ቅዳሜ 26 ኤፕሪል 2014

Ethiopia detains bloggers and journalist


 


The Ethiopian government has arrested six independent bloggers and a journalist in what human rights group Amnesty International has called a "suffocating grip on freedom of expression".
Six members of independent blogger and activist group ‘Zone 9’ and a prominent Ethiopian journalist were arrested on Friday in the capital Addis Ababa.

All six bloggers were arrested at night by armed security forces and taken from their homes to the Federal Police Crime Investigation Sector ‘Maikelawi’, where political prisoners are alleged to be held in pre-trial, and sometimes arbitrary detention.

The Zone 9 group who are said to be very critical of government policy and have a strong following on social media had temporarily suspended their activities earlier this year after accusing the government of harassing their members.

Journalist Tesfalem Waldyes who writes independent commentary on political issues for a Ethiopian newspaper was also arrested.

According to Ethiopian journalist Simegnish Yekoye, Waldyes is being denied visitation by friends and family and it's unclear what prompted his arrest and what charges he is being held under.

Simegnish Yekoye told Al Jazeera she was unaware of why the government had clamped down on journalists and their was growing fear on the future of a free press.

"I am very scared, I don't know what's going to happen next," she said.
Ranked 143 in the 2014 Reporters Without Borders press freedom index, media watchdogs say 49 journalists fled the country between 2007 and 2012 to evade government persecution.

uman rights group Amesty International criticised the arrests, saying "these arrests appear to be yet another alarming round up of opposition or independent voices".

"The Ethiopian government is tightening its suffocating grip on freedom of expression in a major crackdown which has seen the arrest of numerous independent, critical and opposition voices over the last two days", Claire Beston, Ethiopia researcher at Amnesty International, said.
Al Jazeera's Mohammed Adow reporting from Bahir Dar said it was unclear what will happen to the detained journalists.

"There are scores of journalists currently serving between 14 and 27 years in prison with some charged on terrorism offences."


Source : http://www.aljazeera.com/news/africa/2014/04/ethiopia-detains-bloggers-journalist-2014426163222797965.html 

ሰበር ዜና፣ ፖሊስ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትን ማሰሩን ቀጥሏል

በዳንኤል ሃረጋዊSemayawi party members on action
ፖሊስ ቀስቃሾቹን እያሰረ ነው ፖሊስ የእውቅናው ደብዳቤ አልደረሰኝም በሚል በተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍሎች ቅስቀሳ ላይ የተሰማሩትን የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች እያሰረ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት በየካ፣ ካሳንቺስና አቧሬ ሲቀሰቅሱ የነበሩ ወጣቶች በፖሊስ ተይዘው ታስረዋል፡፡ ቀስቃሾቹ ሰልፉ እውቅና እንደተሰጠው የሚያመለክተውን ወረቀት ለፖሊስ ቢያሳዩም ፖሊሶች የእውቅናው ደብዳቡ አልደረሰንም በሚል አስረዋቸዋል፡፡ ቀስቃሾቹ የያዙት የእውቅና ደብዳቤ ግልባጭ ለፖሊስ የተጻፈበት በመሆኑ ሰልፉ እውቅና አግኝቶ እያለ ሆን ተብሎ ለማደናቀፍ እንደሆነ ምክትር ሊቀመንበሩ አቶ ስለሽ ፈይሳ ገልፀዋል፡፡
በላም በረት፣ ቦሌ ድልድይ፣ ኮተቤ፣ መገናኛ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ቅስቀሳቸውን በተሳካ መልኩ አጠናቀዋል፡፡ በሌሎች አካባቢዎች የተሰማሩት አባላት ቅስቀሳውን አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡ በሌላ በኩል በየካ፣ ካሳንቺስና አቧሬን ጨምሮ በሌሎች የከተማይቱ ክፍሎች ፖሊስ ከ20 በላይ አባላትን ማሰሩ ታውቋል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ ፖሊስ ቅስቀሳው ላይ ያልነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችንም እያሰረ ነው፡፡ የታሰሩትን አባላትና ደጋፊዎች ሁኔታ ለማጣራት ወደ የካ ፖሊስ ጣቢያ ያቀኑ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላትን ፖሊስ አስሯቸዋል፡፡
በዛሬው ቀን ካሳንቺስ ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ የታሰሩት
1. ብሌን መስፍን
2. አስናቀ በቀለ
3. መስፍን
4. ተስፋዬ አሻግሬ
5. እዮብ ማሞ
6. ኩራባቸው
7. ተዋቸው ዳምጤ
የካ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች
1. ፍቅረ ማሪያም አስማማው
2. እያስፔድ ተስፋዬ
3. ጋሻው መርሻ
4. ተስፋዬ መርኔ
5. ሀብታሜ ደመቀ
6. ዘሪሁን ተስፋዬ
7. ጌታነህ ባልቻ
8. ንግስት ወንዲፍራው
9. ሜሪን አለማየሁ ናቸው
የካ አካባቢ ታስረው የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ምግብ እንዳይገባላቸው ተከልክለዋል፡፡ በሌላ በኩል አህመድ መሃመድ፣ሀይለማሪያም፣ ሱራፌልና አምሃ የተባሉ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት መገናኛ አካባቢ ተይዘው ወደ የካ ፖሊስ ጣቢያ ተዘዋውረዋል፡፡ በአጠቃላይ የካ ፖሊስ ጣቢያ የሚገኙት 14 መሆናቸው ታውቋል፡፡ በሁሉም ፖሊስ ጣቢያዎች የሚገኙት አመራሮችና አባላት በአሁኑ ወቅት ቃል እየሰጡ ሲሆን ሊያድሩ እንደሚችሉም ተነግሯቸዋል፡፡
በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ቢሮ ተደውሎ የሰላማዊ ሰልፉን አስተባባሪዎች ጧት ሁለት ሰዓት ላይ ‹‹ኑ እና እንነጋገር!›› የሚል ጥሪ አድርጓል፡፡ ከሰልፉ አስተባባሪዎች መካከል አቶ ጌታነህ ባልቻ ታስሮ ይገኛል፡፡

ሰበር ዜና፡ “ሰማያዊ ፓርቲ የእሁዱን ሰልፍ በታቀደው መሰረት ለማከናወን በሙሉ ቁርጠኝነት ላይ ይገኛል!!!”

ከአመራሩ በተጨማሪም የታሰሩ አባላት ዝርዝርSemyawi party leaders arrested
የካ ክፍለ ከተማ ሾላ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የታሰሩ
1. ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት -የፓርቲው ሊቀመንበር
2. ስለሽ ፈይሳ- ምክትል ሊቀመንበር
3. ብርሃኑ ተክለያሬድ-የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
4. ዳዊት ጸጋዬ
5. አወቀ ተዘራ
6. ኢብራሂም አብዱሰላም
7. ሁሴን
8. ሙሉጌታ መኮንን
ጉለሌ ፖሊስ መምሪያ የታሰሩ
1. ዮናስ ከድር
2. እየሩስ ተስፋው
3. እመቤት ግርማ
4. የሽዋስ አሰፋ
5. አበራ
6. አበበ መከተ
ካሳንቺስ ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ የታሰሩት
1. ብሌን መስፍን
2. አስናቀ በቀለ
3. መስፍን
4. ተስፋዬ አሻግሬ
5. እዮብ ማሞ
6. ኩራባቸው
7. ተዋቸው ዳምጤ
ከየካ ፖሊስ ጣቢያ ወደ ቤላ አካባቢ ተዛውረው ታስረው የሚገኙት
1. ፍቅረማሪያም አስማማው
2. እያስፔድ ተስፋዬ
3. ጋሻው መርሻ
4. ተስፋዬ መርኔ
5. ሀብታሜ ደመቀ
6. ዘሪሁን ተስፋዬ
7. ጌታነህ ባልቻ
8. ንግስት ወንዲፍራው
9. ሜሮን አለማየሁ
ስማቸው ያልደረሱን የታሰሩ ሌሎች ወደ 15 የሚጠጉ አባለት እንዳሉ(አድዋ ድልድይ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያና ለጊዜው ቦታቸውን ባላወቅናቸው ፖሊስ ጣቢያዎች ታስረው እንደሚገኙ) መረጃ ደርሶናል ስማቸው ሲደርሰን እናሳዉቃለን፡፡
በተጨማሪ መረጃ ህወሓት/ኢህአዲግ ሰልፉን በተለያየ መልኩ ለማደናቀፍ ቢጥርም ሰማያዊ ፓርቲ የእሁዱን ሰልፍ በታቀደው መሰረት ለማከናወን በሙሉ ቁርጠኝነት ላይ ይገኛል፡፡ የአመራሮችም ሆነ የአባላት እስር የምናደርገውን ትግል ከፍ አድርጎታል፡፡ የያዝነውን የሰላማዊ ትግል ስልትም ከዚህ በበለጠ አጠናክረን ወደፊት እንጓዛለን፡፡ እሁድ 03:00 ሰዓት ላይ ካሳንቺዝ እንደራሴ ሆቴል አካባቢ በሚገኘው በፓርቲያችን ጽ/ቤት ተገናኝተን ስለመብታችን በጋራ እንተማለን!
ኑ ራሳችንን ነፃ በማውጣት የሀገራችንን እጣ ፈንታ እንወስን
ሰማያዊ ፓርቲ!

ረቡዕ 26 ማርች 2014

Washington DC hosts Andualem Aragie’s book signing and celebration


“ከአንድነት ፓርቲ ጋር የሚደረገው ውህደት በግለሰቦች ደረጃ እንጂ በተቋሞቹ ውስጥ አልሞተም”

መጋቢት 11 ቀን 2004 ዓ.ም. በመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና በአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ መካከል የነበረው የቅድመ ፓርቲዎች ውህደት ሳይፈጸም ቀርቷል። ሁለቱም ፓርቲዎች አንዱ አንዱን እየከሰሱ ይገኛሉ።

በተለይ አንድነት በአመራሩ በኩል ከመድረክ ጋር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን መግለፁ ለውዝግቡ መፈጠር በአይነተኛ ምክንያትነት ይጠቀሳል። መኢአድ በበኩሉ በብሔር ከተደራጁ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንደሌለው ከበፊቶቹ አመራሮች እስከ አሁን ፓርቲውን ከሚመሩ አመራሮች ጭምር ወጥ አቋም ሲያንፀባርቁ ይሰተዋላል። ከዚህ መነሻነት ከአንድነት ፓርቲ ጋር ውህደት ለመፈጸም የጀመሩት ጉዞ በአንዳንድ የአንድነት አመራሮች ተጨናግፏል በማለት መግለጫ አውጥቷል። እኛም ይህን የውህደት ልዩነት ከግምት በመውሰድ የመኢአድ ፕሬዝደነት የሆኑትን አቶ አበባው መሐሪን አነጋግረናቸዋል።

ሰንደቅ፡- ድርድሩ ለምን በተፈለገው ፍጥነት አልሄደም? ለድርድሩስ አለመሳካት በመሰረታዊነት የሚያነሷቸው ነጥቦች ምንድን ናቸው?

አቶ አበባው፡-በመጀመሪያ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ማሳወቅ የምፈልገው ድርድሩ አሁን በያዘው ቅርጽ ይሄዳል የሚል እምነት አልነበረንም። ሁሉም ነገር በቀና መንገድ ይጓዛል የሚል ጤናማ አመለካከት ይዘን ነበር ወደ ድርድሩ የገባነው። ሆኖም በእኛ ቀናነት ብቻ የሚሆን ነገር ባለመሆኑ ውህደቱ አለመሳካቱን ግንዛቤ ሊወሰድ ይገባል የሚል እምነት አለን።

ለድርድሩ አለመሳካት ቢያንስ ሶስት መሰረታዊ ነገሮች ማስቀመጥ ተገቢ ነው። አንደኛው፤ አንድነት ፓርቲ ከመድረክ ጋር በግንባር ለመስራት ፈቃድ የወሰደው ከምርጫ ቦርድ ነው። ይሄውም ከሌሎች ሶስት ፓርቲዎች ጋር በጋራ በምርጫ ሕጉ መሰረት ለመስራት አመልክተው ተፈቅዶላቸው እየሰሩ የሚገኙበት ሁኔታ ነው ያለው። ስለዚህም በመጀመሪያ ደረጃ ከመኢአድ ጋር ውህደት ለመፈጸም አንድነት ከመድረክ የግንባር አደረጃጀት መልቀቅ ይጠበቅበታል። አንድነት ከመድረክ መውጣት እስካልቻለ ድረስ ሕዝቡም እንደሚያውቀው ከመኢአድ ጋር መዋሃድ አይችልም። ምክንያቱም መኢአድ ከመድረክ ጋር ያለው ልዩነት ግልፅ በመሆኑ ነው። በእኛ በኩል በመጀመሪያ ከመድረክ ሙሉ ለሙሉ መውጣታችሁን የሚገልጽ መረጃ ስጡን የሚል ጥያቄ አቅርበናል። አያይዘንም ከእኛ ጋር ውህደት ከፈጸሙ፣ ከመድረክ ጋር በጋራ ሊሰሩ እንደማይችሉ አቋማችንን ግልጽ አድርገናል። እነሱም እንደሚገነዘቡት ውህደት ፈጽመን ወደ መድረክ በጋራ ልንሄድበት የምንችልበት አንዳችም ውለታ የለንም። ይህን መስመር ሊያጠራ የሚችል በአንድነት በኩል የቀረበ ማስረጃ የለም። ይህ በሆነበት ሁኔታ በጥድፊያ የቅድመ ፓርቲ ውህደት ፊርማ የምናኖርበት ሁኔታ ሊኖር እንደማይችል ገልጸንላቸዋል።

ሁለተኛው ነጥብ፤ በውህዱ ፓርቲ ውስጥ አስራ ዘጠኝ የሥራ አስፈፃሚ ቦታዎች ላይ እኩል ሃምሳ ሃምሳ ቦታ ይኑረን ብለናል። መኢአድ መዋቅራዊ አደረጃጀትና ስፋቱ የተሻለ መሆኑ ሁሉም ቢያውቀውም በመርህ ደረጃ ይህን ጥያቄ አቅርበናል። ሌላው፣ ለሊቀመንበሩ ቦታ ግልፅ መስፈርት ይውጣለት ለሚለውም ጥያቄ በምንም መልኩ መስፈርት ሊወጣ አይችልም የሚል ምላሽ ነው የተሰጠን። በአጠቃላይ ሲታይ የድርድሩ ነጥቦቹ በግልፅ ሳይቀመጡ እና ውይይት ሳይደረግባቸው እንፈራረም ነው የሚሉት።ይህን መሰል አካሄድ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ ከዚህ በፊት ብዙ ተሞክሮዎች ስላሉ አልተቀበልነውም። ተመሳሳይ ስህተትም ለመፈጸም ዝግጁ አይደለንም።

ሰንደቅ፡- በውህደቱ ላይ የጊዜ ጥያቄ ብቻ ነው ያላችሁ?

አቶ አበባው፡- የጊዜም የሕግም ጥያቄ ነው ያቀረብነው። ጊዜ ለምትለው በአንድነት በኩል እነአቶ ብሩ ቢያንስ የቅድመ ፓርቲው ፊርማ ለመጋቢት 18 ይሁን የሚል መቃወሚያ አቅርበው ነበር። ኢንጂነር ግዛቸው ፈጽሞ አይሆንም የሚል ምላሽ አቅርበው በግድ ለመጋቢት 11 ነው የሆነው። መሰረታዊ ነጥቡ ግን አንድነት በመድረክ ላይ የሚከተለው ግልፅ ያልሆነ አካሄድ ነው። የሚገርመው የተፈጠሩትን ችግሮች ለመመልከት ከሥራ አስፈፃሚዎች መካከል አቶ ካሳሁን አበባ፣ አቶ ሲራክ አጥናፉ እና አቶ ገለቱ ጀጀርሳ የደቡብ ቀጠና አስተባባሪን ልከን ከኢንጅነሩ ጋር ውይይት እንዲያርጉ አድርገናል። በውይይቱም ከስምምነት ለመድረስ የቻሉ ቢሆንም፣ ከተስማሙ በኋላ መኢአድ ድርድሩን አፈረሰው የሚል መግለጫ ማምሻውን ማውጣታቸው በጣም አሳዛኝ ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው። በተለይ ይህን መሰል ጥድፊያ የሚያሳየው፣ ከጀርባቸው የተለየ ተንኮል መኖሩን ነው።

ሰንደቅ፡- ከእርስዎ መረዳት አንፃር፣ የአንድነት ፓርቲ አቀራረብ ስትራቴጂክ ወይንስ ስልታዊ ነበር?

አቶ አበባው፡-እየተፈጸመ ካለው ሁኔታ የተረዳሁት ሂደቱ በሙሉ የአንድነት ሥራ አስፈፃሚ ወይም የምክር ቤቱ አካሄድ አይደለም። የግለሰብ እርምጃ ነው ጎልቶ የወጣው። በግለሰቦች እይታ ድርድሩ የሞተ ነው የሚመስለው። በፓርቲዎቹ በኩል ግን የሞተ ነገር አለ፣ የሚል እምነት የለኝም። በተለይ የአንድነት ሥራ አስፈፃሚ እየሆኑ ያሉትን ነገሮች በጥልቀት ያወቃቸው አልመሰለኝም። የግለሰቦች ማፈግፈግ፣ መቁነጥነጥ ከተመለከትነው ግን የአንድነት አካሄድ ስልታዊ እንጂ ስትራቴጂካዊ አካሄድ አድርጎ ለመቀበል በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ነው ያለው።

ሰንደቅ፡- በሁለቱ ፓርቲዎች መካከል አደራዳሪዎች መኖራቸው ይታወቃል። አደራዳሪዎቹ ይህን ችግር ሊፈቱት አልቻሉም? በምንስ አግባብ ነው የአደራዳሪነት ሚና የወሰዱት?

አቶ አበባው፡- መታወቅ ያለበት እነዚህን አደራዳሪዎች ኢንጅነር ግዛቸው ናቸው መርጠው ያመጧቸው። ቤታችንን አንኳኩተው የገቡት እራሳቸው ናቸው። እኛ አልመረጥናቸውም። እናሸማግላችሁ ሲሉን ነው ያየናቸው። መልካም፣ ለማሸማገል ከሆነ ብለን ተቀበልናቸው። በሂደት ግን ነገሩ ሁሉ የተገላቢጦሽ ነው የሆነው። ይህን ስል ግን ሁሉንም ሽማግሌዎች ማለቴ አይደለም።
ሰንደቅ፡- መኢአድ ባልመረጣቸው ሽማግሌዎች ለመደራደር መዘጋጀቱ በየዋህነት የሚወሰድ ነው ወይንስ የፖለቲካ ስህተት መሆኑን ይቀበላሉ?

አቶ አበባው፡-በእኛ በኩል የነበረው፤ እነዚህ ሰዎች ሙሁራን ናቸው። ለሀገር አስበው ነው ከሚል ቀና መነሻ ነው የተቀበልነው። በጀርባ በኩል የሚመጣ ነገር አለ ብለን አላሰብንም። እየወቀስኩ አይደለም፣ መጡብን ብቻ ለማለት ነው። በቀና ልቦና ነገሮችን መውሰድ በእኔ እምነት የፖለቲካ ስህተት አይደለም።

ሰንደቅ፡- በሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚቀርበው ውህደቱ ሀገር በቀል ሳይሆን ውጭ ባሉ አካላት የተፈበረከ በመሆኑ ነው፣ ለአለመስማማት የዳረጋቸውም ከውጪ የመጣ ስለሆነ ነው እየተባለ ነው። በዚህ ላይ የእርስዎ ምላሽ ምንድን ነው?

አቶ አበባው፡- ትክክል ነው። ሆኖም ውህደቱን ሕዝቡ ይፈልገዋል። ዋናው ነጥብ መታየት ያለበት ይህ ይመስለኛል። ነገር ግን ከሁኔታዎች መነሻነት ከተመለከትነው የውህደቱ ጥንስስ ከውጪ ተቀምሮ የመጣ ነው የሚለው ጥርጣሬ ሚዛን የሚደፋ ነው። ስትራቴጂው የተነደፈው ውጪ ነው። ሀገር ውስጥ ያሉት አስፈፃሚዎች ናቸው። በእውነተኛ ፍላጎት የመጣ የድርድር ሂደት ቢሆን ስህተት ማንም ይስራ ማንም በትዕግስት ውህደቱን መፈጸም እንጂ ይቋረጥ የሚል የተጣደፈ የአደባባይ ምላሽ አይሰጥም። በእኛ በኩል ውይይቱ ይቀጥል እያልን እየጠየቅን በር ዘግተውብን ጥለውን ባልሄዱ ነበር። ስለዚህ የውህደቱ ቅመራው ያለው ውጪ ሀገር ነው።

ሰንደቅ፡- ቅመራው ውጪ ነው ብለው የሚያምኑ ከሆነ፣ እንዴት በዚህ ሂደት ውስጥ ተሳታፊ ይሆናሉ?

አቶ አበባው፡- ይህን ነጥብ በትክክል መመልከት ተገቢ ነው። የአንድነት ሥራ አስፈፃሚ እና የምክር ቤት አባላት ሁኔታውን በጥልቀት ሳይመለከቱት በቀናነት በተቆርቋሪነት እየሰሩ ነው የሚገኙት። የቅመራው ባለቤቶች አንዳንድ ግለሰቦች ናቸው። መታወቅ ያለበት ከአንድነት ፓርቲ ጋር የሚደረገው ውህደት በግለሰቦች ደረጃ እንጂ በተቋም ደረጃ አልሞተም። በርግጠኛነት ሁለቱ ፓርቲዎች ይህን ስልታዊ ቅመራ በጋራ በመሆን እናከሽፈዋለን። ምክንያቱም ይህ አሁን እየተቀነቀነ ያለው አስተሳሰብ የግለሰቦች በመሆኑ ነው። እንዲሁም የአንድነት ሥራ አስፈፃሚ የምክር ቤት አባላት ፍላጎት እንዳልሆነ ስለምንረዳ ነው። 

ሰንደቅ፡- በእናንተ አባላት የሚቀርበው ቅሬታ፣ አንድነት የመኢአድን መዋቅር ጠቅልሎ በመውሰድ ራሱን የበለጠ ለማደራጀት የሚፈልግ ፓርቲ ነው የሚል ነው፤ በዚህ ነጥብ ላይ ምን አስተያየት አልዎት?

አቶ አበባው፡- አንድነት መዋቅር አለው፣ የለውም የሚለው ክርክር እንደተጠበቀ ሆኖ፣ መኢአድ ያለውን መዋቅር ሰጥቶም ቢሆን ለሕዝባችን አማራጭ ፓርቲ መሆን በጋራ እስከቻልን ድረስ ብዙ ችግር የለውም።

ሰንደቅ፡- ሌሎች ወገኖች በበኩላቸው ገዢው ፓርቲ ሁለቱ ፓርቲዎች እንዳይስማሙ ሰርጎ ገብቷል እያሉ ነው የሚገኙት። ይህን ሃሳብ ምን ያህል ይጋሩታል?

አቶ አበባው፡- እንዲህ እንደሚባል እኛም እንሰማለን። የሚገርመው እኛ የተስማማነው ነገር ሳይኖር ገዢው ፓርቲ ምኑን ነው የሚያፈርሰው። አንድነት ከመድረክ ሙሉ ለሙሉ መውጣት አለበት ለሚለው ጥያቄ፣ አንድነት እንጂ ገዢው ፓርቲ ምላሽ መስጠት ያለበት አልመሰለኝም። መጠራጠሩ ግን ክፋት የለውም፣ ተጨባጭ ለማድረግ ግን ብዙ መስራት ይፈልጋል።

ሰንደቅ፡- በተደጋጋሚ ግለሰቦች እያሉ ነው። እነዚህ ግለሰቦች ለምን በይፋ በማሳወቅ አትታገሏቸውም?

አቶ አበባው፡- ጋዜጠኛ እንዲህ ብሎ አይጠይቅም። ከዚህ በፊት የነበረውን ቅንጅት ማን እንዳፈረሰው ታውቃላችሁ። ለምሳሌ ብርቱካን በእስር በነበረችበት ጊዜ ብርቱካን የታሰረችው በራሷ ችግር እንጂ በፓርቲ አይደለም። አዲስ ሰው መሾም አለበት ያለው ማነው? ከዚህ በፊት አንድነትን ከመድረክ ጋር ለማዋሃድ ሽማግሌ የነበሩት ሰዎች እነማን ናቸው? ከዶክተር ነጋሶ ጋር ከስምምነት የደረስንበትን ሰነድ አልፈርምም ያለው ማን ነው? ለምንስ ተደራዳሪ የነበሩት እንዲነሱ ተፈለገ? ድርድሩ ከቆመበት መጀመር ሲገባው ለምን እንደአዲስ እንዲጀመር ተፈለገ? ከመድረክ ውጪ ሆነናል ተብሎ በአደባባይ ከተናገሩ በኋላ፤ መለስ ብሎ ጋዜጦችን ጠርቶ ከመድረክ ጋር እንሰራለን ማለት ምን ማለት ነው? የአንድነት ወጣት አመራሮች መድረክን በአደባባይ እየተቃወሙ፣ ግለሰቦች ግን ከመድረክ ጋር እንሰራለን ለምን ይላሉ? ስለዚሀም የአንድነት ሥራ አስፈፃሚ እና ምክር ቤት ይህን እውነት ፈትሾ የውህደቱን ሂደት እንደሚቀጥል ተስፋ አለኝ። ይህ የማይሆን ከሆነም እንደበፊቱ በትብብር ለመስራት ዝግጁ ነን።

እሑድ 16 ማርች 2014

አንድነትና መኢአድ መጋቢት 11 የቅድመ ውህደት ፊርማ ሊያደርጉ ነው


የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት እና የመኢአድ ላዕላይ ምክር ቤት አባላት በጋር ባካሔዱት ስብሰባ ሁለቱ ፓርቲዎች የፊታችን ሐሙስ መጋቢት 11 ቀን 2006 ዓ.ም የቅድመ ውህደት ፊርማ እንዲያደርጉ መመሪያ ማስተላለፋቸውን ስብሰባውን የተከታተለው የፍኖተ ነፃነት ባልደረባ ዘገበ፡፡







ሰኞ 3 ማርች 2014

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብት አያያዝ አብጠለጠለ

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብት አያያዝ አብጠለጠለ

የካቲት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መስሪያ ቤቱ በ2013 ሪፖርቱ በአገሪቱ የሚታዩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በዝርዝር አስቀምጧል። በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚታዩት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መካከል ሃሳብን በነጻነት የመግልጽና የመደራጀት መብት ቀዳሚ መሆኑን ሪፖርቱ ይገልጻል።
ዜጎች በዘፈቀደ ይታሰራሉ፣ ይታፈናሉ፣ በእስር ቤት ይሰቃያሉ፣ ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ ይገደላሉ፣ በፖለቲካ አቋማቸው ምክንያት ማስፈራሪያ ይደርስባቸዋል እንዲሁም በእስር ቤት ውስጥ አሰቃቂ ድርጊቶች ይፈጸሙባቸዋል።
ፍርድ ቤቶች በመዳከማቸው የፖለቲካ ፍለጎት ማስፈጸሚያ መሳሪያ መሆናቸውን፣ ዜጎች መንግስትን የመለወጥ እድላቸው አነስተኛ መሆኑን፣ ፖሊስ፣ አስተዳደርና ፍርድ ቤቶች በሙስና የተዘፈቁ በመሆናቸው ተጠያቂነት ያለበት ስርአት ማስፈን አለመቻሉን ሪፖርቱ ያስረዳል።
በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎች ቁልቁል የፍጢኝ ታስረው የውስጥ እግራቸው እንደሚገረፍ፣ በውሃ ውስጥ እየገቡ እንዲሰቃዩ እንደሚደረግ፣ በእስር ቤት ውስጥ ድብደባ መፈጸምና ለህይወት አስጊ በሆነ እስር ቤት ውስጥ እንዲቆዩ በማድረግ መቅጣት በኢትዮጵያ የተለመደ ነው ብሎአል።
ከልካይ የሌለበት የሶማሊ ክልል ልዩ ሚሊሺያም ዜጎችን እንደፈለገ እንደሚገድልና እንደሚያስር፣ በክልሎች ውስጥ የሚገኙ ሌሎች ልዩ ሚሊሺያዎችም እንዲሁ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ጉዳይ አስፈጻሚዎች መሆናቸውን አትቷል።
ከሁለት አመት በፊት ባለው አሃዝ በ6የፌደራልና በ120 የክልል እስር ቤቶች ከ70 እስከ 80 ሺ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ወንጀሎች መታሰራቸውን የገለጸው ሪፖርት፣ በይፋ የማይታወቁ በጦር ካምፖች ውስጥ ያሉ እስር ቤቶችንም ዘርዝሯል። ደዴሳ፣ ብር ሸለቆ፣ ጦላይ፣ ሆርማት፣ ብላቴ፣ ታጠቅ፣ ጅጅጋ፣ ሆለታና ሰንቀሌ ስውር እስር ቤቶች ተብለው ተጠቅሰዋል።
የኢድ አል ፈጥር በአልን ለማክበር በስታዲየም ላይ ተገኝተው በነበሩ ሙስሊሞች ላይ መንግስት በወሰደው እርምጃ ከታሰሩት ወደ 1 ሺ ከሚጠጉት ሰዎች መካከል የተወሰኑት በእስር ቤት ውስጥ መሞታቸውንም ሪፖርቱ ጠቅሷል።
የሙስሊም ጉዳዮች መጽሄት አዘጋጅ ሰለሞን ከበደ በእስር ቤት ውስጥ ድብደባ እንደተፈጸመበት የጠቀሰው ሪፖርቱ፣ በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ርእዮት አለሙ፣ በ አንዱአለም አራጌ፣ ኦባና ሊሌሳ፣ በቀለ ገርባና ሌሎችም የፖለቲካ እስረኞች ላይ እየደረሱ ያሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን እንዲሁም በሴቶችና ህጻናት ላይ ስለሚደርሱ የመብት ጥሰቶች፣ በአናሳ ጎሳ አባላት ላይ ስለሚደረሰው መፈናቀልና ግጭት በዝርዝር አስቀምጣል።
የአሜሪካ ምክር ቤት የኢትየጵያ መንግስት የሰብአዊ መብቶች አያያዙን እስከሚያከብር ድረስ የ2014 እርዳታ እንዳይሰጥ  ህግ ማውጣቱ ይታወቃል። የኢትዮጵያ መንግስት እስካሁን ደረስ በዚህ ህግ ዙሪያ የሰጠው አስተያየት የለም።