እሑድ 29 ማርች 2015

የፊታችን እሁድ የሚካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ቅስቀሳ እንቅፋት እየጋጠመው ነው





9 ፓርቲዎች የጠሩት የተቃውሞ ሰልፍ በመጪው እሁድ ሊካሄድ ነው


መጋቢት ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪነት የተሰባሰቡትና ምርጫ ቦርድ ዕውቅና አልሰጠሁም በሚል ትብብራቸውን እንዲያቆሙ
ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ የሰጣቸው ዘጠኝ ፓርቲዎች በትብብር የጠሩት ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ የፊታችን እሁድ የአዲስአበባ እና የድሬዳዋ ከተሞችን ጨምሮ በአስራአምስት ዋና ዋና ከተሞች ይካሄዳል፡፡
ሆኖም አዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ከወዲሁ ሰልፉ በመንግስት በኩል ያልተፈቀደ ነው በሚል ለማጨናገፍ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
በባህርዳር መጋቢት 20 ሊካሄድ የታቀደው ሰልፍ እንደማይካሄድ መስተዳድሩ ደብዳቤ ጽፏል። በደብዳቤው ላይ እንደተመለከተው ሰልፉ በከተማዋ በመካሄድ ላይ ባለው አገራቀፍ የስፖርት ውድድርና በእለቱ የአባይ ቦንድ ግዢ ዝግጅት በመኖሩ ነው።
የምእራብ ጎጃም ዞን የሰማያዊ ፓርቲ የሰልፉ ጊዜያዊ አስተባባሪ ወጣት አዲሱ ጌታነህ  እንደሚለው በምርጫ ወቅት ምንም አይነት ውድድር ቢኖር ቅድሚያ ለምርጫ ዝግጅቶች እንደሚሰጥ ገልጾ፣ ሰልፉ የሚካሄደው ስፖርታዊ ውድድር ከሚካሄድበት
ስታዲየም ራቅ ባለ ቦታ በመሆኑና ለተማሪዎች ውድድር የጸይታ ሃይሎች አስፈላጊነት አናሳ በመሆኑ፣ መስተዳድሩ ሰልፉን ሆን ብሎ መከልከሉን ተናግሯል።
ገዢው ፓርቲ ሰልፉን ለመከልከል የፈለገበት ሌላ ምክንያት ይኖር ይሆን ተብሎ ለተጠየቀው ደግሞ ” ህዝቡ በስርአቱ ላይ ሊያሰማ የሚችለው ተቃውሞ ገዢውን ፓርቲ ስጋት ላይ ስለጣለው ነው በማለት መልሷል
የሰልፉ ዋና አስተባባሪ የሆኑት አቶ ግርማ በቀለ እንደተናገ  ሩት እስካሁን ድረስ ከአዲስ አበባም ሆነ ከሌሎች አካባቢዎች ሰልፉ እንዳይካሄድ የሚያግድ ደብዳቤ አለመቅረቡን ገልጸው፣ ሰልፎቹ በ15 ከተሞች በታቀደላቸው መሰረት ይካሄዳሉ ብለዋል።
አቶ ግርማ እንደሚሉት በምርጫ ቅስቀሳ ወቀት መስተዳድሮች የፖለቲካ ድርጅቶች የሚያካሂዱዋቸውን ሰልፎች መከልከል እንደማይችልና ሰልፎቹ በማንኛውም መንገድ እንደሚካሄዱ ገልጸዋል
«ነጻነት ለፍትሐዊ ምርጫ» በሚል የታሰበው ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ የሚካሄድ ከሆነ በርካታ ቁጥር ያለው ህዝብ ድጋፉን ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል ሲል የአዲስ አበባው ዘጋቢ አስተያየቱን ሰጥቷል።
በግንቦት ወር ከሚካሄደው ምርጫ ጋር ተያይዞ ጠንከር ያሉ መልዕክቶችን ያዘሉና ገዥውን ፓርቲ የሚተቹ የምርጫ ቅስቀሳዎች በመንግስትና እንደራዲዮ ፋና ባሉ የፓርቲ ልሳናት እየታገዱ ሲሆን ፣ በየመንገዱ የሚሰቀሉና የሚለጠፉ የቅስቀሳ መልዕክቶች
ኢህአዴግ ከፍሎ ባሰማራቸው  ወጣቶች አማካይነት በጠራራ ጸሐይ እየተቀደዱ መሆኑን ፓርቲዎቹ በተናጠል በሚያቀርቡዋቸው ተደጋጋሚ ቅሬታዎች  እያሳወቁ ነው፡፡
በአንዳንድ አካባቢዎች ተወዳዳሪ ዕጩዎች ሳይቀር ምክንያት እየተፈለገ በመታሰር ላይ ናቸው።
በሌላ በኩል ደግሞ በአዲስ አበባ ስጋቶች ላይ የመከረው የአዲስ አበባ ካቢኔ የዋጋ ንረት ፤ የገንዘብ ግሽበት ፤ የስኳር እና ዘይት እጥረቶችን በቀዳሚነት አንስቷል።  በመጭው ምርጫ ለስርአቱ ከፍተኛ ስጋት የፈጠረው ሙስሊሙ ማህበረሰብ ነው  ሲል ገምግሟል።
ሙስሊሙ ከፖለቲካው ጋር በፈጠረው ኩርፊያ ፤ ለኢህአዴግ ድምፁን የመንፈግ እና አመፅ የማቀጣጠል እድል እንዳለው ስጋት በሚለው የመጀመሪያ መስመር ላይ ተቀመምጧል፡፡ ምርጫውን ለማሸነፍ የ1ለ 5 አደረጃጀት ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሰተያየት ተሰጥቷል።
ካቢኔው በቅርቡ የተከፋፈሉት የኮንዶሚኒየም ቤቶች ህዝቡ ለኢህአዴግ ድጋፍ እንዲሰጠው እንደሚያግዘው ገምግመዋል።  ብዙዎችን ያስገረመው  የኮምፒዩተር እጣ አወጣጡን ሶፍት ዌር አዘጋጀው ለተባለው ለመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ወይም ኢንሳ 11 ሚሊዮን ብር መከፈሉ ነው።

የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ መልዕክቶች በመንግስት የመገናኛ ብዙሃን እንዳይተላለፉ እየተደረገ ነው

ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን መጋቢት 16/2007 ዓ.ም ለፓርቲው በላከው ደብዳቤ፣ ከተላኩት የቅስቀሳ መልክቶች መካከል ” የመከላከያ ሰራዊቱ ሌሎችም የአገሪቱ ቁልፍ ተቋማት ከገዢው ፓርቲ ካድሬዎች

ውጪ አልሆነም፣ በተለይም በገዛ ሃገራቸው ከስራ ይባረራሉ ፣ ተቋማቱን እውቀት የሌላቸው ካድሬዎች እንዲመሩት ተደርጓል፣ ገዢው ፓርቲ ፖሊስን፣ ሚዲያውን፣ መከላከያ ሰራዊቱን፣ ደህንነቱን ሰማያዊንና ሌሎች ተቃዋሚዎችን ለማጥፋት ሲጠቀምባቸው ቆይቷል
የሚሉትና ሌሎችም በህገ መንግስቱ የተቋቋሙ የዲሞክራሲ ተቋማትን ህልውና የሚክድና ተግባራቸውን የሚያንቋሽሽ መልእክቶች በመሆናቸውና ህገመንግስቱን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ስነምግባር ህጉን እና የድርጅታችንን ኢዲቶሪያል ፖሊሲ የሚጻረሩ ሆነው
ስለተገኙ አይተላለፉም ብሎአል።
ሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክቶቹ እንዳይተላለፉ ሲከለከል የአሁኑ ለ8ኛ ጊዜ ነው፡፡

ረቡዕ 25 ማርች 2015

ታዋቂ ወጣት ፖለቲከኞች ታሰሩ

መጋቢት ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-3 የሰማያዊ ፓርቲ አባላት መታሰራቸውን ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመለከተ።

ወጣት ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ ወጣት ፍቅረማርያም አስማማውና እየሩሳሌም ተስፋው ካለፉት 2 ሳምንታት ጀምሮ በማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ እንደሚገኙ ኢሳት አረጋግጧል።
ወጣቶቹ በምን ምክንያት እንደታሰሩ ለማወቅ አልተቻለም። መንግስትም እስካሁን የሰጠው ይፋ መግለጫ የለም። በሌላ በኩል ደግሞ የፓርቲው ሊ/መንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ወደ ሰሜን አሜሪካ በማቅናት በመጪው ግንቦት በሚካሄደው ምርጫ ውስጥ
ለሚሳተፉ የሰማያዊ ፓርቲ እጩዎች ገንዘብ እንደሚያሰባስቡ የአንድነት የሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበርና የሰማያዊፓርቲ ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበር በጋራ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
ኢ/ር ይልቃል በኢትዮጵያ የምርጫ ሂደት ምን ይመስላል፣ ምርጫው ውስጥ መቆየት ያለው ፋይዳ፣ የሰማያዊ ፓርቲ አጠቃላይ ገፅታና እንቅስቃሴ ምን ይመስላል፣ በሚሉት ጥያቄዎች ላይ ውይይት እንደሚያደርጉ ኮሚቴው ገልጿል፡፡
የፓርቲውን የሰላማዊ ትግል ስትራቴጂዎች በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ማስረዳትና በነዚህ ጉዳዮች እንዲሁም ባጠቃላይ የአገራችን ወቅታዊ ሁኔታዎች ዙሪያ ከኢትዮጵያዊያን ጋር ዉይይት ማኪያሄድም የዝግጅቱ አንድ አካል መሆኑም በመግለጫው ተጠቅሷል።

ዓርብ 20 ማርች 2015

ትንሽ ስለመለሰ መንገሻ

ትንሽ ስለመለሰ መንገሻ
በርካታ ሰዎች ስለመለሰ መንገሻ በቂ መረጃ የለንም የት ነበር ? በመኢአድ ውስጥ ሀላፊነቱ ምንድነበር ? ብላች ለጠየቃችሁኝ ወዳጆቼ ትንሽ ስለመለሰ መንገሻ ልበል
መለሰ መንገሻ በሰሜን ጎንደር የመኢአድ የወጣቶች አደረጃጀት ውስጥ ሲሰራ የነበረ አዲስ አበባ ከመጣም በኋላ የወጣቶች የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ ሆኖ ሲሰራ የነበረ ነው የጥምቀት በአል ለማክበር ጎንደር ሄዶ በነበረበት ጊዜ ተይዞ በአሁኑ ሰአት አዲስ አበባ ማዕከላውይ በእስር ላይ የሚገኝ ነው እስከ አሁን ድረስ የመለሰ መንገሻን ቤተሰብ ማግኘት ባለመቻላችን ስለቤተሰቡ ሁኔታ መረጃ ማግኘት አልቻልንም ።


ሐሙስ 19 ማርች 2015

አንድነት ፓርቲ “የመድብለ ፓርቲ ስርዓት እንዳይፈጠር የምርጫ ቦርድ ታሪካዊ ወንጀል እየፈፀመ ነው” ሲል የአቋም መግለጫ ሰጠ

ከአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ/አንድነት/
የተሰጠ መግለጫ

UDJየአንድንታ ፓርቲ በኢትዮጵያ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት እንዲፈጠር በምንም መለኪያ በገለልተኝነት የማንጠብቃቸውን የዲሞክራሲ ተቋማት በተግባር ለመፈተን እንዲቻል የሁለት ሺ ሰባት ምርጫን በሁሉም ሂደቶች ህዝቡን በማሳተፍ እንደሚወዳደር እና ህዝብን የስልጣን ባለቤት ለማድረግ እና የኢህአዴግ አገዛዝ የመጨረሻ እንዲሆን በቁርጠኝነት እንደሚሰራ መወሰኑ ይታወቃል፡፡ ይህን ስንወስን እነዚህ ተቋማት ገለልተኝነታቸውን አረጋግጠው ታሪክ የሚሰሩበት እድልም ያገኛሉ የሚል ተሰፋ ነበር፡፡

ይሁን እንጂ ምርጫ ቦርድ ይህን እድል ከመጠቀም እና በህግ የተሰጠውን ኃላፊነት በብቃት ከመወጣት ይልቅ ለገዢው ፓርቲ ያለውን ወገንተኝነት በምርጫው ሂደት ዋዜማ በይፋ እያረጋገጠ ይገኛል፡፡ አሁንም ቦርዱ ወሰነ ተብሎ በሚዲያ የተገለፀው እንዲሁም ለፓርቲያችን በፅሁፍ የተሰጠው “በአስራ አምስት ቀን ውስጥ በጋራ ጉባዔ አድርጉ” የሚል ትዕዛዝ፤ ቦርዱ በተደጋጋሚ ፓርቲያችንን ደንብ እንዲያከብር እየጠየኩ ነው በማለት ከደንብ ውጭ እንድንሰራ የአዛኝ ቂብ አንጓች ሆኖዋል፡፡ የአንድነት ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔ የመጥራት ኃላፊትን ያለበት የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት ወይም ደግሞ በአባላት ጥያቄ የጠቀላላ ጉባዔ አባላትን አንድ ሶስተኛ ፊርማ አስባስበው በኦዲትና ኢንስፔክሽን ትዕዛዝ መሆኑ በግልፅ እየታወቀ ከፓርቲያችን መተዳደሪያ ደንብ ውጭ በ15 ቀን ውስጥ ጉባዔ ጥሩ የሚል ትዕዛዝ፤ ቦርዱ ከገዢው ፓርቲ ጎን ተሰልፉ እየተጫወተ አንድነትን ከጫወታ ለማስወጣት ካለሆነ ሌላ ምንም ትርጉም ልንሰጠው አንችልም፡፡ ይህ ደግሞ ቦርዱ እየሰራ ያለውን ታሪካዊ ወንጀል ይፋ የሚያደርግ ነው፡፡

ይህ በማን አለብኝ ሰሜት የተሰጠ ውሳኔ ሳይታረም ቢቀርና ገዢው ፓርቲ ያለምንም ጠንካራ ተቀናቃኝ ብቻውን ሮጦ ብቻውን እንዲያሻንፍ የሚያደረግ ተቋማዊ ሴራ ቦርዱን በታሪክ ተጠያቂ ማድረግ ብቻ ሳይሆን በዚህች ሀገር ዘላቂ ሰላም ላይ ለሚፈጠረው አደጋ ቦርዱ ከተጠያቂነት እንደማይድን ለማስታወስ እንወዳለን፡፡

በዚህ አጋጣሚ አንድነት ፓርቲ የሰላማዊ ትግሉን ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ ለማድረግ እና ህዝቡን የስልጣን ባለቤት የማድረግ እንቅስቃሴውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልና በቀጣይ ሳምንታትም በመንግሰትና በቦርዱ ላይ ጫና ማሳደሩን እንደሚቀጥልበት እያረጋገጥን አንድነት ፓርቲ ወደ ህገወጥነት የሚወሰደውን “የጋራ ጉባዔ” አካሂዱ የሚለው የምርጫ ቦርድ ውሳኔ የማንቀበለው መሆኑን ለመላው አባላትና ደጋፊውች ማረጋገጥ እንወዳለን፡፡
ጥር 8/2007
ድል የህዝብ ነው!!!
አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ/አንድነት/

ሰበር ዜና – ከማህከላዊ ማሰቃያ እስር ቤት!

11070480_793005004117769_6875115708675681738_nየአንድነትና ሰማያዊ ፓርቲ ወጣት ሰላማዊ ታጋዮች ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ከሀያ ቀን በፊት በወያኔ አፋኝ ቡድን መታፈናቸው ከተሰማ ወዲህ ወጣቶቹ በማህከላዊ ማሰቃያ እስር ቤት ውስጥ መገኘታቸው ታውቋል፡፡ይሄንን አስመልክቶ በዛሬው ቀን 10/07/07/ ከ 8/ሰሀት በኃላ ያሉበትን ሁኔታ ለማረጋገጥ ወደ ቦታው በመሄድ ጥየቃ ለማድረግ ብንሞክርም ጥየቃ እንደማይቻል ነገር ግን ስንቅ ብቻ ማስገባት እንደሚቻል ተገልጾልን የቅርብ ቤተሰብ የሆነ ሰው ብቻ ከሆናችሁ ግን ወደ ቢሮ ቁጥር/35/ በመሄድ አስመዝግባችሁ መገናኘት ይቻላል ቢባልም ወደ ቦታው በመሄድ ስንጠይቅ እንደዚ የሚባል እስረኛ የለም ተብሉዋል፡፡

ቀደም ሲል እስረኞቹ መኖራቸው ከመዝገብ ተረጋግጦ መጠየቅ የሚችለው ቤተሰብ ብቻ ነው፡፡ በተባልነው መሰረት የጠየቅን መሆኑን ብንገልጽም የተባሉትን ሰዎች አናውቃቸውም በማለት ሁለት የተለያየ ምክንያቶች ሲሰጡ ለማየት ተችሉዋል፡፡
ነገር ግን ወጣት ብርሀኑ ተ/ ያሬድ ከወላጅ እናት ጋር ለጥቂት ደቂቃ ቢሆንም ያገኙት ሲሆን በመልካም ሁኔታ እንደሚገኝ ለቤተሰቡ መግለጹን ለማወቅ ተችሉዋል፡፡ የወያኔ ምርጫ ቦርድ አንድነት ፓርቲን ካፈረሰ በኃላ ድርጊቱን የተቃወሙ አባሎች ላይ ከፍተኛ መንገላታት እና አፈና እየተፈጸመባቸው የሚገኝ ሲሆን ይሄንን አስመልክቶ ከሀያ ቀን በፊት ከሸዋ ሮቤት የታፈነው ወጣት ዘሪሁን ገሰሰ እስካሁን የት እንዳለ ለማወቅ አልተቻለም፡፡ በማህከላዊ ማጎሪያ እስር ቤት ከሚገኙት ሰላማዊ ታጋዮች ጋርም እንደሌለ ለማወቅ ተችሉዋል፡፡