እሑድ 31 ጃንዋሪ 2016

ኢንሳ የአየር ላይ ፎቶ በማንሳት ላይ የሚገኘው ለሱዳን ተሰጥቷል የሚባለውን አልፋሽጋ ተብሎ የሚጠራውን አካባቢ መሆኑ ታወቀ

ጥር ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ካለፈው ጥር ወር መግቢያ ጀምሮ የአየር ላይ ፎቶ እየተነሳ ያለው አካባቢ የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ” ኢትዮጵያ መሬቱ የእኛ መሆኑን እውቅና ሰጥታለች” በማለት ለአልጀዚራ የተናገሩት አልፋሽጋ እየተባለ የሚጠራው ቦታ መሆኑ ታውቋል።Ethiopian Border Affairs Committee
ትናንት ኢሳት የመረጃና ደህንነት ኢንፎረሜሽን ባለሙያ በማናገር በሰራው ዘገባ ላይ በአሁኑ ሰአት የአየር ላይ ፎቶ ለማንሳት ምልክቶችን መሬት ላይ የማስቀመጡ ስራ የሚከናወነው 365 ኪሜ ርዝመት ባለው ቦታ ላይ መሆኑን ቢዘግብም፣ ይህ ርቀት ግን የአየር ላይ ርቀትን የሚያመለክት እንጅ የመሬትን እርቀት የሚያመለክት ባለመሆኑ ማስተከከያ እንዲደረግበት ጠይቀዋል። በመጀመሪያው ሂደት ድንበር የማካለሉ ሂዳት የሚከናወነው 725 ኪሜ ርዝመት ላይ ባለው መሬት ላይ ሲሆን፣ ይህም አካባቢ ሱዳን የኢትዮጵያ መንግስት የእኔ መሬት መሆኑን አምኖልኛል በማለት የገለጸችው አልፋሽጋ እየተባለ የሚጠራውን ለም መሬት የሚያካትት ነው።
አልፋሽጋ የሚባለው ቦታ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ከመለየቷ በፊት ከራስካሳር እስከ አትባራ የሚደርሰውን ቦታ ያካልል እንደነበር የሚገልጹት ባለሙያዎች፣ የኢህአዴግ መንግስት ለማስረከብ እየተዘጋጀ ያለው ከሰቲት ወንዝ እስከ አትባራ ድረስ ያለውን 725 ኪሜ የሚደርስ ሰፊ መሬት ነው። አልፋሽጋ በደቡብ አጥባራ፣ በሰሜን ሰቲት ማሃል ላይ ባህረነጋሽ በተባለ ወንዝ የተከበበ በመሆኑ፣ መሬቱ ለእርሻ ስራ እጅግ ተስማሚ ነው።
በሁለተኛው ዙር መሬት የማካለል ስራ ከሁመራ ጫፍ እስከ ኤልሚ ወይም የሱዳን፣ ኬንያና ኢትዮጵያ መገናኛ ድንበር ድረስ እንደሚካሄድ ባለሙያዎች ገልጸዋል።
የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አልፋሽጋ ሱዳን መሆኑን ኢትዮጵያ ማረጋገጫ ሰጥታለች ቢሉም፣ በኢህአዴግ መንግስት በኩል እስካሁን ምንም አይነት ማስተባበያ አልተሰጠም። ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያምና ቃለአቀባዩ ጌታቸው ረዳ ከሱዳን ጋር ምንም አይነት የድንበር ማካለል ድርድር እየተካሄደ እንዳልሆነ ገልጸው ነበር።
ሱዳኖች በበኩላቸው የሁለቱ አገራት የድንበር ኮሚቴ ስራውን በማጠቃለል ላይ መሆኑንና የመጀመሪያው ድንበር የመለየት ስራ በቅርቡ እንደሚጀመር ገልጸዋል።
የኢህአዴግ መንግስት የድንበር ጉዳዩን ለህዝብ ለምን ግልጽ ማድረግ እንደተሳነው የታወቀ ነገር የለም። መሬቱን በድብቅ ለማስረከብ የሚደረገው ሂደት በሁለቱ አገራት መካከል ሰላም ያመጣል ተብሎ አይታመንም።
የአካባቢው ነዋሪዎች በእርሻ ማሳዎች ላይ የሚተከሉትን ምልክቶች በመንቀል ተቃውአቸውን እንዲገልጹ ባለሙያዎች ጥሪያቸውን በድጋሜ አቅርበዋል።

ዓርብ 8 ጃንዋሪ 2016

ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በዋሽንግተን ዲሲ የፊታችን ሰኞ ጃንዋሪ 25 / 2015 በኣሜሪካ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት

US Department of State
2201 C St NW
Washington, DC. 20520
Date and Time:
Monday 25th January 2016 at 9:00 AM
Dress code Black
Image
Organizers: Ethiopian Orthodox Religious Leaders, Ethiopian Muslim Leaders (First Higrah), Ethiopian Evangelical Religious Leaders, United OLF, Moresh Wegene, All Amhara Peoples Party, United Ethiopian Muslims Peaceful Movement Support Group, Patriotic Ginbot 7, EPRP, Shengo, AEDP Support Group, SMNE, DC Joint Task Force, Border Committee, SOCEPP, Netsanet Radio

ማክሰኞ 5 ጃንዋሪ 2016

በወቅታዊ የአገራችን አሳሳቢ ጉዳዮች ላይ ለመምከር የተዘጋጀ የዉይይት መድረክ — በዋሽንግተን ዲሲ


ኢትዮጵያ እና የህዝቦቿ የወደፊት እጣ ፈንታ አሳስበዎታል? ያገርዎ፣ የባህልዎ፣ የእምነትዎ ወዘተ ጉዳይ ያገባኛል ይላሉ? እዉነተኛ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር፣ የህግ የበላይነት፣  ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ስርዓት እንዲመጣ ይሻሉ? ለነዚህ እና ለመሳሰሉት አንገብጋቢ ጉዳዮች ገንቢ ሃሳብ ለመስማት እና የርስዎንም ለማካፈል እንዲሁም ባገር ዉስጥ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች እቅድ እና እንቅስቃሴን ለመረዳት በዚህ ዝግጅት ላይ ተካፋይ ይሁኑ!
ተጋባዥ እንግዶች:
(ከአዲስ አበባ)
ዶ/ር መረራ ጉዲና
ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት
አቶ ነጋሲ በየነ
(ከዋሺንግቶን ዲሲ)
አቶ ሀይለገብርኤል አያሌው
አቶ ሄኖክ ጋቢሳ
አወያይ:
አቶ ጥበበ ሳሙኤል
ቀን:       እሁድ Jan 10, 2016    ሰአት:  2pm
ቦታ: 7701 16th St NW, Washington DC, 20012
አዘጋጅ:     የሰማያዊ አንድነት ድጋፍ በሰሜን አሜሪካ
ለተጨማሪ መረጃ: ስልክ፥ (202) 556-3078
ኢሜል፥ info@semayawiusa.org
ድህረ ገጽ፥ www.semayawiusa.org
ይህ ዉይይት የሚካሄደው በአዲስ አበባ እና በዋሺንግቶን ዲሲ በቪዲዮ ግንኙነት ስለሆነ በሁለቱ ከተሞች መካከል ያለዉን የሰአታት ልዩነት ታሳቢ በማድረግ ፕሮግራሙ በሰአቱ የሚጀመር መሆኑን አዘጋጆች ማሳሳብ እንሻለን። እርስዎም ከጥሪው ሰአት ቀደም ብለዉ በመገኝት እንዲተባበሩን በማክበር እንጠይቃለን።