ዓርብ 28 ፌብሩዋሪ 2014

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ………..

‹‹ የኢትዮጵያ ሃየር መንግድ ለአፍሪካ ኩራት ነው ›› ሲባል ከቃላት መፈክርነት ባለፈ የአውነትም ኩራት ስለመሆኑ ጥርጣሪ የሚያድርባቸው ዜጎች እንደሚኖሮ እገምታለው፡፡ ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ አየር መንግድ በረዥም ታሪኩ ውስጥ ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች በአንፃራዊነት በተቋሙ ውስጥ ስማቸው እጅግ የገነነ ብቁ አብራሪዎች፣የቴክኒክ ባለሙያዎች (ግራውንድ ቴክኒሻን) እና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በአብዛኛው በኢትዮጵያዊያን የተሞላ ነው፡፡ ለዚህም ነው የአፍሪካ ኩራት ለመባል የበቃው፡፡ ይህ ኩራት እና አድናቆት ከታላቁ አፍሪካዊ የነፃነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ ጀምሮ ጥቂት በማይባሉ አፍሪካዊያን ዘንድ ተቀባይነት ያገኘ ነው፡፡
በተጨማሪም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሎሜ፣ማላዊ እና ቶጎ በመሳሰሉ የአፍሪካ አገሮች ከፍተኛ አክሲዮን ሼር በመግዛት እያስተዳደረ እና እያንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡እንዲሁም የተለያዩ የአፍሪካ አገር ተወላጆች በአብራሪነት እና በቲክኒሻንነት እያሰለጠነ ይገኛል፡፡ ይህ ደገሞ አየር መንገዱ በይለጠ በአፍሪካ እና በተቀሩት የዓላም አገራት ተቀባይነት ለማግኘት የሚያስችሉት መልካም ተግባራቶች ናቸው፡፡ እንዲ አይነቱ ለውጥ እና እድገት ለአገር ኩራት ስለመሆኑ ጥርጣሪ የሚያሳድር አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ ከላይ የተገለፁት የአየር መንገዳችን መልካም ስራዎች በተቋሙ ውስጥ ለሚታዩ የአስተዳደር ችግሮች እና አየር መንገዱ ሊደርስበት ይገባው ለነበረ የእድገት ደረጃ አለመድረስ ምክንያቱ ምን እንደሆነ እና መሰል አሳቦችን አንስቶ ለመወያየት ብልጭ ድርግም የሚለው የአየር መንገዳችን እድገት የአሳብ ፍጭት ለማድረግ የሚገድብ አይደለም፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ የኢትዮጵያ አየር ኃይል የራሱ የሆነ ድንቅ ታሪክ ያለው ነው፡፡ የአየር ኃይል ካፒቴኖቻችን እንደ ንስር አሞራ ከሰማይ ወደ ምድር በሚገርም ብቃት በመብረር ጠላትን እና የጠላት ሠፈርን አመድ በማድረግ የሚታወቁ ናቸው፡፡እንዲህ አይነቱ ግርማ ሞገስ ያለው የአገር ኩራት የሆነው ተቋም እና ተቋሙ ያፈራቸው ባለሙያዎች በወያኔ/ኢህዴግ መንግስት ቀጥተኛ ትዕዛዝ ለመፍረስ በቃ እንጂ፡፡ ተቋማትን አፍርሶ እንደ አዲስ መገንባት አሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግስት የስርዓቱ ዋንኛ መገለጫ ነው፡፡ ለዚህም ነው ሁሉ ነገር እንደአዲስ የመጀመር መርዘማ የሆነ የኋላ ጉዞ ሙጥኝ ብለው የተያያዙት፡፡ የሰዎቹ አደገኝነት የሚጀምረው ኢትዮጵያ የምትባል አገር እንደ አገር መታየት ከጀመረች መቶ ዓመት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ነው ብለው የነገሩን ዕለት ነው፡፡ በዚህም መሠረት የኢትዮጵያን አየር ኃይል በማፍረስ አሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግስት በአዲስ መልክ እንዲቋቋም ያደረገ ሲሆን፣ በዚህም ምክንያት እጅግ በጣም ድንቅ የሆኑ የአየር ኃይል ካፒቴኖቻችን ከአገር ለመሰደድ ተገደዋል፡፡
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት የአንድ ሳንቲም ግልባጭ የሆኑት የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና አየር ኃይል ካፒቴኖቻችን ሽሽትና ምክንያት እንዲሁም ውጤት በአጭሩ ለማየት ከላይ የቀረበው አሳብ እንደመንደርደሪያን ሊያገለግል ይችላል፡፡
በአብዘኛው የአየር መንገድ ሠራተኞች በተለይ በአብራሪዎች እና በቴክኒሻኖች የሚነሳው ጥያቄ አስተዳደራዊ በደሎች ናቸው፡፡ እነዘህም ተመጣጣኝ የደሞዝ ክፍያ፣የሰራ እድገት እና የስራ ዝውውርን የሚመለከት ነው፡፡ ለምሳሌ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ የሚሰራ ኢትዮጵያዊ አብራሪ የወር ደሞዙ ትልቁ 7 ሺህ ዶላር ሲሆን ( ይህ የገቢ ግብር ጭምር የሚያካትት ነው) ለውጭ አገራት ዜጎች ግን ላቅ እንደሚል ሠራተኞች ይናገራሉ፡፡ በእርግጥ በኢትዮጵያ የኑሮ ሁኔታ ሲታይ የብሩ መጠን ከፍተኛ ነው፡፡ ነገር ግን ክፍያው የሚፈፀመው የኢትዮጵያ አየር መንገዱ አለም አቀፍ እንደመሆኑ መጠን አለም አቀፍ ደረጃ በጠበቀ መልኩ ነው መሆን ያለበት ፤ለዚህም ነው ወራዊ ደሞዝ በብር ሳይሆን በዶላር የሚከፈለው፡፡ይህንን መሠረት በማድረግ ነው የአየር መንገድ ካፒቴኖች ለስራቸው ተመጣጣኝ ክፍያ እንዲከፈላቸው የሚጠይቁት፡፡
ይሁን እንጂ ሠራተኞች እንደሚናገሩት አስተዳደሩ ለጥያቂያቸው ተገቢ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ‹‹ ስራውን መልቀቅ ትችላላችሁ ›› ነው የሚባሉት፡፡ በዚህም ምክንያት ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ዋና እና ምክትል አብራሪዎች ከአገር በመውጣት በተለያየ አገር የሥራ ብቃታቸውን እያሳዩ ይገኛሉ፡፡ ነገሩን የበለጠ ግልፅ ለማድረግ እንዲረዳ ይህን መመልከት በቂ ይመስለኛል ባለፈው ሳምንት ተጠለፈ የተባለው ET 702 አውሮፕላን ዋና አብራሪ የነበሩት ግለሰብ Air Italia ( Al-Itaia ) በተባለ የአየር መንገድ ድርጅት ውስጥ ሲያገለግሉ ቆይተው በውር 3 ሺህ ዶላር እየተከፈላቸው በጡረታ ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ እኚህ ግለሰብ በኢትዮጵያ አየር መንግድ ውስጥ 14 ሺህ ዶላር እየተከፈላቸው ይገኛል ፡፡
ሌላው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ አገራት ውስጥ ሎሜ፣ቶጎ እና ማላዊ እንዲሁም በተቀሩት ማህከላዊ ምዕራብ አፍሪካ አገራት ውስጥ ባለው ከፍተኛ የሼር መጠን የሚያንቀሳቅሳቸው እና የሚያስተዳድራቸው የአየር መንገድ ድርጅቶች አሉ፡፡ በእነዚህ የአየር መንገድ ድርጅቶች ውስጥ በቴክኒሻንነት የሚያገለግሉ ማንኛው የውጪ አገር ዜጋ ከ 3 እስከ 5 ሺህ ዶላር ክፍያ ያገኛል፡፡ነገር ግን ተመሳሳይ የት/ት እና የስራ ልምድ ያለው ኢትዮጵያዊ ቴክኒሻን የሚከፈለው 1 ሺህ ዶላር የማይሞላ ነው፡፡
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ድርጅት ውስጥ ሌላው በሠራተኞች ዘንድ ትልቅ ቅሬታ ሆኖ የሚነሳው የስራ ዝውውር እና እድገት ግልፅነት እና ተጠያቂነት የሌለው መሆኑ ነው፡፡ወደ ተሻለ የስራ ቦታ ለመዘዋወር እና የደረጃ እድገት ለማግኘት በአብዛኛው በቅርብ አለቃ መላካም ፍቃድ ላይ የተመሰረተ እንጂ የሥራ ውጤትን ግብ ያደረገ አይደለም ፡፡ ይህም ማለት በአየር መንገድ ድርጅት ውስጥ በሚኖሩ የስራ ክፍሎች በዋና ተጠሪነት የሚቀመጡት በአብዛኛው ለወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት ቅርብ ከመሆናቸው በላይ ለስርአቱ ደም እና አጥንታቸውን የገበሩ ናቸው፡፡ ይህ መሆኑ ደግሞ ለሰራተኛ እድገት እና ዝውውር ዋንኛ መመዘኛ በማድረግ ተመልክተው ፍቃዳቸውን የሚሰጡት የሰራተኛው የስራ ልምድ እና የት/ት ዝግጅት በመመልከት ሳይሆን፣ ለወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት ያለውን አመለካከት እና ጎሳን መሠረት ያደረገ ነው፡፡ ይህም በመሆኑ አብዛኛው የአየር መንገድ ሰራተኞች በድርጅታቸው ለሚታየው የአስተዳደር ችግሮች በቁጭት ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ የተቀሩት ደግሞ ሰራቸውን በመልቀቅ ከአገር ወጥተው ይገኛሉ፡፡
ይህ በእንዲ እንዳለ ከሰሞኑ ትልቅ አጀንዳ በመሆን መነጋገሪያ የሆነው የረዳት አብራሪ ሃይለመድህን አበራ የአውሮፕላን ጠላፍ ነው፡፡ የአውሮፕላን ጠላፍ ፖለቲካን መሰረት አድርጎ በአገራችን የተጀመረው ህዳር 29 ቀን 1965 ዓ.ም ሲሆን እነዋለልኝ መኮንን እና ማርታ መብራቱ ያካተተ ነበር፡፡የያኔው ጠላፋ ተሳክቶ ቢሆን ኖሮ ዋና አሳቡ ፖለቲካ ጥገኝነትን በመጠየቅ ከአገር ሸሽቱ ለመኖር ሳይሆን በጃንሆይ እና በአስተዳደራቸው ላይ ለተነሳው አመፅ የአውሮፕላን ጠለፋው የአመፁ የእስትራቴጂ አካል ጭምር ስለነበረ ነው፡፡
በእንዲ መልኩ የተጀመረው ፖለቲካዊ ይዘት ያለው የአውሮፕላን ጠለፋ በደርግ መንግስት ምን ያህል ተግባራዊ እንደሆን መረጃ ለማግኘት በእኔ በኩል ያልተቻለኝ ቢሆንም፤ነገር ግን የአውሮፕላን ጠለፋ በቁጥር እና በአይነት በዝቶ ፖለቲካዊ ይዘት ያለው ጠለፋ የታየው በወያኔ/ኢህአዴግ የመንግስት የአስተዳደር ወቀት ስለመሆኑ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ እንዲሁም ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ የመንገደኛ እና የጦር አውሮፕላን ካፒቴኖች በተለያየ አገር የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቀው በመኖር ላይ ይገኛሉ፡፡
በእርግጥ የእነዚህ ካፒቴኖች የፖለቲካ ጥገኝነት መጠየቅ በራሱ የእውነት ፖለቲካዊ ይዘት አለው ወይስ የለውም ለማለት ተገቢ የሆነ ጥናትና እውነታን የሚጠይቅ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ካፒቴን ተሾመ ተንኮሉ እና መስል አጋሮቹ በመንግስት ከደረሰባቸውን በደልና ግፍ በላይ በአገር ላይ የሚፈፀም በደል አላስችል ሲላቸው የፈፀሙት ገድል ሁሌም ታሪክ በበጎ የሚያስታውሰው ነው፡፡
ሌላው እና ለዚህ ጹሑፍ ዋንኛ መነሻ የሆነው አሳብ የረዳት አብራሪ ሃይለመድህን አበራ ጉዳይ ነው፡፡ እኔ ብቻ ሳልሆን ማንም ሰው በእርግጠኝነት ሊናገር የሚችለው አውሮፕላኑ ከአዲስ አበባ መነሳቱ እና ጄኔቫ ማረፉ ሲሆን፣ አውሮፕላኑ በጄኔቫ ያረፈው በታቀደው መልኩ ሳይሆን ከዚያ ውጪ በሆነ በረዳት አብራሪ ሃይለመድን አበራ ፍቃድ ብቻ መሆኑ ነው፡፡ከዚህ ውጪ ያሉ ነገሮች በአብዛኛው መላ ቅጡ በጠፋ መረጃ የተተበተበ ነው፡፡በማህበራዊ ድረ-ገፅ እና በተለያዩ የዜና ማሰራጫዎች የሚነገሩ ነገሮች በአብዛኛው የወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት ደጋፊ፣ እንዲሁም ተቃዋሚም የሆን ሁሉ ዋንኛ መነሻ አሳባብ ከራስ ጥቅም እና ፍላጎት የመነጨ ነው፡፡ ይህም ስለመሆኑ የተነገሩት እና የተለቀቁትን መረጃዎች በማየት መገንዘብ ይቻላል፡፡
የነገሩን ውስብስብነት የበለጥ የሚያገላው ደግሞ የፓይለቱ ቤተሰቦች የሚሰጡት መረጃ ነው፡፡ ለማሳየነትም እንዲረዳ እህቱ ፣አክስቱ ፣ወንድሙ እንዲሁም የአጎቱ ባለቤት እና የቅርብ ጎደኛ በጉዳዩ ላይ የሚሰጡት ቃላቸው ፈፅሞ ሊቀራረብ የማይችል ነው፡፡ በተለይ ታላቅ ወንድሙ በአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ባደረገው ቃለ መጠይቅ በአብዛኞቻቸን ዘንድ ሞቅ አድርግን ይሆናል ብለን በገመትነው ነገር ላይ ቀዝቃዛ ውሃ ነው የደፋበት፡፡
የረዳት ካፒቴን ሃይለመድን አበራ አውሮፕላኑን የጠለፈበት ምክንያት በእርግጠኝነት ልናውቅ የምንችለው ከራሱ በሚነገር እውነት ብቻ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ቀኑ የራቀ አይደለም ፤ስለዚህም ቀኑ ተጠብቁ ሙገሳውም ትችቱም ቢቀርብ ይበለጥ የተሻለ ይሆናል፡፡ እኔ በበኩሌ በዚህ ጉዳዩ ከመጀመሪያው ጀምሮ የያዝኩት አቋም ይህን ነው ፡፡
የዚህ ጹሑፍ ማጠቃለያ የሚሆነው በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚታዩ ችግሮች ዋንኛ ምክንያት የአስተዳደር የአቅም ውስንነት መሆኑ ነው፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ቀጥተኛ የሆነ የመንግስት ጣልቃ ገብነት እና ብልሹ ፖለቲካዊ የአገር አስተዳደር ነው፡፡ በመሆኑም ሥራቸውን ብቻ በማየት በሥራቸው ለደረሰባቸው በደል አየር መንገዱን ለቀው ጥገኝነት የጠየቁ፡፡ እንዲሁም ከሚከፈላቸው ዶላር በላይ ስለአገራቸው እና ስለ ህዝብ ተቆርቁረው እንቢ ለሀገሬ ብለው ለተሰደዱ ለሁሉም ተጠያቂው በስልጣን ላይ ያለው የወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት ነው፡፡
ይድነቃቸው ከበደ

ከ 70 እስከ 80 ሺህ ( የባህር ዳር ሕዝብ አንድ አራተኛ) ነዉ ለሰልፍ የወጣው !

ከ 70 እስከ 80 ሺህ ( የባህር ዳር ሕዝብ አንድ አራተኛ) ነዉ ለሰልፍ የወጣው !

በባህር ዳሩ ሰልፍ ከሰባ እስከ ሰማኒያ ሺህ ሕዝብ እንደነበረ አንድነት ገለጸ። ሰልፉ ገነ እንደተጀመረ ወደ 15 ሺ ሕዝብ አካባቢ የነበረ ሲሆን፣ ከሰልፉ መነሻ እስከ መዳረሻዉ በነበረዉ ጎዞ፣ ሕዝቡ እየተቀላቀለ፣ አስደናቂ የሕዝብ ማእበል ሊፈጠር ችሏል። ለሕዝብ ይፋ የሆኑ ታሪካዊ ፎቶግራፎች፣ ቪዲዮዎችም የሚያሳዩት ይሄንኑ ነዉ።

አንድነት ባወጣዉ መግለጫ በባህር ዳር የታየዉ አይነት በአገሪቷ በሙሉ እንደሚቀጣጠል ለዚህም በአገር ዉስጥና ከአገር ዉጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ድጋፉን እንዲሰጥ ትግሉን እንዲቀላቀል ጥሪ አቅርቧል።

በባህር ዳር የታየው ምንድን ነው ?

በዋናነት የአገዛዙን ካድሬዎችን አፍ ያዘጋዉ የሕዝቡ ሰላማዊነት ነው። የተወረወረ አንዲት ጠጠር የለም። የተሰበረ ወይንም የወደመ ንብረት የለም። የትጎደ ዜጋ የለም። ያ ሁሉ ሺህ ተሰብስቦ ፣ በሚያኮራ መልኩ ፣ ሕዝቡ በሰላም ወጥቶ ነው በሰላም የገባዉ። ይሄም የአንድነት ፓርቲ አባላት እና ደጋፊዎች «ሽብርተኞች» እያሉ ለሚከሱ የአገዛዙ ካድሬዎችና መሪዎች፣ አንድነት ፓርቲ ምን እንደሆነ በድጋሚ ያስመሰከረ ነው።

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው የውጭ ምንዛሬ እጥረት እልባት አላገኘም

-በአስመጭና ላኪ እንዲሁም በግንባታ ስራዎች ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች እንደሚገልጹት፣ በውጭ ምንዛሬ እጥረት ሳቢያ የአገሪቱ የንግድ እንቅስቃሴ በእጅጉ እየተጎዳ ነው። ምንም እንኳ መንግስት የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንዳላጋጠመ በተደጋጋሚ ቢገልጽም፣ በርካታ ነጋዴዎች ወደ ባንኮች ሲሄዱ፣ የሚፈልጉትን መጠን የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት አይችሉም። ከባንኮቹ የሚሰጣቸው መልስ ምንዛሬ የለም የሚል መሆኑን አንዳንድ ነጋዴዎች እንደሚናገሩ የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ገልጿል።
አንዳንዶች እንደሚገምቱት አገሪቱ ከውጭ ንግድ በእያመቱ እስከ 4 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት በማቀድ ብትንቀሳቀስም፣ ማሳካት የቻለችው የዚህን ግማሽ ያክል ብቻ በመሆኑ፣ አሁን ለሚታየው የውጭ ምንዛሬ እጥረት አስተዋጽኦ አድርጓል።

የስዊስ አቃቢ ህግ የረዳት ሃይለመድህን አበራን ሰብአዊ መብቶች ያከብራል ሲሉ ቃል አቀባዩዋ ተናገሩ

የሰዊስ አቃቢ ህግ ቃል አቀባይ ሚስ ያኔት ባልመር በረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ዙሪያ ከኢሳት ለቀረበላቸው ጥያቄ የምርመራ ሂደቱ ያልተጠናቀቀ በመሆኑ ዝርዝር መረጃዎችን ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸው ገልጸው፣ የሰብአዊ መብቱን በመጠበቅ በኩል ለተነሳው ጥያቄ ግን ስዊዘርላንድ የሰብአዊ መብቶችን በጠበቅ በኩል ታዋቂ አገር መሆኑዋን በመግለጽ የሃይለመድህንን የሰብአዊ መብቶች እንደሚያከብሩ ገልጸዋል።
ሃይለመድህን ጠበቃ ተቀጥሮለት ጉዳዩን በመከታተል ላይ ነው። የሃይለመድህንን የፍርድ ቤት ጉዳይ መከታተል ይቻል እንደሆን የተጠየቁት ቃል ሚስ በርነር፣ በአሁኑ ሰአት ስለፍርድ ቤት ሂደት ለማውራት ባይቻልም በስዊዘርላንድ አብዛኛውን ጊዜ ፍርድ ቤቶች በግልጽ ችሎት ጉዳዮችን እንደሚያዩ ተናግረዋል።
የሚቀጥለው የፍርድ ቤት ቀጠሮ ቀን ይታወቅ እንደሆን ሲጠየቁም ” እዛ ደረጃ ላይ ገና አልተደረሰም” በማለት መልሰዋል። የምርምራው ሂደት መቼ እንደሚጠናቀቅ ሲጠየቁም፣ የስዊስ የፍትህ አሰራር መረጃዎችን በሚስጢር መያዝን ስለሚያዝ፣ ምንም አይነት መግለጫ መስጠት እንደማይቻል አክለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ስዊዘርላንድ ለረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ጥገኝነት እንደትሰጥ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ የፊታችን አርብ ፌብሩዋሪ 28 በበርን እንደሚካሄድ በስዊዘርላንድ የ ዲሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያ የስውዘርላንድ የድጋፍ ኮሚቴ ገልጿል።

ረቡዕ 26 ፌብሩዋሪ 2014

በዋሽንግተን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለአበራሪ ሃይለ መድን አበራ ያላቸውን ድጋፍ በሰላማዊ ሰልፈ ገልጹ

በዋሽንግተን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለአበራሪ ሃይለ መድን አበራ ያላቸውን ድጋፍ በሰላማዊ ሰልፈ ገልጹ። ሰለፈኞቹ ትላንት 02/24/2014 በስዊዝ ኤምባሲ ፊት ለፊት ተሰለፈው፤ ሃይለመድን አበራ እንደ ወንጀለኛ እንዳይታይ የስዊዝን መንግስት ተማጽነዋል።
ሰለፈኞቹ፤ አብራሪው የዘጠና ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን  ፍትህ እጦት በአለም አደባባይ ይበልጥ ያስገነዘበ ጀግና ነው ሲሉም አሞካሽተውታል።

በአርማጭሆ የአንድነት ፓርቲ አባላት ከስራ ተባረሩ

የካቲት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፓርቲው አባላት በመንግስት ስራ ውስጥ ድርሻ አይኖራችሁም ተብለው መባረራቸውን የተባረሩ የፓርቲው አባላት ለኢሳት ገልጸዋል። አብዛኞቹ ለሱዳን እየተሰጠ ያለውን መሬት በተመለከተ ተቃውሞ በማሰማታቸው መባረራቸውን ገልጸዋል።

የምእራብ አርማጭሆ የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ የሆነው አቶ አንጋው ተገኝ፣ በድንበር ጉዳይ ጥያቄ በማንሳታቸው መባረራቸውን ገልጸዋል

ከተባረሩት የፓርቲው አባላት መካከል አወቀ ብርሃኑ፣ አባይ ዘውዱ ፣ አንጋው ተገኝ፣ አብርሃም ልጃለም እና አለልኝ አቡሃይ ይገኙበታል።

እሑድ 23 ፌብሩዋሪ 2014

ከ15 ሺህ ህዝብ በላይ የተሳተፈበት ሰላማዊ ሰልፍ በባህር-ዳር [ፎቶ

ተለያዩ መፈክር ያነገቡ ሰልፈኞች በባህር ዳር የአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት አካባቢ በመገኘት ሰልፉን ሲጠባበቁ ነበር በአሁኑ ሰዓት ከ15 ሺህ የሚበልጥ ህዝብ ሰልፉን ተቀላቅሏል:: የአንድነት ፓርቲ ፕሬዝዳንት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው፣ የመኢአድ ፕሬዝዳንት አቶ አበባው መሃሪ እንዲሁም የትብብር ለዴሞክራሲ ሰብሳቢ አቶ ግርማ በቀለ እንዲሁም የአንድነት ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አንጋፋው ፖለቲከኛ ዶ/ር ኃይሉ አርአያን ጨምሮ ሰልፉን በቀዳሚነት እየመሩ ይገኛሉ::
በአማራ ክልል የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የብአዴን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አለምነው መኮንን በአማራ ህዝብ ላይ የሰነዘሩትን ዘለፋ በመቃወም ነው የባህር ዳር ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ ሰላማዊ ሰልፍ ያደረገው።
ድል የህዝብ ነው!! ኢትዮጵያዊ አንድነታችን ከልዩነታችን በላይ ነው!!  ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል!!  ብአዴን የአማራውን ሕዝብ አፍኖ መግዛት ያቁም!! የኢሀደግ አምባገነን አገዛዝ ሰልችቶናል!! የሚሉ መፈክሮችን እያሰሙ ይገኛሉ።
 

ዓርብ 21 ፌብሩዋሪ 2014

ፍኖት - የከተማዋ ነዋሪዎችም በብአዴን ላይ ቁጣቸውን ለመግለፅ እሁድን እየጠበቁ ነው


አንድነትና መኢአድ ብአዴንና አመራሮቹን በመቃወም እሁድ የካቲት 16 በባህር ዳር ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ መጥራታቸው ያሳሰበው ገዢው ፓርቲ አቶ አለምነው መኮንን ትላንት ማስተባበያ እንዲሰጡ ማስደረጉ የባህርዳር ነዋሪዎች እንደ አዲስ ሰውውን የጥላቻ ንግግር በስፋት እንዲደመጥ ምክንት መሆኑንን የፍኖተ ነፃነት ዘጋቢ ያነጋገራቸው ከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

ዘጋቢያችን በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች እየተዘዋወረ እንደታዘበውም የአቶ አለምነው ንግግር በባህር ዳር እንደ አዲስ የመወያያ አጀንዳ መሆኑን ታዝቧል፡፡ በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎችም በብአዴን ላይ ቁጣቸውን ለመግለፅ እሁድን እየጠበቁ ነው፡፡ ብአዴን ከአቶ አለምነው ማስተባበያ ውስጥ የተቀነጨበ መልእክት የያዘ በራሪ ወረቀት ከትላንት አመሻሽ ጀምሮ በባህር ዳር እንዲሰራጭ በማድረግ ላይ መሆኑ ታወቃል፡፡

የብአዴንን አመራር ለመቃወም ቅስቀሳው ጫማ በማውለቅ በባዶ እግር ታጅቦ ቀጥሏል ፤ፖሊስ ቅስቀሳውን ሊያስቆም ቢሞክር...

አንድነት እና መኢአድ፤ በባዶ እግራቸው በመሆን በባህርዳር ቅስቀሳ እያደረጉ ነው።

አንድነት እና መኢአድ፤ በባዶ እግራቸው በመሆን በባህርዳር ቅስቀሳ እያደረጉ ነው።
የአማራ ክልሉ ባለስልጣን፤ “አማራው በባዶ እግሩ ነው የሚሄደው…” ብለው እጅግ የከፋ ዘለፋ ካሰሙ ብኋላ ህዝቡ በያለበት ስለ ሰውዬው ያፈረላቸው ቢሆንም እርሳቸው ግን ሳያፈሩ ትላንት በቴሌቪዥን መስኮት ተከስተው ሲያስቁን ነበር።
ዛሬ እንደሰማነው እና እንዳየነው፤ የመኢአድ እና አንድነት አባላት እሁድ ለጠሩት ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ፤ በባዶ እግራቸው በመሆን ባደረጉት ቅስቀሳ “እኛም ጫማ የለንም፤ እኛም በባዶ እግራችን ነው የምንሄደው ቢሆንም ግን የሞራል ለዕልና አለን” የሚል ቅስቀሳ ሲያሰሙ ውለዋል።
በቅስቅሳው ወቅት ፖሊስ ጉልቤውን ሊያሳያቸው ቢሞክርም ህዝቡ ከበባ እያደረግ ሲከላከላቸው አንድነት ዛሬ ከለቀቀው ቪዲዮ አይተናል።
ድረ ገጻችን፤

ሰኞ 17 ፌብሩዋሪ 2014

BREAKING: Ethiopian Airlines’ Flight 702 Hijacked. Lands in Geneva.

BREAKING: Ethiopian Airlines’ Flight 702 Hijacked. Lands in Geneva.


The unusual flight path the hijacked aircraft took prior to its safe landing. Image - Flightradar24
Photo of the Boeing 767 (reg ET-AMF) that could be possibly hi-jacked as flight ETH702 – Photo: Fabrice Clerc | Flicker CC
At 5:00pm Pacific Time, Ethiopian Flight 702, a Boeing 767-300 was flying over Sudan when it started squawking 7500. The transponder code, is supposed to indicate a “hijacking.”
Sometimes, pilots accidentally switch to this code or equipment malfunctions. This however, does not appear to be the case. The aircraft can be tracked live via Flightradar 24.
This was hopefully just an error, but this iwascertainly a deviation from normal flight.
We have reached out to a source who is an aircraft electrical expert and they confirmed that a “7500″ code can’t come from a glitch.
The flight, operating from Addis Abba to Rome has been confirmed by Rome Airport not to have arrived yet.  It is currently circling over Geneva Airport (GVA), with a military escort.  Emergency crews are standing by a GVA.

እሑድ 16 ፌብሩዋሪ 2014

የጎንደር ከተማ የታክሲ ሹፌሮች የስራ ማቆም አድማ መቱ

-የታክሲ ሹፌሮች አድማውን የመቱት አዲሱን የትራፊክ የቅጣት ደንብ በመቃወም ነው።
በከተማው መሃል ላይ አሽከርካሪዎቹ ተሰብስበው የመኪና ጥሩምባ ማጮሃቸውን የገለጸው የኢሳት ወኪል፣ ከሰአዓታት በሁዋላ ታክሲዎቹ ከአደባባይ ላይ በመሰወራቸው ነዋሪዎች ታክሲዎችን ለማግኘት ሲቸገሩ ታይቷል።
የገዢው ፓርቲ ሰዎችና ትራፊኮች፣ በመንገድ ላይ ያገኙትን ታክሲ በማስገደድ ሰዎችን እንዲጭን ለማድረግ ሞክረዋል። ፈቀደኛ ያለሆኑ ሾፌሮች ጥያቄዎች ይቀርቡላቸው ነበር። አዳመው ለምን ያክል ቀናት እንደሚቆይ ግልጽ የሆነ ነገር የለም።
በሌላ በኩል በነዳጅ ምርቶች ላይ ሰሞኑን የተጣለው እጅግ ከፍተኛ ጭማሪ  በቋፍ ላይ የሚገኘውን የህብረተሰቡን ኑሮ ይበልጥ አስከፊ እንዳደረገው የኢሳት የ አዲስ አበባ ሪፖርተር ዘግቧል።
በቤንዚን ምርቶች ላይ በ አንድ ሊትር  እስከ 45 ሳንቲም፣ ለማገዶነት በሚውለው በኬሮሲን ምርት ላይ በ አንድ ሊትር  እስከ 75 ሳንቲም የተጣለው የሰሞኑ ይፋዊ ያልሆነጭማሪ፣ በነዳጅ ጭማሪ ታሪክ እጅግ አስደንጋጭና ከፍተኛ  ጭማሪ እንደሆነ ነዋሪዎች በምሬት እየተናገሩ ነው። የታክሲ ትራንስፖርት አገልግሎት ከ0.5 ሳንቲም እስከ 0.15 ሳንቲም ጭማሪ ተደርጎበታል፡፡
ሀቁ ይህ በሆነበት ሁኔታ የመንግስትና የድርጅት ሚዲያዎች አስደንጋጩን የነዳጅ ጭማሪ “መጠነኛ ጭማሪ” እያሉ ሲያወሩ መሰማታቸው፤ በህብረተሰቡ ቁስል ላይ ተጨማሪ እንጨት እንደመስደድ ነው ይላሉ ነዋሪዎቹ።

የአዲስ አበባ እድሮች ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በድጋሜ መዋጮ እንዲያዋጡ ታዘዙ

-የአዲስ አበባ መስተዳድር የካቲት 2፣ 2006 ዓም ከእድር ተጠሪዎች ጋር ባደረጉት ስብሰባ እያንዳንዱ እድር በነፍስ ወከፍ 8 ሺ ብር ለአባይ ግድብ ማሰሪያ እንዲከፍል ታዟል።
ትእዛዙ የተጣለው የካቲት 2 ቀም 2006 ሲሆን፣ 650 እድሮች በነፍስ ወከፍ 8 ሺ ብር ይከፋላሉ። በዚሁ ከላይ በወረደው መመሪያ መንግስት ከእድሮች በአንድ ጊዜ 5 ሚሊዮን 200 ሺ ብር ይሰበስባል።
ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ሰው እድሮች በፈቃዳቸው መለገስ ሲችሉ፣ በግዴታ ገንዘብ እንዲያዋጡ መደረጉ በአንጻራዊ መልኩ ገለልተኛ በሚባሉት እድሮች ሳይቀር ጣልቃ እየገባና እየመራ ነው ብለዋል።

ዓርብ 14 ፌብሩዋሪ 2014

"በርካታ ወጣቶች ወደ ማዕከላዊ እስር ቤት እየተጋዙ ነው"

ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ አሸባሪ ካላቸው ግንቦት ሰባት እና ሌሎች ፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ በርካታ የአዲስ አበባና አማራ ክልል ወጣቶች ወደ ማዕከላዊ እስር ቤት እየተጋዙ መሆኑን የአይን እማኞች ተናገሩ፡፡
ኢህአዴግ በጀመረው አዲስ አሰሳ በሀገሪቱ አንድንድ ቦታዎች ኢንተርኔትን ጨምሮ ስልክ እንዳይሰራ የተደረገ ሲሆን በአንዳንድ አካባቢዎችም የመከላከያ ሀይል ተበትኗል፡፡ የዚህን ዜና ዝርዝር በሌላ ጊዜ ይዘን እንቀርባለን። በሌላ ዜና ደግሞ ብአዴን ከፍተኛ የሞራል ውድቀት የደረሰበት መሆኑን ምንጮች ገለጹ።
የብአዴን የጽፈት ቤት ሃላፊ እና የአማራ ክልል ም/ል ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ አለመነው መኮንን የሚመሩት ህዝብ ጸያፍ ስድብ መሳደባቸውን ተከትሎ ብአዴን የሞራል ውድቀት እንደደረሰበት ከክልሉ የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
የክልሉ ህዝብ ያሳየው ቁጣና በብአዴን የንግድ ድርጅቶች ላይ የጣለው ማእቀብ ያሰጋቸው አቶ በረከት ስምኦን ወደ ባህርዳር በማቅናት ፣ የደረሰውን ኪሳራ ለመቋቋም ያስችላሉ የሚሉዋቸውን አማራጮች ሁሉ ለመጠቀም ከሌሎች አመራሮች ጋር እየመከሩ ናቸው።
የብአዴን አመራሮች ባደረጉት የመጀመሪያ ግምገማ “የአማራ ህዝብ ፊት ለፊት የምንናገረውና ከጀርባ የምንናገረው ነገር የተለያየ ነው” ብሎ እንዲያስብና እምነቱን እንዳይጥልብን አድርጓል” ብለዋል። ብአዴን በመጪው ምርጫ ላይ በክልሉ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ኪሳራ ሊደርስበት እንደሚችልም በግምገማው ወቅት ተነስቷል።
የክልሉ ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከአማራ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ፣ በኢሳት የቀረበው የአቶ አለምነው ድምጽ አይደለም ብለው ማስተባበል ሳይችሉ ቀርተዋል። ፕሬዚዳንቱ በባህርዳር ስብሰባ መካሄዱንና ድምጹም በጊዜው የተቀረጸ መሆኑን በተዘዋዋሪ መንገድ ያመኑ ሲሆን፣ መክትላቸው የተናገሩትን በቀጥታ ከማስተባበል ይልቅ አቶ አላምነው ለአማራው ህዝብ ስላላቸው ፍቅር መግለጽን መርጠዋል።
አቶ አለምነው እራሳቸው ቀርበው ለምን መግለጫ እንዲሰጡ እንዳልተፈለገ ግልጽ አይደለም። የክልሉ ህዝብ የብአዴን ንብረት የሆነውን ዳሸን ቢራን እንዳይጠጣ የሚደረገው ቅስቀሳ አግባብ አይደለም ሲሉ አቶ ገዱ ተናግረዋል።
ድርጊቱን ያወገዙት አንድነትና መኢአድ የካቲት 16 ቀን 2006 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ደብዳቤ ማስገባታቸው ታውቋል። ፓርቲዎቹ በጋራ ባወጡት መግለጫ ” ህዝብ ያዋረዱ አመራሮች በተገቢው ፍጥነት ለፍርድ እስኪቀርቡ ድረስ የተቃውሞ ሰልፉ በሌሎች የሀገራችን ክፍሎችም ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል” ብለዋል፡፡
የተቃውሞ ሰልፉ ከጣቱ በሶስት ሰአት ከቀበሌ 12 ( ግሽ አባይ ተነስቶ)፣ በክልሉ መስተዳድር ጽ/ቤት ከቀኑ ስምንት ሰአት ላይ ያበቃል። የባህርዳር እና አካባቢዋ ህዝብ በስፍራው ተገኝቶ የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት በህዝቡ ላይ ያወረዱትን ዘለፋ እንዲያወግዝ ፓርቲዎቹ ጠይቀዋል።

ረቡዕ 12 ፌብሩዋሪ 2014

የጋዜጠኛው ጥያቄ ጠ/ሚኒስትሩን አስቆጣ

ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ  በጽ/ቤታቸው ለአገር ውስጥ ጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ከፎርቹን ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር አቶ ታምራት ገብረጊዮርጊስ በቀረበላቸው ጥያቄ በመቆጣት ዘለፋ ሰነዘሩ፡፡
አቶ ታምራት ለጠ/ሚኒስትሩ ያቀረቡት ጥያቄ በአሁን ሰዓት አገሪትዋን የሚመራት ማንነው ነው የሚል ይዘት ያለው ሲሆን ጠ/ሚኒስትሩም ብስጭታቸውን በምላሻቸው ወቅት አንጸባርቀዋል፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ ለዚህ ጥያቄ ቀጥተኛ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ጋዜጠኛውን ሂድና እዚያ ሐሜት የምትጽፍበት ገጽ ላይ ጻፈው በማለት መዝለፋቸው በርካታ ጋዜጠኞችን አስደንግጦአል፡፡
አንዳንድ ጋዜጠኞች ስለሁኔታው በሰጡት አስተያየት ጋዜጠኛ ታምራትን በማድነቅ አንድ ጋዜጠኛ በሕዝብ ውስጥ የሚነገርን ጥያቄ አውጥቶ መጠየቁ ተገቢና ሙያዊ ሃላፊነቱ መሆኑን በመጥቀስ ጠ/ሚኒስትሩ ጥያቄው የቱንም ያህል ቢያበሳጫቸው በዚህ መልኩ ምላሽ መስጠታቸው ራሳቸውን ከማስገመት ያለፈ ትርፍ እንደሌለው ተናግረዋል፡፡
ከአቶ መለስ ሞት በሃላ ወደስልጣን የመጡት አቶ ኃይለማርያም ቀደም ሲል በአቶ መለስ ብቻ ሲመራ የነበረውን የጠ/ሚኒስትር ስልጣን የጋራ አመራር በሚል ፈሊጥ ሶስት ቦታዎች በመክፈልና በምክትል ጠ/ሚኒስትር ማዕረግ ለኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ስልጣናቸው ማከፋፈላቸው በሕዝብ ዘንድ ያለስልጣን የተቀመጡ አሻንጉሊት መሪ እስከመባል አድርሶአቸዋል፡፡
ጠ/ሚኒስትሩ በዚሁ መግለጫቸው ብዙ ሲባልበት የቆየውን ኢትዮ ሱዳን ድንበር ማካለል ጉዳይ ከውይይት ያለፈ ነገር እንደሌለ በመናገር የሚደርስባቸውን ትችቶች ያጣጣሉ ሲሆን አጀንዳውንም ከመጪው ምርጫ ጋር በማያያዝ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚደረግ ሙከራ መሆኑን ለመናገር ሞክረዋል፡፡ በኢትዮ ሱዳን ድንበር ማካለል ጉዳይ በስፋት የዘገቡትና ሒደቱንም ያሳወቁት የሱዳን ጋዜጦች መሆናቸውን በተመለከተ ያሉት ነገር የለም፡፡
ከኢህአዴግ ጋር በመደራደር አገር ውስጥ ገብተዋል ስለተባሉትም አቶ ሌንጮ ለታ ተጠይቀው ዋሽንግተን ለሚገኘው ኢትዮጽያ ኤምባሲ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ከመስማታቸው ውጪ ስለመግባታቸው የሚያውቁት ነገር እንደሌለ በመናገር ጉዳዩን አስተባብለዋል፡፡

አንድነት እና መኢአድ ብአዴንን በመቃወም የተቃውሞ ሰልፍ ጠሩ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ብአዴንን በመቃወም በባህርዳር ከተማ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ጠሩ፡፡ ፓርቲዎቹ ነገ በ4 ሰዓት በአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት በጋራ መግለጫ እንደሚሰጡ ይጠበቃል፡፡ ለተቃውሞ ሰልፉ አስፈላጊው የማሳወቅ ተግባር መጠናቀቁ ታውቋል፡፡

አንድነትና መኢአድ እሁድ የካቲት 16 ቀን 2006 ዓ.ም የጠሩት የተቃውሞ ሰልፍ መነሻ ምክንያት እንዲያስረዱ በፍኖተ ነፃነት የተጠየቁት የአንድነት ፓርቲ የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ሰለሞን ስዩም “አማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የብአዴን የጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን የአማራን ህዝብን ክብር የሚያዋርድና በለሌሎች ብሔረሰቦች በክፉ እንዲታይ የሚያደርግ የጥላቻ ንግግር በማድረጋቸውና ብአዴንም እንደ ፓርቲ ማስተባበያም ሆነ የማስተካከያ እርምጃ ባለመውሰዱ የግለሰቡን አቋም እንደሚጋራ ያመለክታል” ብለዋል፡፡
የመኢአድ ም/ፕሬዝደንት አቶ ተስፋዬ መላኩ በበኩላቸው “የአማራ ህዝብን እየመራሁ ነው እያለ እንደዚህ አይነት አስነዋሪ ንግግር ያደረገውን ባለስልጣና የሚወክለውን ፓርቲ ለማውገዝ እንዲሁም ለህግ እንዲቀርብ ለመጠየቅ ነው ሰልፉ የተጠራው” ብለዋል፡፡
የፓርቲዎቹ የባህርዳርና አካባቢዋ መዋቅሮች የተቃውሞ ሰልፉን ለማስተባበር ዝግጅታቸውን ያጠናቀቁ ሲሆን የባህርዳር ከተማና የአካባቢዋ ህዝብ በነቂስ በመውጣት በሰልፉ ተቃውሞውን እንዲገልፅም ጥሪ አቅርበዋል፡

እሑድ 9 ፌብሩዋሪ 2014

Home » ዜናዎች... » ጉራማይሌ ፖለቲካ ! ( ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ) ጉራማይሌ ፖለቲካ ! ( ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ )

በምንወዳት ኢትዮጵያችን ከኑሮ እስከ ሮሮ፤ ከማሕበራዊ እስከ ፖለቲካ፤ ከኢኮኖሚ እስከ ትምህርት ፖሊሲ፤ ከመንፈሳዊ እስከ ዓለማዊ… ያሉ ጉዳዮች ጉራማይሌነት ከቀን ወደ ቀን እየጎላ ነው፡፡ በዚህ ፅሁፍም ጥቂት ያህል ማሳያዎችን በአዲስ መስመር እንመለከታለን፡፡Journalist Temasegan Dasaleg
ጎንደር እና ጥምቀት
የሁሉም መነሻና መድረሻ ዓላማ መንፈሳዊ ይሁን እንጂ እንደ መስቀል፣ ጥምቀትና ሬቻ… ያሉ አንዳንድ በዓላት ከመንፈሳዊነታቸው በተጨማሪ የባሕል መገለጫ እስከመሆን ደርሰዋል፡፡ ከዚህ የተነሳም በዓላቶቹ በሚከበሩባቸው ቦታዎች የሚገኘው ስፍር ቁጥር የሌለው ሕዝብ፣ ሰማያዊውን ፅድቅ ብቻ ሳይሆን፣ በባህላዊው አከባበርም በእጅጉ ስለሚማርክ ጭምር ነው፡፡
የሆነው ሆኖ በወዳጆቼ ጋባዥነት የዛሬ አስራ አምስት ቀን በጎንደር ከተማ በተከበረው የጥምቀት በዓል ላይ ተገኝቼ ነበር፤ በወቅቱም የታዘብኩት ጉዳይ ከሺህ ዓመታት በፊት የተፈፀመ አንድ ክስተትን እንዳስታውስ ገፊ-ምክንያት ሆኖኛል፤ ይኸውም በዘመነ ኦሪት የምድረ ባቢሎን ሰዎች አምላካቸውን ከመንበረ ሥልጣኑ ለመገልበጥ አሲረው ወደ ሰማይ የሚያወጣቸውን ታላቅ ግንብ መገንባት የጀመሩ ጊዜ አምላክ በድርጊታቸው ተቆጥቶ ቋንቋቸውን በማደበላለቁ ውጥናቸው በአጭር እንደተቀጨባቸው በመፅሀፉ የተተረከ ነው፡፡ …እነሆም ይህ በሆነ ከሺህ ዓመታት በኋላም የጎንደር ሕዝብ እና መንግስት በአንድ አደባባይ፣ በአንድ ድግስ ላይ ከመቼውም ጊዜ የበለጠ የመግባባት መንፈስ ርቆባቸው፣ ጉራማይሌነታቸው ደምቆ አስተውያለሁ፡፡
እንደሚታወቀው ኢህአዴግ መራሹ-መንግስት ከበረሃ ‹የብሔር ፖለቲካ› የተሰኘ መርዝ ቀምሞ መምጣቱ ሳያንስ፣ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ሰንደቃችን (ባንዲራችን) ላይም ኮከብ ይሉት ዲሪቶ ለጥፎ ‹ጨው ቢጠቀለልበት፣ ስኳር ቢቋጠርበት… ምንድን ነው? ያው ጨርቅ ነው!› ማለቱ ብዙሃኑን ኢትዮጵያዊ እጅግ አስቆጥቶት ነበር፡፡ በነዚህና መሰል ድርጊቶቹም የተነሳ ግንባሩ በሀገር ጉዳይ ላይ ዛሬም ድረስ መናፍቅ ተደርጎ ተቆጥሯል፤ ደግሞም ነው! ምክንያቱም ያቺ ልባችንን በደስታ የምትሞላው ባንዲራ እስከ ደርግ ውድቀት ጧትና ማታ በክብር ስትሰቀልና በክብር ስትወርድ ነው የኖረችው፡፡ ያን ጊዜ በየመንገዱ መኪና ውስጥ ያለው ከመኪናው ወርዶ፣ እግረኛውም የደረሰበት ቦታ ላይ ቀጥ ብሎ ቆሞ፣ ጠዋት ከፍ አድርጎ ሲያውለበልባት፣ አመሻሻ ላይ ደግሞ በዝማሬ አውርዶ በክብር አጣጥፎ ሲያስቀምጣት ማየት በእውነቱ ልብን በከፍተኛ ሃሴት ይሞላ እንደነበር አይዘነጋም፡፡
ግና! ዛሬ ዘመን ተቀይሮ፣ ታሪክ ተሽሮ ስንት የደም መስዋዕትነት የተከፈለባት ውድ ባንዲራችን በተሰቀለችበት ዞር ብሎ የሚያያት ጠፍቶ ተበጫጭቃ ሰርግ ቤት የተጎዘጎዘ ወረቀት መስላ መታየቷ በቁጭት አንገብግቦ፣ በሀዘን ልብ ይሰብራል፡፡ እናም ብዙሃኑ ባንዲራ የሚያውለበልብበት አጋጣሚ በተፈጠረ ቁጥር ከፍ የሚያደርጋት ያችኑ ንፅኋን (የድሮዋን) ሰንደቅ ሆኖ ዘልቋል፡፡ ይሁንና ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ ድንገት ከእንቅልፉ የባነነው ኢህአዴግ በየትኛውም ጊዜና ቦታ ሁሉ መውለብለብ ያለበት ኮከብ የታተመበት ባንዲራ ብቻ እንዲሆን በአዋጅ እስከመደንገግ ደርሷል፡፡ ይህንንም አዋጅ ተከትሎ በተለይም አዲስ አበባን ጨምሮ በዋና ዋና ከተሞች ባንዲራን በተመለከተ ጠበቅ ያለ ቁጥጥር ሲያደርግ ተስተውሏል፡፡
ሰሞኑን በጎንደር ከተማ ያያሁት ግን የዚህን ተቃራኒ ነው፤ ባንዲራችን የባህላዊም ሆነ ኃይማኖታዊ በዓላት ዋነኛ አድማቂ መሆኗ ነባር ልማድ ነው፤ እናም ጎንደር ላይ ዘንድሮ የጥምቀት በዓል በተከበረበት ወቅት በታቦታቱ ዙሪያ በተለያየ መልኩ የተዘጋጀውም ሆነ ሕዝቡ ያነገበው ሰንደቅ፣ አገዛዙ ‹‹ከዚህ ውጪ…›› ብሎ ለእስር እንደሚዳርግ በአዋጅ የለፈፈለትን ባለ ኮከቡን አይደለም፤ ይልቁንም በብዙሃኑ የሀገሬ ሕዝብ ልብ ላይ የታተመችውን ያችን ንፁህ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ባንዲራ ብቻ ነበር፡፡ …ኩነቱም የፓርቲ ‹ፖለቲካዊ ፍቺ› ሰጥቶ ሰንደቁን ላዥጎረጎረው ኢህአዴግ ‹‹እመራዋለሁ›› ከሚለው ሕዝብ ያለውን ዕርቀት አመላካች ሆኖ አልፏል፡፡
ሌላው የዕለቱ ጉራማይሌ ክስተት በተለያየ ቅርፅ የተሰሩ፣ የኢትዮጵያን መልከዓ-ምድር የሚያሳዩ ሶስት ግዙፍ ካርታዎች በመኪኖች ላይ ተጭነው ለዕይታ አደባባይ መቅረባቸው ነው፤ እነዚህ ካርታዎች የሚያመላክቱት የሀገራችን ሰሜናዊ ድንበር መለስ ዜናዊ እና ጓደኞቹ ትግራይ ላይ ተገድቦ እንዲቀር ከሻዕቢያ ጋር የተዋዋሉበትን አይደለም፤ ስመ-ጥሩው ጀግና አሉላ አባነጋ ጦሩን ሰብቆ ‹ቼ ፈረሴ› ብሎ እስከጋለበበት ቀይ ባህር ድረስ የሚዘረጋውን የቀድሞውን የኢትዮጵያ ይዞታ ያካተተ እንጂ፡፡
ይህ መሳጭ ትዕይንትም ሕዝብና መንግስት ያለፉትን ሃያ ሁለት ዓመታት መደማመጥ የማይችሉ (ቋንቋቸው የተደበላለቀባቸው) ሆነው እዚህ እንደደረሱ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡ ለዚህ አይነቱ ጉራማይሌ ግንኙነት ገፊ-ምክንያት ደግሞ የጎንደር ሕዝብ ሕገ-ወጥ በመሆኑ አልነበረም፤ ገዥው ፓርቲ ይቺን ሀገር ለመመስረት እልፍ አእላፍ ቀደምት አባቶች የሞቱላትን፣ ታሪክ የተሰራባትን ባንዲራ በማን አህሎኝነት ያሻውን የለጠፈባት ከመሆኑም በላይ የኢትዮጵያን ጥቅም ያላስከበረ የሀገር ግንጠላ ላይ መሳተፉ የፈጠረው ቁጭት ነው፡፡
…መቼም የዕለቱን ኩነት ቋራ ሆቴል በረንዳ ላይ ከእኛ በጥቂት ሜትሮች ዕርቀት ተቀምጦ ቁልቁል ሲከታተል የነበረው በረከት ስምዖን የተጠናወተው የእብሪት ፖለቲካ አይነ-ልቦናውን ካልጋረደበት በቀር ይህ ጉዳይ የሚያስተላልፍለት አንዳች አገራዊ ምስጢር ያለው መሆኑ አይጠፋውም፡፡
ዛሬም መሬት ማስወሰዱ ቀጥሏልን?
ከእነዚህ ክስተቶች በተጨማሪ በአካባቢው የተመለከትኩት ከባድ ውጥረት አለ፤ ይኸውም ‹ለሱዳን ሊሰጥ ነው› እየተባለ የሚነገርለት የመሬት ጉዳይ ካመጣው ጣጣ ጋር የሚጋመድ ነው፤ በርግጥ በአንዳንዶች ዘንድ መሬቱ ወደ ውስጥ ስልሳ (60)፣ ወደ ጎን ደግሞ አንድ ሺህ (1000) ኪሎ ሜትር ድረስ እንደተሰጠ ይታመናል፡፡ ይሁንና በግሌ ይህ ክስ ማረጋገጫ የሚቀርብበት ሆኖ አላገኘሁትም፡፡
በጉዳዩ ላይ ምክንያታዊ ለመሆንም በዚህ በተጠቀሰው የመሬት ስፋት ውስጥ ሊካተቱ የሚችሉ ከተሞችን መመልከቱ የተሻለ በመሆኑ፣በቀጥታ ከሱዳን ጋር ከሚዋሰኑ ሁለት ከተሞች አንስተን እናስላው፤ እናም ከመተማ ከተነሳን ሸህዲን፣ ወህኒ፣ ነጋዴ ባሕር እያልን ጭልጋን እናገኛለን፡፡ መነሻችን ከሌላኛው የወሰን ከተማ ተሂ ከሆነ ደግሞ ምንጁግጁግ፣ ወዲ በርዚን፣ ኩሊት፣ ሸንፋ፣ ማሕበረ-ስላሴ ገዳምን አልፈን ደንገል እንደርሳለን፡፡ እንግዲህ የሰማነው ወሬ እውነት ከሆነ እነዚህ መሬቶች ሁሉ ለሱዳን ተሰጥተዋል ማለት ነው፡፡ ግን ለምን?
ኢህአዴግ እንዲህ ሙጭጭ ብሎ የያዘውን ሥልጣን ሊያሳጣው የሚችል ውሳኔ ላይ ለመድረስ (ከተሞቹን ለሱዳን ለመስጠት) የተገደደበት ምን ምክንያት አለ? በነገራችን ላይ ይህ አስተያየት ስርዓቱ ለሀገር ጥቅም ይቆረቆራል እንደማለት አይደለም፡፡ ምክንያቱም በሆነ ክፉ ቀን ሥልጣኑን አጣብቂኝ ውስጥ የሚከት ሁኔታ ከገጠመው ሀገር ከመበታተንና ከማፈራረስ የሚመለስ አለመሆኑን የቀድሞው ተሞክሮዎቹ ይነግሩናል፡፡
የሆነው ሆኖ ሊተኮርበት የሚገባው ኢህአዴግ እስከአሁን በጉዳዩ ላይ ምላሽ ሳይሰጥ ያደፈጠበት አንዳች የሸሸገው ሚስጥር ቢኖር ነው የሚለው ይመስለኛል፤ የዚህ መነሻ ምክንያታችን ደግሞ ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ በድብቅ ለሱዳን የሰጣቸው (ዛሬ ተወሰዱ ከሚባሉት ውስጥ የማይካተቱ) መሬቶች የመኖራቸው እውነታ ነው፤ ይኸውም ብአዴን የመሰረተው ‹‹ዘለቀ እርሻ›› የተሰኘው ድርጅት በአንድ ወቅት ያስተዳድራቸው የነበሩት አብደረግ እና ደሎል (ሽመል ጋራ እና ምዕራብ አርማጭሆ) ውስጥ በቁጥር ከአንድ እስከ ስምንት የተሰየሙ ግዙፍ የእርሻ መሬቶች ነበሩ፤ ይሁንና በአሁኑ ወቅት ከቁጥር ሁለት እስከ ስምንት ያሉትን (በድምሩ ወደ ሁለት መቶ ሺህ ሄክታር የሚደርሱ) መሬቶችን አሳልፎ ሰጥቷል፤ ይህንንም ተከትሎ ‹‹ዘለቀ እርሻ›› እንቅስቃሴ አልባ ሆኗል፡፡ በርግጥ ‹ቆራጦቹ› የብአዴን አመራሮችም ቢሆኑ እንዲህ አይነቱን ጥሬ ሀቅ አይክዱም፤ ይልቁንም ‹ቀድሞውንም ግማሹ ይዞታ የእነርሱ ነበር› ብለው ያስተባብላሉ እንጂ፡፡ …ግና! ማን ነበር ‹‹ከሱዳን ነጥቀን የወሰድነው መሬት አለ!›› ያለው? መለስ ዜናዊ ይሆን?
እንዲሁም ‹‹ስናር›› የተባለው ከፊል ቦታ ለሱዳኖች መሰጠቱን ከታማኝ ምንጭ ሰምቻለሁ፤ ርግጥ ስናርን ሱዳኖች እንዲቆጣጠሩት በር የተከፈተላቸው የደርግ መንግስት በወደቀበት ማግስት (በ1983 ዓ.ም መጨረሻ) ነው፤ የዚህ ስጦታ መግፍኤ በትግሉ ዘመን ሱዳን ኢህአዴግን ‹አቅፋና ደግፋ› ለድል እንዲበቃ ያበረከተችው ውለታን ታሳቢ ያደረገ እንደሆነም ይነገራል፡፡ እናም ሱዳኖች እንደ መና የወረደላቸውን ያልታሰበ ገፀ-በረከት ለመጠበቅ ወደ አስራ ሁለት ገደማ የሚደርሱ ወታደራዊ ካምፖችን መስርተው እስከ 1988 ዓ.ም
ድረስ የምድሪቱን በረከት ሲቀራመቱ መቆየታቸው እውነት ነው፡፡
ይሁንና በ1988 ዓ.ም በወቅቱ የሱዳን መንግስት አፈ-ጉባኤ የነበረው ሃሰን አል-ቱራቢ እጅ እንዳለበት የተጠረጠረውን በአዲስ አበባ በቀድሞ የግብፅ ፕሬዚዳንነት ሆስኒ ሙባረክ ላይ የተቃጣውን የግድያ ሙከራ ተከትሎ ኢትዮጵያና ሱዳን (በተለይም ተጠርጣሪዎችን አሳልፎ በመስጠትና ባለመስጠት ጉዳይ) ግጭት ውስጥ ይገባሉ፡፡ ይህን ጊዜም ኢህአዴግ የአካባቢውን አርሶ አደሮች ‹‹መሬታችሁን አስመልሱ›› በሚል ቀስቅሶ በሱዳናውያን ላይ ያዘምታቸውና ድል ያደርጋሉ፤ ስናርም ተመልሳ በኢትዮጵያውያን ይዞታ ለመጠቃለል በቃች፡፡ ግና! አሁንም እንቆቅልሽ በሆነ ሁኔታ (ከ1999 እስከ 2000 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ) እንደገና ወደ ሱዳን ተላልፋ ተሰጠች፤ በነገራችን ላይ ስናር በሃያ ስድስት ‹‹ኮርድኔት›› የተከፋፈለች ስትሆን፣ ዛሬ የኢትዮጵያውያን ይዞታ ሊባል የሚችለው ‹‹ኮርድኔት 24›› በተሰኘው ውስጥ ባለፈው ዓመት ህይወታቸው ያለፈውና በርካታ ታጣቂዎችን ማስከተሉ የሰመረላቸው ባሻ ጥበቡ እና አስመሮም መኮንን የተባሉ ግለሰቦች ለሱዳናውያን ሳያስረክቡ፣ በራሳቸው ኃይል ተገዳድረው ያቆዩት መሬት ነው፡፡ በተቀረ በአካባቢው የምናገኛቸው ኢትዮጵያውያን ከሱዳናውያን ላይ በአረብኛና እንግሊዘኛ በተፃፈ ውል በተከራዩት መሬት ላይ ብቻ ነው፡፡
በአናቱም በአሁኑ ወቅት ለሱዳን ሊሰጡ ነው እየተባለ የሚነገረው እንደ መተማ-ዮሀንስ፣ ዳፋ፣ ሽመል ጋራ፣ ፎርኹመር፣ አብዱራፊ፣ ነፍስ ገብያ፣ አለቃሽ (በረሃማ አካባቢ ነው)… የመሳሰሉ ከተሞች ስማቸው ተደጋግሞ በመነሳቱ፣ አካባቢውን ውጥረት ውስጥ ከትቶታል፡፡ በርግጥም ከአገዛዙ ያደረ ታሪክ አኳያ መሬቶቹን አይሰጥም ተብሎ አይታሰብም፤ በተለይም ጉዳዩን ለጥጠን የሰሜን አፍሪካ አብዮት በፈጠረበት ስጋት፣ በድንገቴ ውሳኔ እየገነባ ካለው የ‹‹ህዳሴ ግድብ›› ጋር አነፃፅረን ካየነው፣ የሱዳንን ድጋፍ ለማግኘት መሬቶቹን አሳልፎ
ሊሰጥ ይችላል ወደሚል ጠርዝ እንገፋለን፡፡ …ግና! ይህ አይነቱ ኢህአዲጋዊ ድፍረት ‹‹አባትየው ቢሞት የለም ወይ ልጅየው?›› በሚል ሕዝባዊ ተቃውሞ መቀስቀሱ አይቀሬ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ዛሬ ‹‹ተሰጡ›› ወይም ‹‹ሊሰጡ›› ነው ብለን የምንጫጫባቸው መሬቶች ‹‹የይገባኛል›› ጥያቄ ያልቀረበባቸው በመሆኑ፣ ኦቦ ሌንጮ ለታ ‹በባሌ ሲጠብቁን፣ በቦሌ ገባን› እንዲል፣ ስርዓቱ ሆነ ብሎ ከእውነታው አርቆ ለማደናገር የሚጠቀምባቸው አጀንዳዎች ሊሆኑ ይችላሉ ብሎ መጠርጠሩ አስተዋይነት ይመስለኛል፡፡ በርግጥም ጉራማይሌ ፖለቲካ ማለት ይህ ነው፡፡
ሌላው ትኩረት የሚያሻው ጉዳይ ኢህአዴግ በእነዚህ አካባቢዎች እያደረገ ያለው የሚከተለው መሆኑ ነው፡- ከኩሊት እስከ ቋራ ድንበር ድረስ ከወሎ፣ ከጎጃም እና ከጎንደር ነዋሪዎች አሰባስቦ የመልሶ ማስፈር ስራ ሰርቷል፤ የሰፈራው ዋነኛ አላማም ለም መሬት ይዘው እያረሱ ቤተሰብ መስርተው እንዲቀመጡ ያማቻቸላቸውን ሰፋሪዎች መሳሪያ በማስታጠቅ በአካባቢው በኩል ሊመጡ የሚችሉ የኃይል አማራጭን የሚከተሉ ተቃዋሚዎችን እንዲከላከሉ እና ከአቅማቸው በላይ ሲሆን ደግሞ አስቀድመው መሬት ለሰጣቸው መንግስት እንዲያሳውቁ ማድረግን ያሰላ ነው፡፡ በዚህም ለሥልጣኑ አስጊ የሆነውን ቀዳዳ ለመድፈን እየሞከረ እንደሆነ መረዳት ይቻላል (በነገራችን ላይ ከጎንደር ተቆርሶ ለትግራይ መሬት ተሰጥቷል የሚል አደገኛ ቅስቀሳም እየተካሄደ ነው፤ በግሌ ይህ ጉዳይ የሚያወዛግብ አይመስለኝም፤ ስርዓቱ ያነበረውን ቋንቋ ተኮር ፌደራሊዝም የማንደግፈው እስከሆነ ድረስ መሬቱ ወደ የትኛውም የሀገሪቱ ክልል ቢሄድ ለውጥ አይኖረውም፤ ምክንያቱም በኢህአዴግ ግብዓተ-መሬት ላይ የሚያብበው መልከዓ-ምድራዊ ፌደራሊዝም (Geographical Federalism) እነዚህን አጨቃጫቂ መሬቶች ለአስተዳደር አመች በሆነ መልኩ ማዋቀሩ አይቀሬ ነውና)
አያሌው ጎበዜና ባሕር ዳር
አቶ አያሌው ጎበዜ ድርጅቱን የተቀላቀለው አስተማሪ ሆኖ እየሰራ በነበረበት አዲስ ዘመን ከተማ በ1984 ዓ.ም ቢሆንም በተፋጠነ ሂደት የሽግግር መንግስቱ የስራ አስፈፃሚ አባል መሆን ችሎ ነበር፤ ከ1987-1992 ዓ.ም የክልሉ አስተዳዳሪ አዲሱ ለገሰ ምክትል ሆኖ ተሹሟል፤ በዮሴፍ ረታ የአስተዳደር ዘመን (ከ1992-97 ዓ.ም) ደግሞ መጀመሪያ የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ኃላፊ፣ ቀጥሎ አፈ-ጉባኤ ሆኖ ሰርቷል፡፡ ይሁንና በምርጫ 97 ዮሴፍ በተወዳደረበት ሰሜን ሸዋ በቅንጅት እጩ ሲሸነፍ፣ አያሌው ደግሞ በማርቆስ ከተማ በባሶ ሊበን ወረዳ ሊያሸንፍ ችሏል (አሸናፊነቱ ምንም እንኳ እንደ ሌሎቹ የኢህአዴግ ተወዳዳሪዎች በድርጅታዊ የድምፅ ስርቆት የተገኘ ቢሆንም) ከ1998 ዓ.ም አንስቶ እስከያዝነው አመት መጀመሪያ ወራት ድረስ የክልሉ ፕሬዚዳንት ሆኖ የቆየው አያሌው ጎበዜ ‹‹ለሱዳን ተሰጠ›› ወይም ‹‹ሊሰጥ ነው›› ከተባለ መሬት ጋር ተያይዞ የማጀገኑና የማንፃቱ ቅስቀሳ የኑፋቄን መንገድ የተከተለ ይመስለኛል (የጉዳዩ ስሁትነት የኛይቷን ‹ፋክት› መፅሄትንም ይጨምራል) በደፈናው ከዚህ ቀደም ‹አያሌው ለሱዳን በሚሰጥ መሬት ላይ አልፈርምም በማለቱ፣ ደመቀ መኮንን ፈረመ› የሚባል ምንጩ የማይታወቅ ወሬ ሁላችንም ጋ ደርሶ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ይሁንና ከብአዴን የመረጃ ምንጮቼ እንዳረጋገጥኩት፣ አያሌው ያውም ርህራሄ አልባ የነበረውን የጉልበታሙ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊን ውሳኔ ተቃውሞ ‹ፈርም›፣ ‹አልፈርምም› አይነት አንጃ ግራንጃ የሚፈጥር ደፋር ልብ ያሌለው መሆኑን ነው፡፡ በግልባጩ ፖለቲካችን ጉራማይሌ ነውና ለብአዴን ፍቅር በሌላት ባሕር ዳር አያሌው ተወዳጅ እንደሆነ ይነገራል፤ ይህ የተወዳጅነቱ ሚስጥር ግን ከድርጅቱ ይልቅ ‹‹መረጠኝ›› ለሚለው ሕዝብ ታማኝ በመሆኑ እና በሀገር ጥቅም ከእነ ‹ኦቦ› አዲሱ ለገሰ ተሽሎ ሳይሆን፣ ከራሱ የግል ባህሪና ሰብዕና ጋር ስለሚያያዝ ነው፤ ይኸውም በመኖሪያ ቤቱ አካባቢ ካሉ ነዋሪዎች እና አብረውት ከሚሰሩ የበታች ሰራተኞች ጋር የመሰረተው ማሕበራዊ ግንኙነት ዋነኛው ነው፤ በርግጥም የሚያውቀውም ሆነ የማያውቀው ሰው ሲሞት ቀብር ላይ ይገኛል፤ ማታም እዝን ይዞ በመሄድ ሲያፅናና ያመሻል፤ ሰርግን በመሳሰሉ የደስታ ዝግጅቶችም ላይ እንዲሁ ይሳተፋል፤ እነበረከት ስምዖን ለሚያቀነቅኑት ግራ ዘመም ፖለቲካም ሩቅ በመሆኑ፣ እጅግ መንፈሳዊ የሆነ ባህሪይ ይስተዋልበታል፤ ለአብነት እምነቱ የሚያዝዘውን (ከመፆም ጀምሮ በቤተ-ክርስቲያን ተገኝቶ እስከ ማስቀደስ ያሉ ጉዳዮችን) እንደ ባለሥልጣን ግብዝ ሳይሆን እንደ ማንኛውም ተራ አማኝ ዕለት ተዕለት ሲፈፅም ይታያል፡፡ በቤተሰብ አስተዳደርም ቢሆን አራት ልጆቹን መንግስት ትምህርት ቤት ከማስተማር አልፎ በኢትዮጵያዊ ጨዋ ስነ-ምግባር ማሳደጉን፣ ብልሹ አድርገው ልጆቻቸውን እያሳደጉ ካሉ ከአንዳንድ ኃላፊነት ከማይሰማቸው ባለሥልጣናት ጋር አነፃፅረው የሚያመሰግኑት የድርጅቱ የቅርብ ሰዎች አጋጥመውኛል፤ ከጥቂት ወራት በፊት በህክምና በማዕረግ የተመረቀችውን ብቸኛና የመጀመሪያ ሴት ልጁንም እንደ ምሳሌ ይጠቅሳሉ፡፡
በአናቱም የትኛውም ባለ ጉዳይ ቢሮው ሲመጣ ያለ ቢሮክራሲ ማስተናገዱም ሆነ ለሚቀርብለት አቤቱታም ጥያቄ ‹አይሆንም› አለማለቱን እንደ በጎ ተግባር የቆጠሩለት ሰዎች ለሰውየው ገፅታ ግንባታ የራሳቸውን ሚና ተጫውተዋል፡፡ በተቀረ ኢህአዴግ እንደ አሰባሰባቸው በርካታ ባለስልጣናት እርሱም አለቆቹን አብዝቶ የሚፈራ ሽቁጥቁጥ ሰው መሆኑን በቅርብ የሚያውቁት ይናገራሉ፡፡ በተለይም የብአዴን ካድሬዎች ‹‹ሽማግሌው›› እያሉ በሹክሹክታ የሚጠሩትን አዲሱ ለገሰን እና ሞገደኛውን በረከት ስምዖንን የ‹መለአኩ ገብርኤል› ያህል እንደሚፈራቸው ሰምቻለሁ፡፡
ይህ ፍራቻውም በፍትሕ እና በሙስና ቢሮዎች አካባቢ ከብቃት ይልቅ ‹‹የራሴ›› የሚላቸውን የትውልድ መንደሩን ሰዎች በመሾሙ ‹‹እመራዋለሁ›› የሚለውን ሕዝብ ለከፋ ብሶትና መከራ አጋልጦ ነው ከሥልጣኑ የተሰናበተው፡፡ ይህም ሆኖ ከኃላፊነቱ ለመልቀቅ ጥያቄ ካቀረበ ከአንድ አመት በኋላ ነው ፓርቲው ያፃደቀለት፤ ያለፈውን ሙሉ ዓመትም በቢሮው ከመገኘቱ እና በትላልቅ ጉዳዮች ላይ ከመሳተፉ ባለፈ፣ ሁሉንም ሥራ ሲሰራ የነበረው ዛሬ በምትኩ የተሾመው የዋድላ ደላንታው ገዱ አንዳርጋቸው ነው፤ ገዱ ድርጅቱን የተቀላቀለው ከአያሌው አንድ ዓመት ቀደም ብሎ ዋድላ ደላንታን ኢህአዴግ ከደርግ መዳፍ በኃይል ነጥቆ በወሰደበት ወቅት ነበር፤ ያን ጊዜ የገበሬ ማሕበር ሕብረት ሱቅ ሠራተኛ የነበረው ገዱ ዛሬ የክልሉ ፕሬዚዳንት ለመሆን ችሏል፤ በርግጥ ይህ ሰው ጠንካራ ሠራተኛ እና የበላይ አመራሮችን ተጋፋጭ እንደሆነ ይነገርለታል፤ እንዲሁም እንደ አያሌው ከሙስና ጋር ብዙም ንክኪ የለውም (በነገራችን ላይ የብአዴን ዋነኛ አመራሮች ለሙስና ሩቅ እንደሆኑ በወሬ ደረጃ ይሰማል፤ ግና! ይህንን እንደምን ማመን ይቻላል? …በርግጥ በክልሉ በተዘዋዋሪ መንገድ የጀነራል አበባው ታደሰ ነው ከሚባለው ባለ አራት ፎቁ ‹‹አልዋቅ›› ሆቴል ሌላ በወሬ ደረጃ የአመራር አባላቱ ንብረት የሆነ አላጋጠመኝም፤ ነገር ግን እኔን አላጋጠመኝም ማለት ሰዎቹ ንፁሃን ናቸው እንደ ማለት አይደለም)
የሆነው ሆኖ ብአዴን በበረከት ስምዖን፣ በአዲሱ ለገሰ፣ በካሳ ተክለብርሃን፣ በታደሰ ጥንቅሹ እና በከበደ ጫኔ ስም የመሰረተው ‹‹ጥረት›› የተሰኘው ኮርፕሬሽን ዳሽን ቢራ፣ ጥቁር አባይ ትራንስፖርት፣ ዘለቀ እርሻ፣ አምባሰል አስመጪና ላኪ፣ ጣና ሞባይል እና ጣና ፍሎራ የተሰኙ የንግድ ድርጅቶችን ያስተዳድራል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አትራፊ የሚባለው ዳሽን 49 ፐርሰንቱን እንግሊዝ አገር ለሚገኝ አንድ ቢራ አምራች ድርጅት ሲሸጥ፤ ጣና ሞባይልም በአሜሪካን ሀገር የታወቀው የሶፍት ዌር ኢንጂነር ባለሙያው ወልደሉዑል ካሳን ጨምሮ ለአራት ሰዎች የአክሲዮን ድርሻን አስተላልፏል፡፡ ይህ ሁኔታም ድርጅቶቹ ትርፍና ኪሳራቸውን በውጪ ኦዲተር እንዲያስመረምሩ የሚያስገድድ መደላድል ፈጥሮላቸዋል፡፡ በርግጥም እንዲህ አይነቱ አሰራር የእነ አዜብ መስፍን መቀለጃ ከሆነው ‹‹ኤፈርት›› በተሻለ መልኩ ለዘረፋ እንዳይጋለጥ መታደጉ አከራካሪ አይደለም፡፡ ምክንያቱም እንግሊዛዊው ድርጅት የዳሽን ቢራ 49 ፐርሰንት ድርሻን ገዝቶ ሲያበቃ፣ ወጪና ገቢውን አይከታተልም ማለቱ ሩቅ ነውና፡፡
በትግራይ ሕዝብ ስም እየነገደ፣ ለህወሓት አመራር አባላትና ቤተሰቦች ብቻ መምነሽነሺያ የሆነው ‹‹ኤፈርት››ም በእንዲህ አይነት መልኩ ለውጭ ድርጅቶች ድርሻ እንዲሸጥ ካልተገደደ በቀር ለቁጥጥር አስቸጋሪ ሆኖ መቀጠሉ ሳይታለም የተፈታ እውነታ ነው፤ ይህ ሁኔታም የፖለቲካ ሥልጣን የጨበጠ ሁሉ የቻለውን የሚዘግንለት ከመሆን የሚተርፍበትን እድል ያመቻችለታል (በነገራችን ላይ እንደሚወራው የብአዴን አመራሮች ወደ ሙስና አለመግባታቸው እውነት ከሆነ፣ ምክንያቱ ጠፍጥፎ የሰራቸውን ህወሓት በመፍራት ብቻ ነው ሊሆን የሚችለው፡፡ በግልባጩ ህወሓት በኢትዮጵያ ሰማይ ስር የሚፈራው የለምና እንዲህ እንደቀለደ በሚቀጥለው ወር የተመሰረተበትን 39 ዓመት ለማክበር ሽር-ጉዱን ከወዲሁ ተያይዞታል)
ሌላው የብአዴን አመራሮች አስገራሚ ታሪክ ከዋነኞቹ መካከል ታምራት ላይኔ፣ በረከት ስምዖን፣ አዲሱ ለገሰ፣ ሕላዊ ዮሴፍን… የመሳሰሉት የትዳር አጋራቸውን ያጩላቸው አንዲት ሴት መሆናቸው ነው፡፡ እኚህ የዋግ ኡምራ ተወላጅ በታጋዮች ዘንድ ‹‹ማዘር›› እየተባሉ ሲጠሩ፣ ኢህአዴግ ውስጥ ባሉ አንዳንድ አሽሟጣጮች ደግሞ ‹‹ጣይቱ›› በሚል ቅፅል ስም ይታወቃሉ፤ ይህ ስያሜ የአጼ ምንሊክ ባለቤት የነበሩት እቴጌ ጣይቱ ታላላቅ መኳንቶችን እየመረጡ ከቅርብ ዘመዶቻቸው ጋር ያጋቡ ነበር ከሚለው ትርክት የሚነሳ ነው፡፡ የሆነው ሆኖ ይህንን ኩነት ጉራማይሌ የሚያደርገው የ1993ቱን የህወሓት ክፍፍል ተከትሎ የብአዴን መሪዎች ‹‹ቦና-ፓርቲዝም››ን በአደባባይ ሲያወግዙና ሲተቹ መስማታችን ነው፡፡
(ቀሪውን ጉራማይሌ የፖለቲካ ወጋችንን በሚቀጥለው ሳምንት እመለስበታለሁ

በለገጣፎ ለገዳዲ አስደንጋጭ የመሬት ዝርፊያ እየተካሄደ ነው

ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው የኦሮምያ ልዩ  ዞን እየተባለ በሚጠራው  የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ የሚገኘው የአርሶአደሩ መሬት በከተማዋ ውስጥ ባልኖሩና ማንነታቸው በማይታወቅ ሰዎች ስም መያዙን ለኢሳት የደረሰው ሰነድ አመልክቷል።
ከ4 ሺ በላይ ሰዎችን ስም ዝርዝር በያዘው በዚህ ሰነድ ማንነታቸው የማይታወቁ ሰዎች የአባታቸውን ስም ብቻ በመቀያየር ከ  140 እስከ 500 ካሬ ሜትር  ቦታዎችን ይዘዋል። አለማየሁ ፣ አልማዝ፣ አለምጸሃይ፣ አሰፋ፣ አበራ  ፣ አብርሃም ፣ አበበ የሚሉ ስሞች ከ15 እስከ 30 የሚጠጉ የቦታ ካርታዎችን በስማቸው አሰርተው ይዘዋል። ግለሰቦቹ  ቦታውን ያገኙት ከ2000 እስከ 2001 ዓም ባለው የአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ነው።
የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ በአንድ ወቅት 15 ሺ በላይ ሰዎች በህገወጥ መንገድ የቦታ ካርታዎችን መያዛቸውን የሚገልጽ መግለጫ ማውጣቱ ይታወቃል። ለኢሳት በደረሰው ሰነድ ላይ ለማየት እንደሚቻለው አብዛኞቹ ሰዎች ቦታዎችን የሚወስዱት ጂ+2 እየተባለ የሚጠራውን ቤት ለመስራት ነው።
በከተማው የሚታየውን የቦታ ዘረፋ በተመለከተ የከተማው ነዋሪ ህዝብ በተደጋጋሚ የተቃውሞ ሰልፍ አድርጓል። የኦሮሚያ ክልል ችግሩን ለመፍታት ቃል ቢገባም የከተማዋ አመራሮች ወርደው በሌሎች እንዲተኩ ከማድረግና የተተኩትም ሰዎች ተመሳሳይ ድርጊት ከመፈጸም ው   የተለወጠ ነገር አለመኖሩን ነዋሪዎች ይናገራሉ።
በለገጣፎ ለገዳዲ በኮምኒኬሽን ሰራተኛነት ሲያገለግል የነበረው የገዢው ፓርቲ አባል  ወጣት መኮንን ተስፋየ በከተማዋ ውስጥ የሚፈጸመውን ዝርፊያ ከሌሎች ወጣቶች ጋር በመሆን በማጋለጥ በኩል ከፍተኛ ሚና ሲጫወት ከቆየ በሁዋላ፣ በመጨረሻም ህይወቱን ለማትረፍ ሲል በቅርቡ ከአገር ተሰዷል። ወጣት መኮንን እንደሚለው እብዛኞቹ የከተማዋ ቦታዎች በባለስልጣናት የተቸበቸቡ ናቸው።
በሙስና የተከሰሱት የቀድሞው የገቢዎችና ጉምሩክ ምክትል ሃላፊ አቶ ገብረውሃድ ወልደ ጊዮርጊስ በዚሁ በለገጣፎ ለገዳዲ የቦታ ካርታ በብዛት ይዘው ከተገኙት መካከል ናቸው።
የአዲስ አበባ መስተዳድር እነዚህን ከተሞች ከአዲስ አበባ ጋር ለመቀላቀል ቢያቅድም፣ የኦሮምያ ክልል ፈቃደኛ ባለመሆኑ እስካሁን አልተሰካም። የኦሮምያ ክልል ከእንግዲህ ለአዲስ አበባ የምንሰጠው መሬት የለም በሚል አቋሙ በመጽናቱ የፌደራሉ መንግስት የቤቶች ልማት እቅድን ለመተግበር እየተሳነው መጥቷል። ከወጣት መኮንን ተስፋየ ጋር ያደረግነውን ቃለምልልስ በቅርቡ ይቀርባል።

ሰኞ 3 ፌብሩዋሪ 2014

በርካታ የአዲስ አበባ ቤት ተመዝጋቢዎች ገንዘባቸውን ከባንክ እያወጡ ነው

ከውስጥ አዋቂ ምንጮች ለማዎቅ እንደተቻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚታየውን የመኖሪያ ቤቶች ችግር በዘላቂነት ለማቃለል በሚል ከዚህ በፊት ከነበረው የ 20/80 የጋራ መኖሪያ ቤት ልማት ፕሮግራም በተጨማሪ በአማራጭ የ 10/90 አነስተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እና ለመለስተኛና መካከለኛ ገቢ ላላቸው በ40/60 የቁጠባ ቤት ፕሮግራም መቅረጹን ተከትሎ እስከ አንድ ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ ተመዝግቦ ነበር።
ይሁን እንጅ በአሁኑ ወቅት እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው የተለያዩ የቤት ልማት ፕሮግራም ተሳታፊ ዜጎች ከፕሮግራሙ እየወጡ መሆኑ ታውቋል። ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ከ30 ሺ በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎች ገንዘባቸውን ከባንክ አውጥተዋል።
ባንክ ቤቶች ከዚህ በፊት ለምዝገባ ስራ ሲጨናነቁ ከነበረው ባልተናነሰ በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ የስራ ጫና ውስጥ እንዳሉና ለዚህ አገልግሎት ብቻ አንድ መስኮት ለመልቀቅ እንደተገደዱ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
የ20 /80፣ የ10/90 እና የ40/60 ቤቶችን ለመገንባት ከገንዘብ እጥረት በተጨማሪ የቦታ እጥረት ማጋጠሙን ኢሳት የውስጥ መረጃዎችን በማሰባሰብ መዘገቡ ይታወሳል። በተለይም የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ ከተሞችን በአዲስ አበባ ታላቁ ካርታ ውስጥ ለማስገባት ፈቃደኛ ሆኖ ባለመገኘቱ የፕሮጀክቱ ተፈጻሚነት አደጋ ውስጥ ወድቋል።
 source : Esat