ማክሰኞ 19 ኤፕሪል 2016
ሰኞ 18 ኤፕሪል 2016
የመላው ኢትዮጲያ አንድነት ድርጅት ( መኢአድ) አመራሮች ዛሬም በሥቃይ ላይ ናቸው
የመላው ኢትዮጲያ አንድነት ድርጅት ( መኢአድ)
አመራሮች ዛሬም በሥቃይ ላይ ናቸው
የነጻነት የፍትህ የኩልነት
ታጋዮች ያለምንም ፍርድ...
በህወሓት ማሠቃያ ቤት እየተሠቃዩ ይገኛሉ
1ዓመት ከ7ወር ሙሉ ያለምንም ማሥረጃ
ያለምንም ፍርድ ታሥረው ይገኛሉ
የህወሓቱ ዳኛ የሁኑትን እሣቸው ዘንድ የቀረበን ሁሉም የፖለቲካ እሥረኛ ተበቂ በላይ ቢከላከል እንኳን መንግሥት ያለመረጃ አይከሥም በማለት ሣያገናዝቡ ፍርድ ይሠጣሉ ከድሜልክ እሥራት እሥከ ሞት በዚህ ፍርድ (አቡሃይ )ችግር የለባችውም እኒህን ዳኛ ይቀየሩልን በማለታቸው ምክንያት
ከታሣሥ 4/4 /2008 ጀምርው ያለምንም ውሣኔ በሥር ላይ ይገኛሉ
በሥር ላይ የሚገኙት ሥም ዝርዝር
በነ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮነን የክሥ መዝገብ ላይ ያሉት 16 ሠዋች
1ኛ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮነን
2ኛ በላይነህ ሢሳይ
3ኛ አለባቸው ማሞ
4ኛ አወቀ ሞኝሆዴ
5ኛ ዘሪሁን ብሬ
6ኛ ወርቅየ ምሥጋናው
7ኛ ኣማረ መሥፍን
8ኛ ተሥፋየ ታሪኩ
9ኛ ቢሆነኝ አለነ
10ኛ ተፈሪ ፋንታሁን
11ኛ ፈረጀ ሙሉ
12ኛ አትርሣው አሥቻለው
13ኛ እንግዳው ዋኘው
14ኛ አንጋው ተገኘ
15ኛ አግባው ሠጠኝ
16ኛ አባይ ዘውዱ
እኒህ የህሌና እሥረኞች ያለምንም ማሥረጃ
በሥር እየተሠቃዩ ይገኛሉ
ህወሃት ሆይ
በማፈን በማሠር በመግደል ሠላም አይገኝም
የነጻነትን ጎህ ሣንቀናጅ በፍጹም ትግሉ አይቆምም
እኛ የተደራጀነው ይህን አሥከፊ አረመኔ ጨካኝ ሥርአት ለማሥወገድ ነውና
በቆራጥ አመራር በቆራጡ ህዝባችን ታጅበን
በበደኖ አርባ ጉጉ
በጋንቤላ ጉራ ፈርዳ
በመላ አገራችን እየተፈጸመ ያለውን የዘር መጽዳት ዘመቻ
ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ ለማሥወገድ ነውና
ከፕሬፌሠር እሥክ ዶክተር
ካርሦ አደር እሥከ ሙህር
ከሹፌር እሥከ ርዳት
ከተማሪ እሥከ አሥተማሪ
ያለውን ያገራችንን ህዝብ አደራጂተው
ያሥረከቡንን
የነጻነት ፋና ቀዳጂ የሆኑትን ክቡር ፕሮፌሠር አሥራት ወልደየሥን
እሣቸው ጀምረው መሣውት የሆኑበትን ኣላማ ከዳር ለማድረሥ
እኛም ልጆቻቸው ጠንክረን እንሠራለን
እሥከ መጨረሻው
አንዲት ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር!!!!!!
ረቡዕ 13 ኤፕሪል 2016
በኢትዮጵያ በአለም ደረጃ በጣም ውድ የሆነ የኢንተርኔት አገልግሎት እንደምታቀርብ ተገለጸ
ኢትዮጵያ በአለማችን ካሉ ሃገራት መካከል የኢንተርኔት አገልግሎትን በጣም ውድ በሆነ ክፍያ በማቅረብ ግንባር ቀደም ሃገር ሆና መገኘቷን በጉዳዩ ዙሪያ ጥናትን ያደረገ አንድ የቴክኖሎጂ ተቋም ይፋ አድርጓል።
ይኸው የ120 ሃገራትን ታሪፍ በንጽጽር ያቀረበው ኑሚቢዬ የተሰኘው አካል በኢትዮጵያ ዝቅተኛ ፍጥነት ባለው የኢንተርኔት አገልግሎት ክፍያው የማይቀመስ መሆኑንም አመልክቷል።
የኢትዮ-ቴለኮም ባለስልጣናት ይህንኑ አገልግሎት ጨምሮ በቫይበር የሚደረግ የስልክ ጥሪ ልውውጥ ላይ ክፍያን ተግባራዊ ለማድረግ ምክክርን በማካሄድ ላይ መሆኑን ባለው ሳምንት ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።
በሃገሪቱ በብቸኝነት የስልክ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው ኩባንያው በአገልግሎቱ ላይ አዳዲስ የቁጥጥር ስርዓቶችን ተግባራዊ ከማድረጉ ጎን ለጎን የተንቀሳቃሽ የእጅ ስልኮችንም ለመመዝገብ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገልጿል።

ማክሰኞ 12 ኤፕሪል 2016
የማህበራዊ ድምጽና ምስል አገልግሎቶች በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ተቋረጡ
መንግስት በኢንተርኔት አማካኝነት የሚደረጉ የድምፅና የምስል አገልግሎቶች ላይ አዲስ መመሪያን እንደሚተገብር ማስታወቁን ተከትሎ አገልግሎቱ በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ተቋረጠ።
በተለይ በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተገናኘ ተቃውሞ በተቀሰቀሰበት የኦሮሚያ ክልል የትዊተርና የWhatsAPP አገልግሎቶች ከተቋረጡ አንድ ወር አካባቢ እንደሆናቸው ብሉምበርግ የዜና ወኪል የተለያዩ መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ ማክሰኞ ዘግቧል።
በኦሮሚያ ክልል በተጨማሪ አገልግሎቶቹ በደቡብ ክልል ሃዋሳ ከተማና በተለያዩ አካባቢዎች ተቋርጦ እንደሚገኝም የተለያዩ አካላት ለዜና ወኪሉ ያስታወቁ ሲሆን፣ በምስራቅ ለንደን ዩኒቨርስቲ የኢኮኖሚክስ መምህር የሆኑት አቶ ስዩም ሃሜሶ ሃገር ቤት ከሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ጋር እንኳን መገናኘት እንዳልቻሉ ተናግረዋል።
የመንግስት ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ አገልግሎቱ ሊስተጓጎል የቻለው በቴክኒክ ችግር ሊሆን እንደሚችል ገልፀው፣ መንግስት የማገድ ፖሊሲ እንደሌለው ለዜና አውታሩ አስተባብለዋል።
ይሁንና የስልክ አገልግሎት ተጠቃውሚዎችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች መንግስት ተግባራዊ ሊያደርግ ያሰበው አዳዲስ መመሪያዎች በኢንተርኔት እና በስልክ የመልዕክት ልውውጦች ላይ ቁጥጥርን እንዲሁም የስነ-ልቦና ተፅዕኖን ለመፍጠር እንደሆነ አስታውቀዋል።
በአምቦ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑት አቶ ስዩም ተሾመ በተቀንሳቃሽ የእጅ ስልክ የሚደረጉ የተለያዩ የኢንተርኔት አገልግሎቶች ተቋርጠው እንደሚገኙ ለብሉምበርግ የዜና አውታር አስረድቷል።
በቅርቡ የWhatsAPP ኩባንያን የገዛው ፌስቡክና ትዊተር ድርጅቶች በኢትዮጵያ እገዳ ተጥሎበት ስላለው አገልግሎት ተጠይቀው ምላሽ ከመስጠት መቆጠባቸው በዘገባው ያወሳው የዜና ወኪሉ እገዳው በተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ዘንድ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖ እንደሚገኝም አስነብቧል።
በኢትዮጵያ የሰብዓዊ የመብት አያያዝና የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ዙሪያ የሰላ ትችትን የሚያቀርበው ሂውማን ራይትስ ዎች በበኩሉ ድርጊቱ ቀድሞ የተተነበየ እንደሆነና መንግስት የመረጃ ልውውጦች ላይ ቁጥጥሩን እንዳጠናከረ ገልጿል።
መቀመጫውን በሰርቢያ ያደረገውን በቴክኖሎጂ ዙሪያ የሚሰራው ኩባንያ በየጊዜው የሚያወጣቸው መረጃዎች በቢቢሲ እና በሌሎች አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘንድ በመረጃነት እንደሚቀርቡም ለመረዳት ተችሏል።
ቤርሙዳ ኢዝቤኪስታን እና ሚያንማር ከኢትዮጵያ በመቀጠል ከሁለተኛ እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል። የኢትዮጵያ መንግስት በኢንተርኔት አገልግሎት ላይ ከሚያደርገው ቁጥጥር በተጨማሪ የሚጠይቀው ክፍያም ውድ መሆኑን የተለያዩ አካላት ሲገልጹ መቆየታቸው ይታወሳል።
መንግስት በገጠመው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ፣ በውጭ ሃገር ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በህዳሴ ግድብ እንዲሁም በመኖሪያ ቤት ግንባታ ገንዘብ ለማሰባሰብ አዲስ ዘመቻ መጀመሩን ለማወቅ ተችሏል

ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
ልጥፎች (Atom)