ሰኞ 29 ጁላይ 2013

የአማራ ብሔር ተወላጆች ዳግም ከጉራፈርዳ እየተፈናቀሉ ናቸው ተባለ

በደቡብ ክልል በቤንቺ ማጂ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ እየሩሳሌም ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ውስጥ ነዋሪ የሆኑ የአማራ ብሔር ተወላጆች፣ ዳግም እየተፈናቀሉ መሆኑን ሰማያዊ ፓርቲና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አስታወቁ፡፡
ሁለቱ ፓርቲዎች ሐምሌ 18 ቀን 2005 ዓ.ም. በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት መንግሥት ቀደም ብሎ በጉራፈርዳ ወረዳ፣ በሸፒ ቀበሌና በተለያዩ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ነዋሪ የነበሩት የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች መፈናቀላቸውን ተከትሎ፣ መንግሥት በአፈናቃዮቹ ላይ ዕርምጃ እንደሚወስድ ቢያሳውቅም፣ ዜጐቹ ግን እስካሁን እየተፈናቀሉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ተወካይ አቶ ተስፋዬ ታሪኩ፣ ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርበው ለዓለም ሕዝብ ጭምር በሰጡት ማብራሪያ፣ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ እንዲፈናቀሉ የተደረጉ የአማራና የኦሮሞ (የዘር ማጥራት ወንጀል እንዳይመስል) ተወላጆችን ያፈናቀሉ ኪራይ ሰብሳቢዎች ላይ፣ መንግሥት ዕርምጃ እንደሚወስድና ተፈናቃዮችም ወደ ቀያቸው በአስቸኳይ እንደሚመለሱ የተናገሩ ቢሆንም ተግባራዊ አልሆነም፤›› በማለት አስረድተዋል፡፡

ሰበር ዜና ፤ አንድነት በመቀሌ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ የፀጥታ ኃይል እጥረት አለብን በማለት ተከለከሉ

ሰበር ዜና፤ አቶ ጌታቸው ገ/ስላሴ የከንቲባ ጽ/ቤት ሀላፊ ፣አቶ ወልዳይ የተባሉና የመቀሌ ዞን የፀጥታ ኃላፊ እንዲሁም ከመቀሌ ወጣቶች ማህበር ተወከልኩ ያለ ግለሰብ የአንድነት አመራሮቸን በመጥራት “መንግስት አጠቃላይ ግምገማ ላይ ስለሆነ የፀጥታ ኃይል እጥረት አለብን” በማለት ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ አትችሉም ብለዋቸዋል፡፡ የአንድነት አመራሮችም መልሳቸሁ ህግ የተከተለ አይደለም፤ እኛ ህገመንግስታዊ መብታችንን ጠይቀናል በየትኛውም ሁኔታ ሰልፉን አንሰርዝም፡፡” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
በተያያዘ ዜና በመቀሌ የሚገኙ የአንድነት ፓርቲ አባላት በደህንነት ኃይሎች ዛቻ እየደረሰባቸው መሆኑ የደርሰን ዜና ያመለክታል።
የሰላማዊ ሰልፍ “የአሸባሪዎች ተላላኪ ናችሁ የመቀሌ ህዝብ እንደዚህ አይነት እንቅስቃሴ አይፈልግም” በማለት አንድነት ፓርቲን የሚመለከት በራሪ ወረቀት የመበተንም ሆነ የቅስቀሳ ስራ የሚያከናውን ሰው ላይ ጥብቅ እርምጃ እንወስዳለን ሲሉም ዝተውባቸዋል፡፡ ሆኖም በመቀሌ የሚገኙት የአንድነት አመራሮች ለሰላማዊ ሰልፉ ቅስቀሳ ለመጀመር ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን ለአከባቢው ባለስልጣናት አሳውቀዋል፡፡ ‪#‎milionsofvoicesforfreedom‬ ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎UDJ‬

የዘመኑ መንፈስ (በእውቀቱ ስዩም)



ባገራችን ባሁኑ ጊዜ ብዙ ተከታይ ያለው ሃይማኖት ብሄርተኝነት ይባላል፡፡የብሄርተኝነት ምእመን ከሆንክ የነፍስ አባት ይኖርሀል፣በጭፍን የምትቀበለው ቀኖና ይኖርሀል፣ነገ የምትገባባት የተስፋ ምድር ይኖርሀል፣ከሁሉ በላይ ደግሞ ብርቱ ችግርህን የምትደፈድፍበት የመስዋእት በግ ይኖርሀል፡፡


ሃይማኖቶች ምእመናንን ብቻ ሳይሆን መናፍቃንንም ያፈራሉ፡፡ብሄርተኞች በስሜት የሚነድደውን ምእመን ብቻ ሳይሆን የኔ ቢጤውን መነፍቅም እንደሚያፈሩ አንርሳ፡፡በነገራችን ላይ ሃይማኖትን መካድ ማለት ሃይማኖት የሚያነሳቸውን አብይ ጥያቄዎች መካድ ማለት አይደለም፡፡እንዲሁም፣ ብሄርተኝነትን መካድ ማለት የኢትዮጵያን ብሄር ብሄረሰቦች ህልውና መካድ ማለት አይደለም፡፡በዚህ ጉዳይ ፣መናፍቅ መሆን ማለት፣ የብሄርተኛ ነቢያት ሰለ ጭቆና ስለ ነጻነት ብሎም ስለ ኢትዮጵያዊነት የሚያቀርቡትን አጉል እምነት መጠራጠር ማለት ነው፡፡



ከኢትዮጵያዊነት እንጀምር፡፡


ከዘመናችን የብሔርተኝነት ነቢያት አንዱ ጃዋር መሐመድ በቅርቡ ከእንቁ መጽሔት ጋር ባደረገው ቃለመጠይቅ ላይ ስለኢትዮጵያዊነት የሚከተለውን ይላል፡፡


‹‹…ኢትዮጵያን የመሠረታት የሶሰትዮሽ ጦርነት ግብግብ ነው፡፡በአማራው፣በኦሮሞው፣በትግሬው ግብግብ ውስጥ ወደ መጨረሻ ላይ በአመራር ስር የበላይነቱን የያዘው አማራው ነበር፡፡በዚህ የተነሳ አሁን የምናያት ኢትዮጵያ ማንነቷ በአማራ ባህላዊ ሥርጭት እና በአማራ ፖለቲካ የተገነባች ነች፡፡…የኢትዮጵያ አገራዊ ማንነት የምንለው የአማራ ባህላዊ ማንነት ነው››


ጃዋር የኢትዮጵያን መሠረት የሦስት ብሄረሰቦች የስልጣን ግብግብ አድርጎ ወስኖታል፡፡ በመጀመርያ፣ ሌሎች ብሄረሰቦች በግብግቡ ተሳትፎ እንዳልነበራቸው አድርጎ ማቅረቡ አንድ





በእውቀቱ ሥዩም


ጉድለት ነው፡፡ ግን ዋናው ቁምነገር ይሄ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ የግጭት ውጤት ብቻ እንደሆነች አድርጎ ማቅረቡ ነው ትልቁ ስሕተት፡፡ ሲጀምር፣ የግብግብ ታሪክ መሠረት ይንዳል እንጂ መሠረት አይገነባም፡፡ እንደኔ ግምት፣የኢትዮጵያ መሠረት የሆነው ብሄረሰቦች ለጋራ ሕልውና ሲሉ የሚያደርጉት የመደጋገፍ ታሪክ ነው፡፡


ዛሬ ዛሬ፣ ታሪክ ከላሾች፣የብሄሮችን የ‹‹ግብግብ››ታሪክ ሞቅ አድርገው፣አኳሽተው ሲጽፉ፣የብሄሮች መደጋገፍ ታሪክን ግን ቸል ይሉታል፡፡ አለያም እጅግ በቀዘቀዘ ስሜት፣ በጥቂት መስመሮች ብቻ ጨረፍ አድርገው ያልፉታል፡፡ለነገሩ፣ከፋፋይነትን ብቸኛ ያስተዳደር ፈሊጥ አድርጎ የሚቆጥር ሰው በታሪክ ገጾች ውስጥ መመልከት የሚፈልገው ክፍፍልን ብቻ ነው፡፡ታሪክ ግን ብዙ በጎ የትብብር ገጠመኞችን መዝግቧል፡፡ለምሳሌ ጀግናው አጼ ዮሐንስ አራተኛ በበዛሬይቱ ኤርትራ የግብጽን ወራሪ ጦር ድል የነሡት የትግራይ ጀግኖችን ብቻ አሠልፈው አልነበረም፡፡ በዚህ ጦርነት ከግብጽ ጎን ሆኖ፣የተዋጋው አሜሪካዊው ጋዜጠኛ ዊልያም ዴይ እንደመሠከረው ወልቃይቶች፣ጥልጣል የተባሉ የአፋር ንኡስ ክፍሎች፣የወረኢሉ ኦሮሞዎች ለንጉሰነገስቱ ድጋፍ ለማድረግ ተሸቀዳድመዋል፡፡በራስ ወሌ የሚመሩ የአማራ ወታደሮች ተሳትፈዋል፡፡የጎንደር ቀሳውስት ለጦርነቱ ድጋፍ ለማድረግ አድዋ ገብተዋል፡፡ የጎጃሙ ራስ አዳል የደርሼልሀለሁ አለኝታቸውን አሳይተዋል፡፡ የሸዋው ንጉስ ምኒልክ ሳይቀር በመቶ የሚቆጠሩ በቅሎዎችንና ማበረታቻ ልከዋል፡፡ ዝርዝሩን ማንበብ ለሚፈልግ Muslim Egypt Christian Abyssinia የተባለውን የዚህ ደራሲ ማስታወሻ ገጽ 291-292 ያንብብ፡፡ መጽሐፉን በኢንተርኔት ቤተ-መጻህፍት ውስጥ በብላሽ ማግኘት ይቻላል፡፡


ከተለያየ መአዘን የመጡ እኒህ ኢትዮጵያውን ከዘመቻው የሚያገኙት ድልን ብቻ አልነበረም፡፡ በዘመቻ ወቅት ባህል ይዋዋሳሉ፣ቃላት ይወራረሳሉ፣ ስንቅ ያዋጣሉ፣ ልምድ ይለዋወጣሉ፡፡ በሂደት ተቃራኒ ከሚመስሉ ልማዶች የነጠረ ኢትዮጵያዊ ባህል እንደ አረቄ ይወጣል፡፡ ይህን በመዋጮ የተገኘ ባህል ‹‹የአማራ ባህል ››ብሎ ማጥበብ የጸና ድጋፍ ያለው አይመስለኝም፡፡


ጃዋር‹‹አሁን የምናያት ኢትዮጵያ ማንነቷ በአማራ ባህላዊ ሥርጭትና በአማራ ፖለቲካ የተገነባች ነች›› በማለት ሳይወሰን ‹‹የኢትዮጵያ አገራዊ መለያ ማንነት የምንለው አማራ ብሄራዊ ማንነት ነው›› ሲል ይጨምራል፡፡ ጎበዝ ኧረ በህግ አምላክ!!! የኢትዮጵያ ባህልኮ ካንድ አለት የተጠረበ ሕንጻ አይደለም፡፡ ከብዙ የመዋጮ ጡቦች የተገነባ ነው፡፡ ጃዋር እያንዳንዱን ጡብ ቀርቦ ቢመረምረው እዚህ የደረሰበት እርግጠኝነት ውስጥ የሚደርስ አይመስለኝም፡፡


እስቲ ከደቃቅ ምሳሌ እንጀምር፡፡ ኢትዮጵያን የማስተዋወቅ ስራ ሲሠራ አስቀድሞ የሚመጣው የቡና ስነ-ስራታችን ነው፡፡ አንዲት ጠይም ፣ባለሹርባ ሴት፣ያበሻ ቀሚስ ለብሳ ቡና ስትቀዳ የሚያሳይ ምስል በየቦታው ማየት የተለመደ ነው፡፡ይህ ችክ ያለ ምስል በስነ-ስእል ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ ቢዮንሴና ጆን ኬሪ አገራችንን በጎበኙበት ሰአት የቡና ስነስርአት ተሳታፊ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ ይህ ማለት የውጭ እንግዳ የቡና ስርአታችንን እንደ ኢትዮጵየዊ መለዮ እንዲመዘግብልን ፈልገናል ማለት ነው፡፡ ለዋለልኝ መኮንን እና ለጃዋር መሀመድ ይህ የአማራ ባህል መሆን አለበት፡፡ በመጀመሪያ እይታ ይመስላል፡፡ ጉዱ ዝርዝሩ ላይ ነው፡፡ የሴትዮዋ ሹርባ ከሐማሴን ወይም ከተንቤን ሴቶች ልማድ ጋር ስምም ነው፡፡ ያበሻ ቀሚሱን የሽሮሜዳ ጋሞ የሸመነው ሊሆን ይችላል፡፡ ጀበናው የጂማ ሙስሊም ኦሮሞዎች ያስተዋወቁት ነው፡፡ አቦል ቶና በረካ አረብኛ ወይም የተወላገደ አረብኛ የተገኙ ቃላት ናቸው፡፡ ዛሬ በክርስቶስ ትንሳኤ በአል በሉባንጃ የሚታጀብ ቡና የማያፈላ ክርስትያን ኢትዮጵያዊ ማግኘት ይከብዳል፡፡ ከጥቂት መቶ አመታት በፊት ግን ቡና የእስላም ልማድ ተደርጎ ይቆጠር ነበር፡፡ የቡና ትርኢት የሙስሊም አበው በኢትዮጵያ ባህል ላይ የጨመሩት በጎ መዋጮ እድርገን ልንቆጥረው እንችላለን፡፡ ኢትዮጵያ ጊዜ በተባለው አናጢ ከብዙ ጡቦች የተገነባች ናት የምንለው ለዚህ ነው፡፡


ጃዋር አማራው የራሱን ባህል በኦሮሞው ላይ እንደጫነ ሲያምን ተገላቢጦሹ ያለው አይታየውም፡፡ ኦሮሞ በረጅም ዘመን፣በሠፊ ምድር፣ ሰፍሮ የመኖሩን ያክል በጎረቤቶቹና በወደረኞቹ ላይ የባህል ተጽእኖ አላሳደረም ማለት ብርቱ ባህል የለውም ከማለት አይለይም፡፡ ባገራችን ዋና ዋናዎቹ የባህል ቀራጺዎች ጦርነትና ሐይማኖት ናቸው፡፡ ለምሳሌ ፣ጀግኖችን እና ነገስታትን አባ በዝብዝ አባ ታጠቅ፣ አባ ዳኘው አባ ነጋ ወዘተ እያሉ መሰየም ገናና ኢትዮጵያዊ ባህል መሆኑን ብዙዎቻችን እናውቃለን፡፡ ብዙዎቻችን የማናውቀው ይህንን ባህል ያስተዋወቁት ለግማሽ ምእተአመት ያክል ኢትዮጵያን ያስተዳደሩት የየጁ ኦሮሞዎች መሆናቸውን ነው፡፡ ብላቴን ጌታ ማህተመ ሥላሴ ወልደ መስቀል ቼ በለው በተሰኘው መጽሐፋቸው ይህንን እንዲህ በማለት ያረጋግጣሉ-


‹‹ነገስታቱ በ‹‹አባ›› ወይም የእገሌ ባለቤት በሚል ቅጽል ስም መጥራት የጀመሩት የኦሮሞዎችን ወይም የወረሸሆችን ልምድ በመከተል ነው ከ1838 ዓም ወዲህ እንደሆነ ታሪክ ይነግረናል፡፡ ወትሮ ግን በተለይም 1474-1713 ዓም ባለው ጊዜ ውስጥ ቅብዓ መንግሥቱ በሚደረግላቸው ሰአት ይወጣላችው የነበረው የግርማ ስም ወይም ስመ መንግስት ‹‹ሰገድ›› የሚል ኃይለቃል በመጨመር እንደነበር ቀጥሎ ያለው ያረጋግጣል፡፡ ወናገድ ሰገድ፣ አጽናፍ ሰገድ፣ አድማስ ሰገድ፣ መለክ ሰገድ፣አድያም ሰገድ ሉል ሰገድ››በማለት ይዘረዝራሉ፡፡


ከጥቅሱ ሦስት ፍሬ ነገሮችን መረዳት ይቻላል፡፡


1- ይህ ባህል ባንድ የዘመን ምዕራፍ ላይ ከኦሮሞ ብሄረሰብ የመነጨ የኢትዮጵያ ባህል ነው፡፡


2- ባህሉ ብርቱ ተጽእኖ ከመፍጠሩ የተነሳ አማራና ትግራይ ነገስታት ለረጅም ዘመን ይጠቀሙበት የነበረውን የስያሜ ዘይቤ ሽሯል፡፡


3- አማራው ታሪክ ጸሀፊ ለባህሉ አስተዋዋቂዎች የባለቤትነት እውቅና ሰጥተዋል፡፡


በሃይማኖት ረገድም ተመሳሳይ ነገር ነው የሚገጥመን፡፡ ለምሳሌ አቴቴ የሚለውን ቃል ደስታ ተክለወልድ ሲተረጉሙ ‹‹ዛር፣በሴት ስም የምትጠራ፣ ውቃቤ ፣ አማሮች ከኦሮሞዎች የወረሷት ጨሌ የሚያጠልቁላት አቴቴ ጊንቢ ሐራ አቴቴ ዱላ እያሉ እንቀት የሚቀቅሉላት አምልኮ ባእድ፣ትርጓሜ ጠባቂ ማለት ነው››ይላሉ፡፡


‹‹አምልኮ ባእድ ››የሚለውን አሉታዊ ሐረግ፣የክርስትያን አድልኦ ያለበት ፍርድ አድርገን እንለፈው፡፡ ዋናው ፍሬ ነገር፣ የአሮሞው ባህል በአማራው ባህል ላይ ተጽእኖ ማሳደሩን ማወቃችን ነው፡፡ ይህም አንዱ ብሄረሰብ ሁልጊዜ ጫኝ ፣ ሌላው ብሄረሰብ ሁልጊዜ ተሸካሚ እንደነበረ አድርገው ሊነግሩን የሚፈልጉትን ሰዎች ያስተባብላል፡፡ በሁለቱ ግዙፍ ብሄረሰቦች መካከል የነበረው ግኑኝነት የእኩዮች ልውውጥ ነው፡፡ የባህሎች ውርርስ ነው ማለት እንችላለን፡፡ ነገርን ነገር ያነሳዋልና፣ የማንኩሳ ዘመዶቼ የሚያስደነግጥ ነገር ሲገጥማቸው ‹‹አቲቲን ወሰድከው›› ይላሉ፡፡ ቀልቤን ገፈፍከው ለማለት ነው፡፡ የኦሮሞ ባህላዊ ተጽእኖ በወለጋ ድንበር ላይ ቆሟል ያለው ማነው?


ስለጉዲፈቻ ባህል ብዙ ሰዉ የሚያውቅ ይመስለኛል፡፡ በጦርነት ወቅት ምርኮኞችን ባርያ ማድረግ ወይም መግደል በብዙ ማህበረሰቦች የተለመደ ነው፡፡ በኦሮሞ አበዋዊ ባህል ውስጥ ግን ምርኮኞች በልጅነት ይታቀፋሉ፡፡ ከሌላ ብሄረሰብ ቢመጡም የኦሮሞ ብሄረሰብ የሚያገኘውን መብት ሳይነፈጋቸው ያድጋሉ፡፡ ይህንን ልማድ በአማራው ማህበረሰብ ውስጥም እናገኘዋለን፡፡ ለምሳሌ በጎጃሙ ንጎስ ተክለይማኖትና በወለጋ መሳፍንት መሀል በተደረገው ጦርነት የተማረከው ብላቴና ነገሮ ዋቅጅራን እንደልጅ አሳድገውታል፡፡ ክርስትና አስነስተው ተክለኢየሱስ አሰኝተውታል፡፡ ራሱ በጻፈው ማስታወሻ ‹‹በጠጅና በስጋ አደግሁ›› በማለት የመሳፍንት ልጆች ያገኙት የነበረውን ምቾት ሳይነፈገው ማደጉን ይመሰክራል፡፡ ነገሮ ፣ ከማእረግ ወደ ማእረግ እየወጣ የንጉሱ ጸሐፌ ትዝዛዝ እስከመሆን ደርሷል፡፡ ተመሳሳይ መልኩ በሸዋ ምርኮኛው ቆሴ ዲነግዴ በቤተመንግስት እየተቀማጠለ አድጎ ሐብተጊዎርጊስ በሚል ስመ ክርስትና የኢትዮጵያ የጦር ምኒስትር እስከመሆን ደርሷል፡፡ ሰዎችን በልዩ ቋንቋቸው ምክንያት ባይተዋር ማድረግ ኢትዮጵያዊ ባህል አልነበረም፡፡


እኩዋን ባህላችን አማርኛችን እንኳ የጉራማይሌነታችን ምስክር ነው፡፡ አሁን ኦሮምኛ ያልተነካካ አማርኛ ማግኘት ይቻላል?፡፡ እሰቲ ለናሙና ያክል ‹‹ተወርዋሪ ኮከብ›› ከተባለው የዮሐንስ አድማሱ ምርጥ የአማርኛ ግጥም ውስጥ ጥቂት መስመሮች ልቆንጥር፡፡


1) ተወርዋሪ ኮከብ በራሱ ነበልባል በራሱ ነዲድ ተቃጥሎ የጠፋ

ተወርዋሪ ኮከብ በምናውቀው ሰማይ ነበረ በይፋ


2) ሜዳና ተራራ በመሐል ሸለቆ

ጨፌውና መስኩ በኒህ ተደብቆ


3) ሐቀኛ ጠፍቶበት በዋለበት መልቲ

ጌጥ ነው ድንቁርና የገዳዮች ሎቲ


4) ብልጭ ብሎ ጠፋ

ተወርዋሪ ኮከብ የሐሳብ አንጋፋ


በመረጥኳቸው መስመሮች ውስጥ የሚገኙት ‹‹ይፋ፣ ጨፌ፣ መልቲ፣ ሎቲ፣ አንጋፋ፣›› የተባሉት ቃላት ኦሮሚኛ ናቸው፡፡ ካንድ የአማርኛ ግጥም ይህን ያህል ኦሮሚኛ ከተገኘ በሙሉ መዝገበ ቃላት ውስጥ ምን ያህል ሊገኝ እንደሚችል አስቡት፡፡ ይህን ያክል ነው የተዋሀድነው፡፡


የኢትዮጵያ ባህል የተውጣጣ ባህል እንጂ ጃዋር እንደሚለው የአማራ ባህል ብቻ አለመሆኑን በመጠኑም ቢሆን ያሳየሁ ይመስለኛል፡፡ ጃዋርን እዚህ ላይ ላሰናብትና ለማጠናቀቂያ የምትሆን አንዲት አንቀጽ ልጨምር፡፡


ባህልን ማክበር ጥሩ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በስሜት ሚነድደው የብሄርብሄረሰብ ፖለቲካችን፣ ዜጎች ለባህል ያላቸውን ፍቅር ወደ ጭፍን አምልኮአዊ ፍቅር እያዘቀጠው ነው፡፡


ባባቶቻችንና በእኛ መካከል የባህል ፋይዳ ልዩነት ያለ ይመስለኛል፡፡ አባቶች ባህላቸውን ያገኙት በኑሮ ጣጣ አስገዳጅነት ነው፡፡ ለምሳሌ የኔ አያት ቁምጣ ሱሪ የሚታጠቀው ከሌሎች ብሄረሰቦች ለየት ብሎ ለመታየት አይመሰለኝም፡፡ በቂ አቡጀዲ ስላላገኘ ነው፡፡ ወይም ለስራ እንዲያመቸው ባጭር መታጠቁ ይሆናል፡፡ እኔ ግን የብሄረሰቦች ቀን ሲከበር ቁምጣ ለብሼ ራሴን በማስጎብኘት እንድኮራ ይጠበቅብኛል፡፡ ጉድ እኮ ነው!!! ጋቢ በጥንት ጊዜ የሙቀት ምንጭ ነበር፡፡ ዘንድሮ የኩራት ምንጭ ሊሆን ይቃጣዋል፡፡


የዛሬዎቹ ባህል አምላኪዎች ባህል ሲያስቡ ለውጥን ይረሳሉ፡፡ ባንድ ወቅት የሚያኮራው ያንድ ብሄረሰብ ባህል በሌላው ወቅት ይናቃል፡፡ ባንድ ወቅት የሚያስሸልመው በሌላ ጊዜ ያስቀጣል፡፡ ከጥቂት መቶ አመት በፊት ዝሆን መግደል በማህበረሰቡ ዘንድ ትልቅ ከበሬታ የሚያጎናጽፍ ተግባር ነበር፡፡ ዝሆን የገደለ ልዩ አምባር ክንዱ ላይ ያጠልቃል፡፡ እስኪ ዛሬ ያባቶቼን ባህል ለማክበር ነው ብለህ ፓርክ ውስጥ አርፎ የተኛውን ዝሆን ግደል፡፡ በአምባር ምትክ ካቴና ይጠልቅልሀል፡፡


የብሄር ብሄረሰቦች አልባሳት የተባለውን የተደጋገመ ግን ያልታሰበበት ቃል ከዚህ አንጻር ቃኙት፡፡ ሲጀምር ፣ዛፍ እንኳ ቅርፊቱን በሚቀያይርበት ዓለም፣ብሄር ብሄረሰቦች በየጊዜው አልባሳታቸውን አይቀያይሩም ወይ?፡፡ የብሄረሰቡ አልባስ ሲባል በየትኛው ዘመን የሚለበሰው ነው? የእንዳለጌታ ከበደ እናት ሲነግሩን፣ ዛሬ በጉራጌ ዘፈን ላይ በቲቪ የምናየው የሴቶች ሻማ ቀሚስ በደርግ ዘመን የተጀመረ ነው፡፡ ከዚያ በፊት የነበረው ሸማ ነው፡፡ ከሸማው በፊት ደግሞ የቆዳ ቀሚስ ይለበስ ነበር፡፡


ሌላው፣ አንድ ማህበረሰብ አልባሳት በየማእረጉ ልዩ ልዩ ልብሶች ይኖሩታል፡፡ ወታደሩ ያባ ገዳውን ልብስ የሚለብስ አይመስለኝም፡፡ ባሮች ከጌቶች ልብስ ጋር የሚመሳሰል ልብስ እንዲለብሱ አይፈቀድላቸውም ነበር፡፡ በፊውዳል ማህበረሰብ ከላይ አስከታች መልበስ መከናነብ የጨዋነት ምልክት ነው፡፡ ይህንን በሸዋና በትግራይ ብቻ ሳይሆን በቅድመ ምኒልክ ከፋ ውስጥ እናገኘዋለን፡፡ ባንጻሩ፣ባሮች በከፊል ተራቁተው መታየት አለባቸው፡፡ ባጠቃላይ በኢትዮጵያ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ አለባበስ በበሄረሰብ ላይ ሳይሆን በመደብ ላይ የተመሰረተ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ስለዚህ የብሄር አልባሳት የሚባለው እንደ ማንኛውም ሾላ በድፍን ሐሳብ በጥርጣሬ መታየት አለበት፡፡


ትውልዱ የባህል ፈጣሪ መሆን ሲገባው፣የባህል ሙዚየም ሆኖ ተተክሏል፡፡አፈወርቅ ገብረኢየሱስ ባንድ ወቅት እንዳለው ‹‹ካባቶቹ የማይበልጥ ትውልድ፣ እንዳልተፈጠረ ይቆጠራል››


ማሳረጊያኢትዮጵያን አንድ አድርጎ ያቆያት የነገስታቱ ጉልበት ብቻ ነው ብለው የሚያስቡ ሰዎች ኢትዮጵያ የተሸመነችበትን ውስብስብ ክር ማየት ያልታደሉ ናቸው፡፡ዛሬ ኢትዮጵያን በታትነን ክልላችንን እናድናለን ብለው ባደባባይ ሳያፍሩ የሚናገሩ ሰዎችን የምናይበት ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡በርግጥ ኢትዮጵያ ማእበል ከበረታባት እንደ ታይታኒክ ትሰጥም ይሆናል፡፡ግን መርከቢቱ ስትሰጥም የመርከቢቱ ሳሎን ብቻውን አይንሳፈፍም፡፡የመርከቢቱ ጓዳ ብቻውን አይተርፍም፡፡ኢትዮጵያ ስትከስም ብሄሮች ተነጥለው ይለመልማሉ ማለት ተፈጥሮ አመሏን እንደ ግትቻ የትም ጥላለች ማለት ነው፡፡

ዓርብ 26 ጁላይ 2013

ስለተፈናቀሉ ሰዎች ሰማያዊ ፓረቲና መኢአድ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ አስገቡ

ከቤንሻንጉል-ጉምዝና ከደቡብ ክልሎች ለተፈናቀሉ አርሶ አደሮች ጉዳይ መፍትሔ እንዲሰጡ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ የፃፉት ደብዳቤ ምላሽ አለማግኘቱን ሁለት ተቃዋሚ ፓርቲዎች አስታወቁ፡፡
የአርሶ አደሮቹ ጉዳይ መፍትሔ የሚያገኝ ከሆነ መንግሥትን ለመክሰስ በጀመሩት ሂደት እንደሚገፉበትም ተቃዋሚዎቹ መኢአድ እና ሰማያዊ ፓርቲ ጠቁመዋል፡፡
ሁለቱ ፓርቲዎች ለዚሁ ዓላማ በዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም የሚመራ የጠበቆች ቡድን ማዋቀራቸው ይታወሣል፡፡
ለተጨማሪና ዝርዝር የተያያዘውን የእስክንድር ፍሬው ዘገባ አለው ያዳምጡ፡፡

http://ecadforum.com/Amharic/archives/9098/ 

House of Commons - Dr Wondimu Mekonnen

የህወሀት ስትራቴጂ በአማራውን ህዝብ ቁጥር ቅነሳ

የተከበሩ የምክር ቤት የተቃዋሚ ተወካይ አቶ ግርማ ሠይፉ ምክር ቤቱ በቀኝ ክንፍ ሲያጠቃ ዋለ ሲሉ ያስነበቡን። ፁሁፍ እኔም በዚህ ጉዳይ ላይ አንድ ነገር እንዳክልበት አስገደደኝ። ለፌዴሬሽን ጉዳዬች ሚኒስቴር የቀረበ ጥያቄ በዋዛ የሚታይ አልነበረም ጥያቄዉም በብዙ የምክር ቤቱ አባል ለመጥቀስ ፈራ ተባ ሲሉ አንደኛዉ የምክር ቤቱ አባል ግን ደፍረዉ የአማራ ክልል ህዝብ በተለየ ሁኔታ በኤድስ ሞቷል መባሉ ትክክል ስላልሆነ ይቅርታ መጠየቅ ሲከፉም በሀላፊነት መጠየቅ አስፈላጊ መሆኑ ሞግተዋል ብለዉ አቶ ግርማ ሠይፉ በፁሁፋቸዉ አስነቡበዉናል።

ይህ በእዉነቱ የምክር ቤቱ ተወካይ በአጋጣሚ አምልጧቸዉ ወይም ደግሞ እዉነታዉን ስለሚያውቁት እንጂ ይህ ለአማራዉ ህዝብ ህወሀት ኢትዬዽያን ከተቆጣጠረ ጊዜ ጀምሮ በፕሮግራም የአማራ እና የኦሮሞን ህዝብ ቁጥር ለመቀነስ በረጅም እቅዳቸዉ ላይ የተቀመጠ ነዉ። ይህንን ልል የቻልኩት እንደ ኢትዬዽያ ዘመን አቆጣጠር በ2002 ዓ፤ም በአለም ጤና ድርጅት እገዛነት በጤና ተቋማት ላይ የሚደረገውን ምዝገባ ወይም ግምገማ በአማራው ክልል ላይ ለመስራት እድሉን አግኝቼ በምሰራበት ወቅት ያየሁትን እይታዬ ለማጋራት ያህል ነው። ይህም ምዝገባ ወይም ግምገማ የሚያካትተው በኢትዬዽያ ዉስጥ ያሉት የጤና ተቋማት ምን ያህል ባለሙያ፥ ታካሚ፥ የወሊድ አገልግሎት፥ የቲቢ እና ኤድስ አገልግሎት፥ የላብራቶሪ አገልግሎት ፥ የህፃናት ህክምና እና ክትትል እንዲሁም የህክምና መሳሪያዎችን እና መድሀኒቶች ከመቼ ጀምሮ እጥረት እንደነበረ እና በተለይ የኤድስ በሽታ እድሜ ማራዘሚያው መድሀኒት እና የቅድመ ምርመራ መሣሪያ ቆጠራ ወይም ምዝገባ ይደረጋል። ነገር ግን የህወሀት መንግስት የተሰበሰበውን መረጃ እንደ ኢኮኖሚው ሁሉ በመቀየር ለፖለቲካ ፍጆታ እና ገንዘብ ማግኛ ዘዴ ሆኖታል። እውነታው ግን ህብረተሰብ በተጏዳኝ በሽታዎች፥ በህክምና መሳሪያዎችና መድሀኒቶች እጥረት እንደሚሰቃይ እና እንደሚማት የአደባባይ ሚስጥር ነው።

የወያኔ መንግስት የአማራውን ህዝብ ቁጥር ለመቀነስ በኤድስና በተጏዳኝ በሽታዎች ዙሪያ ፩ኛ የህብረተሰቡ ጤና አጠባበቅ በተመለከተ ምንም አይነት ግንዛቤ እንዳይኖረዉ በማድረግ ፪ኛ በኤድስ በሽታ ህብረተሰቡ መያዝ አለመያዙ የመመርመሪያ መሳሪያ በክልሉ ሆነ ተብሎ እጥረት እንዲኖርና ምንም አይነት የቅድመ ምርመራ ግንዛቤ እንዳይኖራቸዉ መደረጉ ፫ኛ በኤድስ በሽታ የተጠቁ ሰዎች የእድሜ ማራዘሚያ በአግባቡ እንደማይሰጣቸዉና የመድሀኒቱም ተጠቃሚዎች እንደማይቆጧጠሯቸዉ ከጤና ጣቢያም ሆነ ከሆስፒታል ምንም አይነት ክትትል እንደማይደረግላቸዉ እና ከዚህም በተጨማሪ ይህ የእድሜ ማራዘሚያ መድሀኒትና ሌሎችም ተጏዳኝ በሽታ መድሀኒቶች ከአማራዉ ህዝብ ቁጥር አንጻር ተመጣጣኝ ስርጭት እንደሌለው ፬ኛ ደግሞ የመድሀኒቶቹ የመገልገያው ጊዜ (expired date) በጣም የቀረበ በተለይ ለነዚህ ለሁለቱ ክልሎች እንደሚላክ በጤና ጥበቃ ስር የሚገኘዉ የመድሀኒት ፈንድ ኤጀንሲ መስሪያ ቤት በምሰራበት ወቅት ይህ ከላይ የዘረዘርኳቸውን ለማስተዋል ችያለው።

ማክሰኞ 23 ጁላይ 2013

ኢህአዴግ አንድነት ፓርቲ የጠራው ሰልፍ እንዳይሳካ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው


ሐምሌ ፲፭(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አንድነት የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት በማለት የጠራው ህዝባዊ ንቅናቄ ገዢውን ፓርቲ በማስደንገጡን አዲስ ከጀመራቸው ግምገማዎችና የህብዕ እንቅስቃሴዎች ለመረዳት ተችሎአል።
በደሴ እና በጎንደር የተካሄደውን ስላማዊ ሰልፍ ተከትሎ የፖሊስ እና የቀበሌ የፖለቲካ አመራሮች በጠንካራ ግምገማ ተይዘው መሰንበታቸውን ከኢህአዴግ ምንጮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ስማችን እና ድምጻችን አይተላለፍ ያሉት ምንጮች እንደገለጹት በ1ለ5 አደራጃጀት መሰረት ህዝቡ በሰልፉ ላይ እንዳይገኝ መመሪያ ለሚመለከታቸው ወገኖች ተላልፏል። የፖሊስ አባላት ሰልፎችን በመበተን የድርሻቸውን እንዲወጡ የተሰጣቸው መመሪያ በመካከላቸው ክፍፍል እንዲፈጠር እንዳደረገ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ፖሊሶቹ በስራ አጥነት እና በኑሮ ውድነት የተማረረውን ህዝብ ለማቆም አንችልም በማለት ሲናገሩ ተስምተዋል።
ነሀሴ 26 በደብረማርቆስ ከተማ የሚካሄደውን ህዝባዊ ስብሰባ ለመገደብ እና በ1 ለ 5 አደረጃጀት የተቀየሰውን የማገቻ ስትራቴጂ ተግባራዊ ለማድረግ የብአዴን ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን እና ምክትላቸው አቶ ገዱ አንደርጋቸው የስልጠናና የማሳሰቢያ ስራዎችን ለመስራት ወደ ደብረማርቆስ እየተመላለሱ ነው።

ሐምሌ 28 በባህርዳር የተጠራውን ህዝባዊ ሰልፍ ለማስቆም በየደረጃው ያሉ አመራሮች ሁሉንም መንገዶች እንዲከተሉ፣ የብአዴን ድርጅት ጉዳይ ጽ/ቤት ሃላፊዎች እና ሁሉም የመንግስት አመራሮች በንቃት እንዲሳተፉ ለማድረግ ተወስኖ እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡ በባህር ዳር፣ ሐዋሳ፣ መቀሌና የአዳማ ተመሳሳይ ስራዎችን እንዲያከናውኑ በሚኒስትር ደረጃ የተወከሉ አመራሮች ወደ ስፍራው አምርተዋል፡፡

ከኢህአዴግ ዜና ሳንወጣ ለመለስ ፋውንዴሺን እርዳታ ከህዝቡ የገንዘብ ልመና ጥያቄ መቅረቡን ለማወቅ ተችሎአል።
የመለስ ፋውንዴሺን አመራሮች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነሐሴ 14 በደመቀ ሁኔታ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሙት አመት በሻማ ማብራት ስነ ስርዓት እንዲከበር መታቀዱን ተናግራዋል፡፡

በእለቱም ለፋውንዴሺኑ የተቋም ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ ይጣላል ተብሎአል፡፡

በቀጣይም ለፋውንዴሺኑ እርዳታ የሚሆን ገንዘብ ከዝቅተኛው የህብረተሰብ ክፍል ለመሰብሰብ ታስቦ የባንክ አካውንት ለባለሃብቶች ፤

ለድሃው ደግም በሞባይል ቁጥር በቴሌ በሚቆረጥ ከ2 ብር ጀምሮ 100 ብር የሚደርስ የገንዘብ መክፈያ መዘጋጀቱን ወ/ሮ አዜብ መስፍን ገልጸዋል።

በቂሊንጦ የሚገኙ እስረኞች በሞት አፋፍ ላይ እንገኛለን አሉ

ሐምሌ ፲፭(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእነ አቶ ተሻለ በካሻ መዝገብ ተከሰው ከሁለት አመታት በላይ በእስር ቤት የቆዩት እስረኞች ሰሞኑን ከፍተኛ ድብደባ ከተፈጸመባቸው በሁዋላ ለተከታታይ ቀናት ምግብ ባለመመገባቸው ህይወታቸው አደጋ ላይ መውደቁን በመግለጽ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲደርስላቸው አቤት ብለዋል።
እስረኞቹ በጻፉት ደብዳቤ ላይ  ከውጭ የመጡ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በፌሮ ክፉኛ እንደደበደቡዋቸውና ህክምና በማጣታቸው ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው መሆኑን ገልጸዋል። ፍርድ ቤት በቀጠሮአቸው ቀን እንዳይቀረቡ መከልከላቸውን ለመቃወም ለበላይ አካላት ደብዳቤ በመጻፋቸው ምክንያት ድብደባ እንደተፈጸመባቸው የገለጹት እስረኞቹ ፣ ጉዳዩን ለቂሊንጦ ዋና አስተዳዳሪ ኦፊሰር አምባየ ስናመለክት ” እስከ መግደል ድረስ እርምጃ ለመውሰድ መብት አለን፣ አርፋችሁ ካልተቀመጣችሁ በጥይት እንቆላችሁዋለን፣ የምግብ ማቆም አድማ እናደርጋለን ብትሉም ለእኛ ደንታችን አይደለም”  በማለት እንደመለሱላቸውና ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እየተዛተባቸው መሆኑን ጠቅሰዋል። ለ4 ቀናት ምግብ ማቆማችንን ተከትሎ ማንም ስላልጠየቀን በሞት አፋፍ ላይ እንገኛለን ያሉት እስረኞቹ የኢትዮጵያ ህዝብ እና የሚመለከታቸው አካላት አስቸኳይ እገዛ እንዲያደርግላቸውም እስረኞቹ  ተማጽነዋል።
ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞባቸው ህክምና ከተከለከሉት መካከል ቀጀላ ገላና ገቢሳ፣ በላይ ኮርሜ ባይሳ፣ መንግስቱ ግርማ አየሳ፣ ተፈራ ቀበኔ ገመቹ፣ ሙላት ሽመልስ እጀታ፣ ኢብሳ አህመድ ሙሀመድ እና ሸምሰዲን የተባሉት ሲገኙበት ፣ ድብደባ ከተፈጸመባቸው መካከል ደግሞ ሌሜሳ ዲሴሳ፣ አለሙ ተሾመ ቦኬ፣ ዘርፉ መልካ አባይ፣ ቀበታ ገቢሳ ነባራ፣ ቀበና ነጋሳ ነገራ፣ መልካሙ መገርሳ፣ አዳሙ ሽፈራው፣ ቡልቻ ሱሪሳ ጌታቸው አብራ ቶሎሳ፣ ስለሺ ሶሬሳ፣ የፓርላማ አባል የነበረው ጉቱ ወልዴሳ፣ አለማየሁ ቶሎራ፣ በርሲሳ ሊሙ፣ ብርሀኑ እምሩ፣ ኡርቄና አጀማ፣ አህመድ አብደላ ጎዳ እና ለማ በዳዳ ይገኙበታል።
በኦነግ ስም በሽብረተኝነት ወንጀል የተከሰሱት እስረኞች ያቀረቡትን ተማጽኖ ተከትሎ በኢትዮጵያ የሚገኘውን ቀይ መስቀል ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግ የድርጅቱ ስልክ አይነሳም። የታራሚዎች ፍትህ አስተዳዳር ዳይሬክተር ለሆኑት አቶ ብርሀኔ ሀይለስላሴ  ስልክ ብንደውልም፣ ስልካቸው ቢጠራም አይነሳም።
ኢሳት በእስረኞች ላይ የደረሰውን ድብደባ ተከትሎ አካባቢው በደም በመበከሉ እንዲታጠብ መደረጉን መዘገቡ ይታወቃል። የቂልንጦ እስር ቤት ዋና ሃላፊ በቅጽል ስሙ ሻቢያ ከዚህ ቀደም ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በእሰረኞች ላይ መፈጸሙን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢህአዴግ ላይ ሲቀርቡበት ከነበሩት ሪፖርቶች በተለየ ጥቅሞቹ ላይ ያነጣጠሩ አስደንጋጭ መረጃዎች እንደወጡበት ተሰማ።

ዓለም ባንክ ርምጃ ለመውሰድ ጫፍ ደርሷል ኢህአዴግ ላይ ቀደም ሲል ሲቀርቡበት ከነበሩት ሪፖርቶች በተለየ ጥቅሞቹ ላይ ያነጣጠሩ አስደንጋጭ መረጃዎች እንደወጡበት ተሰማ። መረጃው የኢህአዴግን አንገት የማነቅ ያህል እንደሚቆጠርና ለተግባራዊነቱ የተንቀሳቀሱትን አካላት “የአስተዋይነት” ትግል ውጤት እንደሆነ ተጠቁሟል…
ኢህአዴግ በህዝብ ስም በብድርና በርዳታ የሚያገኘውን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ለፖለቲካ ስራ እንደሚያውለውና ለአፈና ተቋማቱ ማጠናከሪያ እንደሚጠቀምበት የተከሰሰበት ሪፖርት መጠናቀቁን የገለጹት የጎልጉል ታማኝ ምንጮች ናቸው። ምንጮቹ እንዳሉት ሪፖርቱ የቀረበለት የዓለም ባንክ በቅርቡ መረጃውን ተቀብሎ ርምጃ ይወስዳል ተብሎ ይጠበቃል። ኢህአዴግ ርምጃው ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ለማክሸፍ የተለመደውን ሩጫ መጀመሩ ተሰምቷል።
በኢህአዴግ ላይ የቀረበው ሪፖርት የመፍትሄ ሃሳብም ያካተተ እንደሆነ የተናገሩት የጎልጉል ምንጮች፣ የዓለም ባንክ የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ሪፖርቱን ሙሉ በሙሉ እንደሚቀበለውና ይፋ እንደሚያደርገው አስረድተዋል። የምርመራ ዘገባውን ስላጠናውና ስላቀረበው የኢንስፔክሽን ተቋምና የስራ ተሞክሮ በቂ ግንዛቤ ያላቸው እነዚህ ክፍሎች እንደሚሉት የዓለም ባንክ ቦርድ ይህ ተቋም ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ያቀረባቸውን ሪፖርቶች ላለመቀበል አንገራግሮ እንደማያውቅ ያስረዳሉ።
በሚመሩት ህዝብ ላይ ግፍ የሚፈጽሙ መንግስታትና በልማት ስም የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚያካሂዱ አገራት የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በስፍራው በመገኘትና መረጃዎችን ከመሠረታቸው ዘልቆ በመመርመር  አጥንቶ ተጠያቂ የሚያደርገው ኢንክሉሲቭ ዴቨሎፕመንት ኢንተርናሽናል Inclusive Development International (IDI) የሚባለው ተቋም ከኢትዮጵያውያኑ ሰለባዎች ውክልና በመውሰድ ስራውን ለማከናወን እንቅስቃሴ መጀመሩን ጎልጉል ምንጮቹን በመጥቀስ መዘገቡ ይታወሳል። ተቋሙም በውክልናው መሰረት ለኢንስፔክሽን ፓናል በዝርዝር የሰለባዎቹን በደል በማተት አሳውቆ ነበር።
ኢህአዴግ በርዳታና በብድር የሚያገኘውን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ለፖለቲካ ስራ፣ ለአፈና፣ ለወታደራዊ አቅም ግንባታ፣ ለተለያዩ የአፈና ተቋም ሰራተኞቹ ደሞዝና ህዝብን በመርገጥ ስርዓቱን ለሚንከባከቡ የተለያዩ ጥቅማጥቅሞችን በመክፈል ገንዘቡን ለመጠቀም ከታለመለት ዓላማ ውጪ እንደሚያውለው በበርካታ መረጃዎች ያረጋገጠው የኢንስፔክሽን ቡድን ለዚሁ ስራው ኬንያ፣ ደቡብ ሱዳንና ኢትዮጵያ በቅርቡ አቅንቶ ነበር።
ምርመራው ያስደነገጠው ኢህአዴግ በተለያየ መልኩ ሰለባዎች በደላቸውን እንዳይናገሩ፣ በጥቅም የተደለሉ ሰዎችን በየቦታዎቹ በማዘጋጀትና በማስፈራራት አፈና ማካሄዱን የጎልጉል የመረጃ ምንጮች በወቅቱ ቢያስታውቁም ጎልጉል መረጃውን ለስራው መሳካት ሲባል ይፋ ከማድረግ ተቆጥቧል።
ከቀናት በፊት ሪፖርቱን አጠናቆ ለዓለም ባንክ ቦርድ ያቀረበው የኢንስፔክሽን ቡድን (ፓናል) በማያወላዳ መንገድ ተጽኖ ፈጣሪ ተቋም መሆኑንን ያስረዱት ለስራውና ለተቋሙ ቅርበት ያላቸው ክፍሎች፣ ሪፖርቱን ከቦርዱ አባላት አንዱ እንኳ አልቀበልም ቢሉ ምን ሊከሰት እንደሚችልም አብራርተዋል።
“አንድ ወይም ከአንድ በላይ የቦርድ አባላት የፓናሉን ሪፖርት ውይይት እንዲደረግበት እስካልጠየቁ ድረስ ፓናሉ ባቀረበው መሠረት እንዳለ ይጸድቃል። ከጸደቀም በኋላ ሪፖርቱ በዓለም ባንክ ስም ይፋ ይሆናል። ሪፖርቱ ታምኖበት ይፋ ከሆነ በሪፖርቱ የቀረቡት የመፍትሄ ጭብጦች ተግባራዊ ከማድረግ ውጪ ሌላ አማራጭ የለም። እስካሁን ባለው አሰራር የፓናሉ ሪፖርት ተቃውሞ አጋጥሞት አያውቅም” ሲሉ መልስ ሰጥተዋል።
“ይህ ታላቅ ውጤት የተገኘው በእቅድና አስተውሎ በመራመድ ነው። ወደፊትም በቀጣይ የሚከናወኑ ተግባራቶች አሉ። የአገዛዙን ትምክህትና ማን አለብኝነት የሚያረግቡ፣ ብሎም የሚያተኑ ስራዎች ለመስራት ለተጀመረው ስራ ይህ ውጤት ከፍተኛ መነቃቃት ይሆናል” ሲሉ ጉዳዩን በቅርበት በመከታተል እዚህ ያበቁት ክፍሎች አስረድተዋል።
ጉዳዩ እንዴት እዚህ ደረጃ ደረሰ? ለሚሉት ጥያቄዎችና ኢህአዴግ ስለተከሰሰባቸው ዝርዝር ጉዳዮች  October 12, 2012 አስቀድሞ የዘገበውን  ማጣቀስ አግባብ ሆኖ በመገኘቱ ከዚህ በታች እንዳለ አቅርበነዋል።

ኢህአዴግ በ600 ሚሊዮን ዶላር አጣብቂኝ ውስጥ ገባ!!  ብያኔው ከጸና ኪሣራው በቢሊዮን ዶላር ሊደርስም ይችላል!

ኢህአዴግ ከዓለም ባንክ ያገኘውን 600 ሚሊዮን ዶላርና በተመሳሳይ ፕሮጀክት ወደፊት ሊያገኝ የሚችለውን ከፍተኛ ገንዘብ በተመለከተ አደጋ ውስጥ መውደቁ ተሰማ። ኢንስፔክሽን ፓናል (Inspection Panel – IP) የተሰኘ ተቋም ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያመለክተው ኢህአዴግ የቀረበበት ውንጀላ ከተረጋገጠ የሚያጣው ገንዘብ በቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ ታውቋል። ይፋ የሆነውን መረጃ አስመልክቶ ከኢህአዴግ ወገን እስካሁን በይፋ የተሰጠ ምላሽ የለም።
ግፍ የሚፈጽሙ መንግስታትን፣ በልማት ስም የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚፈጽሙ ወንጀሎችን መረጃዎችን በስፍራው በመገኘትና ከመሠረቱ ዘልቆ በመግባት አደራጅቶ ተጠያቂ የሚያደርገው ኢንክሉሲቭ ዴቨሎፕመንት ኢንተርናሽናል Inclusive Development International (IDI) ከሰለባዎቹ ውክልና ተሰጥቶታል። ተቋሙም በውክልናው መሰረት ለኢንስፔክሽን ፓናል በዝርዝር የሰለባዎቹን በደል በማተት አሳውቋል።
የኢህአዴግ መከላከያ ሠራዊት የሚያደርሰውን እስራት፣ ግርፋት፣ አስገድዶ መድፈር፣ ከመኖሪያ ቦታ ማፈናቀል፣ የግዳጅ ሰፈራ ወዘተ በማምለጥ ወደ ኬንያ የተሰደዱ የጋምቤላ ነዋሪዎች ይህ ሁሉ ግፍ የሚፈጽምባቸው የኢትዮጵያ መንግሥት በልማት ስም ከዓለም ባንክ በሚያገኘው የዕርዳታ ገንዘብ በመሆኑ ለባንኩ በላኩት የአቤቱታ ደብዳቤ አመልክተዋል።
አቤቱታውን መሠረት በማድረግ የሚደረገው ምርመራ ውጤት ይፋ ሲሆን፣ በሌሎች አገሮች እንደተደረገው በዕርዳታ ስም የሚገኝን ገንዘብ ኢህአዴግ ለፖለቲካ ተግባር መጠቀሙ ሲረጋገጥ፣ በመስከረም ወር መጀመሪያ አካባቢ ከዓለም ባንክ ተፈቅዶ የነበረው 600ሚሊዮን ዶላር ሊከለከል ይችላል፡፡
የዛሬ ዘጠኝ ዓመት አካባቢ በሟቹ ጠ/ሚ/ርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ መለስ ዜናዊ ቀጥተኛ ትዕዛዝ በጋምቤላ ክልል በተለይ የተማሩ ወንዶች ላይ በማተኮር 424 ንጹሐን የአኙዋክ ተወላጆች በተገደሉበት ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩት ወደ ጎረቤት አገር ኬንያ መሰደዳቸው ይታወሳል፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ክልሉ ሰላም የለም፡፡ በየጊዜውም የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሲካሄዱበት ቆይቷል፡፡ በተለይም ለም የሆነውን እጅግ ሰፋፊ መሬት ለውጪ ባለሃብቶች በሳንቲም በመሸጥ ላይ የሚገኘው የኢህአዴግ አገዛዝ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቀድሞው የደርግ ዘመን ሲካሄድ ከነበረው ባለፈ መልኩ እጅግ በሚያሰቅቅ ሁኔታ በመንደር ምስረታና አስገድዶ የማስፈር ፖሊሲ ከመኖሪያ ቀዬ የማፈናቀል ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን የኦክላንድ ተቋም፣ ሂውማን ራይትስ ዎች፣ … የመሳሰሉ ድርጅቶች ያወጧቸው ዘገባዎች ይጠቁማሉ፡፡
ከ1998ዓም ጀምሮ የመሠረታዊ አገልግሎት ጥበቃ ፕሮግራም (Protection of Basic Services “PBS Program”) በሚል በአራት ተከታታይና ሁለት ተጨማሪ የገንዘብ ድጎማ የሚደረግባቸውን ፕሮግራሞች የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ ይህ መሠረታዊ የሆኑ አገልግሎቶችን ለማሟላት ተወጥኖ የሚካሄድ ፕሮጀክት በትምህርት፣ በጤና፣ በእርሻ፣ በንጹህ ውሃ አቅርቦት፣ በገጠር መንገድ ሥራ፣ ወዘተ መስኮች ላይ እንዲውል (PBS I, PBS I-AF (Additional Financing), PBS II, PBS 11-AF, PBS-Social Accountability Program and PBS III) በማለት በተለያዩ ደረጃዎች ለተከፋፈለው ኦፐሬሽን ማስፈጸሚያ የሚውለው ገንዘብ ከ13ቢሊዮን ዶላር የሚበልጥ ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ ከፍተኛው የዓለም ባንክ ድርሻ 2ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የተቀረው በሌሎች ለጋሽ መንግሥታት እና ድርጅቶች የሚሸፈን ነው፡፡ PBS III የተሰኘውን በሦስት ንዑሳን ፕሮግራሞች የተከፋፈለውን ፕሮጀክት ለማስፈጸም በአጠቃላይ የሚፈጀው 6.3ቢሊዮን ዶላር በላይ ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ የባንኩ ድርሻ የሆነውን 600ሚሊዮን ዶላር ቦርዱ መስከረም 5ቀን 2005ዓም አጽድቋል፡፡
በአስገድዶ ማስፈር፣ መንደር ምስረታና ሌሎች በርካታ የሰብዓዊ መብቶቻቸው የተጣሱባቸው በኬንያ የሚገኙ ሦስት የአኙዋክ ስደተኞች ተወካይ ድርጅቶች በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ ሌሎች የሰብዓዊ ድርጅቶች ጋር በመሆን ባንኩ ሊሰጥ የወሰነውን ገንዘብ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም ከመዋል ይልቅ ለኢህአዴግ የፖለቲካ ዓላማ ማስፈጸሚያ እየዋለ መሆኑን በመጥቀስ ለባንኩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጂም ዮንግ ኪም መስከረም 6፤ 2005ዓም ደብዳቤ ልከዋል፡፡ በጥያቄያቸውም መሠረት በዓለም ባንክ በኩል ወደ ኢትዮጵያ የሚፈሰው ገንዘብ “በልማት ስም የኢትዮጵያ መንግሥት በጋምቤላ ክልል ለሚያካሂደው የመንደር ምስረታ እየዋለ ነው” በማለት ይከሳል፡፡ ሲቀጥልም የአኙዋክ ሕዝብ ለዘመናት ከኖረበት መንደር በማፈናቀል “የተሻለ አገልግሎት ይሰጣችኋል” በማለት በግድ የማስፈር ተግባር እየተፈጸመ ሲሆን “የተባለው አገልግሎትም ሆነ ለእርሻ የሚሆን በቂ ቦታ እንዲሁም ለከብቶች የሚበቃ የግጦሽና የውሃ ቦታ የላቸውም” በማለት ሰፈራውን የተቃወሙ ሁሉ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብት ረገጣ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ጠቁሟል፡፡ ይህንን ግፍ የሚፈጽሙት ደግሞ የዓለም ባንክ ለመሠረታዊ አገልግሎት ጥበቃ ፕሮግራም (Protection of Basic Services “PBS Program”) ስም ለልማት እንዲውል ከሚሰጠው የዕርዳታ ገንዘብ በመንግሥት ተቀጥረው ደመወዝ የሚከፈላቸው ሠራተኞች መሆናቸውን ገልጾዋል፡፡ ይህንን ጉዳይ ከዓለም ባንክ ጋር እንዲነጋገሩላቸው Inclusive Development International (IDI) የተባለውን ድርጅት መወከላቸውን አስታውቀዋል፡፡ (የደብዳቤው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል)
ተመሳሳይ ጉዳዮችን በዓለምአቀፍ ደረጃ በመከታተልና በማስፈጸም የታወቀው IDI በመስከረም ወር አጋማሽ ላይ ጉዳዩ በቀጥታ ለሚመለከተው የመልሶ ማቋቋምና ልማት ዓለምአቀፍ ባንክና (International Bank for Reconstruction and Development (IBRD)) የዓለምአቀፍ ልማት ማኅበር (International Development Association (IDA)) ሥር ለሚገኘው የኢንስፔክተር ፓናል ባለ 18ገጽ ደብዳቤ ጽፏል፡፡ (የደብዳቤው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል) ይህ የኢንስፔክተር ቡድን ከፍተኛ ሥልጣን ያለው መ/ቤት ሲሆን የዓለም ባንክ የሚሰጠውን ገንዘብ በትክክለኛ ቦታ ላይ አለመዋሉን በመጥቀስ ክስ የሚያቀርቡ ወገኖችን ጉዳይ በመከታተልና ቦታው ድረስ የራሱን ምርመራ በማካሄድ ውጤቱ ተግባራዊ እንዲሆን የባንኩን እጅ የማስጠምዘዝ ዓቅም ያለው እንደሆነ ከዚህ በፊት ያካሄዳቸው የምርመራ ውጤቶች ይጠቁማሉ፡፡
ይህ የመርማሪ ቡድን የቀረበለትን አቤቱታ መቀበሉንና በጉዳዩ ላይ የማንም ተጽዕኖ የማይደረግበትን የራሱን ምርመራ እንደሚያደርግ ከትላንት በስቲያ ባወጣው ባለ 8ገጽ መግለጫ ላይ አሳውቋል፡፡ ይህ የአቤቱታ ፋይል ቁጥር የተሰጠው ጉዳይ በግልባጭ ለባንኩ ፕሬዚዳንትና ለከሳሽ ተወካይ ድርጅት (IDI) እንዲደርስ ተደርጓል፡፡(የደብዳቤው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል)
የሰሜን አሜሪካ ዘጋቢ ባጠናከረው መረጃ መሠረት ቡድኑ ከያዝነው ዓመት የጥቅምት አጋማሽ በኋላ ወደ ምስራቅ አፍሪካ ያቀናል። ቡድኑ ስደተኞቹ የሚገኙባቸውን፣ እንዲሁም ጉዳዩን በሚመለከት አስፈላጊ የሚላቸውን ቦታዎችና ግለሰቦች ሙሉ በሙሉ ያነጋግራል። ለስራው መሳካት የሚሆነውን ሁሉ በሚ ፈለግበት ቦታ በመገኘት በግንባር እንደሚያከናውን ለማወቅ ተችሏል።
በተለያየ ጊዜ ኢህአዴግ የሚፈጽመውን ግፍና በደል በማደራጀት ሥርዓቱ ላይ ከትጥቅ የጠነከረ ትግል ማካሄድ እንደሚቻል አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል:: አያይዘውም በመላው አገሪቱ የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብት ረገጣና የመብት ጥሰት በማሰባሰብ የኢህአዴግን የገንዘብ ምንጭ የማድረቅ፣ ብሎም በእርዳታ ገንዘብ የሚገነባቸውን የአፈና ተቋማት ማስለል እንደሚቻል አስታውቀዋል። ይህንን ታላቅ ስራ የሰሩትን አካላት ልምዳቸውን ለሌሎች በማካፈል አስፈላጊውን ስራ ሊሰሩ እንደሚገባም አሳስበዋል።


Source: http://ethioandinet.wordpress.com

ማክሰኞ 9 ጁላይ 2013

አቶ ድሪባ ኩማ የአዲስ አበባ ከንቲባ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲሱ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ዛሬ በይፋ ተመስርቶ ስራውን ጀምሯል።

ምክር ቤቱ ዶክተር ታቦር ገብረመድህንን በአፈ ጉባኤነትና አቶ ወልደገብርኤል አብረሃን ደግሞ በምክትል ከንቲባነት መርጧል ።

ምክር ቤቱ በከንቲባነትም አቶ ድሪባ ኩማን ሾሟል።

አዲሱ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ ለምክር ቤቱ የካቢኒ አባላቶቻቸውን በማቅረብ አስፀድቀዋል ።

በዚህም መሰረት

አቶ አባተ ስጦታው ምክትል ከንቲባ

አቶ ሀይሌ ፍሰሃ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ

አቶ ይስሃቅ ግርማይ የአቅም ግንባታ ቢሮ ሀላፊ

አቶ ጌታቸው ሀይለማርያም የኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ቢሮ ሀላፊ

አቶ ጥላሁ ወርቁ የጥቃቅንና አነስተኛ ቢሮ ሀላፊ

አቶ ገብረ ፃዲቅ ሀጎስ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ

ወይዘሮ ብዙነሽ መሰረት የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ

አቶ ኤፍሬም ግዛው የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ

አቶ ሺሰማ ገብረስላሴ የንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሀላፊ

አቶ ፎርኢኖ ፎላ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሀላፊ

አቶ ሰለሞን ሀይሌ የመሬት ማኔጅመንትና ልማት ቢሮ ሀላፊ

አቶ ዲላሞ ኦቶሬ የትምህርት ቢሮ ሀላፊ

አቶ ፀጋዬ ሀይለማርያም የፍትህ ቢሮ ሀላፊ

ወይዘሮ ፍሬህይወት አያሌው የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ በመሆን ተሹመዋል ።

እዩልኝ ሲያቅመኝ፤ “አቤ ወደ ሙርሲ የላካቸው ጀቶች ግጭት” ጎንደር ዘ ኢትዮጵያ

እዩልኝ ሲያቅመኝ፤  ”አቤ ወደ ሙርሲ የላካቸው ጀቶች ግጭት”
አንድ አማርኛ መመህር ነበሩን ጺማቸው የጎፈረ ጸጉራቸው የተንጨበረረ ነበር፤ በአንዱ ቀን ታድያ ፊት ለፊታችሁ በምታዩት ነገር ግጥም ጻፉ አሉና አዘዙን፡፡ ሁላችንም አንገታችንን ደፍተን ስንንደፋደፍ አንዱ ሳተና ጨርሻለሁ… ሲል እጁ
ን አወጣ… በል እስቲ አጋራን… አሉና መድረኩን ሰጡት፡፡ እርሱም ጀመረ፤
ያጎፈረው ጢምዎ…
ዝንጀሮ አስመስልዎ…
አቤት የፀጉርዎ…. ብሎ ገና ከመጀመሩ ተማሪው ሳቁን መቆጣጠር አቅቶት ከት…ት ብሎ መሳቅ ጀመረ፡፡ ይሄን ጊዜ መምህሩ ተቆጡ…
ተዉ እንጂ ተማሪዎች… ገና እኮ ነው በደንብ ያቅመኝ እንጂ… አሉን፡፡ ሌላ ሳቅ…
አንድ ወዳጄ ባለፈው ግብጽን አስመልክቶ ያወጋሁትን በእንዲህ መልኩ ይዋጋዋል… ደህና አድርጎ አቅሞኛል፡፡ ለነገሩ እኔም የምለቀው አይመስለኝም…  ስለ ባዕድ ሀገር የማውራት ሞራሌ እስኪሰባሰብ ግን እስቲ እርሱ ያቃመኝን ላልደረሰው ላዳርሰው ብዬ በድረ ገፃችን ላይ ለጥፌዋለሁ፡፡
አንዳንዴ ሁለት ተዋጊ ጀቶች ከአንድ የጦር ሰፈራቸው ቦምብና ሮኬት ወይም ሚሳይል አንግበው ይነሱና በጠላት ወረዳ ደርሰው ከማጥቃታቸው በፊት በሚፈጠር ስህተት እርስ በርሳቸው ተላትመው ቦምቡም፣ ሚሳይሉም፣ ሮኬቱም ለጠላት መሆኑ ቀርቶ ለራሳቸውና ለአብራሪዎቻቸው ይተርፋል። አቤ “ደግሞ በግብፅ እንጣላ እንዴ” በሚል አርእስት የላካቸው ጀቶች (ፌስቡክ ላይ ያሰፈራቸው መልእክቶች) ይህ ዕጣ ገጥሟቸዋል እያልኩ ይህን ከበላይ አካል ፈቃድና እውቅና ያገኘ ፅሑፍ ልጋብዝ።
ግጭቱ እንዲህ ነው፤ አቤ በአንድ በኩል ‘ሙርሲ ዋጋውን አገኘ’ ይልና በሌላ በኩል ‘የተመረጠን የገለበጡትን መቃዎም ተገቢ ነው’ ይለናል። እዚህ ላይ አቤን እንደ ፌስቡከኛ ብቻ በማየት ባለማለፍ በጉዳዩ ላይ መነጋገር አስፈላጊ ነው ብዬ አምናለሁ። ለምን አቤ ኢሳት ላይም የሰራልና ነገሮችና የነገሮች ሂደት የሚገዙበት ደንብ መጣረስ የለበትምና። መጣረስ ደግሞ አንዱ የኢሳት ችግር ነው፤ ለምሳሌ ኢሳት በተደጋጋሚ ኢትዮጵያ ውስጥ መከራና ችግር በዛ፣ ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ተጣሱ፣ አምባገነንነቱ ገደብ አጣ፣ የኢትዮጵያ ጉዞ ወደ ጥፋትና ወደ በመበታተን እየሆነ ነው ወዘተ የሚሉ መልዕክቶችን ያስተጋባል። በሌላ በኩል ደግሞ “ምንም የለም በሉ ከደስታ በቀር … ምንም ችግር የለም… አዲስ ነው ዘመኑ … ኧረ አዲስ ነው! ክፉው ዘመን አልፏል…” የሚለውን ዘፈን ደጋግሞ ይጋብዘን ነበር። የአሁኑን እንጃ በናይል ሳት ላይ በነበረበትና እንደ ልብ እንከታተለው በነበረበት ጊዜ ግን ይህ ነገር በተደጋጋሚ ነበር የሚሰማው። ለመሆኑ ዘፈን የምንጋበዘው ስለ መልዕክቱ ነው ወይስ ስለዘፋኙ ወይስ ስለዘፋኙ ቲፎዞዎች ሲባል? አንድ ጊዜ ‘ኢሳቶች ገና ከመጀመራችን ለትችት ተሽቀዳደሙ’ ሲል ሰምቻቸው ነው እንጅ ይህን መሰል ነገር ቀደም ብሎ ማድረግ ጥሩ ነበር። ‘እናቴ ሆይ በእንቁላሉ … ’ አለ ነው የተባለው በሬ ሰርቆ ለስቅላት የቀረበው ሰውዬ?!
በኢሳት የተላለፉ ተመሳሳይ መጣረሶችንና በደንብ ያልታሰበባቸው የሚመስሉ ዝግጅቶችን ከተለያዩ ፕሮግራሞቹ በመሞነታተፍ ማቅረብ ይቻላል። አንድ ቀን ይህን ማድረግ ተገቢ ነው።
ወደ አቤ እንመለስና በመጀመሪያ ሁለቱን ጀቶቹን እንያቸው።
ጀት ቁጥር አንድ
“እንደኔ እምነት የግብፅ ወታደር ኩዴታ ፈፅሟል የሚያስብል ነገር አላየሁም፡፡ በርካታ ህዝብ አደባባይ ወጣ ተቃውሞውንም አሰማ … ሙርሲ ይሂዱልን ከዚ… አሉት ..። ስለዚህ በእኔ በምስኪኑ እምነት የእነዚህ ብዙሃን አቤቱታ መሰማት አለበት፡፡ ለዚህም ወታደሩ ያደረገው መፈንቅለ መንግስት ሳይሆን አፍቅሮተ ህዝብ ነው ባይ ነኝ፡፡ ለብዙሃኑ ጆሮ ሰጥቷልና!” ጥቅስ አቤ ቶኪቻው።
ጀት ቁጥር ሁለት
“ያሳዝናል፡፡ እነዚህ ተቃዋሚዎች (የሙርሲ ደጋፊዎች) እየጠየቁ ያለው ጥያቄ ትክክል ነው፡፡ ድምጻችን የት ነው…! የመረጥነውን ሰውዬ የት አደረሳችሁት…! እያሉ ይገኛሉ፡፡ ይሄ እጅግ በጣም ትክክለኛ ጥያቄ ነው፡፡… እኔ ይቺን እየተየብኩ ባለበት ሰዓት የወታደሩን ጣልቃ ገብነት በመቃወም በተቀሰቀሰው አዲሱ ተቃውሞ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ሃያ ሊደርስ እየተንደረደረ ነበር፡፡ በጣም ያሳዝናል፡፡ እነዚህ ተቃዋሚዎች እየጠየቁ ያለው ጥያቄ ትክክል ነው፡፡ ድምጻችን የት ነው…! የመረጥነውን ሰውዬ የት አደረሳችሁት…! እያሉ ይገኛሉ፡፡ ይሄ እጅግ በጣም ትክክለኛ ጥያቄ ነው፡፡” አሁንም ጥቅስ ከአቤ ቶኪቻው ነው።
የሁለቱ ጀቶች ፍፃሜ
የአሜ ጥቅስ ሲቀጥል የሚከተለውም ይገኝበታል “መጨረሻ ላይ እንደኔ አስቴየት ያኛውም ትክክል ይሄኛውም ትክክል ሆነ ማለት ነው፡፡ እንግዲህ ዲሞክራሲ አጣብቂኝ ውስጥ የምትገባው ይሄኔ ሳይሆን አይቀርም፡፡ የሚል ሌላ አስተያየት ልጨምራ!”
አቤ ይቀጥላል፤ “አሁን ከሙርሲ እና ሌሎች ባለስልጣናት ወደ ማረፊያ ቤት መውረድ በኋላ ተቃዋሚዎቹ (የሙርሲ ተቃዋሚዎች) የልባቸው ደርሶ ወደ ጎጇቸው ሲመለሱ የሙርሲ ደጋፊዎች ደግሞ ይቺን ይወዳል የሙርሲ ልጅ ብለው እየቀወጡት ይገኛሉ፡፡ ይህ ሊመጣ እንደሚችል ተንታኞቹ ድሮውንም ገምተዋል፡፡ ማለቂያው ምን ሊሆን እንደሚችል ግን የሚያውቀው የላይኛው ብቻ ነው፡፡”
የአቤን ጀቶች ይዘት እንመርምራቸው!!
አቤ ጀት ቁጥር አንድን “ብዙሃን” እና “ህዝብ” የሚል ታርጋ በመለጠፍ ጥሩና ትልቅ ጀት አድርጎ ሲያሳየን፤ ቁጥር ሁለት ጀትን ግን “ተቃዋሚዎች” እና “ሰዎች’ የሚል ታርጋ በመስጠት አሳንሰን እንድናያት በዘዴ እየሰራ ነው።
አቤ የሙርሲን ተቃዋሚዎች በወታደራዊ ሃይል መደገፋቸውን እሰየው የሚያስብል፣ በሰዎች ሊደረግ የሚገባው እርምጃ አድርጎ ወሰደውና የመርሲ ደጋፊዎች ወዮታን ግን ከፈለገ የላይኛው ይርዳቸው በሚል ለበጣ አልፎታል።
አቤ እንዳሻኝ እፅፋለሁ ለማለት ‘መቼም ለሙርሲ ሞራል ተጠንቀቅ [አትሉኝም]…’ ሲል ፅፏል። በቀልድ መልክ አስተምራለሁ ብሎ መጣጥፍ የሚያቀርብ ሰው ግን በዚህ ዓይነት አስተሳሰብ መመራት የለበትም እላለሁ። ይህ ፅሑፍ የአበበን አመለካከት ብቻ ሳይሆን አቤ ነገሮችን የሚፈርድበትን ሚዛንም ነው የሚያሳየን። አቤ ስለ ምንም ነገር ሲፅፍ የሱን ፅሑፍ ለሚከታተሉ ሰዎች ስለሚለግሰው እውቀት፣ በልባቸው ሊያኖረው ስለሚችለው ተስፋና ሞራል፣ ዝንባሌና አመለካከት መጠንቀቅ እንደሚጋባው ማሰብ የለበትም ይሆን?
አቤ በድፍረት “እንደኔ እምነት የግብፅ ወታደር ኩዴታ ፈፅሟል የሚያስብል ነገር አላየሁም” ብሏልና ይህ ነገር ብዙ ብዙ ይናገራል።
“በሕዝብ የተመረጠ መሪ አጉራ ዘለል ሆኖ ተገኘ ከተባለ በመጣበት መንገድ ለመሸኘት ድጋሚ ምርጫ ማድረግ ነው የሚገባው ወይስ የአደባባይ ግርግርን መሰረት አድርጎ መዘርጠጥ?” ይህ ለአቤ የማቀርበው ጥያቄ ነው። አቤን የምጠይቀው ሌላም ጥያቄ አለኝ “ይህን ያህል ሃይል ያለው የግብፅ ጦር ለምን ሕዝብ ድምፁን በስነ ስርዓት የሚያሰማበትን ወይም በሕጋዊና ‘ዓለም ዓቀፍ ተቀባይነት’ ባለው የድምፅ አሰጣጥ ስነ ስርዓት የሚካሄድበትን መንገድ አላመቻቸም?”
ስለ ሰልፍ ካነሳን አይቀር የሙርሲ ደጋፊዎችም ገና ከመጀመሪያው አንስቶ አደባባዮች ላይ ነበሩ። በቢቢሲ መስኮት ያልታየ ሕዝብ “ሕዝብ” አይባል ይሆን? ብየም ልጠይቅ።
ሚዲያንና ድምፅን የማሰማትን ነገር ከወሳን አይቀር ከሐምሌ 5-7/ 2013 ባለው ጊዜ ብዙዎቹ የአውሮፓ ሚዲያዎች ለመጥቀስ ያህልም ቢቢሲ፣ ዩሮ ኒውስ፣ ፍራንስ-24 ወዘተ ገና ከማህፀን ያልወጣው ከእንግሊዛዊ ልዑል ባለቤቷ ኬቲ የፀነሰችውን ልጅ ‘መጣ፣ ደረሰ፣ ቀረበ’ ሲሉና ስለ ህፃን አልጋ፣ ስለ ህፃን ልብስ፣ ስለ አራስ ልብስ ወዘተ ሃተታ ብቻ ሳይሆን የዜናቸው ዋና ክፍልም አድርገውት አይተናል። እንግሊዝ ውስጥ ሌሎች የተወለዱ፣ የሚታዩና እዚህና እዚያ የሚኖሩ ድምፃቸው ሊሰማ የሚገባ ሰዎች የሉምና ነው ለአንድ ‘እጭ’ ይህ ሁሉ ጫጫታ?! Mail On Line የተባለው የእንግሊዝ ድረ ገፅ Royal birth the world is waiting for ሲል ነው ነገሩን የዘገበው። ምን ያህል ሕዝብ ቢጓጓ ነው ዓለም በጉጉት የሚጠብቀው መወለድ ያለው? ሚሊዮን ወይስ ቢሊዮን? ሚዲያ እንዲህ ነው። ለራስ ሲቆርሱ…
ሚዲያዎች የተቋቋሙበት ዓላማ አላቸው። ነገራቸው ሁሉ በዚህ የተቃኘ ነው። የግብፅ ጦር ከሄሊኮፕተር አበባና በመልዕክት የተሞላ ወረቀት እየበተነ ያበረታታው ሰልፈኛ (ሕዝብ) የመኖሩን ያህል በተመሳሳይ ዕለት በታጠቀ ሃይል ከበባ ውስጥ አስገብቶ መንቀሳቀሻና መላዎሻ ያሳጣው ሕዝብም ነበር። አቤ ‘ቢቢሲ ሁለቱን ሰልፎች ጎን ለጎን እያሳየ ነው’ ያለን የሙርሲ ቁርጥ ከታወቀ በኋላ ነው፤ ቢቢሲ ለቀናት የሙርሲን ደጋፊዎች ችላ ብሎቿ ነው የነበረው። የአሜሪካ ባለስልጣናትና የአውሮፓ ጋዜጠኞች የስልጣንና የስራ ጊዜያቸው ካለፈ በኋላ ችላ ያሉትን ሃቅ ወደ ኋላ ተመልሰው በማስተጋባት ይታወቃሉ። ይህን የሚያደርጉት የህሊና ወቀሳ አላስተኛ ብሏቸው ወይም በዚያ ሚስጢር ቀዳሚ (ብቸኛ) ተጠቃሚ በመሆን ታዋቂነት ወይም ‘ታላቅነት’ ወይም ገንዘብ ለማግበስበስም ሊሆን ይችላል። ቢቢሲም ይህን ባህል በመጠቀም ይታወቃል። ስለ ቦብ ጌልዶፍና እሱ ያሰባሰበው የዕርዳ ገንዘብ የት ገባ በሚል ፕሮግራም የተሰራው ነገሩ ከተፈፀመ ከ25 ዓመታት በኋላ ነው። መጀመሪያ ላይ ይህ ፕሮግራም ለሕዝብ ቀርቧል። ከዚያም ይህ ታሪክ ብዙ ውዝግብ ፈጥሮ ከቢቢሲ ከድረ ገፅ እስከመሰረዝ ደርሷል። ይህ ለአቤ ቅርብ የሆነው ታሪክ ነውና አቤ የሚዲያዎችን አካሄድ በዚህ ሊመዝነው ይችላል። ቦብ ጌልዶፍ በእንግሊዝ ንግስታዊ መንግስት “ሰር” ተብሎ የተሾመ ነውና ቢቢሲን አናውጦታል። ከማናወጥም አልፎ ቢቢሲን አፉን ይይዝ ዘንድ አስገድዶታል። ሌላም ታሪክ እናስታውስ፤ በአጠያያቂ ሁኔታ ሕይወታቸው ስላለፈው ስለ እንግሊዛዊው ዶክተር ኬሊ እና በግድያው (በሞታቸው) ዙሪያ ጉዱን ለማጋለጥ ያስችላል የተባለን አንድ ፕሮግራም ቢቢሲ ለሕዝብ በማቅረቡ አታካራ መፈጠሩንና አታካራው አንድሬ ግሊጋንን (የቢቢሲ ዳይሬክተር የነበረ) ከሓላፊነቱ ስለ ማስነሳቱ ታሪክ ፈተሽ ፈተሽ እናድርግ!!
ሰውን ማመን ቀብሮ አለች ቀበሮ። ወንድሜ ሚዲያን ማመን ብዙ መርምሮ ነው። ሰሞኑን ኦባማ አፍሪካን ሲጎበኙ “ኦባማ አምባገነን ናቸው ያሏቸውን አገራት አይጎበኙም” እያልን የበኩላችንን ደረት የመንፋትና ክብረ ቢስ ‘ጌቶቻችንን’ የማሸማቀቅ መከራዎችን እያደረግን ነው የሰነበትነው። ለነገሩ ይህን እያልን ሰዎችን እንጎሻሽም እንጅ ኦባማ የአምባገነን አገር አይጎበኝም የሚለው እውነት ሆኖ አይደለም። ኦባማም ይሁን እየተነሳ ያለፈ የአሜሪካ ፕሬዘደንት ሁሉ ከአምባገነን ጋር ሳይላላስ የቀረበት ጊዜ የለም። አዲስ የአሜሪካ ፕሬዘደንት በተመረጠ ቁጥር ወደ ሳውዲ ዓረቢያ ለገብኝት ይጠራል፣ ይሄዳል፣ የውሻ ሰንሰለት የሚያክል የወርቅ ሃብል ከነ ሜዳሊያ ከሳውዲ ነገስታት እጅ በአንገቱ ተጠልቆለት ይመለሳል። በኔ አመለካከት ሳውዲ ውስጥ የለየለት ኋላቀር፣ የለየለት የምዕራባውያን (በተለይ የአሜሪካ) አሻንጉሊት ወይም ገረድ፣ ሰው አራጅ (ስለ ‘Chop Chop Square’ ማንበብ ጥሩ ነው )፣ ሴቶችን እንደ እቃና እንድ እንስሳ የሚቆጥር ወዘተ ወዘተ መንግስት ነው ያለው። ዕድሜ ሚዲያን በገንዘብ ሃይል ሰለመቆጣጠር በሰሜን ኮርያ ስልጣን የቤተሰብ ‘ቮሊቦል’ ሲሆን የተከፉት ‘ዲሞክራቶችና’ ‘ጋዜጠኞች’ በሳውዲ ስልጣን ብቻ ሳይሆን አገር ‘ቮሊቦል’ ሲሆን ጭጭ ነው።
አቤ አንተ እነዚህን ሚዲያዎች ሰምቶ ነው የግብፅ ሕዝብ ሰልፍ ሲባል እነማንን ማሰብ እንደሚገባ የፈረደው። የነፃነትና የዲሞክራሲ ሰባኪ የሆነችው እንግሊዝ ያቋቋመችው የመገናኛ ቢሮ (Office of Communication- OFCOM) ያገዳቸው ወይም አፈና ያካሄደባቸውና በምድረ እንግሊዝ እንዳይሰራጩ የከለከላቸው እነ ፕረስ-ቲቪን ብታይ ደግሞ የተሰለፈው ሕዝብ የሚለው አመለካከትህ ሰፋ ይላል ወይም ይቀየራል ብዬ እገምታለሁ። በእርግጥ እኔ የማምነው ከቢቢሲ፣ ከቪኦኤ፣ ከስካይ ኒውስ፣ ከፎክስ ኒውስ የምሰማውን ብቻ ነው ማለት ይቻላል። ይህ ግን ወደ ትክክለኛና ሚዛናዊ ፍርድ አያመራም።
አቤ “በርካታ ህዝብ አደባባይ ወጣ ተቃውሞውንም አሰማ… ሀቂቃውን ለመናገር ግን በግብጽ ተቃውሞ የወጡት ብዙሃን አንደነበሩ እድሜ ለቴክኖሎጂ በወቅቱ በቦታው ተገኝተው ሲዘግቡ የነበሩቱ ቀጥታ ሲያነፃጽሩልን ነበርና፤ ሙርሲ ይሂዱልን ከዚ… ያሉት ብዙ እንደነበሩ ድንጋይ ነክሰን ብንምልም አንፈራም” ብሎናል። ይህ አቤ ከምዕራቡ ዓለም ሚዲያዎች የወረደን ነገር እንዳለ የመቀበልና አማራጭ ሚዲያዎችስ ምን ይላሉ ብሎ ቅራና ቀኝ ለማየት እንደማይፈልግ ወይም ለዚህ ጊዜ እንደሌለው ወይም ከቢቢሲ ወዲያ ለአሳር ብሎ የማለ መሆኑን ያሳየናል ለማለት ልድፈር ይሆን? አቤ ለጠቅ አደረገና ሚዛኑን ሲያሳየን በድጋሜ “ወታደሩ ያደረገው መፈንቅለ መንግስት ሳይሆን አፍቅሮተ ህዝብ ነው ባይ ነኝ፡፡ ለብዙሃኑ ጆሮ ሰጥቷልና!” ብሎናል። ለአቤ መረጃ አቀባይ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማለት ቢቢሲ እና መሰሎቹ ብቻ ይሆኑን? ብዙ ድረ ገፆችና ነፃ ሚዲያዎች እንደ ልብ በሞሉበት በዚህ ዘመን… ምነው… ምነው… ?
አቤ በዜማ (በግጥም) ይህን ብሏል “ተመረጥኩኝ ብለሽ አትበይ ደንበር ገተር… ከልተመቸው “ንኪው” ይልሻል ባላገር…” የሚል ዘፈን አለ አይደል…። የዚህን ዘፈን ዜማ ባልሰማውም ከ1997 ምርጫ በኋላ የአና ጎሜዝን ሪፖርት ተከትሎ አንድ ጋዜጠኛ ለአንድ የአውሮፓ ፓርላማ አባል ‘ምርጫ ተጭበርብሯል እየተባለ የአውሮፓ መንግስታትም ሆኑ የአውሮፓ ህብረት ለምን ጠንካራ እርምጃ ከመውሰድ ተቆጠቡ?’ ሲል ጥያቄ አቅርቦላቸው ነበር። ለዚህ መልስ ነው ብለው የፓርላማ አባሉ ብዙ ነገር ነው የተናገሩት። ዋና ዋና ነጥቦች ለመጥቀስ ያህል “… የአካባቢው (የአፍሪካ ቀንድ) ወታደራዊ ሚዛን ሊዛባና ክልሉ ሊበጣበጥ ብሎም የሽብር መነሃሪያ ሊሆን ይችላል… የመለስ ተቃዋሚዎች ከአዲስ አበባ ውጭ ጠንካራ መሰረት የላቸውምና… ሂትለር ወደ ስልጣን የመጣው በምርጫ ነበር፤ የሰው ልጅ ነገሮችን አስቀድሞ የሚያይ ቢሆንና ያንን የምርጫ ውጤት ቢቀለብሰው ኖሮ ለዓለማችን ትልቅ በረከት በሆነ ነበር። ያ የምርጫ ውጤት ቢገለበጥ ለዓለማችን ትልቅ ጠቀሜታ ነበረው ነገር ግን ይህ ነገር ተደርጎ ቢሆን ኖሮ ምርጫ ተጭበረበረ እያልን እንተቸው ነበር እንጅ ምርጫው መገልበጡ ያስቀረውን ችግርና መከራ ስለማናውቀው እናመሰግነውም ነበር…” እኝህ ሰው በግልፅ ይናገሩት እንጅ ምዕራባውያን ለጥቅማቸው ሲሉ ከዚህ የከፋ ምክንያትም ሊዘረዝሩ ይችላሉ። የ1997ተን ምርጫ ከታዘበ በኋላ ጂሚ ካርተር ቦሌ ላይ ምን ብሎ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሰጠ ሰምተኸዋል የሚል ግምት አለኝ። ካርተር ሃሳቡን የቀየረው የአና ጎሜዝን መግለጫና ጥንካሬ ካየ በኋላ አልነበረምን?
አቤ! ወደራዊ ጣልቃ ገብነት በለው መፈንቅለ መንግስት ይህ ነገር በቱርክ ቢፈፀ ምን ትለን ነበር? የቱርክ ወታደር አደባባይ የወጡ ቱርካውያንን በመደገፍ ተመሳሳዩን እርምጃ ቢወስድ እነ ኦባማ እነ ሜርክል ምን ይሉ ይመስልሃል? ሚዲያዎችስ?
የሙርሲንና የጓደኞቹን መታሰርም ልትቀልድበት ሞክረሃል። ማንም ሰው በምንም ላይ ቢቀልድ ‘መብቱ’ ሊሆን ይችላል ወይም በማን አለብኝነት መብቴ ነው ብሎ ሊያደርገው ይችላል። ነገር ግን ሁልጊዜም አሳሪ ትክክለኛ ታሳሪ ወንጀለኛ አድርገን ከወሰድን ምርጡ ኢትዮጵያዊ ወንድማችንንና ምርጧን ኢትዮጵያዊት እህታችንን (እስክንድርና ርዕዮት) ከነ ምርጥ የሙያና የአላማ ጓደኞቻቸው እስር ቤት ናቸው። ጊዜ የሰጣቸው ደግሞ ‘አሸባሪዎቹ’ እያሉ ነው የሚያብጠጥሏቸው። ሰው የፈለገው አቋም ሊኖረው ይችላል በሚዲያ ላይ የሚቀርብ ሲሆን ግን ቢያንስ የህሊና ተጠያቂነትን ግምት ውስጥ ያስገባ ስራ ቢሰራና አስተሳሰቡንም በዚሁ ቢቃኝ ጥሩ ነው። ምዕራባውያን ድሮ ለቅኝ ግዛት ሲመጡ እንስረቅ፣ እንግደል ብለው አልመጡም። ክርስትና እናስፋፋ፣ ጣዖት አምልኮና አረመኔነትን እናስወግድ፣ የባሪያ ንግድን እናጥፋ ወዘተ ነበር ያሉት። እዚህ ላይ ጣሊያን ኢትዮጵያን ሲወርር የሰጠውን ምክንያት ለማወቅ ‘The Lion of Judah’ የሚለውን ጥናታዊ ፊልም ልጋብዝ።
ለነገሩ አቤ ባለስልጣናትን አስመልክቶ ለበጣ ይፅፋል ይናገራል፤ ይህን ስለ እንግሊዟ ንግስት ማድረግ የሚቻል ይመስላችኋል? አቤ ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለእነሱ በሚገባ ጥሩ እንግሊዝኛ የዚህ ዓይነት ነገር መፃፍ ቢጀምር ከሁለትና ከሶስት መጣጥፍ አያልፍም። ቀልድ አይደለም ወቅቶችን ጠብቀው ንግስቲቱንና የቤተመንግስቱን ቡድን የሚቃዎሙ እንግሊዛውያንን ሰልፍ እየተከታተለ በጥሩ እንግሊዝኛ ቀጥተኛ ዘገባ ቢሰራበት መዘዝ ያለው መሆኑን መርሳት አይገባም። እኛ ሰማይ አይታረስ ንጉስ አይከሰስ እንደምንለው በእንግሊዝም “What happens in the Palace Remains in The Palace” የሚል መመሪያ አለ። በደም የጨቀየ ታሪክ ያለው ቤተመንግስት ነው ባኪንግሃም ፓላስ። ስለ ዲያና አሟሟት የተሰራውን ፊልም እንውሰድ። ይህ ፊልም እንግሊዝ ውስጥ ለመታየት ከ80 በላይ ክፍሎች ተቆርጠው መውጣት አለባቸው ተብሎ ታግዷል። ልክ ነው ‘ዘ-ዲክታተር’ የተባለው ልብ-ወለድና በተራ ጭብጥ ላይ ተመርኩዞ የተሰራ ፊልም በአፍሪካና በዓረቡ ዓለም ሲከለከል ብዙ የተጮኸውን ያህል በዲያና ታሪክና በአሟሟቷ ላይ ብዙ መረጃዎችን አጭቆ የተሰራው እውነተኛ ፊልም በምድር እንግሊዝ እንዳይታይ ሲከለከል ሚዲያዎች ብዙ አልደሰኮሩም። ከዚህ ሌላ በቅርቡ ሰሞኑን ብዙ የተወራለት የኬቲ ፅንስ ምርመራ እየተካሄደለት በነበረበት ጊዜ ወደ ሆስፒታሉ ስልክ ተደውሎ ነበር፣ ይህን ተከትሎ ስልኩን ተቀብላ ነበር የተባለችና በዚያ የምትሰራ አንዲት ነርስ ሞታ ወይም ተገድላ መጠነኛ ውዝግብ ተከትሎ ነበር። ነገር ግን ብዙም ሳቀጥል ጭጭ ተብሎ ታልፏል- What happens in the Palace Remains in The Palace። ይህ ደግሞ ገና በፅንስነቱ ማስገደል ጀመረ ያሉ ግን አሉ።
አበበ ሆይ ይህን መሰል (የግብፅንና የመርሲን) ነገር ለሕዝብ የምታቀርብ ከሆነ ግራና ቀኝ ማየት አለብህ ብዬ አልመክርህም። ምክንያቱም ይህን አንተ አታጣውምና። በተጨማሪም የታላላቅ ሚዲያዎችን አሰራር ታውቀዋለህና። አበበ ገላው በዋሽንግተኑ የሬገን አዳራሽ የቃውሞውን ባወረደበት ወቅት በዚያ ወኪሉን (ሪፖርተሩን) ያልላከ የሚዲያ ድርጅት አልነበረም። የአበበ ጩኸት ለሁሉ ተሰምቶ ይሆን የሚል ጥርጣሬ የሚያጭርም አልነበረም። በዚያች ደቂቃ በዚያ አዳራሽ ሁሉም ነገር ሰአቶች ሳይቀሩ የቆሙ የሚያስመስል ተአምር ስለተፈጠረ በዚያ የተገኘ ሁሉ የአበበን ስራ ተግቶታል። “አቶ መለስ ሆይ ንግግርዎ አይሰማም፣ ድምፅ ይጨምሩ” ያለ መስሎን ነው እንዳይሉ ደግሞ በጠራ እንግሊዝኛ ነው መልዕክቱን ያስተጋባው። በዚያ ቦታ በዚያች ዕለት እንግሊዝኛ ቋንቋ የማይሰማ ጋዜጠኛ ወይም ሪፖርተር የላካል ብሎ መገመት ጅልነት ነው የሚሆነው። ነገር ግን ይህ ነገር ዜና ላይ አልተሰማም። ቪኦኤን ጨምሮ በዝምታ ነው ያለፉት። ቪኦኤ ነገሩን የዘገበው ከአድማጮች ብዙ ኡኡታና ተቃውሞ ከገጠመው በኋላ ነው። በተቃራኒው የኢራኑን መሪ በአንድ የአሜሪካ ዩንቨርስቲ ውስጥ አንድ ተማሪ ኢራን የግብረ ሰዶማውያንን መብት አታከበርም ብሎ ዘለፋ ሲሰነዝርባቸው ግን ሚዲያዎች እንዴት እየተቀባበሉ እንዳስተጋቡት እናስታውሰዋለን!!
የግብፅን ነገር ወይም የሙርሲን መውደቅ ብዙ ሰዎች ነገሩን የክርስቲያን-ሙስሊም ቁርቁስ አድርገው ያዩትና ሙርሲ እንኳን ሄደ ሲሉ ይሰማሉ። በሌላ ወገን ደግሞ ሙርሲና ደጋፊዎቹ ‘እስማለዊ’ ስለሚባሉ በጭፍን እስልምና ተጠቃ የሚሉ ወገኖች ይታያሉ። እኔ ግን አንድ ጥያቄ አለኝ?
የአሜሪካና የአውሮፓ ሚዲያዎች ለምንድን ነው የሙርሲን ደጋፊዎች ‘ኢስላሚስቶች’ የሚሏቸው?
ይህ ብቻ አይደለም አልሸባብ፣ ቦኮሃራም፣ የማሊ ተዋጊዎች ወዘተ ሲጠቀሱ ይህ ‘እስላማዊው’ የሚለው ቅጥያ ተዘውትሮ ጥቅም ላይ ይውላል። ቪኦኤ የአማርኛና የትግርኛ ክፍለ ጊዜ ‘እስላማዊው’ ሲሉ ቪኦኤ ኦሮምኛ ደግሞ ‘ኢስላሙማ’ ሲል ይሰማል። የቸችኒያ፣ የሶርያ፣ እየኮሰመኑ የመጡት የኢራን መጂሃዲኖችና የመሳሰሉት የአሜሪካ ጠላት የሆኑ መንግስታትን ያጠቃሉ የሚባሉ ተዋጊዎች ሙስሊሞችና የእስልምናን መመሪያ አንግበው የሚዋጉ ቢሆንም ‘እስላማዊ’ ሲባሉ አይሰሙም። በአውሮፓና በአሜሪካ ለእስልምና ጥላቻን ማራመድ እየተስፋፋ ነው፤ ታዲያ ይህ ‘እስላማዊው’ ማለት ‘የምትጠሉት’ ወይም ‘መጠላት ያለበት’ እንደማለት ሆኖ እያገለገለ ነውን? በኡጋንዳ የጌታን ትዕዛዛት ለማስከበርና ይህን መሰረት ያደረገ መንግስት ለመመስረት እዋጋለሁ የሚለው ‘የጌታ ተፋላሚ ጦር (Lord’s Resistance Army- LRA) መኖሩ ይታወቃል። ለምን ይህንን ቡድን ‘ክርስቲያናዊው’ እያሉ ሲጠሩት አልተሰሙም?
እኔ ሙስሊም አይደሁም። ነገር ግን የኢትዮጵያ ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች ለዘመናት አብረን የኖርን ወንድማማቾች ነንና አንዱ የውስጥ ወይም የውጭ አካል ለራሱ ይመቸው ዘንድ እኛን ሊያጫርስ የሚጭራትን ትንሽ እሳት ገና በእንጭጯ ለማጥፋት ንቁ መሆን እንዳለብን ይሰማኛል።
በመጨረሻም የሙርሲን አባባል ያጋነንከውና ልዩ ትርጉም የሰጠኸው ይመስለኛል። ይህን ያደረግከው ለአገርህ ብለህ ነው ወይስ ሙግትህን ለማጠናከር። አቶ ሙርሲ “ኢትዮጵያውንን እርስ በርስ እናበጣብጣታቸው ብለው ሲዶልቱ” ያልከው የኢትዮጵያን ተቀዋዋሚዎች በመርዳት የኢትዮጵያን መንግስት እናዳክመው ያሉትን ነው? እዚህ ላይ ምን እንደምልህ እንጃ! አንድ ታሪክ ግን ልንገርህ። ዚያድ ባሬ ኢትዮጵያን ወረረ፣ ከሸፈበት። ዚያድ ባሬ ያልተቋጨ የግዛት ጥያቄ አለውና ኢትዮጵያን እያዳከመ መቆየትና ሌላ ጦርነት ማካሄድ እንዳለበት ተሰማው። ሻዕቢያንና ወያኔን ማገዝ ጀመረ፣ አስታጠቀ፣ ፓስፖርት ሰጥቶ በፈለጉበት እየተንቀሳቀሱ የውጭ ሃይሎችን ድጋፍ እንዲያገኙና ደጋፊዎዎቻቸውን ማደራጀት ይችሉ ዘንድ ሀኔታዎችን አመቻቸ። በዚህ ግዙፍ እገዛ ዚያድ ባሬና ሶማሊያ ባይጠቀሙም ዚያድ ባሬ የረዳቸው በጣም እንደተጠቀሙ፣ ኢትዮጵያችን በእጅጉ እንደተጎዳች እያየን ነው። ይህ ጉዳት ይሽር ይሆን? “የጠላቴ ጠላት…” ሲባል ምን ማለት ነው?
የቪኦኤዋነ አዳነች ፍስሃዬ የሙርሲን ንግግር በዚህ መልኩ ደጋግማ አስተጋብታዋልች። ሙርሲ ሲወድቁም ለውድቀታቸው ድጋፍ የመሰለ ፕሮግራም ሰርታለች። ለኢትዮጵያ አስባ ነው ወይስ በአሜሪካ ሲገደፍ የነበረው የሙባረክ መውደቅ አሳስቧት ወይስ የአሜሪካ አሻንጉሊቶች የሆኑ አምባገነኖችን መገልበጥ አደጋ አለው የሚል ትምህርት ልትሰጠን ፈልጋ?

ምንጭ/ከአቤ ቶክቻው