የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ላዕላይ ምክር ቤት ሰኞ ጥር 16 ቀን 2008 ዓ.ም. ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ፣ የፓርቲውን ፕሬዚዳንት አቶ አበባው መሐሪን አገደ፡፡ ቀጣዩ ጠቅላላ ጉባዔ እስከሚካሄድ ድረስም ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ እንድርያስ ኤሮ ፓርቲውን እንዲመሩ ወስኗል፡፡
‹‹ፕሬዚዳንቱ ስብሰባ እንዲጠሩንና ጠቅላላ ጉባዔ እንዲካሄድ በተደጋጋሚ ብንጠይቅም ፈቃደኛ ካለመሆን አልፈው፣ ወደ አምባጓሮ በመግባታቸው ይህን ለመወሰን ተገደናል፤›› ሲሉ ተቀዳሚ ፕሬዚዳንቱ አቶ እንድርያስ ለሪፖርተር አስታውቀዋል፡፡
ፓርቲው ከገዥው ፓርቲ የሚደርሱበት ጫናና ፈተናዎች እንደተጠበቁ ሆነው፣ ጥቂት የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች የውስጥ ችግሮችን ተወያይተው እንዳይፈቱ መሰናክል እየሆኑ ነው በማለት ገልጸው፣ ‹‹የፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ አበባው መሐሪ የላዕላይ ምክር ቤቱን በደንቡ መሠረት ስብሰባ ባለመጥራት፣ እንዲሁም የፓርቲውን ጠቅላላ ጉባዔ በወቅቱ እንዳይካሄድ በማድረግ ላይ ናቸው፤›› በማለት ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ስብሰባ እንዲጠሩ በተደጋጋሚ ጠይቀው እንደነበር የገለጹት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንቱ፣ ‹‹አቶ አበባው ይህን ማድረግ ባለመፈለጋቸው ከአንድ ሦስተኛ በላይ የምንሆን የምክር ቤቱ አባላት ተሰባስበን በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መክረን ፕሬዚዳንቱን ለማገድ ወስነናል፤›› በማለት አስረድተዋል፡፡
የፓርቲው ላዕላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንቱን በመተካት እስከ ቀጣይ ጠቅላላ ጉባዔ ድረስም በተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንቱ እየተመራ እንዲቆይም እንዲሁ ወስኗል፡፡
ቀጣይ የፓርቲው ጠቅላላ ጉባዔ መቼ እንደሚካሄድ ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ‹‹በመጪዎቹ ስድስት ወራት ውስጥ ይካሄዳል፤›› ሲሉ አቶ እንድሪያስ መልሰዋል፡፡
ከዚህ ውሳኔ በተጨማሪም የፓርቲው ላዕላይ ምክር ቤት ምንም እንኳን የፓርቲው ፕሬዚዳንት የሥልጣን ዘመናቸው የተጠናቀቀ ቢሆንም፣ በመጪው ጠቅላላ ጉባዔ የፓርቲውን ሙሉ ሪፖርት፣ የውስጥና የውጭ ኦዲተሮችን ሪፖርትን ያካተተ ሪፖርት ይዘው እንዲቀርቡም መወሰኑ ተሰምቷል፡፡
የላዕላይ ምክር ቤቱ አባላትም ባወጡት መግለጫ፣ ‹‹እኛ የመኢአድ የላዕላይ ምክር ቤት አባላት መጪው ጠቅላላ ጉባዔ እስኪደረግ ድረስ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንቱና አመራሩ የሚያወርደውን ማንኛውም የድርጅቱ ሥራዎችን ለማከናወን ዝግጁ መሆናችንን እናረጋግጣለን፤›› በማለት ለተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ይሁንታውን መግለጹን አስታውቋል፡፡
ምርጫ 2007 ከመከናወኑ ወራት በፊት መኢአድ ተመሳሳይ ችግር አጋጥሞት እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ በወቅቱ ፓርቲውን በፕሬዚዳንትነት ለመምራት በአቶ ማሙሸት አማረና በአቶ አበባው መሐሪ መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ ነበር፡፡
በወቅቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሰጠው ውሳኔ መሠረት አቶ አበባው የፓርቲው ፕሬዚዳንት ሆነው እንዲቀጥሉ መደረጉ የሚታወስ ነው፡፡
በመኢአድ ላዕላይ ምክር ቤት ከፕሬዚዳንትነት ሥልጣናቸው የታገዱትን አቶ አበባው በአካልም ሆነ በተንቀሳቃሽ ስልካቸው ለማግኘት የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡

ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ