ረቡዕ 13 ኤፕሪል 2016

በኢትዮጵያ በአለም ደረጃ በጣም ውድ የሆነ የኢንተርኔት አገልግሎት እንደምታቀርብ ተገለጸ


ኢትዮጵያ በአለማችን ካሉ ሃገራት መካከል የኢንተርኔት አገልግሎትን በጣም ውድ በሆነ ክፍያ በማቅረብ ግንባር ቀደም ሃገር ሆና መገኘቷን በጉዳዩ ዙሪያ ጥናትን ያደረገ አንድ የቴክኖሎጂ ተቋም ይፋ አድርጓል።
ይኸው የ120 ሃገራትን ታሪፍ በንጽጽር ያቀረበው ኑሚቢዬ የተሰኘው አካል በኢትዮጵያ ዝቅተኛ ፍጥነት ባለው የኢንተርኔት አገልግሎት ክፍያው የማይቀመስ መሆኑንም አመልክቷል።
የኢትዮ-ቴለኮም ባለስልጣናት ይህንኑ አገልግሎት ጨምሮ በቫይበር የሚደረግ የስልክ ጥሪ ልውውጥ ላይ ክፍያን ተግባራዊ ለማድረግ ምክክርን በማካሄድ ላይ መሆኑን ባለው ሳምንት ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።
በሃገሪቱ በብቸኝነት የስልክ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው ኩባንያው በአገልግሎቱ ላይ አዳዲስ የቁጥጥር ስርዓቶችን ተግባራዊ ከማድረጉ ጎን ለጎን የተንቀሳቃሽ የእጅ ስልኮችንም ለመመዝገብ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገልጿል።

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ