ሰኞ 23 ጁን 2014

የአምባገነኖችና ዴሞክራሲ ናፋቂዎች ግብግብ በአዋሳ


አዋሳ ሆይ እስከመቼ የዳንስ ከተማ ብቻ እንድትሆኝ ይፈረድብሻል? የፖለቲካ ከተማም ሁኝ እንጅ!!!
የህዝቡ የለውጥ ፍላጎት ገፍቶ በወጣ ቁጥር የአምባገነኖች መደናበር ያይላል፡፡ ሲደናበሩም ህግ ይጥሳሉ፣ ህዝብ ያሰቃያሉ፣ ሀገር ይበድላሉ፡፡ ግን እድሜ ልክ ዕየተጨቆኑ መኖር አይቻልም፡፡ ‹‹ተቀምጦ ከመኖር ቆሞ መሞት ይሻላል›› እንዲሉ፡፡ ቆሜ መሞት ይሻለኛል የሚሉ ዴሞክራሲ ናፋቂዎች እየበረከቱ ነው፤ እምቢ ከፈለግህ ይሄው እሰረኝ! የሚሉ ትንታግ ወጣቶች እየተፈጠሩ ነው፡፡
እንደዚህ እንድል ምክንያት የሆነኝ ‹በደቡብ ክልል› አዋሳ ከተማ አንድነት ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቶ ነበር፡፡ ህጉንም ጠብቆ ለሚመለከታቸው አካላት አሳውቆም ነበር፡፡ ትናንት ይካሄድ ለነበረው የተቃውሞ ሰልፍም አዋሳ ካለው መዋቅር ጋር ተቀላቅለው ቅስቀሳ የሚያካሂዱ ትንታግ ወጣቶች ከአዲስ አበባ አዋሳ ገብተውም ነበር፡፡
ነገር ግን የአቶ ኃይለማርያምን በድጋፍ ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ በተለይ በደቡብ የገዥነት መጥፎ ስሜት የተጠናወታቸው የታች ባለስልጣናት ህግ በአደባባይ እየደፈጠጡ ነው፡፡ ስለዚህ በቅስቀሳ ላይ የነበሩትን አባላትና አመራሮች አሰሩ፡፡ ዴሞክራት ወጣቶች ግን በእስሩ አልተበገሩም ‹‹ህጉን ጠብቀን አሳወቅን፣ የእውቅናውን ደብዳቤ መስጠት ይህን ሊሰራ የተቀመጠው አካል ድርሻ ነው፡፡ እውቅና ወረቀቱን የሚሰጠው አካል ስራውን ስላልሰራ እኛ ስራ ማቆም የለብንም፡፡›› በማለት ስራቸውን እንደሚቀጥሉ አሳውቀዋቸዋል፡፡ ይህ የሆነው ሐሙስ ነበር፡፡ አሳሪዎቹ ያለምክንያት ማሰራቸው ሲያስጨንቃቸው ማታውኑ ‹‹ነገ እንዳትቀሰቅሱ፣ ከቀሰቀሳችሁ እናስራችኋለን›› ብለው ይለቋቸዋል፡፡
ትንታጎቹ የዴሞክራሲ ናፋቂዎች ግን ህገ ወጡን ትእዛዝ አልተቀበሉም፡፡ ህገወጡን ትእዛዝ ከመቀበል መታሰር እንደሚሻል ወሰኑ፡፡ አርብ ጠኋትም ወደ ቅስቀሳቸው ገቡ፡፡ አሳሪዎችም ካቴናቸውን ይዘው መጡና አሰሯቸው፡፡ በአጠቃላይ በአዋሳ የሚገኙ አመራሮችንና አባላትን ከየቦታው ለቃቅመው አሰሯቸው፡፡ ሰልፉም በዴሞክራሲ ደፍጣጮች ጉልበት ለጊዜው ተስተጓጎለ፡፡
ግን ግን ‹‹መብቴን አሳልፌ ከምሰጥ መታሰርን እመርጣለሁ!!!›› የሚለውን የዚህ ትውልድ ቁርጠኝነት እንዴት ማሸነፍ ይቻላቸዋል???

ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ጽ/ቤት የተሰጠ መግለጫ


በደቡብ ክልል በግንቦት 3/2006 በጐፋ ሳውላ በተደረገው የመኢአድ የተቃውሞ ሠላማዊ ሰልፍ ምክንያት በመኢአድ አባላት ላይ እየተፈጸመ ያለው የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዲቆም እንጠይቃለን፡፡
ኢህአዴግ የግንቦት 3 ቀን 2006 ዓ.ም የጐፋ ሳውላ ሰላማዊ ሰልፍን እቅድ ከሰማበት ጊዜ አንስቶና ከሰልፍ በኋላም እጅግ አስከፊ የሰብአዊ መብት ረገጣ እየፈጸመ ይገኛል፡፡ ይህም የሰላማዊ ትግሉን ሂደት ከምርጫ 2007 የቅድመ ዝግጅት የዕለት ተዕለት ሥራው አንዱ ዲሞከራሲን የማጥፋት ተግባር በመሆኑ ለጐፋ አካባቢ ከተማ ፍ/ቤት ጀምሮ እስከ ወረዳ ፍ/ቤቶች ከፓሊስ ኃይል ጋር በመተባበር እያጠቁ ናቸው፡፡ ተግባሩን በምንከታተልበት ጊዜም ሊያነጋግሩን ፈቃደኛ አይደሉም የዜግነት መብታችንም እየረገጡ ይገኛሉ፡፡
የደምባ ጎፋ ወረዳ ፍ/ቤት ተከሳሽ ኮልታ ቀበሌ የመኢአድ አመራሮች 1ኛ. አቶ ባሻ በላይነህ እና አቶ በቀለ ዋና በወረዳው የኢህአዴግ ካድሬዎች በአቶ ለሌ ለበኔ ተልካ ማሳቸውን ተነጥቀው እና የፓርቲ ኘሮግራም ከእጃቸው ተቀምተው በሐሰት ክስ ወንጀል ተከሰው የብዙ ቤተሰብ አስተዳዳሪ የሆኑት ለ3 ወር ያህል ወደ ወህኒ ተወርውረዋል፡፡ በጌዜ ጎፋ ወረዳ፡- 12 የመኢአድ አባላት የቀበሌ መዋቅር በኃይል ማፍረስ፣ በራሳቸው ጊዜ ስልጣን መያዝ፣ ልማትን ማደናቀፍ፣ ሕገ-መንግሥቱን በኃይል ለመናድና የመንግሥት ንብረት ማውደም በሚል መጋቢት ወር 2006 ዓ.ም በፋይል ቁጥር 03673 ተከሰዋል፡፡
ይህንም በይግባኝ በአዋሳ ጠቅ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ጉዳያቸው እየታየ እያለ በቀን 26/09/2006 ዓ.ም ከሳውላ ማረሚያ ፍ/ቤት በደረቅ ፖሊስ ጣቢያ መልሰው በማሰር በድጋሚ በሦስት የወንጀል ክሶች ማለትም 1ኛ. ዕውቅና ያልተሰጠ ስብሰባ በማድረጋቸው 2ኛ. 226 የመኢአድ አባላትን በማሰባሰብ የመኢአድን መታወቂያ የያዛችሁ በሙሉ የልማት ሥራ እንዳትሠሩ በማለት አስተባብሯል፣ የመንግሥትን ትዕዛዝ እንዳይፈጸሙ በማለት የውንብድና ወንጀል ፈጽመዋል የሚሉ ናቸው፡፡ 3ኛ. በቡልቂ ከተማ ውሰጥ በመሆን በስልጣን ያለውን የመንግሥት መዋቅር ሳያስፈቅድ የፓርቲ መዋቅር በመዘርጋት አመራር በመሾም 226 አባላት በማደራጀት በሕገ-ወጥ መንገድ መዋጮ አሰባስቧል ተብለው ታስሯል፡፡
የአይዳ ልዩ ወረዳ ፍ/ቤት እነ አቶ አልታዬ ኤሶ 7 የመኢአድ አመራሮችና አባላትን በመንግሥት ላይ የሐሰተኛ ሐሜት በማነሳሳት በማለት በወረዳ ፋ/ቁ. 07417 ተከሰው በጎፋ አካባቢ ፍ/ቤት ፋይል ቁ. 10492 በተሰጠው ውሳኔ 1ኛ. በፋ/ቁ. 06362 በ16/09/05 የመንግሥት ሥራ አስናከሉ ከማለቱ በፊት ለ3 ወራት አስሯቸዋል፡፡ 2ኛ. በፍይል ቁ.06656 በቀን 09/05/2006 የሙታን ክብር በመንካት በሚል 300 ብር ተቀጥተዋል፡፡ 3ኛ. በፋ/ቁ. 06298 በቀን 27/06/05 በብር 150.00 ቅጣት ተከሰው ተቀጥተዋል፡፡ በ1ኛ ተከሳሽ ላይ 1 ዓመት በ8ኛ እና በ2ኛ ተከሳሽ ላይ 10 ወር በ3ኛ ተከሳሽ እና 5ኛ ተከሳሽ ላይ 9 ወር የተፈረደባቸው ሲሆን ይህ ድርጊት በቂም በቀልነት የተፈፀመ እየገለጽን፣ በመኢአድ ፓርቲ ተደራጅተው የመቃወም መብት አጥተው ሰላማዊ ትግሉን እንዲያቋርጡ የአፈና ተግባር እየተፈጸመባቸው ስለሆነ በአስቸኳይ እንዲቆም እንጠይቃለን፡፡
አንዲት ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)

ሰኞ 12 ሜይ 2014

መኢአድ ሳዉላ

መኢአድ ሳዉላ የተቃዉሞ ሰልፍ

 መኢአድ ሳዉላ
የተቃዉሞ ሰልፍ
ከ30000 ህዝብ በላይ በተቃዉሞ ሰልፍ ተገኝቶል፡፡
ፖሊስ እና የወያኔ ደህንነት ከፍተኛ ግፍ ፈጥሞል፡፡
የመኢአድ አመራሮች ኪሳቸዉ ሳይቀር ተፈተሸ፡፡
ደቡብ ኦሞ የትጥቅ ትግል ተጠናክሮል፡፡
የነፍጠኛዉ ቤዝ ደቡብ ነዉ ተባለ፡፡
ሰልፉ ከፍተኛ መሰዋትነት ተከፍሎበት በድል ተጠናቆል፡፡
ወያኔ የሞት ሞቱን ተፍጨርጨር፡፡
ሰላማዊ እንቢተኝነት በተግባር ዋለ፡፡
ቪዲወ እንለቃለን
ኔትዎርክ ሙሉ በሙሉ በሳዉላ ከተማ አልነበረም፡፡
ከምሽቱ 4 ሰዓት የመኢአድ አመራሮች ወላይታ ሶዶ ገቡ፡፡

 

ቅዳሜ 3 ሜይ 2014

Ethiopia: John Kerry raised concerns over the detention of bloggers

Ethiopia growth strains expose political fault-lines

US Secretary of State John Kerry yesterday raised concerns with the Ethiopian government about the detention in the past week of several journalists and bloggers. A number of opposition Blue Party members were also arrested last week ahead of a planned demonstration. US and other donor influence on the question of media freedom and repression of opposition is fairly limited, despite Ethiopia’s dependence on foreign aid. Nevertheless, the recent clampdown — coming amid a wave of protests by students at universities in the Oromo regional state against the pace of the capital city Addis Ababa’s expansion — highlights tensions created or exacerbated by the aggressive growth policies of the ruling Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF).

Secretary Kerry Speaks During News Conference in Ethiopia

በሰፊው የኦሮሞ ህዝብ እና ልጆች ላይ እየተፈፀመ ያለውን ግፍ በአጽንኦት እናወግዛለን!!! ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በኢትዮጵያ የመሬት ስሪት ላይ ግልፅ አቋም እና ፖሊሲ ያለው ፓርቲ መሆኑ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ በዚህም መሰረት መሬት በሦስት መሰረታዊ አውድ ላይ እንዲመሰረት ይህም ማለት በወል፣ በመንግስትና በግል ይዞታነት እንዲከበር አቋም ይዞ ይታገላል፡፡ ነገር ግን ከወልና ከመንግስት ውክልና ውጪ ያሉት ይዞታዎች በግል ይዞታነት እንዲከበሩ አቋም ይዞ ይታገላል፡፡ ኢህአዴግ የገጠሩ መሬት የግል ከሆነ አርሶ አደሩ መሬቱን እየሸጠ ወደ ከተማ ይፈልሳል ብሎ ያምናል፡፡ ከምንም የተነሳ ስጋት ነው ባይባልም አንኳ ኢትዮጵያውያን ከመሬት ጋር ያለንን ስነልቡናዊ፣ ማህበራዊና ሁለንተናዊ መስተጋብርን ያላገናዘበና የተጋነነ ስጋት ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ከመሬት ጋር የተለየ ቁርኚት እንዳላቸሰው ለማወቅ ሞታቸውን ሲያስቡ እንኳ “የሀገሬ አፈር ይብላኝ” ሲሉ መመኘታቸው በቂ ማስረጃ ነው፡፡UDJ/Andinet party logo
ኢህአዴጎቹም በቀድሞ ስርዓት ሲተገበር የታገሉትን የመጨቆኛ መሳሪያ ለራሳቸው ሲሆን ተጠቀሙበት፡፡ የሆኖ ሆኖ ይህ የኢህአዴግ ስጋት እውነት ነው እንኳ ቢባል ኢህአዴግ የከተማውን መሬትስ የግል ይዞታ ያላረገው ከተሜው ወዴት እንዳይሰደድ ነው? ዋናው የገዥው ፓርቲ ፍላጎት መሬትን በጁ በማድረግ የዜጎችን ነፃነት በዚያኑ ያክል ለመሸበብ ነው፡፡ አርሶ አደሩም ሆነ የከተማው ህዝብ መሬት የኔ ነው ብሎ ካመነ ለኢህአዴግ ጫና ስለማያጎበድድ መያዣ ለማድረግ ነው፡፡ የህዝቡ የመሬት ባለቤትነት ቢረጋገጥ በመንግስትና ለኢንቨስትመንት በሚፈለጉ መሬቶች ላይ የመደራደር አቅሙ እጅግ ከፍ ይላል፡፡ መሬቱን በመልቀቁ በሚሰጠው ካሳ (ዋጋም) በቂ የኑሮ ዘዬ ሽግግር የሚያገርግበት አጋጣሚ ይፈጥራል፡፡ ይህ ሊሆን አልቻለም፡፡ በ02/ 08/ 06 ዓ.ም ቡራዩ አካባቢ በተደረገ የመሬት የሊዝ ጨረታ ለተነሺው አርሶ አደር በካሬ 10 ብር የታሰበለት መሬት በጨረታ በካሬ 17 ሺህ ብር መሸጡን ፓርቲያችን ያሰባሰበው ማስረጃ ያሳያል፡፡ በ10 ብር የታሰበለት አርሶ አደር የሚሰደደው በዚህ መልኩ መንግስት ሲቀማው እንጂ የመሬቱ ባለቤት ሆኖና ተደራድሮ በሚሸጥበት ወቅት አልነበረም፡፡
መሬት የምርጫ ድምፅ መያዣ፣ ለኢህአዴግ ገንዘብ ማሰባሰቢያ እና የድጋፍ ምንጭ ሆኗል፡፡ በቅርቡ በጉጂ ዞን ኦዶ ጉዶ አካባቢ ለ2007 ዓ.ም ምርጫ ሞዴል የተባሉ አርሶ አደሮች በቁጥር ከፍ እንዲሉ እንደሹመት ተሰጥቷቸው ሲያበቃ 500 ብር እንዲያዋጡ የመሬት ይዞታቸው ለማስፈራሪያነት መዋሉ እንደማሳያ ሊወሰድ ይችላል፡፡
በሌላ በኩል ምንም አይነት ህዝባዊ ውይይት ሳይደረግበት ከሰማይ ዱብ ያለው የአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የልማት መሪ ፕላን ያስቆጣቸው የኦሮሞ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሰልፍ በማድረጋቸው የደረሰባቸውን ህገ ወጥ ድብደባና እስራት አንድነት በእጅጉ ይቃወማል፡፡ ለእውነተኛ ልማት ነው እንኳ ተብሎ ቢታሰብ ኢህአዴግ ካለበት የተአማኒነት ችግር የተነሳ ተማሪዎቹ ለተቃውሞ አደባባይ ቢወጡ ተፈጥሯዊ እና ህገ መንግስታዊ መብታቸው ሊከበር በተገባ ነበር፡፡ ነገር ግን ሁሉን ነገር ካልጋትኳችሁ የሚለውና ለዴሞክራሲያዊ ሽንፈት የማይገዛው ኢህአዴግ በተማሪዎቹ ላይ ያደረሰውን እንቃወማለን፡፡ የታሰሩ ተማሪዎችም በአስቸኳይ እንዲፈቱም እንጠይቃለን፡፡ የኦሮሞ ተማሪዎችን በገፍ ከዩኒቨርሲቲ የትምህር ገበታቸው በማባረር የሚታወቀው የኢህአዴግ መንግስት ከዚህ ተደጋጋሚ ተግባሩ ታቅቦ ልጆቹን በአስቸኳይ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመልስ እንጠይቃለን፡፡
በአጠቃላይ መሬት የዜጎች መያዣ መሆኑ እንዲቀር እንታገላለን፡፡ ዜጎች በመሬታቸው የመደራደር እውነተኛ መብት ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ተቃውሞ የሚያነሱ ዜጎችም ድምፅ እንዲሰማ እናሳስባለን፡፡
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ
ሚያዚያ 22 ቀን 2006 ዓ.ም
አዲስ አበባ

ወያኔ የሚፈራው ምርጫ ወይስ ሕዝባዊ እምቢተኝነት (አመጽ)


በዚች አለም በሕዝቦቻቸው ላይ የሚፈነጩ አምባገነኖችን ለማስወገድ የሚደረጉ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች ሁሉ የወያኔ ዘረኛችን ለምን ሲያስደነብራቸውና በፍርሃት ሲያሸማቅቃቸው እንደሚኖር የሁሉም ሰው ጥያቄ ነው፡፡ የህውሃት ዘረኛ ቡድን በሕዝብና በሃገር ላይ የሚያደርሰው መጠነ ሰፊ ጥቃት ወይም ውድመት በተለያየ መንገድ ሕዝቡ ቅሬታውን ቢያሰማም እራሱ ለፈጠረው ዘርፈ ብዙ ችግር መፍትሄ ከመሻት ይልቅ የሕዝቡን ብሶት ለማዳፈን ሀላፊነት የጎደለው ተግባራትን እየፈፀመ ሃገርን የመበተን ስራውን ቀጥሎበታል፡፡The long youth march to freedom and dignity has begun in Ethiopia. It is beautiful.
በአዋጅ የተደነገጉ የሕዝብን አሳብን በነጻነት የመግለጽ፣ የመደራጀትና የመሰብሰብ እንዲሁም ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብትን እየሸረሸሩና አዋጅን በተራ መመሪያ እየሻሩ የስቃይ ቀንበሩን ያከብዱበታል ፡፡በየትኛውም ሁኔታ ማለትም የሰብአዊ መብቱ የተረገጠውን፣ የሃገሬ ጉዳይ ያገባኛል ስላለ እንደ ሁለተኛ ዜጋ እየታየ የሚሰቃየውን የነፃነት ታጋይ፣ በስርዓቱ ብልሹና የተዝረከረከ አሰራር በኑሮ ውድነት እየማቀቀ ያለው የህብረተሰብ ክፍል ለጥያቄው ተገቢውን መልስ ወይ መፈትሄ ከመስጠት ይልቅ በተራ ካድሬያዊ ዲስኩር ከላይ ለዘረኛው ስርዓት ቃል አቀባይ ከሆነው ጠ/ሚ ተብዬው እስከ ልማታዊ ጋዜጠኛ ነን እስከሚሉት ድረስ በርሃብ ለጠወለገው ምስኪን ሕዝብ ጥጋብን፣ በገዛ ሃገሩ ፍትህ አጥቶ ለሚሰቃየው ፍትሃዊነትን እንዲሁም ሰብአዊ መብቱ ተገፎ ነፃነቱን ለተነጠቀው ሕዝብ ዴሞክራሲን ነጋ ጠባ ይሰብኩታል፡፡
ይህው የወያኔ ዘረኛ ቡድን ስለፈጠረው ሃገራዊ ቀውስ ብዙ ብዙ ቢባልም የዚህን መርዘኛ ስርዓት ሰንኮፍ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ነቅሎ ለመጣል ከምርጫ ይልቅ ሕዝባዊ እምቢተኝነት(አመጽ) ስለመሆኑ ስርዓቱ በሚያሳየውና ከሚሰጋባቸው ነገሮች ለመረዳት ይቻላል፡፡
እንደሚታወቀው በተደጋጋሚ የተካሄዱት ምርጫዎች ከምርጫ 97 ውጪ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ለወያኔ መሳሪያ ከመሆን ወጪ የስርዓቱ የአፈና መዋቅር ተቃዋሚዎችን የሚያወላዳ አልነበረም፡፡ ይህ ማለት ይካሄዱ የነበሩ ምርጫዎች በህውሃት ዘረኛ ቡድን በተጠና የአፈና እንዲሁም በዋነኝነት ምርጫን ምርጫ ሊያሰኙ የሚችሉ ገለልተኛ ተቋማት በጠቅላላ በስርዓቱ መዋቅር የተዋጡና የተተበተቡ በመሆናቸው ለመገናኛ በዙሃን ሸፋንና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ መደለያ ካልሆነ በስተቀር ምርጫው ሳይጀመር ውጤቱ የታወቅ እንደ ነበር ከማንም የተሰወረ አደለም፡፡ ስለሆነም የህውሃት ቡድን አምስት አመት ጠብቆ የሚመጣ ምርጫ ከላይ እንደተጠቀሰው ለአንዳንድ ግብአት ይጠቀምበት እንደሆን እንጂ ምርጫ ስለተቃረበ እንቅልፍ የሚያጣ አይመስልም ምክንያቱም የምርጫ አስፈጻሚ አካላት እስከ ፍትህ ስርዓቱ በእጁ ናቸውና፡፡
የልቁንም ለዚህ እኩይ ስርዓት የራስ ምታት የሚሆንበትና ሰላም የሚነሳው ሕዝባዊ እምቢተኝነት(አመጽ) ነው፡፡ በቃ የሚል ትውልድ ግፍና በደል ያንገሸገሸው ሕዝብ ለመሆኑ ማሳያ ይሆኑ ዘንድ አንዳንድ ነጥቦች እናንሳ፡፡
ከአመታት በፊት ቱኒዚያዊው ሙሃመድ ቡዋዚዝ የቢን አሊን አንባገነን መንግስት በሃገሩ በቱኒዚያና በሕዝቧ ላይ የሚያሳደረውን ዘርፈ ብዙ ችግር በመቃወም እራሱ ላይ ነዳጅ አርከፍክፎ ካቃጠለ በሗላ ቱኒዝያን ጨምሮ ሊቢያ፣ ግብጽ፣ የመን፣ እስካሁንም በነወጥ ውስጥ ያለች ሶሪያ የደረሰውን ሕዝባዊ እምቢተኝንትና በየሃገሩ የተለኮሰው አመጽ የወያኔን ዘረኛ ቡድን ያስፈራውና ያሸማቀቀውን ያህል አምስት አመት ጠበቆ የሚካሄደው የየስሙላ ምርጫ አላሸበረውም፡፡
ይህንንም ለመገንዘብ በዛን ወቅት ሟቹ መለስ ዜናዊ የወሰዳቸውን እርምጃዎች ማየት የበቃል፡፡ በመጀመሪያ የአረብን አለም አብዮት የሚዘገቡ አለም አቀፍ የመገናኛ ቡዙሃንን ማፈር ቀዳሚ ተግባሩ ነበር ሆኖም መረጃው በተለያየ መንገድ ሕዝብ ጋር መድረሱን የተረዳው ሟቹ ጠ/ሚንስትር የሕዝብን መንፈስ ለመሳብና ቤሔራዊ ስሜትን ሰቅጦ ይይዝልኛል ያለውን መላ ምቱ ዘየደ ባይሳካም ኤርትራን ለመውረር መዘጋጀቱን ማወጅ ነበር፡፡ ይህ ሁሉ የሚሆነው አብዮቱ የኢትዮጲያንም በር እንዳያንኳኳ ካለው ከልክ ያለፍ ፍርሃት ነበር፡፡ ሆኖም ሕዝብ ኖሮውን እንጂ የወረራ ዲስኩር ችላ እንዳልው ሲረዳ በኤኮኖሚም በፖለቲካ እንዲሁም ሃገራችን ያላትን መልካም የውጪ ገንኙነት የላገናዘበ በተጨማሪም በባለሞያዎች በቃ ጥናትና ምርምር ያልተደረገበትን እስካሁንም ዘርፈ ብዙ ችግር አዝሎ የሕዝብ ኪስ የራቆተውን የአባይ ግድብን እንካችሁ ብሎ ሻማ አለን፡፡ የሟቹን አላማ ይህኛው በተወሰነ መጠን አሳካለት ሆኖም አብዮት የፈራው ወይም ሕዝባዊ እምቢተኝነትን የፈራው የህውሃት ዘረኛ ቡድን የማይገፋ እዳ ለሃገርን ለሕዝብ ትቶ ችግሩን ፍርሃቱ ፈታበት፡፡
በተጨማሪ ይህው ዘርኛ ቡድን በአለም ዙሪያ የተደረጉ የተሳካላቸው ምርጫዎችን እያነሳ የሰጋበት ግዜ አይታወስም፡፡ በአንጻሩ ምርጫ ያጭበረበሩ አምባገነኖችን ሕዝብ ሲቃወምና ድምጹን ለማስመለስ የሚያደርገውን የነፃነት ትግል አሉታዊ መልክ ሰጥቶ ባዘጋጃቸው የፖለቲካ ተንታኝ ተብዬዎች ውግዝ ከማርዮሰ ሲያስብላቸው ይውላል፡፡ በየትኛውም መልኩ የሚካሄዱ ሕዝባዊ እቢተኝነት(አመጽ) ከማውገዝ ወደ ሗላ ብሎ የማያቀው ይህ ስርዓት ሰሞኑን ዘጋቢ ፊልም መስራት በማይሰለቻቸው ልማታዊ ጋዜጠኞቹ ይቀርብ የነበረው የዚሁ የፍርሀትና እራሱን እየከፈነ ያለው ያበቃለት የህውሃት ዘረኛ ቡድን ቅዠት ነው፡፡
ቅዠቱ የቀለም አብዮት ይልና ከብርቱካናማው የዩክሬን አብዮት ጀምሮ ቬንዙዌላ የድርሳል አጠቃላይ ምልከታው አብዮት ወይም ሕዝባዊ እምቢተኝነት የሚከናወነው ሕዝብ ፈልጎት ሳይሆን ከምዕራባዊያን እዲሁም በምዕራባዊያን ሃገራት ከሚኖሩ ዜጎች ፈላጊነት የሚመነጭ ነው ይለናል ኸረ እንደውም እነዚሁ ምዕባዊያን የማይፈልጓቸውን መንግስታት የሚያሶግዱበት አንዱ መሳሪያ ሕዝባዊ አመፅ ነው በማለት ይቀጥላል፡፡ ሌላው የሚገርመው የ 97 ምርጫን ተከትሎ ሕዝብ የተቀማ ድምጹን ለማሰመለስ ያደረገውን እንቅስቃሴና ንጹሃን ወገኖቻችንን በዚሁ ዘረኛ ቡድን የተነጠቅንበት ትእይንትም እንደ ዘጋቢ ፊልሙ አገላለጽ በሌሎች ሃገራት እንደተደረገው ሁሉ በምህራባዊያንና በነዚሁ ሃገራት በሚኖሩ ዜጎች የተቀነባበረ እንደሆነ ያትታል፡፡ የሚገርመው ታዲያ ወያኔን ይህንን ያህል ዘመን በሕዝብ ጫንቃ ላይ ያስቀመጡት እነሱ ምዕራባዊያን ሆነው ሳለ ስጋቱን ምን እንዳመጣው ነው፡፡
ሕዝብ ለሚያቀርበው የመልካም አስተዳደር ጥያቄ፣ የፍትህ ጥያቄ እንዲሁም የዴሞክራሲና የነፃነት ጥያቄ ጀርባ ሰጥቶ በትምክህት መኮፈስ በቃኝ ለሚል ለውጥ ፍላጊ ትውልድ እሳት ላይ ነዳጅ እንደማርከፍከፍ ነው፡፡ የህውሃት ዘረኛ ቡድን አሁን የተያያዘው መንገድ ይህው ነው፡፡
ምን ያለበት ምን አይችልም እንደሚባለው የትም ይሁን የት መሰል የአመባገነኖችን ዙፋን የሚያነቃንቅ ሕዝባዊ አመጽ የሕውሃት ቡድን እራስ ምታት ነው፡፡ ሕዝብንም በመከፋፈልና በመለያየት የተጋው ፍርሃቱን ለማብረድ ነው፡፡ በተረፈ አምስት አመት ቆጥሮ የሚመጣን ምርጫ ያውም 99.6% ሊሰርቅበት የሚችል ለእርሱ በእርሱ የተከፈተ የምርጫ ስርዓት ያሰጋዋል ተብሎ አይገመትም፡፡ ከላይ እንደተገለጸው በፍርህት የሚያርደውም የሚያሶግደውም ሕዝባዊ እምቡተኝነት(ሕዝባዊ አመጽ) ነው፡፡ በተለይ አሁን ስርዓቱ በስብሶ እራሱን በገነዘበት ሰዓት ሊቀብረው የሚችል በኢትዮጲያዊነት ጥላ ስር በአንድነት የተደራጀ በቃ በሎ ነፃነቱ የሚያውጅ ተውልድ ነው!!!
ድል ለኢትዮጲያ ሕዝብ!!!