እሑድ 21 ፌብሩዋሪ 2016

በኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳደር አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማወጅ የቀረበው ሃሳብ በሕወሓት ውድቅ ተደረገ::

በኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳደር አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማወጅ የቀረበው ሃሳብ በሕወሓት ውድቅ ተደረገ::

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – የወያኔን ትንፋሽ በጣረ ሞት የሸበበው የኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ ቀጥሏል::በተለያዩ ወረዳዎች የቀጠለው ተቃውሞ ሕዝቡ በወያኔ አገዛዝ የሚደረግበትን የፖለቲካ ጫና የኢኮኖሚ በደል እና ወታደራዊ እርምጃዎች በመቃውም ተቃውሞውን ለማሰማት አደባባይ የወጣ ሲሆን በየአከባቢው መንገዶችን በመዝጋት ለለውጥ ያለው ቁርጠኝነት በትግሉ እያሳየ ይገኛል::በተለየ ሁኔታ በሃረርጌ ጉራዋ በዳዋ አከባቢ እንዲሁም በበደኖ ተቃውሞ የተደረገ ሲሆን በዳዋ ያሉ ነዋሪዎች የአግኣዚ ሰራዊት ወደ በደኖ ዘልቆ ለመግባት ሙከራ ሲያደርግ ድልድዩን በመዝጋት የመግባት አላማውን አጨናግፈውበታል::
በሻሸመኔ በአምቦ በወለጋ ቀለም ወረዳ በተከታታይ የሚደረጉት ተቃውሞዎች በዛሬው እለት ቀጥለው የዋሉ ሲሆን በጉጁ በተደረገው የቦኮ የአገር ሽማግሌዎች በየ8 አመቱ የሚፈጸመው የመሪዎች ሽግግር እንደተለመደው የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳደር በሃገር ውስጥ ስላሌለ የተገኘው አሻንጉሊቱ ሙላቱ ተሾመ የተባለው የወያኔ ሹም ፕረዚዳንት ሲሆን በከፍተኛ የደህንነት እና ወታደራዊ ኮማንዶዎች አጀብ ተከቦ ውሏል::ርእሰ መስተዳደሩ ሙክታር ከድር ለሕክምና ባንኮክ ነው ይባል እንጂ ምናልባት በቁም እስር ላይ ሊሆን ይችላል የሚሉ የደህንነት ማስረጃዎች ተገኝተዋል::የአግኣዚ ወታደሮች አብዛናው የኦሮሚያ ክልል ከተሞችን ከበው እጥረት ለመፍጠር ቢሞክሩም ሕዝቡ ያለውን አቋም ዝንፍ ሳያደርግ በተቃውሞ ትግሉን ገፍቶበታል::
ይህ በእንዲህ እንዳለ በኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳደር አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ የኦሕዴድ ከፍተኛ አመራር ሁለት አባላት በወይዘሮ አስቴር በኩል ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረቡት ሃሳብ አሻንጉሊዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ሳይደርስ በደህንነት ሹሙ በአላቃ ጸጋይ ውድቅ መደረጉን ምንጮች ጠቁመዋል::ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ ኦሮሚያ የጦርነት ቀጠና ትሆናለች ያሉ አመራሮች ከሕወሓት የተሰጣቸው መልስ ግን ልክ እናስገባቹሃለን የሚል ነው::ከባለፈው ግምገማ በኋላ በሕወሓት እና በኦሕዴድ አመራሮች መካከል ከፍተኛ የከንፈር መነካከስ እንዳለ ሆኖ አለመተማመኑ እና በጥርጣሬ መተያየቱ ስብሰባዎችን እየወገኑ መጥራት እና የማይፈለጉ አባላትን ማግለል እና ማስደንገጥ በሕወሓት እየተፈጸመ መሆኑ ሲገለጽ ተቃውሞውም እየጋለ መምጣቱ ታውቋል::ሕወሓት በአሁን ወቅት ተቃውሞ በርዶ የክልሉን ባለስልጣናት በሰበብ በማሰር በማባረር እና በመበታተን በመፐወዝ ካድሬዎችን አዳዲስ ኦሮሚኛ በተማሩ የሕወሓት ሰዎች በመተካት አዲስ የጭቆና ስልት ለማስፈጸም ዝግጅት እያደረገ ይገኛል::ኦሮሚያ በከፍተኛ ደረጃ በተቃውሞ ባለችበት በዚህ ወቅት ላይ የአግኣዚ ጦር የዘር ማጥፋት ስራ ላይ ተሰማርቶ ባለበት በዚህ ቀውጢ ሰአት ላይ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አላውጅም ሲል ወያኔ ማገዱ ለሕዝብ ሕይወት ደንታ ቢስነቱን ከማሳየቱም በላይ ተቃውሞውን አቅልሎ ለማሳየት መሞከሩ የባሰ እያጋጋለው እንደመጣ ታውቋል::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬
Minilik Salsawi's photo.

ዓርብ 19 ፌብሩዋሪ 2016

የበይነመረብ ዘመቻ ጋዜጣዊ መግለጫ : Online Campaign Press Release



የዘመቻው ርዕስ፦ የኅሊና እስረኞች ይፈቱ!
የዘመቻው ቀናት፦ የካቲት 16-17, 2008
የዘመቻው ዓላማ፦
1ኛ) በግፍ የታሰሩ ጓደኞቻችን እንዲሁም ሁሉም የኅሊና እስረኞች (በምርመራ ቀጠሮ ላይ ያሉ፣ ክስ ተመስርቶባቸው ፍርድ ቤት የሚመላለሱ እና የተፈረደባቸው) ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ መንግሥትን ለመጠየቅ እና ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የሚሠሩ አካላትም ተፅዕኖ እንዲያደርጉ ለመጠየቅ፤
2ኛ) በየእስርቤቱ ያሉ የፖለቲካ እስረኞች ያሉበትን ሁኔታ ለሕዝብ ማሳወቅ፤
3ኛ) ስለመረጃና የመናገር ነፃነት፤ ስለፍትሕ፣ ስለመንቀሳቀስ መብት፤ እና መሰል ሰብኣዊ መብቶች ግንዛቤ ማስጨበጥ እና መንግሥት እነዚህን መሠረታዊ መብቶች እንዲያከብር ዜጎች እስከጥግ ስለመብታቸው በመጠየቅ የድርሻቸውን እነወዲወጡ ማበረታታት።
የዘመቻው ቦታ፦ ዘመቻው በዋነኛነት የሚካሄደው ‹‹ፌስቡክ›› እና ‹‹ትዊተርን›› በመጠቀም ይሆናል፡፡ በተጨማሪም የተለያዩ ጦማሪዎችና የዜና አውታሮች በየጦማሮቻቸው ላይ በመጻፍ ዘመቻውን መቀላቀል ይችላሉ።
የዘመቻው ዋና፣ ዋና ሃሽታጎች፦ #FreeAllPoliticalPrisoners #ሁሉም_የኅሊና_እስረኞ_ችይፈቱ #FreeZelalem #ዘላለም_ይፈታ #FreeEthiopia #ኢትዮጵያ_ትፈታ #FreeAllBloggersAndJournalists #ጋዜጠኞችና_ጦማሪዎች_ይፈቱ #FreeJournalists #ጋዜጠኞች_ይፈቱ
የዘመቻው ተሳታፊዎች፦ ያገባናል የሚሉ ሁሉ!
ዘመቻው ላይ መሳተፍ የሚቻልባቸው መንገዶች፦
1ኛ) በዘመቻው ወቅት ዘማቾች ፕሮፋይል ፎቶዎቻቸውን እና የከቨር ምስሎቻቸውን ለዘመቻው በተዘጋጁ የፖለቲካ እስረኞች ፎቶዎች (ወይም ራሳቸው ባዘጋጁት ምስል) እነወዲሁም አባባሎች በማስዋብ መቀየር፣
2ኛ) በየዕለቱ የተለያዩ ግንዛቤ የሚያስጨብጡ፣ በፖለቲካ እስረኞች አያያዝ፣ በፍርድ ቤት ቤት ሒደት እና መሰል ጉዳዮች ላይ የሚያውቁትን መረጃ በመጻፍ እና የተጻፉትንም በማጋራት፣
3ኛ) ስለሚያውቁት የፖለቲካ እስረኛ ማንነት እና ስለእስሩ ዝርዝር መረጃዎችን በማጋራት፣
4ኛ) መጠየቅ የሚፈቀድላቸው የፖለቲካ እስረኞችን በመጠየቅ አሰተያየቶቻቸውን እና ያሉበትን ሁኔታ መልሶ ለሕዝብ በማድረስ፣
5ኛ) ከፖለቲካ እስረኛ ቤተሰቦች ጋር በመነጋገር ያሉበትን ጥቅል ሁኔታ ይፋ በማድረግ… እና ወዘተ።

——
ዘላለም ወርቃገኘሁ ደ ብርሃን ብሎግ ላይ አጋር ጦማሪ ሆኖ ሰርቷል። በታሰረበት ወቅት ሃምሌ ሁለትሺ ስድስት በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የፐብሊክ አድሚኒስትሬሽን የማስተርስ ዲግሪ ተማሪ ነበር። ከአራት ወራት በሁዋላ ሲከሰስ  የግንቦት ፯ አባል በመሆን፤  በዓረቡ አገር የተከሰተው ሽብር በኢትዮጵያም ተከስቶ ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በአመጽ ለመጣል ሰዎች መልምሏል ፣ ለዚህም የሚጠቀምበት አሥር ሺሕ ብር ተልኮለታል ተብሎ ተከሷል። በተጨማሪም ማኅበራዊ ድረ ገጽ በመክፈት፣ በአንድ አገር በአመጽና በግጭት ማኅበራዊ ለውጥ የሚመጣበትን ማብራሪያ የሚጠይቅ መልዕክት ተላልኳልም ተብሎ ተከሶ ነበር::  ይሄ ብቻ አደለም  ስለጎንደር ዩንቨርሲቲ ረብሻ በፈረንጆች አቆጣጠር ፳፩፩ መፃፉና ይህም በውጭ አገር ባሉ ድህረ ገፆች ላይ መውጣቱ፣ ሃገር ቤት ውስጥ ካሉ ጓደኞቹ ጋራ ስለፖለቲካ መወያየቱ መምከሩ ሁሉ በክሱ ወስጥ ተጠቅሰዋል። ከዘላለም ጋራ ሌሎች ሁለት ጓደኞቹ ታስረዋል፥ ዮናታን ወልዴና ባህሩ ደጉ፣  ጥፋታቸው ደሞ አንድ አሜሪካን አገር ያለ ኢትዮጲያውዊ ጋዜጠኛ አለ ባለው የኢንተርኔት ስልጠና ላይ ለመካፈል በማመልከታቸው። ክሱ ግን የሽብር ስልጠና ነው ይለዋል።
ከስድስት ወር በፊት ፍርድ ቤቱ ብዙዎቹን ክሶች ውድቅ አድርጎ አባላት ለመመልመል መሞከርና የኢንተርኔት ስልጠናውን ማመቻቸት በሚሉት ላይ እንዲከላከሉ ወሥኖ ነበር። በዚህም መሠረት ሁሉም የመከላከያ ምስክሮች የተሰሙ ሲሆን (ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ)፤ በየካቲት 16 የመጨረሻው የመከላከያ ምስክር አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲሰሙ  ቀጠሮ ተይዟል። ዘላለም አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን መከላከያ ምስክር አድርጎ የጠራው በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ተገናኝተህ ነበር የሚል ክሱ ውስጥ ስለተካተተ ነው።
ደብርሃን ብሎግና ወዳጆቻችን የሁለት ቀን የበይነ መረብ ዘመቻ አዘጋጅተናል። በዚህ ዘመቻ ላይ በመሳተፍ እነዘላለምንና እነሱን የመሳሰሉ ሰዎች ከእስር እንዲፈቱ፤ ይህን አይነትም ኢፍትሃዊነት እንዲበቃ በጋራ እንድንጠይቅ ጋብዘናችሗል።
ስለ ተከሳሾቹ ወይም ስለክሶቹ ጠለቅ ያለ መረጃንማግኘት ይህንይህንይህንይህን ወይም ይህን  ማስፈንጠሪያ ወይም ሊንኮች ይጠቀሙ።

ረቡዕ 17 ፌብሩዋሪ 2016

መኢአድ ፓርቲ እርስ በርሱ ሲባላ በደቡብ የወያኔ-ደህንነት ቢሮ ሶስት የተቃዋሚ አመራሮችን አፍኗል::

 

ወያኔ ሰላማዊ ፓርቲዎችን እና አመራሮችን ማሸበሩን ቀጥሏል::በኢንጂነር ሃይሉ ሻውል ፓርቲ መኢአድ ውስጥ በፕሬዚደንቱ አበባው መሃሪ እና በማእከላዊ ምክር ቤቱ መካከል በተነሳው አምባጓሮ ደክሞ የነበረው ፓርቲ ተሽመድምዶ እየሞተ ነው ሲሉ አባላቱ ማማረራቸው ሲታወቅ አቶ አበባ ያልታወቀ ሃይል መከታ በማድረግ የፍርድ ቤት ማገጃ በመጣስ ማህተሙን ለሕገወጥ ስራ እየተጠቀሙበት ነው ሲሉ አባላቱ ይናገራሉ::
አቶ አበባው መሃሪ በመኢአድ ማዕከላዊ ምክርቤት በጥር 15 ቀን, 2008 ዓ.ም ከፕሬዚዳንትነት ሃላፊነታቸው የማንሳቱን ውሳኔ እና በጥር 23 ቀን, 2008 ዓ.ም በፍርድቤት ተከሰው የድርጅቱን ማህተም እንዳይጠቀሙ መታገዳቸውን አምነው እና አክብረው ከተቀበሉ በኋላ ፤በህገወጥ መንገድ የፓርቲው ማዕከላዊ ምክር ቤትን ውሳኔ እና የፍርድቤት የዕግድ ትዕዛዝ በመጣስ የፓርቲውን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ እንድሪያስ ጨምሮ ሌሎች የላዕላይ ምክር ቤት አባላትን በግላቸው አግጃለው እያሉ ደብዳቤ እያሰራጩ መሆኑ ስለተደረሰባቸው ፓርቲው በማጭበርበር ወንጀል ሕግ ሊጠይቃቸው ነው ። ሲሉ አባላቱ ተናግረዋል::
ይህ በእንዲህ እንዳለ በደቡብ ክልል ሲዳማ አርነት ንቅናቄ አመራሮች ባለታወቀ ምክንያት ከያሉበት በደህንነት ሃይሎች ታፍነው መታሰራቸው ታውቋል።በዚህም መሰረት የታፈኑ አመራሮች
1ኛ ደሳለኝ ሜሳ(ሲአን ፖሊቲካ ዘርፍ ኃላፊ )
2ኛ ተሾመ ደበበ (የሲአን ወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ)
3ኛ ደበሳ ዳካ ( የሲአን ቱላ ዞን ሊቀመንበር) ሲሆኑ የደቡብ ክልል ደህነቶችና ፖሊሶች ተባብረው አመራሮቹ በማፈን ወደ ተለያዩ እስር ቤቶች መወሰዳቸው ታውቋል::

ሰማያዊና መድረክ ከስዊድን የፓርላማ አባላት ጋር ተወያዩ

Negere Ethiopia's photo.

የሰማያዊ እና የመድረክ ፓርቲዎች አመራሮች ከስዊድን የፓርላማ አባላት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ተናግረዋል፡፡
የፓርቲዎቹ አመራሮች የሆኑት ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ፣ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት እና ዶ/ር መረራ ጉዲና ከስዊድን ፓርላማ የውጭ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ልዑክ ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ዛሬ የካቲት 9/2008 ዓ.ም መወያየታቸው ታውቋል፡፡
የፓርቲ አመራሮቹ ከስዊድን ስድስት ፓርቲዎች ከተውጣጡ 11 የልዑካኑ አባላት ጋር በተወያዩበት ወቅት በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በኦሮሚያ በተቀሰቀሰው የህዝብ ተቃውሞ እና በጋምቤላ ክልል ስለነበረው ግጭት ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡
Negere Ethiopia's photo.
አመራሮቹ ለተቃውሞ አደባባይ በወጣው ህዝብ ላይ የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እየወሰዱት ያለውን እርምጃ በተመለከተም በውይይታቸው አንስተዋል፡፡
አሁን ላይ በኢትዮጵያ የተቃውሞ ድምጽ የሚያሰሙ የፓርቲ አባላትን እና በነጻነት ስራቸውን በሚያከናውኑ ጋዜጠኞች ላይ እንዲሁም በአጠቃላይ ተቃውሞ በሚያሰማው ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው አፈና እየጨመረ መሆኑንና በሀገሪቱ ፓርላማም አንድም ተቃዋሚ ድምጽ የማይሰማበት መሆኑን እንደገለጹላቸው ታውቋል፡፡
የስዊድን ፓርላማ አባላትም የተቃዋሚ ፓርቲዎች እያደረጉት ስላለው የፖለቲካ እንቅስቃሴና በጋራ ስለሚሰሩበት ጉዳይ ጥያቄ አንስተው በፓርቲዎች አመራሮች ገለጻ እንደተደረገላቸው ኢ/ር ይልቃል ተናግረዋል፡፡
የስዊድን የፓርላማ አባላት ጠ/ሚ ኃ/ማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ከተለያዩ የመንግስት አካላት ጋር እንደተወያዩም ለማወቅ ተችሏል፡፡

ረቡዕ 3 ፌብሩዋሪ 2016

በኦሮሚያ ክልል አዲስ የጸጥታና የደህንነት/ስለላ መዋቅር ሊዘረጋ ነው::በጋምቤላ የሕወሓት ባለስልጣናትና ቤተሰቦቻቸው ንብረት በታጠቁ የደቡብ ሱዳን ቅጥረኞች እና በአግአዚ ወታደሮች መጠበቅ ተጀምሯል::


ልዩነት ውበት ነው…ግን አልፈጠረብንም::መቻቻል ያልተጋባቸው ያልበሰሉ ጭፍኖች በ2 ጽንፍ ማሕበራዊ ድህረገጾችን ወረዋል:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎Gambella‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬
በኦሮሚያ ክልል አዲስ የጸጥታና የደህንነት/ስለላ መዋቅር ሊዘረጋ ነው::በጋምቤላ የሕወሓት ባለስልጣናትና ቤተሰቦቻቸው ንብረት በታጠቁ የደቡብ ሱዳን ቅጥረኞች እና በአግአዚ ወታደሮች መጠበቅ ተጀምሯል::
===========================================================
Minilik Salsawi – በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ አከባቢዎች አሁንም ውጥረት የነገሰ መሆኑን የደህንነት ቢሮ የሚደርሱ ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙ ለጉዳዩ ቅርበት ያላችው ወገኖች መረጃ ሰጥተዋል::በኦሮሚያ ክልል በጥሩ ክፍያ በፎቶግራፍ እና በቭድዮ ቀረጻ ላይ ተሰማርተው የነበሩ የኦሕደእድ ካድሬዎች እየተለቀሙ መሆኑ ታውቋል::የወያኔው ጁንታ አገዛዝ አስፈላጊውን ግድያና የጅምላ እስር ከፈጸመ በኋላ ለይስሙላ የመለሳለስ ባሕሪያ በማሳየት የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን አቆምኩት እንዲሁም የሕዝቡ ጥያቄ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ነው በሚል የሰራውን እኩይ ተግባር ለመሸፋፈን ቢዳክርም የሕዝቡ ተቃውሞ እያገረሸ ብሎም እንዳተኮሰ ይገኛል::መሰሪ እና ውሸታም የሆነው የወያኔ አስተዳደር ላይ ላዩን በመለሳለስ ውስጥ ውስጡን አዲስ የጸጥታ እና የደህንነት/ ስለላ መዋቅር ሊዘረጋ ሲሆን ሕዝቡ ግን አሁንም ለአንድ ለአምስት የአፈና መዋቅር ያልተበገረ ለአዲሱም የስለላ መዋቅር እንደሚያስቸውግር ስጋት መኖሩት የወያነ የደህንነት መረጃዎች ጠቁመዋል:: የመዋቅሩ አዘረጋግ በተመለከተ አስፈላጊው ስራ እየተሰራ ሲሆን ይህ መረጃ የደረሳችሁ ማንኛውም የሕዝብ አካላት የወያኔን መዋቅር በማፈራረስ ዳግም ለህዝባዊ እምቢተኝነት እንድትዘጋጁ ምንጮቹ አሳስበዋል::
በጋምቤላ ክልል አኙዋክ ብሄሮች ላይ ከቀያቸው አፈናቅሎ በሕወሓቶች ለመተካት በደቡብ ሱዳን ቅጥረኛ ኑዌሮች የተጀመረው ግድያ እና ማሳደድ የቀጠለ ሲሆን የሕወሓት ባለስልጣናትና ቤተሰቦቻቸው ንብረት በታጠቁ የደቡብ ሱዳን ቅጥረኞች እና በአግአዚ ወታደሮች መጠበቅ ተጀምሯል::በአኙዋክ ሕዝብ ላይ እጅግ አደገኛ የሚባልለት ይህ የዘር ማጽዳት ከዚህ ቀደም የተካሄደ ሲሆን ለም መሬቶችን ለመቀራመት ባሰፈሰፉ የሕወሓት ስዎች እና ጋሻጃግሬዎቻቸው የደቡብ ሱዳን ኑዌር ስደተኞችን በማስታጠቅ አከባቢው በደም እንዲጨቀይ አድርገዋል::በአለም አቀፉ እና በሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ጫና ግጭቱ ራሱ በከፈተው መንገድ ራሱ ያቀዘቀዘው ሕወሓት አሁንም በበቂ ሁኔታ ለመስፋፋት እና አዳዲስ ለም መሬቶችን ለመያዝ እንዳቀደ በስፋት እየተነገረ ይገኛል::በሃገሪቱ ከባድ እና አደገኛ ውጥረት በመጫር ዘእጎች በሞት እንዲያልኡ እያደረገ የሚገኘውን የሕወሓት አገዛዝ ከስሩ ነቅሎ ለመጣል ትግላችንን አጠናክረን መቀጠል እንዳለብን አሳስባለሁ::
Minilik Salsawi's photo.

ማክሰኞ 2 ፌብሩዋሪ 2016

የመኢአድ ላዕላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንቱን አገደ

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ላዕላይ ምክር ቤት ሰኞ ጥር 16 ቀን 2008 ዓ.ም. ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ፣ የፓርቲውን ፕሬዚዳንት አቶ አበባው መሐሪን አገደ፡፡ ቀጣዩ ጠቅላላ ጉባዔ እስከሚካሄድ ድረስም ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ እንድርያስ ኤሮ ፓርቲውን እንዲመሩ ወስኗል፡፡
‹‹ፕሬዚዳንቱ ስብሰባ እንዲጠሩንና ጠቅላላ ጉባዔ እንዲካሄድ በተደጋጋሚ ብንጠይቅም ፈቃደኛ ካለመሆን አልፈው፣ ወደ አምባጓሮ በመግባታቸው ይህን ለመወሰን ተገደናል፤›› ሲሉ ተቀዳሚ ፕሬዚዳንቱ አቶ እንድርያስ ለሪፖርተር አስታውቀዋል፡፡
ፓርቲው ከገዥው ፓርቲ የሚደርሱበት ጫናና ፈተናዎች እንደተጠበቁ ሆነው፣ ጥቂት የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች የውስጥ ችግሮችን ተወያይተው እንዳይፈቱ መሰናክል እየሆኑ ነው በማለት ገልጸው፣ ‹‹የፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ አበባው መሐሪ የላዕላይ ምክር ቤቱን በደንቡ መሠረት ስብሰባ ባለመጥራት፣ እንዲሁም የፓርቲውን ጠቅላላ ጉባዔ በወቅቱ እንዳይካሄድ በማድረግ ላይ ናቸው፤›› በማለት ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ስብሰባ እንዲጠሩ በተደጋጋሚ ጠይቀው እንደነበር የገለጹት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንቱ፣ ‹‹አቶ አበባው ይህን ማድረግ ባለመፈለጋቸው ከአንድ ሦስተኛ በላይ የምንሆን የምክር ቤቱ አባላት ተሰባስበን በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መክረን ፕሬዚዳንቱን ለማገድ ወስነናል፤›› በማለት አስረድተዋል፡፡
የፓርቲው ላዕላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንቱን በመተካት እስከ ቀጣይ ጠቅላላ ጉባዔ ድረስም በተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንቱ እየተመራ እንዲቆይም እንዲሁ ወስኗል፡፡
ቀጣይ የፓርቲው ጠቅላላ ጉባዔ መቼ እንደሚካሄድ ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ‹‹በመጪዎቹ ስድስት ወራት ውስጥ ይካሄዳል፤›› ሲሉ አቶ እንድሪያስ መልሰዋል፡፡
ከዚህ ውሳኔ በተጨማሪም የፓርቲው ላዕላይ ምክር ቤት ምንም እንኳን የፓርቲው ፕሬዚዳንት የሥልጣን ዘመናቸው የተጠናቀቀ ቢሆንም፣ በመጪው ጠቅላላ ጉባዔ የፓርቲውን ሙሉ ሪፖርት፣ የውስጥና የውጭ ኦዲተሮችን ሪፖርትን ያካተተ ሪፖርት ይዘው እንዲቀርቡም መወሰኑ ተሰምቷል፡፡
የላዕላይ ምክር ቤቱ አባላትም ባወጡት መግለጫ፣ ‹‹እኛ የመኢአድ የላዕላይ ምክር ቤት አባላት መጪው ጠቅላላ ጉባዔ እስኪደረግ ድረስ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንቱና አመራሩ የሚያወርደውን ማንኛውም የድርጅቱ ሥራዎችን ለማከናወን ዝግጁ መሆናችንን እናረጋግጣለን፤›› በማለት ለተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ይሁንታውን መግለጹን አስታውቋል፡፡
ምርጫ 2007 ከመከናወኑ ወራት በፊት መኢአድ ተመሳሳይ ችግር አጋጥሞት እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ በወቅቱ ፓርቲውን በፕሬዚዳንትነት ለመምራት በአቶ ማሙሸት አማረና በአቶ አበባው መሐሪ መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ ነበር፡፡
በወቅቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሰጠው ውሳኔ መሠረት አቶ አበባው የፓርቲው ፕሬዚዳንት ሆነው እንዲቀጥሉ መደረጉ የሚታወስ ነው፡፡
በመኢአድ ላዕላይ ምክር ቤት ከፕሬዚዳንትነት ሥልጣናቸው የታገዱትን አቶ አበባው በአካልም ሆነ በተንቀሳቃሽ ስልካቸው ለማግኘት የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡