መገናኛ አካባቢ ወደ ጉርድ ሾላ በሚወስደው መስመር፣ አንድ መንገደኛ ትናንት ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ሚኒባስ ታክሲ ውስጥ ካልተሳፈርኩ ብሎ ሾፌሩን ወንደሰን ደምሴን በሽጉጥ ገደለ፡፡ “ታክሲው ውስጥ ካልተሳፈርኩ፣ አትሳፈርም” በሚል በተነሳው ጭቅጭቅ፣ ሾፌሩን ገድሏል የተባለውን ደጀኔ ገመቹ በቁጥጥር ስር እንደዋለ የገለፀው ፖሊስ፤ የአይን ምስክሮችን ቃል በመቀበል ምርመራ እያካሄደ ነው፡፡ ታክሲ እየጠበቁ የነበሩ የአይን ምስክሮች በወቅቱ አቶ ደጀኔ እጁን በማወዛወዝ ሚኒባስ ታክሲውን እንዳስቆመ ተናግረው፣ ከሾፌሩ ጋር ጭቅጭቅ እንደተፈጠረ ገልፀዋል፡፡ አቶ ደጀኔ በታክሲው ለመሳፈር ሲጠይቅ፣ ሾፌሩ “ቤተሰቤን ነው የጫንኩት፣ ሌላ ሰው አላስገባም” በማለት ምላሽ እንደሰጠው በአካባቢው የነበሩ መንገደኞች ተናግረዋል፡፡ ታክሲ የሚጠባበቁ ብዙ ሰዎች በአካባቢው ስለነበሩ፣ ጭቅጭቁን ከመነሻው እስከ መጨረሻው የተመለከቱ እማኞች በርካታ ናቸው፡፡ የፖሊስ መረጃ እንደሚጠቁመው፤ የሾፌሩ አባት ታክሲው ውስጥ ነበሩ፡፡ “አትሳፈርም የምትለኝ ንቀት ነው” በሚል ክርክርና “የጫንኩት ቤተሰቦቼን ስለሆነ ሌላ ሰው አልጭንም” በሚል ምላሽ በተባባሰው ጭቅጭቅ፣ አቶ ደጀኔ ሽጉጥ እንዳወጣ እማኞች ተናግረዋል፡፡ ሽጉጡን ሾፌሩ አንገት ስር በመደገን ነው የተኮሰው ብለዋል-ምስክሮች፡፡ በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሰው መግደል ዲቪዥን ክፍል ተወካይ፣ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን ገልፀዋል።
ቅዳሜ 28 ዲሴምበር 2013
ረቡዕ 25 ዲሴምበር 2013
ሚሊየነሩ ኒቆዲሞስ ዜናዊ (ከእየሩሳሌም አርአያ)
ኒቆዲሞስ ዜናዊ የአቶ መለስ ዜናዊ ወንድም ነው። ከወ/ሮ አለማሽ ገ/ልኡልና ከአቶ ዜናዊ አስረሳኸኝ የተወለዱ ወንድማማቾች ናቸው። ኒቆዲሞስ በደርግ ስርአት በክብሪት ፋብሪካ ተቀጥሮ በተራ ሰራተኝነት ይሰራ ነበር። የአካል ጉዳተኛ (አንድ እግሩ) የሆነው ኒቆዲሞስ ከተራ ወዝአደርነት ወጥቶ ሚሊየነር ለመሆን የበቃው ደርግ ወድቆ ሕወሐት/ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ ነበር። የፋብሪካ ስራውን በግንቦት 1983ዓ.ም ማግስት የለቀቀው የአቶ መለስ ወንድም ኒቆዲሞስ ከአሜሪካ በ25ሺህ ዶላር የተገዛች አዲስ አውቶማቲክ ማርሽ አውቶሞቢል እንዲይዝ ተደረገ። ተራ ወዛደር የነበረ ሰው 25ሺህ ዶላር የሚያወጣ መኪና ሊገዛበት የሚችል የገንዘብ አቅም እንደሌለው ግልፅ ቢሆንም ነገር ግን ይህን ያክል የገንዘብ መጠን በማውጣት ለኒቆዲሞስ የተበረከተለት ስጦታ ወንድሙ አቶ መለስ ዜናዊ የሚመሩት ሕወሐት እንደሆነ ሳይታለም የተፈታ ነበር። ይህም ብቻ አይደለም፤ ኒቆዲሞስ አካል ጉዳተኛ ነው በሚል ሰበብ አውቶሞቢሉ የጉምሩክ ቀረጥ ሳይከፈልበት ነበር አገር ውስጥ የገባው። ይህን ጉዳይ በተመለከተ “ወጋህታ” የተባለች በትግርኛ ቋንቋ በአገር ውስጥ ትታተም የነበረች የነፃው ፕሬስ ጋዜጣ ከጉምሩክ ለኒቆዲሞስ ዜናዊ ያለቀረጥ መኪናው እንዲገባ የተሰጠውን፣ በስሙ ተፅፎ ከነመኪናው ሻንሲ ቁጥር ጭምር የተገለፀበትን ደረሰኝ ማስረጃ በማውጣት ጋዜጣዋ አጋልጣለች። ከዜና ዘገባው ጋር በተያያዘ በወቅቱ በተለያዩ ጋዜጦችና ሌሎች ወገኖች ከተነሱት አስተያየት አዘል ጥያቄዎች ተከታዩ ዋናው ነበር፤ « ..ኒቆዲሞስ ዜናዊ ያለቀረጥ አውቶሞቢል እንዲገባለት የተደረገው ከበላይ አካል በተላለፈ ቀጭን ትእዛዝ ነው። የገንዘብ ምንጩ የገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት እንደሆኑ ግልፅ ነው። ከመኪናው ግዢ እስከ ጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ፍቃድ ድረስ ሙስና ተፈፅሟል። ኒቆዲሞስ ይህን ህገ-ወጥ ጥቅም እንዲያገኝ ሲደረግ የአገሪቱ መሪ አቶ መለስ ወንድም በመሆኑ ነው። ስለዚህም በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ አቶ መለስ ከሙስናው ጋር በተያያዘ ሊጠየቁ ግድ ነው። ለምሳሌ በሙስና እንዲከሰሱ ከተደረጉት ባለስልጣናት አንዱ አቶ ስዬ አብርሃ የቀረበባቸው ክስ በቂ ማስረጃ ወይም ማመሳከሪያ ነው። አቶ ስዬ ለወንድማቸው ምህረተአብ አብርሃ ሰባት መኪኖች ያለቀረጥ እንዲገቡ አድርገዋል የሚለው ክስ ይጠቀሳል። አንድ መኪና ሆነ ሰባት አሊያም ሰባት መቶ..ቀረጥ እስካልተከፈለባቸው ድረስ ሙስና ለመሆኑ አያጠያይቅም። ስለዚህም የኒቆዲሞስ ጉዳይ ሙስና መሆኑ ግልፅ ነው። ከተፈፀመው ቀረጥ ያለመክፈል ክስ ጋር ኒቆዲሞስና ወንድሙ አቶ መለስ በሙስና ሊከሰሱ ይገባ ነበር። » የሚሉ ነጥቦች ነበሩ ከተለያዩ ወገኖች ይነሱ የነበረው። ይህ ጉዳይ በተለይ በስፋት አነጋጋሪ ሆኖ የነበረው በዘጠናዎቹ የመጀመሪያ አመታት ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ተከታዩ ነው። ኒቆዲሞስ ዜናዊ ከተራ ወዝአድርነት ወጥቶ በአንድ ግዜ ሚሊየነር የሆነበት ሚስጥሩ በ1988 ዓ.ም አንድ የኤርትራና ጣልያን ዘር ያለው ግለሰብ ከሮም አዲስ አበባ ይመጣል። ከዚያም ከኒቆዲሞስ ዜናዊ በጋራ « ጃክሮስ ኢትዮጲያ » የተባለ ድርጅት ያቋቁማሉ። ኒቆዲሞስ የጃክሮስ ግማሽ (50%) ባለድርሻ ሆኖ ነበር ድርጅቱ የተመሰረተው። “ጃክሮስ” በተቋቋመ ማግስት የመንግስት ሚዲያ የሆኑትን የኢትዮጲያ ቴሌቪዥንና ራዲዮ እንዲሁም ፋና ራዲዮ በማስታወቂያ ተቆጣጠረው። በተጨማሪ የአማረ አረጋዊ « ሪፖርተር » ጋዜጣ ማስታወቂያ በተጋነነ መልኩ ከማውጣት ባለፈ ስለ ድርጅቱ (ጃክሮስ) ሰፊ የዜና ዘገባና ትንታኔ በመስራት ተከታታይ ሽፋን መስጠት ያዘ። በጋዜጣውና በመንግስት መገናኛ ይቀርቡ የነበሩት ማስታወቂያዎችና ዘገባዎች ፥ « ..ጃክሮስ ኢትዮጲያ, በአገራችን የመጀመሪያው የመኖሪያ ቤት ግንባታ የሚያካሂድ፤ እጅግ ዘመናዊ የሆኑ ቪላዎችን በመገንባት ለደንበኞቹ በአጭር ግዜ ውስጥ ሰርቶ የሚያስረክብ ነው፤ ለግንባታ ከሚጠቀማቸው ቁሳ-ቁሶች መካከል በተለይ ለቪላው ማሳማሪያ የሚጠቀማቸው ከውጭ አገር የመጡና ዘመናዊ ናቸው፤ እንደ ደንበኛው ፍላጎትና ምርጫ የሚገነባው በቂ የዋስትና ሽፋን በድርጅቱ የሚሰጠው ሲሆን፣ ጃክሮስን የተለየ የሚያደርገው የሚገነቡት ቪላዎች ስታንዳርዳቸውን የጠበቁና የውጭ አገር ዘመናዊ ቪላዎች አይነት መሆናቸው ጭምር ነው። ደንበኛው ሙሉ ክፍያ የሚከፍል ከሆነ በአንድ አመት ግዜ ውስጥ መኖሪያውን አጠናቆ ያስረክባል፤ ከደንበኛው ጋር በሚደረግ ስምምነት ክፍያው ተፈፃሚ ይሆናል፤ ይህ ማለት የረጅም አመት ክፍያ ድርጅቱ ይሰጣል።…» የሚሉት በተጋነነ መልክ ይቀርቡ ከነበሩት ይጠቀሳሉ። ድርጅቱ እንደ ሽፋን የተጠቀመበትና የተጠቀሱት ሚዲያዎች ያራግቡ የነበረበት አንድ አጋጣሚ ተፈጥሮ ነበር። በ1988ዓ.ም የአትላንታ ኦሎምፒክ የሚካሄድበት አመት ነበር። እነ ሃይሌ ገ/ስላሴ ለመጀመሪያ ጊዜ ኦሎምፒክ የሚሳተፉበት፣ እነ ፋጡማ ሮባና ደራርቱ ቱሉ የተካተቱበት ጭምር ነበር። ሁሉም ኢትዮጲያዊ ማለት ይቻላል ከወራቶች ቀደም ብሎ ውድድሩን በጉጉት እንዲጠብቅ የተገደደበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር። “ጃክሮስ” ይህን አጋጣሚ ለመጠቀም ኢላማ አድርጎ የተነሳው የአንጋፋው አትሌት ሻለቃ ዋሚ ቢራቱን ቤት በነፃ እገነባለሁ በሚል ነበር። በቀድሞ ወረዳ 12 ቀበሌ 07 የሚገኘውን የዋሚ ቢራቱ መኖሪያ በሁለት ወር ውስጥ ሰርቶ እንደጨረሰ ተናገረ። ቀደም ሲል የነበረውን የዋሚ ቤት በማደስ የሰራውና በከፍተኛ ደረጃ የተራገበለት መኖሪያ በቲቪ መስኮት የታየውና ተጨባጩ እውነታ ለየቅል ነበሩ። ለቤቱ ግንባታ ተብሎ ዙሪያውን የዋለው ለተለያዩ ቁሳቁሶች ማሸጊያነት (ለምሳሌ ከውጭ የሚገቡ ፍሪጆችና ቴፕ..ወዘተ ጉዳት እንዳይገጥማቸው ከውስጥ በማሸጊያነት ) የሚውለው ፎም ነበር። ከዚያ በቀለም እንዲያሸበርቅ ከተደረገ በኋላ « 2 ሚሊዮን ብር በማውጣት ጃክሮስ ለዋሚ ቢራቱ ቤት ገንብቶ አስረከበ..» ተብሎ በጋዜጣውና በሚዲያ አስነገረ። አንጋፋው አትሌት በወቅቱ ከአሜሪካ ለመጣውና ቀበሌ 11 ለሚኖረው እስክንድር አሰፋ ስለቤቱ ሲናገር በሃዘን ጭምር ነበር፤ « የበፊቱ መኖሪያዬ ይሻለኝ ነበር። እንኳን 2 ሚሊዮን ብር 1ሺህ ብር አልወጣበትም። እኔን መነገጃ ማድረጋቸው ለምን እንደሆነ አልገባኝም።» ነበር ያለው ዋሚ። በእርግጥም እነኒቆዲሞስ በዋሚ ነግደዋል። ከአሜሪካ የመጡ መኖሪያ ቤት ፈላጊዎች ጃክሮስን አምነው 70ሚሊዮን አስረከቡ። ሌሎች ወገኖችም ቀለጡ። አንድ አመት ቢጠብቁ ምንም ነገር የለም። ከአሜሪካ የመጡ ወገኖች ከብዙ መንከራተት በኋላ የደረሰባቸውን በደል በኢ.ቲ.ቪ “አይናችን” ፕሮግራም ቀርበው « ለአመታት ሰሃን አጥበን፣ ደም ተፍተን ሰርተን ያጠራቀምነውን ገንዘብ በአደባባይ ተዘረፍን። ህግና መንግስት ባለበት አገር እንዴት እንዘረፋለን?..መንግስት ይፍረደን!.» በማለት በእንባ እየተራጩ አቤቱታቸውን አሰሙ። እነ ኒቆዲሞስ ከህብረት ኢንሹራንስ ጋር የዋስትና ውል አለን ብለው ያሉትም በጭራሽ ከተገለፀው ድርጅት ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌላቸው የህብረት ኢንሹራንስ ዋና ሃላፊ አቶ ኢየሱስወርቅ ዛፉ በወቅቱ አጋለጡ። ኤርትራዊው የጃክሮስ ባለድርሻ ፈረንሳይ ለጋሲዮን በወረዳ 12 ፖሊስ ጣቢያ እንዲታሰር ተደረገ። የሚገርመው ከፍተኛ የማጭበርበር ወንጀል መሆኑ እየታወቀ፣ ጉዳዩ በማእከላዊ ምርመራ መያዝ ሲገባው ወይም የጃክሮስ ቢሮ ይገኝበት በነበረው ቦሌ አካባቢ ባለ ፖሊስ ጣቢያ መታየት ሲገባው…ከድርጊቱ ጋር ግንኙነት በሌለው ወረዳ 12 የፖሊስ ጣቢያ ጉዳዩ መያዙና መታሰሩ እንቆቅልሽ ነበር። ሶስት ቀን ብቻ ከታሰረ በኋላ ፍ/ቤት ሳይቀርብ “በ2ሺህ ብር ዋስ” ተፈታ። በተፈታ ማግስት በቦሌ እንዲወጣ ተደረገ። ከፍተኛውን ሚና የተጫወተው ኒቆዲሞስ ነበር። የተዘረፉት ወገኖች በድጋሚ ወደ ኢ.ቲ.ቪ ቢሄዱም መስተናገድ አልቻሉም። ምክንያቱ ደግሞ ግልፅ ነበር። የዘረፋው ጉዳይ በነፃው ፕሬስ በየግዜው ቢነሳም ሰሚ ግን አልነበረም። ነሐሴ 1993ዓ.ም አቶ መለስ ዜናዊ ከጋዜጠኛ ሴኮቱሬ ስለጉዳዩ ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ አስገራሚ ነበር። ሴኮ « ከወንድሞ ጋር በተያያዘ የሚነሳ ነገር አለ፤ ስለጉዳዩ የሚሉት ነገር ይኖራል?» ብሎ ላቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ « በመጀመሪያ ደረጃ ወንድሜን ያገኘሁት ከአስር አመት በኋላ በእናታችን የቀብር ስነስርአት ላይ ነው። አዲስ አበባ እንደገባን ካገኘሁት በኋላ አግኝቼው አላውቅም። የተባለውን ጉዳይ በተመለከተ እነደሰማሁ ከዚህ ተግባር እንዲታቀብ ነግሬው ነበር» አሉ። የአቶ መለስ ምላሽ እርስ በእርሱ የሚጋጭ ነበር፤ “አግኝቼው አላውቅም” ካሉ በኋላ መልሰው ደግሞ “ከዚህ ተግባር እንዲታቀብ ነግሬው ነበር” አሉ። ሌላው ነጥብ ወንድማቸው ኒቆዲሞስ በዘረፋ ወንጀል ተሰማርቶ እንደነበር ማመናቸውን በግልፅ አስቀምጠዋል። ኒቆዲሞስ ዜናዊ በአቋራጭ ዘርፎ ሚሊየነር ሆነ። እጅግ አምባገነን ባህርይ የተጠናወተው ሰው ነው። ማን እንዳስታጠቀው የማይታወቅ ማካሮቭ ሽጉጥ አለው። በቅሎ ቤት አካባቢ በሚገኘው “ሃረግ” መዝናኛ ያዘወትር ነበር። በሴተኛ አዳሪዎች ላይ ሽጉጥ እየመዘዘ ፍዳቸውን ያሳይ ነበር። ማንም አይጠይቀውም። ሲጠቃለል፥ ከጥቂት ወራት በፊት በመለስ ዜናዊ ቤተሰብ ዙሪያ በኢ.ቲ.ቪ አንድ ፕሮግራም ተሰርቶ ነበር። «ጠላ ሻጭ» ወዘተ ተብለው የቀረቡት ከአቶ መለስ ጋር በአባት የሚገናኙ ናቸው። ኒቆዲሞስና መለስ ግን የአንድ እናትና አባት ልጆች ናቸው። ስለሚሊየነሩ ኒቆዲሞስ ምንም የተባለ ነገር የለም። ለምን እሱ በፕሮግራሙ አልተካተተም?…ምክንያቱ ደግሞ ግልፅ ነው። ዘርፎ ሃብታም እንደሆነ በማስረጃ ስለተጋለጠና ህብረተሰቡ ጉዳዩን ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ነው።
ማቆሚያና ገድብ ያጣው የፖለቲካ እስረኞቹ ስቃይ!
በዛሬው አጭር ፅሁፌ ላተኩረው የምፈልገው በፖለቲካ እስረኞች ላይ እየደረሰ የሚገኘው ስቃይ ላይ ነው። ገዢዎቻችን ምንም አይነት የፖለቲካ እስረኛ የለም ሲሉ ይደመጣሉ። ይህ ምን ያህል እውነት ነው የሚለውን ለአንባቢዎቼ እተወዋለሁ። የቃሊቲ ወህኒ ቤት ማረሚያነቱ ምን ላይ እንደሆነ ስላልገባኝና ስላልታየኝ ጭምር ወህኒ ቤት ለማለት ተገድጃለሁ። ስለዚህም የቃሊቲ ወህኒ ቤት የሚለውን ቃል እጠቀማለሁ።
የፖለቲካ እስረኛ የሆኑት ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ፣ አቶ ክንፈ ሚካኤል ደበበ (አበበ ቀስቶ) ፣ አቶ በቀለ ገርባና አቶ ኦልባና ሌሊሳን ባደረባቸው ህመም ከዝዋይ ማረሚያ ቤት ሪፈር ተፅፎላቸው በቃሊቲ ወህኒ ቤት ይገኛሉ። ሆኖም በቃሊቲ ወህኒ ቤት በኩል ተገቢውን ትብብር እየተደረገላቸው እንዳልሆነ የእስረኛ ቤተሰቦች አስታውቀዋል። ከጅምሩም የፖለቲካ እስረኞቹን ወደ ዝዋይ ማዘዋወር ያስፈለገው ቤተሰቦቻቸው ፣ ወዳጆቻቸውና አድናቂዎቻቸው እንደልብ እንዳይጠይቋቸው በማድረግ የፖለቲካ እስረኞቹ ላይ የሞራል ስብራት ለማድረስ ነው። ይህ አልበቃ ብሎ ደግሞ የፖለቲካ እስረኞቹ ተገቢውን ህክምና እንዳያገኙ እየተደረገ ይገኛል። የትኛውም እስረኛ ህክምና የማግኘት መብቱ የተጠበቀ ቢሆንም እስረኛው የፖለቲካ እስረኛ ከሆነ ግን ይህ መበቱን ይነፈጋል። ለዚህ ደግሞ ተጨባጭ ማስረጃ ካስፈለገ የጋዜጠኛ ውብሸት ታዬን እና አቶ ክንፈሚካኤል አበበን (አበበ ቀስቶ) ሁኔታ ማንሳት ይቻላል።
ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ከዝዋይ ማረሚያ ቤት ሪፈር ተፅፎለት ወደ ቃሊቲ ወህኒ ቤት ቢዛወርም የቃሊቲ ወህኒ ቤት ምንም ህክምና ሳያደርግለት ወደ ዝዋይ ማረሚያ ቤት እንዲመለስ ወስኗል። ውበሸት ባልታወቀ ምክንያት ያንኑ ዕለት ምሽት ወደ ቃሊቲ ወህኒ ቤት እንዲመለስ መደረጉን እና ተመልሶ የመጣበት ምክንያት እንደማይታወቅ የውብሸት ታዬ ባለቤት ወ/ሮ ብርሃኔ ተስፋዬ ለኢትዮ-ምኀዳር ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል አስታውቃለች። ይህን ሁላ ማጉላላት ለምን አስፈለገ? የዝዋይ ማረሚያ ቤት ሪፈር ፅፎለት የቃሊቲ ወህኒ ቤትስ ለምን ህክምናውን ሊነፍገው ፈለገ? እኮ ለምን? የከፋ ነገር ቢመጣስ ተጠያቂነቱን ማን ሊወስድ ነው? እነዚህ ሁላ አፋጣኝ መልስ የሚሹ ጥያቄ ናቸው።
የቃሊቲ ወህኒ ቤት ወደር የለሽ ግፉን መፈፀሙን በጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ብቻ አላበቃም። በመኢዴፓ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበሩት አቶ ክንፈሚካኤል አበበ (አበበ ቀስቶ) ላይም በተመሳሳይ ግፍ ተፈፅሟል። ፓርቲው እና ቤተሰቦቻቸው ለኢትዮ-ምኀዳር ጋዜጣ አቶ ክንፈ ሚካኤል በጠና ታመው ህክምና አለማግኘታቸውን አስታውቀዋል።
ይህ ሁላ እየተደረገ የሚገኘው በቃሊቲ ወህኒ ቤት አስተዳዳሪዎች ነው። ይህ ድርጊት ከማንአለብኝነትና ከእብሪት የሚመነጭ ነው። ከዛም ባለፈ የእኛም ድርሻ አለበት። ይህ ሁላ ግፍ እየተፈፀመ ሰምተን እንዳልሰማን ፣ በእኛ ወይ በእኔ ላይ ካልደረሰ ምን አገባኝ ስለምንል መሆኑን መርሳት የለብንም። እነዚህ የፖለቲካ እስረኞች ከመቼውም ጊዜ በላይ የእኛን ድምፅ ይሻሉ። ድምፃችንን ከፍ አድርገን ልናሰማ ይገባል!
በቀጣዩ የኢህአዴግ ጉባኤ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስተር ከህወሓት እንዲሆን ጥረት ይደረጋል (ዶር ቴድሮስ አድሐኖም)።
ህወሓቶች ለሁለት ተከፍሎው የደብረፅዮን (የአዲስ አበባ) ና የአባይ ወልዱ (የትግራይ) ቡድን ተሰይመው ሲነታረኩ መቆየታቸው ይታወቃል። ከወራት በፊት ጀምሮ ደግሞ ሁለቱም ቡድኖች ‘ለማስታረቅ’ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ጠቅሼ ነበር።
አሁን አቶ ስብሃት ነጋ (ከቢተው በላይ ጋር በመሆን) ሁለቱም ባላንጣ ቡድኖች ‘ማስታረቅ’ ችለዋል። ዕርቁ የተፈፀመው በነ ደብረፅዮን ቡድን አሸናፊነት ነው። የነ አባይ ወልዱ ቡድን በመሸነፉ ምክንያት አቶ አባይ ወልዱ ከነ ስብሃት ነጋ ጋር እንዲስማማ ምክንያት ሁነዋል። የነ አባይ ቡድን የተዳከመበት ምክንያት ለሁለት በመከፈሉ ነው። አቶ አባይ ወልዱ ከአቶ ቴድሮስ ሐጎስ፣ ኢያሱ ተስፋይ፣ ተክለወይኒ አሰፋ፣ ኪሮስ ቢተው፣ በየነ መክሩ ወዘተ መግባባት ባለመቻሉ ከአዲስ አበባዎቹ ጋር ለመስማማት ተገደዋል።
በስምምነቱ መሰረት ህወሓት በአዲስ አበባዎቹ ፕላን ይጓዛል። በ’መለስ ራእይ’ ስም ህዝብ መጀንጀን ይቀራል። በሙስና ሰበብ ባለስልጣናት ማሳሰርም ይቀራል። ከአሁኑ በኋል ከፍተኛ የህወሓት ባለስልጣናት በሙስና ሰበብ አይታሰሩም። በቀጣዩ የኢህአዴግ ጉባኤ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስተር ከህወሓት እንዲሆን ጥረት ይደረጋል (ዶር ቴድሮስ አድሐኖም)።
ይህ የህወሓቶች የ’ዕርቅ ሂደት’ ባብዛኛው የብአዴን አመራር አባላትና በተወሰኑ የኦህዴድ መሪዎች ቅሬታ አስነስተዋል። ህወሓቶች ለመታረቅ የተገደዱበት ምክንያት በተቃዋሚዎች ስልጣን እንዳይነጠቁ በመስጋት ነው። ዓረና ፓርቲ ለህወሓቶች ትልቅ ስጋት በመፍጠሩ ነው። የፀጥታ ሃይሉ መፈራረስም ሌላ ህወሓቶች ያስደነገጠ ጉዳይ ነው። በዕርቁ ሂደት ከፍተኛ ሚና የተጫወተው አቶ ስብሃት ነጋ ነው።
የዕርቅ ሂደቱ በኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ከፍተኛ አለመግባባት ሊፈጥር ይችላል። ኢህአዴግ በዉስጥ ለውስጥ የስልጣን ሹክቻ ምክንያት የሚዳከምበት አጋጣሚ መፈጠሩ አይቀርም። ዕርቁ ግዝያዊና ስትራተጂካዊ ብቻ ነው። የታረቁት መግባባት ስለ ፈጠሩ ሳይሆን የጋራ ጠላትን ለመከላከል ብቻ ነው።
ሰኞ 23 ዲሴምበር 2013
ሰማያዊ ፓርቲ በአስቸኳይ የግንፍሌውን ጽ/ቤት እንዲለቅ ትእዛዝ ተሰጠ
ሰማያዊ ፓርቲ ግንፍሌ አከባቢ የሚገኘውን እና በጽ/ቤትነት የሚጠቀምበትን ቢሮ በዛሬው እለት ከሰኣት በኋላ አቶ ሄኖክ የተባሉ አከራዩ ከ አራት ትግሪኛ ተናጋሪ ግለሰቦች ጋር በመምጣት ቤቱን ለነዚህ ግለሰቦች ስለሸጥኩላቸው እንድትለቁላቸው ሲል አሳስቧል:; ቤቱን ገዛሁት የሚለው ትግሪኛ ተናጋሪ ግለሰብ ቤቱን የገዛሁት ስለሆነ በአስቸኳይ እንድትለቁ ካልሆነ የራሴን እርምጃ እወስዳለሁ ሲል አመራሮቹ ላይ ዝቷል::
ይህ ገዛሁት የሚለው ግለሰብ በማይመለከተው ጉዳይ በመግባት ከዚህ በፊት ልቀቁ ተብላችሁ በተደጋጋሚ እንደተነገራችሁ መረጃው አለኝ በማለት በአመራሮቹ ላይ ቁጣ የተቀላቀለበት ዛቻ በመዛት ሄዷል:; በወቅቱ ይዞት የነበረው ተሽከርካሪ ጥቁር የደህነንት መኪና የሆነች ቶዮታ ኤክስኪዩቲቭ ሲሆን የታርጋ ቁጥሩም ኮድ 2-89176 የሆነ ነው::
ሰማያዊ ፓርቲ ከዚህ ቀደም በመነን አከባቢ ተከራይቶት የነበረውን ጽ/ቤት ገና ሳይገባበት በዝግጅት ላይ እንዳለ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ፖለኢሶች እና ቅጥረኞች ተባብረው በተቀናጀ አፈና ቢሮውን መንጠቃቸው ይታወቃል:: የነጠቁትንም ቢሮ ለካድሬያቸው በመስጠት ፔንሲዎን ከፍቶ እየሰራበት ይገኛል::
:EthiopianReview
እሑድ 22 ዲሴምበር 2013
በደቡብ ሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ለማስወጣት የሚደረግ እንቅስቃሴ የለም ተባለ
በደቡብ ሱዳን የተነሳውን የእርስ በርስ ግጭት ተከትሎ በአገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የደህንነታቸው ሁኔታ አሳሳቢ ቢሆንም መንግስት እስካሁን እርምጃ እየወሰደ አለመሆኑ ታወቀ።
የኢሳት የጁባ ወኪል እንደገለጹት አብዛኛው አገሮች ዜጎቻቻውን እያወጡ ነው ። ኬንያና ኡጋንዳ አውቶቡሶችን
በመላክ ፣ አሜሪካና እንግሊዝ ደግሞ ወታደራዊ አውሮፕላኖችን በመላክ ዜጎቻቻውን እያወጡ ነው። የኢትዮጵያ አየር
መንገድ ንብረት የሆነ አውሮፕላን ጁባ ማረፉን ተከትሎ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ለመመለስ ተስፋ
አድርገው የነበረ ቢሆንም፣ አውሮፕላኑ ግን ቻይናዎችን ብቻ ጭኖ መመለሱ ታውቋል። ኢሳት ከአየር መንገዱ ለማረጋገጥ
እንደቻለው የቻይና መንግስት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ቻርተር አውሮፕላን በመከራየት በነዳጅ ማውጣት ስራ ላይ
የተሰማሩ ዜጎቹን ወስዷል።
እንዲሁም ለሽምግልና ጁባ የሄዱትን የኢትዮጵያን ባለስልጣናት በማሳፈር ጁባ ያረፈ አንድ የኢትዮጵያ አየር
መንገድ አውሮፕላን፣ ባለስልጣኖችን ካወረደ በሁዋላ ትኬት ቆርጠው ለመውጣት ይጠባበቁ የነበሩ ኢትዮጵያውያንን ሳይጭን
ባዶውን ተመልሷል። ኢትዮጵያውያኑ የኬንያንና የኡጋንዳን አየር መንገዶችን ለመጠቀም ጥረት እያደረጉ ቢሆንም፣ አየር
መንገዶቹ ከፍተኛ ዋጋ በመጠየቃቸው ትኬቶችን ለመግዛት አልቻሉም።
ኢሳት ለማረጋገጥ ባይችልም ሶሰት ኢትዮጵያውያን ሴቶች መደፈራቸውን የሚያመለክት ዜና ደርሶታል። አንዳንድ
ኢትዮጵያውያንም ንብረታቸውን ተዘርፈው በጁባ መንገዶች ላይ ያለ ደጋፊ ሲዞሩ እንደሚታይ ወኪላችን ገልጿል።
የኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ጅቡቲ እና ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ላለፉት ሁለት ቀናት በጁባ ተገኝተው
ሁለቱን ሀይሎች ለመሸምገል ጥረት እያደረጉ መሆኑም ታውቋል። ደ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም ሁለቱንም ሀይሎች ለማቀራረብ
ከፕሬዚዳንቱ ጥሩ ምላሽ ማግኘታቸውን ገልጸዋል።
ቦር የተባለው አካባቢ በአማጽያን እጅ የወደቀ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ድንበር በሆነው አኮቦ በትናንትናው እለት
ጦርነት ተከፍቷል። ዛሬ ደግሞ ማላኪ፣ ዋው እና ባንቲዩ በተባሉት አካባቢዎች ጦርነት ተከፍቷል። ባንቱዊ የተባበሩት
መንግስታት ድርጅት ጽህፈት ቤት የሚገኝበት ሲሆን፣ በርከታ የዲንቃ ተወላጆች በጽህፈት ቤቱ ግቢ ውስጥ መግባታቸው
ታውቋል። በጁባ የኑዌር ተወላጆች ከዲንቃ ጎሳዎች ጥቃት ሊሰነዘር ይችላል ብለው በተመድ ጽ/ቤት ውስጥ ሲጠለሉ፣
በቤንቲዩ ደግሞ በተቃራኒው ዲንቃዎች ተጠልለዋል።
ፕሬዚዳንት ኦባማ አዲሲቷ አገር ወደ እርስ በርስ ጦርነት ልትገባ እንደምትችል አስጠንቅቀዋል። እስካሁን ባለው አሀዝ ከ500 ያላነሱ ሰዎች ተገድለዋል።
ቅዳሜ 21 ዲሴምበር 2013
አድርባይነት (ለጥቅም ሕሊናን መሸጥ)
ከማርቆስ ዐብይ
ኢትዮዽያ ሀገሬ ሞኘ ነሸ ተላላ፣
የሞተልሸ ቀርቶ የገደለሸ በላ፣
የሞተልሸ ቀርቶ የገደለሸ በላ፣
አድርባይነት
ቀለል ባለ አገላለጽ ማስመስል ወይም ለጥቅም ሲባል ሕሊናን መሸጥ እንደማለት ነው፣፣ ይህ እኩይ ባሕሪ በኢትዮጵያ
ታሪክ ውስጥ ቀላል የማይባል እድሜ አስቆጥሯል የሩቁን ትተን የቅርቡን ከጣሊያን ወረራ ቦኋላ ያለውን አሁን
እስካለንበት ጊዜ ያለውን ለማየት ብንሞክር እንኳ በጣም ብዙ ነገሮችን መታዘብ እንችላለን።
ጣሊያን
ኢትዮጵያን በግፍ በወረረበት ወቅት የክርስቶስን ወንጌል ይሰብኩ ከነበሩ የሐይማኖት አባቶች መካከል በጥቅማ ጥቅም
የተደለሉ ጥቂት የሐይማኖት አባቶች በየአውደ ምሕረቱ ለምዕመናን ከመጽሃፍ ቅዱስ ላይ ኤሳው ለምስር ወጥ ሲል
ብኩርናውን አሳልፎ ለወንድሙ ለያዕቆብ መሸጡን በመጥፎ ተምሳሌትነት እንዳላስተማሩ ሁሉ ራሳቸው ለቁራሽ እንጀራ ሲሉ
ሕሊናቸውን በመሸጥ ከወራሪው ከጣሊያን ጎን በመሰለፍ ለምዕመናኑ በሃሰት በእግዚአብሔር ሃምሳል ኢትዮጵያን ለመታደግ
የመጣ ነው በማለት ሕዝቡ ወራሪው ጣሊያንን አሜን ብሎ እንዲቀበል ያግባቡ ነበር።
በዚህ የወረራ ዘመን
የንጉሠ ነገሥቱ የቅርብ ባልሙዋል ከነበሩ መኩዋንንቶች እና መሳፍንቶች መካከል ሳይቀር ለጣሊያን ያደሩ ነበሩ፣፣
እነዚህ ሹማምንቶች ህዝቡ ተቃውሞውን በማቆም ይዘውለት የመጡትን እውቀት እና ስልጣኔ በመቅሰም ሀገሩን ያለማ ዘንድ
ሰዎቹን በትዕግሰት እንዲጠብቃቸወ በሀሰት ይሸነግሉት ነበር።
ታዋቂው ደራሲ አቤ ጎበኛ የረገፉ አበቦች
በሚል ርዕሰ ያሳተሟት ልብ ወለድ መፅሃፍ ውስጥ ስለነዚህ ከዳተኞች የአድርባይነት መጠን ማሳያ የሚሆን አንድ ታሪከ
ያሰነብቡናል፣ ይህውም በዚያ ዘመን የነበሩ በአካባቢው ህብረተሰብ ዘንድ ትልቅ ስም ያላቸው አንድ ሰው ነበሩ እኚ
ሰው ባለቤታቸው ሲወልዱ ትልቅ ግብዣ አዘጋጅተው ብዙ ሰው ይጋብዛሉ ከተጋባዡቹ መካከል የጣሊያን ወታደሮች የክብር
ቦታ ተዘጋጅቶላቸዋል በግብዣው ሰፍራ ላይ ተገኝተዋል አሳላፊዎች ሰውን ለማስደሰት ከወዲህ ወዲይ ይራወጣሉ በዚህ
መሀል ከክብር እንግዶች አጠገብ ተጎልተው የነበሩት ጋባዠ በእጅ ምልክት ሰውን ፀጥ እንዲል በማድረግ የልጃቸውን ሰም
በታዳሚው ፊት ለማውጣት እንደሚፈልጉ ገለፁ በማሰከተልም ልጄን ሮማ (ROMA) ብያታለሁ አሉ አድናቆትና ጭብጨባ
የክብር እንግዶች ካሉበት አካባቢ ብቻ ቀረበ የተቀረው ተጋባዠ እነሱን ተከትሎ አጨበጨበ እንጂ ሰለሰሙ የሚያውቀው
ነገር ስለሌለ ነገሩ እሰከሚገለፅለት ድረሰ አላወቀም ነበር፣ በመቀጠልም ሮማ አሉ በአሰመሳይነት ኩራት የጌቶቻችን
ሀገር ዋና ከተማ ነች ብለው ተቀመጡ፣ ሰው ሕሊናውን ሲሸጥ መቼም እራሱንብቻ ሳይሆን ቤተሰቡንም ለመሰዋትነት
ያቀርባል።
መቼም እንዳያልፈው የለምና ያ የመከራ ጊዜ አለፈና በአርበኞች ፅናትና ተጋድሎ ዘመቻው በድል
ተጠናቀቀ ፣ ወራሪው ጣሊያን በኩራት የተመላለሰባቸው እነዛ ጎዳናዎች በሃፍረት አንገቱን አቀርቅሮ የሞተው ሞቶ
የተረፈው በደመነፍሰ ተራወጠባቸው በግፍ የወረራትን ሃገር በሃፍረት ጥሉዋት ፈረጠጠ ፣ እነዛ ወራሪውን አዝለው
ህዝቡን ሲያሰጨንቁት የነበሩት ሆዳደሮች ግን ያዘሉትን ያህል እንኩዋን ሊያዝላቸው ቀርቶ እጃቸውን ይዞ የሸሸበት
ያህል እንኩዋን ይዟቸው ሊሄድ አልወደደም እንደ ፓሰታ መቀቀያው ዕቃ የትም ጥሏቸው ሄደ እንጂ፣ እነዚ ከመጣው ጋር
እንደ ሴተኛ አዳሪ ወዳጅ መሰለው መቅረብ እንደ መልካም በሐሪ የተጣባቸው ግለሰቦች አርበኞች ወደ ከተማ ሲገቡ
ፀጉራቸውን አሳድገው ተቀላቀሉዋቸው እኛ ልጃቸውን ሮማ ብለው የሰየሙ ግለሰብም የልጃቸው ሰም ላይ ’ን’ በመጨመር
ሮማን በማለት አይናቸውን በጨው አጥበው ከአርበኞች ጋር ላይ ታች ሲሉ ያያቸው የሀገሬው ሰው በትዝብት እጁን አፉ
ላይ ጭኖ በመገረም ነበር የሚያያቸው ይሉናል አቤ ጎበኛ።
እሰካሁን ለመቃኝት የሞከርነው ህሊናቸውን ሸጠው
ታሪክ አበላሸተው ወደማይቀረው ሞት ሰለነጎዱ ሰዎች ነው፣ አሁን ደግሞ በህይወት ያሉ ነገር ግን ህብረተሰቡ አፈር
ካለበሳቸውና ሃውልታቸው ላይ ሆዳደር ብሎ ካተመባቸው ግለሰቦች መካከል ለናሙና አንዱን በመውሰድ እናወጋለን ከዛ
አሰቀድመን ግን እንደመሸጋገሪያ ይሆነን ዘንድ ከጥቂት አመታት በፊት ጠቅላይ ምኒሰትር መለሰ ዜናዊ የሀገር
ሸማግሌዎችን ሰብሰበው ሲያወያዩ አንድ የሃይማኖት አባት የተናገሩትን አሰገራሚ ንግግር እናሰቀድም እንዲህ ነበር
ያሉት “በአባቶቻችን እሰከ አሁን ድረስ ሲነገር የቆየው ከወደ ሰሜን በመነሳት ኢትዮዽያን በጠነከረ አንድነት
የሚያሰተዳድራት ንጉስ ይመጠል የተባለው ትንቢት ተፈፀመ ይህውም አንተ ነህ ብለው ጣታቸውን ወደሰብሳቢው ጠቆሙ”
እሳቸውም በትዝብት ፈገግ ብለው ምላሸ ሰጡ፣ እኝህ አሰተያየት ሰጪግለሰብ ሀገሪቱ ቋንቋን መሰረት ባደረገ ክልል
ተሸንሸና እንደባቢሎን ሰዎች እርስ በእርሰ መግባባት እንዳልተቻለ ሳያውቁ ቀርተው አይደለም ይህን ባሉበት ወቅት
ሰዎች በዘመቻ መልክ ክልላችሁ አይደለም እየተባሉ የዘሩትን ሳይሰሰቡ ከየቦታው የሚፈናቀሉበት ውቅትም ነበር ይህንንም
አሳምረው ያውቃሉ ነገር ግን እሳቸው እያሰሉ ያሉት ይህን መናገራቸው እንደውለታ ተቆጥሮላቸው ወደ ቅያቸው ሲመለሱ
ስለሚደረግላቸው ከንቱ ውዳሴ ወይም ስልጣን ብቻ ነው፣ ይህን እዚህ ላይ ቋጭተን እሰኪ በአዲሰ መስመር ላይ እላይ
ወደጀመርነው አንድ አስገራሚ ሰው እንመለስ።
እኚ ሰው የኮሚኒኬሸን ጉዳዮች ሚንስትር ዴእታ አቶ ሽመልሰ
ከማል ይባላሉ፣ አቶ ሽመልሰ በመጀመሪያ ኒሻን የምትባል የግል ጋዜጣ በማቋቋም የመንግስትን ስህተት እየነቀሱ በጣም
ጠንከር ባለ አገላለፅ ይተቹ ነበር ከዚህ ጎን ለጎን ሌላው የሚታወቁበት ደግሞ መንግስት በውሃ ቀጠነ የሀሰት ክሰ
ጋዜጠኞችን ፍርድ ቤት ሲያቆማቸው እሳቸው ባላቸው የህግ እውቀት በነፃ ፍርድ ቤት በመቆም ለንፁሃን ጋዜጠኞች
ሸንጣቸውን ገትረው በመከራከራከረቸው ነበር ፣ እኚህ ስው ታዲያ ትንሽ ጠፋ ብለው ከራርመና ሲመለሱ ባንዴ ጎፈር
ሆነው ሲያወግዙት የነበረው መንግስት ባለስልጣን በመሆነ ከኔ በላይ ታማኝ የለም ብለው ቁጭ አሉ፣ ያኔ በደጉ ጊዜ
ከህሊናቸው ጋር በነበሩ ሰአት ሲሟገቱላቸው የነበሩ በቅርብ የሚያውቋቸውን ንፁሃን ጋዜጠኞችን መሰረተ ልማት
ለማውደምና የመንግሰት ባለስልጣናት ለመግደል ከአሸባሪዎች ጋር ሲያሴሩ እጅ ከፍንጅ ያዝናቸው ብለው በአደባባይ ህጉን
እያወቁት ከፍርድ ቤት ቀደመው ፍርድ አስተላለፉ፣ እነዚያ ንፁሃን ጋዜጠኞችም ያለጥፋታቸው የእድሜአቸውን እኩሌታ
ዘብጥያ እንዲያሳልፉ የፖለቲካ ውሳኔ ተወሰነባቸው እናቃሊቲ ተወረወሩ፣ እኚህ ግለሰብ መንግስት እራሱን አሻሸሎ ነው
የተቀላቀሉት እንኩዋን እንዳይባል እርሳቸው ስልጣን ላይ ከመውጣታቸው በፊት የነበረው የጋዜጠኞች የመሰራት ነፃነት
አሁን ካለው ዘጠና በመቶ ይሻል ነበር ታዲያ ምን ነካቸው ከተባለ መልሱ ለጥቅም ሲባል ሕሊናቸውን ሸጡ ይሆናል።
ሰው
ሕሊናውን በጥቅም ከተያዘ ዕውቀትና ስልጣን መጠሪያው ከመሆን የዘለለ ፋይዳ የለውም ፣ በጣም የሚገርመው እኚህ ሰው
መንግስትን በመወከል በተደጋጋሚ የተናገሩዋቸውን ንግግሮች አለቆቻቸው ውድቅ በማድረግ ሸመልስ ያለው ውሸት ነው
በማለት በአደባባይ ሲያዋርዱአቸው በፊት ለሎች ሲከራከሩ የነበሩ ሰው እንዳልነበሩ ሁሉ በጥቅም ስንሰለት እግር
ተወርቸ ታሰረው እራሳቸውን እንኩዋን መከላከል አቅቷቸው ሲወራጩ በመታዘብ አይተናል።
ባጠቀላይ ህሊና ትንሹ
እግዚአብሔር ነው ይባላል መልካም ስንሰራ የሚያበረታታን መጥፎ ሰንሰራ ደገሞ እንድንፀፀተና ዳግም እንዳንሰራ
እረፍት የሚነሳን ታድያ ሰው ይህንን ትልቅ ነገር አጥቶ ሀብትና ዝናን ቢሰበሰብ እንዴት የዓይምሮ ሰላም ሊያገኝ
ይችላል?
“ሰው እግዚአብሔርን አጥቶ አለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ምን ይጠቅመዋል” እንዳለው መፀሃፍ ቅዱስ፣
ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ይጠብቅ!
ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
ልጥፎች (Atom)




