ኢሳት ዜና :-የመኖሪያና የስራ ፈቃድ የላችሁም በሚል ከሳዑዲዓረቢያ ወደ አገራቸው የሚመለሱ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ሲሆን ቁጥሩ መንግስት አስቀድሞ ካሰበው እጅግ አሻቅቧል፡፡ በዚህ ም ምክንያት ተመላሾቹን ለመቀበልና ለማቋቋም መንግስት በቂ በጀት አለመያዙ እንደ አገር አሳፋሪ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልጸዋል፡፡
መንግስት የተመላሾቹ ቁጥር 23 ሺ ገደማ መሆኑንና እነዚህም ወገኖች ለመመለስ መመዝገባቸውን በመግለጽ ለተመላሾቹ 50 ሚሊየን ብር እንደመበ መግለጹ ይታወቃል፡፡ ይህም ሆኖ የተመላሾቹ ቁጥር ከፍተኛ መሆኑ ከታወቀ በሁዋላ እንደገና መረጃውን በማሻሻል ተመላሾቹ ከ50 እስከ 80 ሺ እንደሚገመቱ ይፋ አደርጎአል፡፡ ይሁን እንጅ እስትናንት ድረስ ከ100 ሺ በላይ ሰዎች መመለሳቸውን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡ከነዚህ መካከል 8 ሺህ የሚሆኑት ነፍሰ ጡር መሆናቸው ተገልጿል ፡፡
መንግስት ለተመላሾቹ 50 ሚሊየን ብር መመደቡን ከመግለጽ ውጪ መልሶ ለማቋቋም ምንም ያሰበው
ነገር አለመኖሩን የጠቀሱት ምንጮቹ ተመላሾቹን ተቀብሎ በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ጊዜያዊ ማረፊያ ካቆየ በኃላ ክልሎች ስራ ይሰጡዋቹሃል በማለት እያባበለ ወደትውልድ አካባቢቸው እንዲሄዱ እያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ተመላሾቹ በሰው አገር መከራና ስቃይን ከማሳለፍ ባሻገር ያፈሩትን ሐብትና ገንዘብ ይዘው መመለስ አለመቻላቸውን ያስታወሱት እነዚሁ ምንጮች በዚህ ሁኔታ ላይ ያሉትንና በተስፋ መቁረጥ የተጎዱትን ወገኖች በባዶ እጅ ወደ ቤተሰብ መስደድ እጅግ አሳዛኝ ነው ብለዋል ፡፡

ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ