መገናኛ አካባቢ ወደ ጉርድ ሾላ በሚወስደው መስመር፣ አንድ መንገደኛ ትናንት ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ሚኒባስ ታክሲ ውስጥ ካልተሳፈርኩ ብሎ ሾፌሩን ወንደሰን ደምሴን በሽጉጥ ገደለ፡፡ “ታክሲው ውስጥ ካልተሳፈርኩ፣ አትሳፈርም” በሚል በተነሳው ጭቅጭቅ፣ ሾፌሩን ገድሏል የተባለውን ደጀኔ ገመቹ በቁጥጥር ስር እንደዋለ የገለፀው ፖሊስ፤ የአይን ምስክሮችን ቃል በመቀበል ምርመራ እያካሄደ ነው፡፡ ታክሲ እየጠበቁ የነበሩ የአይን ምስክሮች በወቅቱ አቶ ደጀኔ እጁን በማወዛወዝ ሚኒባስ ታክሲውን እንዳስቆመ ተናግረው፣ ከሾፌሩ ጋር ጭቅጭቅ እንደተፈጠረ ገልፀዋል፡፡ አቶ ደጀኔ በታክሲው ለመሳፈር ሲጠይቅ፣ ሾፌሩ “ቤተሰቤን ነው የጫንኩት፣ ሌላ ሰው አላስገባም” በማለት ምላሽ እንደሰጠው በአካባቢው የነበሩ መንገደኞች ተናግረዋል፡፡ ታክሲ የሚጠባበቁ ብዙ ሰዎች በአካባቢው ስለነበሩ፣ ጭቅጭቁን ከመነሻው እስከ መጨረሻው የተመለከቱ እማኞች በርካታ ናቸው፡፡ የፖሊስ መረጃ እንደሚጠቁመው፤ የሾፌሩ አባት ታክሲው ውስጥ ነበሩ፡፡ “አትሳፈርም የምትለኝ ንቀት ነው” በሚል ክርክርና “የጫንኩት ቤተሰቦቼን ስለሆነ ሌላ ሰው አልጭንም” በሚል ምላሽ በተባባሰው ጭቅጭቅ፣ አቶ ደጀኔ ሽጉጥ እንዳወጣ እማኞች ተናግረዋል፡፡ ሽጉጡን ሾፌሩ አንገት ስር በመደገን ነው የተኮሰው ብለዋል-ምስክሮች፡፡ በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሰው መግደል ዲቪዥን ክፍል ተወካይ፣ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን ገልፀዋል።
ቅዳሜ 28 ዲሴምበር 2013
ረቡዕ 25 ዲሴምበር 2013
ሚሊየነሩ ኒቆዲሞስ ዜናዊ (ከእየሩሳሌም አርአያ)
ኒቆዲሞስ ዜናዊ የአቶ መለስ ዜናዊ ወንድም ነው። ከወ/ሮ አለማሽ ገ/ልኡልና ከአቶ ዜናዊ አስረሳኸኝ የተወለዱ ወንድማማቾች ናቸው። ኒቆዲሞስ በደርግ ስርአት በክብሪት ፋብሪካ ተቀጥሮ በተራ ሰራተኝነት ይሰራ ነበር። የአካል ጉዳተኛ (አንድ እግሩ) የሆነው ኒቆዲሞስ ከተራ ወዝአደርነት ወጥቶ ሚሊየነር ለመሆን የበቃው ደርግ ወድቆ ሕወሐት/ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ ነበር። የፋብሪካ ስራውን በግንቦት 1983ዓ.ም ማግስት የለቀቀው የአቶ መለስ ወንድም ኒቆዲሞስ ከአሜሪካ በ25ሺህ ዶላር የተገዛች አዲስ አውቶማቲክ ማርሽ አውቶሞቢል እንዲይዝ ተደረገ። ተራ ወዛደር የነበረ ሰው 25ሺህ ዶላር የሚያወጣ መኪና ሊገዛበት የሚችል የገንዘብ አቅም እንደሌለው ግልፅ ቢሆንም ነገር ግን ይህን ያክል የገንዘብ መጠን በማውጣት ለኒቆዲሞስ የተበረከተለት ስጦታ ወንድሙ አቶ መለስ ዜናዊ የሚመሩት ሕወሐት እንደሆነ ሳይታለም የተፈታ ነበር። ይህም ብቻ አይደለም፤ ኒቆዲሞስ አካል ጉዳተኛ ነው በሚል ሰበብ አውቶሞቢሉ የጉምሩክ ቀረጥ ሳይከፈልበት ነበር አገር ውስጥ የገባው። ይህን ጉዳይ በተመለከተ “ወጋህታ” የተባለች በትግርኛ ቋንቋ በአገር ውስጥ ትታተም የነበረች የነፃው ፕሬስ ጋዜጣ ከጉምሩክ ለኒቆዲሞስ ዜናዊ ያለቀረጥ መኪናው እንዲገባ የተሰጠውን፣ በስሙ ተፅፎ ከነመኪናው ሻንሲ ቁጥር ጭምር የተገለፀበትን ደረሰኝ ማስረጃ በማውጣት ጋዜጣዋ አጋልጣለች። ከዜና ዘገባው ጋር በተያያዘ በወቅቱ በተለያዩ ጋዜጦችና ሌሎች ወገኖች ከተነሱት አስተያየት አዘል ጥያቄዎች ተከታዩ ዋናው ነበር፤ « ..ኒቆዲሞስ ዜናዊ ያለቀረጥ አውቶሞቢል እንዲገባለት የተደረገው ከበላይ አካል በተላለፈ ቀጭን ትእዛዝ ነው። የገንዘብ ምንጩ የገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት እንደሆኑ ግልፅ ነው። ከመኪናው ግዢ እስከ ጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ፍቃድ ድረስ ሙስና ተፈፅሟል። ኒቆዲሞስ ይህን ህገ-ወጥ ጥቅም እንዲያገኝ ሲደረግ የአገሪቱ መሪ አቶ መለስ ወንድም በመሆኑ ነው። ስለዚህም በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ አቶ መለስ ከሙስናው ጋር በተያያዘ ሊጠየቁ ግድ ነው። ለምሳሌ በሙስና እንዲከሰሱ ከተደረጉት ባለስልጣናት አንዱ አቶ ስዬ አብርሃ የቀረበባቸው ክስ በቂ ማስረጃ ወይም ማመሳከሪያ ነው። አቶ ስዬ ለወንድማቸው ምህረተአብ አብርሃ ሰባት መኪኖች ያለቀረጥ እንዲገቡ አድርገዋል የሚለው ክስ ይጠቀሳል። አንድ መኪና ሆነ ሰባት አሊያም ሰባት መቶ..ቀረጥ እስካልተከፈለባቸው ድረስ ሙስና ለመሆኑ አያጠያይቅም። ስለዚህም የኒቆዲሞስ ጉዳይ ሙስና መሆኑ ግልፅ ነው። ከተፈፀመው ቀረጥ ያለመክፈል ክስ ጋር ኒቆዲሞስና ወንድሙ አቶ መለስ በሙስና ሊከሰሱ ይገባ ነበር። » የሚሉ ነጥቦች ነበሩ ከተለያዩ ወገኖች ይነሱ የነበረው። ይህ ጉዳይ በተለይ በስፋት አነጋጋሪ ሆኖ የነበረው በዘጠናዎቹ የመጀመሪያ አመታት ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ተከታዩ ነው። ኒቆዲሞስ ዜናዊ ከተራ ወዝአድርነት ወጥቶ በአንድ ግዜ ሚሊየነር የሆነበት ሚስጥሩ በ1988 ዓ.ም አንድ የኤርትራና ጣልያን ዘር ያለው ግለሰብ ከሮም አዲስ አበባ ይመጣል። ከዚያም ከኒቆዲሞስ ዜናዊ በጋራ « ጃክሮስ ኢትዮጲያ » የተባለ ድርጅት ያቋቁማሉ። ኒቆዲሞስ የጃክሮስ ግማሽ (50%) ባለድርሻ ሆኖ ነበር ድርጅቱ የተመሰረተው። “ጃክሮስ” በተቋቋመ ማግስት የመንግስት ሚዲያ የሆኑትን የኢትዮጲያ ቴሌቪዥንና ራዲዮ እንዲሁም ፋና ራዲዮ በማስታወቂያ ተቆጣጠረው። በተጨማሪ የአማረ አረጋዊ « ሪፖርተር » ጋዜጣ ማስታወቂያ በተጋነነ መልኩ ከማውጣት ባለፈ ስለ ድርጅቱ (ጃክሮስ) ሰፊ የዜና ዘገባና ትንታኔ በመስራት ተከታታይ ሽፋን መስጠት ያዘ። በጋዜጣውና በመንግስት መገናኛ ይቀርቡ የነበሩት ማስታወቂያዎችና ዘገባዎች ፥ « ..ጃክሮስ ኢትዮጲያ, በአገራችን የመጀመሪያው የመኖሪያ ቤት ግንባታ የሚያካሂድ፤ እጅግ ዘመናዊ የሆኑ ቪላዎችን በመገንባት ለደንበኞቹ በአጭር ግዜ ውስጥ ሰርቶ የሚያስረክብ ነው፤ ለግንባታ ከሚጠቀማቸው ቁሳ-ቁሶች መካከል በተለይ ለቪላው ማሳማሪያ የሚጠቀማቸው ከውጭ አገር የመጡና ዘመናዊ ናቸው፤ እንደ ደንበኛው ፍላጎትና ምርጫ የሚገነባው በቂ የዋስትና ሽፋን በድርጅቱ የሚሰጠው ሲሆን፣ ጃክሮስን የተለየ የሚያደርገው የሚገነቡት ቪላዎች ስታንዳርዳቸውን የጠበቁና የውጭ አገር ዘመናዊ ቪላዎች አይነት መሆናቸው ጭምር ነው። ደንበኛው ሙሉ ክፍያ የሚከፍል ከሆነ በአንድ አመት ግዜ ውስጥ መኖሪያውን አጠናቆ ያስረክባል፤ ከደንበኛው ጋር በሚደረግ ስምምነት ክፍያው ተፈፃሚ ይሆናል፤ ይህ ማለት የረጅም አመት ክፍያ ድርጅቱ ይሰጣል።…» የሚሉት በተጋነነ መልክ ይቀርቡ ከነበሩት ይጠቀሳሉ። ድርጅቱ እንደ ሽፋን የተጠቀመበትና የተጠቀሱት ሚዲያዎች ያራግቡ የነበረበት አንድ አጋጣሚ ተፈጥሮ ነበር። በ1988ዓ.ም የአትላንታ ኦሎምፒክ የሚካሄድበት አመት ነበር። እነ ሃይሌ ገ/ስላሴ ለመጀመሪያ ጊዜ ኦሎምፒክ የሚሳተፉበት፣ እነ ፋጡማ ሮባና ደራርቱ ቱሉ የተካተቱበት ጭምር ነበር። ሁሉም ኢትዮጲያዊ ማለት ይቻላል ከወራቶች ቀደም ብሎ ውድድሩን በጉጉት እንዲጠብቅ የተገደደበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር። “ጃክሮስ” ይህን አጋጣሚ ለመጠቀም ኢላማ አድርጎ የተነሳው የአንጋፋው አትሌት ሻለቃ ዋሚ ቢራቱን ቤት በነፃ እገነባለሁ በሚል ነበር። በቀድሞ ወረዳ 12 ቀበሌ 07 የሚገኘውን የዋሚ ቢራቱ መኖሪያ በሁለት ወር ውስጥ ሰርቶ እንደጨረሰ ተናገረ። ቀደም ሲል የነበረውን የዋሚ ቤት በማደስ የሰራውና በከፍተኛ ደረጃ የተራገበለት መኖሪያ በቲቪ መስኮት የታየውና ተጨባጩ እውነታ ለየቅል ነበሩ። ለቤቱ ግንባታ ተብሎ ዙሪያውን የዋለው ለተለያዩ ቁሳቁሶች ማሸጊያነት (ለምሳሌ ከውጭ የሚገቡ ፍሪጆችና ቴፕ..ወዘተ ጉዳት እንዳይገጥማቸው ከውስጥ በማሸጊያነት ) የሚውለው ፎም ነበር። ከዚያ በቀለም እንዲያሸበርቅ ከተደረገ በኋላ « 2 ሚሊዮን ብር በማውጣት ጃክሮስ ለዋሚ ቢራቱ ቤት ገንብቶ አስረከበ..» ተብሎ በጋዜጣውና በሚዲያ አስነገረ። አንጋፋው አትሌት በወቅቱ ከአሜሪካ ለመጣውና ቀበሌ 11 ለሚኖረው እስክንድር አሰፋ ስለቤቱ ሲናገር በሃዘን ጭምር ነበር፤ « የበፊቱ መኖሪያዬ ይሻለኝ ነበር። እንኳን 2 ሚሊዮን ብር 1ሺህ ብር አልወጣበትም። እኔን መነገጃ ማድረጋቸው ለምን እንደሆነ አልገባኝም።» ነበር ያለው ዋሚ። በእርግጥም እነኒቆዲሞስ በዋሚ ነግደዋል። ከአሜሪካ የመጡ መኖሪያ ቤት ፈላጊዎች ጃክሮስን አምነው 70ሚሊዮን አስረከቡ። ሌሎች ወገኖችም ቀለጡ። አንድ አመት ቢጠብቁ ምንም ነገር የለም። ከአሜሪካ የመጡ ወገኖች ከብዙ መንከራተት በኋላ የደረሰባቸውን በደል በኢ.ቲ.ቪ “አይናችን” ፕሮግራም ቀርበው « ለአመታት ሰሃን አጥበን፣ ደም ተፍተን ሰርተን ያጠራቀምነውን ገንዘብ በአደባባይ ተዘረፍን። ህግና መንግስት ባለበት አገር እንዴት እንዘረፋለን?..መንግስት ይፍረደን!.» በማለት በእንባ እየተራጩ አቤቱታቸውን አሰሙ። እነ ኒቆዲሞስ ከህብረት ኢንሹራንስ ጋር የዋስትና ውል አለን ብለው ያሉትም በጭራሽ ከተገለፀው ድርጅት ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌላቸው የህብረት ኢንሹራንስ ዋና ሃላፊ አቶ ኢየሱስወርቅ ዛፉ በወቅቱ አጋለጡ። ኤርትራዊው የጃክሮስ ባለድርሻ ፈረንሳይ ለጋሲዮን በወረዳ 12 ፖሊስ ጣቢያ እንዲታሰር ተደረገ። የሚገርመው ከፍተኛ የማጭበርበር ወንጀል መሆኑ እየታወቀ፣ ጉዳዩ በማእከላዊ ምርመራ መያዝ ሲገባው ወይም የጃክሮስ ቢሮ ይገኝበት በነበረው ቦሌ አካባቢ ባለ ፖሊስ ጣቢያ መታየት ሲገባው…ከድርጊቱ ጋር ግንኙነት በሌለው ወረዳ 12 የፖሊስ ጣቢያ ጉዳዩ መያዙና መታሰሩ እንቆቅልሽ ነበር። ሶስት ቀን ብቻ ከታሰረ በኋላ ፍ/ቤት ሳይቀርብ “በ2ሺህ ብር ዋስ” ተፈታ። በተፈታ ማግስት በቦሌ እንዲወጣ ተደረገ። ከፍተኛውን ሚና የተጫወተው ኒቆዲሞስ ነበር። የተዘረፉት ወገኖች በድጋሚ ወደ ኢ.ቲ.ቪ ቢሄዱም መስተናገድ አልቻሉም። ምክንያቱ ደግሞ ግልፅ ነበር። የዘረፋው ጉዳይ በነፃው ፕሬስ በየግዜው ቢነሳም ሰሚ ግን አልነበረም። ነሐሴ 1993ዓ.ም አቶ መለስ ዜናዊ ከጋዜጠኛ ሴኮቱሬ ስለጉዳዩ ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ አስገራሚ ነበር። ሴኮ « ከወንድሞ ጋር በተያያዘ የሚነሳ ነገር አለ፤ ስለጉዳዩ የሚሉት ነገር ይኖራል?» ብሎ ላቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ « በመጀመሪያ ደረጃ ወንድሜን ያገኘሁት ከአስር አመት በኋላ በእናታችን የቀብር ስነስርአት ላይ ነው። አዲስ አበባ እንደገባን ካገኘሁት በኋላ አግኝቼው አላውቅም። የተባለውን ጉዳይ በተመለከተ እነደሰማሁ ከዚህ ተግባር እንዲታቀብ ነግሬው ነበር» አሉ። የአቶ መለስ ምላሽ እርስ በእርሱ የሚጋጭ ነበር፤ “አግኝቼው አላውቅም” ካሉ በኋላ መልሰው ደግሞ “ከዚህ ተግባር እንዲታቀብ ነግሬው ነበር” አሉ። ሌላው ነጥብ ወንድማቸው ኒቆዲሞስ በዘረፋ ወንጀል ተሰማርቶ እንደነበር ማመናቸውን በግልፅ አስቀምጠዋል። ኒቆዲሞስ ዜናዊ በአቋራጭ ዘርፎ ሚሊየነር ሆነ። እጅግ አምባገነን ባህርይ የተጠናወተው ሰው ነው። ማን እንዳስታጠቀው የማይታወቅ ማካሮቭ ሽጉጥ አለው። በቅሎ ቤት አካባቢ በሚገኘው “ሃረግ” መዝናኛ ያዘወትር ነበር። በሴተኛ አዳሪዎች ላይ ሽጉጥ እየመዘዘ ፍዳቸውን ያሳይ ነበር። ማንም አይጠይቀውም። ሲጠቃለል፥ ከጥቂት ወራት በፊት በመለስ ዜናዊ ቤተሰብ ዙሪያ በኢ.ቲ.ቪ አንድ ፕሮግራም ተሰርቶ ነበር። «ጠላ ሻጭ» ወዘተ ተብለው የቀረቡት ከአቶ መለስ ጋር በአባት የሚገናኙ ናቸው። ኒቆዲሞስና መለስ ግን የአንድ እናትና አባት ልጆች ናቸው። ስለሚሊየነሩ ኒቆዲሞስ ምንም የተባለ ነገር የለም። ለምን እሱ በፕሮግራሙ አልተካተተም?…ምክንያቱ ደግሞ ግልፅ ነው። ዘርፎ ሃብታም እንደሆነ በማስረጃ ስለተጋለጠና ህብረተሰቡ ጉዳዩን ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ነው።
ማቆሚያና ገድብ ያጣው የፖለቲካ እስረኞቹ ስቃይ!
በዛሬው አጭር ፅሁፌ ላተኩረው የምፈልገው በፖለቲካ እስረኞች ላይ እየደረሰ የሚገኘው ስቃይ ላይ ነው። ገዢዎቻችን ምንም አይነት የፖለቲካ እስረኛ የለም ሲሉ ይደመጣሉ። ይህ ምን ያህል እውነት ነው የሚለውን ለአንባቢዎቼ እተወዋለሁ። የቃሊቲ ወህኒ ቤት ማረሚያነቱ ምን ላይ እንደሆነ ስላልገባኝና ስላልታየኝ ጭምር ወህኒ ቤት ለማለት ተገድጃለሁ። ስለዚህም የቃሊቲ ወህኒ ቤት የሚለውን ቃል እጠቀማለሁ።
የፖለቲካ እስረኛ የሆኑት ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ፣ አቶ ክንፈ ሚካኤል ደበበ (አበበ ቀስቶ) ፣ አቶ በቀለ ገርባና አቶ ኦልባና ሌሊሳን ባደረባቸው ህመም ከዝዋይ ማረሚያ ቤት ሪፈር ተፅፎላቸው በቃሊቲ ወህኒ ቤት ይገኛሉ። ሆኖም በቃሊቲ ወህኒ ቤት በኩል ተገቢውን ትብብር እየተደረገላቸው እንዳልሆነ የእስረኛ ቤተሰቦች አስታውቀዋል። ከጅምሩም የፖለቲካ እስረኞቹን ወደ ዝዋይ ማዘዋወር ያስፈለገው ቤተሰቦቻቸው ፣ ወዳጆቻቸውና አድናቂዎቻቸው እንደልብ እንዳይጠይቋቸው በማድረግ የፖለቲካ እስረኞቹ ላይ የሞራል ስብራት ለማድረስ ነው። ይህ አልበቃ ብሎ ደግሞ የፖለቲካ እስረኞቹ ተገቢውን ህክምና እንዳያገኙ እየተደረገ ይገኛል። የትኛውም እስረኛ ህክምና የማግኘት መብቱ የተጠበቀ ቢሆንም እስረኛው የፖለቲካ እስረኛ ከሆነ ግን ይህ መበቱን ይነፈጋል። ለዚህ ደግሞ ተጨባጭ ማስረጃ ካስፈለገ የጋዜጠኛ ውብሸት ታዬን እና አቶ ክንፈሚካኤል አበበን (አበበ ቀስቶ) ሁኔታ ማንሳት ይቻላል።
ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ከዝዋይ ማረሚያ ቤት ሪፈር ተፅፎለት ወደ ቃሊቲ ወህኒ ቤት ቢዛወርም የቃሊቲ ወህኒ ቤት ምንም ህክምና ሳያደርግለት ወደ ዝዋይ ማረሚያ ቤት እንዲመለስ ወስኗል። ውበሸት ባልታወቀ ምክንያት ያንኑ ዕለት ምሽት ወደ ቃሊቲ ወህኒ ቤት እንዲመለስ መደረጉን እና ተመልሶ የመጣበት ምክንያት እንደማይታወቅ የውብሸት ታዬ ባለቤት ወ/ሮ ብርሃኔ ተስፋዬ ለኢትዮ-ምኀዳር ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል አስታውቃለች። ይህን ሁላ ማጉላላት ለምን አስፈለገ? የዝዋይ ማረሚያ ቤት ሪፈር ፅፎለት የቃሊቲ ወህኒ ቤትስ ለምን ህክምናውን ሊነፍገው ፈለገ? እኮ ለምን? የከፋ ነገር ቢመጣስ ተጠያቂነቱን ማን ሊወስድ ነው? እነዚህ ሁላ አፋጣኝ መልስ የሚሹ ጥያቄ ናቸው።
የቃሊቲ ወህኒ ቤት ወደር የለሽ ግፉን መፈፀሙን በጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ብቻ አላበቃም። በመኢዴፓ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበሩት አቶ ክንፈሚካኤል አበበ (አበበ ቀስቶ) ላይም በተመሳሳይ ግፍ ተፈፅሟል። ፓርቲው እና ቤተሰቦቻቸው ለኢትዮ-ምኀዳር ጋዜጣ አቶ ክንፈ ሚካኤል በጠና ታመው ህክምና አለማግኘታቸውን አስታውቀዋል።
ይህ ሁላ እየተደረገ የሚገኘው በቃሊቲ ወህኒ ቤት አስተዳዳሪዎች ነው። ይህ ድርጊት ከማንአለብኝነትና ከእብሪት የሚመነጭ ነው። ከዛም ባለፈ የእኛም ድርሻ አለበት። ይህ ሁላ ግፍ እየተፈፀመ ሰምተን እንዳልሰማን ፣ በእኛ ወይ በእኔ ላይ ካልደረሰ ምን አገባኝ ስለምንል መሆኑን መርሳት የለብንም። እነዚህ የፖለቲካ እስረኞች ከመቼውም ጊዜ በላይ የእኛን ድምፅ ይሻሉ። ድምፃችንን ከፍ አድርገን ልናሰማ ይገባል!
በቀጣዩ የኢህአዴግ ጉባኤ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስተር ከህወሓት እንዲሆን ጥረት ይደረጋል (ዶር ቴድሮስ አድሐኖም)።
ህወሓቶች ለሁለት ተከፍሎው የደብረፅዮን (የአዲስ አበባ) ና የአባይ ወልዱ (የትግራይ) ቡድን ተሰይመው ሲነታረኩ መቆየታቸው ይታወቃል። ከወራት በፊት ጀምሮ ደግሞ ሁለቱም ቡድኖች ‘ለማስታረቅ’ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ጠቅሼ ነበር።
አሁን አቶ ስብሃት ነጋ (ከቢተው በላይ ጋር በመሆን) ሁለቱም ባላንጣ ቡድኖች ‘ማስታረቅ’ ችለዋል። ዕርቁ የተፈፀመው በነ ደብረፅዮን ቡድን አሸናፊነት ነው። የነ አባይ ወልዱ ቡድን በመሸነፉ ምክንያት አቶ አባይ ወልዱ ከነ ስብሃት ነጋ ጋር እንዲስማማ ምክንያት ሁነዋል። የነ አባይ ቡድን የተዳከመበት ምክንያት ለሁለት በመከፈሉ ነው። አቶ አባይ ወልዱ ከአቶ ቴድሮስ ሐጎስ፣ ኢያሱ ተስፋይ፣ ተክለወይኒ አሰፋ፣ ኪሮስ ቢተው፣ በየነ መክሩ ወዘተ መግባባት ባለመቻሉ ከአዲስ አበባዎቹ ጋር ለመስማማት ተገደዋል።
በስምምነቱ መሰረት ህወሓት በአዲስ አበባዎቹ ፕላን ይጓዛል። በ’መለስ ራእይ’ ስም ህዝብ መጀንጀን ይቀራል። በሙስና ሰበብ ባለስልጣናት ማሳሰርም ይቀራል። ከአሁኑ በኋል ከፍተኛ የህወሓት ባለስልጣናት በሙስና ሰበብ አይታሰሩም። በቀጣዩ የኢህአዴግ ጉባኤ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስተር ከህወሓት እንዲሆን ጥረት ይደረጋል (ዶር ቴድሮስ አድሐኖም)።
ይህ የህወሓቶች የ’ዕርቅ ሂደት’ ባብዛኛው የብአዴን አመራር አባላትና በተወሰኑ የኦህዴድ መሪዎች ቅሬታ አስነስተዋል። ህወሓቶች ለመታረቅ የተገደዱበት ምክንያት በተቃዋሚዎች ስልጣን እንዳይነጠቁ በመስጋት ነው። ዓረና ፓርቲ ለህወሓቶች ትልቅ ስጋት በመፍጠሩ ነው። የፀጥታ ሃይሉ መፈራረስም ሌላ ህወሓቶች ያስደነገጠ ጉዳይ ነው። በዕርቁ ሂደት ከፍተኛ ሚና የተጫወተው አቶ ስብሃት ነጋ ነው።
የዕርቅ ሂደቱ በኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ከፍተኛ አለመግባባት ሊፈጥር ይችላል። ኢህአዴግ በዉስጥ ለውስጥ የስልጣን ሹክቻ ምክንያት የሚዳከምበት አጋጣሚ መፈጠሩ አይቀርም። ዕርቁ ግዝያዊና ስትራተጂካዊ ብቻ ነው። የታረቁት መግባባት ስለ ፈጠሩ ሳይሆን የጋራ ጠላትን ለመከላከል ብቻ ነው።
ሰኞ 23 ዲሴምበር 2013
ሰማያዊ ፓርቲ በአስቸኳይ የግንፍሌውን ጽ/ቤት እንዲለቅ ትእዛዝ ተሰጠ
ሰማያዊ ፓርቲ ግንፍሌ አከባቢ የሚገኘውን እና በጽ/ቤትነት የሚጠቀምበትን ቢሮ በዛሬው እለት ከሰኣት በኋላ አቶ ሄኖክ የተባሉ አከራዩ ከ አራት ትግሪኛ ተናጋሪ ግለሰቦች ጋር በመምጣት ቤቱን ለነዚህ ግለሰቦች ስለሸጥኩላቸው እንድትለቁላቸው ሲል አሳስቧል:; ቤቱን ገዛሁት የሚለው ትግሪኛ ተናጋሪ ግለሰብ ቤቱን የገዛሁት ስለሆነ በአስቸኳይ እንድትለቁ ካልሆነ የራሴን እርምጃ እወስዳለሁ ሲል አመራሮቹ ላይ ዝቷል::
ይህ ገዛሁት የሚለው ግለሰብ በማይመለከተው ጉዳይ በመግባት ከዚህ በፊት ልቀቁ ተብላችሁ በተደጋጋሚ እንደተነገራችሁ መረጃው አለኝ በማለት በአመራሮቹ ላይ ቁጣ የተቀላቀለበት ዛቻ በመዛት ሄዷል:; በወቅቱ ይዞት የነበረው ተሽከርካሪ ጥቁር የደህነንት መኪና የሆነች ቶዮታ ኤክስኪዩቲቭ ሲሆን የታርጋ ቁጥሩም ኮድ 2-89176 የሆነ ነው::
ሰማያዊ ፓርቲ ከዚህ ቀደም በመነን አከባቢ ተከራይቶት የነበረውን ጽ/ቤት ገና ሳይገባበት በዝግጅት ላይ እንዳለ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ፖለኢሶች እና ቅጥረኞች ተባብረው በተቀናጀ አፈና ቢሮውን መንጠቃቸው ይታወቃል:: የነጠቁትንም ቢሮ ለካድሬያቸው በመስጠት ፔንሲዎን ከፍቶ እየሰራበት ይገኛል::
:EthiopianReview
እሑድ 22 ዲሴምበር 2013
በደቡብ ሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ለማስወጣት የሚደረግ እንቅስቃሴ የለም ተባለ
በደቡብ ሱዳን የተነሳውን የእርስ በርስ ግጭት ተከትሎ በአገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የደህንነታቸው ሁኔታ አሳሳቢ ቢሆንም መንግስት እስካሁን እርምጃ እየወሰደ አለመሆኑ ታወቀ።
የኢሳት የጁባ ወኪል እንደገለጹት አብዛኛው አገሮች ዜጎቻቻውን እያወጡ ነው ። ኬንያና ኡጋንዳ አውቶቡሶችን
በመላክ ፣ አሜሪካና እንግሊዝ ደግሞ ወታደራዊ አውሮፕላኖችን በመላክ ዜጎቻቻውን እያወጡ ነው። የኢትዮጵያ አየር
መንገድ ንብረት የሆነ አውሮፕላን ጁባ ማረፉን ተከትሎ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ለመመለስ ተስፋ
አድርገው የነበረ ቢሆንም፣ አውሮፕላኑ ግን ቻይናዎችን ብቻ ጭኖ መመለሱ ታውቋል። ኢሳት ከአየር መንገዱ ለማረጋገጥ
እንደቻለው የቻይና መንግስት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ቻርተር አውሮፕላን በመከራየት በነዳጅ ማውጣት ስራ ላይ
የተሰማሩ ዜጎቹን ወስዷል።
እንዲሁም ለሽምግልና ጁባ የሄዱትን የኢትዮጵያን ባለስልጣናት በማሳፈር ጁባ ያረፈ አንድ የኢትዮጵያ አየር
መንገድ አውሮፕላን፣ ባለስልጣኖችን ካወረደ በሁዋላ ትኬት ቆርጠው ለመውጣት ይጠባበቁ የነበሩ ኢትዮጵያውያንን ሳይጭን
ባዶውን ተመልሷል። ኢትዮጵያውያኑ የኬንያንና የኡጋንዳን አየር መንገዶችን ለመጠቀም ጥረት እያደረጉ ቢሆንም፣ አየር
መንገዶቹ ከፍተኛ ዋጋ በመጠየቃቸው ትኬቶችን ለመግዛት አልቻሉም።
ኢሳት ለማረጋገጥ ባይችልም ሶሰት ኢትዮጵያውያን ሴቶች መደፈራቸውን የሚያመለክት ዜና ደርሶታል። አንዳንድ
ኢትዮጵያውያንም ንብረታቸውን ተዘርፈው በጁባ መንገዶች ላይ ያለ ደጋፊ ሲዞሩ እንደሚታይ ወኪላችን ገልጿል።
የኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ጅቡቲ እና ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ላለፉት ሁለት ቀናት በጁባ ተገኝተው
ሁለቱን ሀይሎች ለመሸምገል ጥረት እያደረጉ መሆኑም ታውቋል። ደ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም ሁለቱንም ሀይሎች ለማቀራረብ
ከፕሬዚዳንቱ ጥሩ ምላሽ ማግኘታቸውን ገልጸዋል።
ቦር የተባለው አካባቢ በአማጽያን እጅ የወደቀ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ድንበር በሆነው አኮቦ በትናንትናው እለት
ጦርነት ተከፍቷል። ዛሬ ደግሞ ማላኪ፣ ዋው እና ባንቲዩ በተባሉት አካባቢዎች ጦርነት ተከፍቷል። ባንቱዊ የተባበሩት
መንግስታት ድርጅት ጽህፈት ቤት የሚገኝበት ሲሆን፣ በርከታ የዲንቃ ተወላጆች በጽህፈት ቤቱ ግቢ ውስጥ መግባታቸው
ታውቋል። በጁባ የኑዌር ተወላጆች ከዲንቃ ጎሳዎች ጥቃት ሊሰነዘር ይችላል ብለው በተመድ ጽ/ቤት ውስጥ ሲጠለሉ፣
በቤንቲዩ ደግሞ በተቃራኒው ዲንቃዎች ተጠልለዋል።
ፕሬዚዳንት ኦባማ አዲሲቷ አገር ወደ እርስ በርስ ጦርነት ልትገባ እንደምትችል አስጠንቅቀዋል። እስካሁን ባለው አሀዝ ከ500 ያላነሱ ሰዎች ተገድለዋል።
ቅዳሜ 21 ዲሴምበር 2013
አድርባይነት (ለጥቅም ሕሊናን መሸጥ)
ከማርቆስ ዐብይ
ኢትዮዽያ ሀገሬ ሞኘ ነሸ ተላላ፣
የሞተልሸ ቀርቶ የገደለሸ በላ፣
የሞተልሸ ቀርቶ የገደለሸ በላ፣
አድርባይነት
ቀለል ባለ አገላለጽ ማስመስል ወይም ለጥቅም ሲባል ሕሊናን መሸጥ እንደማለት ነው፣፣ ይህ እኩይ ባሕሪ በኢትዮጵያ
ታሪክ ውስጥ ቀላል የማይባል እድሜ አስቆጥሯል የሩቁን ትተን የቅርቡን ከጣሊያን ወረራ ቦኋላ ያለውን አሁን
እስካለንበት ጊዜ ያለውን ለማየት ብንሞክር እንኳ በጣም ብዙ ነገሮችን መታዘብ እንችላለን።
ጣሊያን
ኢትዮጵያን በግፍ በወረረበት ወቅት የክርስቶስን ወንጌል ይሰብኩ ከነበሩ የሐይማኖት አባቶች መካከል በጥቅማ ጥቅም
የተደለሉ ጥቂት የሐይማኖት አባቶች በየአውደ ምሕረቱ ለምዕመናን ከመጽሃፍ ቅዱስ ላይ ኤሳው ለምስር ወጥ ሲል
ብኩርናውን አሳልፎ ለወንድሙ ለያዕቆብ መሸጡን በመጥፎ ተምሳሌትነት እንዳላስተማሩ ሁሉ ራሳቸው ለቁራሽ እንጀራ ሲሉ
ሕሊናቸውን በመሸጥ ከወራሪው ከጣሊያን ጎን በመሰለፍ ለምዕመናኑ በሃሰት በእግዚአብሔር ሃምሳል ኢትዮጵያን ለመታደግ
የመጣ ነው በማለት ሕዝቡ ወራሪው ጣሊያንን አሜን ብሎ እንዲቀበል ያግባቡ ነበር።
በዚህ የወረራ ዘመን
የንጉሠ ነገሥቱ የቅርብ ባልሙዋል ከነበሩ መኩዋንንቶች እና መሳፍንቶች መካከል ሳይቀር ለጣሊያን ያደሩ ነበሩ፣፣
እነዚህ ሹማምንቶች ህዝቡ ተቃውሞውን በማቆም ይዘውለት የመጡትን እውቀት እና ስልጣኔ በመቅሰም ሀገሩን ያለማ ዘንድ
ሰዎቹን በትዕግሰት እንዲጠብቃቸወ በሀሰት ይሸነግሉት ነበር።
ታዋቂው ደራሲ አቤ ጎበኛ የረገፉ አበቦች
በሚል ርዕሰ ያሳተሟት ልብ ወለድ መፅሃፍ ውስጥ ስለነዚህ ከዳተኞች የአድርባይነት መጠን ማሳያ የሚሆን አንድ ታሪከ
ያሰነብቡናል፣ ይህውም በዚያ ዘመን የነበሩ በአካባቢው ህብረተሰብ ዘንድ ትልቅ ስም ያላቸው አንድ ሰው ነበሩ እኚ
ሰው ባለቤታቸው ሲወልዱ ትልቅ ግብዣ አዘጋጅተው ብዙ ሰው ይጋብዛሉ ከተጋባዡቹ መካከል የጣሊያን ወታደሮች የክብር
ቦታ ተዘጋጅቶላቸዋል በግብዣው ሰፍራ ላይ ተገኝተዋል አሳላፊዎች ሰውን ለማስደሰት ከወዲህ ወዲይ ይራወጣሉ በዚህ
መሀል ከክብር እንግዶች አጠገብ ተጎልተው የነበሩት ጋባዠ በእጅ ምልክት ሰውን ፀጥ እንዲል በማድረግ የልጃቸውን ሰም
በታዳሚው ፊት ለማውጣት እንደሚፈልጉ ገለፁ በማሰከተልም ልጄን ሮማ (ROMA) ብያታለሁ አሉ አድናቆትና ጭብጨባ
የክብር እንግዶች ካሉበት አካባቢ ብቻ ቀረበ የተቀረው ተጋባዠ እነሱን ተከትሎ አጨበጨበ እንጂ ሰለሰሙ የሚያውቀው
ነገር ስለሌለ ነገሩ እሰከሚገለፅለት ድረሰ አላወቀም ነበር፣ በመቀጠልም ሮማ አሉ በአሰመሳይነት ኩራት የጌቶቻችን
ሀገር ዋና ከተማ ነች ብለው ተቀመጡ፣ ሰው ሕሊናውን ሲሸጥ መቼም እራሱንብቻ ሳይሆን ቤተሰቡንም ለመሰዋትነት
ያቀርባል።
መቼም እንዳያልፈው የለምና ያ የመከራ ጊዜ አለፈና በአርበኞች ፅናትና ተጋድሎ ዘመቻው በድል
ተጠናቀቀ ፣ ወራሪው ጣሊያን በኩራት የተመላለሰባቸው እነዛ ጎዳናዎች በሃፍረት አንገቱን አቀርቅሮ የሞተው ሞቶ
የተረፈው በደመነፍሰ ተራወጠባቸው በግፍ የወረራትን ሃገር በሃፍረት ጥሉዋት ፈረጠጠ ፣ እነዛ ወራሪውን አዝለው
ህዝቡን ሲያሰጨንቁት የነበሩት ሆዳደሮች ግን ያዘሉትን ያህል እንኩዋን ሊያዝላቸው ቀርቶ እጃቸውን ይዞ የሸሸበት
ያህል እንኩዋን ይዟቸው ሊሄድ አልወደደም እንደ ፓሰታ መቀቀያው ዕቃ የትም ጥሏቸው ሄደ እንጂ፣ እነዚ ከመጣው ጋር
እንደ ሴተኛ አዳሪ ወዳጅ መሰለው መቅረብ እንደ መልካም በሐሪ የተጣባቸው ግለሰቦች አርበኞች ወደ ከተማ ሲገቡ
ፀጉራቸውን አሳድገው ተቀላቀሉዋቸው እኛ ልጃቸውን ሮማ ብለው የሰየሙ ግለሰብም የልጃቸው ሰም ላይ ’ን’ በመጨመር
ሮማን በማለት አይናቸውን በጨው አጥበው ከአርበኞች ጋር ላይ ታች ሲሉ ያያቸው የሀገሬው ሰው በትዝብት እጁን አፉ
ላይ ጭኖ በመገረም ነበር የሚያያቸው ይሉናል አቤ ጎበኛ።
እሰካሁን ለመቃኝት የሞከርነው ህሊናቸውን ሸጠው
ታሪክ አበላሸተው ወደማይቀረው ሞት ሰለነጎዱ ሰዎች ነው፣ አሁን ደግሞ በህይወት ያሉ ነገር ግን ህብረተሰቡ አፈር
ካለበሳቸውና ሃውልታቸው ላይ ሆዳደር ብሎ ካተመባቸው ግለሰቦች መካከል ለናሙና አንዱን በመውሰድ እናወጋለን ከዛ
አሰቀድመን ግን እንደመሸጋገሪያ ይሆነን ዘንድ ከጥቂት አመታት በፊት ጠቅላይ ምኒሰትር መለሰ ዜናዊ የሀገር
ሸማግሌዎችን ሰብሰበው ሲያወያዩ አንድ የሃይማኖት አባት የተናገሩትን አሰገራሚ ንግግር እናሰቀድም እንዲህ ነበር
ያሉት “በአባቶቻችን እሰከ አሁን ድረስ ሲነገር የቆየው ከወደ ሰሜን በመነሳት ኢትዮዽያን በጠነከረ አንድነት
የሚያሰተዳድራት ንጉስ ይመጠል የተባለው ትንቢት ተፈፀመ ይህውም አንተ ነህ ብለው ጣታቸውን ወደሰብሳቢው ጠቆሙ”
እሳቸውም በትዝብት ፈገግ ብለው ምላሸ ሰጡ፣ እኝህ አሰተያየት ሰጪግለሰብ ሀገሪቱ ቋንቋን መሰረት ባደረገ ክልል
ተሸንሸና እንደባቢሎን ሰዎች እርስ በእርሰ መግባባት እንዳልተቻለ ሳያውቁ ቀርተው አይደለም ይህን ባሉበት ወቅት
ሰዎች በዘመቻ መልክ ክልላችሁ አይደለም እየተባሉ የዘሩትን ሳይሰሰቡ ከየቦታው የሚፈናቀሉበት ውቅትም ነበር ይህንንም
አሳምረው ያውቃሉ ነገር ግን እሳቸው እያሰሉ ያሉት ይህን መናገራቸው እንደውለታ ተቆጥሮላቸው ወደ ቅያቸው ሲመለሱ
ስለሚደረግላቸው ከንቱ ውዳሴ ወይም ስልጣን ብቻ ነው፣ ይህን እዚህ ላይ ቋጭተን እሰኪ በአዲሰ መስመር ላይ እላይ
ወደጀመርነው አንድ አስገራሚ ሰው እንመለስ።
እኚ ሰው የኮሚኒኬሸን ጉዳዮች ሚንስትር ዴእታ አቶ ሽመልሰ
ከማል ይባላሉ፣ አቶ ሽመልሰ በመጀመሪያ ኒሻን የምትባል የግል ጋዜጣ በማቋቋም የመንግስትን ስህተት እየነቀሱ በጣም
ጠንከር ባለ አገላለፅ ይተቹ ነበር ከዚህ ጎን ለጎን ሌላው የሚታወቁበት ደግሞ መንግስት በውሃ ቀጠነ የሀሰት ክሰ
ጋዜጠኞችን ፍርድ ቤት ሲያቆማቸው እሳቸው ባላቸው የህግ እውቀት በነፃ ፍርድ ቤት በመቆም ለንፁሃን ጋዜጠኞች
ሸንጣቸውን ገትረው በመከራከራከረቸው ነበር ፣ እኚህ ስው ታዲያ ትንሽ ጠፋ ብለው ከራርመና ሲመለሱ ባንዴ ጎፈር
ሆነው ሲያወግዙት የነበረው መንግስት ባለስልጣን በመሆነ ከኔ በላይ ታማኝ የለም ብለው ቁጭ አሉ፣ ያኔ በደጉ ጊዜ
ከህሊናቸው ጋር በነበሩ ሰአት ሲሟገቱላቸው የነበሩ በቅርብ የሚያውቋቸውን ንፁሃን ጋዜጠኞችን መሰረተ ልማት
ለማውደምና የመንግሰት ባለስልጣናት ለመግደል ከአሸባሪዎች ጋር ሲያሴሩ እጅ ከፍንጅ ያዝናቸው ብለው በአደባባይ ህጉን
እያወቁት ከፍርድ ቤት ቀደመው ፍርድ አስተላለፉ፣ እነዚያ ንፁሃን ጋዜጠኞችም ያለጥፋታቸው የእድሜአቸውን እኩሌታ
ዘብጥያ እንዲያሳልፉ የፖለቲካ ውሳኔ ተወሰነባቸው እናቃሊቲ ተወረወሩ፣ እኚህ ግለሰብ መንግስት እራሱን አሻሸሎ ነው
የተቀላቀሉት እንኩዋን እንዳይባል እርሳቸው ስልጣን ላይ ከመውጣታቸው በፊት የነበረው የጋዜጠኞች የመሰራት ነፃነት
አሁን ካለው ዘጠና በመቶ ይሻል ነበር ታዲያ ምን ነካቸው ከተባለ መልሱ ለጥቅም ሲባል ሕሊናቸውን ሸጡ ይሆናል።
ሰው
ሕሊናውን በጥቅም ከተያዘ ዕውቀትና ስልጣን መጠሪያው ከመሆን የዘለለ ፋይዳ የለውም ፣ በጣም የሚገርመው እኚህ ሰው
መንግስትን በመወከል በተደጋጋሚ የተናገሩዋቸውን ንግግሮች አለቆቻቸው ውድቅ በማድረግ ሸመልስ ያለው ውሸት ነው
በማለት በአደባባይ ሲያዋርዱአቸው በፊት ለሎች ሲከራከሩ የነበሩ ሰው እንዳልነበሩ ሁሉ በጥቅም ስንሰለት እግር
ተወርቸ ታሰረው እራሳቸውን እንኩዋን መከላከል አቅቷቸው ሲወራጩ በመታዘብ አይተናል።
ባጠቀላይ ህሊና ትንሹ
እግዚአብሔር ነው ይባላል መልካም ስንሰራ የሚያበረታታን መጥፎ ሰንሰራ ደገሞ እንድንፀፀተና ዳግም እንዳንሰራ
እረፍት የሚነሳን ታድያ ሰው ይህንን ትልቅ ነገር አጥቶ ሀብትና ዝናን ቢሰበሰብ እንዴት የዓይምሮ ሰላም ሊያገኝ
ይችላል?
“ሰው እግዚአብሔርን አጥቶ አለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ምን ይጠቅመዋል” እንዳለው መፀሃፍ ቅዱስ፣
ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ይጠብቅ!
ዓርብ 20 ዲሴምበር 2013
ከሚኒስትርነት ወርደው በአምባሳደርነት መሾማቸውን አያውቁም ነበር ተባለ
የማዕድን ሚኒስትር በመሆን ባለፉት ሶስት ዓመታት ያገለገሉትት ወ/ሮ ስንቅነሽ እጅጉ ከኃላፊነታቸው ተነስተው ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ሲሾሙ ምንም የሚያውቁት ነገር እንዳልነበር የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።
ከ16 ዓመታት በላይ በማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስቴር ውስጥ ከኤክስፐርትነት እስከ ሚኒስትር ዴኤታ ባሉት የሀላፊነት ቦታዎች ሲሰሩ የቆዩትና እ.ኤ.አ በጥቅምት ወር 2010 የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተለያየ አደረጃጀት ይዞ ለሁለት ሲከፈል የማዕድን ሚኒስትር በመሆን በአቶ መለስ ዜናዊ አቅራቢነት የተሾሙት የኦህዴድ አባሏ ወ/ሮ ስንቅነሽ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ሳይነገር ከአማራው ክልል ፕሬዚደንት አቶ አያሌው ጎበዜ ጋር ባለሙሉ አምባሳደር በመሆን በፕሬዚደንት ሙላቱ ተሾመ መሾማቸው ይታወሳል፡፡
ምንጮቻችን እንደተናገሩት ወ/ሮ ስንቅነሽ በአቅም ችግር ከዚህ ቀደም የተገመገሙ ሲሆን ከሃላፊነታቸው ሲነሱ እንደማንኛውም ሰው በራዲዮና በቴሌቪዥን ከመስማታቸው ውጪ በቀጥታ የተነገራቸው ነገር አልነበረም፡፡
ወ/ሮ ስንቅነሽ የአዳሚ ቱሉ የኬሚካል ድርጅትና የኢትዮጽያ ማዕድን ልማት ድርጅትን በቦርድ ሰብሳቢነት፣የመንገዶች ባለስልጣን፣የኢትዮጽያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ፣የመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አባልም ነበሩ፡፡
ወ/ሮ ስንቅነሽ ግልጽነት ከጎደለው የጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ካቢኔ በይፋ ከተነሱ ሴት ሚኒስትሮች መካከል ከወ/ሮ አስቴር ማሞ የቀጠሉ ናቸው፡፡
የማለዳ ወግ … ስደተኛው ዘፋኝ በሳውዲ በርሃ …(ከጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ)
እለተ ቅዳሜ በማለዳው ያቀናሁት በያንቦና በጅዳ መካከል በምትገኝ የዋዲ በርሃ ዙሪያ ነበር ። አየሩ ተቀያይሯል ፣ ከዚህ ቀደም ወደዚህ ቦታ ሳመራ እንደ እሳት ነበልባል የሚጋረፈው ሙቀት ዛሬ የለም ። ለስራ ወዳቀናሁበት በድቅድቁ በርሃ ላይ በተሰራው የድንጋይ መከስከሻ ፋብሪካ እንደደረስኩ አንድ መልከ መልካም ወንድም የግቢውን በር ከፍቶልኝ ለመግባት ወዴት መሄድ እንደምፈልግ የጠየቀኝ ወጣት ሃበሻ ለመሆኑ ቅንጣት ያህል አልተጠራጠርኩምና የሚጠይቀኝን ትቸ እኔው ጠየቅኩት “ሃበሻ ነህ! ” ነበር ያልኩ ። ይህን ስጠይቀው እንደ መሽኮርመም እና እንደመሳቅ እያለ “አዎ ሃበሻ ነኝ ፣ ኢትዮጵያዊ! ” ሲል መለሰልኝ! ብዙ ሃበሾች አላችሁ? ስል ጥያቄየን ቀጠልኩ “አዎ አምስት ሃበሾች አለን! ” አለኝ ፈገግ እያለ … በአሻጋሪ መምጣቴን የሚጠብቅ የፋብሪካው ሃላፊ “አስገባው ፣ አስገባው! ” ሲል ፍልቅልቁ ወንድም ተደናግጦ በወራጅ ብረት እንደነገሩ የተዘጋውን የግቢ ብረት አጥር ከፍቶልን እኔና የስራ ባልደረባ ረዳቴ የፊሊፒን ዜጋው ግላዲ ወደ ግቢው ስንገባ በመስኮት በኩል አንገቴን ወጣ አድርጌ ስራየን ከዋውኘ እንደማገኘው ቃል ገብቸለት ወደ ውስጥ ገባሁ …
ሱዳኑ
የፋብሪካ ሃላፊ ከድንጋዩ መፍጫ የቅርብ ርቀት ካለው ጋራጅ አጠገብ ከተሰራች ባለሁለትና ሶስት ዛኒጋባ ቆርቆሮ ቤት
ወጥቶ ሞቅ ያለ ሰላምታ ሰጥቶ ተቀበለን ። ድንጋዩን እየከሰከሰ ጠጠር የሚያደርገው ፋብሪካ ነጭ አመድ ወደ ሰማይ
እየተፋ የጓራል …ዲንጋው እየተፈጨ ጠጠር እየተሰራ መሆኑ ነው! የመንገድ መደልደያ ፣ የምንገድ መጥረጊያ እና
የመንገድ ማለስለሻ ዳምጤ ከባባድ የኮንስትራክሽን መኪኖችን ጨምሮ ጥገና የሚያስፈልጋቸው መኪኖች ጋራጁን
አጨናንቀውታል … ከጋራጁ ጀርባ ደግሞ እኛ መመርመር ያከብን የተሽከርካሪ ጎማ መአት ተከምሯል። …አምስት የተባሉትን
ሃበሾች አግኝቸ እስካዎጋቸው ቋምጫለሁ …የፊት የፊቱን እያስቀረብኩ ለፊሊፒኑ አጋሬ ምን መስራት እንዳለበት
በማሳወቅ ስራውን አጣድፊ ግን በአግባቡ መርምሬ እንደጨረስኩት ሌሎች ሁለት ሃበሾች ሃበሻ ወንድማቸው መምጣቴን
ሰምተው ኖሮ በፈገግታ እየተፍለቀለቁ መጥተው ሰላምታ ተለዋዎጥን …
ሃበሻ ዝር በማይልበት በርሃ ያገኙኝን
ወንድም እነርሱም ሊያስተናግዱ ሊያጫውቱኝ እንደቋመጡ አልጠፋኝም … በተንቀሳቃሽ ኮንቴነር በፋይዚት ግሩም ሆና
የተሰራቸው ማረፊያ ቤት ከጋራጁ የቅርብ ርቀር ትገኛለች ። አቧራ የጎረሰውን እጀን ሳልተጠብ በበርሃው ወዳገኘኋቸው
ወንድሞች ማረፊያ ቤት አመራሁ … ረመድ ረመድ እያልኩ ከመድረሴ ወንድሞቸ በደስታ እየተፍለቀለቁ ግማሽ መንገድ ላይ
ተቀበሉኝ ! ጠባቧ ቤት ማረፊያ ቤት ብቻ እንዳልሆነች ከበር የተደረደሩትን ጫማዎች ስመለከት ገባኝና ጫማየን አውልቄ
“ቤት ለእንቦሳ! ” ብየ ዘው ብየ ገባሁ… ቤቷ ጽድት ያለች ናት … ሶስት አልጋዎች በሶስቱ የቤቱ ማዕዘኖች ጥግ
ይዘው ተዘርግተዋል ። የተቀበሉኝ ወንድሞቸ ሶስት ሲሆኑ ዘግየት ብሎ ሌላ ወንድም ገባ … አምስተኛው ወንድም የት
እንዳለ ስጠይቅ እሱ ስራ ላይ እንደሆነ ገለጹልኝ። ሁላችንም የምናወራው ከአልጋዎች ላይ ተቀምጠን ነው ። እንደገባኝ
ከሆነ አልጋዎች ይተኛባቸዋል ብቻ ሳይሆን በመቀመጫነት ያገለግላሉ! … ጫዎታችን ከመጀመራችን በፊት እጀን ለመታጠብ
ውሃ ቢጤ ስጠይቅ ድምጹ ጎርነን ያለው “ሸዋንግዛው እባላለሁ!” ብሎ የተዋወቀኝ ወንድም በእጅ ከምትያዝ ማቀዝቀዣ
ውሃ ይዞ ወደ ” በር ላይ ላስታጥብህ! ” ብሎ ግማሽ ጎኔን ከበሩበወጣ አድርጌ እንደነገሩ ጣቶችን ውሃ አስነካሁ
ብል ይሻላል ፣ ብቻ ታጠብኩ ።
ወጋችን የጀመርነው በድፍኑ አበሻ ሁኘ እንጅ ማንነቴን የተረዳ ሰው የለም!
ብዙ የህይወት ልምዳቸውንና ስለስራቸው ስለተመለከቱት የቴክኒክ ስራየ ፣ ሱዳኑበሲጠራኝ ስለሰሙት የእንጀራ ስሜና
ስለ አጠቃላይ የሳውዲ ህይወት እንዳንፈራራ ፣ እንዳንደባበቅ ፣ እንደ መተዋወቂያ አወራን … ጋዜጠኛ መሆኔን ትንፍሽ
ሳልል “ራዲዮ ትሰማላችሁ ፣ ኢንተርኔት ፊስ ቡክ ትከታተላላችሁ? ” በማለት ደጋግሜ ጠየቅኳቸው! አዎንታቸወን
ገለጹልኝ ። ስሜን የእኔ ነው ሳልል ታውቁታላችሁ? ስላቸው አዎንታቸውን በዝርዝር ገለጹልኝ! ስገባ በር የከፈተልኝ
እያሱና የቀሩት ሁለት ያህሉ የፊስ ቡክ ጓደኛው እንደሆኑ በኩራት በመግለጽ በቅትቡ የለቀቃቸውን የራዲዮ መጠይቆች
እያነሱ የሚያውቁትን ሰው ስም ስላነሳሁላቸው በደስታ ብዙ አወሩኝ! … እንዲህ ጥቂት ከቀጠልን በኋላ ግን እነርሱ
እዚህ ስላደረሳቸው መንገድ መጠየቅ ጀመርኩ ! ሁሉም የሆነውን ሁሉ ሲያጫውቱኝ ጫፍጫፉን ያወጋኝ ታሪክ ሳበኝ! ”
አበባ ተሸልሜ በጭብጨባ የተሸኘሁ ዘፋኝ ነበርኩ !” ያለኝ ድምጸ ጎርናናው የሸዋንግዛው ታሪክ ልቤን ነካው … ብዙም
ሳልቆይ ግን የእውነተኛው አለም ማንነቴን ገላልጨ ሳጫውታቸው ነገሮት ተቀያየሩ! … በጣም ተገረሙ! ብዙ ተጫወትን …
ለዛሬ እንዳላደክማችሁ በሚል በሳውዲ በርሃ ስላገኘሁት ወንድም ትኩረቴን ላድርግና ላጫውታችሁ …
ሸዋንግዛው
እና ከቀሩት ጓደኞቹ ሃገር ቤት አይተዋወቁም ። ዳሩ ግን ድህነት ፣ የኑሮ ውድነት ፣ የማደግ የመመንደግ ፍላጎት
በቁንጮዋ ነዳጅ አምራች ሀገር በሳውዲ አንድ በርሃ ሳውዲ በርሃ ላይ አገናኝቷቸዋል ! … ከሁሉም ወንድሞች ይልቅ
ዘፋኙን ስደተኛ ሸዋንግዛውን እዚህ ያደረሰ መንገድ ለማወቅ ጓጉቻለሁ! እናም ላፍታ ከዘፋኙ ወንድም ጋር የሆድ
የሆዳችን እድሉን አገኝንና ላፍታ አወጋን … ከሸዋንግዛው ንጉሱ ይባላል ፣ እድሜው በአርባወቹ ውስጥ እንጅ ከዚያ
የማይዘል ዘፋኝ መሆኑን ሲያንጎራጉር ከተቀረጻቸው ድምጾች ብቻ ሳይሆነ የተለቀቀውን ነጠላ ዜማ ሰምቸ ለመረዳት ጊዜ
አልወሰደብኝም … “ዘመኑ የዘፋኝ ነው” በሚባልበት ዘመን ድምጸ መረዋውን ዘፋኝ ወደ ሳውዲ ምን አመጣው ? በሚል
ባለጉዳዩ ስደተኛ ዘፋኝ ጠየቅኩት … መልሶልኛል ….
ሸዋንግዛው ንጉሴ በቀድሞው የአርሲ ክፍለ ከሃገር ሎዴ
ኤዶሳ በሚባል አከቀባቢ በአንድ መንደር ተወለደ። የሙዚቃ ጥበብ ገና በብላቴና እድሜው የለከፈችው ሸዋንግዛው በሎዴ
አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ትምህርቱን ሲከታተል ጥበብ አብራው አደገች ። በሎዴ የትምህርይ
ቤት ኪነት ለመመረጠረም ተሰጥኦ ያደለው ተርገብጋቢ ድምጽ ተሰጥኦውን ደገፈው እናም የቀደሙትን ዜማ እያነሳሳ ሲለው
የራሱን እየገጠመና እያንጎራጎረ ህይወት በፈለገችው መንገድ ትጓዝ ዘንድ ሸዋ ብርታት አገኘ። ብዙም ሳይቆይ ታዳጊው
ሽዋንዳኝ ከትምህት ቤት ወደ ወረዳ ኪነት ከፍ እያለ ሄደ … ከወርቁ ቢቂላ ( በኋላ ከሃይሌ ገ/ስላሴ ጋር አለም
አቀፍ ሩጫን ይሮጥ ነበር) ታዳጊ እያለ የሙዚቃ ዝንባሌ ስለነበረው በአርሲ ሎዴ የወረዳ ኪነት አብረው እንደሰሩ ሸዋ
ሩቅ ተጉዞ ዘርዘር ያለ ትዝታውን በአስደሳቹ ፈገግ እያለ በአስደሳቹ ትዝታ ፈገግ እያለ አጫውቶኛል … ሸዋንዳንኝ
በወረዳው ኪነት ቡድን ተግቶ እየሰራ ባለበት ወቅትም ወደ ክፍለ ሃገር ኪነት ቡድን ለመምረጥ በተደረገ ውድድር
ከወረዳ ወደ አርሲ ክፍለ ሃገር ቢመረጥም የወረዳው ሃላፊዎች በቅንነት “ልጃችን አሰልጥለን አንሰጥም !” በማለታቸው
ወጣቱ በሙያው ርቆ የመሄድ ስሜቱ ተጎዳ ! እናም በብስጭት ወደ ውትድርና አለም ገባ ።
ሸዋንግዛው
ማንጎራጎሩን ባንድ በኩል በሌላ በኩል ሳይወድ በተጎዳ ስሜት ገፋፊነት የገባበትን የውትድርና ስልጠና ወሰደ። ቀን
ቀንን ሲወልድ ግን ውትድርናው ወደ ጦር ሜዳ ሳይሆን ወደ አሳደገው የሙዚቃ ጥበብ ዶለው ! በብስጭት የተጎዳኘው
የውትድርና ስልጠና እንደጨረሰ የባሌ ሸዌ የጦር እዝ ማዕከል የኪነት ቡድን አባል ለመሆን ጊዜ አልፈጀበትም ። በጦሩ
የኪነት ቡድን በመስራት ላይ እንዳለ የደርግን ስርአት የሚታገለው የኢህአዴግ ጦር ወደ ከተማዎች እየገፋ ሲመጣ
የኪነት ቡድኑ ወደ ሲዳሞ በመሄድ ሌላ ተጨማሪ የመከላከል ስልጠና እንዲያደርግ ሲታዘዝ ከጓዶቹ ጋር ስልጠናውን
ወሰደ። ከዚያም ድልድሉ ወደ ሞያሌ ሆነና ወደ ዚያው አመራ። በጭንቁ ቀን ያልተለየው የጥበብ አውሌ ማንጎራጎሩን
ስላላስቆመው እንቅስቃሴውን ያዩ የሰራዊቱ አባላት ሸዋንግዛው የደቡብ እዝ ኦርኬስትራ ቡድን እንዲቀላቀል ግፊት
አድርገው እንዲመረጥ ቢያደርጉም አሁንም የጦር አዛዡ ” ሸዋግዛውን ወደ ደቡብ እዝ አልለቀውም! ” በማለታቸው እድሉ
ተጨናገፈ። ይህም ሲሆን ዳግም እክል የገጠመው ዘፋኙ ወጣት ተስፋ አልቆረጠም። ሙዚቃው እንቢ ቢለው በልጅነት ወደ
ሚወደው ሌላ ሙያ አጋደለ። ባለበት ብርጌድ የእግር ኳስ ብቃቱን አስመስክሮ እግር ኳስ መጫወቱን በደስታ ተቀላቀለ !
በወቅቱ ኳሱም ተሳክቶለት ኮከብ ኳስ አግቢ በመሆን ተመርጦ እንደነበረ ሲያጫውተኝ ህይወት በትግል እንደምትፈተን
አሸንፎም መውጣት ግዴታ እንደሆነ በፈገግታ እየገለጸልኝ ነበር ። ኢህአዴግ መላ ሃገሯን ሲቆጣጠር ጦሩ ፈረሰና
ከሞያሌ ወደ ኬንያ የገባው ሸዋንግዛው እና የቀረው ስደተኛው በቀይ መስቀል ትብብር ወደ ሃገር ቤት ሲገባ ቤተሰቦቹን
ከጠየቀ በኋላ ወደ አዲስ አበባ ገባ ።
አዲስ አበባ ለአርሲው ተወላጅ ለሸዋንግዛው የተመቸች ነበረች።
በተለይም በልጅነት የተለከፋት ሙዚቃ የሚያጎለብትበት ብቸኛ እድል አገኘ ። እናም በየምሺት ቤቶች “ከተፋ ቤቶች”
ተሰማርቶ ምሽቱን እያደመቀ እና ራሱንና ቤተሰቦቹን በመርዳት መስራት ጀመረ ። ባለትዳር የሆነው ሸዋንዳኝ በምሽት
ስራው በአሁኑ ሰአት ታዋቂ ከሆኑ ዘፋኞች ጋር እኩል ድምጽ ማጉያን ተጋርቶ በጥበብ ተናኝቷል !
ይህም ሁሉ ሆኖ ፣ ይህንን የከበደ መንገድ ተጉዶ ሸዋንዳኝ ከልጅነት እስከ እውቀት ሙጥኝ ያላት የተለከፈባት ጥበብ አዳብሮ የራሱን ወጥ ዘፈን ለማውጣት አልሆንልህ እያለው መቸገሩ አልቀረም። ሸዋንግዛው እንዲህ እየሆነ ህይወትን ሲገፋ ለማደግ የሚያደርገው ግብግብ ባያሸበርከውም እንዳደከመው ሳይደብቅ አጫውቶኛል። የጥበብ አውሌ ብቻዋን ከተዘፈቀበት ድህነት ራሱን ቀና አላደረገችውም! ይህ እንዳይሆን ፣ በሰው ሰራሽ በጥበብ ላይ የሚሰራ ደባ እየደሰቀው መፈናፈኛ እንዳሳጣው ሸዋንግዛው ይናገራል ! በተለይም “ከከተፋው” ዘፋኝነት ጎን ለጎን ብዙዎችን ዘፋኞች ያሳወቀውን ነጠላ ዜማ ግጥምና ዜማውን ራሱ ደርሶ ቢያወጣም ሃገር ስራውን እንዳያውቅለት ጫና ፈጣሪዎች አላገዙትምና ድንቅ የባህል ዘፈኑ ሳይደመጥለት እንደቀረ ዜማዋን እንድሰማት በመጋበዝ ሸዋ ብዙ አጫወተኝ። በሙዚቀኞች መካከል ውስጥ ለውስጥ የሚሰራውን “የቲፎዞ ” ድጋፍ ፣ አንዳንድ የሃገር ቤት ኤፍ ኤም ራዲዮ ጋዜጠኞችን ሙስና የማይለየው ድጋፍ ግልጥልጥ አድርገው ካወሩት ጉዳዩ ብዙ እንደሆነ ከዚህ በፊት የማውቀውን ታሪክ ሸዋንግዛው መትቶታልና በግላጭ አጫውቶኛል! …
ይህም ሁሉ ሆኖ ፣ ይህንን የከበደ መንገድ ተጉዶ ሸዋንዳኝ ከልጅነት እስከ እውቀት ሙጥኝ ያላት የተለከፈባት ጥበብ አዳብሮ የራሱን ወጥ ዘፈን ለማውጣት አልሆንልህ እያለው መቸገሩ አልቀረም። ሸዋንግዛው እንዲህ እየሆነ ህይወትን ሲገፋ ለማደግ የሚያደርገው ግብግብ ባያሸበርከውም እንዳደከመው ሳይደብቅ አጫውቶኛል። የጥበብ አውሌ ብቻዋን ከተዘፈቀበት ድህነት ራሱን ቀና አላደረገችውም! ይህ እንዳይሆን ፣ በሰው ሰራሽ በጥበብ ላይ የሚሰራ ደባ እየደሰቀው መፈናፈኛ እንዳሳጣው ሸዋንግዛው ይናገራል ! በተለይም “ከከተፋው” ዘፋኝነት ጎን ለጎን ብዙዎችን ዘፋኞች ያሳወቀውን ነጠላ ዜማ ግጥምና ዜማውን ራሱ ደርሶ ቢያወጣም ሃገር ስራውን እንዳያውቅለት ጫና ፈጣሪዎች አላገዙትምና ድንቅ የባህል ዘፈኑ ሳይደመጥለት እንደቀረ ዜማዋን እንድሰማት በመጋበዝ ሸዋ ብዙ አጫወተኝ። በሙዚቀኞች መካከል ውስጥ ለውስጥ የሚሰራውን “የቲፎዞ ” ድጋፍ ፣ አንዳንድ የሃገር ቤት ኤፍ ኤም ራዲዮ ጋዜጠኞችን ሙስና የማይለየው ድጋፍ ግልጥልጥ አድርገው ካወሩት ጉዳዩ ብዙ እንደሆነ ከዚህ በፊት የማውቀውን ታሪክ ሸዋንግዛው መትቶታልና በግላጭ አጫውቶኛል! …
ሸዋን
ሳውዲ አረቢያ ስላደረሰው መንገድ እና የወደፊት ህልሙ እንዲያጫውተኝ ጠይቄው እንዲህ አለኝ ” ነጠላ ዜማው አልሳካ
ሲለኝ ድህነቱንና የኑሮ ውድነቱን ለማሸነፍ እንዳልቻልኩ የገባት ጅዳ የምትኖረው እህቴ በኮንትራት ስራ እንድመጣ
አመቻቸችልኝ። ተሳክቶም ልክ የዛሬ 11 ወር ወደ ሳውደሀ አረቢያ በኮንትራት ስራ መጣሁ ። በዘፈን ብዙዎች
ይሳላካላቸዋል ። እኔ የእድል ጉዳይ ሆኖ አልተሳካልኝም ። ይህ ደግሞ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ። የመጣውን መቀበል
እንጅ አላማርረውም። አሁን የምሰራው ሮለር በሃገራችን ዳምጤ የሚባለው የኮንስትራክሽን መኪና እየነዳሁ በርሃውን
ማቅመናት ነው ። በቃ ህይዎት እዚህ አድርሶኛል! እንደኔ ሃሳብና ህልም ከሆነ እንደምንም የሁለት አመት ኮንትራቴን
ጨርሸና ገንዘቤን ሰብስቤ እግዚአብሄር ብሎ የሙዚቃዋ አድባር ከጠራችኝ ወደ ሙዚቃው መመለስ ነው ሃሳቤ፣ ካልሆነ
የማገኛትን ይዠ ቤተሰቤንና ራሴን እየረዳሁ በሃገሬ መኖር ነው የምፈልገው! ለእስካሁኑ እግዚአብሔር ይመስገን!
ወደፊትም እሱ ያውቃል! ” በማለት መልሶልኛል።
ሸዋንግዛው “ይሻላል እንደሁ! ” ብሎ ስራውን በኮንትራት
ከመጣ ቀን ጀምሮ ስራውን የበርሃውን ቃጠሎ ተቋቁሞ ከጓደኞቹ ጋር እየሰራ ቢሆንም ደመወዝ አከፋፈሉ ቅሬታ አንዳለው
ፈተና እንደሆነበት ገልጾልኛል። ከሸዋንግዛው ጋር በነበረን ቆይታ በበርሃው ውሎ አዳር ስለሚለከታቸው በእረኝነት
ተቀጥረው ስለሚገፉ ኢትዮጵያውያን ይዞታ ሲያጫውተኝ ” የእኛን ተወው ደህና ነው ፣ የእረኛ ወንድሞቻችነወ ህይወት
ብታየው ያሳዝናል፣ ሃበሾችን ከሩቅ ታውቃቸዋለህ። ስናናግራቸው ደስተኛ እንዳልሆኑ ይገልጹልናል። ወደ ሃገር ቤት
እንዳይመለሱ ከድህነትና ኑሮ ውድነቱ በተጨማሪ ያላቸውን ቅሪት አንጠፍጥፈው ተሰደዋልና ምነወ ይዘን እንግባ ?
ይሉሃል ! ምን ትላቸዋለህ? ያ ያ ስላለ እንጅ ከኢትዮጵያ መጥተህ በበርሃው ውሃ እየተጠማህ የመንጋ በግ ፍየልና
ግመል እረኛ ሆነህ ኑሮን መግፋት ይከብዳል። ታለቅሳለህ! ” ሲል ፊቱን በሃዘን ክችመወ አድርጎ አዘወኖ አሳዘነኝ …
አዎ እኔም በአካል ተገኘወቸ ያየሁትና ዛሬ በርሃ ላይ ባገኘሁት ዘፋኝ የተገለጸልኝ ህይወት በእርግጥም ያሳዝናል!
ያማል! ስሜትን የሚገለወጸው አይሆንም …ብቻ በባለጸጋ አረቦች ሃገር ከአረቦቹ ጓዳ ፣ እስከ ደራው ከተማና በርሃው
የእኛ ህይዎት ሲሰሙት ውለው ቢያድሩ ተነግሮ አያልቅምና በዚሁ ልግታው ወደ በርሃው ውሎ የመጨረሻ ምዕራፍ ላቅና…
ከሸዋንዳኝና
ከጓደኞቹ የነበረኝ አጭር ቆይታ ታለቅ የጽናትን እና ዥጉርጉሩን ህይዎት የተረዳሁበት መልካም አጋጣሚ ሆኗልና
እዚያው ውየ ባድር ደስታየ በሆነ ነበር … ያ እንዳይሆን የእንጀራ እና የህይወት ጉዳይ አልፈቀደልኝም! እናም
መለያየት ግድ ሆነ በሳውዲ ራብቅ በርሃ ላይ ያገኘሁትን ዘፋኙን ሸዋንዳኝ እና ጓኞቹን ስለያቸው በፍቅር ተሳስቀን
እና ተቃቅፈን ተሳስመን ነበር ደግሜ ልጎበኛቸው ቃል በመግባት … ሸዋንዳኝን ስለየው ያቀበለኝን ባንድ ወቅት ሰርቷት
በህዝብ ጀሮ ያልደረሰችውን “ሸዋ ጥበብ ያውቃል! ” ነጠላ ዜማው እየኮመኮምኩ በርሃውን ለቅቄ ወደ ጅዳ መገስገስ
ጀመርኩ … በሸዋ ” ሸዋ ጥበብ ያውቃል !” ደምቄ …
” ከወዲያ ከወዲህ ስታንገላታኝ
ይህች የመንዝ ልጅ አስራ ልትፈታኝ
ቃሌ አይታጠፍም የመጣው ቢመጣ
እንዳሻት ታድርገኝ አላበዛም ጣጣ ” ይለዋል … በጥበቡ የሸዋን ጉብል የከበደ ፍቅር ሲገልጸው ….
ምንጃርኛውን ያሚያስደስተው ሞቅ ደመቅ ባለው ቅንብርና ዜማ የታጀበ ብቻ በመሆኑ አይደለም! የሸዋ ግጥሞች መልዕክት አላቸው …
” ከወዲያ ከወዲህ ስታንገላታኝ
ይህች የመንዝ ልጅ አስራ ልትፈታኝ
ቃሌ አይታጠፍም የመጣው ቢመጣ
እንዳሻት ታድርገኝ አላበዛም ጣጣ ” ይለዋል … በጥበቡ የሸዋን ጉብል የከበደ ፍቅር ሲገልጸው ….
ምንጃርኛውን ያሚያስደስተው ሞቅ ደመቅ ባለው ቅንብርና ዜማ የታጀበ ብቻ በመሆኑ አይደለም! የሸዋ ግጥሞች መልዕክት አላቸው …
የእንጀራ
ነገር ሆኖብኝ እጓዛለሁ ፣ እጓዛለሁ ፣ እጓዛለሁ … እንደጨው ተበትነናልና ስፍር ቁጥር የሌላቸው ወገኖቸን
በየሔድኩበት ከተማ ፣ በቀለጡ በርሃዎች እና መንደሮችም ወንድም እህቶቸን አገኛለሁ ! እንዲህ በማለዳ ወጌ ወጋወጉን
ለተሞክሮ ሳካፍላችሁ ደግሞ ደስታ ይሰማኛል ! ህይዎት እንዲህ ይኖራል …
ሰላም
ነቢዩ ሲራክ
ሙስናው ሄዶ ሄዶ እስር ቤት ገባ ................
ታራሚዎችን ገንዘብ በመቀበል ከማረሚያ ቤት በማስወጣት የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከ300 እስከ 500 ሺህ ብር እየተቀበሉ በሀሰተኛ ሰነድ ታራሚዎችን ከማረሚያ እንዲወጡ አስደርገዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሶስት የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት የስራ ሀላፊዎችና አምስት ተባባሪዎቻቸው በቁጥጥር ስር ውለው ፍርድ ቤት ቀረቡ።
ተጠርጣሪዎቹ ኦፊሰር ገብረመድህን አረጋ፣ ረዳት ኦፊሰር ኢሳያስ ከበደና ዋርደር ኢብራሂም መሀመድ ሲሆኑ፥ በአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት የእስረኞች አስተዳደር የስራ ሃላፊዎችና ሰራተኞች ሆነው ሲሰሩ የነበሩ ናቸው።
ከእነዚህ የስራ ሃላፊዎች ጋር የጥቅም ትስስር በመፍጠር ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት የተቀሩት ግለሰቦች ደግሞ፥ በንግድ ስራ ይተዳደር የነበረው አቶ ሰለሞን ገለታ፣ አቶ ብሩክ ሀይሌ፣ ወይዘሪት ሳባ ገብረሚካኤል፣ አቶ ናታን ዘላለምና አቶ ቴዎድሮስ ግደይ ናቸው።
የፌደራሉ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ የወንጀል ችሎት ባቀረበው የጊዜ ቀጠሮ ማመልከቻ ላይ እንደተመለከተው፥ ከሳባ ገብረሚካኤል ውጪ እነዚህ በንግድ ስራ ይተዳደሩ የነበሩ ግለሰቦች ቀደም ሲል በተለያዩ ወንጀሎች ተፈርዶባቸውና በማረሚያ ቤት የእስራት ጊዜያቸውን ጨርሰው የወጡ ናቸው።
እንደ መርማሪው ማመልከቻ ሳባ ገብረሚካኤል በኮምፒውተር ፅሁፍ እያገዘቻቸው፥ በንግድ ስራ የሚተዳደሩት ግለሰቦችም ከፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ታራሚዎች ከእስር የሚፈቱበትን ትዕዛዝ በሀሰተኛ መንገድ በማዘጋጀት እንዲሁም በሀሰተኛ ፊርማ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ማህተም በማስመሰል አዘጋጅተዋል።
በማረሚያ ቤት የሚገኙና ቅጣታቸው ከአምስት ዓመት በታች ለሆነ 300 ሺህ ብር ከዚያ በላይ ከሆነ ደግሞ 500 ሺህ ብር እየተቀበሉ፥ ከ11 በላይ ታራሚዎችን በዚህ ሀሰተኛ ሰነድ ከእስር እንዲለቀቁ አድርገዋል ይላል።
የሚያገኙትንም ገንዘብ ለኦፊሰር ገብረመድህን አረጋ፣ ረዳት ኦፊሰር ኢሳያስ ከበደና ዋርደር ኢብራሂም መሀመድ ለተባሉት የማረሚያ ቤቱ የስራ ሀላፊዎች በመስጠታቸው ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።
በመርማሪው ማመልከቻ መሰረት እነዚህ የስራ ሃላፊዎች የነበሩ ተጠርጣሪዎች የእስር መፍቻ ደብዳቤው በሀሰተኛ መንገድ የተዘጋጀ እንደሆነ እያወቁ ታራሚዎች እንዲፈቱ በማድረጋቸው ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ከሶስቱ የስራ ሀላፊዎች ውስጥ ኦፊሰር ገብረመድህን አረጋ ሀሰተኛ የእስር መፍቻ ካቀረበ አንድ ታራሚ 40 ሺህ ብር መቀበሉ ተመልክቷል።
የጊዜ ቀጠሮ ማመልከቻውን የተቀበለው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ የወንጀል ችሎት ተጠርጣሪዎቹ ያቀረቡት የዋስትና መብት ጥያቄ ቢለቀቁ መረጃ ያጠፋሉ የሚለውን የመርማሪውን ተቃውሞ በመቀበል፥ ጉዳያቸውን ማረሚያ ሆነው ይከታተሉ ብሏል።
ከወያኔ መንደር ውጡ
አቶ አያሌው እንግዲህ እነዚህ መልካም ነገር ቢኖራቸውም የተሰጣቸውን መክሊት አባክነው የክልሉ ህዝብ በየቦታው ሲፈናቀል የክልሉ መሬት እንደዳቦ እየተሸነሸነ ሲታደል የተቀመጡባትን ወንበር ላለማጣት በዝምታ ማለፍን መርጠዋል፡፡ይህ ደግሞ በምንም መልኩ ከተጠያቂነት አያድንም፡፡ከሌባ ጋር አብሮ ስርቆት ሂዶ በቅርብ ርቀት ሲሰርቁ እያዩ ዝም ማለት እና የሰረቀው አብሮኝ ያለው ሰው ነው አንጂ እኔ ነፃ ነኝ ቢሉ ከቅጣት አያመልጡም፡፡እንግዲህ እርሳቸው በስልጣን ላይ በቀዮበት ጊዜ ለጠፋው ሀይወት፤ለወደመው ንብረት፤ለተፈጠረው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ድቀት የድርሻቸውን ይወስዳሉ፡፡
መቼም በዘመኔ ወያኔ ስራና ሰራተኛ ተገናኝተው ባይውቁም እንደአማራ ክልል ባለስልጣናት በእውቀት ድርቅ የተጠቃ የለም፡፡”ሰው ሢታጣ ይመለመላል ጎባጣ” ነው ነገሩ፡፡ሰው ሲታጣ ማለቴ ለወያኔ በታማኝነት የሚያገለግል ማለቴ ነው፡፡አቶ አያሌውን የተኩት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በርቀት ትምህርት በማኔጅመት የመጀመሪያ ዲግሪ ሲኖራቸው በ1998 ዓ.ም የብአዴን ቢሮ ውስጥ ይሰሩ ነበር፡፡የተኛው የተምህርት ዝግጅት ተዛምዶ የክልሉየግብርና ቢሮ ኃላፊ ሁነው እንዲሰሩ እንዳበቃቸው የሚያውቀው ወያኔ ብቻ ነው፡፡ይባስ ብሎ ክልሉን የመምራት ሀላፊነት ለሳቸው መስጠት ከምጡ ወደ ዳጡ ነው፡፡ አቶ ገዱን የአማራ ወጣቶች ከከፍተኛ ትምህርቶች ተመርቀው የፓሪቲ አባል ካልሆኑ ስራ እንዳይሰጣቸው በክልሉ ላሉ ሁሉም ዞኖች ትእዛዝ ሲያስተላልፉ በተቃራኒው አባል ለሆኑት ስልክ ብቻ በመደወል እንዲቀበሉዋቸው ያል ምንም ውድድር እና ማስታወቂ በደብዳቤ ብቻ ሲመድቡ እንደነበር ይታወቃል፡፡በተለይ በ1998ዓ.ም የንግድ እና ኢንዱስትሪ ጽ/ቤት በወረዳዎች መከፈትን ተከትሎ በሁሉም ወረዳዎች የተመደቡ ፈላፊዎች በዚህ አይነት የተመደቡ ነበሩ፡፡አቶ ገዱ የክልል ፕሬዚዳንት ቀርቶ ለቀበሌ አመራርነት ሚያበቃ ስብእና እንደሌላቸው ሚያወቁዋቸው ሁሉ የሚስማሙበት ሀቅ ነው፡፡ግን ምን ይደረግ ወያኔ በሚመራው ሀገር ውስጥ ለሀገር የሚጠቅም ነገር በነፃነት መስራት ስለማይቻል አንዴ አዲሱ ለገሰ፤አንዴ ደመቀ መኮነን፤አንዴ ገዱ አንዳርጋቸው እተፈራረቁ በህዝቡ ትክሻ ላይ ያለከልካይ ይጫናሉ፡፡
በመጽሀፍ ቅዱስ ታሪክ የምናውቀው ደጉ አብረሀም የተወለደው ያደገው ከጣኦት አምላኪ ቤተሰብ ነበር፡፡ እግዚያብሔርም አብርሀምን “አብርሀም አብርሀም ውጣ !እኔ ወደማሳህም ወደዚያ ተራራ ሂድ አለው”፡፡አብርሀምም ቤተሰቡ የሚያመልከው ጣኦት አይን እያለው የማያይ ጆሮ እያለው የማይሰማ “ልክ እንደ ኢህአዴግ” ነበርና ከፈጣሪው የመጣለትን ትእዛዝ ሳያመነታ ተቀበለው ፡፡በሀጢያት ከረከሰው አካባቢውም ተለይቶ ወጣ፡፡አብርሀም ያደረገው ከሚወደው ቤተሰቡ በባእድ አምልኮ አብሮ ላለመኖር የግድ መለየት ነበረበት ተለያም፡፡ዛሬ በተለያዮ የስልጣን እርከን በወታደራዊም ሆነ በሲቪል ተቋማት ከወያኔ ጋር እየሰራችሁ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን ልክ እንደ አብረሀም በደም ከተበከለው ፤ህዝብን አፍኖ በችግር እየገደለ ካለው ስርኣት ራሳችሁ ለይታችሁ ውጡ፡፡አብርሀም ቅድስናን የተቀዳጀው ከባእድ አምልኮው ተለይቶ ነው፡ለጊዜያዊ ሥልጣን ጥቅም ወዘተ ራሳችህን እስካሁን አስገዛችሁ፡፡መጀመሪያ እውነት አለ መስሎአችሁ ገብታችሁ ይሆናል፡፡ግን ወያኔ ጋ ቀርቦ ያላየ የለም ደረጃው ይለያ እንጂ ፡፡ አንድም እውነት የለም ሁሉም ነገር የውሸት የማስመሰል ነው፡፡ወያኔ ጣኦት ነው፡፡ህገ-መንግስቱ፤የመለስ ራዕይ፤የብሄር መብት፤እድገት እና ትርናስፎርሜሽኑ፤የሚወራው ዲሞክራሲ ሁሉም ባእድ አምልኮዎች ጣኦቶች ናቸው፡፡እውነታውን ታውቁታላችሁ፡፡ስለገባችሁበት ነው እንጂ ሁሉም የህወአትን እድሜ ማራዘሚያ ነው፡፡ማንም ከወያኔ ጋር ሁኖ ህሌናው ያመነበትን እንደማይሰራ እናንተም ታውቁታላችሁ፡፡ፍርድቤቶች የሚፈርዱት በህሌናቸው ነው?ጋዜጠኞች እየሰራችሁ ያላችሁት እውነታውን ነው? ወታደሩ የገንዛ ወንድሙን፣እህቱን በቆመጥ የሚቀጠቅጠው አምኖበት ነው?፤የሚስኪኑዋ እናትክን ቤት እላይዋ ላይ የምታፈርሰው ህሌናህ ፈቅዶ በችግር ለተቆራመደው ወገናችን መርዳት ስንችል ለምን ተጨማሪ እዳ እንሆንባቸዋለን፡፡ከወያኔ ፍርፋሪ መጠበቅ ለጣኦት የተሰዋ መብላት ነው፡፡ ነው?ከወያኔ አገልጋይነት ተለዩ!ከወያኔ መንደር ውጡ!
የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት ከስልጣን ተነሱ
የአማራ ክልልን ላለፉት ስምንት ዓመታት ተኩል በፕሬዚደንትነት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ አያሌው ጎበዜ ከኃላፊነታቸው ተነሱ፤ በምትካቸው ምክትል ፕሬዚደንቱ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ተሹመዋል፡፡
አቶ አያሌው ከኃላፊነታቸው የተነሱት እየተካሄደ ባለው የአማራ ክልል ምክር ቤት አራተኛ ዙር ፤ አራተኛ ዓመት የስራ ዘመን አንደኛ አስቸኳይ ጉባዔ ውሳኔ መሠረት ነው፡፡
ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው በአቶ አያሌው መውረድና በአቶ አንዳርጋቸው መተካት ዙሪያ የብአዴን አባላት ሙሉ ስምምነት ላይ አልደረሱም። አዲሱ ፕሬዚዳንት በሙስና የተዘፈቁ እና በዘመድ አዝማድ ስራዎች የሚታወቁ በመሆኑ፣ በርካታ የብአዴን አባላት ሹመቱን አልደገፉትም።
ያለፈውን አንድ ወር በባህርዳር እና ጎንደር በመመላለስ ያሳለፉት አቶ በረከት ስምኦን ከክልሉ ብአዴን ካድሬዎች ጋር ግምገማዎችን ሲያካሂዱ ቆይተዋል። ካሉት የብአዴን አመራሮች መካከል በአንጻራዊ መልኩ የተሻለ ስም የነበራቸውን አቶ አያሌው ጎበዜን በማንሳት እንደ አቶ በረከት ሁሉ የተበላሸ ስም ያላቸውን አቶ ገዱን ለመተካት የተፈለገበት ጉዳይ ብዙ ውስብስብ ጉዳዮችን ያዘለ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል።
አቶ አያሌው ከኃላፊነታቸው የተነሱት እየተካሄደ ባለው የአማራ ክልል ምክር ቤት አራተኛ ዙር ፤ አራተኛ ዓመት የስራ ዘመን አንደኛ አስቸኳይ ጉባዔ ውሳኔ መሠረት ነው፡፡
ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው በአቶ አያሌው መውረድና በአቶ አንዳርጋቸው መተካት ዙሪያ የብአዴን አባላት ሙሉ ስምምነት ላይ አልደረሱም። አዲሱ ፕሬዚዳንት በሙስና የተዘፈቁ እና በዘመድ አዝማድ ስራዎች የሚታወቁ በመሆኑ፣ በርካታ የብአዴን አባላት ሹመቱን አልደገፉትም።
ያለፈውን አንድ ወር በባህርዳር እና ጎንደር በመመላለስ ያሳለፉት አቶ በረከት ስምኦን ከክልሉ ብአዴን ካድሬዎች ጋር ግምገማዎችን ሲያካሂዱ ቆይተዋል። ካሉት የብአዴን አመራሮች መካከል በአንጻራዊ መልኩ የተሻለ ስም የነበራቸውን አቶ አያሌው ጎበዜን በማንሳት እንደ አቶ በረከት ሁሉ የተበላሸ ስም ያላቸውን አቶ ገዱን ለመተካት የተፈለገበት ጉዳይ ብዙ ውስብስብ ጉዳዮችን ያዘለ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል።
ሐሙስ 19 ዲሴምበር 2013
በጅጅጋ ከተማ ታቆሽሻላችሁ ተብለው ከታሰሩት መካከል ከ40 በላይ ሰዎች ሞቱ
9ኛው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በጅጅጋ ለማክበር ዝግጅት በሚደረግበት ወቅት ከተማ ያቆሽሻሉ ተብለው
ተይዘው ከጅጅጋ 25 ኪሜ ገደማ ከምትገኘዋ ቀብሪበያህ እስር ቤት እንዲገቡ ከተደረጉት መካከል ከ40 በላይ ሰዎች
ምክንያቱ በውል ባልታወቀ ሁኔታ በመሞታቸው በታሰሩበት አካባቢ እንዲቀበሩ ተደርጓል። ሟቾቹ በደንብ ባለመቀበራቸውና
የአንዳንዶችን አስከሬን ጅብ አውጥቶ ስለበላው፣ ሌሎቹ ከእስር ቤቱ ራቅ ብለው በድጋሜ እንዲቀበሩ መደረጉን ኢሳት
ከክልሉ ባለስልጣናት የደረሰው መረጃ ያመለክታል።
በህይወት የተረፉት ሰዎች ከትናንት ጀምሮ የተለቀቁ ሲሆን፣ የዘመዶቻቸውን መሞት የተረዱ አንዳንድ ቤተሰቦች ሀዘን ተቀምጠዋል።
“ከተማ ታቆሽሻላችሁ እና ለጸጥታ ስጋት ትሆናላችሁ” በሚል ምክንያት ታስረው ከነበሩት ሰዎች መካከል ፣ የጎዳና
ተዳዳሪዎች፣ በጋሪ መግፋት እና በጉልበት ስራ የሚተዳደሩ ነዋሪዎች፣ አይነ-ስውሮች፣ አካለ ስንኩላን፣ መታወቂያ
አሳዩ ሲባሉ የክልሉን መታወቂያ ማሳየት ያልቻሉ፣ ከተለያዩ አካባቢዎች በመምጣታቸው ጸጉረ ልውጥ ተብለው የተያዙ
የሌላ አካባቢ ነዋሪዎች ይገኙበታል።
በጅጅጋ መታወቂያ ለማውጣት 1 መቶ 15 ብር የሚጠይቅ ሲሆን፣ በችግር ምክንያት መታወቂያ ያላወጡና በድንገት
መታወቂያ በተጠየቁበት ጊዜ ማሳየት ያልቻሉ በርካታ ሰዎች በእስር ቤት ውስጥ እንዲያሳልፉ ተደርገዋል።
የክልሉን የጸጥታ ዘርፍ ሃለፊ የሆኑትን አቶ አብዱላሂ ኢትዮጵያን ለማግኘት በተደጋጋሚ ስልክ ብንደውልላቸውም ልናገኛቸው አልቻልንም።
Source: esat
የፍርሃት ባህልን እያነገሰ ያለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ፤ አንድ እርምጃ ወደፊት ሁለት ወደ ኋላ (ክፍል ሁለታ)
ኢትዮጵያ የፖለቲካ ሂደት በኢትዮጵያዊያን ላይ እያሰፈነ ስላለው የፍርሃት ባህል ቀደም ሲል ባሰራጨሁት የዚህ
ጽሑፍ የመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ባለሙያዎች በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ ለፍርሃት ባህል መስፈን መንሰዔዎች ያሏቸውን
ነጥቦች ዘርዝሬ ነበር። በክፍል አንድ ጽሑፌ መግቢያ ላይ እንደገለጽኩት ምንም እንኳን ፍርሃት የግለሰቦች ባህሪ
መገለጫዎች መካከል አንዱ ቢሆንም የዚህ ጽሑፍ ትኩረት በወል የምንጋራቸውና በማኅበረሰብ ደረጃም በሚንጸባረቁት
የፍርሃት ምልክቶች ላይ ብቻ ያተኮረ ነው። በመሆኑም በዚህ ክፍል ውስጥ የህሊና እና የአካል ቁስልን ባስከተሉ ትላንቶች ውስጥ ማለፍ የሚፈጥረውን የፍርሃት ቆፈንና የሚያስከትለውን መዘዝ በመቃኘት ፅሑፌን ልደምድም።
በአለማችን
ታሪክ ከሰው ልጅ አዕምሮ ተፍቀው የማይወጡና እጅግ አሰቃቂ በመሆናቸው ሲታወሱ የሚኖሩ በርካታ ጦርነቶችና የእርስ
በርስ እልቂቶች ተከስተዋል። የመጀመሪያውና የሁለተኛው የአለም ጦርነቶች፣ የኦሽዊትዝ ጭፍጨፋ፣ የአፓርታይድ የግፍ
አገዛዝ፣ የሩዋንዳው የዘር ማጥፋት እልቂት፣ እንዲሁም በተለያዩ የአፍሪቃ እና የመካከለኛው ምስራቅ አገራት ውስጥ
የተከሰቱትና የሚሊዪኖችን ሕይወት የቀጠፉት እልቂቶች በዋነኝነት ተጠቃሾች ናቸው። እነኚህ በክፉ ክስተትነታቸው
በታሪክ የሚወሱት አጋጣሚዎች ካስከተሉት እልቆ መሳፍርት የሌለው ሰብአዊ ቀውስ እና የንብረት ውድመት ባሻገር
ከትውልድ ትውልድ የሚወራረስ ትምህርትንም አስተምረው አልፈዋል። በተለይም የምዕራቡ አለም በራሱም ሆነ በርቀት
በሌሎች ላይም የተፈጸሙትን እነዚህን መሰል መጥፎ ክስተቶች በአግባቡ በመመርመር፣ መረጃዎችን ሰብስቦና አደራጅቶ
በማስቀመጥ፣ በመጽሐፍ ከትቦና እና በፊልም ቀርጾ በማኖር ቀጣዩ ትውልድ እነኚህን መሰል አደጋዎችን ከሚያስከትሉ
የፖለቲካ፣ የማኅበራዊ፣ ኃይማኖታዊና ኢኮኖሚያው ቀውሶችና ቅራኔዎች እራሱን በማራቅ ችግሮችን እጅግ በሰለጠነና
ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እንዲፈታ ማድረግ ችለዋል። ዛሬ ላይ ያለው ትውልዳቸውም እነ ናዚ እና ሌሎች አንባገነኖች
በታሪካቸው ውስጥ ያደረሱትን ሰቆቃና ግፍ እያሰብ የሚሸማቀቅ ወይም በፍርሃት የሚርድ ሳይሆን ታሪክን በታሪክነቱ
ትቶ ሙሉ አቅሙንና ጊዜውን ከሳይንስና ተክኖሎጂ ጋር አዋህዶ በዚህ ምድር ላይ ያሻውን ሁሉ ለማድረግ የሚያስችል
አቅም በመገንባት ላይ ይገኛል።
ወደ አገራችን ስንመለስ ኢትዮጵያም ዛሬ ያለችበትን ጂዮግራፊያዊ፣
ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊም ሆነ ሌሎች ገጽታዎች ለመላበስ ያበቋት እጅግ በርካታ ክፉ እና በጎ ተበለው የሚጠቀሱ የታሪክ
ክስተቶችን አስተናግዳለች። ምንም እንኳን ከላይ ከተጠቀሱት የአለማችን አሰቃቂ ታሪኮች ጋር ባይወዳደርም አገራችንም
ከውጭ ወራሪዎች በተሰነዘረባት ጥቃትም ሆነ በልጆቿ መካከል በተከሰቱ የእርስ በእርስ ግጭቶች በብዙ ሚሊዮኖች
የሚቆጠሩ ውድ ልጆቿን አጥታለች። ድህነትን ጠራርጎ ሊያስወግድ ይችል ከነበረው አቅም በላይ በብዙ እጥፍ የሚገመት
አንጡራ ሃብቷን በጦርነቶች፣ በግጭቶችና በዘራፊዎች ተነጥቃለች። ይህ እና ሌሎች በርካታ ምክንያቶችም ተደራርበው
አገሪቱን ከድሃም ድሃ ተብለው ከሚጠቀሱት አገሮች ተርታ አሰልፈዋታል። እንግዲህ ትልቁ ጥያቄ እኛስ እንደ ሌላው
ዓለም ሕዝብ አገራችን ካለፈችበት የረዥም ዘመን ታሪክ እና በየወቅቱ ከተከሰቱ መጥፎና በጎ የታሪክ ክስተቶች ምን
ተማርን? ተምረንስ ለዛሬ እኛነታችን ምን አተረፍን? በአያቶቻችን እና በእኛ መካከል በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊ እና
በፖለቲካ ተክለ አቋማችንም ሆነ አመለካከታችን ዙሪያ ለውጦች አሉ ወይ? ለውጣችን ቁልቁል ወይስ ካለፉት ወገኖቻችን
የህይወት ተመክሮ ትምህርት ወስደን የደረስንበት የላቀ የአስተሳሰብና የኑሮ ደረጃ አለ? የታሪክ መዛግብቶቻችንስ
ያለፉ ነገስታቶችን እና የጦር አበጋዞቻቸውን ከማወደስና ገድላቸውን ከመተረክ ባለፈ በቀጣዩ ትውልድ ሕይወት የጎላ
ሚና ሊኖራቸ በሚችል መልኩ ተዘጋጅተዋል ወይ? ወይስ ‘እኔ የገሌ ዘር’ እያለ እንዲያዜምና በአያቶቹ ገድል
እንዲያቅራራ ብቻ ተደርገው ነው የተዘከሩት? እንደ እኔ እምነት ከምዕራቡ አለም እኛንና ብዙዎች የአፍሪቃ አገራትን
ከሚለዩን ነገሮች መካከል ጥቂቶቹ ከነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ የሚመነጩ ይመስለኛል።
የዛሬ መቶ እና ሁለት መቶ
አመት በፊት የተፈጠሩ የታሪክ ክስተቶችን ፍጹም በተዛባ መልኩ እያጣቀስን ልክ የእኛ የልፋት ውጤት አስመስለን
እስኪያልበን የምንፎክርና የምንጨፍር እኛ ነን። ታሪክን እና ጀግኖችን ማወደስ ተገቢ ቢሆንም የኛን ድርሻ እነሱን
በማወደስ ብቻ ስንገታው አደጋ ላይ ይጥለናል። እንደ አያቶቻችን ታሪክን መስራት ሲያቅተን ታሪክ ሰሪዎችን በማውሳትና
በዜማና በግጥም ማወደስ ብቻ ብንኮፈስ የዛሬውን ማንነታችንን አይሸፍነውም። ይህ በአያቶቻችን ታሪክ ውስጥ ተደብቀን
‘በኢትዮጵያዊነቴ እኮራለሁ’ እያሉ ማዜም፣ መፎከር፣ ማቅራራትና ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት ዛሬ ከተጣቡን የድህነት፣
የፖለቲካ ጭቆና እና ማኅበራዊ ቀውስ የማያስጥለን እና ነፃ የማያወጣን እሰከ ሆነ ድረስ ኩራታችን ከድንፋታ
አያልፍም። አገሬን እወዳልሁ፣ በኢትዮጵያዊነቴ እኮራለሁ እያሉ ባንዲራ ለብሶ ማቅራራት በተግባር ካልታገዘ የውሸት
ወይም ባዶ ኩራት (false pride) ነው የሚሆነው። እውነተኛ ኩራት የሚመነጨው ከራስ ነው፤ የራስን ማንነትን
በማወቅና በመቀበል ላይ የሚመሰረት ነው። ማንነትን አምኖ መቀበል አቅማችንንም አብረን እንድፈትሽ ይረዳል። የዛሬ
ባዶነታችንን በአያቶቻችን የታሪክ ገድል እንድንሞላ ወደሚያስገድድ የሞራል ክስረት ውስጥም እንዳንገባ ይረዳናል።
የዛሬ ውርደታችንን በአድዋ ድል እና በሌሎች የአያቶቻችን ተጋድሎዎች በተገኙ ስኬቶችን ልንሸፍነው ከመጣር ይልቅ
ታሪክ እንድንሰራ ብርታት ይሆነናል።
በሌላ በኩል የአውሮፓ ቅኝ ገዢዎች ያሳቀፉንን የዘረኝነት መርዝ
እያራባን በታሪክ ተፈጽመዋል የተባሉ አንዳንድ ክስተቶችን እየመነዘርን ‘ያንተ ቅም ቅም አያትህ የእኔን ቅም ቅም
አይታቶች በድሎ ነበር፤ ስለዚህ በቅም ቅም አያቶቼ ላይ ያንተ ዘሮች ላደረሱት በደል ኃላፊነቱን አንተ ትወስዳለህ
እያልን ድርጊቱን ዛሬ ላይ እንደተፈጠረ በመቁጠር የምንጋጭና ለመነጣጠል እንቅልፍ አጥተን የምናድርም አለን። እራስን
እንደተበዳይ ሌላውን የኅብረተሰብ ክፍል እንደ በዳይ በመቁጥርና የተዛባን ታሪክ በመተንተን ለዛሬው በዘረኝነት
መርዝ ለተለወሰው የፖለቲካ አጀንዳቸው ማሳኪያነት ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ካፈር የሚለውሱ ኢትዮጵያዊያኖችም
(እነሱ ኢትዮጵያዊ አይደለንም ቢሉም) ልብ ሊገዙ ይገባል። በአገሪቱ ውስጥ ያሉ የተለያዩ ጎሣዎች በገዛ አገራቸው
እኩል መብትና ጥቅም እንዲረጋገጥላቸውና የሁሉም አገር እንድትሆን ከመጣር ይልቅ በዘረኝነት ስሜት ውስጥ ተወጥሮ
ኢትዮጵያዊነትን መካድና ከራስ ጎሣ ውጭ ያለውን የኅብረተሰብ ክፍል እንደ ጠላት መቁጠር መዘዙ ብዙ ነው። ይህን
ለመረዳት ብዙ ምርምር አያስፈልገውም። በቅርባችን ካለችው ከሩዋንዳ ትምህርት መውሰድ ይቻላል። ይህን የዘረኝነት
እሳት እየተቀባበሉ የፖለቲካ መታገያቸው ያደረጉ ኃይሎችም ከዚህ እኩይ ተግባራቸው እንዲታቀቡ በስሙ የሚነግዱበት
ሕዝብ ሊያወግዛቸው ይገባል።
እርቀን ሳንሄድ የቅርብ ጊዜ ታሪካችንን እንኳን ብንፈትሽ ዛሬ ለምንገኝባቸው
እጅግ ውስብስብ እና ፈታኝ ችግሮች መንስዔ የሆኑትን ነገሮች በቀላሉ ልንገነዘብ እንችላለን። የችግሮቻችንን ምንጮች
እና ያስከተሉብንን መዘዝ በቅጡ መረዳት ከቻልን ከተዘፈቅንበት አረንቋ ውስጥ ለመውጣት ጊዜ ላይወስድብ ይችላል።
መወጣጫውም ላይርቀን ይችላል። ትልቁ ጥያቄ ችግሮቻችንን ከመዘርዘር ባለፈ ምንስዔዎቻቸውንም በቅጡ ተረድተነዋል ወይ?
እንደ አንድ አገር ሕዝብ በችግሮቻችን እና በችግሮቹ ምንጭ ዙሪያ የጠራ የጋራ ግንዛቤ አለን ወይ? በፖለቲካ እና
በሌሎች ማኅበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ስንደራጅስ ከነዚህ ግንዛቤዎች ተነስተን ነው ወይ? የጋራ የሆኑ ችግሮች ሰዎችን
ያስባስባሉ፣ ለድርጅቶች መፈጠርም መንስዔ ይሆናሉ፣ ችግሮቹንም ለመቋቋም እና ለማስወገድ “ከአንድ ብርቱ …”
እንደሚባለው ኃይልን ይፈጥራሉ። ይሁንና ስብስቡ ወይም የተደራጀው ኃይል ፊት ለፊት ከተጋረጡት ችግሮች ጋር ከመፋለም
ባለፈ በድጋሚ እንዳይከሰቱ ምንጮቻቸውን ለማድረቅ የሚያስችል እይታ ከሌለው እና አቅሙንም በዚያ ደረጃ ካላሳደገ
ይህ አይነቱ ማኅበረሰብ ሁሌም ለተመሳሳይ አደጋዎች የተጋለጥ ነው። የችግሩን መንሰዔ አጥንቶ ምንጩን ለማንጠፍ
ከሚያወጣው ጉልበት፣ ገንዘብና ጊዜ የበለጠ አዳዲስ ችግሮች በተከሰቱ ቁጥር ከተኛበት እየባነነ ተነስቶ ችግሮቹን
ለመቋቋም የሚያስችሉ ድርጅቶችን ለመፍጠርና ለማፍረስ የሚያወጣው ጊዜ፣ ገንዘብና ጉልበት እጅግ የላቀ ነው። በእንዲህ
አይነት ማኅበረሰብ ውስጥ ጠንካራ የሆኑና ልምድ ያካበቱ ድርጅቶችን መፍጠር አይቻልም። ብዙዎቹ ድርጅቶች
ሳይጎረምሱ፣ ሳይጎለምሱ እና ሳያረጁ በጨቅላነታቸው ይሞታሉ ወይም ደንዝዘው ስማቸውን ብቻ ይዘው ይቀራሉ። ይህ
አይነቱ ማህበረሰብ አውራ የሚሆኑና በምሳሌነት ሊጠቀሱ የሚችሉም የፖለቲካ፣ የኃይማኖት እና የማኅበራዊ ህይወት
መሪዎችን የመፍጠር አቅም የለውም፤ አይፈጥርምም፤ በራሳቸው ጥረት ቢፈጠሩም ጎልተው እንዲታዩ እድሉን አይሰጥም።
ትላንት ያነገሳቸውን በማግስቱ አፈር ከድሜ ሲደባልቃቸው ምንም አመክንዮ አይፈልግም። ሲያከብርም፣ ሲሾምም፣
ሲያዋርድም ሆነ ሲኮንን በስሜት ነው። በተለይም እንደኛ በብዙ ውስብስብ ችግሮች ውስጥ ተተብትቦ ግራ ለተጋባ
ማኅበረሰብ ልምድና በእውቀት የጎለበቱና የሕዝብ አመኔታን ያገኙ ባለ ዕራይ ድርጅቶችና ግለሰቦች መኖር እጅግ ወሳኝ
ነው።
የፖለቲካም ሆነ ሌሎች ልዩነቶቻችንን የምንይዝበት መንገድ ሊፈተሽ ይገባዋል። የቀዝቃዛው የአለም
ጦርነት ማብቂያን ተከትሎ የፈረሰውና ጀርመንን ለሁለት ከፍሏት የነበረው ግንብ ሲናድ ምስራቅና ምዕራቡን ወደ አንድ
አገር ከመለወጥ ባለፈ መላው አውሮፓን አንድ ያደረገ ክስተትን ፈጥሯል። የሰብአዊ መብቶች እና የዲሞክራሲ ጽንሰ
ሃሳቦች የልዩነት ማጦዣ ምክንያቶች ከመሆን ወጥተው ጀርመንን ብቻ ሳይሆን አውሮፓን ያዋሃዱ ተጨባጭ እውነታዎችን
ፈጥረዋል። ይህን ተከትሎም ከታሪክ ለመማር ዝግጁ በሆኑ በበርካታ የአለማችን አገራት በመሬት የተገነቡም ሆነ በሰዎች
አዕምሮ ውስጥ የተካቡ የልዩነት ግንቦች ሁሉ ፈርሰው ዜጎች ለጋራ ራዕይ በጋራ የመቆም ጽናትን አሳይተዋል።
ሕዝባቸውንም ነጻ አውጥተዋል። ሌሎች እንደ ኢትዮጵያ ያሉ የተለያዩ አገሮች (አብላጫዎቹ የአፍሪቃ አገራት)
የልዩነቶቻቸውን ግንቦች አጠንክረውና አዳዲስ ግንቦችን በአይምሯቸው ውስጥም ገንብተው የተሰበጣጠረና የሚፈራራ
የኅብረተሰብ ክፍልን በመፍጠር ጉዞዋቸውን ቀጥለዋል። የጎሣ ግንቦች፣ የሥልጣን ግንቦች፣ የኃይማኖት ልዩነት ግንቦች፣
የድሃና የሃብታም ግንቦች፣ የጨቋንና የተጭቋኝ ግንቦች፣ ሌሎች ማኅበረሰቡን በአንድ ላይ እንዳይቆም እና ድህነትና
አንባገነንነትን አሽቀንጥሮ እንዳይጥል አቅም የሚያሳጡ በርካታ የልዩነት ግንቦች ተገንብተዋል።
ድርጅቶችን
እና መሪ የሚሆኑ ግለሰቦችን እየፈጠርንና መልሰን እየደፈጠጥን የመጣንበትን የ50 ዓመታት የፖለቲካ ጉዞ ወደ ኋላ
መለስ ብለን ብንቃኝ ይህንን እውነታ ያረጋግጥልናል። ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ ለቁጥር የሚታክቱ የፖለቲካ፣ የሙያና
በማኅበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮሩ ድርጅቶች ተፈጥረው ብዙዎች ካለሙበት ሳይደርሱ ከስመዋል። ጥቂቶችም ባልሞት ባይ
ተጋዳይነት በመኖርና ባለመኖር መካከል ሆነው ቀጥለዋል። በከሰሙትም እግር ሌሎች በርካቶች ተተክተው በተመሳሳይ
አዙሪት ውስጥ ወድቀው የኅብረተሰቡን ቀልብ ለመሳብ ደፋ ቀና ሲሉ ይስተዋላል። እዚህ ላይ ልብ ልንለው የሚገባው
በዚህ ዘመን ውስጥ ብቅ ብለው በከሰሙትም፣ ተውተርትረው ቆይተው በተዳከሙትም፣ አዳዲስ ስም እየያዙ በተፈጠሩትም
ድርጅቶች ውስጥ ዋነኛ ተዋናዮቹና የድርጅቶቹ ፈጣሪዎችም ሆኑ አጥፊዎቹ አንድ አይነት ሰዎች መሆናቸው ነው። ትላንት
በአንድ ድርጅት ጥላ ስር ሆነው ሌሎችን እንደ ጠላት ይፈርጁ የነበሩ ሰዎች ዛሬ የብዙ ድርጅቶች ፈጣሪዎች ሆነዋል።
ትላንት በጠላትነት የሚፈራረጁ ድርጅቶች አባል የነበሩ ሰዎች ቂማቸውን እንዳረገዙ ዛሬ በአንድ ድርጅት ጥላ ሥር
የተሰባሰቡበትንም ሁኔታ እናያለን። በድርጅቶቹ መካከል እጅግ ጠባብ የሆኑ የርዕዮታለም ልዩነቶች ከመኖራቸው ውጭ
አብዛኛዎቹ የመጨረሻ ግባቸው አንድ እና አንድ ነው። ዲሞክራሲ የሰፈነባት፣ የሕግ ልዕልና የተረጋገጠባት፣ ሰብአዊ
መብቶች የተከበሩባት እና ድህነትን ያሸነፈች ኢትዮጵያን ማየት፣ መፍጠር ነው። በነዚህ መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ
የሚለያዩ ድርጅቶች ያሉ አይመስለኝም፤ ሊኖርም አይችልም። ልዩነቱ እነዚህ ግቦች ላይ ለመድረስ ድርጅቶቹ በሚከተሉት
አቅጣጫና መንገድ ቅየሳ ላይ ነው።
በዚህ የ50 ዓመት ጉዞ ውስጥ በሽብር መንፈስና በነውጥ ተግባራት
የተሞላው የኢትዮጵያ ፖለቲካ በድርጅቶች መካከል እርስ በርስ አለመተማመንንና መካካድን ፈጥሯል። ይህም አለመግባባቶቹ
ከጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት አልፈው እልቂትን አስከትለዋል። በዚያም የተነሳ አገሪቷ በፍርሃት እንድትዋጥና ሕዝቧም
በስጋት እንዲኖር፤ የፍርሃት ባህልም እንዲጎለብት ከፍ ያለ ሚና ተጫውቷል። ዛሬ በእያንዳንዳችን አዕምሮ ውስጥ
በርካታ የልዩነት ግንቦች ተፈጥረዋል። በፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በሲቪክ ማኅበራት፣ በኃይማኖት ተቋማት፣ በማኅበረሰብ
ድርጅቶች መካከልም የበርሊን ግንብ አይነት ግዙፍ የልዩነት ግንቦች ተፈጥረዋል። የዛሬዎቹ ኃይሎች ከገዢው ፓርቲ
በስተቀር በትጥቅ የተደራጁ ስላልሆኑ ነው እንጂ ለመጠፋፋት ቅርብ ናቸው። ትልቁና እያንዳንዳችን እራሳችንን ልንጠይቅ
የሚገባን፤ እነዚህን ግንቦች ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዴት ንደን እና በላያቸው ላይ ተረማምደን ልብ ለልብ
እንዋሃዳልን? እንዴት እንደ አንድ ሕዝብ የጋራ ዕራይ፣ የጋራ መዝሙር፣ የጋራ ህልም፣ የጋራ መፈክር፣ የጋራ
መድረክና የጋራ አገር እንፈጥራለን? እንዴት ከቂም፣ ከበቀልና ከቁርሾ ሽረን ከታይታና ከቧልት ፖለቲካ ወደ እውነተኛ
የፖለቲካ ሕይወት እንመለሳለን?
ለማጠቃለል ያህል በእኔ እምነት ከተተበተብንበት ውስብስብ ችግሮችና
ከተጫነን የፍርሃት ድባብ ለመላቀቅ፤ አልፎም ጤናማ የሆነ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ሥርዓት ባለቤት የሆነ
ማኅበረሰብ ለመፍጠር የሚከተሉት ተግዳሮቶች ቢቀድሙ ይበጃል እላለሁ::
- ዛሬ ለፖለቲካ
ንትርክና እርስ በርስ መፈራራት እንደ ምክንያት የሚነሱት የታሪካችን ክፍሎች ከፖለቲካ፣ ከኃይማኖት እና ከሌሎች
ወገንተኝነት ነጻ በሆኑ ምሁራን በአግባቡ የሚጠኑበት ማዕከል ቢኖረን። የመወዛገቢያ ነጥብ የሆኑትም ታሪካዊ ኩነቶችን
በአግባቡ ቢጠኑ እና በተለያዩ መንገዶችም ተደግፈው ለማስተማሪያነት ቢውሉ በድንቁርና ላይ ከተመሰረቱት ታሪክ ጠቀስ
የሆኑና በጥላቻ መንፈስ የተሞሉ ክርክሮች ወጥተን እውቀትን በዋጁ ውይይቶች ላይ እናተኩራልን።
-
የሩቁን ለታሪክ ምሁራን እንተወና ባለፉት አምሣ ዓመታት ከ1960 ዎቹ የተማሪዎች ንቅናቄ ጀምሮ በፖለቲካ ትግል
ውስጥ ዋነኛ ተዋናይ የሆኑ ኃይሎች ዛሬም በአገሪቷ የለት ተዕለት የፖለቲካ ህይወት ውስጥ በግራና በቀኝ ሆነው እና
በመቶ ድርጅቶች ጉያ ውስጥ መሽገው በአገሪቷና በድሃው ሕዝብ እጣፈንታ ላይ ወሳኞች ሆነው ቀጥለዋል። በተለይም ‘ያ
ትውልድ’ በሚል የሚታወቀው የኅብረተሰብ ክፍል ከልጅነት እስከ አዋቂነት ክቡር ሕይወቱን፣ ጊዜውን፣ ገንዘቡን እና
እውቀቱን ያለምንም ስስት የዛችን አገር እጣ ፈንታ ለማቅናት መስዋዕትነት ሲከፍል ቆይቷል፤ ዛሬም ዋነኛ ተዋናይና
አድራጊ ፈጣሪ ሆኖ ቀጥሏል። ይህ ትውልድ ትላንትናም ሆነ ዛሬ በገዢና በነጻ አውጪዎቻች ቡድኖች ተፈራርጆ እርስ
በርሱ ተጨራርሷል፣ ቂምና ቁርሾም ተጋብቷል፣ ተሰዷል አሰድዷል። ዛሬም በልቡ ቂም ይዞና በቀልን አርግዞ በተለያዩ
ድርጅቶች ውስጥ መሽጎ የጎሪጥ ይተያያል። ባገኘው አጋጣሚም ሆሉ ይናቆራል። ‘ቂም ተይዞ ጉዞ’ እንዲሉ ትላንት
በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ ሆነው በጠላትነት ይፈራረጁና ሊገዳደሉ ይፍላለጉ የነበሩ ሰዎች ይህን ሸክማቸውን በንስሃ
እና በይቅር ባይነት ከላያቸው ላይ ሳያራግፉ ውስጥ ውስጡን እየተብሰከሰኩና እየተፈራሩ ገሚሶቹ በልጅነታቸው
በቆረቡባቸው ድርጅቶች እየማሉ ቀሪዎቹም ዘመኑ በወለዳቸው አዳዲስ ድርጅቶች ውስጥ ሆነው የለበጣ ውህደት እየመሰረቱ
በዋዜማው ይፈረካከሳሉ። እንደ እኔ እምነት ከዚህ የእርስ በርስ መፈራረጅ፣ መፈራራትና የቆየ ቂምና ጥላቻ ሳንሽር
የምንክበው ካብ ሁሉ የእምቧ ካብ ነው የሚሆነው። እየሆነ ያለውም ይሄው ነው። ከዚህ አዙሪት ወጥተንና ከቂም ተላቀን
የጋራ ራዕይ እንዲኖረን እያንዳንዱ ግለሰብ እራሱን ለይቅርታ ማዘጋጀት አለበት። ከልብ የበደላቸውን ይቅርታ
ለመጠየቅና ይቅርታ ለመቀበል። ከድርጅታዊ ወገንተኝነትም እራሱን ነጻ አውጥቶ በሱና በድርጅቱ ላይ የተፈጸመውን በደል
ብቻ ሳይሆን እሱም ጠላት ብሎ በፈረጃቸው ሰዎችና ድርጅቶች ላይ ያደረሰውን ግፍና በደል ለመናዘዝና ለደረሰውም ሁሉ
አቀፍ ጥፋት ድርሻቸውን በድፍረት በማንሳት የተጠታቂነት ባህልን ‘ሀ’ ብለው ሊጀምር ይገባዋል።
-
ይህ ሁኔታም የደረሰውን የጉዳት መጠን በቅጡ እንድናውቅ ከማድረጉም ባሻገር እርስ በርስ የመወነጃጀሉን ታሪክ
እንድንገታውና ልባችንንም በፖለቲካ ንስሃ አንጽተን የሚነገርለትን ያህል የተሳካ ባይሆንም እንኳ ልክ እንደ ደቡብ
አፍሪቃው ‘በእውነት’ ላይ ወደ ተመሰረተ የእርቅ እና የሰላም መድረክ እንድቀርብ እድል ይፈጥርልናል።
-
የልጆቹን እርስ በርስ መጨራረስ እየተመለከት ፓለቲካ እንዲህ ከሆነ አርፎ መቀመጥ ይበጃል፤ እርም የፖለቲካ ነገር
በሚል አይምሮውን ጥርቅም አድርጎ ዘግቶ የለት ጉርሱን ብቻ እየቃረመ የአገሩን የፖለቲካ እጣፈንታ ለእዝጌሩ ትቶ ደግ
ቀንና መልካም አስተዳደርን እንደመና ከሰማይ እንዲወርድለት የሚጠባበቀውም የኅብረተሰብ ክፍል አይኑን ይገልጣል፤
ከመጠፋፋት ወደ ሰለጠነ የውይይት ባህል በሚሻገረው የፓለቲካ ኃይልም ላይ እምነት ያሳድራል፤ እራሱንም ከፍርሃት ነጻ
አውጥቶ በሙሉ ልብ በአገሩ ጉዳይ ባለቤት ይሆናል።
- ስለዚህም የገዢው ኃይል ወያኔ ካለበት
ጥልቅ ፍርሃት እና የሥልጣን ጥም የተነሳ ለእንዲህ ያለው ለውጥም ሆነ የሰላምና የእርቅ ጎዳና ገና ዝግጁ ባይሆንም
የተቀሩት የፖለቲካ ሃይሎች መንገዱን በመጀመር ለዘመናት በመካከላቸው የቆየውን ቁርሾና ቂም ከአዕምሯቸው በማውጣት
ከልብ የመነጨ እርቅ በማድረግ የልዩነት ግንቦችን ማፈራረስ ይጠበቅባቸውል። የሰላም፣ የእርቅ እና የእውነት አፈላላፉ
ጉባዔ ያስፈልገናል።
በእውነት ላይ ተመስርተው ተቃዋሚዎች በቅል ልቦና ከታረቁ አብረው ከሠሩ
በኢትዮጵያዊና በኢትዮጵያዊያን ላይ ለዘመናት እንደ መዥገር ተጣብቀው ደማችንን የሚመጡትን፣ ክብራችንን ገፈው እርቃን
ያስቀሩንን፤ ድኅነት፣ እርዛት፣ አንባገነናዊ ሥርዓትና ጭቆና፣ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት፣ ጦርነትና የእርስ በርስ
ግጭቶች፣ ድንቁርና፣ ጨለምተኝነት፣ ፍርሃት፣ ሙስና እና ጥላቻን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ነቅለን መጣል እንችላለን።
ቅን ልቦና ይኑረን! ለዘመናት የተጫነንን ሸክማችንንም እናራግፍ። ያኔ ለፍቅር በፍቅር፣ ለሰላም በሰላም፣ ለነጻነት
በነጻነት፣ ለአንድነታችን በአንድነት የምንሰራበትና ታሪክ ዘካሪ ብቻ ሳንሆን ታሪክ ሰሪ የምንሆንበት ጊዜ እሩቅ
አይሆንም።
Source: www.ecadforum.com
ረቡዕ 18 ዲሴምበር 2013
የጌዲዮ ዞን የሀገር ሽማግሌዎች በረሀብ መጠቃታቸውን የሚያመለክት ደብዳቤ ተፈራርመው ለዞኑ መስተዳድር አቀረቡ
በጌዲዮ ዞን በሚገኙ 9 ወረዳዎች ውስጥ በዚህ ወር ውስጥ ባልተለመደ ሁኔታ ከፍተኛ ረሀብ በመከሰቱ
የዞኑ የአገር ሽማግሌዎች ህዝቡ ያለበትን አሳሳቢ ሁኔታ በመግለጽ የተፈራረሙበትን ደብዳቤ ዛሬ ለዞኑ መስተዳድር
አስገብተዋል። በከፍተኛ ደረጃ ተደናገጡት የዞኑ ባለስልጣናት መረጃው ይፋ እንዳይወጣ ለማድረግ ዛሬ ቀኑን ሙሉ
በስብሰባ ተወጥረው መዋላቸውን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።
የአገር ሽማግሌዎቹ የገጠሩ ህብረተሰብ በከፍተኛ ሁኔታ በመራቡ መንግስት በአስቸኳይ እንዲደርስላቸው ጠይቀዋል።
የአገር ሽማግሌዎቹ ” የገጠሩ ህዝብ በረሀብ የተነሳ እየፈለሰ ወደ ከተማ እየተሰደደ ነው፣ እናንተ ምን እየሰራችሁ
ነው ?” የሚል ጥያቄ አንስተዋል።
በዚህ ወር የጌዲዮ ዞን ነዋሪዎች ከፍተኛ ቡና በማምረት የእህል ሸመታ የሚያካሂዱበት ነበር የሚሉት ምንጮች፣ አሁን ግን ሁኔታው ተቀይሮ የህዝቡን ህይወት አሳሳቢ ደረጃ ላይ የጣለ ረሀብ ተከስቷል ብለዋል።
በጌዲዮ ዞን ከ900 ሺ በላይ ህዝብ የሚኖር ሲሆን አብዛኛው ህዝብ ገቢውን የሚያገኘው ከቡና ነው።
በመላ አገሪቱ በሚታየው የኑሮ ውድነት ህዝቡ ምሬቱን እየገለጸ ነው። የዞኑን ባለስልጣናት ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።
በሌላ ዜና ደግሞ በሸዋ ሮቢት በርካታ መምህራን ስራቸውን እየለቀቁ ነው። መምህራኑ ስራቸውን የሚለቁት ከኑሮ
ውድነት ጋር በተያያዘ መሆኑን መምህራን ተናግረዋል። መምህራኑ ወደ ዋና ከተሞችና ወደ ውጭ አገር እየሄዱ መሆኑን
ለማወቅ ተችሎአል።
ኢሳት ዜና :-
Ethiopian Boeing 767 has made a minor overrun while landing
Information was just received from a regular airline source in Tanzania
that Ethiopian Airlines apparently had an unscheduled landing of a
B767-300ER at the Arusha Municipal Airport around 13.15 hrs local time.
The airport’s runway is reportedly only 1.620 metres long, or 5.315
feet, too short for regular B767 operations, so the question is now
being asked what prompted this high risk landing at ARK (IATA three letter
code) / HTAR (ICAO four letter code). The airport’s elevation is given
in official documents as 4.550 feet above mean sea level or 1.387
metres.
The aircraft, registered as ET-AQW was operating on
flight number ET815 from Addis via Kilimanjaro to Zanzibar and back to
Addis.
From initial reports it appears that none of the
passengers or crew have been injured and that the plane made it to a
complete halt just before the end of the runway. The airport in Arusha
has reportedly been closed for any other flights in and out of ARK
requiring the rescheduling of Precision Air’s flights as well as a
number of charters from and to the national parks.
Additional
sources from Kilimanjaro International Airport just gave added details
that the flight was approaching JRO but could not land due to an
aircraft on the runway with a problem. Why the flight was then diverted
to ARK and not a standard diversion airport like Nairobi or Dar es
Salaam will be subject to a detailed investigation, especially if
rumours were to be confirmed that the incoming flight was short of fuel.
The diversion to Arusha Municipal Airport is already being hotly
debated in local aviation circles as it put passengers, crew and
aircraft at extreme risk. It is unclear if the B767, even if stripped of
equipment and seats, will be able to safely take off from ARK and fly
to JRO, when that airport is eventually open and fully operational
again.
While full compliments must be extended to the cockpit
crew for their skills to land the plane safely the reasons for the
diversion will be subject to a full air incident enquiry with all
options presently kept open as to the reasons for the unscheduled
diversion. Stand by for more updates as and when more news and
additional information become available.
Source eTN
የትግራይ ህዝብ ስማ!!
ሰሞኑን በውዴታም ይሁን በግዴታ በመቀሌ እጅግ ከፍተኛ የሚባል
ቁጥር ያላቸው የትግራይ ተወላጆች ሲጨፍሩ፣ ሲዘሉ፣ ከበሮ እየመቱ የባህላቸውን ዘፈንና ውዝዋዜ ሲያወርዱ አይተናል።
ምክንያቱ በግልጽ ባይነገርም ሲደበቅ የነበረው የህወሃት ሃብትና ንብረት ውጤት የሆኑ፣ በልዩ የመንግስት ድጋፍ
የተከናወኑ ግዙፍ ተቋሞች በጎዳና ለህዝብ ሲቀርቡም ተስተውሏል። ልማቱ መልካም ነው። ደስ ይለናል። ምንም ተቃውሞ
የለንም። ግን መልዕክት አለን።
ለማን?
ምሬትን፣ ጭቆናና መንገፍገፍ ሲበዛ በፍቃደኛነት በቦንብ ላይ እንደሚያስሮጥ ለሚያውቀው የትግራይ ህዝብ!! የትግራይ ህዝብ ስማ!!
ሰሞኑን ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም
ሪፖርት የትግራይ ክልል በትምህርት፣ በኤሌክትሪክ፣ በመንገድ፣ በእርሻ፣ በደን፣ በኢንዱስትሪ፣ በጤና፣ ወዘተ ከሌሎች
ክልሎች ሁሉ ርቃ መሄዷን ይፋ አድርጓል። በዚህም ደስ ይለናል። አይከፋንም። ከዚህ በላይ እንዲሆን እንመኛለን።
ነገር ግን አንድ መልዕክት አለን።
ለማን?
አሁንም ለትግራይ ህዝብ!!
ሓውዜን የትግራይ ወጣቶች ለትግል ግልብጥ ብለው እንዲወጡ
አደረገ። ሓውዜን የደረሰው የቦንብ ድብደባ ማንና እንዴት እንደተቀነባበር ብዙ የሚባልለት ቢሆንም የምሬት ጫፍ ሆኖ
ህዝብን አሸፍቷል። ዛሬ መጨቆን ያንገፈግፋል ብለው ለትግል በተነሱና በተሰው ታጋዮች ደምና አጥንት ላይ የቆሙ ሌሎች
ሓውዜኖች እንዲፈጠሩ አድርገዋል። እያደረጉም ነው።
ይህ በማን ስም እየሆነ ነው? በህወሃት አማካይነት በትግራይ ህዝብ ስም!!
ኦሮሚያ ልጆቿን በእስርና በጥይት እያጣች ነው። በጨለማ ቤት
እየተሰቃዩ ያሉ የኦሮሞ ልጆች ግፍ ሰፍሮ ሞልቷል። አማራው አገር አልባ ሆኖ በየጎዳናው እየወደቀ ነው። እየተለዩ
ከየክልሉ እየተባረሩ ነው። የመኖር ዋስትናቸውን ተከልክለው በሞትና በጣር መካከል ያሉ ህጻናትና ነፍሰጡሮች ለቅሶ
ሰማይ ደርሷል። ይህ ሁሉ አልበቃ ብሎ እስር ቤት የሚማቅቁና የሚሰቃዩ ሰውነታቸውም የሚተለተል አሉ። የተገደሉ አሉ።
ይህንን የሚያደርገው ደህንነቱ የተቆጣጠረውና መሳሪያ ያነገተው ኃይል ነው። ይህ ኃይል ደግሞ ህወሃት ነው። ህወሃት
ይህንን ሁሉ ግፍ የሚፈጽመው በትግራይ ህዝብ ስም ነው። እያመረተ ያለው ደግሞ ብዙ ሓውዜኖችን ነው። በደልና
የበቀል ስሜት ላንድ ጎሳ ወይም ሕዝብ ብቻ የተሰጠ አይደለምና ሌሎችም ሊነሱ ይችላሉ። መቼና እንዴት? አይታወቅም።
በሲዳማ፣ በሶማሌ፣ በአፋር፣ … ብዙ ችግርና ምሬት አለ።
በጋምቤላ ግፍ ነዶውን እየወዘወዘ ነው። በጋምቤላ በዘመናት
ወደፊት የማናገኛው የደን ሃብት እየወደመ ነው። በጋምቤላ ሰላማዊ ህዝቦች ከቀያቸው እየተፈናቀሉ መሬታቸውን
እየተነጠቁ ለውጪ “ባለሃብቶች” እንዲሁም ለትግራይ ተወላጆች እየተከፋፈለ ነው። በባሌ፣ በቦንጋ፣ በወለጋ፣ ድፍን
ኦሮሚያና የደቡብ ክልል ደን እየተጨፈጨፈ ትግራይ በደን እየተሸፈነች ነው ብሎ መጨፈር ለትግራይ ህዝብ ኩራት
አይሆነውም። ኢትዮጵያዊ ነው የሚባለው የትግራይ ህዝብ እሱ የሚጠላውና ልጆቹን የገበረለት ግፍ በሌሎች ወገኖቹ ላይ
ሲፈጸም ዝም ማለቱ ለምንና ከምን የመነጨ እንደሆነ ለማወቅ የሚፈልጉ አሉና ጥያቄውን እናቀርባለን።
ስለመፈናቀል ስናወራ “የትግራይ ተወላጆች ተፈናቀሉ” ሲባልና
“ተፈናቀልን” ብለው ቅሬታና አቤቱታ ሲያቀርቡ አንሰማም። ይልቁኑም የአማራን ለም መሬት ለትግራይ በመከለል በደል
የሚፈጽመው ህወሃት የሚባለው በትግራይ ህዝብ ስም የተደራጀና በነጻ አውጪ ስም እስካሁን አገር የሚመራ ቡድን ነው።
ይህ ሁሉ ሲደረግ የትግራይ ህዝብ ያውቃል። ቢያንስ ቢያንስ የሰው መሬት ወርረው የተቀመጡት አይክዱትም። ግን ይህ
እስከመቼ ይቀጥላል? ፍርሃት አለን። ለምን? ይህ ሁሉ ሌላኛው የሓውዜን ክፍል ነዋ!!
ስለ ግብር ሲነሳ የትግራይ ተወላጆች በግብር ዕዳ፣ በባንክ እዳና
እንደ ልብ ነጻ ሆኖ በመንቀሳቀስ ችግር ቅሬታ ሲያሰሙ አይደመጥም። በመላው አገሪቱ በኢንቨስትመንት ተሰማርተው
በሰላም እየሰሩ ነው። ሌሎች ግን በብሔር ተለይተው መከራ ይደረስባቸዋል። ህወሃት በማንነታቸውና ባመለካከታቸው
እየነጠለ ከጨዋታና ከኑሮ መስመር ያወጣቸዋል። የጭቃ ቤት፣ አርሰው የሚበሉበት ከብት፣ ዶሮና በግ ሃብት ተብሎ
ይወረስባቸዋል። ይህ እውነት ለትግራይ ምሁራን የተሰወረ አይደለም። ይህም ሌላው ህወሃት በትግራይ ህዝብ ስም በሌሎች
ዜጎች ላይ የሚፈጥረው የምሬት ሓውዜን ነው!!
ኮንትሮባንድና ህገወጥ ንግድ ሲነሳ የመጀመሪያው መስመር ላይ
ሆነው አገሪቱን የሚያልቡት የቀድሞ ታጋዮችና የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ነጋዴዎች ናቸው። ጤፍ ወደ ኤርትራ በማጋዝ፣
ባህር ዛፍና ቡና በማሻገር፣ የዱር እንስሳትን ቆዳና ቀንድ በመነገድ የተሰማሩት ይታወቃሉ። ብዙ እጅግ ብዙ ማለት
ይቻላል። የምናነሳቸው ማሳያዎች ሁሉ የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ፣ የፖለቲካ፣ … ሓውዜኖች ናቸውና እዚህ ለጊዜው ላይ
እናቁም!!
ሻዕቢያ ድንገት ወረራ አካሂዶ ድፍን ትግራይን ሲቀጠቅጥ፣
ህጻናትን በቦንብ ሲቆላ፣ አገሬ ብሎ የተነሳን ህዝብ በማያውቀው ወንጀል እየሰፈሩ ማሰቃየት ይቆም ዘንድ የትግራይ
ህዝብ በቀጥታ ድምጹንና ተቃውሞውን በአግባቡ ማሳየት የሚገባው ወቅት ላይ እንደሚገኝ ይሰማናል፤ ደግሞም እናምናለን።
ዛሬ “ውርሱን እንጠብቃለን” በማለት የሚጮህላቸው አቶ መለስ በወቅቱ ክህደት ሲፈጽሙ የደረሰው ዛሬ እየተነጠሉ
የሚመቱትና መድረሻ ያጡ ወገኖች ናቸው። ዛሬም ቀበሮ ጉድጓድ ውስጥ ናቸው። በሰባና ሰማንያ ሚሊዮን ህዝብ ልብ ውስጥ
የተፈጠሩት ሓውዜኖች ወደ ቁጣ ሲለወጡ አምስት አምስት ሆኖ መደራጀት፣ በስውር መታጠቅና በየሰፈሩ ያሉትን
አስተባባሪዎች ስም ለቅሞ በመያዝ “ሳልቀደም ልቅደም” ብሎ መራወጥ አያዋጣም፤ ጊዜው ስለሚያልፍበት የትም
አያደርስም። ሓውዜናዊ ህይወት የሚኖር ሕዝብ ከደረሰበት በላይ የሚያጣው ስለማይኖር እንኳን ስለማጣት ስለመኖርም
አያስብም፡፡ በዚህ ከቀጠለ የቀን ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር በየቦታው ራሱ ህወሃት የፈጠራቸው ሓውዜኖች መናደፍ
መጀመራቸው አይቀርም።
“ህወሓትን እናስቀድም … ጠላቶቻችንን እናጥፋ” በሚል የማያቋርጥ
ጥላቻ መቀጠል ተጨማሪ ሓውዜኖችን ከመፍጠር በስተቀር “ጠላትን” ማጥፋት የማይቻል እንደሆነ ከዚህ በፊት በሕዝብ
ላይ ተመሳሳይ እርምጃ የወሰዱ ተሞክሮ ማስረጃ ነው፡፡ በበረሃ “ጠላትን እናጥፋ”፤ ሥልጣን ይዞ “ጠላትን እናጥፋ”፤
አገር እየመሩ “ጠላትን እናጥፋ”፤ ኢኮኖሚውን ተቆጣጥሮ “ጠላትን እናጥፋ” … 40ዓመት ሙሉ በ“ጠላትን እናጥፋ”
መርህ የሚጓዘው ህወሃት “ጉድጓድ የሚምስ ራሱ ይወድቅበታል” የተባለው የተቀደሰ አባባል ሲፈጸም እንዳየነው ከ70
ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ለማጥፋት የሚመኘው ህወሃት የራሱ መጥፊያ የሆኑ በርካታ ሓውዜኖችን ፈጥሯል፡፡
“የ100 ዓመት የቤት ስራ ሰጥተናቸዋል” በሚል በየድረገጹ
የሚለጠፉ ተራ ድንፋታና ትዕቢት የሚፈጠሩትን ሓውዜኖች ከማብዛት ውጪ ትርፍ የላቸውምና ወደ ደጉ መንገድ መመለስና
ሰብዓዊነትን በማስቀደም፤ ተደጋግፎ መኖርን ማጎልበት ይሻላል ለማለት እንወዳለን። ተሳስበውና ተረዳድተው የሚገነቡት
የትም ሆነ የት የአገር ነውና ሁሉም ይኮራበታል፤ ይጠብቀዋል። ተጠቃሚ ይሆንበታል። የሚያምርብንም ይህ ነው። ህወሃት
አልሰማም ብሏል። የትግራይ ህዝብ ግን ስማ!! ይህ ሁሉ የሚደረገው በስምህ ነው!!
: http://www.goolgule.com/
ኢህአዴግ ከብሔር “ተኮር” ተቃዋሚዎች ጋር ሊሸማገል ነው
ህወሃት አሁን በአገሪቱ ከቀን ወደ ቀን እየተስፋፋ የሄደው አለመረጋጋት እንዳሳሰበው የጠቆሙት የኢህአዴግ ሰው ድርጅቱ እርቅ ላይ ከመቼውም በላይ ትኩረት ሰጥቶ ለመስራት ስትራቴጂ መንደፉን አመልክተዋል።
“ከውጥረት ለመውጣት ወይም ውጥረትን ለመቀነስ” በሚል ኢህአዴግ
ትኩረት ሰጥቶ የጀመረው አዲሱ የ”ሰላም” መንገድ ህብረ ብሔር ድርጅቶችን ያላከተተበትን ምክንያት አልተብራራም።
ይሁን እንጂ ከኢህአዴግ ባህሪ አንጻር አቋሙ ሊቀየር የሚችል መሆኑን አልሸሸጉም።
ለድርድር የተመረጡትን ብሔርና ክልል “ተኮር” ድርጅቶች ይፋ
ማድረግ ለጊዜው እንደሚቸግራቸው ምንጮቹ ተናግረዋል። በድፍኑ ግን በተለይ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ክልልና ምስራቅ
ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ የነጻ አውጪና ብሔርን መሰረት ያደረጉ ድርጅቶች በማዕቀፉ ውስጥ እንዳሉ አመላክተዋል።
ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ የውጪ ኢንቨስተሮች ፍሰት መቀነሱ፣ ገብተው
በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙት ድርጅቶችም ከጸጥታና መሰል ችግሮች አገር ለቀው ወደመውጣቱ ላይ በመሆናቸው፣ አገሪቱ
ውስጥ ያለው የስራ አጥነት ችግር እየተወሳሰበ መሄዱና ድህነት በቃላት ሊገለጽ ከሚችለው በላይ መስፋቱ ህወሃቶችን
እንዳሳሰባቸው ያስታወቁት የጎልጉል መረጃ ሰጪዎች “የኢህአዴግ አቻ ፓርቲዎችም ለህወሃት ያላቸው የአገልጋይነት
መንፈስ እየተመናመነ መሄዱ ዋንኛው የህወሃት ጭንቀት ነው” ብለዋል። በዚህም የተነሳ እርቅ ከምንጊዜውም በላይ
አስፈላጊ የሆነበት ወቅት ነው።
ህወሃት ባደራጃቸው የብሔርና የጎሳ ድርጅቶች ጥላ ስር ለይስሙላ
ራሳቸውን በራሳቸው ያስተዳድራሉ ከሚባሉ ክልሎችና ዞኖች “እውነተኛ ውክልና አለን” የሚሉ ብሄርን፣ ክልልንና ዞንን
መሰረት አድርገው ከሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ጋር ለማካሄድ የታሰበው ድርድር ተግባራዊ ከሆነ አተገባበሩ እንዴት ሊሆን
እንደሚችልም ምንጮቹ አላብራሩም። ይሁን እንጂ ቀደም ሲል ኦህዴድንና ኦነግን ለማስማማት ተካሂዶ በነበረው ንግግር
ኦነግን ወደ ኦህዴድ ለማጠቃለልና ለኦነግ ስልጣን ለማጋራት የታቀደው እቅድ መክሸፉን አስታውሰዋል።
መረጃ ሰጪዎቹ አያይዘው እንደተናገሩት በቀዳሚነት በተለይ ከሶስት
ክልልና ብሔር “ተኮር” ድርጅቶች ጋር ኢህአዴግ ለማከናወን የሚፈልገው እርቅ በክልሉ ወይም በዞኑ በህዝብ ዘንድ
ተቀባይነት ያላቸውን መሪዎች እጁን ዘርግቶ እስከመቀበል የሚያደርሰው ነው። ቀጥለው ሲያስረዱም ሙሉ አስተዳደራዊ
ስልጣን እስከመስጠት ሊደርስ እንደሚችል ተናግረዋል።
ህወሃት ከአፈጣጠሩ ጀምሮ አገሪቱን አሳንሶ አዳክሞና ቆራርጦ የማቀራመት ዓላማ ስላለው ምን አልባትም በደቡብ ክልል አዲስ ክልል ሊወለድ ይችላል የሚል ስጋት እንዳለ ከምንጮቹ መረጃ ለመረዳት ተችሏል።
በማስታረቁ ስራ ላይ የተሰማሩትን ማንነት መግለጽ ለጊዜው አግባብ
አይደለም በማለት ዝምታን የመረጡት የኢህአዴግ ሰዎች እርቅ በመላው አገሪቱ እንደሚያስፈልግ አብዛኛው ካድሬና
የበላይ አመራሮች ምኞት መሆኑን ጠቁመዋል። ዋናው ቁልፍ ያለው በህወሃት እጅ በመሆኑ ክልሎችን ቀደም ሲል ያስቀየመ
አካሄድ በመሆኑ በአሁኑ እርቅ አካሄድ ላይ የክልል ከፍተኛ ባለስልጣኖችም እንደተሰማሩበት ተመልክቷል። ሰሞኑን
ግንቦት 7 የፍትህና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ኢህአዴግ ለሶስት ጊዜ ያህል የእርቅ ጥያቄ እንዳቀረበለት መግለጹና
ኢህአዴግም በኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በኩል ግንቦት 7ን የመታረቅ እቅድ እንደሌለው በመግለጽ ጉዳዩን ማጣጣሉ
ይታወሳል።
ደቡብ ሱዳን ኢትዮጵያና ኤርትራን ለመሸምገል በይፋ ማስታወቋ፣
ኳታርም ቀደም ሲል በተመሳሳይ ለእርቅ ላይ ታች ስትል መቆየቷ የሚታወስ ነው። የሁለቱም አገራት የሽምግልና ሩጫ ምን
ውጤት እንዳስመዘገበ የሚታወቅ ኦፊሳላዊ መረጃ ከየትኛውም ወገን አልተደመጠም። ይልቁኑም ህወሃትና ሻዕቢያ አንዱ
የሌላውን ባላንጣ በማደራጀት ስራ ላይ መጠመዳቸው ነው በይፋ እየተነገረ ያለው።
በሌላ በከል ደግሞ ኢጋድንና የኢጋድ አገራት መሪዎችን በይፋ
ሲዘልፉ የነበሩት የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ሰሞኑን በሱዳን ያደረጉት ጉብኝት ተከትሎ አዳዲስ መረጃዎች
እየተሰሙ ነው። ከኢጋድ ጋር ያላቸውን ግንኙነት በይፋ ለማደስ እየሰሩ መሆናቸውም ተነግሯል። ኤርትራ በተባበሩት
መንግስታት የተጣለባት እቀባ እንዲነሳላት አጠንክራ እየተከራከረች ባለችበት ወቅት ላይ ሆና ኢጋድን በወጉ ለመወዳጀት
ወስናለች መባሉ ወሬውን ሚዛን የሚደፋ እንደሚያደርገው በርካቶች ይስማሙበታል።
ኢህአዴግ በቀጠናው ብሎም በኢጋድ ውስጥ ባለው ተሰሚነት የተነሳ
መድረኩ ሻዕቢያንና ወያኔን በማገናኘት ለማሸማገል ለሚደረገው ጉዞ የመጀመሪያው ርምጃ እንደሆነ ከግምት በላይ
የሚናገሩም አሉ። ከካርቱሙ ጉብኝት በኋላ በኬኒያ 50ኛ ዓመት የነጻነት በዓል ላይ የተገኙት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ
በጉዳዩ ላይ ከቀጣናው አገራት ጋር እንደሚመክሩበት በመግለጽ ጉብኝታቸውን ከዚሁ ጋር የሚያይዙ አሉ። ይህን
አስመልክቶ ግን ከየትኛውም ወገን በገሃድ የተሰጠ መግለጫ ግን የለም።
: በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®
የኢህአዴግ አመራር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሐኖምን ገሰጸ
የወደፊቱ ጠ/ሚንስትር ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ የሚነገርላቸው ዶ/ር ቴዎድሮስ ግሳጼው የቀረበባቸው ” በሳውድ አረቢያ ላይ ተመጣጣኝ የአጸፋ እርምጃ እንወስዳለን” ብለው መናገራቸውን ተከትሎ ነው።
ኢህአዴግ በጉዳዩ ላይ ለመነጋገር አስቸኳይ ስብሰባ የጠራ ሲሆን ዶ/ር ቴዎድሮስም ” ያለግንባሩ ውሳኔ እንዲህ አይነት ጠንካራ አስተያየት ለምን እንደሰጡ እንዲያብራሩ ተጠይቀዋል። “ዶ/ር ቴዎድሮስ በቂ ማብራሪያ ለመስጠት ባለመቻላቸው ግለ-ሂሳቸውን እንዲያወርዱ ተጠይቀዋል። ከፓርቲው ይልቅ የግል ዝናቸውን እየገነቡ ነው በሚልም ተገምግመዋል።
የሳውድ አረቢያ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ቴዎድሮስ አድሀኖም በሰጡት መግለጫ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጠው ለ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ደብዳቤ ማስገባቱን ተከትሎ ነው ግምገማው የተካሄደው።
በሳውድ አረቢያ መንግስት ደብዳቤ የተደናገጡት አቶ ሀይለማርያም ወዲያውኑ በቴሌቪዥን ቀርበው ከሳውድ አረቢያ ጋር የቆየ የዲፕሎማሲ ግንኙነት መኖሩን፣ ይህን ግንኙነት አሁን በተፈጠረው ችግር እንደማይለወጥና ለወደፊቱም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
አቶ ሀይለማርያም የተናገሩትን ተከትሎ በሳውዲ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ሙሀመድ ካቢራ የኢትዮጵያ መንግስት 361 የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠታቸውን፣ ሳውዲ በኢትዮጵያ ታላቁ ኢንቨስተር መሆኑን ገልጸዋል።
ዶ/ር ቴዎድሮስ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በጥሩ ስሜት ላይ እንዳልሆኑ ምንጮች ገልጸዋል። ሚኒሰትሩ በፌስቡክ ላይ ባሰፈሩት መልእክት ጠ/ሚንስትሩን በማጀብ በማንዴላ ቀብር ላይ ሊገኙ ያልቻሉት በጤና ችግር ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል። ኢህአዴግ በሳውድ አረቢያ ላይ ያሳየው የተለሳለሰ አቋም እየተተቸ ነው። ዶ/ር መረራ ጉዲና ሰሞኑን ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ መንግስት በሳውዲ አረቢያ ላይ የያዘውን ፖሊሲ መተቸታቸው ይታወቃል።
ለሚቀጥሉት ሶስት አመታት ለመንግስት ሰራተኛው የሚጨመር ደሞዝ አይኖርም ተባለ
የመንግስት ሰራተኛው በከፍተኛ የኑሮ ውድነት እየተሰቃዩ መሆኑን እንደሚያዉቁ የተናገሩት ሁለት የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣኖች፣ ይሁን እንጅ በሚቀጥሉት ሶስትና አራት አመታት በጉልህ የሚታይ ደሞዝ ጭማሪ እንደማይኖር ገልጸዋል።
በየአምስት አመቱ የቤተሰብ ፍጆታቸው በተመረጡ ናሙናዎች ተወስዶ በሚለካው የግሽበት አሃዝ ስሌት መንግስት የኑሮ ውድነቱ በአንድ አሃዝ መውረዱን ቢገልጽም፣ የኑሮ ውድነት ግን አለመርገቡን ነዋሪዎች ይናገራሉ።
የማእከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሳሚያ ዘካርያ እንደተናገሩት የፍጆታ እቃዎች የዋጋ ግሺበት በአንዴ የሚለካው ለአምስት አመታት ነው ።ያነጋገርናቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በየቀኑ በሚጨምረው ገበያ እና በምርት እጦት እየተማረሩ መሆኑን ይገልጻሉ፡፡
የማእከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ባጠናው ጥናት 57 በመቶ የሚሆነው ኢትዮጵያዊ ገቢውን የሚያውለው ለምግብ ነክ ጉዳዩች ነው፡፡ አሁን ያለውን የኑሮ ውድነት እንዴት ያዩታል ተብለው የተጠይቄት ወ/ሮ ሳምያ ” የዋጋ ግሽበቱን አይተው የደሞዝ ማሰተካከያ የሚያደርጉ ሃገራት አሉ ፤ ማስተካከያ ካልተደረገ የዋጋ ግሺበቱን ጫና መቀነሳ አይቻልም” የሚሉት ወ/ሮ ሳምያ ማሰተካካያ ማድረግ በጣም አስፈላጊ ቢሆንም የመንግስት ፖሊሲ እንደማይፈቅድ ተናግረዋል።
“አሁን ያለውን የኑሮ ውደነት እኔም አውቃለሁ” የሚሉት ሃላፊዋ ፣ ችግሩን ስር እንደሰደደ የምረዳው በርካታ ሰራተኛች ከአዲስ አበባ ለመልቀቅ ማመልከቻ ለማስገባት ሲረባረቡ ሳይ ነው” ብለዋል፡፡
“የወር ደሞዛቸው የቤት ኪራይ መሸፈን እንኳን አለመቻሉ የሚናገሩት ወ/ሮ ሳምያ፣ የህዝብና ቤት ቆጠራ ስናይ አሁን ከዚህ ቤት ሰው ይኖራል ወይ ብለን እንጠይቃለን ” በማለት በኢትዮጵያ ስላለው የኑሮ ውድነት በግልጽ ተናግረዋል።
የፋይናንስ ና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አብርሃም ተከስተ ” የመንግስት ሰራተኛው በልቶ የማደር ፈተና ውስጥ እና መጠለያ ቤት እጦት እንደሚያንገላታው እናውቃለን” ያሉ ሲሆን፣ ጫናው በርካታ ባለሙያዋች ስራቸውን እንዲለቁ እንዳደረጋቸው መረጃ አለኝ ብለውል፡፡
“በ2006 ዓ.ም ምንም አይነት የደሞዝ ጭማሪ በጀት የለም” ያሉት ሚኒስትር ዲኤታው፣ እንዲያውም የፋይናንስ እጥረት እያጋጠመ በመምጣቱ ከቴሌ ኮሚኒኬሺን ፣ ከመብራ ሃይል እና ከውሃ ከሚሰበሰበው በብድር መልክ ተቀብለን ያስተላለፍነው የደሞዝ ክፍያ በርካታ ነው ሲሉ ለዘጋቢያችን ተናግረዋል፡፡
የደሞዝ ጭማሪው ለመጭዎች ሶስት እና አራት አመታት የሚታይ ጭማሪ ሊኖረው አይችልም ሲሊ ሚኒስትር ዴኤታው ለዘጋቢያችን በስልክ አረጋግጠዋል።
ኢሳት ዜና :-
በሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ በተደረገው ውይይት ምሁራኖች ስለ አምዬ ምኒልክ የተናገሯቸውን አንኳር ጉዳዮች
"አጼ ምኒልክ ‹‹ታላቁ›› የሚለው ስያሜ ይገባቸዋል::" ዶ/ር ያቆብ ኃ/ማሪያም
አጼ ምኒልክ ‹‹ታላቁ ዳግማዊ አጼ ምኒልክ›› ሊባሉ ይገባል፡፡ ለዚህ ምክንያት አለኝ፡፡ በተለያዩ አገራት ትልቅ ታሪክ የሰሩ መሪዎች ታላቅ ተብለዋል፡፡ ለምሳሌ ያህል ‹‹ቴተር ዘ ግሬት›› በሩሲያ በሰራው ታሪክ የተሰጠው ስም ነው፡፡ ‹‹ካትሪን ዘ ግሬት›› የተባለችው መሪም ሩሲያውያን ላበረከተችው ስራ የሰጧት ስም ነው፡፡ ‹‹አሌክሳንዴር ዘ ዘግሬት›› ለግሪክ ባበረከተው ታሪክ ይህን ስም ተሰጥቶታል፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እስካሁን የምኒልክን ያህል ታሪክ የሰራ መሪ አለ ለማለት አይቻልም፡፡ በመሆኑም ከአሁን በኋላ ምኒልክ ይህንን ስም እንዲሰጣቸው አሳስባለሁ፡፡
"ተቃዋሚዎች ከአጼ ምኒልክ ሊማሩ ይገባል::" ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ
የአጼ ምኒልክ ታሪክ ክርክር የሚያስነሳው ከእሳቸው ትልቅነት የነተሳ ነው፡፡ ትልቅ ስራ ያልሰራ መሪ ሊያከራክር አይችልም፡፡ ኢትዮጵያውያን የተለያየ አመለካከት እንዳለን ሁሉ በምኒልክ ታሪክም አለመስማማትና የየራሳችን አመለካከት መያዝ እንችላለን፡፡ እርሳቸው አዋጅ ሲያስነግሩ እንኳ ‹‹አመልህን በሆድህ ሰንቅህን በአህያህ›› ጭነህ ተከተለኝ ነው ያሉት፡፡ የተለያየ አመልና አመለካከት እንዳለን ምኒልክም አልዘነጉትም፡፡ ግን በዋና ዋና ጉዳዮች መስማማት አለብን፡፡ በብዙዎቹ ባንግባባ በአድዋ ልንስማማ ይገባናል፡፡ ከምንም በላይ የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ከአጼ ምኒልክ ሊማሩ ይገባል፡፡ አጼ ምኒልክ ዓለምን ያስደመሙት ድል በማድረጋቸው ብቻ አይደለም፡፡ የጦር አበጋዞች በእሳቸው ላይ ሳይከዱ ተባብረው ለአገራቸው እንዲሰለፉ በማድረጋቸው፣በወቅቱ መቻቻል በመፍጠራቸው ነው፡፡ ጣሊያን የጦር አለቆቹ ከምኒልክና እርስ በእርሳቸው ለማጣላት ያልፈነቀለው ድንጋይ ባይኖርም አጼ ምኒልክ ግን በሰከነ መልኩ በተቀናቃኞች መካከልም ጭምር አንድነት በመፍጠር ታሪክ ሰርተዋል፡፡ አጼ ምኒልክ ስሜታዊ አልነበሩም፡፡ እርሳቸው ያራምዱ የነበሩት መሬት የያዘ ፖለቲካን ነው፡፡ ከአጼ ዮሀንስ ጋር አለመግባባት በተፈጠረበት ወቅት አጼ ዮሃንስ ወደ ሸዋ ይዘው የዘመቱት ልምድ ያለው ሰራዊት ነው፡፡ በወቅቱ ምኒልክ በስሜት ለመግጠም አልሞከሩም፡፡ ለሶስት ቀን ያህል ተወያዩበት፣ እኔ ምን አለኝ፣ እነሱስ? የሚለውን መሬት የነካ ፖለቲካ አጤኑት፡፡ የሀይል አሰላለፉን ተገንዝበውም አስር አመት ጠበቁ፡፡ ፖለቲካ ትግስት ይጠይቃል፡፡ ቅንጅቶች ፓርላማ የመግባት አለመግባት ክርክር ሲነሳ አምስት አመት ጠብቁ ሲባሉ አልጠበቁም፡፡ እንግሊዝና ሱዳን በተጣሉበት ወቅት ሁለቱም ምኒልክ ጦር እንዲልክላቸው ጥያቄ አቀረቡ፡፡ አጤ ምኒልክ ሁለቱንም እምብይ አላሉም፡፡ ለሁለቱ ቀና ምላሽ አሳይተው (ለይምሰል ነው) በርካታ ሺህ ወታደሮችን ወደ ሱዳን ልከዋል፡፡ ሆኖም ሰራዊቱ ቶሎ እንዳይደርስ ቀስ ብሎ እንዲሄድ አድርገዋል፡፡ ሰራዊቱ ሱዳን ድንበር የደረሰው ጦርነቱ ካበቃ በኋላ ነው፡፡ ከሁለቱም ጋር አለመግባባት ውስጥ ሳይገቡ ቀርተዋል፡፡ ሁለት አይነት ፖለቲካ አለ፡፡ አንዱ የሀላፊነት ፖለቲካ ነው፡፡ ሌላኛው የእልከኝነት፣ የስሜታዊነት ፖለቲካ ነው፡፡ በሀላፊነት ፖለቲካ ፖለቲከኛው ቅስሚያ የሚሰጠው ድርድርን ነው፡፡ የአጼ ምኒልክ ፖለቲካ የድርድር ፖለቲካ ነበር፡፡ የምኒልክ ቤት የምክክር ቤት ነበር፡፡ በደርግ ዘመን ምክክር የሚባል ነገር አልነበረም፡፡ ኢህአዴግ መጀመሪያ እንደገባ በፈለጉት መልኩ ይደራደሩ ነበር፡፡ ከዛ ግን አንድ ሰው የሚወስነው ሆነ፡፡ የመንግስቱና የመለስ ቤት የምክክር ቤት አልነበረም ማለት ይቻላል፡፡ በተቃዋሚ ፓርቲዎችም ተመሳሳይ ነው፡፡ ኢህአፓም የሀላፊነት ፖለቲካ አልተወጣም፡፡ በዓለም ከፍተኛ ወታደራዊና ሌሎች ድጋፎችን የሚያገኘውን ደርግን ፊት ለፊት ነው የገጠመው፡፡ እንደ ምኒልክ ምን አለው፣ እኔስ ምን አለኝ የሚል የሀላፊነት ፖለቲካ አልተከተለም፡፡ ትልቅ ሀይል ካለው ደርግ ጋር የእልህ ፖለቲካ ነው የገባው፡፡ ለዛ ነው የእሳት እራት የሆነው፡፡ የዛሬዎቹ የሀላፊነት፣ የምክክር፣ የድርድር ፖለቲካንና ሌሎች አሳምኖ አንድነት የመፍጠር ፖለቲካን ከምኒልክ ሊማሩ ይገባል፡፡
"ታሪክ እንዳይሰረቅ መጠበቅ ያስፈልጋል::" አቶ ታዲዮስ ታንቱ
ምኒልክ ድሮ በህይወት እያሉ ከነበራቸው ታሪክ በላይ በአሁኑ ወቅት በርካታ ጠላች አሏቸው፡፡ አክሱም ሆቴል ውስጥ ለመቁጠር የሚታክቱ በርካታ ምኒልክን የሚሰድቡ መጽሃፍቶች ተመርቀዋል፡፡ የምኒልክን ታሪክ ለማንቋሸሽ ብዙ እየተሰራ ነው፡፡ ይህን ለመከላከልም ታሪካችን ማወቅ አለብን፡፡ ታሪካችን ሰው እንዳይሰርቀን መጠበቅ አለብን፡፡ ታሪካችን ለልጆቻችን ካላስተማርን ከ80ና 90 አመት በኋላ አድዋን ያሸነፈው መለስ ነው ይሉናል፡፡ የአባይን የጀመረው መለስ ዜናዊ እንደሆነ እየነገሩን ነው፡፡ የድሮዎቹ መሪዎች አባይን ማንም ሳያግደን እንገድባለን ብለው ጊዜ ሲጠብቁ ቆይተዋል፡፡ መንግስቱ ሀይለማሪያም ሳይቀር አባይን ለመገሰደብ ትልቅ ጥረት አድርጓል፡፡ እንዲያውም የድሮዎቹ መሪዎች ገና ከራባት እንዳሰሩ የሙባረክን እግር ስመው ‹‹እባክህን አባይን ልገድብ›› ብለው አልጠየቁም፡፡
"ለነገስታቶቻችን ክብር መስጠት አለብን::" አስራት አብርሃም
ሰማያዊ ፓርቲ የታላቁን ዳግማዊ አጼ ምኒልክ 100ኛ ሙት አመት በማስታወሱ ሊመሰገን ይገባዋል፡፡ ለነገስታቶቻችን ክብር መስጠት አለብን፡፡ እኔ ለአጼ ምኒልክ ከፍተኛ ክብር አለኝ፡፡ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ የአድዋን ድል እንዳሸነፈው ምኒልክ ያህል ሊቀርበኝ የሚችል የለም፡፡ ሆኖም የነገስታቶቻችን ታሪክ ሁሉም መልካም አሊያም መጥፎ ሊሆን አይችልም፡፡ የኢትዮጵያውያን ችግራችን ይህ ነው፡፡ የእኛ ዋናው ችግር ታሪክና ፖለቲካን መቀላቀል ነው፡፡ ምኒልክን አንዱ ሰይጣን ሲያደርገው ሌላኛው ጻድቅ ያደርገዋል፡፡ ለእኔ ሁለቱም አይደለም፡፡ እውነታው መሃል ላይ ነው፡፡ እንዲህ ከሆነ ነው ብሄራዊ መግባባት መፍጠር የምንችለው፡፡
ማክሰኞ 17 ዲሴምበር 2013
አቶ ልደቱ ወደ ፖለቲካ ተመለሱ
አቶ ልደቱ ለረጅም ጊዜ ጠፍተዋል..ከፓለቲካውም ከሃገሪቱም.. ከመገናኛ ብዙሃን ትንሽ ራቅ ስላልኩ የጠፋሁ ይመስላል፡፡ ላለፉት ሁለት ዓመታት ለትምህርት ከኢትዮጵያ ውጪ ነው የነበርኩት፡፡ ሁለተኛው ምክንያት ከሃያ አምስቱ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት አንዱ ብሆንም፣ በጠቅላላ ጉባኤ ከሊቀመንበርነት ስለወረድኩ የፓርቲው የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ አልመራም፡፡ በነዚህ ምክንያቶች ከመገናኛ ብዙሃን ርቄያለሁ፡፡ ከኢትዮጵያ ፓለቲካ ግን አልራቅኩም፡፡ አሁን ትምህርቴን አጠናቅቄ እዚሁ አገሬ እየኖርኩ ነው፡፡ የነበሩበት ትምህርት ቤት ምንድን ነበር የሚባለው… ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ኦፍ ለንደን ውስጥ፤ ስኩል ኦፍ ኦሬንታል ኤንድ አፍሪካን ስቴዲስ የሚባል አለ፡፡ እዚያ ነው ዲቨሎፕመንት ስተዲስ ያጠናሁት፡፡ ከ1997 ዓ.ም. ምርጫ በኋላ ኢዴፓ ‹‹ሶስተኛ አማራጭ›› የሚል ሃሳብ ይዟል፡፡ ይሄ ሃሳባችሁ ከምን አደረሳችሁ? ‹‹ሶስተኛ አማራጭ›› የምንለውን ነገር በአግባቡ ያለመረዳት ነገር አለ፡፡ እኛም በበቂ ሁኔታ አላስረዳን ሊሆን ይችላል፡፡
ሶስተኛ አማራጭ ሲባል፣ ልዩ የርዕዮተ አለም መስመርን ለመግለጽ ሳይሆን፣ የአቀራረብና የስልት ጉዳይ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ፓለቲካ፣ እስከ አሁን ድረስ ሁለት ፅንፍ የያዘ ነው። ሁለትም ነገር መደገፍ ወይም ሁሉንም ነገር መቃወም፡፡ የገዥው ፓርቲ አባል ከተሆነ፤ ተቃዋሚ የሚሰራውን ነገር ሙሉ በሙሉ ማጥላላት፤ የተቃዋሚ አባል ከተሆነ ደግሞ መንግስት የሚሠራውን ነገር ሁሉ መቃወም፡፡ እንዲህ ሁለት ጫፍ የያዘ አሰላለፍ፤ ለአገራችን ፖለቲካ አልጠቀመም፡፡ ከመቻቻል ከመደማመጥ አርቆናል፡፡ ለዚህም ነው፤ ከሁለቱ ጽንፎች የተለየ አማራጭና የተለያየ አቀራረብ ያስፈልጋል የሚል አስተሳሰብ ይዘን የመጣነው፡፡ በመንግስትም ሆነ በተቃዋሚ የተሠራ ነገር ለአገርና ለህዝብ የሚጠቅም ከሆነ ልንደግፈው ይገባል፡፡ የማይጠቅምና የሚጐዳ ከሆነ ደግሞ በተጨባጭ መረጃ መቃወምና እንዲቀየር መታገል ያስፈልጋል፡፡ በስሜታዊ ጽንፍ ሳይሆን በምክንያታዊ አስተሳሰብ ነው ፖለቲካው ሊመራ የሚገባው፡፡ አለበለዚያ፣ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ወደ ዲሞክራሲያዊ የመቻቻል ባህል ሊቀየር አይችልም። ሁለት ስሜታዊ ፅንፎችን ይዞ፣ ብሔራዊ መግባባት ለማምጣት በጣም አስቸጋሪ ስለሆነ፣ ምክንያታዊ አስተሳሰብ ነው የሚያዋጣን ብለን ሶስተኛ አማራጭ ይዘናል፡፡ ይሄንን አቀራረብ ይዘን ስንመጣ ፈተናዎች ገጥመውናል፡፡
ሁለቱ ጽንፎች ለረዥም ጊዜ ስር የሰደዱና የከረሩ ስለነበሩ፣ ብዙ ሰዎች የእኛን አስተሳሰብ ለመቀበል በጣም አስቸግራቸዋል፡፡ ደግሞም አያስገርምም፡፡ ሰዎች በቀላሉ ይሄን አስተሳሰብ የሚቀበሉ ከሆነ፤ ከመነሻው የአገራችን ፖለቲካ ከባድ ችግር የለበትም ማለት ነው፡፡ የአገራችን ፖለቲካ ግን ለረዥም ጊዜ የዘለቀ ትልቅ ችግር አለበት፡፡ ስለሆነም፤ ሦስተኛ አማራጭ ብለን ያቀረብነው የምክንያታዊ አስተሳሰብ አቅጣጫችንን ብዙ ሰዎች በቀላሉ ሊቀበሉት አልቻሉም። “ተቃዋሚ ከሆንክ በቃ ማንኛውንም ነገር ትቃወማለህ፡፡ ኢህአዴግም ከሆንክ ማንኛውንም ነገር ትደግፋለህ፤ ሌላ ሦስተኛ አማራጭ የለም” የሚል የተዛባ አመለካከት ይሰነዘርብን ነበር፡፡ “እንዲያውም ሦስተኛው አማራጭ የምትሉት ነገር ወላዋይነት ነው” በማለት ውዥንብር የመፍጠር ነገርም ነበር። በሂደት ግን፣ ብዙ ሰው ጉዳዩን እያብላላው፣ እያጤነውና እየተገነዘበው እንደሆነ አይተናል፡፡ እኛ በምንፈልገው ፍጥነት ህብረተሰቡ ተረድቶታል የሚል እምነት የለንም፡፡ ገና ብዙ ይቀራል፡፡ የኢትዮጵያ ፖለቲካ እስከአሁን በመጣበት የጽንፈኝነት መንገድ የትም ሊያደርሰን እንደማይችል ብዙዎች እየገባቸው ነው፡፡ ሁለቱ ጽንፎች የሚፈጥሩት ቅራኔና ውጥረት፣ ከዴሞክራሲ እያራቀን እንጂ ወደ መቻቻል እያመጣን እንዳልሆነ ሰው እየተገነዘበው ነው፡፡
“ሁለቱ የፅንፍ ሃይሎችና ጐራዎች አይጠቅሙም ትክክል አይደሉም” የሚለው አስተሳሰብ እየጐላ መጥቷል፡፡ “ሁለቱም ፅንፎች አይጠቅሙም፤ ችግር አለባቸው” ከተባለ ክፍተት መኖሩን ነው የሚያሳየው፡፡ ያንን ክፍተት የመሙላት ጉዳይ ነው የሶስተኛው አማራጭ ፋይዳ፡፡ ይሄንን አስተሳሰብ ይዘን እንደነበር በተለይ በፓርላማ በነበረን ተሳትፎ በደንብ ማሳየት ችለን ነበር፡፡ ፓርላማ ውስጥ ሌሎች ተቃዋሚዎች ከሚያራምዱት አስተሳሰብ በተለየ ሁኔታ፣ መንግስት ከሚሠራቸው ነገሮችና ከሚያራምዳቸው አቋሞች ውስጥ ለህዝብና ለሀገር የሚጠቅም ነገር ስናገኛቸው በድፍረት ስንደግፍ ታይቷል፡፡ ሰው ለዛ የሚሠጠው ትርጉም ምንም ይሁን እኛ ለሀገርና ለህዝብ ይጠቅማል ብለን እስካመንበት ድረስ በድፍረት ወጥተን፤ ይሄ አቋም ከገዢው ፓርቲም ይምጣ ከተቃዋሚ ፓርቲም ይምጣ ለአገርና ለህዝብ የሚጠቅም እስከሆነ ድረስ እንደግፋለን ብለን ማሳየት ችለናል፡፡ ገዢው ፓርቲ ጥሩ ያልሆኑ ነገሮችን ሲሰራ ደግሞ ከሌሎች ተቃዋሚዎች በበለጠ በመረጃ በተደገፈ ከመተቸትና በጠነከረ መልኩ በመታገል ምክንያታዊነታችንን ማሳየት ችለናል፡፡ ከተቃዋሚ ፓርቲ ውስጥም ጥፋት ወይም ድክመት ሲኖር፣ ተቃዋሚ ነውና እሱን አንነካውም አንልም፡፡ እንዲስተካከል እንተቻለን፡፡ ለሰላማዊ ትግልና ለአገር የማይበጅ፣ ለመቻቻል ፖለቲካ ማይጠቅም ሆኖ ካገኘነው፣ ተቃዋሚውንም ቢሆን በድፍረት የመተቸት አዲስ ባህል ይዘን መጥተን አሳይተናል፡፡ ያን የማይወዱ ሰዎች ብዙ ነበሩ፡፡
በሂደት እየተረዱ ሲመጡ፣ ግን እኛ የያዝነው አቋም ትክክል እንደሆነ መገንዘብ የቻሉ ሰዎች ብዙ ናቸው፡፡ ይሄ አቋማችን በአገራችን ያልተለመደ አዲስ አቋምና አካሄድ ስለሆነ፤ አንዳንድ ሰዎች በእኛ ላይ የሚያወሩትን አሉባልታ ማራገብ ተጠቅመውበታል። በእኛ ላይ ከንቱ ጥርጣሬና ጥላቻ እንዲስፋፋ በማድረግ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳርፈዋል። በሌላ በኩል ግን ከነባሩ የጽንፈኝነት ፖለቲካ የተለየ ምክንያታዊ ፖለቲካ ማራመድ ለዚህ አገር እንደሚያስፈልግ በደንብ ለማሳየት ችለናል፡፡ ስለዚህ ሦስተኛ አማራጭ ይዘን መምጣታችን፣ ጥቅምም ጉዳትም ነበረው፡፡ ከአጭር ጊዜ አንፃር፣ ሊያስወድድ የሚችል የፖለቲካ አቋም አልነበረም፡፡ ለአሉባልታ አጋልጦናል፡፡ ከረጅም ጊዜ አንፃር ግን ይሄ ምክንያታዊ የፖለቲካ መስመራችን እየሰፋና እያደገ፣ በተለይ በአዲሱ ትውልድ ዘንድ ተቀባይነት እያገኘ የሚመጣ አቋም ነው፡፡ ስለዚህ ጠቀሜታው ከፍተኛ ነው ብዬ ነው የማስበው፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ የበለጠ እየተጠናከረ ነው፡፡ ግን ሂደቱን እኛ ስለተናገርነውና ስላራመድነው ብቻ ውጤት ያመጣል ማለት አይደል፡፡ ከአጠቃላይ ከአገራቱ ሶሽዬ ኢኮኖሚክ የእድገት ደረጃ ጋር ተያይዞ ነው ተቀባይነት ሊያገኝ የሚችለው፡፡ አንድ የፖለቲካ ፓርቲ ወጥቶ ስለተናገረ ብቻ፣ የበቃ የፖለቲካ አመለካከት ያለው ህብረተሰብ ይፈጠራል ማለት አይደለም፡፡ እንደዛ አይነት ህብረተሰብ የሚመጣው ኢኮኖሚያችን ሲያድግና ሲዳብር፤ ትምህርት ሲስፋፋና ከሌላው አለም ጋር መስተጋብራችን የበለጠ ሲጠናከር ነው፡፡ በአጭር ጊዜ የሚቀየር ነገር አይደለም፡፡
የአስተሳሰብ ለውጥ እውን የሚሆንበት ሂደት በጣም የተራዘመ እንዳይሆንና እንዲፋጠን በማድረግ ረገድ ግን የኢዴፓ ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ እንግዲህ መንግስት ኢኮኖሚው በደብል ዲጂት እያደገ መሆኑን ይገልፃል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የህብረተሰቡ ኑሮ ግን መንግስት ከሚገልፀው የተለየ ነው፡፡ በዚህ ዙሪያ ምን ይላሉ? ኢኮኖሚውን በሚመለከት፣ የኛ አመለካከት ከሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች ይለያል፡፡ በመጀመሪያ እድገት አለ ብለን እናምናለን፡፡ ነገር ግን መንግስት ሁሌም በሚናገረው መጠን ደብል ዲጂት እድገት አለ ብለን አናምንም፡፡ አንዳንድ አለማቀፍ ድርጅቶች እንደሚገልፁት እድገቱ ወደ ስምንት ሰባት ፐርሰንት አካባቢ ሊሆን ይችላል ብለን እናምናለን፡፡ አቅሙን ለመናገር የሚያስችል በቂ መረጃ በእጃችን የለም፤ ሊኖረንም አይችልም፡፡ ነገር ግን ከአጠቃላይ ግንዛቤ ተነስተን ስናየው፤ መንግስት ከበታች አካላት እያገኘ ያለው መረጃ ትክክል ነው ብለን አናምንም፡፡ በብዙ ምክንያቶች የተዛባ መረጃ ነው ከታች ወደ ላይ የሚመጣው፡፡ የሚመጣውን ዳታ አምኖ መቀበል ያስቸግራል፡፡ በዚህ ምክንያት ፓርላማ በነበርኩበት ጊዜ፣ የመረጃ ምርምራ ወይም ኦዲቲንግ ሲስተም ያስፈልገናል እል ነበር፡፡ የገንዘብ እና የአሠራር ኦዲቲንግ ብቻ ሳይሆን የመረጃዎች ትክክለኛነት ለመፈተሸ ኦዲት መደረግ አለበት የሚል ሃሳብ ስናነሳ ነበር፡፡ ያን ጊዜ ይሄን ሃሳብ የሚቀበለን አልነበረም፡፡ አሁን ግን መረጃዎችን ኦዲት ማድረግ አለብን የሚል ሃሳብ በመንግስት እየተነሳ እያየን ነው፡፡ ይሄ የኢኮኖሚ እድገት አለ የሚባለው፡፡ መኖሩ ጥር ጥር የለውም፡፡ በምን ይገለፃል? ስለመኖሩ ህብረተሰቡ ውስጥ የምናያቸው እንቅስቃሴዎች በግልጽ የሚያሳዩ ናቸው፡፡ ለምሳሌ የልማቱን እንቅስቃሴ እንውሰድ፡፡ በመንግስት በኩል ከፍተኛ መዋለ ንዋይ እየፈሰሰ መሠረተ ልማት እየተስፋፋ ነው፡፡ ይሄ በየትም አገር ቢሆን የኢኮኖሚ እድገትን ያመጣል፡፡ የግሉ ክፍሉ ኢኮኖሚ ከድሮ በተሻለ ሁኔታ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ በኮንስትራክሽን ዘርፍም በሁሉም የአገሪቱ ክፍል ከፍተኛ የግንባታ እንቅሰቃሴ አለ፡፡ እንዲያም ሆኖ እድገቱ ሙሉ በሙሉ ጤናማ ነው ማለት አይደለም፡፡ ችግሮች የሉበትም ማለት አይደለም፡፡ ዕድገቱ መንግስት በሚለው መጠን ነው ማለት አይደለም፡፡
የእድገቱ መጠን መንግስት እንደሚለው ሳይሆን፣ ስምንትና ሰባት ፐርሰንት ይሆኖል ብዬ አምናለሁ፡፡ ይሄም ቢሆን መጥፎ እድገት አይደለም፤ ጥሩ እድገት ነው፡፡ በእርግጥ በኢትዮጵያ ደረጃ ላለ ድሃ አገር ከስድስት ፐርሰንት በታች የወረደ እድገት፤ ኢኮኖሚው እንደተኛ (ሪሴሽን ውስጥ እንደገባ ነው የሚቆጠረው፡፡ በጣም በከፍተኛ ደረጃ ማደግ ነው የሚጠበቅብን፡፡ የሌሎችም አገራትም ታሪክ ያንን ነው የሚያሳየው፡፡ እንደ አሜሪካና እንደ እንግሊዝ አገር አይነት ትልቅ ኢኮኖሚ ውስጥ ሶስትም አራትም ፐርሰንት ማደግ ከባድ ነው፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ዓይነት ኢኮኖሚ ተይዞ ግን፤ ደብል ዲጂት ማደግ ይቻላል፡፡ መጣ የሚባለው እድገት በህብረተሰቡ ህይወት ውስጥ መታየት አልነበረበትም ወይ? ሊታይም ላይታይም ይችላል፡፡ አንድ ኢኮኖሚ ማደግ ሲጀምር ሁሉንም ህብረተሰብ ይጠቅማል ማለት አይቻልም፡፡ ይሄ በየትም አገር ሆኖ አያውቅም፡፡ እንኳን ዘጠና ሚሊዬን ህዝብ ያለበት አገር ይቅርና፣ 3ሚሊዮን ህዝብ ባለበት አገርም ኢኮኖሚው ማደግ ሲጀምር ሁሉም ህብረተሰብ ተጠቃሚ ይሆናል ማለት አይደለም፡፡ ቀስ በቀስ ነው ተጠቃሚው እየበረከተና እያደገ የሚመጣው፡፡ ስለዚህ አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ድህነት ይታያል። ድህነት ብቻ አይደለም በርሃብም የሚሰቃዩ ሰዎች ብዙ ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች መኖራቸው ግን እድገት የለም ወደሚለው ድምዳሜ አይወስደንም፡፡ እድገትም ባለበት አገር ሰው ይራባል፤ ሰው በድህነት ይማቅቃል፡፡ እንኳን በእኛ በጀማሪ አገር ቀርቶ፣ የዳበረ እድገት አላቸው የሚባሉ አገሮችም የሚቸገሩ ሰዎች አሉ፡፡
እነዛ ሰዎች ስላሉ ግን ያ አገር አላደገም ማለት አይደለም፡፡ በተለይ ደግሞ የካፒታሊስት (የነፃ ገበያ) ስርዓት ውስጥና በአንድ ጊዜ ሃብት በእኩል መጠን ሊዳረስ አይችልም፡፡ በሂደት ነው፡፡ እንግዲህ የመንግስት ሚና እዚህ ላይ ነው የሚጠበቀው፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ እድገት መኖሩ ጥርጥር የለውም፡፡ ዋናው ችግር ሌላ ነው። አሁን የምናየው እድገት በአገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ መሠረታዊና መዋቅራዊ ለውጥ ሚያመጣ ነው ብዬ አላምንም ዘላቂነት የለውም፡፡ አሁንም የዝናብ እርሻ ጥገኛ ነኝ፡፡ እንደዚህ ዓይነት ኢኮኖሚ ዘላቂ ነው ሊባል አይችልም፡፡ ባለፉት ሃያ ዓመታት፣ የኢንዱስትሪው ዘርፍ በተለይ ማኑፋክቸሪንግ ተረስቶ ነው የኖረው፡፡ እኛ ለኢንዱስትሪው ትኩረት መስጠት እንዳለበት ስንናገር አይቀበሉንም ነበር፡፡ በእርግጥ ለእርሻው ትኩረት መስጠት ተገቢ ነው፡፡ የግድ ነው፡፡ ሰማንያ በመቶ ህዝብ በእርሻ ላይ ጥገኛ ሆኖ እርሻውን መዘንጋት አይቻልም፡፡ ግን በተመሳሳይ ሁኔታ ለኢንዱስትሪውም ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶ፤ ኢኮኖሚው በየዓመቱ ከእርሻ ጥገኝነትን ወደ ኢንዱስትሪው እስካልተሸጋገረ ድረስ፣ የኢኮኖሚ እድገቱ ዘላቂነት አይኖረውም፡፡ በዚህ ከተመዘነ የአገራችን ኢኮኖሚ ፈተናውን ወድቋል፡፡ ኢህአዴግ አገሪቱን ከተቆጣጠረ ወዲህ የገበሬ መጠን ምን ያህል ቀነሰ ብትይ፣ ከሶስት ፐርሰንት በላይ አልቀነሰም፡፡ አሁንም የእርሻ ጥገኛ ነን፡፡ አጭሩ መዋቅራዊ የሆነ ለውጥ አላመጣም፡፡ ግን እድለኞች ሆነን፣ በአለፉት ዘጠኝና አስር ዓመታት ጥሩ ዝናብ አለ፡፡ ይሄ ዝናብ ቢቋረጥ የምናወራለት የኢኮኖሚ እድገት እንክትክት ብሎ ነው የሚወድቀው፡፡ ለፓርቲው ስራ እና በትምህርት ወደ ውጭ አገራት ሲጓዙ ከዳያስፖራው ማህበረሰብ ጋር ስለአገሪቱ ፖለቲካና ወቅታዊ ጉዳይ ይወያያሉ? በተለያየ አጋጣሚ ውጭ አገር ሄጄ የኢትዮጵያውያንን የፖለቲካ እንቅስቃሴ ለማየት ለማታዘብ እድል አግኝቻለሁ፡፡
በደፈናው ውጭ አገር የሚኖር ኢትዮጵያዊ ሁሉ እንዲህ ነው ብሎ ለመፈረጅ ያስቸግራል፡፡ ምክንያቱም ብዙ ዓይነት ነው፡፡ ዝም ብሎ ስራውን የሚሠራ አለ፡፡ ገባ ወጣ የሚል አለ፡፡ አገር ቤት ገብቶ ብዙ ስራ የሚሠራ አለ፡፡ ከኢትዮጵያ ከወጣ የሰላሳና የአርባ ዓመት የቆየ አለ፡፡ ከሶስት ዓመት በፊት ሄጄ ተመልሻለሁ፡፡ ከፓለቲካው የራቀ አለ፡፡ አይነቱ ብዙ ነው፡፡ በውጭ አገር የለው ተቃዋሚ ሃይል እየሰራው ያለው ፖለቲካ ግን በአብዛኘው ለአገር የሚጠቅም አይደለም፡፡ የነሱ ተፅዕኖ ባይኖር፣ እዚህ አገር ያለው ፖለቲካ የተሻለ ይንቀሳቀስ ነበር፡፡ የዳያስፖራ ፓለቲካ፣ የአገሪቱን ፓለቲካ ወደ ጽንፈኝነት የሚገፉ አሉታዊ ተፅዕኖ ስለሆነ አገሪቱን እየጠቀማት አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ ፖለቲካ እንዲበላሽ፣ ወደ ፅንፍ የከረረ አቅጣጫ እንዲሄድ የማድረግ አዝማሚያ ነው የማየው፡፡ ግን ኢዴፓን ጨምሮ ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች ቅርንጫፍ ቢሮዎች በአሜሪካ በአውሮፓ አላችሁ፡፡ አይደለም? አዎ ኢዴፓ በውጭ አገራት ድጋፍ ሰጪ ኮሚቴ አለን፡፡ ነገር ግን እዚያ ያለው መንፈስ እንከተላለን ማለት አይደለም፡፡ አገር ውስጥ ያለው ሁኔታና በዳይስፖራ ተቃውሞ የሚያስተጋባው ነገር በጣም የተራራቀ ነው፡፡ እነሱ የሚሉትን ከሰማሽ፤ እዚህ አገር አንድ ሰው በጠዋት ከቤቱ ወጥቶ ማታ በሰላም ይመለሳል ብለሽ አታስቢም፡፡ ሰው ስራ ሰርቶ እንጀራ በልቶ ይኖራል ብለሽ አታስቢም፡፡ ይሄ ሲባል ግን፣ ሁሉም አንድ ዓይነት አስተሳሰብ አላቸው ማለት አይደለም፡፡ እንዲያው አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ዳይስፖራ ከፖለቲካው ርቆ የሚኖር ነው፡፡ ‹‹ሳይለንት ማጆሪቲ›› እንደሚባለው ዓይነት ነው፡፡
በፖለቲካው በጣም ገንነው የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ከአገር ከወጡ ብዙ ዓመት የሆናቸውና አንዳንዶቹ ሆን ብለው ኢትዮጵያ ውስጥ ጥሩ ነገር አይፈጠርም ተብሎ ማውራት ተገቢ ይመስላቸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ተተረማመሰች ብሎ መናገር ይጠቅመናል ብለው የሚያስቡ ሰዎችም አሉ፡፡ አስተዋጽኦ ማድረግ የሚችልና የሚገባው የዳይስፖራው ማህበረሰብ አሁን እያደረገ ያለው ነገር በጣም ጐጂ መሆኑን ተገንዝቦ ይሄን ነገር መለወጥ አለበት ብዬ አምናለሁ፡፡ በእርግጥ እነዚህ ሰዎች በቀላሉ የሚለወጡ ናቸው ማለት ይከብዳል። ካልተለዋወጡ ግን ህዝቡ ስለነሱ ያለውን ግምት መለወጥ ይችላል፡፡ ‹‹ውጭ አገር ያለ ፖለቲከኞች የተማሩ፣ ገንዘብ ያላቸው፣ ዲሞክራሲ ባለበት አገር የሚኖሩ ናቸው ስለዚህ ከአገራችን ጥሩ ነው የሚያስቡት፤ እውቀት አላቸው›› ብሎ ማሰብ በራሱ ትክክል ነው ብዬ አላምንም፡፡ ምን ያህል ፖለቲካችንን እየጐዳው እንዳለ እንቅስቃሴያቸውን መገንዘብ አለበት፡፡ ዛሬ ዛሬ የፓርላማ ስብሰባዎችን ሲመለከቱ ምን ይሰማዎታል? አንድ የተቃዎሚ ፓርቲ ተመራጪ ብቻ ናቸው፤ በፓርላማ ውስጥ የሚታዩት? እውነት ነው፡፡ ከ1997 ዓ.ም ምርጫ በፊት አስራ አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ ተመራጮች ፓርላማ ውስጥ ነበሩ፡፡ በ1997 ዓ.ም. የተቃዋሚ ፓርቲ ተመራጮች ቁጥር ጨምሯል፡፡ ወደ ሰማኒያ ያህሉ ፓርላማ ገብተዋል፡፡ በ2002 ዓ.ም. ምርጫ ሁላችንም ተጠራርገን ወጣን፤ የአንድ ተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ ብቻ ነው የቀረው፡፡ ይሄ የሚያሳየው የአገሪቱ የዲሞክራሲ ሂደት ከመሻሻል ይልቅ የኋሊት መመለሱን ነው ፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ የተቃዋሚው ጐራ በሂደት እየተጠናከረ ከመምጣት ይልቅ እየተዳከመ መምጣቱን ነው የሚያሳየው፡፡ በዋናነት በ1997 ምርጫ ከተሠራው አጠቃላይ ስህተት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በአንድ በኩል ገዢው ፓርቲ ምህረት የለሽ ሆኖ በሃይል የማፈን ጥረት አደረገ፡፡
በሌላ በኩል አብዛኛው የተቃዋሚ ጐራ፣ ህዝብ የጠሰውንና እጁ ውስጥ የገባውን የምርጫ ውጤት ይዞ በአግባቡ እየተጠቀመ መቀጠል ሲገባው፣ ፓርላማ አልገባም ብሎ ህብረተሰቡን በምርጫ ሂደት ተስፋ እንዲቆርጥ አድርጎታል፡፡ ያኔ በቅንጅት ፓርቲዎች መካከል ቅራኔ ሲፈጠር፤ የአዲስ አበባ አስተዳደርን እንረከብ፤ ‹‹ፓርላማ አንገባም›› በሚለው ውሳኔ የኢትዮጵያን የዲሞክራሲ ሂደት የኋሊት ለአስራ አምስት ዓመት የሚመልስ ስህተት መሆኑን ገልጸን ነበር፡፡ በዚያ ስህተት ሳቢያ ነው ዛሬ ዋጋ እየከፈልን ያለነው፡፡ ያኔ በአግባቡ ያገኘነውን የፓርላማ ወንበር ተረክበን፤ የአዲስ አበባ አስተዳደርንም ተረክበን በመስራት ህዝቡን ከነስሜቱ ይዘን ብንቀጥል፤ ኖሮ እስከአሁን መንግስት የመሆን እድል ይኖረን ነበር ብዬ አምናለሁ፡፡ ያኔ የኛን ሃሳብ መስማት ያልፈለጉ ጎራዎች፤‹‹ መንግስትን በሁለት እና በሶስት ወር እንጥለዋለን፤ ዕድሜ የለውም›› ብለው ነበር የሚናገሩት፡፡ ኢህአዴግ አልቆለታል፤ ነበር የሚሉት። ታሪካዊ ስህተት ነው የተፈፀመው፡፡ አሁንም ቢሆን፣ ተቃዋሚው ጎራ በነገሩ የፅንፍ ፓለቲካ የሚንዙ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሂደት ሌላ 15 ዓመት ወደኋላ ይሄዳል፡፡ ኢህአዴግ ወደፊት ለሃያና ለሰላሳ ዓመት በስልጣን ላይ የመቆየት እድል ያገኛል ማለት ነው፡፡ በአጠቃላይ፣ ይሄንን አለን፡፡ አሁን እየታየ ያለው አሳዛኝ የፓለቲካ ሁኔታ ለእኛ አዲስ አይደለም፤ ያኔ የተሠራው ስህተት ውጤት ነው፤ የዘራነውን እያጨድን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ እያደገ መሄድ ሲገባው ወደኋላ እየሄደ ነው፡፡ ይሄ ለገዥው ፓርቲ ሆነ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ትልቅ ሽንፈት ነው፡፡ የአገር ሽንፈት ነው፡፡ በዚህ ማንም መደሰት ያለበት አይመስለኝም፡፡ ከዚህ በኋላ ተቃዋሚዎች በቀጣዩ ምርጫ ራሳቸውን አጠናክረው መምጣት ይችላሉ? ተቃዋሚው ጎራ ራሱን እንዲያሻሽልና እንዲጠናከር አስተዋጽኦ ማድረግ የሚገባቸው ሶስት አካላት አሉ፡፡ መንግስት፣ የዲሞክራሲ ሂደቱ የበለጠ እንዲፋፋ አፋዊ ሳይሆን ተግባራዊ እርምጃ መውሰድ አለበት፡፡ በአብዛኛው ስለ ዲሞክራሲያዊ ሂደት መንግስት እየተናገረ ያለው አፋዊ ነው በተግባር የሚገለፅ አይደለም፡፡ ወረቀት ላይ ይቀመጣል፡፡ በቲቪና በሬዲዮ ሲነገር እንሰማለን፡፡ በተግባር ግን የሚሠራው ከዛ የተለየ ነው፡፡
ሁለተኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ቆም ብለው ማሰብ አለብን፡፡ “የህዝብ ድጋፍ የለውም” የምንለውን ኢህአዴግን ለ22 ዓመታት ታግለን ለውጥ ያላመጣነው ለምን እንደሆነ ቆም ብለው በሃቅና በድፍረት ራሳችንን መመርመር ካልቻልነው፤ ከዛ ሂደት ተምረን መሠረታዊ የሆነ የአካሄድ ለውጥ እስካላደረግን ድረስ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሊቀየር አይችልም፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከመጠናከር ይልቅ በተቃራኒው እንደውም በሂደት እየተዳከምን የመጣነው ለምንድን ነው? እውን ይሄ የሆነው በኢህአዴግ ተጽዕኖ ብቻ ነው ወይ? የራሳችን የውስጥ ችግር፤ ድክመት፣ ስህተት የለብንም ወይ? ተቃዋሚ ፓርቲዎች እነዚህን ጥያቄዎች መርምረንና ራሳችንን ፈትሸን ራሱን ገምግሞ መሠረታዊ የመፍትሄ ሃሳብ ይዘን ካልመጣን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ይሻሻላል ብዬ አላምንም፡፡ ኢዴፓ ይንንን ሃላፊነት ለመወጣት የድርሻውን እየሰራ ነው፡፡ በርካታ ተቃዋሚ ወገኖች ግን ራሳቸውን ለመፈተሽ ዝግጁ አይመስለኝም፡፡ በድፍረት መናገር የምችለው፣ ከኢዴፓ በስተቀር ‹‹እኔ ስህተት አለብኝ፤ እስከአሁን የመጣንበት ጉዞ ስህተት ነበረበት፡፡ ያ ስህተት ነው ደካማ ያደረገን›› ብሎ የገመገመ ሌላ ፓርቲ ያለ አይመስለኝም፡፡ አብዛኛው ተቃዋሚ ‹‹እኛ ስህተት የለብንም፤ ሁሌም ስህተት የሚፈጥረው ከገዢው ፓርቲና ከሌሎች ነው›› ብሎ ነው የሚያስበው፡፡ ራሱን ገምግሞ ተገቢ የመፍትሔ ሃሳብ የማያመነጭ ተቃዋሚ፣ በኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ሂደት ላይ ለውጥ ያመጣል ብዬ አላስብም፡፡ ለራሱም፣ ለሀገሩም አይሆንም፡፡ ሶስተኛው አስተዋፅዖ ከህዝብ ነው የሚጠበቀው። ምክንያቱም ህዝብ ነው የጉዳዩ ባለቤት፡፡ እኛ የፖለቲካ ፓርቲ ተሳታፊዎች ነን፡፡ የጉዳዩ ዋና ባለቤት ግን ህዝብ ነው፡፡ ህዝብ ለውጥ ይፈልጋል፤ ለውጥ የሚመጣው ግን የዳር ተመልካች በመሆን አይደለም፡፡ ገዢው ፓርቲና፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የየራሳቸውን አስተዋጽኦ ማድረግ አለባቸው፡፡
ህብረተሰቡም የድርሻውን መወጣት ይኖርበታል፡፡ ተቃዋሚዎች ተጠናክረው እንዲወጡ የሚፈልግ የህብረተሰብ ክፍል አለ፡፡ ግን ፍላጎት ብቻውን በቂ አይደለም፡፡ ህብረተሰቡ፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ውስጥ ያሉ ስህተቶችን በአግባቡ ማወቅና እንዲታረሙ መታገል አለበት፡፡ ተቃዋሚ ስለሆኑ ብቻ በአዘኔታና በርህራሄ ‹‹ተቃዋሚዎች ናቸውና መተቸት የለባቸውም›› ማለት የለበትም፡፡ ፓርቲዎች ስህተት ሲሰሩ ካየ፣ ህብረተሰቡ መንግስትን ተቃዋሚዎችንም እየተቸ እንዲስተካከሉ ማገዝ አለበት፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከህዝብ የመነጨ ስለሆነ ህብረተሰቡ በገንዘብና በእውቀት ካልረዳቸው በስተቀር በሆነ ተአምር ተጠናክረው ሊወጡ አይችሉም፡፡ የህዝቡ መገለጫዎች ናቸው ስለዚህ ህብረተሰቡ ተቃዋሚዎች እንዲጠነክሩ የሚፈልግ ከሆነ፣ በተግባር አስተዋጽኦ ማድረግ አለበት፡፡ የእነዚህ ሁሉ ድምር ውጤት ነው የአገራችንን ፖለቲካ ወደተሻለ ደረጃ ሊያደርስ የሚችለው፡፡ ከ1997 ዓ.ም ምርጫ በኋላ ገዢው ፓርቲ ያወጣቸው አዳዲስ ህጐች አሉ፡፡ የፀረ ሽብር አዋጅ፣ የፕሬስ ህጉ፤ የፓርቲ ምስረታ አዋጅ፣ የኤንጂኦ ህግ ተቃዋሚዎችን ለማዳከም ገዢ ፓርቲ የፈጠረው ጫና ነው የሚል አስተያየት በስፋት ይደመጣል፡፡ እርስዎ ምን ይላሉ? በአንድ በኩል፤ አዎ መንግስት እየፈፀመ ያለው ድርጊት፤ እያወጣቸው ያሉ ፖሊሲዎችና ህጎች፣ ለተቃዋሚ ጐራ መዳከም የራሳቸው አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ ብቸኛ ምክንያቶች ናቸው ማለት ግን አይደለም። ራሱ የተቃዋሚ ጐራ ችግሮችም ለሱ መዳከም ምክንያት መሆኑን ቀደም ብዬ ጠቅሼዋለሁ፡፡ ገዢው ፓርቲ ውስጥ የምናያቸው፣ የጭፍን ስሜታዊነት፣ የሙስና፣ የዘረኝነት፣ የአምባገነንነት፣ ችግሮች፤ ሳይቀነሱ ሳይደመሩ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ውስጥም እናያቸዋለን፡፡ ገዥው ፓርቲ የሚጎድለው ዲሞክራሲያዊ ባህሪ፣ በተቃዋሚ ፓርቲዎችም ጎድሎ ይታያል፡፡
ስለዚህ መንግስት የሚፈጥረው ጫና ለተቃዋሚዎች መዳከም አንድ ምክንያት ነው እንጂ ብቸኛ ምክንያት አይደለም፡፡ አንድ ተቃዋሚ ፓርቲ እኮ ጠንካራ ነው የሚባለው፤ መንግስት የሚያደርግበትን ተጽዕኖ ተቋቁሞ ማሸነፍ ሲችል ነው፡፡ መንግስት ተጽእኖ የማያደርግ ከሆነማ ሁሉን ነገር የተመቻቸ ከሆነማ ትግልም አያስፈልግም። አገራችን እንደ አሜሪካ ሆናለች ማለት ነው። መንግስት ተፅዕኖ የማያደርግ ከሆነ፣ በጣም የምንመኘው ደረጃ ላይ በቀላሉ ደርሰናል ማለት ነው፡፡ ተዝናንተን በምዕራቡ ዓለም እንደምናየው በምርጫ እየተወዳደርን አሸናፊና ተሸናፊ ልንሆን እንችላለን ማለት ነው፡፡ ግን እዚያ ደረጃ ላይ ለመድረስ ቀርቶ ጨርሶ አልተጠጋንም፡፡ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ ጫና የሚያደርግ መንግስት ነው ያለን፡፡ ይህን ለመለወጥም ነው የፖለቲካ ትግል እያካሄድን ያለ፡፡ ህዝቡን አስተባብረንና አታግለን፤ የመንግስት ጫና እንዲቆምና ለውጥ እንዲመጣ ማድረግ እንችላለን፡፡ ይልቅስ ትልቅ እንቅፋት የሆነብን ውስጣዊ ችግር እንዳለብን መገንዘብ አለማቻላችን ነው፡፡ ውስጣዊ ድክመቶችን ለመፈተሸ አለማድረጋችን ነው ካንሠር ሆኖ የሚበላን፡፡ በ1997 ዓ.ም ምርጫ ተቃዋሚዎች ጥምረት እየፈጠሩ የህዝቡን ትኩረት በመሳብ በምርጫ ውጤት አምጥተዋል፡፡ የፓርቲዎችን ብርቱ ፉክክር የሚያካሂዱበት ነፃነት ተፈጥሮ ነበር፡፡ ለ2007 ዓ.ም ምርጫ ግን ጥምረት የመፍጠር ህዝቡን የማንቀሳቀስና ብርቱ ፉክክር የማካሄድ ሁኔታ ጎልቶ አይታይም፡፡ ኢዴፓስ ለቀጣዩ ምርጫ ምን ያስባል? በቀጣዩ ምርጫ መሰረታዊ ለውጥ ይመጣል ብዬ አላስብም፡፡ አንደኛ ነገር ገዢው ፓርቲ ከስህተቱ እየተማረ አይደለም፡፡ አሁንም በየቀኑ የሚነግረን፤ ዲሞክራሲ ኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲ ሞልቶ እንደተትረፈረፈና ተቃዋሚ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ ለማድረግ ምንም ችግር እንደሌላቸው ነው፡፡ ይህቺ አገር በልማት ብቻ ሳይሆን በዲሞክራሲም እያደረገች እንደሆነ ነው ኢህአዴግ የሚነግረን። ይሄ ቀልድ ነው፡፡ በተጨባጭ ያለው ሁኔታ ኢህአዴግ እንደሚለው አይደለም፡፡ የዲሞክራሲ ስርዓት በአግባቡ በዚች አገር እንዲያብብ እያደረገ አይደለም።
ገዢው ፓርቲ ላይ ቁርጠኝነት እየታየ አይደለም፡፡ በተቃዋሚ ፓርቲዎች በኩልም አብዛኛው ውስጣዊ ድክመታቸውን ሳይፈትሹ ነባሩን አስተሳሰብና አቀራረብ እንደያዙ ናቸው፡፡ ስለዚህ በ2007 ዓ.ም ምርጫ፣ መሠረታዊ ለውጥ ያመጣል የሚል እምነት የለኝም፡፡ መሠረታዊ ለውጥ ቢመጣ የሚችለው እነዚህ ሁለት ጐራዎች ከስህተታቸውና ከችግራቸው ተምረው የተግባር ማሻሻያዎችን ሲያደርጉ ነው። ይሄን ሲያደርጉ አይታይም፡፡ አሁን የቀረው አንድ ዓመት ነው፡፡ በዚህ አንድ ዓመት ውስጥ መንገዳቸውን ካላስተካከሉ፣ ምርጫው ከአለፉት ምርጫዎች የተሻለ ይሆናል ብዬ አላምንም፡፡ በሌላ በኩል አብሮና ተቀናጀን የመስራት ፍላጎት ቢኖር ኖሮ ያለ ጥርጥር የተሻለ ነገር መስራት ይቻል ነበር፡፡ ተቃዋሚው ጎራ እርስ በርስ ተቻችሎ እንዲሰራ የሚያደርግ ሃይል ቢኖር ጥሩ ነበር፡፡ አቶ ልደቱ በሚቀጥለው ሳምንት፣ ከአቶ መለስ ዜናዊ ህልፈት ወዲህ ያለውን የኢህአዴግ፣ የመንግስትና የአገሪቱን ሁኔታ ይተነትናሉ፡፡ የኢትዮጵያ ሦስት ዋና ዋና ፈተናዎች ምን እንደሆኑ በመዘርዘር የመፍትሔ ሃሳቦችን ያቀርባሉ። የአረቡን አለም አዝማሚያዎችንና የግብጽና የአባይ ጉዳዮችን እንዲሁም የኢትዮጵያውያን ስደትን በተለከተም አቶ ልደቱ ሃሳባቸውን ይገልፃሉ፡፡
ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
ልጥፎች (Atom)