የዘመቻው ርዕስ፦ የኅሊና እስረኞች ይፈቱ!
የዘመቻው ቀናት፦ የካቲት 16-17, 2008
የዘመቻው ዓላማ፦
1ኛ) በግፍ የታሰሩ ጓደኞቻችን እንዲሁም ሁሉም የኅሊና እስረኞች (በምርመራ ቀጠሮ ላይ ያሉ፣ ክስ ተመስርቶባቸው ፍርድ ቤት የሚመላለሱ እና የተፈረደባቸው) ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ መንግሥትን ለመጠየቅ እና ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የሚሠሩ አካላትም ተፅዕኖ እንዲያደርጉ ለመጠየቅ፤
2ኛ) በየእስርቤቱ ያሉ የፖለቲካ እስረኞች ያሉበትን ሁኔታ ለሕዝብ ማሳወቅ፤
3ኛ) ስለመረጃና የመናገር ነፃነት፤ ስለፍትሕ፣ ስለመንቀሳቀስ መብት፤ እና መሰል ሰብኣዊ መብቶች ግንዛቤ ማስጨበጥ እና መንግሥት እነዚህን መሠረታዊ መብቶች እንዲያከብር ዜጎች እስከጥግ ስለመብታቸው በመጠየቅ የድርሻቸውን እነወዲወጡ ማበረታታት።
የዘመቻው ቦታ፦ ዘመቻው በዋነኛነት የሚካሄደው ‹‹ፌስቡክ›› እና ‹‹ትዊተርን›› በመጠቀም ይሆናል፡፡ በተጨማሪም የተለያዩ ጦማሪዎችና የዜና አውታሮች በየጦማሮቻቸው ላይ በመጻፍ ዘመቻውን መቀላቀል ይችላሉ።
የዘመቻው ዋና፣ ዋና ሃሽታጎች፦ #FreeAllPoliticalPrisoners #ሁሉም_የኅሊና_እስረኞ_ችይፈቱ #FreeZelalem #ዘላለም_ይፈታ #FreeEthiopia #ኢትዮጵያ_ትፈታ #FreeAllBloggersAndJournalists #ጋዜጠኞችና_ጦማሪዎች_ይፈቱ #FreeJournalists #ጋዜጠኞች_ይፈቱ
የዘመቻው ተሳታፊዎች፦ ያገባናል የሚሉ ሁሉ!
ዘመቻው ላይ መሳተፍ የሚቻልባቸው መንገዶች፦
1ኛ) በዘመቻው ወቅት ዘማቾች ፕሮፋይል ፎቶዎቻቸውን እና የከቨር ምስሎቻቸውን ለዘመቻው በተዘጋጁ የፖለቲካ እስረኞች ፎቶዎች (ወይም ራሳቸው ባዘጋጁት ምስል) እነወዲሁም አባባሎች በማስዋብ መቀየር፣
2ኛ) በየዕለቱ የተለያዩ ግንዛቤ የሚያስጨብጡ፣ በፖለቲካ እስረኞች አያያዝ፣ በፍርድ ቤት ቤት ሒደት እና መሰል ጉዳዮች ላይ የሚያውቁትን መረጃ በመጻፍ እና የተጻፉትንም በማጋራት፣
3ኛ) ስለሚያውቁት የፖለቲካ እስረኛ ማንነት እና ስለእስሩ ዝርዝር መረጃዎችን በማጋራት፣
4ኛ) መጠየቅ የሚፈቀድላቸው የፖለቲካ እስረኞችን በመጠየቅ አሰተያየቶቻቸውን እና ያሉበትን ሁኔታ መልሶ ለሕዝብ በማድረስ፣
5ኛ) ከፖለቲካ እስረኛ ቤተሰቦች ጋር በመነጋገር ያሉበትን ጥቅል ሁኔታ ይፋ በማድረግ… እና ወዘተ።
——
ዘላለም ወርቃገኘሁ ደ ብርሃን ብሎግ ላይ አጋር ጦማሪ ሆኖ ሰርቷል። በታሰረበት ወቅት ሃምሌ ሁለትሺ ስድስት በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የፐብሊክ አድሚኒስትሬሽን የማስተርስ ዲግሪ ተማሪ ነበር። ከአራት ወራት በሁዋላ ሲከሰስ የግንቦት ፯ አባል በመሆን፤ በዓረቡ አገር የተከሰተው ሽብር በኢትዮጵያም ተከስቶ ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በአመጽ ለመጣል ሰዎች መልምሏል ፣ ለዚህም የሚጠቀምበት አሥር ሺሕ ብር ተልኮለታል ተብሎ ተከሷል። በተጨማሪም ማኅበራዊ ድረ ገጽ በመክፈት፣ በአንድ አገር በአመጽና በግጭት ማኅበራዊ ለውጥ የሚመጣበትን ማብራሪያ የሚጠይቅ መልዕክት ተላልኳልም ተብሎ ተከሶ ነበር:: ይሄ ብቻ አደለም ስለጎንደር ዩንቨርሲቲ ረብሻ በፈረንጆች አቆጣጠር ፳፩፩ መፃፉና ይህም በውጭ አገር ባሉ ድህረ ገፆች ላይ መውጣቱ፣ ሃገር ቤት ውስጥ ካሉ ጓደኞቹ ጋራ ስለፖለቲካ መወያየቱ መምከሩ ሁሉ በክሱ ወስጥ ተጠቅሰዋል። ከዘላለም ጋራ ሌሎች ሁለት ጓደኞቹ ታስረዋል፥ ዮናታን ወልዴና ባህሩ ደጉ፣ ጥፋታቸው ደሞ አንድ አሜሪካን አገር ያለ ኢትዮጲያውዊ ጋዜጠኛ አለ ባለው የኢንተርኔት ስልጠና ላይ ለመካፈል በማመልከታቸው። ክሱ ግን የሽብር ስልጠና ነው ይለዋል።
ከስድስት ወር በፊት ፍርድ ቤቱ ብዙዎቹን ክሶች ውድቅ አድርጎ አባላት ለመመልመል መሞከርና የኢንተርኔት ስልጠናውን ማመቻቸት በሚሉት ላይ እንዲከላከሉ ወሥኖ ነበር። በዚህም መሠረት ሁሉም የመከላከያ ምስክሮች የተሰሙ ሲሆን (ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ)፤ በየካቲት 16 የመጨረሻው የመከላከያ ምስክር አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲሰሙ ቀጠሮ ተይዟል። ዘላለም አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን መከላከያ ምስክር አድርጎ የጠራው በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ተገናኝተህ ነበር የሚል ክሱ ውስጥ ስለተካተተ ነው።
ደብርሃን ብሎግና ወዳጆቻችን የሁለት ቀን የበይነ መረብ ዘመቻ አዘጋጅተናል። በዚህ ዘመቻ ላይ በመሳተፍ እነዘላለምንና እነሱን የመሳሰሉ ሰዎች ከእስር እንዲፈቱ፤ ይህን አይነትም ኢፍትሃዊነት እንዲበቃ በጋራ እንድንጠይቅ ጋብዘናችሗል።
ስለ ተከሳሾቹ ወይም ስለክሶቹ ጠለቅ ያለ መረጃንማግኘት ይህን: ይህን: ይህን: ይህን ወይም ይህን ማስፈንጠሪያ ወይም ሊንኮች ይጠቀሙ።
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ