ማክሰኞ 30 ኤፕሪል 2013

ከፋውንዴሽኑ ጀርባ...(ከተመስገን ደሳለኝ (ክፍል ፩)

ያለ ወቅቱ በደረሰ ዝናብ እየራሰች ያለችው አዲስ አበባ ዛሬም ከመለስ መንፈስ ተፅእኖ ነፃ አልወጣችም፤ ጣራና ግድግዳዎቿ እንዲህ በምስሉ እና በድርጅቱ አርማ መዥጎርጎሯን ያስተዋለ አንድ ቀልደኛ የባህር ማዶ ወዳጄ ‹‹እኔ ከሀገሬ ከወጣሁ በኋላ የኢህአዴግ ዋና ከተማ ሆነች እንዴ?›› ብሎ ፈገግ አሰኝቶኛል፡፡ በእርግጥ ይህችን ቀልድ ስንፍቃት የምናገኘው ቁም ነገር፡- ከተማዋ በመለስ ውርስ ድንዛዜ ላይ መሆኗ፣ አስተዳደሯም ያለ ቅድመ-ዝግጅት ‹‹አፍርሼ ካልሰራሁሽ›› በሚሉ ካድሬዎች ጫጫታና ሩጫ ልቧን እያጠፋት እንደሆነ፣ አንድ ፓርቲ ተመራጭ፣ አስመራጭ፣ ታዛቢ መሆኑን እና የመሳሰሉትን ነው፡፡ የአቶ መለስ ሞትም ወቅቱን የጠበቀ ባለመሆኑ ስርዓቱን እያንገጫገጨው ነው፡፡ በግሌ በመለስ ህልፈት ያለማዘን በሥነ-ምግባር የመዝቀጥ ጉዳይ ነው ብዬ አላስብም፡፡ ምክንያቴ ሰውየው ክፉ አምባገነን ከመሆኑም በላይ በዙፋኑ ሙጭጭ እንዳለ ህይወቱ በማለፉ ነው፤ ታዲያ ይህንን ሰው እንዴት አድርገን ነበር ከስልጣን ማውረድ የምንችለው? መቼም አቅመቢሶች ከመሆንም አልፈን በተራራና ሸንተረር ሳይቀር የተከፋፈልን ለመሆናችን ከራሳችን በላይ መስካሪ የሚያሻን አይመስለኝም፡፡ እዚህች ጋ ከሩሲያዊው ሌኒን ህልፈት ጋር የተያያዘ አንድ ነገር ትዝ ስላለኝ ልንገራችሁ፡-

እንደሚታወቀው ሌኒን የሩሲያ አብዮትን የመራ ሁነኛ ኮሚዩኒስት ቢሆንም፣ ምሁራዊ ሰውነቱ ከሌሎች አብዮተኞች በእጅጉ ይገዝፍ እንደነበረ ጠላቶቹም ሳይቀር የመሰከሩለት ጉዳይ ነው፡፡ እናም ህልፈቱ ሲሰማ፣ ሩሲያን በአይነ ቁራኛ ይከታተሉ የነበሩ ምዕራባውያን ድንጋጤ አደረባቸው፡፡ ከእነዚህ ሀገራት የአንዱ መሪም ድንጋጤውን እንዲህ ሲል ገልጾ ነበር አሉ፡-
.
‹‹ሌኒን ሆይ፣ ባትወለድ መልካም ነበር፤ ከተወለድክ ደግሞ ትንሽ ብትቆይ ይሻል ነበር፤ ምክንያቱም ለማን ትተኽን እንደሄድክ እኔ አውቃለሁና!››

በእርግጥም ሌኒንን የተካው ባለ ብረት መዳፉ ጆሴፍ ስታሊን መሆኑን ስናስተውል የሰውየው ቁጭት ይገባናል፤ ግና ከአስር ወር በኋላም ሊገባን ያልቻለው የእኛው መለስ ለማን ትቶን እንደሄደ ነው፡፡ ከስታሊንም ለባሱት? ወይስ…

የሆነ ሆኖ መለስን ተክተው ከጀርባ የሚዘውሩትን አንጋፋ ታጋዮች ለጊዜው ባሉበት አቆይተን፣ ገብስ ገብሱን እንነጋገር ካልን የኃይለማርያም ደሳለኝ ሹመት ወቅቱን የጠበቀ አይደለም የሚለው አያከራክረንም፡፡ የሶስቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሹመትም እንዲሁ፡፡ የእነዚህ ድምር ውጤት ነው አገዛዙን ወቅቱን ባልጠበቀ አጀንዳ እንዲወጠር ያደረገው፡፡
ያለወቅታቸው ‹‹ተከሰቱ›› ተብለው ሊጠቀሱ ከሚችሉ አጀንዳዎች መካከል ‹‹የመለስ ፋውንዴሽን ምስረታ›› አንዱ ነው፡፡ በእርግጥ መለስ ባይሞት ኖሮ፤ ከሞተም በኋላ ስርዓተ ቀብሩ ትኩረት ባይስብ ኖሮ፤ ከተቀበረ በኋላም ‹‹ሌጋሲው ይቀጥላል›› ባይባል ኖሮ፤ ከሌጋሲው ውስጥም ‹‹ራዕዩ ፈለቀ›› ባይባል ኖሮ… ‹‹ፋውንዴሽን›› ጂኒ ቋልቋል… ባልተከታተለብን ነበር እያልን መቆጨታችን አይቀሬ ነው፡፡

ኢህአዴግ ከመለስ ህልፈት በኋላ ‹‹የመለስ ራዕይ›› እያለ መጮኹ አናዳጅ ብቻ ሳይሆን ‹‹እመራዋለሁ›› ለሚለው ህዝብም ያለውን ንቀት የሚያሳይ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ይህ አይነቱ ፕሮፓጋንዳም ነው ‹‹መለስ ኖሮ፣ ራዕዩ በሞተ›› የሚያስብለው (አሁን የፋውንዴሽኑ ምስረታ ዕለት የተከሰቱ ፖለቲካዊ አንድምታ ያላቸውን ጉዳዮች በአዲስ መስመር ጨርፎ ወደማየቱ እንለፍ)

ፋውንዴሽኑ ደረጃውን የጠበቀ መናፈሻ፣ ቤተ መፅሀፍት (የመለስ ስራዎች በአማርኛ ተተርጉመው ይቀመጡበታልም) እና የተለያዩ መዝናኛዎችን ጨምሮ አስክሬኑ የሚያርፍበት ልዩ ስፍራ እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡ በግልባጩ ግንባታው የሚካሄድበት ቦታ አዲስ አበባ ነው ከማለት ባለፈ በትክክል የት አካባቢ እንደሆነ ተለይቶ አልተገለፀም፡፡ ሆኖም ለግንባታው ተብሎ በግዴታ በርከት ያሉ መኖሪያ ቤቶች ከይዞታቸው እንደሚነሱ ተነግሯል፡፡ በግሌ ይህ አግባብ ነው ብዬ አላስብም፡፡ ምንም እንኳ በ‹‹ስመ-ልማት›› እየተደረገ ያለውን ማፈናቀል ጠቀሜታው የሀገር ነው ብለን ልንወስደው ብንችልም፤ ይህ ግን… (አጀንዳዬ የፋውንዴሽኑን ጥቅም ወይም ጉጂ ጎን መተንተን ሳይሆን፣ በምስረታው እለት የታዩ ጥቂት ተመንዛሪ ክስተቶችን መተንተን ነው ብያለሁና ወደዚያው አልፋለሁ)

ከዚህ ቀደም የህወሓት አመራር አባላት የመለስ ህልፈትን ተከትሎ በሁለት ጎራ ተቧድነው ‹‹ቀዝቃዛ ጦርነት›› ውስጥ መግባታቸውን ያመላክታሉ ያልኳቸውን ፍንጮች ጠቅሼ መነጋገራችን አይዘነጋም፡፡ (‹‹ቀዝቃዛው ጦርነት፡- ከአመታት በፊት ዓለም በአሜሪካን እና ሶቭየት ህብረት ፊት አውራሪነት በርዕዮተ-ዓለም ተከፍሎ ሲፋለም ነበር፤ ያለታንክና መድፍ፤ ያለ ተዋጊ ወታደርና ያለ አዛዥ ጄነራል፤ ፍልሚያው ሟችም ሆነ ቁስለኛ፣ አሊያም ምርኮኛ አልነበረውም፤ የርዕዮተ-ዓለምን ልዩነት በበላይነት ለመወጣት ነበርና፡፡ አንደኛው ከሌላኛው ጎራ ከቻለ ሀገርን፣ ካልቻለም ስልጣን ላይ ያለ ግለሰብን ለማስኮብለል ይቀምራል፣ ያሴራል፣ ይሰልላል…፤ ይህንን ሁኔታ ነው የፖለቲካ ተንታኞች ‹‹ቀዝቃዛው ጦርነት›› (Cold War) ያሉት) ዛሬ ደግሞ የህወሓት የአመራር አባላት በእንዲህ አይነት ጦርነት መጠመዳቸውን ጆሮአችን እስኪግል እየሰማን ነው፤ ልዩነቱ የህወሓት ችግር ርዕዮተ-ዓለምን መሰረት ያደረገ አለመሆኑ ነው፡፡ በእርግጥ ህወሓት እንኳን ዛሬ፣ በትልቁ የተሰነጠቀ ጊዜም (በ1993 ዓ.ም.) ርዕዮተ-ዓለም አላጨቃጨቀውም፡፡ የስዬ አብርሃ ወደ አንድነት መግባትም ሆነ፣ የእነ ገብሩ አስራት በ‹‹ሶሻል ዴሞክራሲ›› አስተሳሰብ የሚመራውን አረናን መመስረት የልዩነቱ ምክንያት አልነበረም፡፡ እነገብሩ አረናን ለመመስረት ሲንቀሳቀሱ፣ በክፍፍሉ ወቅት ‹‹የቡድን አባታቸው›› እንደነበር የሚነገርለት ተወልደ ወ/ማርያም የአዲሱ ፓርቲ መስራች እንዲሆን ሲጠየቅ ‹‹ርዕዮተ-ዓለማችሁ ‘አብዮታዊ ዴሞክራሲ’ ከሆነ ብቻ ነው የምቀላቀለው›› አለ መባሉ መከራከሪያችንን ያጠነክረዋል፡፡

እናም የህወሓት ሰዎች (ከእነ አረጋዊና ግደይ ዘርአፅዮን ዘመን ጀምሮ) ስልጣን እንጂ፣ የፖለቲካ አመለካከት የፀብ መንስኤ ሆኗቸው አያውቅም፡፡ የዘንድሮውም ‹‹ቀዝቃዛ ጦርነት›› ቡድተኝነትና የስልጣን ፍላጎት የፈጠረው ቅራኔ ነው፤ አሊያም ከጆርጅ ኦርዌል ‹‹እንሰሳት ሁሉ እኩል ናቸው፤ አንዳንድ እንሰሳት ግን ከሌሎች ይበልጥ እኩል ናቸው›› መንፈስ የተናጠቀ ሊሆን ይችላል፡፡ እንዲሁም የፋውንዴሽኑ ምስረታ የእነአዜብን ቡድን የሚያጠናክር ፖለቲካዊ አንድምታ አለው፡፡ በእነአባይ ፀሀዬ ቡድን ውስጥ ከተሰባሰቡት አብዛኛው ለመለስ ያደሩት ፈርተው እንጂ አምነውበት ወይም ወደውት አይደለም፡፡ ለዚህም ይመስለኛል ከእነርሱ ቡድን አንድም የአመራር አባል የፋውንዴሽኑ ቦርድ አባል ሆኖ ያልተመረጠው፡፡
የሁለቱ ቡድኖች አሰላለፍ በ‹‹አባይ-ደብረፅዮ››ን እና በ‹‹አዜብ-አባይ ወልዱ›› አስተባባሪነት መሆኑን ሰምተናል (በነገራችን ላይ ከ1983-1993 ዓ.ም ኢህአዴግ ‹‹ሁሉም የግንባሩ አባል ፓርቲዎች እኩል ናቸው፤ ህወሓት ግን ከሁሉም ይበልጣል›› የሚል ያልተፃፈ ህግ ነበረው፡፡ በ93ቱ ክፍፍል አብዛኛው የህወሓት አመራር ከተባረረ በኋላ ደግሞ ያ ህግ ‹‹ሁሉም የኢህአዴግ የአመራር አባላት እኩል ናቸው፤ መለስ ግን ከሁሉም ይበልጣል›› ወደሚል ተቀይሮ ነበር፡፡ አሁን መለስ አልፏል፤ እናም አፍጦ የመጣው ጥያቄ ‹‹ከሁሉም የሚበልጠው ማን ነው?›› የሚለው ነው ብል ማጋነን አይሆንም)
የሆነ ሆኖ በ‹‹የመለስ ፋውንዴሽን ምስረታ›› ወቅት የታዩ ሁነቶች ሁለት ነገር ይፋ አድርገዋል፡፡ የመጀመሪያው በእነአዜብ ጎራ እነማን እንደተሰለፉ የሚያሳይ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ የጦር አዛዦችም ፍልሚያውን መቀላቀላቸውን ማመላከቱ ነው፡፡

የእነአዲሱ ለገሰ-ብአዴን ገና ከመነሻው ከእነአዜብ ጎን መሰለፉ ይታወቃል፡፡ በፋውንዴሽኑ ምስረታ ወቅትም ይኸው ነው የታየው፡፡ ‹‹የጠቅላይ ሚንስትር መለስ የሌጋሲ ኮሚቴ›› ሰብሳቢ የነበረው አዲሱ ለገሰ፣ የስብሰባውን አካሄድ እየተከታተለ የተጣመመውን ሲያቃና፣ ማጣመም የፈለገውን ደግሞ ሲገፋ ተስተውሏል፡፡ ለምሳሌ የብአዴኑ ካሳ ተ/ብርሃን የፋውንዴሽኑ የቦርድ አባል ሆኖ መመረጡን ተቃውሞ በእርሱ ምትክ ሌላ ሰው እንዲመረጥ ሲጠይቅ፣ አዲሱ ስራው ጊዜን የማይሻማና ቦርዱን የሚመለከት ነገር ሲኖር ብቻ ውሳኔ መስጠት እንደሆነ ጠቅሶ ካሳ መቀጠል እንዳለበት ሲናገር፣ የመድረክ መሪው በፍጥነት ሃሳቡን ቤቱ እጅ በማውጣት እንዲደግፍ ቀስቅሶ የሰውየውን ተቃውሞ ውድቅ አድርጓል፡፡ በግልባጩ የኦህዴዱ ሙክታር ከድር ሲመረጥ፣ የብአዴኑ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) የሴቶች ተሳትፎ አናሳ መሆኑን መግለፁን ተከትሎ፣ ሙክታር ‹‹ድርጅቶቹ ራሳቸው ለምን አይጠቁሙም?›› ገና ከማለቱ፣ እነአዲሱ ተሽቀዳድመው ‹‹ከአንተ ነው መጀመር ያለበት›› የሚል ግፊት በማድረግ የተመረጠውን ሙክታር ከድርን በ‹‹ድርጅታዊ አሰራር›› ከጨዋታ ውጪ አድርገው፣ አስቴር ማሞን አስገብተዋል፡፡ ሶፍያን አህመድ፣ ቴዎድሮስ አድሀኖም፣ ቴዎድሮስ ሀጎስም የቦርዱ አባል ሆነው ተመርጠዋል፡፡ በመጨረሻም አዜብ የፋውንዴሽኑ ፕሬዚዳንት ሆና ስትመረጥ፣ ምክትሏ ደግሞ የብአዴኑ ካሳ ተ/ብርሃን እንዲሆን ተደርጓል (ሁሉም በእነአዜብ ቡድን ስር ናቸው)
የሁለቱም ቡድን አባላት ‹‹ቃየል››ን እንጂ ‹‹አቤል››ን መሆን አይፈልጉም፡፡ እናም የከፋ ነገር ከመጣ ‹‹ቃየላዊ›› እርምጃዎችን እስከመውሰድ ሊደርሱ ይችላሉ፡፡ በእርግጥ ይህ ሁኔታም ሊሳካ የሚችለው የታጠቀውን ኃይል ፍላጎት ታሳቢ አድርጎ ለተንቀሳቀሰ ኃይል ነው፡፡ እናም ከእርስ በእርስ ግጭቱ በበላይነት ለመውጣት እንቅልፍ አጥተው እየሰሩ (እያሴሩ) ነው (እስከአሁን ባለው ሁኔታ ብአዴን ሙሉ ድጋፍ እያደረገለት ያለው የእነአባይ ወልዱ ቡድን ‹‹የተሻለ›› ሊባል የሚችል የበላይነት አሳይቷል)፡፡ በዚህን ጊዜም ከድንገቴ አደጋ ራስን መከላከል አስፈላጊ በመሆኑ የግል ጥበቃቸውን አጠናክረዋል፡፡ ለምሳሌ በረከት ስምዖን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጠባቂዎቹን ከሁለት ወደ ስድስት አሳድጓል፤ ሁለት ተጨማሪ መኪናዎችም ከፊትና ኋላ ሆነው እንዲያጅቡት አሰማርቷል፡፡

ባለፈው ወር በተካሄደው የግንባሩ ዘጠነኛ ጉባኤ አዜብ መስፍን ‹‹መለስ በስልጣን ላይ እያለ ደሞዙ ስለማይበቃን ብዙውን ጊዜ ከወር እስከ ወር ቀለብ ሳያልቅብን ለመድረስ እንቸገር ነበር›› የሚል አንድምታ ያለው ንግግር አድርጋ ካለቃቀሰች በኋላ ‹‹በደሞዝ (በፔሮል) የሚኖረው ባለስልጣን መለስ ብቻ ነው›› ስትል ማድመጣችን ይታወሳል፡፡ በእርግጥ አዜብ ልታስተላልፍ የፈለገችውን መልዕክት አንጓ ከ‹‹ሰሙ›› ለይተን ስናወጣው ‹‹ቅልጥ ባለ ዘረፋ ላይ የተሰማራችሁ ባለስልጣናት በልዩነታችን ላይ ካልተግባባን ላጋልጣችሁ እንደምችል እንድታውቁት›› የሚል ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ የበረከት ‹‹ቴሌቪዥን ጣቢያ››ም ይህንን ሃሳብ በተለየ ሁኔታ ያስተላለፈው ትርጉሙ ሳይገባው ቀርቶ አይመስለኝም፡፡ እነዚህን ኩነቶችም ስንጨምቃቸው ‹‹ህወሓት የውስጥ ችግሩ ከቀን ወደ ቀን እየባሰ ሄዶበታል›› የሚል ድምዳሜ ላይ ያደርሱናል (የአዜብን መልዕክት ባደመጥን ማግስት አራት ኪሎ አካባቢ ከአንድ የአረና አመራር አባል ጋር ድንገት ተገናኝተን ይህንን ሁኔታ አንስተን ስናወራ እንዲህ አለኝ፡- ‹‹እነርሱ ቀልደኞች ናቸው፤ በ1993 ዓ.ም የክፍፍሉ ወቅት መለስ ለቤተመንግስቱ የተመደበው ሁለት ሚሊዮን ባጀት የት እንደሚገባ ሲጠየቅ ‹ይሄ ግቢ እኮ ከምንሊክ ዘመን ጀምሮ ጮማ የለመደ ነው› ብሎ አድበስብሶ አልፎት እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ በተቀረ አዜብ ‹በመለስ ደመወዝ ብቻ ስለምተዳደር ሽሮና በርበሬ እያለቀብኝ እቸገራለሁ› ማለቷ ከእርሷ ጋር የአቋም ልዩነት ላላቸው የህወሓት አመራር በጎንዮሽ የማስፈራሪያ መልዕክት ከማስተላለፍ የዘለለ ቁም-ነገር ያለው አይመስለኝም፡፡››)

ሌላኛው በዕለቱ የታየው ዓብይ ጉዳይ መከላከያን የሚመለከተው ነው፡፡ የተመረጡት ሰዎች ውክልናቸው ተቋምን መሰረት ያደረገ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በዚህ መሰረትም መከላከያን ወክለው የቀረቡት ጄነራል ሳሞራ የኑስና ጄነራል ሰዓረ መኮንን ናቸው፤ ሳሞራ ሙሉ ጀኔራል ነው፣ ሰዓረ ደግሞ ሌፍቴናንት፡፡ ስለዚህም መከላከያን ወክሎ የቦርድ አባል መሆን ያለበት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ባለ አራት ኮከብ ጄነራል የሆነው ሳሞራ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ የሆነውም ይኸው ነው፤ በዚህም ማንም አልተቃወመም-ከጄነራል ሰዓረ በቀር፡፡ ለምን? ሁለቱ ጄነራሎች በግል ስለማይግባቡ? በጥቅም ተጋጭተው? ሰዓረ ‹‹ሳሞራ አይመጥንም›› ብሎ አስቦ? እውነት ጉዳዩ የሁለቱ ብቻ ነው? ወይስ የሰዓረ ተቃውሞ መነሻ ምንድር ነው? …ይህንን ተቃውሞ የግለሰብ አድርገን እንዳንወስደው የሚያስገድዱ ገፊ ምክንያቶች የምላቸውን መጥቀስ እችላለሁ፡- ሁለቱም ተመሳሳይ ተቋም ወክለው መቅረባቸው አንዱ ነው፤ ሁለቱም ወታደሮች መሆናቸው ሌላኛው ነው (የወታደር ዲሲፕሊን በተለይም የኢህአዴግ ወታደራዊ አደረጃጀት ከታች ወደላይ ተቃውሞን እንደማያበረታታ ማንም አይጠፋውም) ሆኖም ‹‹የሳሞራን የቦርድ አባል መሆን በምን አያችሁት?›› ሲል የተቃውሞ ድምፁን አሰምቷል፡፡ በተጨማሪም ሰዓረ ያ ሁሉ ህዝብ በተሰበሰበበት አዳራሽ የሳሞራን ስም ሲያነሳ በሰራዊቱ ደንብ መሰረት በማዕረግ ስሙ አልነበረም፡፡ ለዚህም ነው በዕለቱ የተከሰተው ነገር ሁለቱ ጄነራሎች እያራመዱት ያለውን ልዩነት የሚያሳይ ነው የሚለውን መከራከሪያ የሚያጠናክረው፡፡ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ለሚከታተል የሠራዊቱን ወሳኝ ጄነራሎች ከጎኑ ማሰለፍ የቻለ ማንኛውም ቡድን ዳዊት የማይኖርበት ጎልያድ ሊሆን እንደሚችል አይጠፋውም፡፡ እናም ይህ ኩነት አንደኛ ዓመቱን ሊደፍን እየተቃረበ ላለው የሁለቱ ቡድኖች ፍጥጫ የመቋጫው ቀናት እየቀረበ እንደሆነ የሚያመላክት ይመስለኛል (በነገራችን ላይ በመከላከያ ውስጥ ከሳሞራ ቀጥሎ ባለ የስልጣን ወንበር ላይ የምናገኘው በተመሳሳይ ማዕረግ የሚገኙ ሶስት አቻ ጄነራሎችን ነው፡፡ ሁለቱ ጄነራል አበባው ታደሰ እና ጄነራል ሰዓረ መኮንን ናቸው፡፡ እነዚህ ጄነራሎች አንም ቀን ተስማምተው ሰርተው አያውቁም፡፡ ስልጣናቸውና ኃላፊነታቸው ተመሳሳይ ቢሆንም አበባው የሚመራው ቢሮ በተሰሚነት ጎላ ያለ ነው፡፡ …ሳሞራ በግልፅ ‹‹በዚህ ቀን›› ብሎ ባይናገርም ከኤታማዦር ሹምነቱ የመልቀቅ እቅድ አለው፡፡ በአሁኑ አሰላለፍም ከእነአዜብ ጎን ይመደባል፡፡ አበባውና ሰዓረ ደግሞ የእርሱን ቦታ ይፈልጉታል፡፡ አበባው የሳሞራ የቅርብ ሰው ነው፡፡ ከሰዓረ ጋር ያለው ግጭትም ከሳሞራ ጋር ካለው ግንኙነት ጋር ይያያዛል)

የሆነ ሆኖ ‹‹ቀዝቃዛው ጦርነት››ን በሚመለከት ተጨማሪ ነጥብ ልጥቀስ፡፡ ከቀኑ ስብሰባ በኋላ በሸራተን ሆቴል ለፋውንዴሽኑ ገቢ ማሰባሰቢያ አንድ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ነበር፡፡ በዚህ ፕሮግራም ላይ የጎረቤት ሀገራትን ጨምሮ የክልል አስተዳደሮች ‹‹አቅማችን ይመጥናል›› ያሉትን ያህል የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል፡፡ ከሁሉም ቀድሞ አንድ ሚሊዮን ብር ያዋጣው እነአዲሱ ለገሰ እንደግል ንብረታቸው የሚቆጥሩት ‹‹ጥረት ኢንዶውመንት›› ሲሆን፣ የአላሙዲ ‹‹ሚድሮክ ኢትዮጵያ››ም ሃያ አምስት ሚሊዮን ብር ለመለገስ ቃል ገብቷል፡፡ ትኩረቴን የሳበው ግን ይህ አይደለም፤ ገቢና ወጪው ከህዝብ ብቻ ሳይሆን ከውጪ ኦዲተርም አይን የተሰወረ ነው የሚባለው እጅግ ባለፀጋው የህወሓቱ ‹‹ኤፈርት›› በዕለቱ ሰባራ ሳንቲም ለማዋጣት ቃል አለመግባቱ እንጂ፡፡ ለምን? ኤፈርት በእነአዜብ ስር ከመሆኑ አኳያ ለትችት ያጋልጠናል በሚል? ወይስ ገና ያልተደረሰበት እንቆቅልሽ ይኖር ይሆን? ጥያቄው ይህ ነው፡፡ የዚህን መልስ ጨምሮ ከላይ ያነሳኋቸው ነጥቦች ሲፍታቱ ልዩነቱን እና አሰላላፉን ያጎሉታል ብዬ አስባለሁ፡፡

እንደመውጫ

በሀገራችን ላይ ‹‹ለውጥ አመጣለሁ›› የሚለው የተቀውሞ እንቅስቃሴ ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ከመጣ ጀምሮ ‹‹ይህን ዓመት አያልፍም!›› በሚል ሟርት ሲጠመድ፣ ድርጅቱ ግን ሃያ ሁለተኛ ዓመቱን ሻማ ለኩሶ ሊያከብር ቀናት ብቻ ቀርተውታል፡፡ ዘንድሮም የመለስን ሞት ወይም የግንባሩን መከፋፈል ብቻ ስናመነዥክ የቋመጥንለት ለውጥ የውሃ ሽታ ሆኖ ነገሩ ሁሉ ‹‹የሞትንም እኛ፤ ያለንም…›› እንዳይሆን እሰጋለሁ፡፡

እናም በላያችን ላይ እያመፀ ያለውን ፍርሃት ማረቅ ያስፈልጋል፤ ከመቼውም ጊዜ በላይ አንድነት ያስፈልገናል፤ ከኢህአዴግ በኃላም ሊኖር ስለሚገባው ለውጥ መነጋገር ያስፈልጋል፤ ስርዓቱ ሀገር የሚጠቅም አለመሆኑን በበቂ ሁኔታ ገብቶናልና፣ የርዕዮተ-ዓለም ወይም የፖሊሲ ድክመቱን በምክንያትና አመክንዮ (ሎጂክ) እየተነተንን ብቻ ተጨማሪ ጊዜ ማባከኑ ፋይዳ የለውም፡፡ ፋይዳ ያለው በሰላማዊ መንገድ አደባባይ ወጥቶ የስርዓት ለውጥ ማድረግ ነው፤ ትንተናዎችም ይህ አይነቱን እንቅስቃሴ ወደ መሬት ማውረድ የሚቻልበት እና ከኢህአዴግ በኋላስ? የሚለው ላይ ሲያተኩሩ ነው፡፡

:ከተመስገን ደሳለኝ

ማክሰኞ 23 ኤፕሪል 2013

ህዝብ እየተፈናቀለ ያለው ከፌዴራል መንግስት በሚሰጥ ትዕዛዝ መሆኑን መኢአድ አሳወቀ


“የአገሪቱ ህዝብ በተለይ የአማራው ህዝብ ከሥራውና ከመኖሪያ እየተፈናቀለ ያለው በክልል ወይም በወረዳ ባለሥልጣናት ውሳኔ ሳይሆን ከፌዴራል መንግስት በሚሰጥ ትዕዛዝ ነው፡፡” ሲል የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት/መኢአድ/አስታወቀ፡፡
መኢአድ ይህንን ያሳወቀው ባለፈው አርብ ረፋዱ ላይ በጽ/ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡ ፓርቲው ወደ ዓለም አቀፍ ፍ/ቤት በመሄድ የኢትዮጵያ መንግስት በዘር ማጥፋት ወንጀል ለመክሰስ እየተዘሰጋጀ መሆኑን አስታውቋል፡፡



መኢአድ “በአማራ እና በአፋር ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው የአምባገነኖች እና ዘረኞች ጥቃት እንዲሁም የዘር ማጥፋት ወንጀል በአስቸኳይ እንዲቆም እንጠይቃለን፡፡” በሚል ርዕስ ባለ አራት ገጽ መግለጫ አውጥቷል፡፡ መግለጫው በመግቢያው ላይ “ኢህአዴግ የምኒሊክ ቤተመንግስትን ከተቆጣጠረ ጊዜ ጀምሮ በአማራ ህዝብ ላይ ያነጣጠረ የጥቃት ዘመቻ ሲፈጽም ቆይቷል፡፡ በበደኖ፣በአርባጉጉ፣በአረካና በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ጭፍጨፋ ፈጽሟል፡፡ ጥቃቱ ለ22 አመት ቀጥሎ ዛሬም በጉራፈርዳና በአፋርና በቤኒሻንጉል የዘር ማጥፋት ሥራ እየተሰራ ነው፡፡”  በማለት ይዘረዝራል፡፡ መግለጫው በመጨረሻም “እንዲመለሱ ለተደረጉ ወገኖች ተገቢው የህግ ጥበቃ እንዲደረግላቸው፣ ለደረሰባቸው አካላዊና ሞራላዊ ጥቃት ተገቢው ካሳ እንዲከፍል፣ ድርጊቱን የፈፀሙትን ለፍርድ እንዲያቀርብ፣ ጥላቻንና ክፍፍልን የሚያራግቡ ኃይሎች ከዚህ እኩይ ድርጊታቸው ባስቸኳይ እንዲታቀቡ፣ ሕዝብን በዘርና በኃይማኖት ከፋፍሎ በማፋጀት ሥልጣንን ለማራዘም የሚደረገው ጥረት ላለፉት 21 ዓመታት ደም ያፋሰሰ በመሆኑ ባስቸኳይ እንዲቆም እንጠይቃለን ብሏል፡፡
መግለጫውን የሰጡት የፓርቲው ፕሬዘዳንት ኢ/ር ኃይሉ ሻውል፣ የፓርቲው ም/ሊቀመንበርና የቀጠና አደራጅ አቶ ተስፋዬ ታሪኩ ናቸው ፡፡ መግለጫው በንባብ ከተሰማ በኃላ ከጋዜጠኞች ለቀረቡ ጥያቆዎች መልስ ተሰቷል፡፡ ኢ/ር ኃይሉ በሰጡት መልስ “ ከቤኒሻንጉል ጉምዝ የተፈናቀሉት ሰዎች በወረዳ ባለሥልጣናት እንደሆነ በመግለጽ ስህተቱ ታርሞ ተፈናቃዮች ወደ ሥፍራቸው ተመልሰዋል ይባላል፡፡ ሐሰት ነው፡፡ የዘር ማጥፋት ዘመቻው የሚከናወነው የፌዴራል መንግስት በሚሰጠው ትእዛዝ መሆኑን መረጃ አለን፡፡ ህዝቡን እየደበደበ እያሰረ የሚያፈናቅለው ልዩ ኃይል የሚባለው ጦር ነው፡፡ ልዩ ኃይልን የሚያዘው ደግሞ ፌዴራል መንግስት ነው፡፡ ተፈናቃዮች ፍኖተ ሠላም በሠፈሩበት ወቅት ውሃ አጥተው የወንዝ ውሃ ሲጠጡ ነበር፡፡ ብዙዎቹ በተቅማጥ እየተሰቃዩ ናቸው፡፡ አሁን ወስደው ያስገቧቸው ቤታቸው በፈረሰበት፤ መዝጊያቸው ተነቅሎ በተወሰደበት ቤት ውስጥ ነው፡፡ ቻግኒ ያሉትን አልመለሷቸውም ፍኖተሠላም ያሉትንም የወሰዳቸው የአገር ውስጥና የውጭ ጩኸት ስለደረሰባቸው 2 ተቃውሞውን ለማብረድ ተብሎ እንጂ በድርጊቱ ተፀጽተው አይደለም መንግስት በግልጽ ይቅርታ መጠየቅ አለበት፡፡ ወደ ዓለም አቀፍ ፍ/ቤት ሄደን ለመክሰስ የሚያስችለን ከበቂ በላይ ማስረጃ አለን ፡፡ ለመክሰስ ዝግጅት እያደረግን ነው፡፡ ኮስማና መስለን ብንታይም ይህንን ለማድረግ አቅም አለን፡፡ ከጉራፈርዳ ተፈናቅለው በእኛ ጽ/ቤትና በአዲስ አበባ ከተማ ተጠልለው የነበሩት ተፈናቃዮች ለሊት አፍነው የት እንዳደረሷቸው አይታወቅም፡፡ በህይወት መኖር አለመኖራቸውም መረጃ የለም፡፡” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አቶ ተስፋዬ ታሪኩ በበኩላቸው በሰጡት መልስ በቅርቡ ከቤኒሻንጉል ክልል የተፈናቀሉትን ተዘዋውረው መመልከታቸውን ገልፀዋል፡፡ “ በአሶሳ ኩምሩክ 60 ኢንቬስተሮች አሉ፡፡ 60ዎቹም የቀድሞ የህውሃት ታጋዮች ናቸው፡፡ በአካባቢው ከ200 በላይ ትግሪኛ ተናጋሪዎች አሉ፡፡ በርካታ ኦሮምኛ ተናጋሪዎችም ይገኛሉ፡፡ ማንም የነካቸው የለም፤ አማርኛ ተናጋሪዎችን እየለቀሙ እየደበደቡ እያሰሩ ከአካባቢው ያባርራሉ፤ ባንባሲ ያለው ካድሬ አካባቢውን ከአማራ ሳላፀዳ ዕረፍት የለኝም፤ እያለ በግልጽ ይፎክራል፡፡ ሰብስበው ጭድ የተከመረበት ቦታ ሜዳ ላይ አስረዋቸዋል፡፡ ጭዱን ለኩሰው በእሳት ሊፈጁን ነው ብለው ሥጋት ላይ ናቸው፡፡ አንድ ተፈናቃይ የኤች.አይ.ቪ መድኃኒት ተጠቃሚ ነኝ በፖሊስ ሄጄ መድኃኒት ላምጣ ብሎ ቢጠይቅ አትሄድም ድብን በል ተብሎ ተከልክሏል፡፡ ስለዚህ ወደ ዓለም አቀፍ ፍ/ቤት መሄዳችን የማይቀር ነው፡፡” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ረቡዕ 17 ኤፕሪል 2013

የቀድሞዋ የህወሀት ታጋይ ወ/ሮ አዜብ መስፍንን ተቹ


ወ/ሮ አዜብ መስፍን የባለቤታቸው ወርሃዊ ደመወዝ አነስተኛ እንደነበር በመጥቀስ በኢህአዴግ ጉባዔ ላይ ያደረጉትን ስሜታዊ ንግግር የሕዝብን የማመዛዘን ችሎታ ግምት ውስጥ ያላስገባ ነበር ሲሉ የቀድሞ የህወሃት ታጋይ ወ/ት አረጋሽ አዳነ ተቹ፡፡ወ/ት አረጋሽ በዛሬው ዕለት በአዲስአበባ ለንባብ በበቃው “ኢትዮ ምህዳር” ጋዜጣ በሰጡት ሰፊ ቃለምልልስ ላይ የወ/ሮ አዜብን ንግግር አስመልክቶ ጠንከር ያለ ትችት ሰንዝረዋል፡፡አቶ መለስ በፔሮል 6ሺ500 ብር ደመወዝ የሚከፈላቸው ብቸኛው መሪ እንደነበሩ ወ/ሮ አዜብ መናገራቸውን በመጥቀስ ጋዜጣው ላቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ
“የኢትዮጽያን ሕዝብ መቼም የማመዛዘን ችሎታ ያለው ነው፡፡የማስተዋል ችሎታ አለው፡፡ያውቃል፡፡የወ/ሮ አዜብ አባባል ግን የሕዝብን የማመዛዘን ችሎታ በትክክል የሚመዝን አድርጌ አልወሰድኩትም፡፡ምክንያቱም ሕዝቡ እውነታው ይህ እንዳልነበር ያውቃልና” ብለዋል፡፡አያይዘውም ጠ/ሚ/መለስ ቤተመንግስት ውስጥ ነው የሚኖሩት፡፡ቤተመንግስት ደግሞ የራሱ አስተዳደር ያለው ትልቅ ተቋም ነው፡፡ራሱን የቻለ ባጀት አለው፡፡ይህ ባጀት የት እንደሚውል የማይታወቅ አይደለም፡፡ቤተመንግስት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች የሚተዳደሩበት፣የሚኖሩበት ነው፡፡እንግዶች የሚያስተናግዱበትና የሚጠሩበት በጀት አላቸው፡፡ይህ አሁንየተፈጠረ ሳይሆን በፊትም የሚታወቅ ነገር ነው፡፡በየስብሰባው በሚሄዱበት ጊዜ ውጪ አገር ከሆነ በውጪ ምንዛሪ ይከፈላቸዋል፡፡የአገር መሪ ስለሆነ የአልጋና የምግብ ሊከፍሉ አይችሉም፡፡ስለዚህ ምን ያህል የውጪ ገንዘብ መሰብሰብ እንደሚቻል መገመት ይቻላል” በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
እነአቶ መለስ ልጆቻቸውን ውድ የተባለ ት/ቤት እንደሚያስተምሩ ያስታወሱት ወ/ት አረጋሽ አዳነ ከዛሬ 12 እና 13 ኣመት በፊት ለአንዱ ልጃቸው ብቻ በዓመት 35 ሺ ብር ይከፍሉ እንደነበር አውቃለሁ ብለዋል፡፡ሶስቱም ልጆቻቸው በዚህ ሁኔታ እንደተማሩ ቢታሰብ ገንዘቡ በዓመት 100ሺ ብር ይከፍሉ ነበር ማለት ነው ካሉ በኃላ ይህን
በስድስት ሺ ብር ደመወዝ ሊያደርጉት አይችሉም ብለዋል፡፡በተጨማሪም ኢንዶውመንት የሚባለው ግዙፉ የኤፈርት ሐብት በወ/ሮ አዜብ ቁጥጥር ስር መሆኑም ወ/ት አረጋሽ በማስታወስ በ6 ሺ ብር ገቢ ብቻ ኖረዋል የተባለውን አጣጥለውታል፡፡


ኢሳት ዜና:-

ማክሰኞ 16 ኤፕሪል 2013

ገዢው ፓርቲ ያልጠበቀውን የምርጫ ውጤት አገኘ

ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ያለምንም ጠንካራ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ባደረገው ምርጫ ያልጠበቀውን ውጤት ማግኘቱን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ያሰባሰብናቸው መረጃዎች አመለከቱ።

ምንም እንኳ ኢህአዴግ ምርጫውን ከ99 እስከ 100 ፐርሰንት እንደሚያሸንፍ ቢጠበቅም ህዝቡ በምርጫ ካርዶች ላይ ያሰፈረው መልእክት ግን ገዢው ፓርቲ ያልጠበቀውና ያለሰበው ነበር እንደ ታዛቢዎች አገላለጽ።

በአንዳንድ አካባቢዎች የቀበሌ እና የወረዳ ሹሞች የምርጫ ታዛቢዎች እና የድምጽ ቆጣሪዎች የተመለከቱዋቸውን ነገሮች በሚስጢር እንዲጠብቁ ሲያግባቡዋቸው መታየታቸውን ተዛቢዎች ገልጸዋል።

በሰሜን ወሎ ዞን ወልድያ ውስጥ በሚገኝ አንድ የምርጫ ጣቢያ ከገቡት የምርጫ ወረቀቶች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ባዶ ነጭ ወረቀት፣ ሌሎቹ ደግሞ ገዢው ፓርቲ ከስልጣን እንዲወርድ የሚጠይቁ ነበሩ። የሀይማኖት ነጻነታችን ይከበር፣ የታሰሩ መሪዎች ይፈቱ፣ የኑሮ ውድነቱ አስመርሮናል፣ ኢህአዴግ በቃህ ውረድ፣ ለውጥ እንፈልጋለን የሚሉት ጽሁፎች በዚህ የምርጫ ጣቢያ በብዛት ከተላለፉት መልእከቶች መካከል ይጠቀሳሉ እንደ አይን እማኞች አገላለጽ።

በሰሜን ሸዋ አጣየ ከተማ በሚገኝ አንድ ጣቢያ ደግሞ አብዛኛው ህዝብ ምንም ምልክት ሳያደርግ ነጭ ወረቀት ብቻ ማስገባቱን አንድ ታዛቢ ተናግረዋል::

በአዲስ አበባ አንድ የምርጫ ጣቢያ ደግሞ ጥቂት መራጮች ብቻ ድምጽ የሰጡ ሲሆን፣ ሌሎች መራጮች ገዢውን ፓርቲ የሚሰድቡ እና ለውጥን የሚጠይቁ መልእክቶችን ማስገባታቸውን በቦታው የነበረው ታዛቢ ገልጿል::

በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለከተማ ዋልያ ትምህርት ቤት ውስጥ በነበረው ምርጫ ደግሞ አስመራጮች ሰው በማጣታቸውን ቁርስ እንብላ በማለት የምርጫ ጣቢያውን ዘግተው መሄዳቸውን ተከትሎ፣ በግዳጅ ለመምረት እንዲወጡ የተገደዱት ሰዎች፣ ጣቢያው ተዘግቶ በማየታቸው ወደ የቤታቸው የተመለሱ ሲሆን፣ ጉዳዩን ሰምተው የመጡት የኢህአዴግ ካድሬዎች ከአስመራጮች ጋር አምባጋሮ ፈጥረው ነበር።

በአዋሳ ከተማ ደግሞ ምርጫው ከመካሄዱ ከአንድ ቀን በፊት የኢህአዴግ ካድሬዎች ቤት ለቤት እየዞሩ የምርጫ ካርድ ያካሂዱ ነበር። በጎንደር ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ እና አደባባይ ኢየሱስ ባሉ የምርጫ ጣቢያዎች እስከ ሐሙስ ሚያዚያ 3 ቀን 2005ዓ.ም. ድረስ የመራጮች ካርድ ሲሰጥ መዋሉን ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዛሬ ባወጣው ዘገባ አመልክቷል።

ምርጫ ቦርድ በመላው ሃገሪቱ በሚገኙ 954 ወረዳዎች ፣ በተዘጋጁ 44 ሺ 509 የምርጫ ጣቢያዎች ፥ 3 ነጥብ 6 ሚሊዮን እጩዎችም ለውድድር ቀርበው 90 በመቶው ድምጹን መስጠቱን ገልጿል።

የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና ህብረተሰቡ በምርጫው ያሳየው ተሳትፎ የጎላ እንደነበር ገልጸው ተሳትፎው ህዝቡ ስለምርጫና ስለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ያለው ግንዛቤ ከፍተኛ እንደሆነ ያሳየበት ነበር ብለዋል።

በአንዳንድ አካባቢዎች የወጡ የምርጫ ውጤቶች እንደሚያሳዩት ኢህአዴግ ከ99 እስከ 100 በመቶ አሸንፎአል። በዚህ ምርጫ ገዢው ፓርቲ በ2002 ዓም ይዞት የነበረውን የ99 ነጥብ ስድስት በመቶ ውጤት ረከርድ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ የምርጫ ታሪክ የተገኘውን ሪከርድ ሁሉ የሚያሻሽልና ለዘመናትም ሳይሰበር እንደሚቆይ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።


ኢሳት ዜና:

ሐሙስ 11 ኤፕሪል 2013

በፍኖተሰላም ከተማ የሚገኙ ተፈናቃዮች ወደ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እንዲመለሱ እየተደረገ ነው


ዛሬ ሊነጋጋ ሲል ከ20 በላይ መኪኖች የፍኖተ-ሰላም ከተማን ማጨናነቃቸውን የተናገሩት ተፈናቃዮች፣ ከብር-ሸለቆ የመጡ የፌደራል ፖሊስ አባላት ከዞን እና ከወረዳ ፖሊስ አባላት ጋር በመተባበር፣ ተፈናቃዮቹ ወደ መኪኖቹ እንዲገቡ አዘዋል።
ጥሪው ድንገተኛ የሆነባቸው ተፈናቃዮች የሚያደርጉት ጥፍቷቸው ሲላቀሱ ፣ ወላጆቻቸውን ተከትሎም ህጻናት ሲያለቅሱ ይታዩ እንደነበር የአይን እማኞች ይናገራሉ።
አንድ ሌላ ተፈናቃይ ዛሬ ስላጋጠማቸው ነገር ሲናገሩ ” ሰው በተወለደበት አገር ይህን አይነት በደል ይደርስበታል” ብየ አላስብም ነበር ብለዋል።
ወደ መጣበት ቦታ ለመመለስ በመጠባበቅ ላይ የነበረ አንድ ወጣት ፣ ቤቱ መቃጠሉን ቢገልጽም መንግስት እንዳደረገ ያድርገን በማለት እንደሚሄድ ገልጿል።
ወደ መጣበት ቦታ ለመመለስ ፈቃደኛ ያልሆነ አንድ ተፈናቃይ፣ ለምን እንደማይመለስ ሲጠየቅ ” በእርሱና በልጆቹ ላይ ለሚደርስበት ጉዳት ዋስትና ስላልተሰጠው” መሆኑን ገልጿል። የ2 ልጆች አባት መሆኑን የገለጸው አርሶአደሩ የልጆቹ እናት በህመም ምክንያት ራቅ ወዳለ ቦታ በመሄዷ፣ ልጆቹን ይዞ ለመመለስ አለመድፈሩን ተናግሯል።
በዛሬው እለት 16 መኪኖች ወደ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ያቀኑ ሲሆን፣ በነገው እለትም ተጨማሪ ሰዎች ይሄዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ተፈናቃዮች ስለሚያቀርቡት አቤቱታ የዞኑን የጸጥታ ሀላፊ ለማነጋገር በተደጋጋሚ ስልክ ብንደውልም ስብሰባ ላይ ናቸው በሚል ምክንያት ለማነጋገር ሳይቻል ቀርቷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በኖርዌይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአማራ ተወላጆች ላይ የተወሰደውን እርምጃ በማውገዝ ሰላማዊ ሰልፎችናንና የተለያዩ ዝግጅቶችን እንደሚያደርጉ ታውቋል።
ስርክአዲስ ታየ ተጨማሪ ዘገባ ልካለች።


ኢሳት ዜና:

ማክሰኞ 9 ኤፕሪል 2013

ምርጫ እስኪያልፍ ሙዚቃ ቤቶች የቴዲ አፍሮና የፀጋዬ እሸቱን ዘፈኖች መክፈት ተከለከሉ


ምርጫ እስኪያልፍ ሙዚቃ ቤቶች የቴዲ አፍሮና የፀጋዬ እሸቱን ዘፈኖች መክፈት ተከለከሉ

በአዲስ አበባ የተለያዩ ስፍራዎች በሚገኙ መዝናኛዎችና ሙዚቃ ቤቶች በሚያዝያ መጀመሪያ የሚደረገው የአካባቢ ምርጫ ሳያልፍ ሀገር ፍቅር ስሜት የሚቀሰቅሱ ዘፈኖችን እንዳይከፍቱ ክልከላ ተደረገ፡፡ ከጥቂት ቀናት በኋላ በሚደረገው የከተማ መስተዳድርና የአካባቢ ምርጫ ብቻውን የሚወዳደረው ኢህአዴግ በካድሬዎቹ አስገራሚ ትዕዛዞችን እየሰጠ እንደሚገኝ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ጠቆሙ፡፡
በአዲሱ ትዕዛዝ መሰረት ምርጫው እስኪያልቅ ድረስ ሙዚቃ ከፍ አድርገው የሚያጫውቱ ሙዚቃ ቤቶችና የመዝናኛ ስፍራዎች የሀገር ፍቅር ስሜት የሚቀሰቅሱና ስለባንዲራ የተዜሙዘፈኖችን መክፈት ተከልክለዋል፡፡ በትዕዛዙ በተለይ የተከለከሉት የቴዲ አፍሮና የፀጋዬ እሸቱ አዲሱ አልበም ላይ የተካተቱት ዜማዎች ይጠቀሳሉ፡፡ ነጋዴዎቹ “ክልከላው ከምርጫው ጋር ምን እንዳያያዘው አልገባንም፣ሆኖም ከመንግስት የመጣ ትዕዛዝ ስለሆነ ላለፉት ሁለት ሳምንታት ዘፈኖቹን ማጫወት አቁመናል” ብለዋል፡፡ነጋዴዎቹ ጨምረው ለፍኖተ ነፃነትእንደገለፁት በተለያየ ጊዜ ለቁጥጥር የሚመጡት የወረዳ ካድሬዎችየተከለከሉትን ዘፈኖች ተከፍቶ ከሰሙ ዛቻና ማስፈራሪያ እንደሚያደርሱባቸው ፡፡

“የቴዲን ዘፈን በተለያዩ ወቅቶች አትክፈቱ ተብለን እናውቃለን” የሚሉት ነጋዴዎቹ የፀጋዬ እሸቱ አዲሱ አልበም ውስጥ ያሉት ሀገርንና ባንዲራን የሚመለከቱ ዘፈኖች በሬዲዮ እየተለቀቁ እነሱ እንዳይከፍቱ መደረጋቸው እንዳስገረማቸው ገለፀዋል፡፡ ምንጮቻችን ተዘዋውረው ያነጋገሯቸው ነጋዴዎች እንደገለፁት ይህ ክልከላ ጎልቶ የታየው በመርካቶና በፒያሳ አካባቢ ነው፡፡

“ህወሓት የአማራ ፖለቲከኞች ከኢትዮጵያዊ ብሔረተኝነት ርዕዮተአለም እንዲወጡ ማድረግ ይፈልጋል”


“ህወሓት የአማራ ፖለቲከኞች ከኢትዮጵያዊ ብሔረተኝነት ርዕዮተአለም እንዲወጡ ማድረግ ይፈልጋል”

JawarMohammed2010_2አቶ ጃዋር መሀመድ የፖለቲካ ተንታኝ
ፍኖተ ነፃነት፡- ኢህአዴግ የብሔር ጥያቄ መልሻለሁ ይላል፤ ሆኖም ብሔርን መሰረትያደረጉ በደሎች ሲፈፀሙ ይታያል፡፡ በርግጥ የብሔር ጥያቄ ተመልሷል ማለት ይቻላል?
ጃዋር፡- እንደምታውቀው የብሄር ጥያቄ ሁለት አይነት መልስ ነበር የሚያስፈልገው፡፡ አንደኛ እራስን በራስ የማስተዳደር፣ በራስ ባህል ላይ፣ በራስ አከባቢ ላይ ራስንችሎማስተዳደር ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ የጋራ ሀገርን በጋራ ማስተዳደር፣ ማለትምእንደሀገር በጋራ ያፈሩትን በጋራ የመጠቀም፣ በጋራ ተካፍሎና ተቋድሶ መኖር ነው፡፡ይህ ማለት የሀገሪቷን ኢኮኖሚ፣የሀገሪቷን ስልጣንና ባህላዊ እሴቶች በጋራ እያዋጡ
በጋራ ተቋድሶ መኖር ማለት ነው፡………………………………….

የፍትህ ጋዜጣ አሳታሚ እና የሰማያዊ ፓርቲ አመራር ከመንግስት ሸሽተው ተሰደዱ!

የፍትህ ጋዜጣ አሳታሚ የሆነችው ማስተዋል የህትመት ስራ ድርጅት ስራ አስኪያጅ የነበረው ማስተዋል ብርሃኑ እና የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር እና የፍትህ ጋዜጣ ድረ ገጽ አዘጋጅ የሆነው አርአያ ጌታቸው መንግስትን ሸሽተው ከሀገር ተሰደዱ! 

ማስተዋል ብርሃኑ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የሚያዘጋጃት ፍትህ ጋዜጣ አሳታሚ የነበረ ሲሆን በተለይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት በኋላ ፍትህ፤ "ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሞቱስ ለምን ሞቱ ትላለች…" ተብላ ከሰላሳ ሺህ ኮፒ በላይ እንድትቃጠል ቢደረግም መንግስታችን በቅጡ ስላልተደሰተ በአዘጋጁ ተመስገን እና በአሳታሚው ማስተዋል ብርሃኑ ላይ ክስ መመስረቱ ይታወቃል፡፡ (የማይታወቅ ከሆነ አሁን ይታወቅ) 

እነ ማስተዋል ብርሃኑ በተከሰሱበት በዚህ ክስ በ50 ሺህ ብር ዋስትና ተለቀው ለሚያዝያ 17 2005 የተቀጠሩ ሲሆን በክሱ ጥፋተኛ ከተባሉ እስከ አስራ ሰባት አመት እስር ይጠብቃቸዋል፡፡ ማስተዋል ሸሽቶ ከመውጣቱ በፊት የመንግሰት ደህነነት ሰዎች በተደጋጋሚ እየተከታተሉ የእጅ ስልኩን በመንጠቅ ከማን ጋ እንደተደዋወለ እና ምን አይነት መልዕክት (ሜሴጅ) እንደተለዋወጠ በግድ ያዩበት እንደነበር ነግሮኛል፡፡

በነገራችን ላይ የፍትህ አሳታሚ እና ፍትህ ጋዜጣ በቀጠሮ ከተያዘው ክስ በተጨማሪ ወደ አርባ የሚጠጉ በይደር የተያዙ ክሶችም አሉበት፡፡

በተጨማሪም ከስድስት አመታት በፊት የተቃውሞውን ጎራ የተቀላቀለው ወጣት አርአያ ጌታቸው በበኩሉ በተለይ የፍትህ ጋዜጣ ድረ ገጽን ማሰናዳት ከጀመረ ወዲህ የበረታ ክትትል እና ማስፈራሪያ ከመንግሰት የስጋ ዘመዶች እንደደረሰበት ይናገራል፡፡

ከዚህ በፊት አንድ የፌደራል ፖሊስ ኮማንደር በመኪና አፍኖ የማያውቀው ቦታ ከወሰደው በኋላ ለተመስገን ደሳለኝ ከውጪ ሀገር ያሉ አሸባሪ ዲያስፖራዎች የሚያደርጉለት የገንዘብ እርዳታ መኖሩን እና በመሃል ሆኖ ገንዘቡን የሚያቀባብለው ደግሞ እርሱ እንደሆነ ነግሮት፤ ይህንን ድርጊቱን የማያቆም ከሆነ በእህትህ እና በእናትህ ላይ ፈርደሃል ማለት ነው… የሚል ዛቻ አድርሶበታል፡፡

ከአመት በፊት ይህ ማስፈራሪ የደረሰው አርአያ፤ ለቤተሰቦቹ ደህንነት ሲል ቤት ተከራቶ መኖር ቢጀምርም፤ ከአመት በላይ የዘለቀው ይኸው ማስፈራሪያ አሁንም እጅግ ተባብሶ "ከፍትህ ጋዜጣ ጋር ያለህን ግንኙነት አቁም ብለንህ እስካሁን አላቆምክም ስለዚህ እንገድልሃለን!" በሚል ቃል በቃል ማስጠንቀቂያ ሲደርሰው "ገዳዮቹን" መሸሹን ይናገራል፡፡ አርአያ የፍትህ ጋዜጣ ድረ ገጽ አዘጋጅ የነበረ ከመሆኑም በላይ ሰማያዊ ፓርቲን ከመሰረቱት ግንባር ቀደም ወጣቶች አንዱ ነው፡፡

በፍትህ ምክንያት የተሰደዱት ማስተዋል ብርሃኑ እና አርአያ ጌታቸው አሁንም የደህንነታችን ነገር ስጋት ላይ ነው፤ ብለው ያሉበትን ቦታ እንዳልናገር አደራ ብለውኛል፡፡ የምናገረው ነገር ግን አለኝ፤ በአዲስ መስመር እንዲህ እላለሁ፤

እንደዚህ እያባረሩ እና እንደዚያ እያማረሩ ስንት አመት መዝለቅ ይቻላል፡፡ እውነት እውነት እላችኋለው ከጥቂት እርምጃ በኋላ እግራችሁ እግራችሁን ጠልፎ ይጥላችኋል!


:Source Abetokichaw

የፍትህ ጋዜጣ አሳታሚ እና የሰማያዊ ፓርቲ አመራር ከመንግስት ሸሽተው ተሰደዱ!

የፍትህ ጋዜጣ አሳታሚ የሆነችው ማስተዋል የህትመት ስራ ድርጅት ስራ አስኪያጅ የነበረው ማስተዋል ብርሃኑ እና የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር እና የፍትህ ጋዜጣ ድረ ገጽ አዘጋጅ የሆነው አርአያ ጌታቸው መንግስትን ሸሽተው ከሀገር ተሰደዱ! 

ማስተዋል ብርሃኑ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የሚያዘጋጃት ፍትህ ጋዜጣ አሳታሚ የነበረ ሲሆን በተለይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት በኋላ ፍትህ፤ "ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሞቱስ ለምን ሞቱ ትላለች…" ተብላ ከሰላሳ ሺህ ኮፒ በላይ እንድትቃጠል ቢደረግም መንግስታችን በቅጡ ስላልተደሰተ በአዘጋጁ ተመስገን እና በአሳታሚው ማስተዋል ብርሃኑ ላይ ክስ መመስረቱ ይታወቃል፡፡ (የማይታወቅ ከሆነ አሁን ይታወቅ) 

እነ ማስተዋል ብርሃኑ በተከሰሱበት በዚህ ክስ በ50 ሺህ ብር ዋስትና ተለቀው ለሚያዝያ 17 2005 የተቀጠሩ ሲሆን በክሱ ጥፋተኛ ከተባሉ እስከ አስራ ሰባት አመት እስር ይጠብቃቸዋል፡፡ ማስተዋል ሸሽቶ ከመውጣቱ በፊት የመንግሰት ደህነነት ሰዎች በተደጋጋሚ እየተከታተሉ የእጅ ስልኩን በመንጠቅ ከማን ጋ እንደተደዋወለ እና ምን አይነት መልዕክት (ሜሴጅ) እንደተለዋወጠ በግድ ያዩበት እንደነበር ነግሮኛል፡፡

በነገራችን ላይ የፍትህ አሳታሚ እና ፍትህ ጋዜጣ በቀጠሮ ከተያዘው ክስ በተጨማሪ ወደ አርባ የሚጠጉ በይደር የተያዙ ክሶችም አሉበት፡፡

በተጨማሪም ከስድስት አመታት በፊት የተቃውሞውን ጎራ የተቀላቀለው ወጣት አርአያ ጌታቸው በበኩሉ በተለይ የፍትህ ጋዜጣ ድረ ገጽን ማሰናዳት ከጀመረ ወዲህ የበረታ ክትትል እና ማስፈራሪያ ከመንግሰት የስጋ ዘመዶች እንደደረሰበት ይናገራል፡፡

ከዚህ በፊት አንድ የፌደራል ፖሊስ ኮማንደር በመኪና አፍኖ የማያውቀው ቦታ ከወሰደው በኋላ ለተመስገን ደሳለኝ ከውጪ ሀገር ያሉ አሸባሪ ዲያስፖራዎች የሚያደርጉለት የገንዘብ እርዳታ መኖሩን እና በመሃል ሆኖ ገንዘቡን የሚያቀባብለው ደግሞ እርሱ እንደሆነ ነግሮት፤ ይህንን ድርጊቱን የማያቆም ከሆነ በእህትህ እና በእናትህ ላይ ፈርደሃል ማለት ነው… የሚል ዛቻ አድርሶበታል፡፡

ከአመት በፊት ይህ ማስፈራሪ የደረሰው አርአያ፤ ለቤተሰቦቹ ደህንነት ሲል ቤት ተከራቶ መኖር ቢጀምርም፤ ከአመት በላይ የዘለቀው ይኸው ማስፈራሪያ አሁንም እጅግ ተባብሶ "ከፍትህ ጋዜጣ ጋር ያለህን ግንኙነት አቁም ብለንህ እስካሁን አላቆምክም ስለዚህ እንገድልሃለን!" በሚል ቃል በቃል ማስጠንቀቂያ ሲደርሰው "ገዳዮቹን" መሸሹን ይናገራል፡፡ አርአያ የፍትህ ጋዜጣ ድረ ገጽ አዘጋጅ የነበረ ከመሆኑም በላይ ሰማያዊ ፓርቲን ከመሰረቱት ግንባር ቀደም ወጣቶች አንዱ ነው፡፡

በፍትህ ምክንያት የተሰደዱት ማስተዋል ብርሃኑ እና አርአያ ጌታቸው አሁንም የደህንነታችን ነገር ስጋት ላይ ነው፤ ብለው ያሉበትን ቦታ እንዳልናገር አደራ ብለውኛል፡፡ የምናገረው ነገር ግን አለኝ፤ በአዲስ መስመር እንዲህ እላለሁ፤

እንደዚህ እያባረሩ እና እንደዚያ እያማረሩ ስንት አመት መዝለቅ ይቻላል፡፡ እውነት እውነት እላችኋለው ከጥቂት እርምጃ በኋላ እግራችሁ እግራችሁን ጠልፎ ይጥላችኋል!


:Source Abetokichaw

የፍትህ ጋዜጣ አሳታሚ እና የሰማያዊ ፓርቲ አመራር ከመንግስት ሸሽተው ተሰደዱ!

የፍትህ ጋዜጣ አሳታሚ የሆነችው ማስተዋል የህትመት ስራ ድርጅት ስራ አስኪያጅ የነበረው ማስተዋል ብርሃኑ እና የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር እና የፍትህ ጋዜጣ ድረ ገጽ አዘጋጅ የሆነው አርአያ ጌታቸው መንግስትን ሸሽተው ከሀገር ተሰደዱ! 

ማስተዋል ብርሃኑ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የሚያዘጋጃት ፍትህ ጋዜጣ አሳታሚ የነበረ ሲሆን በተለይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት በኋላ ፍትህ፤ "ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሞቱስ ለምን ሞቱ ትላለች…" ተብላ ከሰላሳ ሺህ ኮፒ በላይ እንድትቃጠል ቢደረግም መንግስታችን በቅጡ ስላልተደሰተ በአዘጋጁ ተመስገን እና በአሳታሚው ማስተዋል ብርሃኑ ላይ ክስ መመስረቱ ይታወቃል፡፡ (የማይታወቅ ከሆነ አሁን ይታወቅ) 

እነ ማስተዋል ብርሃኑ በተከሰሱበት በዚህ ክስ በ50 ሺህ ብር ዋስትና ተለቀው ለሚያዝያ 17 2005 የተቀጠሩ ሲሆን በክሱ ጥፋተኛ ከተባሉ እስከ አስራ ሰባት አመት እስር ይጠብቃቸዋል፡፡ ማስተዋል ሸሽቶ ከመውጣቱ በፊት የመንግሰት ደህነነት ሰዎች በተደጋጋሚ እየተከታተሉ የእጅ ስልኩን በመንጠቅ ከማን ጋ እንደተደዋወለ እና ምን አይነት መልዕክት (ሜሴጅ) እንደተለዋወጠ በግድ ያዩበት እንደነበር ነግሮኛል፡፡

በነገራችን ላይ የፍትህ አሳታሚ እና ፍትህ ጋዜጣ በቀጠሮ ከተያዘው ክስ በተጨማሪ ወደ አርባ የሚጠጉ በይደር የተያዙ ክሶችም አሉበት፡፡

በተጨማሪም ከስድስት አመታት በፊት የተቃውሞውን ጎራ የተቀላቀለው ወጣት አርአያ ጌታቸው በበኩሉ በተለይ የፍትህ ጋዜጣ ድረ ገጽን ማሰናዳት ከጀመረ ወዲህ የበረታ ክትትል እና ማስፈራሪያ ከመንግሰት የስጋ ዘመዶች እንደደረሰበት ይናገራል፡፡

ከዚህ በፊት አንድ የፌደራል ፖሊስ ኮማንደር በመኪና አፍኖ የማያውቀው ቦታ ከወሰደው በኋላ ለተመስገን ደሳለኝ ከውጪ ሀገር ያሉ አሸባሪ ዲያስፖራዎች የሚያደርጉለት የገንዘብ እርዳታ መኖሩን እና በመሃል ሆኖ ገንዘቡን የሚያቀባብለው ደግሞ እርሱ እንደሆነ ነግሮት፤ ይህንን ድርጊቱን የማያቆም ከሆነ በእህትህ እና በእናትህ ላይ ፈርደሃል ማለት ነው… የሚል ዛቻ አድርሶበታል፡፡

ከአመት በፊት ይህ ማስፈራሪ የደረሰው አርአያ፤ ለቤተሰቦቹ ደህንነት ሲል ቤት ተከራቶ መኖር ቢጀምርም፤ ከአመት በላይ የዘለቀው ይኸው ማስፈራሪያ አሁንም እጅግ ተባብሶ "ከፍትህ ጋዜጣ ጋር ያለህን ግንኙነት አቁም ብለንህ እስካሁን አላቆምክም ስለዚህ እንገድልሃለን!" በሚል ቃል በቃል ማስጠንቀቂያ ሲደርሰው "ገዳዮቹን" መሸሹን ይናገራል፡፡ አርአያ የፍትህ ጋዜጣ ድረ ገጽ አዘጋጅ የነበረ ከመሆኑም በላይ ሰማያዊ ፓርቲን ከመሰረቱት ግንባር ቀደም ወጣቶች አንዱ ነው፡፡

በፍትህ ምክንያት የተሰደዱት ማስተዋል ብርሃኑ እና አርአያ ጌታቸው አሁንም የደህንነታችን ነገር ስጋት ላይ ነው፤ ብለው ያሉበትን ቦታ እንዳልናገር አደራ ብለውኛል፡፡ የምናገረው ነገር ግን አለኝ፤ በአዲስ መስመር እንዲህ እላለሁ፤

እንደዚህ እያባረሩ እና እንደዚያ እያማረሩ ስንት አመት መዝለቅ ይቻላል፡፡ እውነት እውነት እላችኋለው ከጥቂት እርምጃ በኋላ እግራችሁ እግራችሁን ጠልፎ ይጥላችኋል!

:Source Abe tokichaw

ሰኞ 8 ኤፕሪል 2013

አቶ መለስን የተኩት ሰዎች ከእረሱም የባሱ ጭፍን አምባገነኖች ናቸው፡፡ (ከተመስገን ደሳለኝ )


አቶ መለስን የተኩት ሰዎች ከእረሱም የባሱ ጭፍን አምባገነኖች ናቸው፡፡ (ከተመስገን ደሳለኝ )

ከምሽቱ አንድ ሰአት አልፏል፤ የእጅ ስልኬ ደጋግሞ ቢጮኽም ትኩረት አልሰጠሁትም፡፡ ከጥቂት ሰከንዶች ፋታ በኋላ የቢሮዬ ስልክ ጮኸ፤ አነሳሁት፡፡ ለካስ እንዲህ በአንዱ አልመልስ ስላት፣ በሌላው እያፈራረቀች የምትደውለው ዕድሜዋ ወደ ሰባ እየተጠጋ ያለው አሮጊቷ እናቴ ኖራለች፡-
‹‹አቤት! እናቴ››
‹‹ለምንድነው የዚህን ያህል ስልኩ ሲጮኽ የማትመልሰው?›› ቆጣ ብላ ጠየቀችኝ፡፡ ‹‹አስቸኳይ ስራ ላይ ስለነበርኩ ነው››
‹‹ኤዲያ! አንተ ደግሞ ሁል ጊዜ ጠብ ለማይል ነገር፣ ችክ ማለት ትወዳለህ›› …በእርግጥ እናቴ እውነቷን ነው! ችክ ያልኩ ቸካካ ነገር ሳልሆን አልቀርም ፡፡
ተመስገን ደሳለኝ
‹‹ልዕልና›› ጋዜጣ ታግዳለች፤ እንደ‹‹ፍትህ›› እና ‹‹አዲስ ታይምስ›› ሁሉ የስርዓቱ የአፈና ሰለባ ሆናለች፤ የሚገርመው ግን መታገዷ አይደለም፣ የታገደችበት መንገድ እንጂ፡፡ ከዚህ ቀደም ደጋግሜ እንደገለፅኩት አቶ መለስን የተኩት ሰዎች ከእረሱም የባሱ ጭፍን አምባገነኖች ናቸው፡፡ ማንንም አይፈሩም፡፡ እግዚአብሄርንም ቢሆን ‹‹በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ካልተጠመቅህ አምላክ ሆነ እንድትቀጥል አንፈቅድልህም›› ከማለት አይመለሱም፡፡
የሆነ ሆኖ የስርዓቱ አይን አውጣነት የደረሰበትን ደረጃ ለመገንዘብ የሚከተለውን በጥሞና አንብቡ፡፡
የ‹‹ልዕልና›› አሳታሚ ድርጅት በሁለት ወዳጆቼ ስም ከተገዛ በኋላ፣ ስም ከመዞሩ በፊት ስርዓቱን ወጥመድ ውስጥ የሚከት ስልት (አይን ያወጣ አምባገነን ባህሪውን ወዳጆቹ ሳይቀር ይኮንኑት ዘንድ ወደ አደባባይ የሚያወጣ) ተነደፈ፡፡ በስልቱ መሰረትም ከቀድሞ
የድርጅቱ ባለቤቶች ጋር አንድ ስምምነት ተደረገ፡፡ ይኸውም እኔ የሚጠበቅብኝን የአክሲዎን ሽያጭ ክፍያ አስቀድሜ ብከፍልም፤ ምንም አይነት የስም ዝውውር ሳይደረግ ባለቤትነቱ በእነርሱ ስም ሆኖ እንዲቀጥል ተስማማን፡፡ በዚሁ መንገድ ስራው ተጀመረ፡፡ ለአፈና ሲንደረደር ግራና ቀኝ ለማያጣራው መንግስት ደግሞ እንዲህ የሚል የ‹‹ተጋገረ›› መረጃ በጋዜጣችን ላይ አስተላለፍን ፡-
‹‹በህጋዊ መንገድ የስም ዝውውር አድርገን ነው ስራ የጀመርነው፡፡››
እነሆ ይህ በሆነ በአስራ ሶስተኛው ቀን (13/07/05) ብሮድካስት ውስጥ ያሉ ዞምቢዎች
‹‹ድርጅቱ ለሌላ ሶስተኛ ወገን በህገ-ወጥ መንገድ የስም ዝውውር አስተላልፏል›› ሲሉ ድምፃቸውን አሰሙ፡፡
መቼ ተላለፈ? የተላለፈላቸው ሰዎችስ ስም ማን ይባላል? የሚሉት መሰረታዊ ጥያቄዎች ብሮድካስትን አያሳስቡትም፤ ያውም አንድ የሚዲያ ተቋምን ያህል ነገር ሲዘጋ (በነገራችን ላይ የስም ዝውውር የተደረገው ብሮድካስት ደብዳቤውን ከፃፈ ከአምስት ቀን በኋላ /በ18/07/05/) ነው፡፡
ለብሮድካስት ህገ-ወጥ እግድ ጋዜጣዋ መገዛት እንደሌለባት አዘጋጆቹ ስምምነት ላይ ስለደርሰን በ20/07/05 ታተመች፡፡ ሆኖም ሌላው ዞምቢ ድምፁን አሰማ-ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፡፡ ይህ መስሪያ ቤት ያለምንም ማጣራት ጋዜጣዋ በወጣችበት ዕለት (20/07/05) ንግድ ፍቃዳችንን መሰረዙን የሚገልፅ ደብዳቤ ላከልን፡፡ በእጅጉ የሚገርመው ሁለቱም ‹‹ተቋምዎች›› ህገ-ወጥነታችንን የገለፁት ተመሳሳይ የአዋጅ ቁጥር በመጥቀስ መሆኑ ነው፡፡ ‹‹ከመገናኛ እና ብዙሃን የመረጃ ነፃነት አዋጅ ቁጥር 590/200 ከሚፈቅደው ውጪ…›› በማለት፡፡ …ይህ ምን ማለት ነው? በዚህ አዋጅ ውስጥ በርካታ አንቀፆች ተደንግገዋል፡፡ ስለአታሚ፣ አሳታሚ፣ ዋና አዘጋጅ፣ መረጃ
የማግኘት መብት፣ የማሳተምና የመደራጀት ነፃነት፣ ስለአከፋፋዮች… አጅግ ብዙ ጉዳዮችን ያካትታል፡፡ ታዲያ እኛ የታገድነው ከእነዚህ ሁሉ አንቀፆች የትኛውን ተላልፈን ነው? …ቢያንስ መንግስት የሚመስል ነገር ወይም ‹‹መንግስት ነኝ›› የሚል ካለ ጥፋታችንና የተላለፍነውን የአዋጁን አንቀፅ ቢነግረን ሌላው ቢቀር ከስሜት መጎዳት እንድን ነበር፡፡ ነገር ግትን ዞምቢዎቹ እንደከዚህ ቀደሙ አንቀፅ በመጥቀስ ማስመሰል እንኳን አልቻሉም፡፡ በደፈናው የአዋጅ ቁጥር ጠቀሱና አረፉት፡፡
…አሁን ሀገራችን አስፈሪ ደረጃ ላይ ደርሳለች፡፡ በአደባባይ ህግ ለመጣስና የፈቀዳቸውን ለማድረግ ትንሽ እንኳ በማያመነቱ አደገኛ ሰዎች መዳፍ ስር ወድቃለች፡፡ የአማርኛ ቋንቋ ተናገሪዎች ለዓመታት ከሰፈሩበት ቀዬ በኃይል መፈናቀላቸው ቀጥሏል፡፡ በእርግጥ በመለስ ዘመንም ቢሆን መፈናቀሉ ነበር፡፡ ኧረ እንዲያውም ‹‹ደን እየጨፈጨፉ ስላስቸገሩ ነው›› ብሎ ሁሉ አላግጦባቸዋል፡፡
የአማራው ‹‹ወኪል›› ነኝ የሚለው ብአዴንም ቢሆን ከታምራት ላይኔ ክፉ መንፈስ ገና ነፃ አልወጣም፡፡ ታምራት ላይኔ በስልጣን ዘመኑ በርካታ የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ተወላጆች በየአካባቢው ሞትና መፈናቀል እየደረሰባቸው እንደሆነ ሲነገረው ‹‹እኛ ከክልል ሶስት ውጪ ስለሚኖሩ አማሮች አያገባንም፡፡ ምክንያቱም በነፍጠኝነት ለወረራ የሄዱ ናቸው›› ብሎ ተሳለቆ ነበር፡፡ ዛሬ እነኦቦ አዲሱ ለገሰም ከዚህ አቋማቸው አልተቀየሩም፡፡ ተወልደ ወ/ማርያም በክፍፍሉ ወቅት ብአዴኖች ከመለስ ጎን በመቆማቸው ተበሳጭቶ ‹‹የፖለቲካ ደሀ ናችሁ›› ሲል መተቸቱ በረከት ስምዖን ዛሬም የገባው አይመስለኝም፡፡
የማፈናቀሉ መሀንዲስ ህወሓትም ቢሆን ይህ መንገድ ብዙ ርቀት የማያስኬድ ስለመሆኑ ከሃያ ዓመት በኋላም አልተገለፀለትም፡፡ ለዚህም ይመስለኛል ከፋፍሎ በመግዛት እና በማዳከም ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ በመከተል ጉልበቱን እያዛለ ያለው፡፡ በነገራችን ላይ መረሳት የሌለበት ቁም-ነገር የጥፋት ስራው ተጠያቂ ህወሓት እንጂ ‹‹እወክለዋለው›› የሚለው የትግራይ ህዝብ አለመሆኑ ነው፡፡ አማራ- በብአዴን፣ ኦሮሞ-በኦህዴድ እንደማይገለፀው ሁሉ፣ የትግራይ ህዝብም በህወሓት ይገለፃል የሚል የጨዋታ ህግ የለም፡፡ እነዚህ ሰዎች ለስልጣናቸው እስከጠቀመ ድረስ የማይፈፅሙት ህገ-ወጥ ድርጊት አለመኖሩ ላይ መስማማት የሚኖርብን ይመስለኛል፤ የማይፈፅሙት ጭካኔም የለም፡፡ ይህንን የሚያሳይ አንድ ነገር ልንገራችሁ፡፡ ታሪኩ የቀድሞ የደህንነት ሹም የነበረው ክንፈ ገ/መድህንን በጥይት ደብድቦ ስለገደለው ሻለቃ ፀሀዬን የሚመለከት ነው፡፡ እንደሚታወቀው ሟችም ገዳይም ትግርኛ ተናጋሪዎች ቢሆኑም፣ ሻለቃው ወንጀሉን ከፈፀመ በኋላ ለብዙ ችግር ተዳርጎ ነበር፣ ያውም ከነቤተሰቡ፡፡ መጀመሪያ ባለቤቱን ከምትሰራበት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት አባረሯት፡፡ እግር በእግርም እየተከታተሉ በኪራይ ከምትኖርበት ቤት አፈናቀሏት (በጊዜው እስክንድር ነጋ የገንዘብ ድጋፍ ያደርግላት ነበር) ሻለቃውም ለስድስት ዓመት ያህል በጨለማ ቤት ውስጥ በመታሰሩ የአይን ብርሃኑ በከፍተኛ ደረጃ ተጎዳ፡፡ ፍርድ ቤት ሲቀርብ እንዴት ለመራመድ ይቸገር እንደነበረ አስተውለናል፡፡ እኔ እያልኩ ያለሁት ያጠፋ ሰው በህግ አይጠየቅ አይደለም፤ ከህግ ውጪ ስለምን የበቀል ሰለባ ይሆናል ነው? ሰዎቹ ከየትኛውም ብሄር ተወለዱ በጠላትነት ከመዘገቧችሁ ለጭካኔያቸው ወደር የለውም፡፡
የሆነው ሆኖ ስርዓቱ ገደብ ላጣው ጭካኔው ‹‹ብሄር›› የተሰኘ አጥር የለውም ያስባለኝ በሻለቃው ህይወት መጨረሻ የተፈፀመው ድርጊት ነውና እሱን ልንገራችሁ፡፡
ዕለቱ የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች ‹‹ፍልሰታ›› እያሉ የሚጠሩት የአስራ ስድስት ቀን ፆም ዋዜማ ነው-ሐምሌ 30ቀን፡፡ ሻለቃው ይህች ቀን የመጨረሻዋ መሆኗን ሊያውቅ የሚችልበት አገጣሚ አልነበረምና ጥብቅ ሀይማኖተኛ በመሆኑ ለፆሙ የመንፍስና የቁስ
ዝግጅቱን አጠናቆ በደስታ እየጠበቀ ነው፡፡ የሆነው ግን በተቃራኒው ነበር፡፡ በፃሃፊ ብዕር ልተርክላችሁ፡፡
…ወቅቱ ክረምት ቢሆንም ፀሀይ ህቡዕ የገባች እስኪመስል ድረስ ዝናብን አግደው የያዙ የሰማይ መስኮቶች ከንጋት ጀምረው ላንቃቸውን ከፍተው ምድሪቱን እያረሰረሷት ነው፡፡ ቀኑ ተገባዶ አስር ሰዓት ላይ ደርሷል፡፡ አብዛኛው እስረኛ በየክፍሉ ከቷል፡፡ ጥቂቶቹ ደግሞ ውሽንፍሩን ተከትሎ ያረበበውን ቅዝቃዜ ይከላከልልናል በሚል ካፍቴሪያ ውስጥ ቁጭ ብለው ሻይና ቡና ደጋግመው ያዛሉ፡፡
አንዲት የደህንነት መኪና ሾፌሩን ጨምሮ አራት ሰዎች አሳፍራ ወደማረሚያ ቤቱ አስተዳደር መግባቷን ማንም አላስተዋለም፡፡ መኪናዋ የኃላፊውን ቢሮ ታካ ስትቆም የቡድኑ መሪ ቀልጠፍ ብሎ ወርዶ በቀጥታ ከፊቱ ወደአለው ቢሮ በመግባት፣ ከማረሚያ ቤቱ ኃላፊ ጋር ለጥቂት ደቂቃዎች ቆይታ ከአደረገ በኋላ በወህኒ ቤቱ ውስጥ ያልተለመደ ትዕዛዝ ተላለፈ፤ ሁሉም እስረኛ ወደ ክፍሉ እንዲገባ የሚል፡፡
እስረኞቹ በሙሉ ወደ ክፍላቸው መግባታቸው ከተረጋገጠ በኋላ የሞት ፍርድ ተፈርዶበት ቀኑን እየጠበቀ የነበረው ሻለቃ ፀሀዬ
ከክፍሉ ወጥቶከደህንነትቢሮወደመጣችውመኪናውስጥእንዲገባተደረገ፡፡መኪናዋምበመጣችበትፍጥነትየመልስጉዞአደረገች፡፡ ይህ ሁሉ ነገር ተካሄዶ ያለቀው በአስራ አምስት ደቂቃ ውስጥ ነበር፡፡
…ጎዳናው ላይ አልፎ አልፎ እየተንገዳገደ ከሚያዘግም ሰካራም እና ከሚያላዝኑ የመንገድ ዳር ውሾች በቀር አንዳች እንቅስቃሴ አይታይም፤ ጭር ብሏል፡፡ የክረምቱ ቅዝቃዜ በድቅድቅ ጨለማ ቁጥጥር ስር ከዋለው ሌሊት ጋር ተቀላቅሎ በእጅጉ ያስፈራል፡፡ የሻለቃው ባለቤት
ወ/ሮ አምሳለ የመኖሪያ ቤቷ በር ሲንኳኳ ከሶስት ልጆቿ ጋር በእንቅልፍ ዓለም ውስጥ ነበረች፡፡ ማንኳኳቱ ሳይቋረጥ ለደቂቃዎች በመቀጠሉ ድንገት ካሰጠማት እንቅልፍ አባነናት፡፡ እናም በሩን ከፈተች፡፡ ከዚህ ቀደም አይታቸው የማታውቃቸው ሁለት ሰዎች ቆመዋል፡ ፡ ደነገጠች፡፡
‹‹ምንድን ነው? ምን ፈልጋችሁ ነው?›› አከታትላ ጠየቀች፡፡
‹‹ፖሊሶች ነን፣ ሻለቃ ፀሀዬ በጣም ስለታመመ አምሳለን ጥሩልኝ ስላለን ነው የመጣነው›› ሲል መለሰ አንደኛው ሰውዬ፡፡ ‹‹ቀን ስንቅ ስወስድለት ደህና አልነበረ እንዴ? አሁን ምን ተፈጠረ?››
‹‹ድንገት ነው የታመመው፤ ልታዪው የምትፈልጊ ከሆነ ቶሎ እንሂድ?›› አለና አጣደፋት በሌሊት ከሰው ደጅ ቆሞ መመላለሱ ያልተመቸው ሁለተኛው ሰው፡፡ ወ/ሮ አምሳለም ስጋት እንደሞላት ሰዎቹን አሳፍራ በመጣችው መኪና ውስጥ ገብች፡፡ ሆኖም መኪናዋ ወደመጣችበት መመለሰ ስትጀምር መንገዱ ወደቃሊቲ የሚወስደው እንዳልሆነ ተረዳች፡፡ ከሃያ ደቂቃ ጉዞ በኋላም መኪናዋ አንድ ግቢ ውስጥ ገብታ ቆመች፡፡ ሁሉም ወረዱ፡፡
‹‹የታለ ባለቤቴ?›› አምሳለ ጠየቀች፣
‹‹ያው! እዛ ክፍል ውስጥ ግቢ፣ እየጠበቀሽ ነው›› አላት አንደኛው ሰው፣ በሩ ወደተከፈተ ክፍል በእጁ እያመለከተ፡፡
እንደተባለችው ገርበብ የተደረገውን በር ሙሉ በሙሉ ከፍታ ገባች፡፡ …ክፍሉ ወለል መሀል ላይ ሻለቃው በጥይት ተበሳስቶ በጀርባው ተዘርሯል፡፡ …ያልጠበቀችውን ክስተት የተመለከተችው የሻለቃው ባለቤት እንደሎጥ ሚስት የጨው አምድ ሆነች፡፡ …የዚህን ያህል ነው የህወሓት ጭካኔ፡፡ ከመስመሩ ካፈነገጣችሁ ትግሬ ሆናችሁ አማራ ጉዳዩ አይደለም፡፡ እናም ማቆሚያ ላጣው የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች መፈናቀልም ብቸኛው ተጠያቂ ህወሓት እንጂ ‹‹ወከልኩት›› የሚለው ህዝብ በፍፁም ሊሆን አይችልም፡፡ ይህ አመለካከት የተሳሳተ ከመሆኑም በላይ የማይታረም አደጋ ያስከትላል፡፡
የሆነ ሆኖ እንዲህ አይነቱን አጓጉል ችግር ፈጣሪ ድርጊት ሁላችንም በጋራ ለማስቆም መሰለፍ አለብን፡፡ በይበልጥ ደግሞ ከሀገሪቱ የተለያዩ አካባባዎች መጥታችሁ፣ የተለያየ አካባቢ ሰፍራችሁ ሀብት እያፈራችሁ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን ነጋዴዎች ይህ አይነቱ ማፈናቀል ባስቸኳይ ይቆም ዘንድ ነግ በእኔ ብላችሁ ስርዓቱ ላይ ጫና ማሳደር አለባችሁ፡፡ ቀጣዩ ተረኛ እናንተ ላለመሆናችሁ ምንም ማረጋገጫ የለም፡፡
የስርዓቱ ደጋፊዎችም ሆናችሁ ልሂቃኖች፣ በአሰልቺ ዜማ ጠዋትና ማታ ‹‹አባይ፣ አባይ…›› የምትሉ አርቲስቶች ከምንም በፊት ስለንፁሀን እምባመገደብልትናገሩይገባል፡፡አገዛዙየዱርዬባህሪውንይገድብዘንድስትዘምሩመስማትእንፈልጋለን፡፡ …እስቲዙሪያችንን እንመልከት፤ ትላንት ከኋላችው ቆምን ነፃ ያወጣናቸው ሀገራት ዛሬ የብሄር ፖለቲካን ለእኛ ጥለውልን ርቀው ሄደዋል፡፡ በዘላቂነት አብሮን ለማይቆይና ጠብ ለማይል ነገር እንማስናለን፡፡ እናቴም እንዲሁ ነበር ያለችኝ ‹‹ችክ አትበል! ጠብ ለማይል ነገር!›› ሆኖም ግሳጼዋን ችላ ብዬ ለምን እንደደወለችልኝ ጠየኳት፡፡
‹‹ትላንት ለምን ወደ ቤት አልመጣህም?›› ‹‹ምነው ፈልገሽኝ ነበር እንዴ?››
‹‹አዎ! የአባትህ 13ኛ ሙት ዓመት ነበር እኮ›› …ደነገጥኩ፡፡ ጊዜው እንዴት ይሮጣል? ግና በለሆሳስ ‹‹አባቴ ሆይ ነፍስህ በአፀደ ገነት እንዳለችአምናለሁ!›› ስልእናቴማነብነቤንሰምታኝኖሮምንእንዳልኩጠየቀችኝ፡፡
‹‹አይ! ምንም አላልኩም››
‹‹ለማንኛውም ዛሬ ወደ ቤት እንድትመጣ?››
‹‹እናቴ! ቢሮ ስለማመሽ ልመጣ አልችልም፤ ራሴ ቤት ነው የማድረው›› ‹‹እረስተከዋል እንዴ! ዛሬ እኮ መጋቢት ሀያ ሰባት ነው››
‹‹እና ታዲያ?››
‹‹የተወለድክበት ቀን ነዋ!›› …ሌላ የተረሳ ጉዳይ፡፡ ይህ ሳምንት ድብልቅልቅ ያለ ነው፡፡ የአባቴ 13ኛ ሙት ዓመት፣ የልደት ቀን፣ ሽልማት (በነገራችን ላይ ‹‹ኢትዮቲዩብ›› ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን ለማስከበር አስተዋፆ አድርገሀል በማለት የሸለመው እኔን ብቻ ሳይሆን ባልደረቦቼንና አንባብያንንም ጭምር በመሆኑ በሁሉም ስም እንዲህ ማመስገኑ አስፈላጊ ሆኖ አግኝቸዋለው፡- ‹‹እንዳከበራችሁን እግዚአብሄር ያክብርልን፤ መጪውም ከዚህ የበለጠ ስራ የምትሰሩበት የስኬት ዘመን ይሆንላችሁ ዘንድ እመኛለሁ››)
ይህንን ርዕሰ ጉዳይ ከማሳረጌ በፊት መልዕክቴን ላስተላልፍ፡-
አሁንም ትግሉ ይቀጥላል፡፡ ‹‹ልዕልና›› ብትዘጋም ሌላ ይከፈታል፡፡ ትግል… ሽንፈት፤ …ድል፤ እንደገና መሸነፍ… ተስፋ አንቆረጥም፤ ገና ወደፊት እንቀጥላለን፤ በዘመናችን ብዙ ነገር አይተናል፤ ርዕዮተ-ዓለም ሲሸነፍ ተመልከተናል፤ ስርዓት ድል ሲመታ አይተናል፤ ህዝብ እንደ ህዝብ ሲሸነፍ ግን ማንም ተመልክቶ አያውቅም፡፡ እናም እኔ ጋዜጠኛ ነኝ ‹‹ለዲሞክራሲና መልካም አስተዳደር ፀልዩ›› ብዬ ልመክር አልችልም፡፡ ነገር ግን እልፍ ሆነን እንዘምር ዘንድ ድምፄን ከፍ አድርጌ እጠይቃለሁ፡-
አትነሳም ወይ? አትነሳም ወይ?
ይሄ ባንዲራ የአንተ አይደለም ወይ?
…ኢ-ፍታሀዊነትን እንዋጋለን፣ የከፋፍለህ ግዛን አስተዳደር እንቀይራለን፡፡ በሩንም በሰላም ይከፍቱልን ዘንድ ደጋግመን እናንኳኳለን፤ ካልከፈቱልንም ገንጥለን እንገባለን፡፡ ከዛ በኋላም ሀገራችንን የራሳችን እናደርጋለን! ያዘኑትም ይስቃሉ፤ የታሰሩትም ይፈታሉ፤ የተሰደዱትም ይመለሳሉ፤ የወጡትም ይወርዳሉ፡፡
(መጋቢት 27/2005 ዓ.ም እኩለ ሌሊት)

በጀሞ የጋራ መኖርያ መንደር አንድ ኮንዶሚኒየም ለመፍረስ እያዘነበለ ነው










ባለሙያዎች አስተዳደሩን ተጠያቂ ያደርጋሉ
• አስተዳደሩ ነዋሪዎችን አስወጥቷል
• አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መንስዔውን እንዲያጠና ተጠይቋል
በአዲስ አበባ አስተዳደር የቤቶች ልማት ፕሮጀክት የተገነባው የከተማዋ ትልቁ የጋራ መኖርያ መንደር በሆነው ጀሞ መንደር ውስጥ ጥቅም ላይ የዋለ አንድ ኮንዶሚኒየም ለመደርመስ ወደኋላ እያዘነበለ ነው፡፡
የዝግጅት ክፍላችን በደረሰው ጥቆማ መሠረት የተባለውን ሕንፃ በመመልከት በግንባታው ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎችን ማብራሪያ ጠይቋል፡፡ የጀሞ የጋራ መኖርያ መንደር በ1.3 ቢሊዮን ብር የተገነባ ሲሆን፣ 10 ሺሕ የተለያዩ መጠንና ክፍሎች ያላቸው ቤቶች የሚገኙበት፣ እንዲሁም 50 ሺሕ ያህል ነዋሪዎችን የሚያስጠልል ነው፡፡ በዚህ ጀሞ ቁጥር አንድ ተብሎ በተሰየመው መንደር ውስጥ ብሎክ ቁጥር 220 የጋራ ሕንፃ ግን ከሌሎቹ በአካባቢው ከተገነቡ ቤቶች ተለይቶ ለመውደቅ በማዘንበል ላይ ይገኛል፡፡
ዕጣ ደርሷቸው የሕንፃው ባለቤት የሆኑ ነዋሪዎች በሕንፃው የውስጥ ክፍሎች ያስተዋሉትን መሰነጣጠቅና አጠቃላይ የሕንፃውን ወደ አንድ ጐን መስመጥና ማጋደል አሳስቧቸው ቤቱን ላስተላለፈላቸው የከተማዋ አስተዳደር አሳውቀዋል፡፡ የአስተዳደሩ የሥራ ኃላፊዎችም አካባቢውን በመጐብኘት የነዋሪዎችን ሥጋት የተቀበሉ መሆናቸውንና በዚህ ሳምንት ውስጥም ለሁሉም ተለዋጭ ቤት እንዲሰጣቸው መወሰኑን አረጋግጠናል፡፡ የችግሩ መንስዔ፣ ተጠያቂውስ ማን ሊሆን ይችላል? መፍትሔውስ? በሚሉ ጥያቄዎች ዙሪያ ማብራሪያ እንዲሰጡን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ካሳ ወልደ ሰንበትን ብንጠይቅም፣ በአሁኑ ወቅት ይህንን መመለስ እንደማይቻል ገልጸዋል፡፡ ለዚህ የሚሰጡት ምክንያት የችግሩ መንስዔ ገና ያልተጠና መሆኑን ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ነዋሪዎቹ እንዲለቁ የተደረገ መሆኑን፣ ከዚህ በመቀጠል ደግሞ ጥናቱ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንደሚከናወን የገለጹት አቶ ካሳ፣ ኮንዶሚኒየሙን በተመለከተ ዝርዝር ጉዳዮችን መናገር የሚቻለው ከጥናቱ በኋላ ነው ብለዋል፡፡
የዝግጅት ክፍላችን ግን በግንባታና ተያያዥነት ባላቸው የሥራ ዘርፎች ላይ ባለሙያ የሆኑና በዚህ መንደር የቅድመ ግንባታ ጥናቶች ላይ የተሳተፉ ባለሙያዎችን አነጋግሯል፡፡ ሁሉም ማለት በሚቻል ደረጃ የችግሩ መንስዔ የአስተዳደሩ የቁጥጥር ቸልተኝነት ሊሆን እንደሚችል ይስማማሉ፡፡ ሰሞኑን ‹‹የከተማ ሕዝቦች አገልግሎት በኢትዮጵያ›› በሚል በተዘጋጀ መድረክ ላይ ጥናታቸውን ያቀረቡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ አርክቴክት፣ የሕንፃ ግንባታና የከተማ ልማት ኢንስቲትዩት የኢኮ ሲስተም ዕቅድና ማኔጅመንት ኃላፊ ዶክተር ቁምላቸው የሺጥላ ስለጀሞ የጋራ መንደር ሙያዊ ሂሳቸውን አቅርበው ነበር፡፡ ዶ/ር የሺጥላ እንደሚሉት፣ ጀሞ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን መሠረት ለከተማ ግብርና እንዲሆን የተከለለና ለግብርና ምቹ የሆነ የከርሰ ምድር ውኃ ያዘለ አካባቢ ነው፡፡ ይሁን እንጂ የአዲስ አበባ አስተዳደር ከማስተር ፕላኑ ውጭ ለጋራ መኖርያ ቤቶች ግንባታ እንዳዋለው ተናግረዋል፡፡
ከዶ/ር የሺጥላ ጥናት መረዳት የሚቻለው፣ አስተዳደሩ ከማስተር ፕላኑ ውጭ ለመኖርያ ቤቶች ግንባታ አካባቢውን ሲመርጠው የከርሰ ምድር ውኃ ያዘለና ለግንባታ ምቹ ያልሆኑ ጥቁር አፈር ያለበት አካባቢ መሆኑን እየተረዳ እንደሆነ ነው፡፡
በሥፍራው ተገኝተው የተባለውን ሕንፃ በመጐብኘት አስተያየታቸውን የሰጡ ባለሙያዎችም ግንባታው ከመካሄዱ በፊት ጥቁር አፈሩ ሙሉ ለሙሉ መውጣት እንዳለበት ይናገራሉ፡፡ ጥቁር አፈር ከወጣ በኋላም ቢሆን በሌላ የግንባታ አፈር መሞላት እንደሚገባው ያስረዳሉ፡፡ በአካባቢው የሚገኘው የከርሰ ምድር ውኃም በክረምት ወቅት የበለጠ የሚሞላ በመሆኑ ይህንን ያገናዘበ ግንባታ ማካሄድ የአካባቢው ነባራዊ ሁኔታ ይጠይቃል ብለዋል፡፡
በጀሞ መንደር ግንባታ ከመካሄዱ በፊት በአስተዳደሩ ተቀጥረው የጂኦቴክኒካል ጥናት ላይ ከተሳተፉ ድርጅቶች መካከል ማንነቱ እንዳይጠቀስ የጠየቀ አንድ የግል ድርጅት በበኩሉ፣ በተደረገው ጥናት መሠረት የግንባታ ሥራውን ለማካሄድ ለአስተዳደሩ የመፍትሔ ሐሳቦችን እንዳቀረበ ይህም ከሌሎቹ ድርጅቶች ጋር ተመሳሳይ ሊሆን እንደሚችል ገልጿል፡፡ ነገር ግን የተጠቆሙትን የመፍትሔ ሐሳቦች ለመተግበር እንዲሁም ተጨማሪ ጥናት ለማካሄድ አስተዳደሩ የመደበው በጀት አነስተኛ በመሆኑ ተግባራዊ ለማድረግ ሊቸገር እንደሚችል ድርጅቱ አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡ አንዳንድ ድርጅቶች የተከፈላቸው ገንዘብ አነስተኛ እንደነበር በዚህም ሳቢያ ሙሉ ጥናት ማከናወን እንዳልቻሉ በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ በማስታወስ ገልጸዋል፡፡
ግንባታውን የፈጸመው ኮንትራክተርን የሚቆጣጠረው አማካሪ ድርጅትም በቁጥጥር ወቅት ቸልተኝነት አሳይቶ ሊሆን ስለሚችል አስተዳደሩ አማካሪ ድርጅቱ ያሳለፋቸውን የግንባታ ውሳኔዎች ወደኋላ ተመልሶ ሊመረምር ይገባል ብለዋል፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚደረገው ጥናት ከተጠቀሰው ሕንፃ ውጭ በአጠቃላይ በመንደሩ ላይ ሊያተኩር ይገባል ሲሉም ይመክራሉ፡፡ http://www.ethiopianreporter.com/

ዓርብ 5 ኤፕሪል 2013

በአዲስ አበባ የሚኖሩ ነዋሪዎች ቤቶቻችን ሆን ተብሎ በመንግስት ሰዎች እየተቃጠሉብን ነው አሉ

በአዲስ አበባ የሚኖሩ ነዋሪዎች ቤቶቻችን ሆን ተብሎ በመንግስት ሰዎች እየተቃጠሉብን ነው አሉ
መጋቢት ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ በትናንትናው እለት ብቻ ሁለት ቦታዎች ላይ በተመሳሳይ ሰአት ቃጠሎ የደረሰ ሲሆን፣ ድርጊቱ ያበሳጫቸው ወጣቶች ከፌደራል ፖሊስ አባላት ጋር መጋጨታቸውን የአይን እማኞች ተናግረዋል።
የመጀመሪያው የእሳት አደጋ የደረሰው በአባኮራን ሰፈር ፋሲል ሆቴል አጠገብ ከቀኑ 5፡10 ሲሆን፣ ቃጠሎውም እሰከ 7፡30 ድረስ መቆየቱ ታውቋል። አንድ ሰው ጭንቃላቱ አካባቢ ቃጠሎ ሲደርስበት ሌላ አንዲት ወጣት ደግሞ ሰውነቷ ተቃጥሎአል። ከ40 በላይ ቤቶች እና ብዙ ንብረትም መውደሙን የአይን እማኞች ገልጸዋል።
የእሳት አደጋ መኪኖች ከ45 ደቂቃ በሁዋላ የደረሱ ሲሆን፣ ከቦታው ከደረሱም በሁዋላ ውሀ የለንም በማለታቸው ከአካባቢው ወጣቶች ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞአቸዋል። ከወጣቶች ጋር በተፈጠረ ግጭት አንድ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ መኪና በድንጋይ የተሰበረ ሲሆን፣ የመኪናው ሾፌርም ተደብድቧል። የፌደራል ፖሊስ ወደ አካባቢው በመድረስ በወጣቶች ላይ ድብደባ የፈጸመ ሲሆን፣ 3 ሰዎችም ተይዘው ታስረዋል። አንድ የእሳት አደጋ ሰራተኛ ነፍስ ማዳኑን ትቶ ፣ ገንዘብ ሲሰበስብ እጅ ከፍንጅ መያዙም ታውቋል። የአካባቢው ሰዎች ቤታቸውን ያቃጠለባቸው መንግስት መሆኑን ይናገራሉ።
በዚሁ እለት በተመሳሳይ ሰአት አውቶቡስ ተራ አካባቢ 32 ቀበሌ ላይ የሚገኙ ቤቶች ለሁለተኛ ጊዜ ተቃጥለዋል። በዚህ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ነዋሪዎች ቀደም ብሎ አካባቢውን እንዲለቁ ተነግሮአቸው የነበረ ቢሆንም ነዋሪዎቹ ለመልቀቅ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተው ነበር። ከሁለት ሳምንት በፊት በዚህ አካባቢ በደረሰው የእሳት አደጋ 11 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል። የመንግስት መገናኛ ብዙሀን የሟቾች ቁጥር 8 መሆኑን መዘገባቸው ይታወሳል። ትናንት በተነሳው ቃጠሎ ጊዚያዊ መጠለያ በመስራት ተጠልለው የነበሩት ሰዎች መጠለያቸው ሙሉ በሙሉ እንደወደመባቸው ታውቋል።
ነዋሪዎች መንግስት ተለዋጭ ቤት ሳይሰጠን ቤታችንን ለቀን አንወጣም በማለት ለረጅም ጊዜ ሲያንገራግሩ ቆይተዋል።

ሐሙስ 4 ኤፕሪል 2013

ሳውዲያ ውስጥ ያሉ ወገን ስደተኞች ተረጋግተው መኖር አልቻሉም ::በርሜል ውስጥ ተደበቀው ሆኖም አልቀረለትም ይዘውታል.


ሳውዲያ ውስጥ ያሉ ወገን ስደተኞች ተረጋግተው መኖር አልቻሉም ::በየለቱ የሚደረገው አፈሳ ፥ቤት ሰበራ ድብደባ የሚያበቃም አይመስልም :: የኢትዮጵያ ዜጋ የሆነ ሁሉ ወረቀት አለው የለውም ብለው ማጣራት እንኳን የለም ያለ አግባብ ይደበደባሉ ፥ ይታሰራሉ ፥ ይንግላታሉ::
ይህን ምስል የምትመለከቱት ቤት ውስጥ ሰብረው በመግባት ሲፈትሹ ከሚመቱኝ ከምታሰር በማለት በርሜል ውስጥ እንደተደበቀ ነው:: ሆኖም አልቀረለትም ይዘውታል ::በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ ከመያዙ የሚፋጸመው ድብዳባ ነው::ኤንባሲ ተብዬዎች ግን የት ነው ያላችሁት::ማንን ለማገልገል ነው ወንበር ላይ የተዘረፈጣችሁት?ወይ ዝጉትና ኤንባሲ ስለሌላቸው ነው ይህ በደል የሚፈጸምባቸው ብለው ሌሎች የሰው ልጅ መብት ተቆርቋሪ ከጎናችን ቢቆሙ ለራስ ጥቅም ብቻ ማጎብደድ ብታቆሙ መልካም ነው::

በሰፈሩት ልክ መሰፈር አይቀርም::

ብአዴን የት ናት…?

ባለፈው ሰሞን ከደቡብ ክልል ጉራ ፈርዳ "አማሮች ስለሆናችሁ ወደ ሀገራችሁ ሂዱ" ተብለው ሲፈናቀሉ የነበሩ ዜጎች ጉዳይ ምን እንደደረሰ ምንም የረባ ነገር ሳንሰማ ይሄው ዛሬ ደግሞ ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል "አማሮች ውጡ" ተባሉ ሲባል እየሰማን ነው፡፡ የአሁኑ ይባስ እንዲሉ፤ የአሁኑ ደግሞ ጭራሽ ተፈናቃዮቹ ሲጓዙበት የነበረው መኪና አደጋ ደርሶበት ስደተኞቹ በሙሉ ህይወታቸው ተቀጥፏል፡፡ 

በየአመቱ ህዳር አስራ አንድ ልደቷት የምታከብር አማራውን እወክላለሁ የምትል ብአዴን የተባለች ፓርቲ አለች፡፡ 
ብአዴንን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርች አንዱ የሆኑት አቶ ደመቀ መኮንን ይመሯታል፡፡ በስራቸውም በርካታ አንጋፋ ታጋዮች ይገኛሉ፡፡ አቶ አያሌው ጎበዜም አቶ አዲሱ ለገሰም አንዱ እና ሁለቱ ናቸው፡፡ ሌሎችም ብዙ አበል የሚበሉ አባሎች አሏት… ብአደዴን!

እንግዲህ በተደጋጋሚ የክልሉ ተወላጆች በዘራቸው የተነሳ ወደ ሀገራችሁ ሂዱ እየተባሉ ከተለያዩ ክልሎች ሲባረሩ ብአዴን ምን እያደረገች ነው… መቼም ወግ ነውና ልጠይቅ ብዬ ነው አንጂ… ብአዴንም ሆነች መላዋ የትዳር አቻዎቿ በጥቅሉ እነ ኢህአዴግ ጥያቄ ለመመለስ ጊዜ ያላቸው አይመስሉም፡፡ አነርሱቴ፤ ርስ በርስ ተቃቅፈው የሞቀ ፍቅር እየሰሩ ነው፡፡

ሳስባት ብአዴን የኢህአዴግ ፍቅር አለቅጥ አስክሯታል፡፡ "በልጆቿ" ላይ የሚያደርሰው መከራም ከነጭርሹ ሊታያት አልቻለችም፡፡ ፍቅር እውር ነው ብቻ ሳሆን እውርም ያደርጋልና እነሆ ብአዴን ልጆቿን ረስታለች፡፡ የት እንደሆኑ ምን እንደሆኑም አልሰማችም፤ አላየችምም፡፡

ብትሰማም ጆሮ ዳባ ብላለች፡፡ ብታም አይኔን ግንባር ያድርገው ብላለች፡፡

ጥያቄዬ አጭር ናት፤ ብአዴን የት ናት…!? ብኤዴን የማናት…!? ለመሆኑ ደህና ናት…!? ስራዋስ ምን ይሆን…!?
ብአዴን ሆይ ልደት ማክበር፤ መጨፈር እና ከጎረምሳው ኢህአዴግ ጋር ሲቃበጡ ማደር… በቃ ይሄው ነው ያንቺ ሞያ…!? እባክሽ ተንፍሺ…!

እንበል ይሆን… !?


Source:Abe Tokichaw

ሰኞ 1 ኤፕሪል 2013

ኩዌት ከኢትዮጵያ የሚመጡ ሠራተኞችን አልቀበልም አለች


ኩዌት በቅርቡ የሕክምና ምርመራ እንዲከናውኑ ተብለው በተመለመሉ አዳዲስ ክሊኒኮች አማካይነት አልፈው የሚመጡ ኢትዮጵያዊያን ሠራተኞችን ወደ አገሯ እንደማታስገባ አስታወቀች፡፡
በአዲስ አበባ የሚገኘው የኩዌት ኤምባሲ መጋቢት 11 ቀን 2005 ዓ.ም. በጻፈው ደብዳቤ፣ ኩዌት ወደ ባህረ ሰላጤው አገሮች የሚሄዱ ሠራተኞች የጤና ምርመራ እንዲያደርጉ በቅርቡ ለተመለመሉ አዳዲስ ክሊኒኮች ዕውቅና አልሰጠችም፡፡
ኩዌት ኤምባሲ በዚሁ ደብዳቤው እንደገለጸው፣ ራሱ ሌላ ማረጋገጫ ደብዳቤ እስካልጻፈ ድረስ የክሊኒኮችን ሥራ የሚያስተባብረው ጋምካ የተባለው አስተባባሪ ተቋም አንድም ተመርማሪ ሠራተኛ በቅርቡ ምርመራ እንዲያካሂዱ ወደተመደቡ የጤና ማዕከላት እንዳይልክ አሳስቧል፡፡
የባህረ ሰላጤው አገሮች ማኅበራት (Gulf Cooperative Council) አባላት ሳውዲ ዓረብያ፣ ኩዌት፣ ኦማን፣ ባህሬን፣ ኳታር፣ የመንና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስን የሚያጠቃልል ሲሆን፣ የእነዚህ አገሮች የጤና ሚኒስትሮች በበኩላቸው የራሳቸውን ማኅበር አቋቁመው በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡
የጤና ሚኒስትሮቹ ማኅበሩ ባለሙያዎችን ወደ አዲስ አበባ በመላክ በከተማው ውስጥ የሚገኙትን ክሊኒኮች ከገመገመ በኋላ አልአፍያ ከፍተኛ ክሊኒኮች፣ አልያንስ ሜዲካል ክሊኒክ፣ ቶዝ ከፍተኛ ክሊኒክ፣ ወሰን ከፍተኛ ክሊኒክ፣ ቤተዛታ ከፍተኛ ክሊኒክ፣ ኦአይሲሶ ስፔሻላይዝድ ክሊኒክ፣ ሜዲገልፍ የጤና አገልግሎትን የመረጠ ሲሆን፣ ኩዌት ለጊዜው በእነዚህ ክሊኒኮች ተመርምረው የሚመጡ ሠራተኞችን እንደማትቀበል ገልጻለች፡፡
ከዚህ በፊት በጤና ሚኒስትሮቹ ተመርጠው ከግንቦት 2000 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ባህረ ሰላጤ አገሮች ለሥራ የሚሄዱ ሠራተኞች ጤና ለመመርመር አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩት አርሾ ሜዲካል ላቦራቶሪ፣ ቢታንያ ከፍተኛ ክሊኒክ፣ ሃሌሉያ ከፍተኛ ክሊኒክ፣ ኬቲ ቅዱስ ገብርኤል ከፍተኛ ክሊኒክ፣ ሰንቴ ከፍተኛ ክሊኒክ፣ ዘንባባ ከፍተኛ ክሊኒክ፣ ዛክ ከፍተኛ ክሊኒክና ሳይመን ከፍተኛ ክሊኒክ ነበሩ፡፡

ተማሪዎች ብሪትሽ ካውንስልና መንግሥትን ለመክሰስ ዝግጅት እያደረጉ ነው


ከእንግሊዙ ካምብሪጅ ኮሌጅ ዲግሪ ለማግኘት በማሰብ በአገር ውስጥ በትብብር ሥልጠናውን ይሰጥ ከነበረ ተቋም የተልኮ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩና የተመረቁ መንግሥትን ጨምሮ፣ ተቋሙንና የብሪትሽን ካውንስልን ፍርድ ቤት ለማቆም እየተዘጋጁ መሆናቸውን አስታወቁ፡፡
ዘመን ዲቨሎፕመንት ኤንድ ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት የተሰኘው የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በድንበር ዘለል ትምህርትና ሥልጠና ዘርፍ ዕውቅና ተሰጥቶት፣ 400 ያህል ተማሪዎችን ሲያስተምር ቆይቷል፡፡ ሆኖም ካለፈው ታኅሳስ ወር 2005 ጀምሮ ዕውቅናው መሰረዙን የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡ ለዚህ ውሳኔው ኤጀንሲው ምክንያት ያደረገው ከካምብሪጅ ኢንተርናሽናል ተሰጥቶኛል ያለውን የታደሰ የዕውቅና ማረጋገጫ፣ ዘመን ኢንስቲትዩት እንዲያቀርብለት ቢጠይቅም ሊቀርብለት ባለመቻሉ እንደሆነ አስታውቆ ነበር፡፡
ይሁንና ይህንን ውሳኔ በመቃወም ለትምህርት ሚኒስቴር ደብዳቤ ቢጽፍም ትምህርት ሚኒስቴር ግን የኤጀንሲው ውሳኔ እንዲፀና በማድረግ የትምህርት ተቋሙ የተጠየቀውን ዕውቅና እንዲያመጣ አሳስቧል፡፡ ይልቁንም ካምብሪጅ ኮሌጅ በእንግሊዝ አገር በማስትሬት ዲግሪ መርሐ ግብሮች ሥልጠና ለመስጠት ዕውቅና የተሰጠው ነው በማለት ምስክርነቱ ሰጥቶ የነበረው ብሪቲሽ ካውንስል ሁለት ጊዜ መሰል ማረጋገጫ መስጠቱ ስህተት እንደሆነ በመግለጽ ይቅርታ መጠየቁን የተገነዘበው ትምህርት ሚኒስቴር፣ ተቋሙ በድንበር ዘለል ትምህርት ዘርፍ ሥልጠና እንዳይሰጥ ብቻ ሳይሆን መዝግቦ ሲያስተምራቸው የነበሩትንም ተማሪዎች ተመጣጣኝ ወደሆኑ ሌሎች ተቋማት እንዲያዛውር፣ በትምህርት ጥራትና አግባብነት ኤጀንሲ የተወሰነበትን ውሳኔ አጠናክሮበታል፡፡ ከዚህም ባሻገር ኤጀንሲው ከዚህ ቀደም በዘመን ኢንስቲትዩት ለተመረቁ ተማሪዎች ዕውቅና እንደሚሰጥ አስታውቋል፡፡
እንዲዘጋ የተወሰነበት ዘመን ኢንስቲትዩት በምትኩ ብሪቲሽ ስኩል ኦፍ ቢዝነስ ኤንድ ፋይናንስ ከተባለ ተቋም ጋር የመግባቢያ ስምምነት መፈረሙን በማስታወቅ፣ ወደሌላ ተቋም እንዲያዛውራቸው የተባሉትን ተማሪዎች በዚህ ተቋም ዕውቅና በሚሰጠው አኳኋን ለማስተማር እንዲፈቀድለት ጠይቆም ውድቅ ተደርጎበታል፡፡
እነዚህን ውሳኔዎችና ሒደቶች ሲከታተሉ የቆዩት ተማሪዎች ግን ዕውቅና ከሌለው ተቋም ለተገኘ ዲግሪ ዕውቅና ይሰጠዋል በማለቱና በአግባቡ ዕውቅናውን ሳያጣራ የድንበር ዘለል ሥልጠና እንዲሰጥ ለዘመን ኢንስቲትዩት ዕውቅና በመስጠቱ ጭምር ኤጀንሲው መከሰስ እንደሚገባው በመመካከር ላይ ይገኛሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ዘመን ኢንስቲትዩት ላደረሰባቸው የጊዜ፣ የገንዘብና የሞራል ኪሳራ በፍርድ ቤት እንደሚጠይቁ መወሰናቸው ሲታወቅ፣ ብሪቲሽ ካውንስልም ዕውቅና የሌለውን ተቋም ዕውቅና እንዳለው በማስመሰል ማረጋገጫ መስጠቱ፣ ለተፈጠረው ችግር ተጠያቂ እንደሚሆን ከተማሪዎቹ መካከል ሪፖርተር ያነጋገራቸውና ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ ተማሪዎች ተናግረዋል፡፡
ወደሌሎች የትምህርት ተቋማት እንዲዛወሩ የተባሉት ተማሪዎች በማስተር ኦፍ ቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን እንዲሁም በፕሮጀክት ማኔጅመንት በማስተር ኦፍ አርትስ ዲግሪ ደረጃ ትምህርታቸውን ለመከታተል የተመዘገቡ በመሆናቸው፣ በእነዚህ ዘርፎች ውስጥ ከሚሰጡት ጥቂቱ ብቻ በሁለቱ ተቋማት እንደሚሰጡ በማረጋገጣቸው ችግር ውስጥ መውደቃቸውን ይገልጻሉ፡፡ አንዳንዶቹም ከሁለቱ ተቋማት የሚገኘውን ዲግሪ ለማግኘት ሳይሆን ዓለም አቀፍ ዲግሪ ለማግኘት ብለው ከፍተኛ ወጪ በማውጣት ሲማሩ እንደቆዩም አስታውቀዋል፡፡ ከዚህ ይልቅ መንግሥት እዚህ አገር በመስጠት ላይ ካሉ የአሜሪካ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ሊያስቀጥልላቸው ይገባ እንደነበር በመግለጽ ይወቅሳሉ፡፡
ethiopian reporter

እጅግ አስደንጋጭ ቭዲዮኢትዮጵያውያን በመደበኛነት ከቆሻሻ ገንዳ የተደፉ ምግቦችን በመሰብሰብ ይመገባሉ::


እጅግ አስደንጋጭ ቭዲዮኢትዮጵያውያን በመደበኛነት ከቆሻሻ ገንዳ የተደፉ ምግቦችን በመሰብሰብ ይመገባሉ::



ከ100.000 በላይ ኢትዮጵያውያን በመደበኛነት ከቆሻሻ ገንዳ የተደፉ ምግቦችን በመሰብሰብ ይመገባሉ::ይህ የሚያሳየው ሃገራችንን የሚያስተዳድረው የወያኔ ጁንታ 11% እድገት አለ እያለ ቢሆንም ዉሸት መሆኑን ነው ::ወያኔ እየደረሰበት እያለው ኪሳራ መውድቂያው በመሆኑ ህዝቡን ለከፋ ችግር ዳርጎታል::https://www.youtube.com/watch?feature=player_embedded&v=MNY_7cUDHcU

አዲሱ የስም ማጥፋት ዘመቻ በሎሚ መፅሔተ በልዕልና አዘጋጆች ላይ



መጀመሪያም በፍትህ አዘጋጀች ከዛም በአዲስ ታይምስ መታተም ከጀመረች ጀምሮ በስርአቱ ሎሌዎች ፍትህን ለማዘጋት ያልፈነቀሉት ድንጋይ አልነበረም ከዚህም ውስጥ የአዲስ ዘመን ገፅ 3፣ አይጋ ፎረም፣ዋልታ ፣ እንዲሁም በተረጴዛዋ ሟርተኛ ሚሚ ስብሃቱ የሚመራው ዛሚ ፌፍ ኤም ከነዚህ ውስጥ ይገኛሉ፡፡የሚገርመው የአሁኑ ዘመቻ ከበፊቱ ለየት ያለ መሆኑን ፍንጭ የደረሳቸው የልዕልና አዘጋጀች በልዕልና ጋዜጣ ቅፅ 1 ቁጥር 4 አርብ መጋቢት 13 2005 ባወጡት ፅሁፍ እንዲህ ብለው ነበር‹‹ከዚህ ቀደም ከተለመደው የመፈረጅ ፣ የማስፈራራት ፣ የማጥላላት ፣የማንኳሰስ ዘመቻ ይህንን ለየት የሚያደርገው እንደዚህ ቀደሙ በአዲስ ዘመን፣ በአይጋ ፎረም፣እና ዛሚ ሬዲዮ ጣቢያ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን ፤ በአዲሱ ዘመቻ በ‹‹ግል(ነፃ)›› ስም የሚታተሙ መፅሔቶችንም በተባባሪነት መጠቀምን የሚጨምር እንደሆነ የልዕልና ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡›› እያለ ይቀጥልና በመጨረሻም
‹‹ ልዕልና ነፃ ፕሬሱን ለማፈን ለሚደረገው ኢህአዴግ መራሹ ዘመቻ ‹‹ ነፃ ፕሬስ ››ን እንደ ሽፍን በመጠቀም መፅሔታቸውን በማከራየት የሚተባበሩትንም ሆነ በአዲስ ዘመን እና በአይጋ ፎረም ላይ በብዕር ስም ይህንኑ የአፈና ተግባር የሚፈፅሙትን እየተከታተለች ለአንባቢን ታቀርባለች ፡፡››
የሚገርመው ይህ ፅሁፍ በወጣ በነጋታው ቅዳሜ ነው ሎሚ መፅሔት ‹‹ለተመስገን ደሳለኝ የኢህአዴግ ማስተንፈሻ ማን ነው? በሚል ርዕስ አዲሱን ዘመቻ የጀመሩት ከዚህ ቀደም ካነበብኳቸው የዘለፋ ፅሁፎች የዚኛው በጣም ስልታዊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ ፡፡ ይህም የልዕልናን አዘጋጆች ከገዢው ፓርቲ ጋር እያገናኘ የፃፈው ነው፡፡;ይህን ማንም ሊጠረጥረው የማይችለው እና የተረጋገጠ እውነት የሆው ነገር አምባገነኑ ስርአት የነዚህን አይነት ጋዜጦች መኖር ከናካቴው አይፈልግም የልጁ መከራከሪያ ምን ያህል ዜሮ እንደሆነ የሚያረጋግጠው ጋዜጣው ብርሃንና ሰላምን በመሰሉ ማተሚያ ቤቶች በአነስተኛ ዋጋ ማሳተም እንዳይችሉ አድጎ በተለየ ይዘት እና በውድ ዋጋ እንዲያሳትሙ አስገድዷቸዋል፣ እንዲሁም 30 ሺህ ኮፒ ከታተመ ቦኋላ እንዳይወጣ አድርጎ አቃጥሎታል ፡፡ ይህም የሚያረጋግጠው ስርአቱ እንደ ፍትህ አይነት ጋዜጣዎችን መመልከት አለመፈለጉን ያሳያል፡፡ምንልክሳልሳዊ ብሎግ
ሌላው ደሞ እነእስክንድር ነጋ ጋዜጣ እንዳያወጡ ታግደው ፣የአወራምባ ታይምስ አዘጋጆች አውራምባ ታይመስ ከተዘጋች ቦኋላ ተሰብስበው ሄደው ሌላ ጋዜጣ ለማተም ሳይፈቀድላቸው ለነፍትህ አዘጋጆች ግን በየ 6 ወር በአዲስ ጋዜጣ የሚመላለሱት እነሱ ማን ሆነው ነው አይነት ከስርአቱ ጋር የማያያዝ ነገር ያንፀባርቃል ፡፡ ይህንን ማንም የሚያወቀው ሃቅ ይመስለኛል፡፡ እስክንድር ነጋ የታገደው ዛሬ አይደለም እሱምኖ ሆነ ባለቤቱ የታገዱት ምርጫ 97 ቦኋላ ነው እንጂ ዛሬ አይደለም ልጁም እንዲህ ማለቱ ለተነሳለት የቅጥፈት ተግባር ማለትም ከ97 ቦኋላ የተከፈቱትን አዲስ ነገር ፣ አውራምባ ታይምስ ፣ ፍትህ ፣ አዲስ ታይምስ እንዲሁም አሁን በነብስ ያለችውን ልዕልናን ገዢው ፓርቲ በማስተንፈሻነት እንደሚጠቀምባቸው ለመግለፅ ፈልጎ ነው ይህም የሎሌ እና የአድርባዮች ተላላኪ መሆኑን በደንብ የሚያሳይ ነው፡፡ ከዚህም ውስጥ 4ቱ በህትመት የሉም ታድያ እንዴት ሆነው ነው በህትመት ሳይኖሩ ማስተንፈሻ የሆኑት ደሞም እነዚህ ጋዜጦች በህትመቱ ለመዝለቅ የቻሉት ስርአቱን በማስገደድ ነው እንጂ ስርአቱ ፈልጎ እንዳልሆነ ሰይጣንም ያውቀዋል፡፡ 
ሌላው ደሞ ሌሎች ተከልክለው ፍትህ በአዲስ ታይመስ አሁንም በልዕልና ይመላለሳሉ የሚል ነው ፡፡ ይህም ቢሆን ምንም እውነትነት የሌለው ነው፡፡ ተመስገን ደሳለኝን ጨምሮ የፍትህ አዘጋጆች ፍትህ የሚሰደዱ እግሮች የሏትም ብለው በቁርጠኝነት መነሳታቸው ለስርአቱ አንንበረከክም ማለታቸውን የሚያሳይ ነው ፤ ይህም አንዱ በር ቢዘጋ በአንዱ መምጣታቸው ነገር ለፕሬሱ የሚያስብ ሰው ቢሆን በመልካም ጎኑ ሊያየው በተገባ ግን ምን ዋጋ አለው አቶ ታዲዮስ ታንቱ እንዳሉት አድርባይ እንዴት ሀገር ሊጠቅም ይችላል? ሲሉ የጠየቁት መጣልኝ እውነትዎን ነው አቶ ታድዮስ በምንም መንገድ አድርባይ አገር ሊጠቅም አይችልም ፡፡ ብሮድካስትም ሆነ አንባገነኑ መንግስት ለነሱ አዲስ የጋዜጣ ፍቃድ እንደማይሰጣቸው እርግጠኛ ስለሆኑ ወደህትመት ለመመለስ ሌላ አማራጭ መውሰድ ግድ ስለሆነባቸው ነው ከህትመት የወጡትን ጋዜጦችና መፅሔቶች እየገዙ ለመመለስ የተዘጋጁት ይህም እንደሚመስለለኝ በንግድ ህጉ መሰረት ባለቤትነትን ማዘዋወር በመሆኑ ለአፈና ብዙም ያልተመቸ በመሆኑ እንጂ ስርአቱ የነሱን መኖር ስለሚፈልግ አይደለም፡፡
ተመስገንን እና የልዕልና አዘጋጆችን እራሳቸውን እንደ እውነተኛ ሌላውን እንደሎሌ ያያሉ የሚል ነው፡፡ ይህ እኮ እሙን የሆነ ነገር ነው ለምሳሌ ሪፖርተር እና አዲስ አድማስ ጋዜጦች ከ 97 ሱናሚ አምልጠው አስራምናምን አመት መቆየታቸው በምን ምክንያት እደሆነ ሳያውቅ ነው እንግዲህ የፍትህ 4 አመት የአዲስ ታይምስ 6 ወር መቆት ያንገበገበው ይህ ደሞ ግልፅ ነው በ2004 መጨረሻ ፍትህ የጠቅላዩን ሞት ይዛ ስለወጣች ስትታገድ አዲስ አድማስ እና ሪፖርተር አንድ ግዜ ጠቅላይ ሚንስትሩ በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ አንድ ግዜ ከህመማቸው አገግመው በቤተመንግስት አመራር እየሰጡ ነው እያሉ ውሸት ሲዘባርቁ ነበር ይሄ በራሱ ተመስገንም ሆነ የልዕልና አዘጋጆች ያሉት እውነት መሆኑን ያሳያል፡፡ ይህ ሲባል ግን ከልእልና ውጪ ያሉ ጋዜጦችን እና መፅሔቶችን የስርዐቱ ሎሌዎች ናቸው ማለት አይደለም፡፡
እንግዲህ ለዚህ ሎሌ አዲስ ነገር ፣ አውራምባ ታይምስ ፣ ፍትህ ፣ አዲስ ታይምስ አይነት የዕውነት ነፃ ፕሬሶች የህብረሰቡን ንቃተህሊና በማጎልበት ሰርተው ያለፉትን እንዲሁም ልዕልና አሁን እየሰራችው ያለቸውን ስራ ለሱ ምንም አለመሆኑ እሙን ነው ለኛ ግን ብዙ ነገሮቻችን ናቸው ወደፊት በሁሉም መንገድ አድጋ በልፅጋ ማየት ለምንፈልጋት ኢትዮጵያ የነዚህ አይነት ጋዜጦች መኖራቸው ግድ ነው!!
ከ97 ሱናሚ ቦኋላ ተከፍተው አሁን በህትመት የሌሉ ጋዤጦች አዲስ ነገር፣አውራምባ ታይምስ፣ጉግል፣ ፍትህ፣ፍኖተ ነፃነት፣ ነጋድራስ፣አዲስ ታይምስ ፣አዲስ ወሬ፣መሰናዘሪያ፣ኢትዮ ምሕዳር ወ.ዘ.ተ ይህም የሚያሳየው ስርዐቱ ፕሬሱን ምን ያህል እንደ ጦር እንሚፈራው ነው፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ ፕሬሱ አሁን ሰለሚገኝበት ሁኔታ ለመገንዘብ በልዕልና ጋዜጣ ቁጥር 3 የ‹‹ፍትህ›› ወደ ‹‹አዲስ ታይምስ›› ከዚያም ወደ ‹‹ልዕልና ›› መቀየር ፤ የመንግስት ‹‹ትልቅነት›› ወይስ ‹‹ትንሽነት›› ማሳያ? በሚል ብርሀኑ ደቦጭ የፃፈውን ፅሁፍ ማንበብ በጣም ጠቃሚ ነው!!

በሳኡዲአረቢያ ሊያኖረው የሚችል ፈቃድ ስለሌለው ብቻ ረቡእ ማታ 1 ወጣት አውራሪስ ተሾመ ከለሊቱ አምስት ሰአት ገደማ በአረቦች ተገደለ :

በሳኡዲ አረቢያ በአቋራጭ ጎዳና በመሰደድ አስከፊ ህይወታቸውን ለመታደግ ብሎም ቤተሰቦቻቸውን ለመርዳት ደፋ ቀና እያሉ ከአገራቸው ዳር ድንበር እየተሰደዱ የሚገኙት ወጣቶች ከፍተኛ ስቃይ እና እንግልት እየደረሰባቸው መሆኑን የደረሰን ዜና ዘገባ
ያመለክታል ።
በዚህ ባሳለፍነው ረቡእ ማታ ከለሊቱ አምስት ሰአት ገደማ በአረቦች ተገደለ የተባለው ወጣት ።በሳኡዲአረቢያ ሊያኖረው የሚችል ፈቃድ ስለሌለው ብቻ እንዲገደል ማድረጋቸውን እና አስከሬኑ ወደ ሃገሩ ይላክ ሲባልም ህገወት የገባ ስደተና ስለሆነ ልንሰጣችሁ አንችልም በማለት ምላሽ መስጠታቸውን ከስፍራው ያነጋገርናቸው ወገኖቻችን ገልጸዋል ። እንደ ህበረተሰቡ አገላለስ ከሆነ ልጁን እኛ አልገደልነውም እያሉ ይዋሹናል የገደለው መብረቅ ነው ብለው እያሉ እኛንም እያስፈራሩን ይገኛሉ ሲሉ ተናግረዋል ።

የተገደለው ልጅ ስሙ ወጣት አውራሪስ ተሾመ የሚባል ሲሆን ትውልዱም በሰሜን ሸዋ ክፍለ ሃገር በኤፍራታና ጅሌ ወረዳ የካራቆሬ ከተማ ተወላጅ እንደሆነ ካገኙት የመታወቂያ መረጃ ለማወቅ ተችሎአል ።የማለዳ ታይምስ ዝግጅት ክፍል በአሁን ሰአት በጂዳ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኢምባሲ ለማነጋገር እና የዚህን ሟች አስከሬን ወደ ትውልድ አገሩ የሚላክበት ዘዴ ይፈጥር ዘንድ ትረት በማድረግ ላይ እንገኛለን ።
እንዲህ አይነቱ ችግር ሲፈጠር ማናቸውም ግለሰቦችም ቢሆኑ በግላቸው ጥረት በማድረግ አስፈላጊውን ነገር ከማድረግ ወደ ኋላ እንዳይታቀቡ የማለዳ ታይምስ ዝግጅት ክፍል ያሳስባል ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰሞኑን በአረብ አገር ላይ እየተሰደዱ በሚገኙት ወጣቶች ላይ የድብደባ እና ግድያ ወንጀል መበራከቱን ባሳለፍነው ሳምንታት ያቀረብናቸው የምስል ቅንብሮች ማስታወስ የሚቻል ነው ። ማለዳ ታይምስ ዝግጅት ክፍል ለወላጅ ቤተሰቦቹ መጥናናትን እየተመኘ ለእልፈተ ህይወቱም የሰላም እረፍት ነፍስን በገነት ያኑርልን ይላሉ ።source Minilik Salsawi

ወ/ሮ አዜብ ተጨንቀዋል


አቶ መለስ ከሞቱ ጀምሮ በተለያዩ መድረኮች ንግግርና መዕልክት የሚያስተላልፉት ወ/ሮ አዜብ መስፍን መረጋጋት እንደማይታይባቸው ተገለጠ። አሁንም በባለቤታቸው ስምና መንፈስ ሙግትና ማብራሪያ ከማቅረብ አልተላዘቡም። ይህን የሚያደርጉት ከጭንቀት የተነሳ እንደሆነ ተመልክቷል።

ሰሞኑንን በተጠናቀቀው የኢህአዴግ ጉባኤ አቶ መለስን አስመልክቶ ወ/ሮዋ የተናገሩት ንግግር በጭንቀት ውስጥ ስለመሆናቸው ማሳያ እንደሆነ የተናገሩት አብረዋቸው ባህር ዳር ስብሰባ የተቀመጡ የድርጅታቸው ኢህአዴግ “ባልደረቦቻቸው” ናቸው።

በጉባኤው ወቅት አቶ መለስ ዜናዊን በማወደስ የተዘጋጀው “ዝክረ – መውደስ” ታሪካዊ ሰነድ እንዲሆን ከመጽደቁ በፊት ወ/ሮ አዜብ በሰጡት አስተያየት “በፔሮል የሚከፈለው ብቸኛ መሪ መለስ ብቻ ነው” በማለት ራሳቸውን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች በፔሮል በሚከፈላቸው ገንዘብ ብቻ እንደማይኖሩ የሚያመላክት ንግግር አድርገዋል።

መለስ ደመወዛቸው ስድስት ሺህ ብር እንደሆነ፣ ሁለት ሺህ ብር ሲቆረጥ አራት ሺህ እንደሚቀርና “ይህችኑ ገንዘብ” እየተቀበሉ ላገር ሲሰሩ ያለፉ መሪ መሆናቸውን ያወሱት ባለቤታቸው፣ ለመለስ ዝክረ-መወደስ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ይህ መካተት ይገባዋል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።

“መለስ ጭንቅላቱን ይዞ ወደዚህች ዓለም መጣ፣ ለዚህች ዓለም፣ አገር፣ ምድር፣ የምታገለግል ሃሳብ አመነጨ” ያሉት ወ/ሮ አዜብ፣ ባለቤታቸው ግለኝነት ሳይፈታተናቸው፣ ቤተሰቦቻቸውን በመርሳት፣ ላገራቸው የለፉና ድህነትን ሲዋጉ ኖረው ያለፉ መሪ መሆናቸው ሊረሳ እንደማይገባው አመልክተዋል። አያይዘውም ሊተኩ የሚችሉ መሪ እንዳልሆኑ በማሳሰብ ዝክረ-መወድሱ ከአቶ መለስ የሕይወት ጉዞ ብዙ ቁምነገሮችን የዘለለና ያልተሟላ ነው ብለውታል፡፡ እንዲሁም መለስ የኢትዮጵያ መሪም ብቻ ሳይሆኑ የአዲስ ራዕይ መጽሄት አዘጋጅ መሆናቸው አለመጠቆሙ አግባብ እንዳልሆነ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

በጉባኤው ላይ የተገኙ የድርጅት አባላት እርስ በርሳቸው ሲለዋወጡ የነበረውን የተከታተሉና በግልጽ ከስርዓቱ ባህርይ በመነሳት ስማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ እንዳሉት ወ/ሮ አዜብ የቀድሞው ስብዕናቸው አብሯቸው የለም። እንዲያውም በጭንቀት ውስጥ ያሉ ይመስላሉ ብለዋል።

በድርጅቱ አባላት ከላይ እስከታች የባለቤታቸውን ስልጣን ተገን በማድረግ በጣልቃ ገብነታቸውና ከፍተኛ የሚባል ንብረት በማካበት የሚታሙት ወ/ሮ አዜብ የባለቤታቸውን ስም በመደጋገም የሚያነሱት የሚታሙበትን ጉዳይ ለማስረሳት እንደሆነ እርስ በርስ በእረፍት ሰዓት ይወራ እንደነበር እነዚሁ ክፍሎች ተናግረዋል።

“ሴትየዋ በግልጽ ስለሚነሳባት ጉዳይ ለምን አትናገርም” በማለት የጠየቁ እንዳሉ፣ ከዚህም በላይ በድርጅቱ ውስጥ ነግሷል የሚባለው ሙስና በግልጽ ለምን አጀንዳ ሆኖ እንደማይቀርብ አባሉ ውስጥ ውስጡን ሲያወራ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። በትክክለኛው መንግድ ለመታደስና ለመጥራት የሙስና ጉዳይ የድርጅቱ ቀዳሚ አጀንዳ መሆን እንዳለበት አስተያየት የሰጡም አሉ።

ወ/ሮ አዜብ ይህ ገብቷቸው ይሁን አይሁን ስለ ባለቤታቸው ድህነት ሲናገሩ “እንደሚባለው ሳይሆን እኛ እንኮራበታለን” ማለታቸው ከሙስና ጋር በተያያዘ ስጋት ስለገባቸው የአባሉን ልብ ለማራራት እንደሆነ አድርገው የወሰዱትም እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል። በግልጽ ባያብራሩትም “እንደሚባለው” ብለው በመጥቀስ በይፋ እስከማስተባበል መድረሳቸው በባለቤታቸው ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ራሳቸውም የተረዱት አይመስልም፡፡

አቶ መለስ ከሞቱበት ጊዜ ጀምሮ በሚያገኙት መድረክ ስለ ባለቤታቸው ድህነትና ያለ እረፍት ያለፉ መሪ በማድረግ በስፋት የሚናገሩት ወ/ሮ አዜብ፤ ባለቤታቸውን ዴሞክራት መሪ አድርገው ቢስሉም ሪፖርተር በፖለቲካ አምዱ ያስነበበው እውነተኛ ታሪክ የስጋታቸውና የፍርሃታቸው መነሻ እንደሚሆን ከግምት በላይ የሚናገሩ አሉ። ሪፖርተር ወ/ሮ አዜብን በስም ባይጠቅስም፣ “መሐንዲስ አልባው መተካካት” በሚል ርዕስ በጻፈው “(መለስ) በተለያዩ ጊዜያቶች የፖለቲካ ተቀናቃኞቻቸውን ከፖለቲካ ጨዋታ ውጪ ማድረግ ቢችሉም፣ እስከ 1993 ዓ.ም. ድረስ ሥልጣን የግላቸው አልነበረም፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ ላይ ሆነው የፈለጉትን ማድረግ የሚችሉ ሰውም አልነበሩም፡፡ በወቅቱ የሕወሓት መሰንጠቅን ተከትሎ የድርጅቱ ርዕዮተ ዓለም ቁንጮ (አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም) የወታደራዊ ስትራቴጂ ባለቤት (የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ስዬ አብርሃ)፣ የፕሮፓጋንዳ ኃላፊው (የቀድሞ የትግራይ ፕሬዚዳንት አቶ ገብሩ አስራት) እና ሌሎች የድርጅቱ ከ10 በላይ ከፍተኛ አመራሮች መወገድን አስከትሏል፡፡ የእነዚህ የድርጅቱ ወሳኝ ሰዎች መወገድን ተከትሎ በመንግሥትም ሆነ በፓርቲ ሥልጣናቸውን የተደላደለና ምንም የፖለቲካ ተቀናቃኝ የሌላቸው ሰው መሆን የቻሉበት ጊዜ ነበር፡፡ የፈለጉትን ሕግ ማውጣት ያልፈለጉትን የመደቆስ ሥልጣኑም ጉልበቱም ነበራቸው” ሲል ሪፖርተር የጻፈላቸው አቶ መለስን ተገን በማድረግ ወ/ሮ አዜብ በሃብት፣ በጣልቃገብነት፣ በተለያዩ ውሳኔዎች፣ ፈላጭ ቆራጭ ሆነው መቆየታቸው በርካታ ወዳጅ ያፈራላቸው ባለመሆኑ የስጋታቸው መጠን ሰፊና ጥልቅ እንደሆነ በስፋት አስተያየት እየተሰጠበት ነው። 
(http://www.goolgule.com/)