ሰኞ 23 ዲሴምበር 2013

ሰማያዊ ፓርቲ በአስቸኳይ የግንፍሌውን ጽ/ቤት እንዲለቅ ትእዛዝ ተሰጠ


ሰማያዊ ፓርቲ ግንፍሌ አከባቢ የሚገኘውን እና በጽ/ቤትነት የሚጠቀምበትን ቢሮ በዛሬው እለት ከሰኣት በኋላ አቶ ሄኖክ የተባሉ አከራዩ ከ አራት ትግሪኛ ተናጋሪ ግለሰቦች ጋር በመምጣት ቤቱን ለነዚህ ግለሰቦች ስለሸጥኩላቸው እንድትለቁላቸው ሲል አሳስቧል:; ቤቱን ገዛሁት የሚለው ትግሪኛ ተናጋሪ ግለሰብ ቤቱን የገዛሁት ስለሆነ በአስቸኳይ እንድትለቁ ካልሆነ የራሴን እርምጃ እወስዳለሁ ሲል አመራሮቹ ላይ ዝቷል::

ይህ ገዛሁት የሚለው ግለሰብ በማይመለከተው ጉዳይ በመግባት ከዚህ በፊት ልቀቁ ተብላችሁ በተደጋጋሚ እንደተነገራችሁ መረጃው አለኝ በማለት በአመራሮቹ ላይ ቁጣ የተቀላቀለበት ዛቻ በመዛት ሄዷል:; በወቅቱ ይዞት የነበረው ተሽከርካሪ ጥቁር የደህነንት መኪና የሆነች ቶዮታ ኤክስኪዩቲቭ ሲሆን የታርጋ ቁጥሩም ኮድ 2-89176 የሆነ ነው::

ሰማያዊ ፓርቲ ከዚህ ቀደም በመነን አከባቢ ተከራይቶት የነበረውን ጽ/ቤት ገና ሳይገባበት በዝግጅት ላይ እንዳለ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ፖለኢሶች እና ቅጥረኞች ተባብረው በተቀናጀ አፈና ቢሮውን መንጠቃቸው ይታወቃል:: የነጠቁትንም ቢሮ ለካድሬያቸው በመስጠት ፔንሲዎን ከፍቶ እየሰራበት ይገኛል:: 

:EthiopianReview

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ