በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሳውድ አረቢያ የሚገቡ ኢትዮጲያዊያን የሳዑዲን አንድነት ለማፈራረስ እና ፀጥታ ለመንሳት የመጡ ስለሆኑ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድባቸው በማለት የሃገሪቱ ጋዜጦች ግፊት እያደረጉ መሆኑ ተገለፀ፡፡
ባለፈው ማርች 5 እና 6 ብቻ እንኳን በ16 እለታዊ ጋዜጦች 24 ጊዜ ሽፋን የሰጠው በኢትዮጵያዊያን ተወረናል መንግስትና የፀጥታው ክፍል ለምን ዝም ይላል የሚል ጩኻት በየዕለቱ ከ120 እስከ 160 ሺህ ኮፒ ሽፋን እንደነበረው የገለፁት መረጃዎች ሣውዲ ዓረቢያን በቀይ ባህር በኩል ለመምታት የሃበሻን ስደተኞች አስታጥቆ እየላከ ነው የሚል ስጋት እንዳላቸው አስነብበዋል፡፡
የሣዑዲ ዐረቢያ የድንበር ጠባቂ ሃይል ባወጣው መረጃ በአንድ አመት ብቻ 330 ሺ ኢትጵያዊያን በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ሳውዲ የገቡ ሲሆን 5ሺ እነዚህን ግለሰቦች በኮንትሮባንድ የሚያንቀሳቅሱም ተይዘዋል ይላል፡፡
146 ሺ 546 ጥይት 1468 ክላሺንኮቭ ጠመንጃ 646 የውስኪ ጠርሙስ 3 ሚሊየን 964 ሺ 298 ኪ.ግ ሜትር እንዲሁም 15 ሺ ኪ.ግ ሃሺሽ ተገኝቷል የሚለው የድንበር ጠባቂ ሃይል መረጃ በተጨማሪም 2 ሚሊየን 652 ሺ የሳዑዲ ሪያል በካሽ እና 15ሺ 315 ኪ.ግ ሺሻ ተገኝቷል በማለት አስረድተዋል ፡፡
በታዋቂው የሳዑዲ አረቢያ አል መዲና ጋዜጣ ላይም ሀበሾች ሣዑዲ ሲመጡ ዝም ብለው ሳይሆን ዓላማና እቅድ አላቸው ብሎ መፃፍ ያስቆጣቸው የሳዑዲ ዜጎች የመንግስት አካላት በአንድ ጊዜ ተባብረው አንድ ወር ባላሞላ ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያዊያንን ጠራርገው እንዲያስወጡ አስተያየት እየሰጡ ነው፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ