሊስ መርማሪየ አይደለም በተያዝኩበት እለት የተወሰዱብኝ ንብረቶች ሞባይልና ላፕቶፕ አልተመዘገበልኝም በማለት ለችሎት አቅርቦ እንዲመዘገብለት ዳኛው አዟል በቀጠሮው መሠረት ከቀረበ ነገ በ10/2007 ዓም 4:30 ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል