ማረሚያ ቤቶች ነው የሚሏቸው። ሆኖም የኢትዮጵያ እሥር ቤቶች በዜጎች ላይ ከፍተኛ ስቃይ፣ ድብደባ፣ ቶርቸር የሚፈጸምባቸው ናቸው። መጀመሪያው አብዛኛው ታሳሪ ባላጠፋው ጥፋት ነው “ሽብርተኛ” ተብሎ ወደ ወህኒ የሚወርደው። አገሩን እና ሕዝቡ በመዉደዱ፣ ፍርትህን ለመብት በመቆሙ። ያ ሳይንስ ደግሞ ህወሃቶች በ እስር ቤትም ከአዉሬ እንጂ ከሰው የማይጠበቅ ከፍተኛ ስቃይ እያደረሱባቸው ነው።
አቶ ዘመነ ምህረት የጎንደር ከተማ ነዋሪ፣ የመኢአድ ምክትል ፕሬዘዳንት ናቸው። እርሳቸውን እነ ሌሎች በርካታ የሰላማዊ ታጋዮች ሽብርተኞች ተብለው ታስረዋል።
“ራቁታችንን ትግሪኛ ተናገሩ ተብለነ ተገፈናል “ ሲሉ አቶ ዘመነ ምህረት በርሳቸው ላይ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ጓደኞቻቸው ላይ የደረሰውን ግፍ ለዳኛው ገልጸዋል።
ግንቦት 27 ቀን ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር። አቶ ለገሰ ወልደሃና የፍርድ ቤቱን ዉሎ እንድሚከተለው ነበር የዘገበው
የፍርድ ቤት ዉሎ -ለገሰ ወልደሃና
ግንቦት 27/09/2007 ዓም ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለሁለተኛ ጊዜ የቀረቡት የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት/መኢአድ/ አመራሮች ተከሳሾቾ እነ
1. ዘመነ ምህረት
2. መለሰ መንገሻ
3. ጌትነት ደርሶ
በ3:00 ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኘ ችሎት ተሠይመዋል። ከነሱ በፊት 7 የጋሞቤላ አካባቢ ተወላጅ የሚመስሉ ቀረቡ በመቀጠል 8 ሙስሊሞች በአንድ መዝገብ ቀረቡ
.............. እያለ ሁሉሞ ቀጠሮ እየተሠጣቸው ወጥተዋል መጨረሻ አካባቢ የታየው የነ ዘመነ ጉዳይ ነበረ ቀደም ሲል በቀረቡበት ጊዜ የክስ ቻርጅ ተነቦለቸው እንደነበር ዳኛው ጠይቋቸው አዎ ተነቦልናል ብለው መልሰዋል ፡፡
ቀደም ሲል እዚሁ ችሎት በቀረቡበት አለት ጠበቃ ማቆም ይችሉ እንደሆነ ተጠይቃችሁ ጠበቃ ተመካክራችሁ እንደምታቆሙ ነበር ምን አደረጋችሁ ሲል ዳኛ ጠይቋቸው ነበር የተለያየ ቦታ ስላለን መገናኘት እና መነጋገር ስላልቻልን ቤተሰብም በቅርብ ስለሌን ማድረግ አልቻልንም ብለው መልስ ሰጥተዋል።
ጌትነት ደርሶ ክሱም የሀሰት ስለሆነ ፍትህ አገኛለሁ ብየ ስለማላምን ጠበቃ ማቆም አያስፈልገኝም በማለት ተናግሯል ዳኛው ጌትነትን እንዲህ ብሎ መናገሩ ስህተት እንደሆነ በመገሰጽ አስቁሞዉታል።
ዘመነ ምህረት እና መለሰ መንገሻ ሁኔታዎች ምቹ ስላልሆነ ጠበቃ ማቆም የሚችል አቅም ሰለሌለን ጊዜያዊ የመንግስት ጠበቃ ይቁምልን ብለዋል።
ዘመነ ምህረት፣ ጓደኛየ ጌትነት የተናገረው የልቡን ነው። በምርመራ ወቅት ልብሳችንን አስወልቀው እራቁታችንን ትግሪኛ ተናገሩ እየተባልን ተደብድበናል። ጌትነት ብሶት ስላለበት ነው “በአማራነታችን ተደብድበናል” እያለ ሲናገር የነበረው ሲል፣ ፓሊሶቹም ከዳኛው ይልቅ ቀድመው ለማስቆም ሙከራ አድርገው የነበረ ቢሆንም፣ በኋላ ዳኛው ራሳቸው አቶ ዘመነ እንዳይናገር አስቁመዉታል። ዳኛው “እዛ የነበረውን ስሜት እዚህ አታንፀባርቁ። ለቀረበባችሁ ክስ ማስረጃ ከሌለ አይፈረድባችሁም። ፍረድ የምንሰጠው በማስረጃ ነው” በማለት እንዳይናገሩ ከልክሎ ሊያማክራችሁ የሚችል ጠበቃ ማረሚያ ቤት ድረስ መጥቶ ያማክራችኀል በማለት ቀጣይ ቀጠሮ ሰኔ 11/10/2007 እንዲቀርቡ በማዘዝ የእለቱ ችሎት ተዘግቷል ፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ