መረጃ ለሁሉም
INFO FOR ALL ETHIOPIAN
ማክሰኞ 19 ኤፕሪል 2016
ሰኞ 18 ኤፕሪል 2016
የመላው ኢትዮጲያ አንድነት ድርጅት ( መኢአድ) አመራሮች ዛሬም በሥቃይ ላይ ናቸው
የመላው ኢትዮጲያ አንድነት ድርጅት ( መኢአድ)
አመራሮች ዛሬም በሥቃይ ላይ ናቸው
የነጻነት የፍትህ የኩልነት
ታጋዮች ያለምንም ፍርድ...
በህወሓት ማሠቃያ ቤት እየተሠቃዩ ይገኛሉ
1ዓመት ከ7ወር ሙሉ ያለምንም ማሥረጃ
ያለምንም ፍርድ ታሥረው ይገኛሉ
የህወሓቱ ዳኛ የሁኑትን እሣቸው ዘንድ የቀረበን ሁሉም የፖለቲካ እሥረኛ ተበቂ በላይ ቢከላከል እንኳን መንግሥት ያለመረጃ አይከሥም በማለት ሣያገናዝቡ ፍርድ ይሠጣሉ ከድሜልክ እሥራት እሥከ ሞት በዚህ ፍርድ (አቡሃይ )ችግር የለባችውም እኒህን ዳኛ ይቀየሩልን በማለታቸው ምክንያት
ከታሣሥ 4/4 /2008 ጀምርው ያለምንም ውሣኔ በሥር ላይ ይገኛሉ
በሥር ላይ የሚገኙት ሥም ዝርዝር
በነ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮነን የክሥ መዝገብ ላይ ያሉት 16 ሠዋች
1ኛ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮነን
2ኛ በላይነህ ሢሳይ
3ኛ አለባቸው ማሞ
4ኛ አወቀ ሞኝሆዴ
5ኛ ዘሪሁን ብሬ
6ኛ ወርቅየ ምሥጋናው
7ኛ ኣማረ መሥፍን
8ኛ ተሥፋየ ታሪኩ
9ኛ ቢሆነኝ አለነ
10ኛ ተፈሪ ፋንታሁን
11ኛ ፈረጀ ሙሉ
12ኛ አትርሣው አሥቻለው
13ኛ እንግዳው ዋኘው
14ኛ አንጋው ተገኘ
15ኛ አግባው ሠጠኝ
16ኛ አባይ ዘውዱ
እኒህ የህሌና እሥረኞች ያለምንም ማሥረጃ
በሥር እየተሠቃዩ ይገኛሉ
ህወሃት ሆይ
በማፈን በማሠር በመግደል ሠላም አይገኝም
የነጻነትን ጎህ ሣንቀናጅ በፍጹም ትግሉ አይቆምም
እኛ የተደራጀነው ይህን አሥከፊ አረመኔ ጨካኝ ሥርአት ለማሥወገድ ነውና
በቆራጥ አመራር በቆራጡ ህዝባችን ታጅበን
በበደኖ አርባ ጉጉ
በጋንቤላ ጉራ ፈርዳ
በመላ አገራችን እየተፈጸመ ያለውን የዘር መጽዳት ዘመቻ
ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ ለማሥወገድ ነውና
ከፕሬፌሠር እሥክ ዶክተር
ካርሦ አደር እሥከ ሙህር
ከሹፌር እሥከ ርዳት
ከተማሪ እሥከ አሥተማሪ
ያለውን ያገራችንን ህዝብ አደራጂተው
ያሥረከቡንን
የነጻነት ፋና ቀዳጂ የሆኑትን ክቡር ፕሮፌሠር አሥራት ወልደየሥን
እሣቸው ጀምረው መሣውት የሆኑበትን ኣላማ ከዳር ለማድረሥ
እኛም ልጆቻቸው ጠንክረን እንሠራለን
እሥከ መጨረሻው
አንዲት ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር!!!!!!
ረቡዕ 13 ኤፕሪል 2016
በኢትዮጵያ በአለም ደረጃ በጣም ውድ የሆነ የኢንተርኔት አገልግሎት እንደምታቀርብ ተገለጸ
ኢትዮጵያ በአለማችን ካሉ ሃገራት መካከል የኢንተርኔት አገልግሎትን በጣም ውድ በሆነ ክፍያ በማቅረብ ግንባር ቀደም ሃገር ሆና መገኘቷን በጉዳዩ ዙሪያ ጥናትን ያደረገ አንድ የቴክኖሎጂ ተቋም ይፋ አድርጓል።
ይኸው የ120 ሃገራትን ታሪፍ በንጽጽር ያቀረበው ኑሚቢዬ የተሰኘው አካል በኢትዮጵያ ዝቅተኛ ፍጥነት ባለው የኢንተርኔት አገልግሎት ክፍያው የማይቀመስ መሆኑንም አመልክቷል።
የኢትዮ-ቴለኮም ባለስልጣናት ይህንኑ አገልግሎት ጨምሮ በቫይበር የሚደረግ የስልክ ጥሪ ልውውጥ ላይ ክፍያን ተግባራዊ ለማድረግ ምክክርን በማካሄድ ላይ መሆኑን ባለው ሳምንት ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።
በሃገሪቱ በብቸኝነት የስልክ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው ኩባንያው በአገልግሎቱ ላይ አዳዲስ የቁጥጥር ስርዓቶችን ተግባራዊ ከማድረጉ ጎን ለጎን የተንቀሳቃሽ የእጅ ስልኮችንም ለመመዝገብ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገልጿል።

ማክሰኞ 12 ኤፕሪል 2016
የማህበራዊ ድምጽና ምስል አገልግሎቶች በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ተቋረጡ
መንግስት በኢንተርኔት አማካኝነት የሚደረጉ የድምፅና የምስል አገልግሎቶች ላይ አዲስ መመሪያን እንደሚተገብር ማስታወቁን ተከትሎ አገልግሎቱ በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ተቋረጠ።
በተለይ በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተገናኘ ተቃውሞ በተቀሰቀሰበት የኦሮሚያ ክልል የትዊተርና የWhatsAPP አገልግሎቶች ከተቋረጡ አንድ ወር አካባቢ እንደሆናቸው ብሉምበርግ የዜና ወኪል የተለያዩ መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ ማክሰኞ ዘግቧል።
በኦሮሚያ ክልል በተጨማሪ አገልግሎቶቹ በደቡብ ክልል ሃዋሳ ከተማና በተለያዩ አካባቢዎች ተቋርጦ እንደሚገኝም የተለያዩ አካላት ለዜና ወኪሉ ያስታወቁ ሲሆን፣ በምስራቅ ለንደን ዩኒቨርስቲ የኢኮኖሚክስ መምህር የሆኑት አቶ ስዩም ሃሜሶ ሃገር ቤት ከሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ጋር እንኳን መገናኘት እንዳልቻሉ ተናግረዋል።
የመንግስት ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ አገልግሎቱ ሊስተጓጎል የቻለው በቴክኒክ ችግር ሊሆን እንደሚችል ገልፀው፣ መንግስት የማገድ ፖሊሲ እንደሌለው ለዜና አውታሩ አስተባብለዋል።
ይሁንና የስልክ አገልግሎት ተጠቃውሚዎችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች መንግስት ተግባራዊ ሊያደርግ ያሰበው አዳዲስ መመሪያዎች በኢንተርኔት እና በስልክ የመልዕክት ልውውጦች ላይ ቁጥጥርን እንዲሁም የስነ-ልቦና ተፅዕኖን ለመፍጠር እንደሆነ አስታውቀዋል።
በአምቦ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑት አቶ ስዩም ተሾመ በተቀንሳቃሽ የእጅ ስልክ የሚደረጉ የተለያዩ የኢንተርኔት አገልግሎቶች ተቋርጠው እንደሚገኙ ለብሉምበርግ የዜና አውታር አስረድቷል።
በቅርቡ የWhatsAPP ኩባንያን የገዛው ፌስቡክና ትዊተር ድርጅቶች በኢትዮጵያ እገዳ ተጥሎበት ስላለው አገልግሎት ተጠይቀው ምላሽ ከመስጠት መቆጠባቸው በዘገባው ያወሳው የዜና ወኪሉ እገዳው በተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ዘንድ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖ እንደሚገኝም አስነብቧል።
በኢትዮጵያ የሰብዓዊ የመብት አያያዝና የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ዙሪያ የሰላ ትችትን የሚያቀርበው ሂውማን ራይትስ ዎች በበኩሉ ድርጊቱ ቀድሞ የተተነበየ እንደሆነና መንግስት የመረጃ ልውውጦች ላይ ቁጥጥሩን እንዳጠናከረ ገልጿል።
መቀመጫውን በሰርቢያ ያደረገውን በቴክኖሎጂ ዙሪያ የሚሰራው ኩባንያ በየጊዜው የሚያወጣቸው መረጃዎች በቢቢሲ እና በሌሎች አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘንድ በመረጃነት እንደሚቀርቡም ለመረዳት ተችሏል።
ቤርሙዳ ኢዝቤኪስታን እና ሚያንማር ከኢትዮጵያ በመቀጠል ከሁለተኛ እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል። የኢትዮጵያ መንግስት በኢንተርኔት አገልግሎት ላይ ከሚያደርገው ቁጥጥር በተጨማሪ የሚጠይቀው ክፍያም ውድ መሆኑን የተለያዩ አካላት ሲገልጹ መቆየታቸው ይታወሳል።
መንግስት በገጠመው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ፣ በውጭ ሃገር ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በህዳሴ ግድብ እንዲሁም በመኖሪያ ቤት ግንባታ ገንዘብ ለማሰባሰብ አዲስ ዘመቻ መጀመሩን ለማወቅ ተችሏል

እሑድ 27 ማርች 2016
የሄነከን ቢራ ዘረፋ ምስጢር በኢትዮጵያ ሲጋለጥ – ክንፉ አሰፋ
የሄነከን ቢራ ዘረፋ ምስጢር በኢትዮጵያ ሲጋለጥ – ክንፉ አሰፋ
የሆላንድ ዜምብላ[1] ጋዜጠኞች የኦሮሞ ጸሃፊው የሆነውን ያሶ ካባባን ይዘው ወደ ጊንጪ ያመራሉ። እግረመንገድ ላይ የሚያገኟቸው ገበሬዎችም ሲጠይቋቸው በምስሉ ይታያል። እነዚያ በቀያቸው ማረፍያ እንኳን የሌላቸው ገበሬዎች የጋዜጠኞቹን መኪና ከብበው እንዲህ ሲሉ ይደመጣሉ። “መሬታችንን ቀምተው ለነጮች ሰጡብን። እኛንም በታተኑን…”
በገዛ ቀያቸው ስደተኛ የሆኑ እነዚህ ወገኖቻቸን ሰቆቃቸው የከፋ ነበር። በመጨረሻ ተሰባሰቡና መከሩ። ሰባት ሺህ የሚሆኑ የጊንጪ ተወላጆች ሆ! ብለው ወጥተው ይህንን የሁለት ሚሊዮን ዩሮ (ሃምሳ ሚልዮን ብር) ንብረት በሰኮንዶች ውስጥ አወደሙት። ምስላቸውን ለካሜራ ሳይደብቁ፣ ስሜታቸውን እና የወደፊት እቅዳቸውን ይናገራሉ። “ከአንባገነን መንግስት ጋር አብሮ ከመስራት ይልቅ የአካባቢው ነዋሪዎች ሊጠቀሙ በሚችሉበት መንገድ መስራት እንደሚችሉም።” ለፈረንጆቹ ይመክራሉ። “ይህ ካልሆነ ግን ማውደሙን እንቀጥልበታለን!” ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ይህ ማስጠንቀቅያ ግዙፉ አለም አቀፍ ኩባንያ የሆነው ሄነከን ቢራንም ይመለከታል።
ባለፈው ሳምንት በሆላንድ ብሄራዊ ቴለቭዥን የተላለፈው ዜምብላ ፕሮግራም የሚሊዮኖችን ቀልብ ስቧል። ለዚህም ምክንያቶች አሉት። አንደኛው ምክንያት፤ የዜምብላ ፕሮግራም በምርመራ ጋዜጠኞች የሚሰራ በመሆኑ እጅግ የሚፈራ እና በሃገሪቱ ፖለቲካ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ማሳደሩ ሲሆን፣ በሁለተኛ ደረጃ በኢትዮጵያ እየወደመ ያለው ይህ ንብረት የተቋቋመው በሆላንድ መንግስት ድጎማ ሲሆን፣ ይህ ደግሞ የእያንዳንዱ ሆላንዳዊ ግብር ከፋይ ገንዘብ በመሆኑ ነው።
የሆላንድ የልማትና ትብብር ሚንስተር ለድሃ ሀገሮች እርዳታ ከመለገስ ይልቅ ወደ ንግድ ድጎማ ፊቱን ባዞረ ግዜ፣ 130 አትራፊ የንግድ ድርጅቶች ድጎማ እየተቀበሉ ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል። ከነዚህ ውስጥ ትልቁን የድጎማ ድርሻ የወሰደው ሄነከን ቢራ ነው። ሄነከን ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ የሆላንድ መንግስት አንድ ቢሊየን ዩሮ ድጎማ አድርጓል። እንደ ሆላንድ መንግስት እሳቤ፣ ይህንን የልማት ትብብር ገንዘብ በእርዳታ መልክ ከመስጠት ይልቅ ይህንን አትራፊ ተቋም አበራትቶ ስራ በመፍጠር እና በንግድና በስራ ታክስ ሃገሪቱ ተጠቃሚ እንድትሆን ማድረግ ነበር። የሆነው ግን በተቃራኒ ነው።
የዜምብላ ቴሌቭዥን ዘገባ ያጋለጠው ጉዳይ በእጅጉ ያስደምማል። እንዲህ ነው የሆነው። እ.ኤ.አ. በ 2011 ሄነከን ወደ ኢትዮጵያ እንደገባ የቢራ ስራ አዋጭ መሆኑን ስለተገነዘበ ስመ ጥሮቹን በደሌ እና ሃረር ቢራን ገዛቸው። ስራውንም በእጅጉ አስፋፋ። በአኢትዮጵያ የቢራ ተጠቃሚዎች ቁጥር በእጥፍ እንዳደገም ዘገባው አስምሮበታል። ትርፉም እንደዚያው አደገ።
በደሌ ቢራ ከመሸጡ በፊት አንድ ነጥብ አምስት ሚሊየን ዩሮ ግብር ይከፍል ነበር። ሄነከን ከገዛው በኋላ ግን የከፈለው ዘጠኝ መቶ ሺህ ዩሮ ብቻ ነው። አንድ ሚሊየን ዩሮ ግብር ይከፍል የነበረው ሃረር ቢራም አሁን ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ዩሮ ብቻ ነው ያስገባው። ትርፉ ከእጥፍ በላይ እያደገ፣ ግብሩ ከእጥፍ በላይ የመቀነሱ ምስጢር ምን ይሆን?
የግብር ማጭበርበር ጥቆማ የደረሳቸው እነዚህ ጋዜጠኞች ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ንግድ ሚንስትር ሄዱ። ምኒስትሩ በዚህ የማጣራት ጉዳይ ላይ ሊተባባራቸው ፈቃደኛ አልነበረም። ከዚያም ወደ ጉምሩክ እና ቀረጥ ቢሮ አመሩ። እዚያም ምንም መረጃ እንሰጥም ይሏቸዋል። ምስጢሩን ለማውጣት የጓጉት እነዚህ ጋዜጠኖች ተስፋ አልቆረጡም። በመጨረሻ ወደ ንግድ ምክር ቤት አመሩ። የዚያ ባለስልጣን የሰጧቸው ምላሽ የሚያስቅ ነው። “የንግድና ትርፍ ዘገባ አይደርሰንም።” አሉ። ታዲያ ንግድ ምክር ቤት ይህንን ካልመዘገበ ምን ይሆን የሚሰራው?
የንግድና የስራ ግብር መቀነሱ ብቻ አይደለም። ቀድሞ በሃረር እና በበደሌ ቢራ ቋሚ ሰራተኛ የነበሩ 699 (44%) ሰራተኞችም ከሄነከን ቢራ ተቀንሰዋል። የሆላንድ መንግስት ስራ ፍጠሩ ብሎ ድጎማ ሲያደርግ፣ ይልቁንም ነባሩን ሰራተኛ ከስራው አፈናቀሉት።
በኢትዮጵያ የሄነከን ተወካይ ሆላንዳዊ ነው። የዜምብላ ጋዜጠኖች የዚህን እንቆቅልሽ ለመፍታት እሱን ማፋጠጥ ይችላሉ። ስለዚህም ወደሱ አመሩ። የገቢና ወጪ ዘገባውን እንዲሰጣቸው ጠየቁት። እንቢ እንዳይል ቸገረው። ምክንያቱም በዚያ ዘገባ የሆላንድ መንግስት የድጎማ ገንዘብ ሰላለበት። እሺ ብሎ ይፋ እንዳያደርገው ደግሞ ምስጢሩ ለህዝብ ሊወጣ ነው። እሱም አለ። “የፋይናንስ ሪፖርቱን እሰጣችኋለሁ። እናንተ ግን ለህዝብ ይፋ እንደማታደርጉት ቃል ግቡልኝ።”
ዘገባውን በእጃቸው ያስገቡት እነዚህ ጋዜጠኖች፣ ዶክመንቱን አለም አቀፉ የገንዘብ ተቁዋም አማካሪዎች ጋ ይዘውት ሄዱ። የ አይ. ኤም. ኤፍ. ባለሙያው ወረቀቱን እንዳየ ምስጢሩን ለማወቅ ሰከንዶች አልፈጁበትም። የኢትዮጵያ ህዝብ በታክስ ተዘርፏል። ሰራተኛውም ወገን ከስራው እንዲፈናቀል ተደርጓል።
የመንግስት ባለስልጣን ሃገር ሲዘረፍ እና ወገን ከስራ ሲፈናቀል፣ ጉዳዩን ማፈን መርጠዋል። ምክንያት ቢኖራቸው እንጂ ይህን መረጃ መስጠት ሀገርን የሚጠቅም ነበር። በእርግጥ ይህ የግብር ማጭበርበር ተግባር እነሱ ሳያውቁት ሊሆን አይችልም። “የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ!” ነው ነገሩ። እንዲህ እየተዘረፈ ኢኮኖሚው እንዴት ነው በ 11 በመቶ የሚያድገው?
እንግዲህ ይህ በኢትዮጵያ ከዘመቱት 130 የሆላድ የንግድ ድርጅቶች አንዱ ታሪክ ነው። ገቢውና ወጭው በግልጽ የሚታይ፣ ግዙፍ እና አለም አቀፍ ድርጅት። ሄነከን ከገዥው ፓርቲ ባለስልጣናት ጋር በመመሳጠር ይህንን ያህል ከዘረፈ የሌሎቹ – የማይታወቁት ምን ያህ ይሆን?
የቀድሞው የሆላንድ ልማትና ትብብር ሚንስቴር የነበሩት ጃን ፕሮንክ፣ በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ከልማት እና እደገት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ለሌላቸው የንግድ ድርጅቶች የገንዘብ ድጋፍ ማድረግን ክፉኛ ይወቅሳሉ። በተለይ መንግስታቸው በልማትና ትብብር ስም፣ በብሄራው ጥቅም ስም የስብአዊ መብት ረገጣን ችላ ማለቱን ያወግዛሉ።
በልማት ስም በሚሊዮኖች እየፈሰሰ ያለው የሆላንድ ግብር ከፋዮች ገንዘብ በኢትዮጵያ ስራ አልፈጠረም። እንደውም ሰራተኞችን አፈናቀለ። ሀገሪቱን በበለጠ የስራና የንግድ ግብር ተጠቃሚ ያደርጋል ይባል እንጂ ግብሩ በ 70 እጅ ያነሰ ሆኗል። ከሁሉም በላይ ደግሞ የገበሬው መሬት እየተነጠቀ ለነዚህ ዘራፊዎች መሰጠቱ የህዝብ ቁጣን አስነስቷል።
በኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት እየተካሄደ ያለው ህዝባዊ አመጽ የገዥው ፓርቲ ችግር ብቻ ሳይሆን የሆላንድም ችግር መሆኑን በመግለጽ ዜምብላ ዘገባውን ይደመድማል።
ረቡዕ 16 ማርች 2016
Ethiopians hold demonstration in DC denouncing human rights violations in their country, demand US to take firm stand
Ethiopians living in the metropolitan Washington, DC area held a
demonstration at the US State Department on Tuesday denouncing the human
rights violations perpetrated by the tyrannical regime in their country
against the people of Surma in South Ethiopia as well as the human
rights abuses at various locations in the country.
The demonstrators also demanded the US government to show unwavering
stance against the human rights abuses perpetrated by its ally in
Ethiopia.
An international uproar ensued last week after a picture of Surma men
in a chain gang, loaded on a police pickup, surfaced on the social
media. They were apparently held by the regime’s forces for protesting
the seizure of their land by the government for sugar plantations.
The Ethiopians demanded the regime in their country to immediately
desist the wide range of human rights violations in Oromia, Wolkait in
Amahra and Gambella regions and other corners of the country. The
demonstrators hold the oppressive regime in Ethiopia responsible for the
death of hundreds of people in the Oromia region of Ethiopia in the
last four months protests.
The organizers of the demonstration have submitted to the US State
Department a paper detailing the various human rights violations in
Ethiopia.
Tuesday’s demonstration was organized by the Washington DC Joint Task Force, civic, political and religious organizations.
ሰኞ 14 ማርች 2016
በኮንሶ ግጭቱ አገረሸ ፤ ሰዎች ተገደሉ:: የካራት ከተማና አጎራባች ቀበሌዎች ትምህርት ቤቶች ተዘጉ::
– በኮንሶ ህዝብ የተነሳውን የአከላለል ጥያቄ ተከትሎ በሕወሓት አገዛዝ ታጣቂ ኃይሎችና በህዝቡ መካከል የተነሳው
ግጭት ላለፉት ሁለት ቀናት ጋብ ብሎ የነበረ ቢሆንም እንደገና አገርሽቶ ሦስት ሰዎች ሲሞቱ ሁለት ደግሞ ቆስለዋል፡፡
የካራት ከተማ አጎራባች ከሆኑት ቀበሌዎች አንዱ በሆነው ደበና ቀበሌ ወጣት ፋንታዬ ጊዮርጊስ፣ ወጣት ሞሎ ቱሌ እና
አንድ ስሙ ያልደረሰን 10ኛ ክፍል ያጠናቀቀ ሥራ አጥ ወጣት በሕወሓት አገዛዝ የጸጥታ ኃይሎች የተገደሉ ሲሆን
በተጨማሪም ሁለት ወጣቶች ቆስለዋል ፡፡ በዚህ ግጭት ሳቢያ የካራት ከተማና አጎራባች ቀበሌዎች እስካሁን ትምህርት
ቤቶች እንደተዘጉ ሲሆን ከተማዋና አካባቢው በመኪና ላይ በተጠመዱና የነፍስ ወከፍ መትረየስ ታጣቂዎች ተወሮ፣ ኮንሶ
ልዩ ወረዳ ከዳር እስከ ዳር በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ናቸው፡፡

የኮንሶ ህዝብ የጀመረውን የአከላለል ጥያቄ ጋር በተያያዘ በህዝቡ ላይ በደቡብ ልዩ ኃይልና መከላከያ ሰራዊት
እየደረሰ ያለው የአፈና ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በዚሁ መሰረት በከተማው የሰፈረው ታጣቂ ከከተማዋ አጎራባች
ቀበሌዎች እየዘመተ በህዝቡ የተዘጉ መንገዶችን ለማስከፈት በሚል በዜጎች ላይ በሚወስደው የኃይል እርምጃ በ- ደቤና
ቀበሌ ገ/ማ አቶ ‹‹ሷይታ ጋራ ›› ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ወጣት ‹‹ ተስፋዬ ማሙሽ›› ከ -ከርታሌ ቀበሌ እግሩ
ተሰብሮ በባህል ህክምና እየተደረገለት በካራት ከተማ የሚገኝ ሲሆን አንድ የ65 ዓመት አዛውንትም ተሰብረው ባሻ ጤና
ጣቢያ ይገኛሉ፡፡ ከባለፈው ዓርብ/25-06-08/ ጀምሮ 23 ሰዎች/ሃያ ሁለት ወንዶችና አንዲት ሴት/ ከፍተኛ
ድብደባ ተፈጽሞባቸው በከተማዋ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ማዕከል ውስጥ ታስረው እንደሚገኙ ተገልጧል፡፡ በከተማዋ
የሚገኙት የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በሙሉ የተዘጉ ሲሆን የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛው ወደ እስር ቤት
ተቀይሯል፡፡
ወደከተማው የሚያስገቡ መንገዶች እስካሁን የተዘጉ ሲሆን በተለይ የ -ደራ እና ጃርሶ ቀበሌ ነዋሪዎች መትረየስ በታጠቁ የልዩ ኃይል አባላት ተወረዋል፡፡ በጃርሶ ቀበሌ ሰገን ወንዝ ዳር የሰፈረው ኃይል የነዋሪዎችን ፍዬሎች እየዘረፈ አርዶ እንደሚበላ፣ የፓፓያ፣ማንጎ አቮካዶ እና የፍራፍሬ ዛፎችን በበቀል ስሜት እያበላሸ/እያወደመ እንደሚገኝም ህዝቡ በምሬት እየገለጸ ነው፡፡
ታጣቂ ኅይሉ በዚህ የኃይል እርምጃ የካራትን ከተማ አቋርጦ የሚያልፈውን የአርባ ምንጭ -ጂንካ መንገድ ማስከፈት ቢችልም ከተማዋን ከማሳለፍ ውጪ የሚሰጠው ዋስትና ያለመኖሩ አሽከሪካሪዎችን ስጋት ላይ በመጣሉ ከመንግስት መኪናዎች ውጪ የትራንስፓርት እንቅስቃሴ አይታይም፡፡ የመንግስት መኪና ተጠቃሚዎችም ቢሆኑ ከልዩ ኃይል ጋር ተነጋግረው መግባባት ባለመቻላቸው በትናንትናው ዕለት የደቡብ ኦሞ/ጂንካ ባለሥልጣናትን ይዞ ይጓዝ የነበረ መኪና ለ2 ሰዓታት ካራት ላይ በታጣቂ ኃይሎች ታግቶ ቆይቶ እንደተለቀቀ ምንጮች ገልጸዋል፡፡
በአጠቃላይ ከተማዋና አካባቢው በመኪና ላይ በተጠመዱና የነፍስ ወከፍ መትረየስ ታጣቂዎች ተወሮ፣ ኮንሶ ልዩ
ወረዳ ከዳር እስከ ዳር በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ይገኛል ፡፡ የአገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች ፣ሴቶችና ህጻናት ሳይቀሩ
ቱንም ዋጋ እንከፍላለን እንጂ ጥያቄኣችን ሳይመለስ ወደቤት አንገባም /አንመለስም በማለት ያላቸውን ቁርጠኝነት
እየገለጹ መሆኑን እነዚሁ ታማኝ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡ እኛም የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ሆይ ‹‹አፈና እና
የኃይል እርምጃ ›› የህዝብን ብሶት ሲባብስ እንጂ ለህዝብ ጥያቄ መልስ አይሆንምና ከህዝቡ ላይ እጅህን አንሳ፣
ለሰላማዊ ጥያቄው ተገቢውን ምላሽ ስጠው፣ ህገ መንግስታዊ መብቱን አክብርለት እንላለን ፡፡
ወደከተማው የሚያስገቡ መንገዶች እስካሁን የተዘጉ ሲሆን በተለይ የ -ደራ እና ጃርሶ ቀበሌ ነዋሪዎች መትረየስ በታጠቁ የልዩ ኃይል አባላት ተወረዋል፡፡ በጃርሶ ቀበሌ ሰገን ወንዝ ዳር የሰፈረው ኃይል የነዋሪዎችን ፍዬሎች እየዘረፈ አርዶ እንደሚበላ፣ የፓፓያ፣ማንጎ አቮካዶ እና የፍራፍሬ ዛፎችን በበቀል ስሜት እያበላሸ/እያወደመ እንደሚገኝም ህዝቡ በምሬት እየገለጸ ነው፡፡
ታጣቂ ኅይሉ በዚህ የኃይል እርምጃ የካራትን ከተማ አቋርጦ የሚያልፈውን የአርባ ምንጭ -ጂንካ መንገድ ማስከፈት ቢችልም ከተማዋን ከማሳለፍ ውጪ የሚሰጠው ዋስትና ያለመኖሩ አሽከሪካሪዎችን ስጋት ላይ በመጣሉ ከመንግስት መኪናዎች ውጪ የትራንስፓርት እንቅስቃሴ አይታይም፡፡ የመንግስት መኪና ተጠቃሚዎችም ቢሆኑ ከልዩ ኃይል ጋር ተነጋግረው መግባባት ባለመቻላቸው በትናንትናው ዕለት የደቡብ ኦሞ/ጂንካ ባለሥልጣናትን ይዞ ይጓዝ የነበረ መኪና ለ2 ሰዓታት ካራት ላይ በታጣቂ ኃይሎች ታግቶ ቆይቶ እንደተለቀቀ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
ልጥፎች (Atom)