ዓርብ 18 ዲሴምበር 2015

‘አማራ ነን‘ የወልቃይት ሕዝብ ያልተመለሰ ጥያቄ – የወልቃይት ሕዝብ አቤቱታ እንደሚከተለው ቀርቧል።


የወልቃይት ማህበረሰብ ከአዲስአበባ በ977 ኪሎሜትር ላይ በትግራይ ክልል ስር በሁመራ ዞን አድረመጭ ወረዳ የሚገኝ ነው።
በ11ሺ 149 ስኩዌር ኪሎሜትር ላይ ሰፈረውና 413ሺ564 ሕዝብ እንዳለው የሚነገርለት የወልቃይት ማህበረሰብ ባለፉት 24 ዓመታት የአማራ ብሄር ነን በሚል በአማራ ክልል ለመካለል ተደጋጋሚ ጥያቄዎች ሲቀርብ ቢቆይም ጥያቄው በትግራይ ክልል በአዎንታ መልኩ ባለመታየቱ ለእስር፣ ለሞትና ለስደት መዳረጉን ከሕዝቡ የተወከሉ የኮምቴ አባላት ያስረዳሉ። ባለፉት 24 ኣመታት አማራ ነን የሚል የብሄርተኝነት ጥያቄ በማቅረባቸው ብቻ 116 ያህል ሰዎች ታስረው የገቡበት እንዳልታወቀ የኮምቴ አባላቱ በስም ዝርዝር አሳውቀዋል። በተጨማሪም ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ንብረታቸው በጠራራ ጸሀይ የተነጠቁ ሰዎችንም ዝርዝር እንዲሁ በማስፈር አቤቱታቸውን ለፌዴሬሽን ም/ቤት እና ለሰብዓዊ መብት ኮምሽን ሰሞኑን በጹሑፍ አሳውቀዋል።
የወልቃይት ሕዝብ አቤቱታ እንደሚከተለው ቀርቧል።
……………

የወልቃይት የአማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄ መነሻ፣

በመሰረቱ የወልቃይት የአማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄ አሁን የተነሳ ጥያቄ ሳይሆን ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ የተነሳና በሕገ-መንግስቱ የሰፈሩትን ሃሳቦች ታይተው ምላሽ ያልተሰጠው በየጊዜው እየተንከባለለ  የመጣ ነው። ጥያቄው እንደ ጥያቄ ማንሳት በሕግ እንደሚያስቀጣ ሕገመንግስታዊ መብት ነው ብሎ እንደመብት ተደርጎ ባለመወሰዱ የተነሳ ሲንከባለል የቆየ ጥያቄ እንጂ አዲስ ጥያቄ አይደለም።

የወልቃይት የአማራ ብሔተኝነት ጥያቄ እንደ ጥያቄ ሲነሳ ዋናው መነሻው ሕገ-መንግስቱን መሠረት ያደረገ ነው። በሕገ-መንግስቱ አንቀፅ 39 ተራ ቁጥር 2 ተራ ቁጥር 5 እንደሚከተለው ያስቀምጠዋል።

ተራ ቁጥር 2 “ማንኛውም የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰብ ህዝብ በቋንቋው የመናገር የመፃፍ ቋንቋውን የማሳደግ እና ባህሉን የመግለፅ የማዳበር የማስፋፋት እንዲሁም ታሪኩን የመንከባከብ መብት አለው” ይላል። ከዚህ በተጨማሪም በተራ ቁጥር 5 በዚህ ሕገ-,መንግስት ውስጥ “ብሔር ብሔረሰቦች ሕዝቦች ማለት ከዚህ ቀጥሎ የተገለፀውን ባህሪይ የሚያሳይ ማህበረሰብ ነው። ሰፋ ያለ የጋራ ጠባይ የሚንፀባርቅ ባህል ወይንም ተመሳሳይ ልምድ ያላቸው ሊግባቡ የሚችሉበት የጋራ ቋንቋ ያላቸው የጋራ ወይም የተዛመድ ህልውና አለን ብለው የሚያምኑ የሥነ-ልቦና አንድነት ያላቸውና በአብዛኛው በተያያዘ በመልክዓምድር የሚኖሩ ናቸው።

በሕገመንግስቱ አንቀፅ 39 ተራ ቁጥር 2 እና 5 በተቀመጠው መሰረት እኛ የወልቃይት ሕዝቦች የራሳችን አማራዊ ባህል ያለን ሲሆን ይህ ባህል ከትውልድ ትውልድ በቅብብሎሽ የተረከብነው እና ከዘመን ዘመን እያደገ የመጣ የነበረ ነው። ሆኖም ግን በዚህ 24 ዓመታት ውስጥ ይቅር የራሳችን ባህል ማሳደግ፣ ማስፋፋት፣ መከባከብ ይቅርና እነሆ የማንነታችን መገለጫ የሆነው ባህላችን እየጠፋ በሌላ ባህል እየተተካ የእኛ ባህል እየከሰመ በምትኩ የሌላ ባህል የሚያድግበት የሚስፋፋበት ሁኔታ ተፈጥሯል። ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው ህገመንግስቱ ያስቀመጠው መብቶቻችን ተረግጦ በምትኩ አዲሱ ትውልድ የሌላ ብሔር ባህል እንዲቀበል በመደረጉ የአንድ ብሔር ባህል ጠፍቶ በሌላ ባህል መተካት ሕገመንግስታው ጥሰት መሆኑ እየታወቀ በእኛ ላይ ይህ መሰል ሕገ-መንግስታዊ የመብት ጥሰት የተካሄደብን ስለሆነ ይህን ሕገ መንግስታዊ ጥሰት ቆሞ ታሪካችን ወጋችን ባህላችን በአጠቃላይ ማንነታችን ወደሚከበርበት አማራ እንድንከለል የተነሳ ጥያቄ ነው።

በሌላ በኩል ከደርግ ውድቀት በፊት ሃገራችን በተማከለ አስተዳደራዊ ስርዓት ስትመራ በነበረበት ወቅት እኛ የወልቃይት ህዝቦች በጎንደር ክ/ሃገር በወገራ አውራጃ ውስጥ ስንተዳደር የነበርን ከአማራ ህዝብ ጋር ተፋቅረን ተመሳሳይ ሳይሆን አንድ አይነት ባህል ወግ ታሪክ ያለን የስነ ልቦና ትስስር ያለን በተያያዘ መልክአምድር ጋር የምንኖር ህዝቦች ሁነን እያለን ህገ መንግስቱ ባስቀመጠው አቅጣጫ እነዚህ እላይ የተገለፁትን የብሔር ብሔረሰብ መገለጫ ተጠቃሚ ሳንሆን ቀርተናል። ያለ ህዝቡ ፍላጎትና ምርጫ ተከለልን እንጂ በራሳችን ፍቃድና ሕገ-መንግስቱ ባረጋገጠልን መስፈርት ተመስርቶ ባለመካለላችን ማንነታችን እንዲጠፋ አድርጓል።

ስለሆነም ዛሬ በዓለማችን ሆነ በሃገራችን ዴሞክራሲ በማደግ ላይ ነው። ምንጊዜም ቢሆን ዴሞክራሲ የሚያድገው በሂደት ስለሆነ ትላንትና እንደነውር ወይንም እንደወንጀል የሚታዩ የነበሩ፣ ነገር ግን የዴሞክራሲ መብቶች የሆኑ ጊዜአቸው ሲደርስ መብት ሁነው ሲገኙ በዴሞክራሲ ስርዓት መልስ ያገኛሉ። ስለዚህ በሀገራችን ሁሉን ያካተተ ህገመንግስት አለን። ስለዚህ ሕገመንግስት ሲባል ክብረ መስዋትነት ተከፍሎበታል። በመሆኑም በሕገ መንግስቱ አማካኝነት የሚመለስ ጥያቄ እስከአለን ድረስና ይህን ጥያቄ የሚመልስ ሥርዓት እስካለን ድረስ የወልቃይት የአማራ ብሔርተኝነት ጥያቄ ማነሳታችን ወንጀል ሳይሆን ሕገመንግስታዊ መብታችን መሆኑ አሁንም ሊታወቅልን ይገባል።

በወልቃይት ሕዝብ የደረሱ የፖለቲካ ተፅዕኖዎች

  •    ልጆቻችን በቋንቋቸው እንዳይማሩ በግድ ትግርኛ እንዲማሩ ተደርገዋል፣
  •    በየትኛው መ/ቤት የስራ ቋንቋ በግድ በትግርኛ እንድንናገር ተገደናል፤
  •    የአማርኛ ባህል ቀይራችሁ የትግርኛ ባህል በግድ ተቀበሉ እየተባልን ነው
  •    የአካባቢያችን ጥንታዊ ያሀገር፣ የወል እና የጋራ ስሞች ማትም የወረዳ፣ ከተማ መንደር፣ ወንዝ ጋራ ሸንተረር ምንጭ በትግራይ ስም ተሰይመዋል።
  •    በትግራይ ባሉ መስሪያ ቤቶች የወልቃይት ተወላጆች 5 በመቶ የትግራይ ተወላጅ 95 በመቶ ሲሆን፤ ያሉትም እኩል መብትና ስልጣን የላቸውም፤
  •   ትግራይ ክልል መሆን አንፈልግም ብለው የተቃወሙትን ከ300 በላይ የሚሆኑ የወልቃይት ተወላጆች ከየቤታቸው በጨለማ ታፍነው ተወስደው ያለፍርድ ጠፍተዋል። ለዚህ አባሪውን መመልከት ይቻላል። የእነዚህ ወገኖች በአመለካታቸው መጥፋት ዋናው ምክንያት የማንነት ጥያቄ በማንሳታቸው በመሆኑ የወገኖቻችን መጥፋት ሕገ-መንግስታዊ ጥሰት ስለሆነ ይህን የፈፀመው የትግራይ መንግስት መሆኑ፤
  •    ወልቃይት በመወለዳችን በማንነታችን እንድናፍር ሁነናል፤
የወልቃይት ህዝብ በኢኮኖሚ የደረሰበት በደል፣
  •    ትግራይ አይደለንም ያሉትን በቀጥታ ንብረታቸውን ሀብታችን ተወርሰዋል። ሃብትና ንብረታቸው የተወሰደባቸው ዝርዝር ከአባሪው ጋር ተያይዟል፤
  •    መሬታቸው ተነጥቆ ለትግራይ ተወላጅ በመስጠት የወልቃይት ተወላጆች ወደ ድህነት እንዲወርድ ተደርገዋል።
  •    በግልባጩም የትግራይ ተወላጅ አለአግባብ ሃብታም እንዲሆኑ ተደርጓል
ለዘመናት የወልቃይት ህዝብ ገበሬ ሲያርሰው የነበረ መሬት ተነጥቆ ለትግራይ የእርሻ ድርጅት ተሰጥቷል። እኛ የት እንውደቅ ተብሎ አቤቱታ እንኳን ቢያቀርብ ህዝቡን የትግራይ ክልል በየአመቱ ለምዕራባዊ ዞባ እያለ አዳዲስ የመሬት አዋጅ በማውጣት ለትግራይ ተወላጅ በወልቃይት መሬት ባላባት ሆነው እንዲያስተዳድሩት ሲደግፍ የወልቃይት ህዝብ ግን ከመሬቱ እንዲነሳና እንዲሰደድ የተለያዩ እርምጃዎች ወስዷል። የዚህ ሰለባ የሆኑት ሰዎች የወልቃይት ተወላጆች ለአብነት በአማራ ክል በሶረቃ፣ በአብራሃጅራ፣ በአብደራሬ፣ በመተማ፣ በቋራ በሽህዲ፣ በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል እና በጋምቤላ ክልል ተሰደው ይገኛሉ። የትግራይ ተወላጆች ግን በሰፈራ የመጡ አሁን ከሁለት ሄክታር አሳልፈው የአምሳ እና የመቶ ሄክታር ከዛም በላይ ባለቤቶች ሆነው ይታያሉ። በአጠቃላይ በአካባቢያችን አልምተን እንዳንጠቀም እድሉ ተፈፅሞብናል።

በወልቃይት ሕዝብ በማህበራዊ ኑሮ ላይ የደረሰው ጉዳት፣
  •   ከመንገድ አንጻር የትግራይ አካባቢ ከወረዳው ቀበሌ የሚያገናኝ ጥርጊያ አብዛኛው ተሰርቷል። የወልቃይት አካባቢ ግን ከወረዳ ቀበሌ ይቅርና ከወረዳ ወደ ወረዳ የሚያገናኝ አንኳን በቅጡ ተሰርቶ አይታይም። ዛሬም የወልቃይት እናት መኪና አጥታ በወሊድ የምትሞት ናት።
  •   ውሃ ዛሬ በብዙ የትግራይ አካባቢ ንፁህ ውሃ ሲጠጣ የወልቃይት ህዝቦች ግን እንስሳ እና ሰው በአንድ የሚጠቀሙበት በብዙ ቦታ ይታያል።
  •   ትላንትና የመጣ የትግራይ ሰፋሪ ህዝብ ቧንቧ ውሃ ሲዘረጋለት ጥንታዊ የወልቃይት ህዝብ ግን ምንም ውሃ እና የጉድጓድ ውሃ ሲጠቀም ይታያል የህክምና ተቋማትም ተመሳሳይ ለትግራይ ተወላጆ በሚጠቅም መልኩ የተሰራ ነው።
  •   የትምህርት ተቋማትም አንድም ኮሌጅና ዩኒቨርስቲ የለም
የወልቃይት ህዝብ ልጆቹን አስተምሮ በተወለዱበት አገር ስራ ቅድሚያ መስጠት እና ማግኘት ሲገባቸው ቅድሚያ ለትግራይ ተወላጆ የስራ ቦታ እና እድል ይሰጣል ሊሰጥ ከሆነ ደግሞ በናቱ ወይም በአባቱ የትግራይ ዘር መወለድ ቅድሚያ በሚሰጥ ይጠናል። አጠቃላይ የወልቀቃይት ህዝብ ማህበራዊ ኑሮውን ከትግራ ተወላጆች ተጠግቶ እንዲጠቀም የተፈረደበት ይመስላል። ከላይ በዝርዝር ለመግለፅ እንደተሞከረው አሁን ሀገራችን በዴሞክራሲና በልማት ጎዳና ባለችበት ወቅት ምንም እንኳ አንዴት እነዚህ ችግሮች ሊከሰቱ ይችላሉ ብሎ የሚጠይቅ አካል ስለማይጠፋ የተዘረዘሩትን ችግሮች ለመፈፀማቸውና እየተፈፀሙ እንዳሉ ዋናው ምስክር ህዝባችን ስለሆነ ህዝባችን የፌዴሬሽን ምክር ቤት እንዲያነጋገርልን።

የፌዴሬሽን ም/ቤት ባለው ስልጣንና ኃላፊነት በሰላማዊ መንገድ ያነሳነው የዴሞክራሲ ጥያቄያችን ተመልክቶ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጠን፣ እኛ የህዝባችን ተወካዮች ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ህዝባችን የደረሰበት ሕገመንግስታዊ ጥሰትና እየደረሰበት ያለ በዴሞክራሲ መንገድ እንዲፈታ ከህዝባችን ጋር ለመወያየት እንዲፈቀድልን፣ የህግ ከለላ እንዲሰጠን። በሌላ በኩል ወደእዚህ የመጣን የህዝባችን ወኪሎች ስንመለስ በራሳችን፣ በቤተሰቦቻችንና በሀብታችን ላይ ጉዳት እንዳይደርስብን የሕግ ከለላ እንዲደረግልን በታላቅ ትህትና እንጠይቃለን።

ልጆች በጥይት አይቀጡም፣ የትኛው መንግስት ዛሬ ተማሪዎችን በጥይት ይደበድባል?

ልጆች በጥይት አይቀጡም፣ የትኛው መንግስት ዛሬ ተማሪዎችን በጥይት ይደበድባል?

ዛሬ የዓለም መሪዎች በፓሪ ፈረንሳይ ስለ ዓለማችን ያየር ንብረት ችግሮች እየመከሩ ነው።ችግሩ ደግሞ ቀድሞ ሰለባ ያደረገው ደሃ አገሮችን መሆኑ ግልጽ ነው።ኢትዮጵያም አንድዋ ናት።ከኢትዮጵያ ህዝብ አስራ አምስት ሚሊዮን ለራብ መጋለጡ መደበቅ የማይቻል እውነት ነው።ወያኔ ሃላፊነት ያለው መንግስት ቢሆን እዲህ ጊዜ የማይሰጥ ችግር ላይ ያተኩር ነበር።የአስራ አምስት ሚሊዮን ህዝብ ለራብ መጋለጡን የአውሮፓ ህብረት ጉዳዬ ብሎ ሲመክርበት ህወሃት ይህን ችግር ከፖለቲካ ተቃውሞ መለየት ተስኖት ከውይይቱ እንኳን ለመሳተፍ አልመረጠም።ካአየር ንብረት ችግሩ እጅግ የከፋው የአስተዳደር ጉድለቱ የሚፈጸመው ግፍ ነው በኢትዮጵያችን።ኢትዮጵያ መንግስትዋ ሽብርተኛ ያየር ንብረት ችግሯ በጣም ፈታኝ የሆነበት ዘመን ዛሬ ነው።ያየር ንብረት ችግር ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ልጆችዋን እየገበረች ነው።ልጆች በጥይት ይቀጣሉ።የህወሃት ግፍ ይህ ነው።TPLF killing Oromo students
ህወሃት የዛሬውን አይበለውና የትግራይ ህዝብን አታግልለታለሁ ሲል “ሃረሽታይ ሸቃላይ” ወይም አርሶአደር ላብአደር ይል ነበር። ለህዝብ እንደቆመ ሁሉ።ዛሬ “መሬት ላራሹ”ን ተረተረት አድርጎ የኢትዮጵያን አርሶ አደር መሬት ንብረቱን ቀምቶ እያራቆተው ይገኛል። ከአርሶ አደሩ አብራክ የወጡትን ልጆቹን ለአርሶ አደሩ በደል ቢነሱ በጥይት ይደበድባቸዋል። የዓለም ዜና ይህን ባያተኩርበትም ዛሬ የኢትዮጵያ ሁኔታ በከፋ መጠን እየተናጋ መሆኑን ማንም ሊክድው አይችልም።በዓለም ተበትነን ያለነው ዜጎች በየሰዓቱ የምንከታተለው ይህንኑ ነው።
ማንም ህብረተሰብ ቀጣዮን ትውልድ ያስተምራል።ፈደል ተቆጥሮ፤ሂሳብ ተምሮ፤ ቋንቋ ሰዋስው አጥንቶ፤ሳይንስን ተቃምሶ የህብረተሰብ ጥናት ታሪክንም ለካክፎ ወደከፍተኛ ትምህርት ማምራት አለ።ከፍተኛ ትምህርት አንድ ህብረተሰብ ለወጣት ዜጋው የሚያቀርበው ትልቁ የውቀት ገበታ ነው።አላፊነት የሚሰማው አገሩን የሚወድ ትውልድ የሚዘጋጅበት፤ራስንም ዓለምን ለማወቅ የሚሞከርበት የድሜ ዘመን የሚልፍበት ነው ማለት ስተት አይሆንም።በከፍተኛ ትምህርት ቅጥር ውስጥ እማይጠየቅ የለም።እማይፈተን የለም። ሁሉም በነጻነት ይፈተሻል።ይሞከራል።ጉልበት፤ ስልጣን አለው ተብሎ የሚፈራ የለም።በከፍተኛ ትምህርት ተቋም ሁሉም ይተቻል።ይጠናል።ይተነተናል።የበደለም ይኮነናል።ለውነት ለፍትህም ቆምን ይባላል።ዛሬ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለተቃውሞ ቢወጡ ለአገር ለወገን ብለው ነው።ተቃወሞ ወግ ነው።ልጆች ስለተቃወሙ በጥይት አይቀጡም።የትኛው መንግስት ዛሬ ተማሪዎችን በጥይት ይደበድባል ? ፈሪው ህወሃት ብቻ!ጨካኙ ህወሃት ብቻ!ከፖለቲካ ድርጅትነት ዘቅጦ የእጽ ሻጭ ካርቴል የነብሰገዳይ ጥርቅም ዓይነት የሆነው ህወሃት ብቻ!
ህወሃት መሩ መንግስት ከፍተኛ ትምህርት ቅጥር ግቢን የሞት አውድማ ያደረገው ገና ድሮ ነው። የመለስ ዜናዊም “ሌጋሲ” “ትሩፋት” አንዱ ይህ ነው። ሰሞኑን በሀረር ሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ የሆነው ዘግናኝ ነው። በሌሎቹም ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁ። የህወሃት አገዛዝ ከጅምር አካሄዱ ይሄው ጥፋት ነበር።በዘውዱ ስርዓት ፖሊስ ዩንቨርሲቲ ቅጥር ሲገባ እጅግ ይኮነን ነበር።ወታደራዊ ደርግም ወጣቱን በቀይ ሽብር ቢጨፈጭፍም እዲህ እንደ ህወያት መሩ መንግሰት ዩንቨርሲቲውን የጦር ቀጠና አላደረገውም ነበር።ህወያት መሩ መንግሰት ቁንጮ ላይ ያሉት ጥራዝ ነጠቅ የዛሬ ተራ ቀማኞች “መሬት ላራሹ” ካለው ትውድ እንደመር ይሉ ይሆን ?ያትውልድ ህወያት የሚባል ጉድ ትቶ አለፏል።ግን የኢትዮጵያ ተማሪዎችን አኩሪ የትግል ታሪክን ህወሃት አይሽረውም።እዚህ ቀጣይ የሞት ሂደት ውስጥ የከተተው የቀማኛ ቡድንን አስወግዶ የዜግነት ክብር የነገሰባትን፤እኩልነት የሰፈነባትን ነጻ ኢትዮጵያ ከህዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሀይሎች ጋር በመሆን ይመሰርታል።እልሙ ኢትዮጵያ! ናት።ድል የሚገኘው በህብረት ትግል እንደሆነ ይገነዘባል።
የኢትዮጵያ ተማሪዎች ቀድሞ ሲነሱ ኢትዮጵያ! ነው ያሉት።”መሬት ላራሹ” የተባለው ለትግራዩ፤ለኦሮሞው፤አማራው፡ለአፋሩ፤ለሱማሌው ለደቡቡ ለሁሉም ነው፤የህወሃት የአዲሱ አገዛዝ አናት ላይ መሆን እንጂ ”መሬት ላራሹ” ዛሬም ፍቺ ያላገኘ የዴሞክራሲ ጥያቄ ነው።የምናየውን እልቂትን የሚገፋው ምክንያት ይሄው ነው።”አዲስ ንጉስ እንጂ ለውጥ መቼ መጣ?” ቴዲ አፍሮ ጨርሶታል። እኩይ ንጉስ ነው የመጣ!
በኦሮሚያ ክልሎች የሆነው ከላይ ያልኩት ነው። የከፍተኛ የትምህርት ገበታን የሞት አውድማ ማድረግ ነው ።ተማሪዎች ልክ ድሮ የኢትዮጵያ ተማሪዎች እንደታገሉት ሁሉ “መሬት ላራሹ” ብለው ዛሬም እየታገሉ ነው።የወገንን መሬት “ኢንጉርጉረምቱ!” አይሸጥም ! ነው ያሉት።ጥያቄው የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች ሁሉ ጥያቄ ነው።በተለይ የኦሮሚያ ክልል ብቻ ብሎ የሚፈረጅ አይደለም።የአፋሩ፤የጋምቤላው በደል ከአማራውና ከኦሮሞው የሚለይ አይደለም።
የገጠመንን ችግር የከልል ማድረግ የኢትዮጵያን ሁኔታ ጠንቅቆ አለመረዳት ነው።የልጆቻችን ተስፋም እመረቃለሁ፤ ለማዕረግ እበቃለሁ እንጂ እሞታለሁ መሆን አይገባውም። የልጆቻችን ሞት የኢትዮጵያዊ ወገናችንም ሁሉ ሞት ሊያገሸግሸን ይገባል።ኢትዮጵያ ተበደለች። ልጆችዋን ገበረች።ተምሬ ወግ ማእረግ አይባታለሁ የምትባለዋን ኢትዮጵያን የምናይበት ጊዜው እሩቅ አይሆንም።የሚጠይቀው ህብረታችንን ብቻ ነው። ህወሃት መሩን መንግስት ተባብረን እንሸኝ።ከዚህ ወዲያ ድርድር የለም።
የኦሮሚያ ክልልን መዝረፍና ማስዘረፍ የአማራውን ክልል የሞት፤የቃጠሎ የእስራት ቀዬ ማድረግ በሁለቱም የኢትዮጵያ አካሎች ላይ የዘር ማጥፋት ወጀልን ወደ መፈጸም የሚቀርብ ክፋት ነው።የጎንደር ህዝብ በደል የኢትዮጵያ በደል ነው።በተለይ አጠገቡ ለሆኑት የትግራይና የወሎ ህዝቦች በደል ነው።ጎንደርን መሸንሸን እንደምን ይሆናል ? የኢትዮጵያ አንድነት ምንጭ መሰረቱን ?! የወልቃት አልበቃ ብሎ ቅማንትን! ከወንድም እቶቹ ማጋጨት ?ወሰን ድንበር ለባዕድ ለመለገስ ሸር ጉድ? አዲሳባን እናስፋ በማለት ዝርፊያ አሁን ይቁም! ራብም እየፈጀን ልጆቻችንም እየሞቱ እየተቃጠልን እየደማን እስከ መቼ? ወገኖቼ።ዘረፋው እስከመቼ? ምን እንጠብቃለን።
ለደሃው የኢትዮጵያ አርሶ አደር አለኝቶቹ ዛሬ በዳያስፖራ የምንገኝ ነን!
በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የህወሃት ገዳዮች የሚፈጽሙትን በህብረት እናውግዝ!
ኢትዮጵያን ከክፉ መከራ አላህ የሰውራት! ሁላችንም እየጸለይን እንታገል!

ለወያኔ ድርጊት፣ ምን ስም እናውጣለት (ይገረም ዓለሙ)

ለወያኔ ድርጊት፣ ምን ስም እናውጣለት (ይገረም ዓለሙ)

ይገረም ዓለሙ
ወገንን ጨፍጫፊ ቆዳው የነጣ ነው
በአበሻ የሚጨክን ፈረንጅ ብቻ ነው፤
እያለ የሚያስብ የዋህ ፍጡር ማነው
ጨፈጫፊ ከሆነ አበሻም ጣሊያን ነው
እንቶኔም በተግባር ሲኞር እንቶኔ ነው፤
Police brutality in Ethiopia
በየግዜው እየከፋ የሄደውን የወያኔ አረመኔነትና የሀገራችንን ጉዞ ወዴትነት ሳስብ ትውስ ያለችኝን ይህችን ስንኝ ወደ ማስታወሻየ ገልብጬ ያኖርኳት በ1980ዎቹ መጨረሻ ግድም ለንባብ ይበቁ ከነበሩት መጽሄቶች ከአንዱ ነው፡፡ ወያኔ ዴሞክራት መስሎ ለመታየት በሞከረበትና ትክክለኛ ማንነቱ ገሀድ ወጥቶ ብዕርን ከጠመንጃ አስበልጦ መፍራት ባልጀመረበት በዛ ወቅት እንዲህ የጻፉት ሰው ዛሬ በህይወት ካሉ ምን ሊሉ እንደሚችሉ መገመት ይቸግራል፡፡
ወያኔዎች ደርግን በጨፍጫፊነት በማውገዝ ዛሬም ድረስ ፈሺስት ናዚ ወዘተ በማለት ይገልጹታል፡፡ በዘመነ ደርግ የተፈጸመውን ቀይ ሽብርም ለአንድ ሰሞን የፖለቲካ ፍጆታ ሊጠቀሙበት ሞክረዋል፡፡ ግን ካወገዙት ተግባር ተምረው ከተጸየፉት ድርጊት ርቀው ሊገኙ አልቻሉም፡፡ በርግጥም ከጅምሩ ስለ ቀይ ሽብር የነበራቸው አያያዝ ሊማሩበት ሳይሆን ሊያደናግሩበት፤ ለተበዳዮች ፍትህ ሊያስገኙበት ሳይሆን ጥላቻን ሊያነግሱበት እንደነበረ መለስ ብሎ በማስታወስ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ከቀይ ሽብር ቢማሩ ኖሮ ራሳቸው ያቋቋሙት የቀይ ሽብር ኮሚቴ ይዞት የነበረውን “ያለመቻቻል ፖለቲካ ሰማዕታት፣መቼም እንዳይደገም” የሚለውን መርህ ተግባራዊ ባደረጉና እንዲህ የለየላቸው ጨፍጫፊ ባልሆኑ ነበር፡፡
የቀይ ሽብር ነገር ለወያኔ የፖለቲካ ካርድ በነረበት ወቅት የቀይ ሽብር ኮሚቴ ባዘጋጀው አንድ የውይይት መድረክ ላይ የጥናት ወረቀት ያቀረቡት ፕ/ር ባህሩ ዘውዴ “…የፖለቲካ ልዩነቶችንም በተመለከተ አንዱ ወገን ምንግዜም ቢሆን ፍጹማዊ እውነትን ሊታደል እንደማይችል ተገንዝቦ የሌላውን ወገን ሀሳብ እህ ብሎ ማዳመጥ መቻል ይኖርበታል፡፡ የተቀዋሚ ወገን አየለ ብሎ ቃታ ለመሳብ መጣደፍ ዞሮ ዞሮ ሀገርን በብርቱ የሚጎዳ መሆኑን ከ « ቀይ» ሽብር ያተረፍነው ትልቁ ትምህርት ነው” ብለው ነበር፡፡ ነገር ግን ወያኔዎች ቀይ ሽብርን ያራገቡት ፖለቲካ ሊቆምሩበት እንጂ ሊማሩበት ያለመሆኑን ውለው ሳያድሩ በጀመሩት የሁሉም ነገር መፍትሄ ከጠመንጃ ይመነጫል አይነት ተግባራቸው አሳይተውናል፡፡
ሌላው ተናጋሪ የነበሩት ዶ/ር የራስ ወርቅ አድማሴ ባቀረቡት ጽሁፍ ደግሞ “ከኛ ትውልድ ስህተት በመማር የልጆቻችንን ትውልድ ከፖለቲካ ግድያ፣ከዘር ማጥፋት ፍጅትና ከስጋትም ጭምር ነጻ በሆነችና ፍትህ በነገሰባት ኢትዮጵያ እንዲኖሩ እንመኛለን፡፡ ይህን ምኞታችንን እውን ካደረግን ደግሞ እሱ ጊዜ የማይሽረውና የማያደበዝዘው ዕውነተኛው የሰማዕታት መታሰቢያ ይሆንልናል፡፡”» በማለት ዋናው ቁም ነገር የድንጋይ ሀውልት ማቆሙ ሳይሆን ካለፈው ተምሮ መሰል ጥፋት እንዳይደገም ማድረጉ እንደሆነ ነበር የገለጹት ፡፡ግና አንደ አለመታደልም ሆነና ወያኔን ሀይ የሚለውም ጠፋና ይሄው ዛሬ ድረስ ስጋቱም ፍጅቱም እንዳለ አለ፡፡
ባለፉት ሀያ አራት ዓመታት ወያኔ ከምንይልህ ቤተ መንግሥት ሆኖ የፈጸማቸው ኢ- ሰብአዊ ተግባሮቹን ለታሪክና ለትውልድ ፍርድ ትተን ዛሬም በእብሪትና በማን አለብኝነት የሚፈጽማቸውን ተግባራት ስናስተውል ጨፍጫፊ ከሆነ ሀበሻም ጣሊያን ነው የሚያሰኙ ናቸው፡፡ታዲያ እኒህን ከእለት እለት እየባሱ የመጡ አረመኔያዊ ድርጊቶቹን ምን ስም አንስጣቸው፡፡ ይመጥ አይመጥነው ባይታወቅም አንድ ሰሞን አንዳንድ ሰዎች ጥቁር ሽብር ማለት ጀምረው ነበር፡፡
ከወራት በፊት አቶ ኤፍሬም ማዴቦ “አይኔ እያየስ እዚህ ውስጥ አልገባም, መሠረት ሙሴ” በሚል ርዕስ ባስነበቡን ጽሁፍ ስሙ የተጠቀሰው ወጣት ከሌሎች ሁለት ወጣቶች ጋር ጎነደር መተማ ላይ ተያዘ፡፡ ሁመራ ተወስደው ጫካ ውስጥ ሊረሸኑ ጉድጓድ አፍ ላይ ቆመው ገዳዮቹ አንደኛውን ወጣት በጥይት መትተው ወደ ጉድጓድ ሲከቱት አይኔ እያየስ እዚህ ውስጥ አልገባም ያለው መሰረት እግሬ አውጪኝ ብሎ ሮጦ አካሉ በጥይት ቢነዳደልም አምልጦ በሻዕቢያ ወታደሮች እጅ መውደቁንና ታክሞ ድኖ ግንቦት ሰባትን መቀላቀሉን ነግረውናል፡፡( ይህን አንብበን ዝም ማለታችን ራሱ አስገራሚ ነው)
ወጣቱ በፈጣሪ ቸርነት በማምለጡና አቶ ኤፍሬምንም በማግኘቱ የአይን ምስክርነቱን ሊሰጥ ቻለ፡፡ ባይሆን ኖሮ ይኑሩ ይሙቱ ሳይታወቅ ቤተሰብም እርሙን ሳያወጣ ጫካ እንደተጣሉ ይቀሩ ነበር፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በየደረጃው ባሉ ዘመንኞች እየተረሸኑ በጅምላ የተቀበሩና በየጫካው የተጣሉ ዜጎችን ቤት ይቁጠራቸው ማለት ይቻላል፡፡ አንድ ቀን ግን መጋለጡ አይቀርም፡፡
እዛው ጎንደር ውስጥ የወንድሞቹ በረሀ መግባት በሰላም ለሚኖረው ክብሩ አሰፋ ወንጀል ሆኖ 18 ዓመታት አስፈርዶበት በጎንደር ወህኒ ቤት ስድስት ኣመታትን ካሳለፈ በኋላ ከእስር ቤት ተወስዶ መረሸኑን ከአርበኞች ግንቦት ሰባት መግለጫ አንብበናል፡፡ይህም ወያኔዎች ጠላታችን የሚሉትን ሰው አስረው እንኳን እንቅልፍ የማይወስዳቸውና ካልገደሉ የማይረኩ መሆናቸውን የሳየ ነው፡፡ በዚህ መልክ የተረሸኑ ወገኖቻችንስ ምን ያህል ይሆኑ?
ከሁለት ዓመት በፊት አዲስ አበባ ውስጥ ከስድስት ኪሎ ወደ ፈረንሳይ የሚሄደው መንገድ ሲሰራ ሶስተኛ ሻለቃ በመባል ይታወቅ የነበረውና ወያኔ ስሙን እየቀያየረ የሚጠቀምበት የጦር ሰፈር ጫፉ ላይ አጥሩ ፈርሶ ሲቆፈር የቅርብ ግዜ አስክሬን ከነተጠቀለለበት ብርድ ልብስ መገኘቱ ይታወሳል፡፡ በማህበራዊ ድረ ገጽም ምስሉ ተለቆ ለአንድ ሳምንት መነጋገሪያም ሆኖ ነበር፡፡ (ንዴት ቁጣችን፣ ተቃውሞ ፉከራችን ከአንድ ሳምንት አይዘል አይደል!) ሳይታሰብ በመንገድ ስራ ቁፋሮ ምክንያት ለእይታ የበቃው ያ የወገን አጽም የወያኔ የጦር ካምፖች ለወታደራዊ ተግባር ብቻ ሳይሆን ታፍነው ለሚሰወሩ ዜጎች ማሰቃያ መግደያና መቀበሪያነትም የሚያገለግሉ መሆናቸውን ያጋለጠ ነው፡፡ በዚህ መልክስ ስንት ወገኖቻችን በአረመኔዎች እየተገደሉ በየቦታው ተቀብረው ይሆን; ጠያቂ ጠፍቶ ጯሂ አልተገኝቶ ሆኖ እንጂ ቁፈራው ሰፋ ተደርጎ ቢቀጥል ብዙ ጉድ በተጋለጠ ነበር፡፡
የፖለቲካ ትርፍ አገኛለሁ ብሎ በደርግ እየተገደሉ በየቦታው የተቀበሩ ወገኖቻችንን አጽም እያወጣና በቴሌቭዥን እያሳየ ሲያስለቅሰንና ሲያላቅሰን የነበረው ወያኔ እሱ በተራው ሀያ አራት ዓመት ሙሉ አስሮ አሳቃይቶና ገድሎ ሊረካ አልቻለም፡፡ መታሰር መሰቃየትና መገደል በቃን ብለን ካላመረርንና ካልተባበርን አለበለዚያም ለወያኔ ሰጥ ለጥ ብለን ካላደርን በስተቀር ወያኔ ከዚህ አድራጎቱ መቼም የሚገታ አይመስልም፡፡ ግና ዘላለማዊ ምድራዊ ኃይል የለምና አንድ ቀን የጨለመው ሲበራ ህሊናቸው ፋታ ነስቶአቸው ወይንም ህግ አስገድዷቸው ወያኔ በዘመነ ሥልጣኑ እየገደለ በየቦታው ስለቀበራቸው ኢትዮጵያውያን የአይን እማኝነታቸውን የሚሰጡ ሰዎች መኖራቸው አይቀርም፡፡
ይሄው ሰሞኑን ደግሞ በየመድረኩ ስለፍትህ ስለ መልካም አስተዳደር ተቃውሞን በሰላማዊ መንገድ መግለጽ ስለመቻል ወዘተ እየደሰኮሩ በተግባር ግን በሰላማዊ መንገድ ጥያቄ ባቀረቡና ተቃውሞ ባሰሙ ወጣቶች ላይ ነብሰ ገዳይ ወታደሮቻቸውን አሰማርተው እያስደበደቡ እያሳሰሩና እያስገደሉ ነው፡፡ ለሀያ አራት አመታት በስልጣን ለመቆየት የቻሉት በማናቸውም ወገን የሚነሳን ማናቸውንም ጥያቄና ተቃውሞ በእስር በድብደባና በግድያ ጸጥ በማሰኘት በመሆኑ ሌላ ለጥያቄ መልስ መስጫ ዘዴም ሆነ ተቃውሞን ማስተናገጃ መንገድ አያውቁም፡፡
የአረመኔነታቸው ክፋት ጎንደር እስር ቤት ተቃጥሎ እስረኞች ህይወታቸውን ለማትረፍ ሲሮጡ እየተኮሱ ገድለዋል፡፡ ያለህበት ቤት ሲቃጠል አይንህ እያየ ዝም ብለህ ተቃጠል የሚሉ ነው የሚመስለው፡፡ እንደው እነዚህ ከእሳት የሚያመልጥን ዜጋ ተኩሰው የሚገድሉ ነብሰ በላዎች ከምን አይነት ማህጸን የተፈጠሩ ይሆኑ! ወይስ ወያኔዎች ሲያሰለጥኑዋቸው ከምግብ ወይንም ከሚጠጣ ነገር ጋር ቀላቅለው የሚሰጡዋቸው ከሰውነት ወደ አንስሳነት የሚቀይር፣ ሰዋዊ አስተሳሰብን አደድቦ ህሊና ቢስ የሚያደርግ ነገር ይኖር ይሆን፡፡
ወያኔዎች የአረመኔነታው ክፋትና የንቀታቸው ብዛት አንድም ገደሉ መቶ ለአፋቸው ይህል እንኳን በተፈጠረው ነገር እናዝናለን አይሉም፡፡ እነርሱ የሚያውቁት በሟች ቁጥር ላይ መሟገት ነው፡፡ ሰሞኑን የምንሰማውም ይህንኑ ነው፡፡
በሰላም ተቃውሞ በሚያሰሙ ( ቢቢስ ድንጋይ ይወረውሩ ይሆናል) ወጣቶች ላይ እንዲህ በየግዜው ግድያ የሚፈጽሙት ወያኔዎች ደርጎች ላይ እንደሆነው በአዲስ አበባ ከተማ በትላልቆቹ ባለሥልጣኖች ላይ ቢተኮስባቸው፣ ከመካከላቸው ቢቆስልና ቢሞትባቸው ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉ መገመት አይከብድም፡፡ አብርሀ ደቦጭና ሞገስ አስግዶም የጣሊያኑን ጀነራል በቦምብ ካቆሰሉ በኋላ ጣሊያኖች በአዲስ አበባ የፈጸሙት ጅምላ ፍጅት መቼም የሚረሳ አይደለም፡፡ ወያኔዎች ከእስከዛሬ ተግባራቸው እንዳወቅናቸው ከመካከላቸው አንድ ሰው ቢገደል ወይንም ቢቆስል ተመሳሳይ ተግባር ከመፈጸም ወደ ኋላ እንደማይሉ ፡፡ ታዲያ ይህን በቀይ ሽብር ለተጨፈጨፉ ወገኖች ሀውልት አቁሞ ጭፍጨፋ የሚፈጽም አረመኔ ቡድን ለእሱም ሆነ ለድርጊቱ ምን ስም እናውጣለት፡፡

የኦሮሞ ህዝብ ብሶት፥ ወደ የጋራ ነጻነት

የኦሮሞ ህዝብ ብሶት፥ ወደ የጋራ ነጻነት


“ከአዲስ አበባዉ የእርሻ መሬት እስከ አሜሪካዊ ቤተ መንግስት፥መብትን የማስከበር ጣምራ ሒደት!”
በአሜሪካዉ ቤተ መንግስት እና በዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የኢትዮጵያ መንግስት በሰላማዊ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ የሚያደርገዉን ግድያ፣ድብደባ፣ እስር፣ወከባና ማፈናቀልን በመቃወም በተደረገዉ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በመገኘት ሳዲቅ አህመድ ያዘጋጀዉ ልዩ ፕሮግራም።

Washington DC protest against the killing of Oromo students

ረቡዕ 11 ኖቬምበር 2015

ረሃቡና እድገታችን፡ ተጠያቂው ማን ነው? (በአብዱረዛቅ ሑሴን)

ክፍል አንድ፡ እድገቱን የጎሪጥ!
ምስራቅ አፍሪካ ላይ በዚህ አመት 22 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች በረሃብ እንደሚጠቁና ከዚያም ውስጥ 68% (15 ሚሊየኑ) ከኢትዮጵያ እንደሚሆን የተባበሩት መንግስታት እየተናገረ ይገኛል፡፡ መጀመሪያ ምንም አይነት ስጋት እንደሌለ፣ ከዚያም 4 ሚሊየን ቆየት ብሎ ደግሞ 8 ሚሊየን ህዝብ ተጠቂ እንደሆነ ዘግይተው ላመኑት ሹማምንቶቻችን ከፍተኛ ዱብ እዳ እንደሚሆንባቸው አያጠያይቅም፡፡ የሀገርም ውስጥ ይሆን አለም አቀፉ ህብረተሰብ አንድ ተመሳሳይ ጥያቄ እንደሚጠይቅ ይጠበቃል፡- ‪ላለፉት‬ አስር አመታት በሁለት ዲጅት ያደገ ኢኮኖሚ እንዴት የህዝቡ 15% በረገብ ሊጠቃ ቻለ?15 million people in need of food aid
ለዚህ ጥያቄ የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትራችን ያላቸውን የኢኮኖሚክስ እውቀት ተጠቅመው ቢያንስ መልስ ሚመስል ነገር ይሰጡን እንደነበረ እርግጠኛ መሆን ይቻላል፡፡ እሳቸው ከነጎዱ ወዲህ ግን ‪‎ወይ‬ አያውቁ፣ ወይ የሚያውቁትን አያመጡ፣ ወይ አይወጡ; ሆኖብን እንጨት እንጨት የሚል የወረዱ ትንታኔዎቻችን የሚሰጡን ከጠቅላይ ሚንስተሩ እስከ ኮሚኒኬሽን ሚንስትሮቻቸው ድረስ ያሉ ባለስልጣናት ግራ አጋብተውናል፡፡ የዋጋ ግሽበት ፣የኑሮ ውድነቶችን እና የመሰረታዊ አገልግሎት አቅርቦት እጥረትን የመሳሰሉ ችግሮች ሲነሱ አቶ መለስ በተደጋጋሚ የእድገታችን ውጤት እንደሆነ ለኛም ለተተኪዎቻቸውም ሲነግሩን ነበር፡፡ ይህ ምላሽ መንግስትን ከተጠያቂነት ባያስመልጥም በከፊልም ቢሆን ኢኮኖሚክሲያዊ መሰረት ያለው ምሁራዊ ትንተና ሊባል የሚችል ነው፡፡ ከሳቸው መሞት በኋላ የመጡ መሪዎቻችን ለተመሳሳይ ጥያቄዎች ተመሳሳይ መልስን ሲሰጡን ቆይተዋል፡፡ ራእያቸውንም ብቻ ሳይሆን ለጥያቄዎች የሰጡትንም መልሶቻቸውን እያስቀጠሉም ይገኛሉ፡፡ ረሃብ ሀገራችንን ተለይቷት ባያውቅም በዚህ መጠን ግን የሁለት ዲጅት እድገት ትርክት ከተጀመረ ወዲህ ስላልተከሰተ የቀድሞውም ጠቅላይ ሚንስትር አልተጠየቁምም ለወራሾቻቸውም መልሱን አላስቀመጡም፡፡ በተወሰኑ አጋጣሚዎች ወደ ሚዲያ ብቅ ያሉትም ባለስልጣናት ችግሩን ከመካድ፣ መጠኑን ከማስተባበልም አልፎ የወረዱ ምክንያቶችን ሲደረድሩ ታዝበናቸዋል፡፡ መልሽ ያጣውን ጥያቄ ዛሬ በከፊልም ቢሆን ለመመለስ እንሞክር፡፡
ረሃብ! ድሮና ዘንድሮ
የሰባ ሰባቱ ድርቅና ረሃብ ሀገራችንን አለም ፊት አንገት ያስደፋ አሳዛኝ ክስተት ነበር፡፡ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የተከሰተው ድርቅ ከፍተኛ የሆነን ረሃብና እልቂት አስከትሎ ነበር፡፡ ዶክተር እሌኒን የመሰሉ ምሁራን እንደሚሞግቱት በወቅቱ የሰሜኑ ክፍል በድርቅ ቢጠቃም በሌላው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ግን በቂ ምርት እንደነበረ ይገልፃሉ፡፡ ሀገሪቱ በዛ ወቅት ምርት ከተትረፈረፈበት ደቡብ እጥረት ወደተከሰተበት ሰሜን እንዲሄድ የሚያስችል በቂ የኢንፍራስትራክቸርና በተለይም የገበያ ተቅዋም አለመኖሩን ለችግሩ መባባስ እንደ ዋና ምክንያትም ያቀርባሉ፡፡ በሌላ አባባል በቂ የኢንፍራስትራክቸር ዝርጋታ ኖሮ በነበረና ምርትን ከፍላጎት ጋር ለማገናኘት የሚያስችል የገበያ መረብ ኖሮ በነበረ ድርቁ ያስከተለውን እልቂት መቀነስ ይቻል ነበር፡፡ ይህ ምልከታም በዶክተር እሌኒ መሪነት የተቋቋመውን የEthiopia Commodity Exchangeን ለመመስረት እንደ ዋነኛ መከራከሪያ ሆኖ በተለያዩ የጥናት ፅሁፎቻቸው ውስጥ ተካቶ እናየዋለን፡፡
አስከፊው የሰባ ሰባቱ እልቂት ከተከሰተ ከሰላሳ አመት በኋላም ይኸው ድርቅ አገሪቱን እያሳሰበ ይገኛል፡፡ እነ ዶክተር እሌኒ የሞገቱለት የኢንፍራስትራክቸርና የገበያ ተቋማት አለመኖር በፊት ከነበረው በእጅጉ የተሻለ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ጥርጥር የለውም፡፡ የመንገዶችም ሆነ የኮሚኒኬሽን ኢንፍራስትራችቸሩ ከድሮው ጋር ሊወዳደር በማይችል መልኩ አድጓል፡፡ በሀገሪቱ በየትኛውም ቦታ የአቅርቦት እጥረት እናዳለና ተመጣጣኝ ትርፍ ሊገኝ እንደሚችል የሚያውቅ ነጋዴ ወሬውን ሰምቶ ተኝቶ ያድራል ብሎ ማሰብ ይከብዳል፡፡ ወሬውን ለመስማት የሚያስችለው የኮሚኒኬሽን ኢንፍራስትራችቸርም ይሁን ምርቱን እጥረት ወደ አለበት ቦታ ወስዶ ለማትረፍ የሚያስችለው የትራስፖርት አማራጮች በብዙ እጥፍ ተሻሽለውለታል፡፡ ይህ ባለበት ሁኔታ ረሃቡ በድጋሚ መከሰቱ እነ ዶክተር እሌኒ የዘነጉት ወይም ትኩረት ያልሰጡት ሌላ ተጨማሪ የረሃብ መንስኤ እንዳለ ያሳየናል፡፡ ይህም የህዝብ ወይም የመንግስት የመግዛት አቅምን ይመለከታል፡፡
ነጋዴው ያማሩ መንገዶችን ተጠቅሞ ትርፍ ምርት ካለበት ወደ እጥረት ወደተከሰተበት የሀገሪቱ ክፍል ምርቱን ቢያቀርብ ለረሃቡ መፍትሄ ሊሆን አይችልም፡፡ በችግሩ የተጠቃው የህብረተሰብ ክፍል የምርት አቅርቦት ብቻም ሳይሆን የመግዛት አቅሙም ሊኖረው ይገባል፡፡ ምርቱ በድርቅ የረገፈበት ገበሬ በደህናው ጊዜ ተቀማጭ ሀብት እስካላፈራ ድረስ የምርት አቅርቦትን ማሻሻልና ማቀላጠፍ ብቻ በራሱ ችግሩን አይፈታውም፡፡ ኑሮው ከእጅ ወደ አፍ ስለሆነና የመግዛት አቅሙም ስለማይኖረው ከመንግስት እርዳታን መከጀል ብቸኛ ምርጫው ይሆናል፡፡ መንግስት ፈርጣማ አቅሙን በመጠቀም ትርፍ ምርት ካለባቸው አካባቢዎችም ካልሆነም የውጭ ሀገራት ገዝቶ ተጠቂውን ህዝብ የመድረስ ግዴታ ይወድቅበታል፡፡ አሁን እንደሚታየው ከሆነ ግን ገበሬውም ለነገዬ ብሉ ያስቀመጠው ቅሪት ሳይኖረው በረሃብ አለንጋ እየተጠበሰ፤ መንግስትም ሲፎክርበት የነበረው ፈርጣማ አቅሙ በሞት አፋፍ ላይ ላሉት 15% ህዝቡ የቁርጥ ቀን ደራሽ መሆን ያዳገተው ይመስላል፡፡ ላለፉት አስርት አመታት ተኣምራዊ እድገትን ስታድግ የነበረችው ኢትዮጵያ፤‪‎ግብርናን‬ መሰረት ያደረገ; የእድገት ስትራቴጂ እየተከተለች እንዳለች የምትነግረን ኢትዮጵያ፤ ገበሬዋ እራሱን መመገብ ሲያቅተውና መንግስቷም የክፉ ቀን ደራሽ መሆን ሲሳነው እድገቱን የጎሪጥ ብናየው ይፈረድብን ይሆን?

ቅዳሜ 7 ኖቬምበር 2015

ድል ለመቀዳጀት በአንድ ማሊያ መጫወት (ይገረም ዓለሙ)

ይገረም ዓለሙ

የላቀ የኳሽ ችሎታ ያላቸው ተጨዋቾች በሀገራቸውም ሆነ ከሀገራቸው ውጪ በከፍተኛ ገንዘብ እየተሸጡ ይጫወታሉ፡፡ እነዚህ ዘር፣ቀለም ፤ኃይማኖትም ሆነ ቋንቋ ሳይገድባቸው በችሎታቸው ተመርጠው በየትኛውም የአለም ክፍል የሚጫወቱ ተጨዋቾች ገንዘብ የሚከፍላቸውን ቡድን የዋንጫ ባለድል ለማድረግ ለራሳቸውም ተዋቂነት ለማትረፍ በቁርጠኝነት ይጫወታሉ፡፡ የአንድ ሀገር ልጆች የተለያየ ማሊያ ለብሰው ለተለያዩ ቡድኖች ተሰልፈው ሲጫወቱ የተሰለፉለትን ቡድን ለአሸናፊነት ለማብቃት ይሻኮታሉ ይጎሻሸማሉ፡
አህጉራዊ ወይንም ዓለም አቀፋዊ ጨዋታ ሲኖር ግን ከየሄዱበት ተመልሰው ከተበታተኑበት ተሰባስበው በአንድ ማሊያ ለሀገራቸው ይሰለፋሉ፡፡ ለሀገራቸው ቡድን የመሰለፍ ምክንያታቸው በአሰልጣኙ መመረጣቸውና ሀገራቸው ችሎታቸውን መፈለጉ ብቻ ሳይሆን የእነርሱም ሀገራቸው አሸንፎ ባለ ድል አንዲሆን ከምር መፈለጋቸው ጭምር ነው፡፡ ባለፈው የዓለም ዋንጫ የእግር ኳስ ውድድር ላይ ከአሸናፊነት ክብር ብር በልጦባቸው ከሀገራቸው አልፎ አፍሪቃን መሳቂያ ያደረጉትን ተጨዋቾች ሳንጨምር ነው ታዲያ፡፡
በዚህ ተምሳሌት የሀገራችንን ፖለቲካ ብንመለከተው ወያኔ በዚህ መንገድ በሚገባ እየተጠቀመበት መሆኑን እናያለን፡፡ ተቀዋሚው ግን….. ፡፡ ወያኔ አባል አጋር ሌላም በውል ስም ያልወጣላቸው ቡድኖችን አቋቁሞ በተለያየ ማሊያ የክልል ጨዋታውን ያካሄዳል፤ አምስት ዓመት ጠብቆ ሀገራዊው ጨዋታ ሲካሄድ ደግሞ ሁሉንም በአንድ ማሊያ በኢህአዴግ ስም ያሰልፋል፡፡
ወያኔ ማሊያ እየቀያየረ መጫወት የጀመረው በህውኃት ማሊያ ወደ ጎነደርና ወሎ መሸጋገር እንደማይቻል በተረዳበት ግዜ ነው፡፡እናም የአማራ ክልል የሚል ስያሜ በሰጠው የኢትዮጵያ ክፍል ለመረማመድ እንዲቻለው ኢህዴን ይባል የነበረውን ሕብረ- ብሔራዊ ድርጅት ስሙንም ዓላማውን አስለውጦ ብአዴን በሚል መጠሪያ የአማራነት ማሊያ አለበሰው፡፡ወያኔ ይህን ሲያደርግ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ነው የመታው፡፡ አንዱ በአማራ ክልል ለመረማመድ የሚያስችለው ቡድን መፍጠር ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የማይፈልገውንና ለእቅዱ አንቅፋት አድርጎ የሚያየውን ሕብረ ብሄር ፓርቲ ማክሰም፤ ሀገራዊ አስተሳሰብን ማጥፋትና ዘረኝነትን ማስፋፋት ነው፡፡ ወደ ሸዋ ሲጠጋ ደግሞ እሱም ጋር ሻዕቢያም ዘንድ የነበሩ ኦሮምኛ ተናጋሪ ምርኮኞችን ሰብስቦ በኦሮምያ ውስጥ ለመረማመድ የሚያስችለውን የኦሮሚያ ማሊያ ለብሶ የሚጫወት ቡድን ( ኦህዴድን) ፈጠረ፡፡አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ ደግሞ የሱን ሥልጣን የሚያረጋጉና የሚያስጠብቁ ደኢህዴንና እና አጋር የሚባሉትን ቡድኖችን መፍጠሩን ሁሉም የሚያውቀው ነው፡፡
እነዚህ የተለያያ ማሊያ ለብሰው የተለያየ ቡድን ተመስለው የሚጫወቱ ቡድኖች የቡድን መሪያቸው አሰልጣኛቸው አስተዳዳሪያቸው ህወኃውት መሆኑን አሌ የሚል አይኖርም፡፡እናም ለዘወትሩ ጨዋታ በክልል ማሊያ እያሰለፈ በየአምስት ዓመት ለሚካሄደው ጨዋታ ደግሞ የኢህአዴግን ማሊያ እያሰለፈ ሀያ አራት አመት ሙሉ የዋንጫው ባለቤት እንደሆነ አለ፡፡
ይህን ጨዋታ ቅንጅትም ሞክሮት ውጤታማነቱን አሳይቷል፤ምርጫ 97 በአጃቢነት የምንገባበት፣ ለአድማቂነት የምንሰለፍበት ሳይሆን ከምር ተወዳድረን የምናሸንፍበት መሆን አለበት ያሉ ወገኖች ለማሸነፍ ደግሞ በተለያየ ስም ሆኖ የተለያያ ማሊያ ለብሶ ሳይሆን በአንድ ቡድን መደራጀት በአንድ ማሊያ መሰለፍ እንደሚስፈልግ ተናገሩ-ሰሩ፡፡ በዚህ ጥረትም አደረጃጀታው ሀገራዊ መገኛቸው ሀገር ቤት የሆኑ አራት ድርጅቶች ስማቸውን ቅንጅት ብለው ምልክታቸውን ሁለት ጣት አድርገው በአንድ ማሊያ ተሰልፈው መጫወት በመቻላቸው መቼም የማይረሳውንና መቼ ሊደገም እንደሚችል መተንበይ የማይቻለውን ውጤት አስገኙ፡፡
ይህ ከሆነ በኋላ ሁለት ምርጫዎች ተደርገው ተቀዋሚው እንደለመደው ጨዋታውን በተለያየ ማሊያ ማድረጉን በመቀጠሉ በአንዱ አንድ ወንበር ሲያገኝ በሁለተኛው ፓርላማውን ጨርሶ አስረክቧል፡፡ ሀገራዊ ውድድርን በአሸናፊነት ለመወጣት ካልሆነም ትንሽ ወንር ከፓርላማ ለማግኘት አንድ ቡድን መስርቶ በአንድ ማሊያ መጫወት ያለውን ጠቀሜታ ከወያኔ መማር ባይቻል ወይንም ባይፈለግ እንደምን ከቅንጅት መማር ይቸግራል፡፡
ለውጤታማነት በአንድ ማሊያ መጫወት የሚያስፈልገውና የሚጠቅመው በሀገር ቤት ለሚደረገው ትግል ብቻ አይደለም፡፡የትግሉ መነሻ ቦታ ኢትዮጵያም ይሁን አሜሪካ፣ ኤርትራም ይሁን በርበራ፣አሰብም ይሁን ሱዳን በሁሉም የሚፈለገው ውጤት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ማየት ከሆነ በአንድ ቡድን ተሰባስቦ አንድ ማሊያ ለብሶ አንድ ሀገራዊ ገዢ መርህ አንግቦ መጫወት የግድ ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ ውጪ እስካሁን በተመጣበት ሁኔታ የሚካሄድ ውድድር(ትግል) ይህን ያህል ቡድን እዛና እዚህ አለ ከመባል ባለፈ ብሎም አንድ ቡድን ብቻውን ለጨዋታ ሜዳ አይገባምና የወያኔ አጨዋች ከመሆን የዘለለ የሚፈይደው ነገር የለም፣ አለ ከተባለ እገሌ የዚህ ቡድን መሪ እገሌ የዛኛው ቡድን ሊቀመንበር እየተባሉ መኖርን ትግልም ድልም ላደረጉ ሰዎች የሥልጣን ጥም ርካታ ማስገኘቱ ብቻ ነው፡፡ የፓርቲ መሪነት ሥልጣን ሆኖ፡፡
ሀያ አራት አመት እጅግ ብዙ ነው፡፡ስለሆነም ከዚህ በኋላ ሊመረን ይገባል፡፡በርግጥ ለውጥን ዓላማቸው አድርገው ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መሥረታ ከልብ አምነው ለዚህም ከምር ቆርጠው ለመታገል የወሰኑትና የፓርቲ ሊቀመንበር እየተባሉ መኖርን መነሻ ዓላማቸው መድረሻ ግባቸውም አድርገው የሚኖሩት ይለዩ፡፡ አንድ ቡድን መስርቶ በአንድ ማሊያ ተወዳደሮ የዋንጫ ባለቤት ላለመሆን ምክንያት ተደርጎ የሚቀርበው ቡድኖች ያላቸው የአደረጃጀት ፣ የጨዋት ስልት ፣የሚገኙበት ቦታ ወዘተ ልዩነት አሳማኝ አይደለም፡፡ ዋናው ምክንያት ሀገራዊ ለውጥ እንዲመጣ ያለመፈለግ ወይንም ቁርጠኝት ማጣት ነው፡፡ ለለውጥ በቁርጠኝነት የተሰለፈ ለለውጥ እንቅፋት ለሆኑ ችግሮች መፍትሄ ይፈልጋል እንቅፋት ሊሆኑ የሚችሉ ሰበቦችን ያስወግዳል እንጂ ልዩነትን ለማስፋት ሲማስን አያድርም፣በእያንዳንዱ ርምጃ ሰበብ እየፈለገ እንቅፋት አይፈጥርም፣ስለ ሀገራዊው ድል እንጂ ስለ እርሱ ቦታ አይጨነቅም፡፡
አንድ በግልጽ የሚታይ ነገር ላንሳ ጀነራል ከማል ገልቹና ጀነራል ሀይሉ ጎንፋ ሁለቱም ከወያኔ ከድተው አስመራ የገቡ የኦሮሞ ተወላጆች ናቸው፡፡እዛ ደርሰው ግን በአንድ ቡድን ተሰልፈው አንድ ማሊያ (ኢትዮጵያዊ ቢቀር ኦሮሚያዊ)ለብሰው መጫወት ተስኖአቸው ተለያይተው በኦሮሞ ስም የተለያየ ቡድን መስርተው እንደሚገኙ ነው የሚሰማው፡፡ ለያዙት ማእረግ የበቁት ውትድርናውን መቼ ጀምረውት እንደሆነ ማስረጃ ባይኖረኝም እዚህ ማዕረግ እስኪደርሱ በቃልም በተግባርም፤ በክፍልም በመስክም ወዘተ ሰፊ ወታደራዊ እውቀት እንደቀሰሙና ልምድ እንዳካበቱ እሙን ነው፡፡ ታዲያ በዚህ ወቅት ከሀገር ቤት ብቻ አይደለም ከአውሮፓና አሜሪካ ጭምር ከፕሮፌሰር እስከ ጳጳስ ከምር ቆርጠው ትግሉ ቦታ ሲወርዱ ጀነራሎቹ አሥመራ ተቀምጠው እንኳን ከሌላው መተባበር ርስ በርሳቸውም መነጋገር አቁመው አመታት መቁጠራቸውን መስማት እንቆቅልሽ አይሆንም!
ከምር ራሳቸውን ለትግሉ የሰጡና ለሥልጣን ሳይሆን ለነጻነት የሚታገሉ ስራቸው ምስክር ነውና በተግባራቸው እንለያቸው በምንችለውም አንደግፋቸው ይጠናከሩ፡ከውጤት አልባው የአመታት ጉዞአቸው ተምረው ለመለወጥ ያልፈቀዱትና ትግሉን ለስማቸው መጠሪያ ብቻ አድርገውት የሚኖሩት እንደዚሁ በተግባራቸው ይለዩ ፡፡ የእነዚህ መኖር ለሀገራዊው ትግል ከሚጠቅም ይልቅ ጉዳት ናቸውና ድጋፍ እንነሳቸው፤ከመኖራችሁ አለመኖራችሁ ይሻላል ብለን በግልጽ እንንገራቸው፡፡
ለነገሩ ሀገር ውስጥ ያሉት ብዙዎቹ ፓርቲዎች በወያኔ ዘንድ ነው እንጂ አሉ የሚባሉት ቆሞ ያልጠቀመ ሞቶ ምን ሊጎዳ ብሎ ሕዝቡ ከሸኛቸው አመታት ተቆጥረዋል፡፡ በውጪም በሚገኙት ላይ ይሄው መደገም አለበት፡፡ ሀገራዊውን ጨዋታ በአሸናፊነት ለመወጣት በአንድ ማሊያ መጫወት በምንልበት በዚህ ሰዐት እንወክለዋለን በሚሉት የአንድ አካባቢ ሕዝብ ስም የተደራጁ ሁለትም ስድስትም ድርጅቶች ስም እንሰማለን፡፡ የድርጅቶቹ መስራቾች ሁሉም ሊቀመንበር መባል በመፈለጋቸው ነው፡፡ ብዙም አባል አንደሌላቸው ይታወቃል፤ደጋፊው ግን ምን ይባላል፡፡ ትግሉን ከምር ያዙት አለያም ተዉት ማለት አያስፈልግም ትላላችሁ፡፡
በመጨረሻም ሎሬትን እንጋራ
Loret Tsegaye Gabre-Medhin

የፓርላማው ድራማ (ይገረም ዓለሙ)

ይገረም ዓለሙ
ሙሉ በሙሉ በአብዮታዊ ዴሞክራቶች በመያዙ የተለየ ሀሳብ የማይሰማበት ሙት የሆነውን ፓርላማ ህይወት ያለው ለማስመሰል የተዘጋጀው ድራማ ማክሰኞ ጥቅምት 16/2008 መታየት ጀምሯል፡፡ ይህ የፓርላማ ድራማ ቤቴሌቭዥን እንደምናያቸው ድራማዎች ሰሞነኛውን ትኩሳት እየተከተለ በየሳምንቱ የሚጻፍና የሚዘጋጅ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ በዚህ የመጀመሪያ ቀን ትዕይንት መሪ ተዋናይ ሆነው የቀረቡት ጠቅላይ ምኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ከፓርላማው አባላት መካከል በተመረጡት ተዋንያን እየተጠየቁ በመመለስ ሲተውኑ ታይተዋል፡፡Hailemariam Desalegn in the TPLF parliament
ከቀደሙት ጠቅላይ ምኒስትር ጀምሮ ሲነገር እንጂ ሲተገበር የማይታየው ከተቀዋሚዎች ጋር አብሮ የመስራት ጉዳይ ለመጀመሪያው ቀን ድራማ ማድመቂያነት ከተመረጡት ጉዳዮች አንዱ ነበር፡፡ ተባብሮ መስራት ማለት እንደ ተቀዋሚዎች በመሰረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመነጋገር ሀገራዊ መግባባት ከመፍጠር የሚጀምር እንደ ወያኔ ደግሞ እሱ በሚፈልገው ጉዳይ ሲፈልጋቸው ብቻ በመጥራት የሚገለጽ ነው፡፡ እንዲ ሆነናም በአምስት ዓመቱ ዕቅድ ላይ ለማወያየት ምርጫ ቦርድ መዝግቦ ለሚያውቃቸው ፓርቲዎች በሙሉ መንግጨሥታቸው ሰነድና ደብዳቤ መላኩን የገለጹት አቶ ኃይለማሪያም ብዙዎቹ በስብሰባው ላይ ሲገኙ ጥቂቶች ውኃ የማይቋጥር ምክንያት በመስጠት አልተገኙም አሉ፡፡ ያልተገኙት ፓርቲዎች ያቀረቡት ምክንያት ውኃ የማይቋጥር ነው ያሉበትን ምክንያትም ሲያረዱ በሕጋዊ መንግድ የተመረጠ መንግሥት ስላልሆነ ከእርሱ ጋር አንነጋርም ማለታቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ለመሆኑ ጥሪያችንን ተቀብለው ብዙዎቹ ተገኝተዋል የተባሉት ፓርቲዎች የትኞቹና እነማን ናቸው፡፡ዝቅ ብለን እናያቸዋለን፡፡
የመሳሪያ ትግል የሚያካሂዱትን ድርጅቶች አስመልክቶም ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ለራሱም መሆን ካልቻለው ሻዕቢያ ጋር ሆነው የሚያመጡት ውጤት ስለማይኖር ጊዜያቸውን በከንቱ ባያባክኑ በማለት ምክር ለመስጠት የዳዳቸው አቶ ኃይለማሪያም አንዳንዶቹ እኮ ጭራሽ የሌሉ ናቸው በማለት ኦነግን ኦብነግንና የጋምቤላ ህዝቦች ንቅናቄን ጠቀሱ፡፡ ይቺ ገለጻ የቀረበችው በደራሲውና አዘጋጁ ስህተት ይሁን ወይንም በርሳቸው የጥናት ጉደለት ባይታወቅም ሁለት መልእክት ታስተላልፋለች፡፡ አንደኛ እነዚህ የተጠቀሱት ድርጅቶች ሰሞኑን ተባብረው ለመስራት የደረሱበት ስምምነት እነ አቶ ኃይለማያም ሰፈር የፈጠረው ነገር መኖሩን እንድንጠረጥር ያሚያደርግ ፣ ሁለተኛ ደግሞ በሰሜን በኩል ድምጻቸው የሚሰማው ድርጅቶች እነዚህ ብቻ አይደሉምና ለሌሎቹ መኖሮና ጠንካራ መሆን በዘወርዋራ እውቅና የሰጠ ነው፡፡
አቶ ኃይለማሪያም የአቶ መለስ ሌጋስ አስቀጣይ እንደመሆናቸው ስለ ድርጅቶቹ የተናገሩት ከርሳቸው የወሰዱትን ነው፡፡ አቶ መለስ ብረት አንስተው መንግሥታቸውን የሚታገሉ ድርጅቶችን አስመልክቶ ሲላቸው አጥፍተናቸዋል የሉም ሲሉ ሌላ ግዜ ደግሞ በግላቸው ብዙ ርቀት ሄደው ከድርጅቶቹ መሪዎች ጋር ለመገናኘትና ለመደራደር እንደጣሩ ሲናገሩ ሰምተናል፡፡ ሌላ ግዜ ደግሞ ወድመዋል ተደምስሰዋል የተባሉት ደርጅቶች በዚህ ቦታ እንዲህ አደረጉ ጥፋት አደረሱ የሚል ዜና ስንሰማ ኖረናል፡፡ የሉም በተባሉ ድርጅቶች ስምም ዜጎች እየተወነጀሉ ታስረዋል እየታሰሩም ነው፡፡ አቶ መለስ አይደለም የሀገር ውስጥ ተፋላሚዎችን ሶማሌ ተሻግረው አልሻባብን ድምጥማጡን አጥፍተነዋል ብለውንም ነበር፡፡
አቶ ኃይለማሪያም ባያስታውሱም እኛ አንረሳውም፡፡ አቶ መለስ ከርሳቸው ፍላጎት ውጪ ስንዝር መሄድ የማይችለውን ፓርላማ አስፍቅደው(ነግረው) እንዲህ አስታዋሽ አጥቶ የቀረውን ሰራዊት ሶማሊያ በላኩበት ወቅት የገጠማቸውን ተቃውሞ ዝም ለማሰኘት ሰራዊታችን አልሻባብን ደምስሶ አሁን የቀረው ቃርሚያ ብቻ ነው፣ ያንን አጠናቆ በቅርብ ቀን ይመለሳል ብለውን ነበር፡፡ ነገር ግን ይኸው እስካሁን አልሻባብም አልጠፋ ሰራዊቱም አልተመለሰ፡፡ እንደውም በተቃራኒው ወንድሞቻችን የአልሻባብ ጥቃት ሰለባ እየሆኑ ነው፡፡ አቶ ኃለማሪያም እኔም አንደ መለስ ብለው በንቀት ስሜት የሉም ጠፍተዋል ስላሉዋቸው ድርጅቶች መረጃ ስለሌለኝ የምለው አይኖርም፤ የላችሁም የተባላችሁ መኖራችሁን አሳይዋቸውና አቶ ኃይለማሪም በዚህ አፋቸው ምን እንደሚሉ ለመስማት አብቁን የሚለው ግን መልእክቴ ነው፡፡
አቶ መለስ የሻዕቢያና ወያኔ ጸብና ፍቅር ለወላይታው ምኑ ነው ብለው ለአቶ ኃይለማሪያም አለነገሯቸው እንደሁ እንጂ ወያኔን አዲስ አበባ ያደረሰው ለራሱም የማይሆን ያሉት ሻዕቢያ ነው፡፡ ይህም ብቻ አይደለም ሌላው ኢትዮጵያዊ (የወያኔ ታጋይ ጭምር ) የማይታመን ሆኖ እስከ ተጣሉበት ግዜ ድረስ ቤተ መንግሥቱ ይጠበቅ የነበረው በሻዕቢያ ሰራዊት እንደነበረ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ስለሆነም አቶ ኃይለማሪያም ወያኔዎች ስለ ሻዕቢያ ዛሬ የሚሉትን ብቻ እየተቀበሉ መናገር ሳይሆን ትናንት ምን ይሉ ምንስ ያደርጉ እንደነበር የተጻፈ አንብበው የነበረ ጠይቀው ቢናገሩ ቢያንስ ጠቅላይ ምኒስትር ለሚለው ማዕረጋቸው( ይስሙላም ቢሆን) የሚመጥን ይሆናል፡፡
ከላይ እንደተገለጸው አቶ ኃይለማሪያም ስለ አብሮ መስራት ሲናገሩ ምርጫ ቦርድ የመዘገባቸውን ፓርቲዎች በሙሉ ጠርተን አብዛኛዎቹ ተገኝተዋል ነው ያሉት፡፡ አብዛኛው የሚለው የጥቅል መጠሪያ ለወያኔም ለፓርቲዎቹም ለምርጫ ቦርድም እያገለገለ ነው፡፡ እነዚህ ፓርቲዎች በቁጥር ሲገለጹ እንጂ በስም ሲጠሩ አይሰማም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ምርጫ ቦርድ መዝገብ ላይ ሰፍረው የሚገኙት አንዳንዶቹ የሌሉ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ምርጫ ሲመጣ ብቻ ብቅ የሚሉና ለምርጫ የሚሰጣቸውን ገንዘብ ተቀብለው የአጃቢነት ሚናቸውን ተወጥተው ለአራት ዓመት የሚጠፉ ናቸው፡፡ ጥቂቶቹም ፓርቲ ለመባል የሚያበቃ ቁመና የሌላቸው አቶ በረከት የፓርቲዎቹ ጥቅማቸው አልታይ ብሉአቸው ይሁን ስሜት ገፋፍቶአቸው ወይንም እውነት ተናንቆአቸው ባይታወቅም በመጽሀፋቸው የቤተሰብ ፓርቲ ሲሉ የገለጹዋቸው ናቸው ፡፡ በርግጥ ለመናገር አንዳንዶቹ ሊቀመንበር ተብሎ ከሚጠራው ሰው ቀጥሎ የሚጠራ ሶስትና አራት ሰው የሌላቸው በመሆኑ የቤተሰብ ፓርቲ የሚለውንም አያሟሉም፡፡ ብዙዎቹ ከተባሉት ከእነዚህ ስመ ፓርቲዎች ውስጥ ብዙዎቹን እንኳን ህብረተሰቡ ምርጫ ቦርድም አያውቃቸው፡፡ ድረ ገጹን ብትጎበኙ ቦርዱ ስለማያውቃቸው የተመዘገቡበትን ቀን መሙላት አቅቶት ቦታው ክፍት ሆኖ ታገኙታላችሁ፡፡ ፤ብቻ ብዙዎች እየተባሉ ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ይውላሉ፡፡እነዚህን በስም እየጠቀሱ መሪ የሚባሉትን ሰዎች ምንነትና ማንነት እያሳዩ መግለጽ የሚቻል ቢሆንም የሚፈይደው ነገር የለም፡፡ የምርጫ ቦርድን ድረ ገጽ ከጎበኙ ሌላም ነገር ይታዘባሉ፣ ምርጫ የማስፈጸም ብቃት አለው ተብሎ ምስጋና የተዥጎደጎደለት ይህ ተቋም ድረ- ገጹን ወቅታዊ ማድረግ ተስኖት ከአስር ዓመት በፊት የነበረ መረጃ ነው የሚያገኙት፡፡
ፓርቲ ማለት በምርጫ ቦርድ ተመዝግቦ የህጋዊነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የተሰጠው ነው ካልተባለ በስተቀር ብዙዎች የሚባሉት ከወያኔ ዳረጎት እየተቀበሉ፤ በምርጫ ቦርድ መልካም ፈቃድ ፓርቲ እየተባሉ፤ በአዳማቂነትና በአጃቢነት የሚያገለግሉ፣ እንኳን አባል የተሟላ አመራር የሌላቸው ናቸውና ፓርቲ ሊባሉ የሚበቁ አይደሉም፡፡ መሪ ለሚባሉት ሰዎች ግን የእለት እንጀራም የሕይወት መንገድም ሆኖ እየጠቀማቸው ነው፡፡ በአንጻሩ ብዙም ባይሆን ለወያኔ ዕድሜ መርዘምም እየረዱ ነው፡፡ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግን ኖሩም አልኖሩ “ተለበሰ ቀረ የደበሎ ቅዳጅ ”እንደሚባለው ናቸውና ምንም ፋይዳ የላቸውም፡፡ እንደውም የማይቻል ሆኖ እንጂ አለመኖራቸው ይሻል ነበር፡፡
ሙቱን ፓርላማ ህይወት ያለው ለማስመሰል የተጀመረው ድራማ ደራሲና አዘጋጁ ሰልችቶአቸው እስካላቆሙት ድረስ በጀመረው መልኩ ወቅታዊ የትኩረት አቅጣጫዎችን እየተከተለ የሚቀጥል ይሆናል፡፡ የእኛም ማየትና መስማት ብሎም ከምናይ ከምንሰማው ተነስተን ብዕር ከወረቀት ማገናኘት እንዲሁ ይቀጥላል፡፡እስካላቆሙት ድረስ ያልኩት አቅጣጫ ለማስቀየሻ እየተባሉ በዚህ መልኩ የሚጀመሩ ጉዳዮች ሲዘልቁ ስለማይታይ ነው፡፡ደግሞስ የማስመሰል ስራ መች ብዙ መንገድ ያስኬዳል፡፡ይህ የፓርላማ ድራማ ቀልቡን የሚስበው ሰው ኖር ይሆን!!

ለጥቅምት 22 ሰማዕታት የመታሰቢያ ፕሮግራም ተካሄደ (ነገረ ኢትዮጵያ) ለጥቅምት 22 ሰማዕታት የመታሰቢያ ፕሮግራም ተካሄደ (ነገረ ኢትዮጵያ)

http://ecadforum.com/Amharic/wp-content/uploads/2015/11/semayawi-party-remembering.jpg?bd378dምርጫ 1997 ዓ.ምን ተከትሎ ጥቅምት 22/1998 ዓ.ም በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ቀጥታ ትዕዛዝ በ‹‹ፀጥታ ሀይሎች›› በጭቃኔ ለተገደሉት ሰማዕታት እና ለቆሰሉት ኢትዮጵያውያን በሰማያዊ ፓርቲ ፅ/ቤት መታሰቢያ ተደረገ፡፡ የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች ጥቅምት 22/1998 ዓ.ም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የገጠማቸውን በተለይም ኢትዮጵያውያን ሲገደሉ ያዩትንና የራሳቸውን ገጠመኝም አካፍለዋል፡፡
የፕሮግራሙ ተሳታፊዎቹ የተገደሉትን በክብር መቅበር እንዳልቻሉ እና ታፍሰው በተለያዩ እስር ቤቶች መታሰራቸውን አስታውሰዋል፡፡ አዛውንቶችንና ህፃናትን በጭካኔ ተገድለው ባንክ ሊዘርፉ ነው የተባለበትና የሥርዓቱን የህግና ሞራል የማይገድበው መሆኑን ያሳየበት ነውም ብለዋል፡፡ ሥርዓቱ ካለፈው ስህተቱ ሳይማር ዛሬም ለመግደል ዝግጁ እንደሆነ መቀጠሉንም ገልፀዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ሥርዓቱ ወደ ባሰ አምባገነንነት በመግባቱም ትግሉን መቀላቀላቸውን ገልፀው፣ ዘላቂው አማራጭ የሰማዕታቱን የትግል መንፈስ ፅናት ይዞ መታገል ነው ብለዋል፡፡ እነሱ አላማ ያደረጉትን ተጉዘው በአንድነት የኢትዮጵያን እጣ ፋንታ መወሰን እንደሚገባቸውም ገልፀዋል፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በ1997 ዓ.ም በኋላ የሥርዓቱ ሁኔታ እየተባባሰ እንደመጣና ለዚህም ዋናው ምክንያት ኢትዮጵያውያን ሥርዓቱ የሚያደርስብንን በደል ችለን ወደ ውስጥ የምናለቅስ መሆናችን ነው ብለዋል፡፡ ሥርዓቱ ይቅር የማይደረግለት ሆኖ፣ ፖለቲካው በመነታረክ መቀጠሉን ትክክል እንዳልሆነም ገልፀዋል፡፡
‹‹ሥርዓቱ ታሪክና የጋራ ነገር የላችሁም ብሎናል፡፡ መናናቅንና ሀይማኖትን ማቃለልን በተግባር አሳይቶናል፡፡ የወደፊት ኢትዮጵያ በእኛ እጅ እንድትሆን ከፈለግን የነበረውን የሀገራችን እሴት ማናናቅ የለብንም፡፡›› ያሉት ኢ/ር ይልቃል ኢትዮጵያውያን የገነቧቸው እሴቶች ሁሉ በወጣቱ ልብ ውስጥ ማደር እንዳለባቸው፣ ሰማዕታቱ የሞቱለት አላማና ኢትዮጵያውያን የገነቡት እሴት መጠበቅ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

ቅዳሜ 26 ሴፕቴምበር 2015

በኢትዮጵያ ታሪክ ጉዳይ ላይ ኢሕአዴግን እንዴት ማመን ይቻላል?!

በኢትዮጵያ ታሪክ ጉዳይ ላይ ኢሕአዴግን እንዴት ማመን ይቻላል?!

በዲ/ን ኒቆዲሞስ
ወንድማችን ዲ/ን ዳንኤል የኢትዮጵያችን ልዩ ቅርስ በኾነው የዘመን አቆጣጠራችንን በተመለከተ አንድ ጥያቄ አንስቶአል፡፡ ይኸውም የኢትዮጵያን የዘመን አቆጣጠር በተመለከተ ‹‹ጠቅላይ ሚ/ሩን እንመን ወይስ አርቲስቶቻችንን?!›› የሚል ጥያቄ አንስቶ አንድ ትዝብትና ማሳሰቢያ አከል ጽሑፍ አስነብቦናል፡፡ እኔ ግን እንዲህ እላለሁ በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠርም ሆነ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ታሪክ ጉዳይ ላይ ኢሕዴግን/ክቡር ጠቅላይ ሚ/ሩን እንዳናምናቸው የሚያደርጉን አንዳንድ የታሪክ ሐቆች እንዳሉ ላንሣ፡፡
እስቲ እነዚህን ሐቆች በጥቂቱ ብቻ ለማየት እንሞከር፡፡ በመሠረቱ የአገሪቱን ታሪክ ወደ መቶ ዓመት አውርዶ ለሚተነትነው፣ ጥንታዊው የሆነው ፊደላችን፣ ሦስት ሺሕ ዘመንን ያስቆጠረውን የሥነ-መንግሥት ታሪክ ‹‹የአቢሲኒያውያን/የነፍጠኞች ቅኝ ገዢዎች ታሪክ›› አድርጎ የኢትዮጵያን ሕዝቦች ታሪክ በብሔር ብሔረሰቦች ማዕቀፍ ቀንብቦ ዳግም ለመፍጠር ለሚውተረተረው፤ አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የሚመሩት የኢሕአዴግ መንግሥት በምን ሞራልና ተጠየቅ፡- ‹‹ከአፍሪካ አገራት ሺሕ ዘመናትን ያስቆጠረ የራሳችን ፊደልና የዘመን አቆጣጠር ያለን ኩሩ ሕዝቦች …፡፡›› ተብሎ በአደባባይ ሊነግሩን እንደደፈሩ አይገባኝም፡፡ የታሪክ እውነት/ሐቅ ሲያሻን የምንደርበው እንዲያ ሲል ደግሞ አውልቀንና አሽቀንጥረን የምንጥለው የበረሃ ሽርጥ ኾነ እንዴ ጎበዝ …?! ይሄ በእውነት ያስተዛዝባል፡፡ ወይስ ደግሞ እንደው ሳንሰማ ኢሕአዴግ በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ያለውን አቋም አስተካክሎ ይሆን እንዴ … እ…እ…እ… አይመስለኝም፡፡
በዚህ ረገድ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትራችን የነበሩት አቶ መለስ ዜናዊም፣ ‹‹… የኢትዮጵያ ታሪክ የመቶ ዓመት ታሪክ ነው፣ የአክሱም ሐውልት ለወላይታው ምኑ ነው …?! እንዳላሉን ኹሉ የኢትዮጵያ ሚሊኒየም ሲከበር ባደረጉት ንግግራቸው፣ ‹‹… እኛ ኢትዮጵያውያን የሦስት ሺሕ ዘመን ታሪክና መንግሥት ያለን ነጻና ኩሩ ሕዝቦች …›› ሲሉ ሰምተናቸው መገረማችንን አስታውሳለኹ፡፡ እዚህ ጋራ የኢትዮጵያን ታሪክ ‹‹በአቢሲኒያውያን/በነፍጠኞች ቅኝ ግዛት ወረራ›› የታሪክ መነጽር የሚመለከተው ኢሕአዴግ ሙሉ ድጋፉንና ፈቃዱን በቸረበትና የኤርትራውያን ጥያቄ ‹‹የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው›› በሚል የኤርትራውያን ነጻ እንዲወጡ ባደረገበት ወቅት የኾነውን የታሪክ ቀውስም በጥቂቱ ማየት እንችላለን፡፡
ትናንትና የኢትዮጵያ አካል የነበሩት ኤርትራውያን ወገኖቻችን ነጻነታቸውን ባወጁ ማግሥት የዘመን አቆጣጠራቸውን ወደ ጎርጎርሳውያን የቀየሩት የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ቅኝ ገዢዎቹ አቢሲኒያውያን/ነፍጠኞች እንደ ብርድ ልብስ የደረቡብን የእኛ ያልሆነ- ታሪካችንን፣ ቅርሳችንንና ማንነታችንን የሚያራክስ፣ የሚያጣጥል ነው በሚል አመክንዮ እንደሆነ የምንስተው አይመስለኝም፡፡ የኋላ ኋላ የኾነውን ነገር ኹሉ እናስታውሳለን፤ ባልነበረ የፈጠራ ታሪክ ሺሕዎች ጭዳ የኾኑበትን የጦርነት፣ እልቂት መዘዝ በኀዘን እናስታውሳለን፡፡ አሁንም ድረስ የኹለቱ አገራት ጉዳይ የተዳፈነ እሳት ሆኖ አለ፡፡
በዚሁ የፈጠራ ታሪክ ጦስ የሆነውን ሌላኛው ትዝብቴን ላክል፡፡ ኤርትራዊ ብሔርተኝነትን በአዲስ የታሪክ ሂደትና ትንታኔ ለመፍጠር ሲውተረተር የነበረው የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂና ደጋፊዎቹ/ብሔርተኛ ኤርትራውያን ባለፈው ዓመት ደግሞ፣ ‹‹… ለመሆኑ እንደው የሆነስ ሆነና ኢትዮጵያ ከማን ተሸላ ነው እኛን ሥልጡን፣ የራሳችን የዘመናት ታሪክ፣ ቅርስ፣ ባህልና ሥልጣኔና ያለንን ሕዝቦች ቅኝ ለመግዛት የቻለችው?!›› በሚል ለዓመታት ሲያቀነቅኑ የነበረውን ‹‹ኢትዮጵያ ቅኝ ገዘታናለች›› የሚለውን የታሪክ ምጸት በውስጣቸው የፈጠረውን የበታችነት ስሜትና የማንነት ቀውስ በሌላ ተረት ተረት ላማከምና ኤርትራዊ ብሔርተኝነትን በሁለት እግሩ ለማቆም ደፋ ቀና ሲሉ ታዝበናቸዋል፡፡
በተጨማሪም ሰፊው የኦሮሞ ሕዝብንም ለዘመናት ሲጠቀምበት የነበረውን ፊደሉን ከግእዝ ፊደል ወደ ላቲን ፊደል እንዲቀይር ያስገደደው ይኸው ኢሕአዴግ በሚያቀነቅነው ‹‹የአቢሲኒያውያን/የነፍጠኞች የቅኝ ገዢዎች ታሪክ›› ትንታኔ መነሻነት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ታዲያ ባለ ሥልጣኖቻችን እንዲህ የሚያጣጥሉትንና የሌሎችና ታሪክና ቅርስ፣ ማንንት ያመከነና የዘረፈ ነው ብለው የሚከራከሩበትን የኢትዮጵያን ታሪክና ቅርስ እንዴት በአደባባይ ሺሕ ዘመናትን ያስቆጠር የፊደል፣ የዘመን አቆጣጠር ያለን የሦስት ሺሕ ዘመናት ታሪክ ባለቤት ሕዝቦች ሊሉን የቻሉበትን ድፍረት የት እንዳገኙት ለመጠየቅ፣ ለመሞገት እንገደዳለን፡፡ እንዲህ እንደ እስስት በመለዋወጥስ የታሪክ ሐቅን መለወጥ ይቻላል እንዴ?!
ከኢትዮጵያን ታሪክ አንስቶ እስከ ፊደላችን ድረስ በርካታ ጥያቄዎች አሉብን፡፡ ለአንዳንዶች የኢትዮጵያ የሺሕ ዘመናት ታሪክ የአቢሲኒያውያን/የነፍጠኞች ቅኝ ግዛት ታሪክ እንደሆነ ነው የሚሰማቸው፡፡ ለአንዳንዶች ደግሞ ፊደላቱ ያለ ቅጥ በዝተዋልና ይቀነሡ በሚል ሽንጣቸውን ገትረው ይከራከራሉ፡፡ ይህን ጥያቄ መዳኘትና መልስ መስጠት የሚገባቸው ከእውነት ጋር የወገኑ የእውቀት ሰዎች-ጠቢባኑ ደግሞ ከመድረክ ተገፍተው ታሪክን እንዳሻቸው የሚተነትኑ አድር ባዮች፣ በአገሪቱ ታሪክ ማኅፀን ሌላ ለከፋፋይ ፖለቲካቸው የሚመቻቸውን ጽንስ እያበጁ እያየንና እየሰማን ይኸው በፍርሃት ተሸብበን አለን፡፡ እነርሱም ያለ ምንም እፍረት ታሪካችንን ለጊዜያዊ ፖለቲካቸው ጥቅም ሲሉ እንዳሻቸው ሲለዋውጡት በአግርሞት እያየናቸውና እየሰማናቸው ነው፡፡
በመጨረሻም ወደ ዘመን አቆጣጠራችን ጉዳይ ስመለስ ዛሬ ዓለም ኹሉ እየተደመመበት ያለውንና ይህ የዘመን አቆጣጠርም ከሥነ ፍጥረት ሕግና ሂደት ጋራ የተስማማ እንደሆነ የሚያሳዩ መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡ ባለፈው ዓመት የካቶሊኩ ፖፕ የነበሩት ጀርመናዊው ፖፕ ቤኔዲክት የአውሮፓውያኑ የዘመን አቆጣጠር ስህትት እንደሆነና ከአውሮፓውያኑ የዘመን አቆጣጠር ይልቅ ይኸው የእኛው የኢትዮጵያ ዘመን አቆጠጠር ትክክል እንደሆነ Jesus of Nazareth: The Infancy Narratives በሚል መጽሐፋቸው ለመላው ዓለም አሳውቀዋል፡፡
የኢትዮጵያን ዘመን አቆጣጠርና ደማቅ ክብረ በዓሉን በተመለከተ ደግሞ ዘንድሮ በተለየ ሁኔታ እንደ ለንደኑ ቢ.ቢ.ሲ፣ የአሜሪካው ሲ.ኤን.ኤን፣ የዶሃው አልጀዚራና የኢራኑ ፕሬስ ቴሌቪዥኖች ሽፋን በመስጠት ዘግበውት ነበር፡፡ በተለይ ደግሞ የኩባ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በስፓኒሽ ቋንቋ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ኩባውያን ስለ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ሰፊ ሽፋን ሰጥተው ልዩ ዘገባ እንዳቀረቡ ተከታትለናል፡፡ ተወደድም ተጠላ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቅርስ የኾነው ይህ የዘመን አቆጣጠራችን ከአፍሪካ አልፎ የዓለም ኹሉ ቅርስ ወደመሆን እየተሸጋገረ እንዳለ እየታዘብን ነው፡፡ ይህን ዓለም ሁሉ አምኖ የተቀበለውንና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አሻራ ያለበትን የአገሪቱን የታሪክ ሐቅ መካድ፣ ማፋለስ፣ መበረዝ፣ … ከራስ ጋራ፣ በፍቅርና በአንድነት የጥበብ ልዩ ሸማ ከተዋበው፣ ዘመናት ካልሻሩት ኢትዮጵያዊ ማንነት፣ ታሪክና ቅርስ ጋራ መጣላት መሆኑን በመግለጽ ልሰናበት፡፡
ሰላም!

ሐሙስ 6 ኦገስት 2015

የናትናኤል ማስታወሻ – ጥቂት ስለ ማዕከላዊ (ከቂሊንጦ እስር ቤት)

የናትናኤል ማስታወሻ – ጥቂት ስለ ማዕከላዊ (ከቂሊንጦ እስር ቤት)

(ከቂሊንጦ እስር ቤት)
ናትናኤል ፈለቀይህንን ጽሁፍ ስጽፍ ዓላማዬ ማዕከላዊ ያሉ ሥራቸውን አክብረው የኢትዮጵያውያንን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ የሚሰሩ ጥቂት ፖሊሶችን (ምናልባትም በአንድ እጅ ጣቶች ተቆጥረው የሚያልቁ መርማሪዎችን) ለማበረታታት አይደለም፡፡ይህን ዓላማ በሌላ ጽሁፍ እመለስበት ይሆናል፡፡ ለነገሩ ሥራቸውን አክብረው የሚሰሩ ባለሙያ ፖሊሶች የኔ ማበረታታትን የሚፈልጉ አይደሉም፡፡ያሉበት ደረጃ ላይ ለመድረስ በኃላፊነት ማሰብ የቻሉ ስለሆኑ፡፡
ስለዚህ የዚህ ጽሁፍ ዓላማ በተቋሙ ውስጥ ኢትዮጵያ የምትተዳደርባቸውን ሕጎች ለማክበር(የተላለፉትን ለይቶ ለማስቀመጥና በስህተት የተጠረጠሩትን ነጻ ለማውጣት) ሳይሆን የአገዛዙን ዕድሜ ለማርዘም የሚሰሩትን አብዛኞቹን ሙያቸውን የማያከብሩ ፖሊሶች ‹‹ምርመራ›› ሴራቸውን እንዴት እንደሚፈትሉ ለማሳየት፣ ቢያንስ ሌላ ስልት እስኪፈጥሩ ድረስ በሀገሪቷጉዳይ ያገባናል የሚሉ ኢትዮጵያውያን አንዴ በተቋሙ ውስጥ ከገቡ በኋላ ሊገጥማቸው የሚችለውን የተንኮል መረብ ለማስረዳት እና ቀድሞለማዘጋጀት ያሰበ ነው፡፡
እውነት ለመናገር እነዚህ የስርዓቱ ጠባቂ ሎሌዎች የህዝብን ደህንነት ለአደጋ የሚያጋልጥ ወንጀልን እና ወንጀለኞችን ለይተው አውቀው ፍትህ እንዲያገኙ አድርገው ጭራሹንም አያውቁም ማለት አልችልም፡፡ ስለዚህ አሁን የማብራራው ጉዳይ ለወንጀለኞችም መዘጋጃ ሊሆን እንደሚችል አምናለሁ፡፡ ነገር ግን ወንጀለኞች ከፍትህ እንዲያመልጡ ጠብታ ውሃ ማቀበል አልፈልግም፡፡አንድ ነጻ ሰው ባልሰራው ወንጀል ከሚቀጣ መቶ ወንጀለኞች ቢያመልጡ ይሻላል የሚለው የህግ መርህ የበለጠ አቋሜን ያስረዳል፡፡
ሁለት ማሳሰቢያዎች አሉኝ፤ አንደኛ፡-እኔ ተይዤ ማዕከላዊ እስክገባ ድረስ ልታሰር እንደምችልአስቀድሜ ባውቅም ሊጠብቀኝ የሚችለውን የ‹‹ምርመራ›› ሂደት (የሴራ መረብ የበለጠ ይገልጸዋል) አጽንዖት ሰጥቼ አላሰብኩበትም፡፡የምርመራው ሂደትን ተንተርሼ የማነሳቸውን ሀሳቦች የተረዳሁት በምርመራ ውስጥ ካለፍኩ በኋላ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ይህንን ጽሁፍየሚያነቡ ሰዎች እኔ በፍርሃት ያላደረኳቸውን ነገሮች እንዲያደርጉ (በምርመራ ሂደት) የሚያመለክቱ ናቸው፡፡ ሁለተኛ ይህንን ጽሁፍ በሀገሬ ጉዳይ ያገባኛል የሚል እና ሀሳቡን ሕገ-መንግስታዊ ድንጋጌዎች በሚፈቅዱት መሰረት በነጻነት የሚገልጽ ሁሉ ጊዜ ሳይሰጥ ቢያነበው እመክራለሁ፡፡
ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ሀሳብ የአቃቤ ህግ ምስክር ከተሰማ በኋላ በብይን የተለቀቁ ሙስሊምወንድሞች መጻፋቸውን አስታውሳለሁ፡፡ ያ ጽሁፍ የተሻለ የተደራጀ ነው ብየ ስለማስብ እንዲነበብ እጋብዛለሁ፡፡ በተጨማሪም ስርዓቱንየሚደግፉ ሰዎች ይህንን ጽሁፍ በማንበብ ወንጀለኞች ከሚጠቀሙበት ለተሻለ አላማ ያውሉታል ብዬ ስለማስብ ሁለቱም ባያነቡት ይሻላቸዋል፡፡
ወደ ዋናው ሀሳብ ልግባ፤ ከተያዝኩ በኋላ በነበሩ የመጀመሪዎቹ ቀናት ውስጥ የነበሩት‹‹ምርመራዎች›› እውነቱን እና የማውቀውን ብቻ በመናገር እራሴን ነጻ ማውጣት እንደምችል መተማመኛ መስጠትን ያለሙ ነበሩ፡፡ ለምሳሌሚያዝያ 18/2006 (በተያዝኩኝ በማግስቱ ቅዳሜ) የነበረውን ምርመራ ም/ሳጅን መኮንን በተረጋጋ ሁኔታ የምርመራው ሂደት በመከባበርእንደሚቀጥል፣ ልክ እኔ የዕለት ስራየን ለማከናወን ሙያ እንደሚጠይቀው ያክል የፖሊስ ምርመራም ተመሳሳይ እንደሆነ፣ በቁጥጥር ስርየዋልኩት ተጠርጥሬ ብቻ እንደሆነ እና በምርመራው ሂደት ወንጀል አለመፈጸሜ ከተረጋገጠ በነጻ ወደቤቴ እንደምሄድ ነበር ያስረዳኝ፡፡ይንቁናል የሚል ስሜት አስቀድሞ ስለሚያድርባቸው ተቋሙን እና እራሳቸውንም ከፍ የሚያደርግ ነገር በነዚህ የመጀመሪያ ‹‹የምርመራ››ቀናት ይናገራሉ፡፡
‹‹ይህ የወረዳ ጣቢያ አይደለም፡፡ የክልልም አይደለም፡፡ ይህ የፌደራል ወንጀል ምርመራነው፡፡ ሚኒስትር ደረጃ የደረሱ የመንግስት ባለስልጣናት ሳይቀር እዚህ ተመርምረዋል›› ነበር ያለኝ ም/ሳጅን መኮንን በአጽንኦት፡፡ከዚህ ገለጻ በኋላ ነበር ስለህይወት ታሪኬ በመጠየቅ ቃል የመስጠት ሂደቱን የጀመርኩት፡፡
ማስታወሻ- 1. ቃል ያለመስጠት መብት
ቃሌን ያለመስጠት መብት ስላለኝ ቃሌን አልሰጥም ለማለት መጀመሪያ መብቱ እንዳለ ማወቅይጠይቃል፡፡ በወቅቱ ይህ መብት እንዳለኝ ማወቄን እጠራጠራለሁ፡፡ አውቅ ከነበረም ግን በፍጹም ትዝ አላለኝም፡፡ ቃል አለመስጠትአንድ ለምርመራ ሂደቱ ተባባሪ አለመሆንን ማሳያ ነው፡፡ ለተቋሙ የጭቆና መሳሪያ ስለመሆኑ በቂ ማስረጃ እንዳለ አምነን ተጨማሪ ማረጋገጫዕድል (benefit of the doubt) መስጠት የማንፈልግ ከሆነ ይህ ትክክለኛው አማራጭ ይመስለኛል፡፡ ከግምት መግባት ያለበትቃል በመስጠቱ ሂደት ውስጥ ፖሊስ በእርግጠኝነት ስህተት መስራቱ አይቀርም፡፡ ይህም የማይቀረው ክስ ሲመጣ ተቋሙን ማጋለጥ እንደስልት የሚወሰድ ከሆነ እንደማስረጃ ሊቀርብ ይችላል፡፡ ለምሳሌ በኛ ጉዳይ የቀረበብን ክስ የሽብር ቡድን በኅቡዕ አደራጅተዋል በሚልሲሆን ሁላችንም ቃል ስንሰጥ የተጠየቅነው እና ስናብራራ የነበረው ግን በይፋ ስንጽፍበት እና ዘመቻዎቻችንን ስናካሂድበት ስለነበረውዞን 9 ነው፡፡
አቃቤ ህግ በክሱ እያለ ያለው የከሰስኳችሁ በመጻፋችሁ እና መብትን የሚጠይቁ ዘመቻዎችንበማድረጋችሁ (በአጠቃላይ ከዞን-9 ጋር በተያያዘ) ሳይሆን ሌላ የህቡዕ ቡድን መስርታችሁ ለሽብር ዓላማ ስትንቀሳቀሱ ስለነበር ነው፡፡የሰጠነው ቃል እና ክሱን ለመደገፍ የቀረቡት ማስረጃዎች ግን ስለ ዞን-9 አውርተው አይጠግቡም፡፡ በመጀመሪያዎቹ ቀናት የሚነግረውን‹‹ተቋሙ ገለልተኛ ነው፣ ሰዎችን ወንጀለኛ ለማድረግ ሳይሆን እውነትን ፈልፍሎ አግኝቶ ነጻ ሰውን ወደቤቱ ይሸኛል›› የሚለውን ዕምነትበቀላሉ ማስረጽ ከቻሉ የሚቀጥሉት ጥርጣሬ ወደመዝራት ይመስለኛል፡፡ በቀላሉ ያሉትን የማያምኑ ከሆነ ግን የተጠርጣሪውን በራስ መተማመንለመሸርሸር ህገ-ወጥ ተግባራቸውን ይቀጥላሉ፡፡
‹‹ምርመራ›› በጀመርኩ በአራተኛው ቀን የተከሰተው ይሄው ነው፡፡ ሚያዝያ 21/2006ዓ.ም ምሽት ድረስ ‹‹በምርመራው›› ሂደት ውስጥ ስሳተፍ የነበረው በሙሉ የራስ መተማመን ነበር፡፡ ለምሳሌ ም/ሳጅን መኮንን፣ ም/ሳጅንእቴነሽ፣ እና ሳጅን ፈይሳ በነበሩበት ታስሬ ‹‹እየተመረመርኩ›› ያለሁት ሀሳቤን በነጻነት ለመግለጽ ባለመፍራት ነው፡፡ ያኔ ‹‹ፖሊስለህዝብ የሚሰራ ተቋም ነው የምትሉትንም አላምንም፡፡ በአሁኑ ሰዓት ፖሊስ እንደ ተቋም እየሰራ ያለው አገዛዙን ስልጣን ላይ ለማቆየትነው›› ብያቸዋለሁ፡፡
ከላይ በጠቀስኩት ቀን ማታ ግን ሌላ ሊከሰት እንደሚችል የማውቀው፣ ግን ከምር ያልተዘጋጀሁበትነገር ተከሰተ፡፡ ምሽት 1፡00 አካባቢ የተጀመረው ‹‹ምርመራ›› ቶሎ ኃይለ ቃል ወደመሰንዘር እና ዛቻ ተለወጠ፡፡ በወቅቱ ም/ሳጅንመኮንን፣ የመጀመሪያ ቀን ፍርድ ቤት የወሰደን እና በየመተላለፊያው ሳገኘው ጭምር ቤተሰብ እንዲያገኘን መብት አለን፣ ፍርድ ቤትአዝዞልን ሳለ ለምንድነው የማታገናኙን እያልኩ ስጠይቀው የቆየሁት ሳጅን ምንላርግልህ እና ማዕረጉን የማላስታውሰው ፀጋየ (በቅጽልስሙ ጥጋቡ) የሚባል መርማሪ ነበሩ፡፡ የ‹‹ምርመራ››ውም ዋነኛ አጀንዳ የዞን 9 ድብቅ ግብ እና የውስጥ የስራ ክፍፍል (መዋቅር)በተመለከተ ነበር፡፡ በሁለቱ ጉዳይ ላይ እውነተኛው የማውቀው መልስ ‹‹መዋቅር የለውም›› የሚለው ነበር፡፡ ዞን 9 ድብቅ ግብምመዋቅርም ኖሮት አያውቅም፡፡ ሳጅን ምንላርግልህ መልሴ አላጠገበውም፡፡ ‹‹እኔ እንደሱ እንዳልመስልህ (የእኔን ጉዳይ በዋነኛነትወደያዘው ም/ሳጅን መኮንን እየጠቆመ) አለቅህም! ሽባ ነው ማደርግህ! ልብስህን አስወልቄ ሳልለጠልጥህ እውነቱን ብትነግረኝ ይሻልሃል!››የሚሉ ዛቻዎች ደረደረ፡፡ እኔ ግን መዋቅሩን በተመለከተ ስራ ለማቅናት ሲባል ምክረ ሀሳብ ቀርቦ እንደተወያየንበት፣ ነገር ግን ሀሳቡውድቅ እንደተደረገ ከማስረዳት በቀር የምጨምረው የማውቀው እውነት አልነበረም፡፡ ም/ሳጅን መኮንን እና ፀጋየ (ጥጋቡ) በየተራ ክፍሉንለቀው ከወጡ በኋላ ሳጅን ምንላርግልህ ከወንበሩ በመነሳት ምቾት በሚነሳ ሁኔታ ከተቀመጥኩበት ፊት ተጠግቶኝ ቆሞ ጥያቄዎችን ይደረድርጀመር፡፡
ጥያቄ፡- ‹‹ለምንድነው እነ ርዕዮትን ብቻ የምትጠይቁት?››
መልስ፡- ‹‹ኢትዮጵያውያን ስለሆኑ እና የታሰሩት በፖለቲካ አቋማቸው ምክንያት ነው ብለንስለምናምን፡፡››
ጥያቄ፡- ‹‹(በቁጣ) ባንክ የዘረፈውስ ኢትዮጵያዊ አይደለም? ለምንድነው ሌላውን ወንጀለኛየማትጠይቁት?››
በእውነት እዚህ ጋ ሳቄ መጥቶ ነበር፡፡ በርግጥ የታሰረን ሁሉ ከተቻለ መጠየቅ ለህሊናየሚያስደስት ስራ ነው፡፡ እግዜርም ይወደዋል፡፡ ግን ርዕዮትን ስጠይቅ እንዲሰማት የምፈልገው፣ ትግሏ ዋጋ እንዳላጣ እና እንዳልተረሳችነው፡፡ ይህም ትንሽም ቢሆን ብርታት ይጨምርላታል ከሚል ተስፋም ጭምር ነው፡፡ ተመሳሳይ ነገር የባንክ ዘራፊ እንዲሰማው በፍጹምአልፈልግም፡፡ ጥያቄው ቀጠለ፣
‹‹ዝዋይ ለምን ሄዳችሁ?››
‹‹እነ ውብሸትን ለመጠየቅ››
‹‹አትዋሽ! በቀለ ገርባን ለመጠየቅ ነበር?››
‹‹አዎ በቀለንም ለመጠየቅ ነበር፡፡››
‹‹በቀለ ምን እንደሚል ታውቃለህ? ለምን እንደታሰረ ታውቃለህ? ኦሮምኛ ትችላለህ?››
‹‹አልችልም››
‹‹በቀለ እኮ የሚለው ኦሮምኛ የማይችሉ ሰዎች በሙሉ ይታረዱ ነው፡፡››
ስለ በቀለ ገርባ የማውቀው ጥቂት ነገር ከሚለኝ ጋር ፍጹም የሚጣጣም ስላልነበር የፊቴንመለዋወጥ መቆጣጠር አልቻልኩም፡፡ ፊት ለፊቴ ተደንቅሮ የጥያቄ ዝናብ ሲያወርድ የነበረው ሳጅን ምንላርግልህ አሁን ማድረግ የሚፈልገውንለማድረግ በቂ ምክንያት አገኘ፡፡ የመጀመሪያዋን ጥፊ ሰነዘራት፡፡ መብቴን እየነካ እንደሆነ ስነግረው ‹‹ይህንን ነው አይደል ፈረንጆቹወስደው የሚያሰለጥኗችሁ?›› በማለት ስራውን ቀጠለ፡፡ ድብደባው እዚያ ቤት ከሚፈጽሙት ሰቆቃዎች (torture) አንጻር ትንሽ ቢሆንምአሸነፈኝ፡፡ አሁን የሚጸጽቱኝንም ቃላት ተናገረኝ፡፡ ከውጭ የነበሩት ሁለቱ መርማሪዎች ድብደባ ሲፈጸምብኝ በነበረበት ወቅት በመሐልመጥተው ገላጋይ ሆነው ነበር፡፡ ምንላርግልህ ግን ለያዥ ለገናዥ አስቸገረ፡፡
ማስታወሻ፡-2. መርማሪዎች አንድ አላማ ነው ያላቸው
ሁለትና ከዚያ በላይ ሆነው ሲመረምሩ የትኛውንም ማመን አያስፈልግም፡፡ በኋላ ላይ ከሌሎችተጠርጣሪዎች ጋር ሳወራ የተረዳሁት ይህ የተለመደ አሰራር መሆኑን ነው፡፡
ሌላ ተጠርጣሪ ሲመረመር ሳጅን ምንላርግልህ ገላጋይ ሌላኛው ደግሞ እምቡር እምቡር ይላል፡፡ከዚያም ፀጋየ (ጥጋቡ) እኔ ላይ ሲያደርግ እንደነበረው ገላጋይ የሚሆነው መርማሪ ‹‹እኔ ችግር ውስጥ እንድትገባ አልፈልግም፤ ለምንእውነቱን አትነግረንምና ራስህን አትጠብቅም? ደግሞ ዘጠኝ ሆናችሁ ለሰራችሁት ስራ አንተ ብቻህን ለምን ትጎዳለህ? ሌሎቹ እኮ እየተናገሩነው፤ አይደለም ዘጠኝ ሰው የሚያውቀው ነገር ይቅርና ለሌላ አንድ ሰው የነገርከው ነገር እኮ ሚስጥር መሆኑ ያበቃል›› የሚሉ ማግባቢያዎችበመደርደር ምስኪን ምስኪን ሊጫወት ይሞክራል፡፡
የዛን ምሽት ምርመራ ሲጠናቀቅ የሁለት ሰዓት ማሰቢያ ጊዜ ተሰጥቶኝ የዞን 9 ግብ ምንእንደሆነ እና የመዋቅራችንን እያንዳንዱን የስራ ዘርፍ እንዳስታውስ የቤት ስራ ተሰጥቶኝ ከሌሊቱ አምስት ሰዓት ተመልሼ እንደምጠራተነግሮኝ ነበር ወደ ማረፊያ ቤት ውስጥ የተመለስኩት፡፡
በተለምዶ ሳይቤሪያ የሚባለው ማረፊያ ቤት ባለአንድ ፎቅ ህንጻ ሲሆን የታችኛው ወለል በኮሪደርተከፍሎ በግራና በቀኝ አምስት አምስት ክፍሎች አሉት፡፡ ኮሪደሩ መሀል ላይ አንዱ የግድግዳ ሰዓት ተሰቅሏል፡፡ የመጀመሪያ ሰሞንልብ ስላልኩት ሰዓት የማውቀው ምርመራ ክፍል ካሉት ሰዓቶች በመነሳት በግምት ነበር፡፡ ከሳጅን ምንላርግልህ በተሰጠኝ የቤት ስራመሰረት ከምሽቱ አምስት ሰዓት ሲል ተመልሼ ወደምርመራ እጠራለሁ፡፡ ከምርመራ ከተመለስኩ ጀምሮ በአዕምሮዬ ሲመላለስ የነበረው ነገርተጨማሪ መልስ ልሰጣቸው እንደማልችል እና በዚህ ምክንያት ተመልሼ ከሄድኩ በኋላ የሚደርስብኝ ሰቆቃ ማብቂያ ምን እንደሚሆን ማሰብነበር፡፡ ቀኑን ሙሉ በምርመራ በማሳለፌ ድካም የነበረብኝ ቢሆንም እንቅልፍ ሊወስደኝ ግን አልቻለም፡፡ ራሴን አረጋግቼ በተሰጠኝሁለት ሰዓት እረፍት መውሰድ ብፈልግም ምንም ዓይነት ድምጽ በሰማሁ ቁጥር አምስት ሰዓት የሆነ እየመሰለኝ እባንን ነበር፡፡ እነምንላርግልህ ግን አልፈለጉኝም፡፡ አይነጋ የለም ሌሊቱም ነጋ፡፡ ጠርተው ቢደበድቡኝ ይሻል ይሆን እንደነበር እንጃ!
ማስታወሻ፡- 3. እራስን አረጋግቶ በቂ እረፍት መውሰድ
መርማሪዎቹ መቼም ቢሆን ምርመራ ጨርሰናል ደህና እደሩ ብለው አይሸኙም፡፡ ሁል ጊዜ‹‹በኋላ እንገናኛለን፤ አስብበት›› ብለው ነው የሚጨርሱት፡፡ አንዳንድ ጊዜ በቀጠሮ መሰረት ምርመራው ይቀጥላል፡፡ አንዳንድ ጊዜደግሞ የውሃ ሽታ ይሆናሉ፡፡ በቀጠሮ መሰረት ብጠራም ባልጠራም ያለችውን ጊዜ በቂ እረፍት ለማድረግ መጠቀሚያ ማድረግ የሚያዋጣውአማራጭ ነው፡፡ ከድብደባው በባሰ የሚጎዳው የማያቋርጥ ጭንቀት እና የእረፍት እጦት ነው፡፡ ከአሁን አሁን ወደምርመራ ተጠራሁ ብሎመጨነቅ ጥሪውን የማዘግየትም የማስቀረትም አቅም የለውም፡፡ ‹በኋላ እንገናኝ› የምትለዋ ቀጠሮ እረፍት መንሻ ዘዴ ናት፡፡
በመቀጠል የምርመራው ዓላማ የነበረው ከጓደኞቼ ያገኟቸውን መረጃዎች በመጠቀም ብዙ እንደሚያውቁጥያቄ የሚጠይቁትም ከኔ ይምጣ ብለው እንጂ ሁሉ ነገር ላይ መረጃ እነዳላቸው ለማሳመን መጣር ነበር፡፡ በወቅቱ የእኔ ምላሽ የነበረውሁሉንም የሚያውቁ ከሆነ ለኔ ጥሩ እንደሆነ እና ምንም ጥፋት እንደሌለብኝ ከዛ በላይ ማስረጃ እንደሌለ የሚያስረዳ ነበር፡፡
ማስታወሻ፡-4. አብረው የሚሰሩ ጓደኛሞች ወጥ መልስ ለመስጠት አስቀድመው ስምምነት ላይ መድረስ
ስለ አንድ ጉዳይ ሁለት ጓደኛሞች የተለያየ መልስ ከሰጡ ሰቆቃው ሁለቱም ላይ የጠና ነው፡፡አንደኛው ወደሌላኛው መልስ የሚጠጋ ነገር እስካልተናገረ ድረስ ሁለቱም ይሰቃያሉ፡፡ በኛ ምርመራ ወቅት አስቀድመን ምንም የምንደብቀውወይንም የምንዋሸው ነገር እንዳይኖር ስንነጋገር ስለከረምን በተነጋገርነው መሰረት የአንዳችን ቃል ከሌላችን የጎላ ልዩነት አልነበረውም፡፡
በጓደኞች መሀከል ክፍተት ለመፍጠር ሙከራ ያደርጋሉ፡፡ ለምሳሌ ለበፍቄ ‹‹ናትናኤል እኮእውነቱን ነግሮናል፡፡ በፍቃዱ ነው አብዮት እና አመጽ እንድንጠራ የሚገፋፋን ብሏል፡፡ አንተ ለምንድነው እንዲህ የምትደብቅላቸውእነሱ እውነቱን እየተናገሩ›› ብለውታል፡፡ ቀዳዳ ካገኙ ቅያሜ በመፍጠር ከጓደኛሞች መሀል አንዱን መስካሪ ለማድረግ ይጥራሉ፡፡ ማስፈራሪያዎችበታጨቁበት ምርመራ መሀል እራሴን ነጻ ማውጣት ቀላሉ አማራጭ እንደሆነ ደጋግመው ይነግሩኝ ነበር፡፡ ፀጋዬ (ጥጋቡ)፣ ም/ሳጅን መኮንንእና ኢንስፔክተር አሰፋ እየመረመሩኝ በነበሩበት ወቅት ፀጋዬ ተራ ስድቦችን እና ዛቻዎችን ከሰነዘረ በኋላ በዛው አፉ እኔን ማቆየትእንደማይፈልጉ እና የሚፈልጉትን ካልኩላቸው ወዲያውኑ ወደቤቴ እንደሚሸኙኝ አባቴንም መንከባከብ እንደሚሻለኝ ሲነግረኝ ነበር፡፡ የአባቴጤንነት እንዳሳሰበኝ ስለገባቸው ባገኙት አጋጣሚ ለምርመራው ግብአትነት ይጠቀሙበት ነበር፡፡
አብዛኛው የምርመራ ጊዜ በተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና ተደጋጋሚ መልሶች የሚያልፍ ነው፡፡ ይህምምርመራዎችን እጅግ አድካሚ እና አሰልቺ ያደርጋቸዋል፡፡ ዝርዝር ጉዳዮችን በተደጋጋሚ በመጠየቅ ከምሰጠው መልስ ላይ ልዩነት ለማግኘትይህንንም ተጠቅሞ ሌላ አዲስ ነገር ለማውጣጣት ይጥሩ ነበር፡፡ የተሳካላቸው ግን አይመስለኝም፡፡ በተቻለኝ አቅም ቀዳዳ ሳገኝ የማምንበትንአቋም ከመናገር ወደኋላ አላልኩም፡፡ የማውቀውን ለማካፈልም እንደዚያው፡፡ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ-መንግስት አንቀጽ 39ን የሚቃወም መርማሪአግኝቼ ለምን ልክ ነው ብዬ እንደማምን አስረዳኋቸው፡፡ በተለያየ ጊዜ የወሰድኳቸው የበይነ መረብ ደህንነት መጠበቂያ መሳሪያዎችንምበተመለከተ ያብራራሁለትም መርማሪ ነበር፡፡
ማስታወሻ፡-5. በተገኘው አጋጣሚ አቋምን ማስረዳት
መርማሪዎቹ በተደጋጋሚ ስለተነገራቸው ብቻ የሚያምኑት ብዙ ነገር አለ፡፡ ኢህአዴግ ትግልላይ በነበረበት ወቅት ጭራቅ ተደርጎ ይሳል እንደነበረው አሁንም የነጻነት ትግል እያደረጉ ያሉትን ሰዎች እንደ ሰው በላዎች የሚቆጥሯቸውመርማሪዎች ብዙ ናቸው፡፡ በነዚህ መርማሪዎች ይህን ከተማ (አ.አ) ተወልዶ ያደገ ሰው ፖለቲካ ውስጥ ቦታ የለውም፡፡ ተደጋግሞ ሲነሱልኝከነበሩት ጥያቄዎች መሀል ይህ መንግስት ምን በድሎሃል (በግል) እንዴት እንደዚህ አይነት አቋም ልትይዝ ቻልክ? የሚለው እንደነበርአስታውሳለሁ፡፡ መልሴ ግን አጭር ነበር፡፡ ነጻነቴን ዋጋ እሰጠዋለሁ!!
ከምክትል ሳጅን መኮንን ጋር በነበረን ጊዜ የተረዳሁት ስለ አቋሞቼ በጥልቀት ማወቅ ቢፈልግምእንደ ጦር እንደሚፈራቸው ነው፡፡ ገና ማስረዳት ስጀምር ቶሎ ብሎ ‹ወደጉዳያችን እንመለስ፣ ዳግም ወደ አንተ ልትስበኝ ነው?› ይለኝነበር፡፡ ሌሎችም መርማሪዎች ተመሳሳይ ፍላጎት አይቸባቸዋለሁ፡፡ አንድ የማይረሳኝ ምሳሌ ከኢሜሌ ላይ የተገኘውን የዜና መጽሔት በተመስጦሲያነብ የነበር አንድ መርማሪ አለቃቸው ድንገት ቢሮውን ከፍቶ ሲገባ ወረቀቱን በድንጋጤ ወርውሮታል፡፡ ከዚህ መገንዘብ የቻልኩት እነዚህን በአንድ በኩል መረጃ የተደፈኑ ሰዎች ሌላኛውን ጎን ማሳየት በሌላ አማራጭ የማያገኙት መረጃ ምንጭ መሆን ስለሆነ በምርመራወቅት እንደ አንድ ዓላማ ሊወሰድ እንደሚገባ ነው፡፡
አልፎ አልፎ ከሌላ ቦታ የሚመጡ (ከደህንነት መስሪያ ቤት) መርማሪዎች ለመመለስ አደጋችየሆኑ ውስብስብ ጥያቄዎችን ከመጠየቃቸው ውጭ የሚጠየቁት ጥያቄዎች እዚህ ግባ የሚባሉ አይደሉም፡፡ አንዳንድ ጊዜ መርማሪዎች የሚጠይቋቸውጥያቄዎች ለራሳቸውም ግልጽ አይደሉም፡፡ ጥያቄዎችን የሚያበጁት ከጀርባ ሆነው ምርመራውን የሚመሩት አለቆቻቸው ናቸው፡፡ አልፎ አልፎለመመለስ አደጋች የሚመስሉ ጥያቄዎች ይነሳሉ፡፡ ለምሳሌ ሚያዝያ 27 ቀን (የአርበኞች ድል ቀን) ኢንስፔክተር አሰፋ እና አንድየደህንነት ባልደረባ ሆነው ባካሄዱብኝ ምርመራ ወቅት አንድ አስቸጋሪ ጥያቄ ተነስቶ ነበር፡-
የደህንነት ባልደረባው፡- ‹‹ዞን 9 ምን ማለት ነው?››
መልስ ፡- ‹‹ዞን 9 ማለት ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ውጭ ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነቱን የተነጠቀ ታሳሪ ነው ለማለት የተጠቀምንበት ስም ነው፡፡››
‹‹እኔም የዞን 9 አባል (ነዋሪ) ነኝ ማለት ነው?››
‹‹አዎ!››
‹‹ጥሩ! ስለዚህ የኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነቱን የተነጠቀ ከሆነ መቼ እና እንዴት ነው ዞን9 ነጻ የሚወጣው?››
ይህ ጥያቄ ትንሽ ለመመለስ አስቸጋሪ ነበር፡፡ በርግጥ እንደማነኛውም ግለሰብ የኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነቱን መቼ ያገኛል ለሚለው ጥያቄ የራሴ አስተያየት ቢኖረኝም በዚህ ምርመራ ወቅት ሀሳቤን በነጻነት ብናገር የሚያመዝነውአደጋው ነበር፡፡ ስለዚህ ማለት የቻልኩት ዞን 9 የሚለውን ተምሳሌታዊ ስያሜ አምነንበት ብንጠቀምም የዞን 9 ነዋሪዎችን ነጻ ማውጣትግን እንደ ግብ ያስቀመጥነው እና እንዲሳካም ኃላፊነት ወስደን የሰራንበት ጉዳይ እንዳልነበር ነው፡፡
አጠቃላይ የእስር ቤቱ የአያያዝ ሁኔታና የምርመራው አሰልቺነት በየዕለቱ መርማሪዎቹ ከሚነግሩኝየራሳቸው እውነት ጋር ተደማምሮ ሊያሸንፈኝ ዳር ዳር ብሎ ነበር፡፡ ነገር ግን በተባራሪየምንሰማቸው ጓደኞቻችን እና መታሰራችን የሚቆረቁራቸው ሰዎች የሚያደርጉት ሰላማዊ ሰልፍ እና የበይነ መረብ ዘመቻ ተጨማሪ የጥንካሬምንጭ ሆነውኛል፡፡ የማታዎቹ ምርመራዎች ለዚህ ምቹ ናቸው፡፡ ካስተዋልኩት የተረዳሁት የማታውን (የሌሊቱን) የምርመራ ጊዜ መርማሪዎቹለሚከፈላቸው ተጨማሪ ገንዘብ እና ስላመሹ መ/ቤቱ ለሚያቀርብላቸው ቆሎ እና ውሃ ካልሆነ በስተቀር አይፈልጉትም፡፡
በማታው ምርመራ ወቅት ቶሎ የመሰላቸት እና የኃይል እርምጃ ወደመውሰድ ይሄዳሉ፡፡ ብዙ ማውራት አይፈልጉም፡፡ ስለዚህአለቆቻቸው የሰጧቸው ጥያቄዎች ሲያልቁባቸው የተለያዩ ስፖርታዊ ቅጣቶች በማዘዝ በተንቀሳቃሽ ስልካቸው አማካኝነት ጨዋታ(game) ይይዛሉ፡፡ ወይንም ሌላ ክፍል ምርመራ ላይ ካለ ጓደኛቸው ጋር በኢንተር ኮም ወግ ይይዛሉ፡፡ በተመርማሪዎች ላይ ያላግጣሉ፡፡በማታዎቹ ምርመራዎች ወቅት ለሚነሱ ጥያቄዎች ረዘም ያሉ መልሶችን መምረጥ ተገቢ ይመስለኛል፡፡ መልሶችንም በህገ-መንግስቱ ስለተፈቀዱመብቶች፣ ስለ ተቋማት ነጻነት አስፈላጊነት፣ እና መሰል ፖለቲካዊ ጉዳዮች ወደማብራራት ማጠጋጋት፣ ከተቻለ የመርማሪዎቹን ቀልብ ለመሳብእና ከሚወስዷቸው አላስፈላጊ የኃይል እርምጃዎች መከላከል ይቻላል፡፡
ማስታወሻ፡-6. አቤቱታ ማሰማት
የጊዜ ቀጠሮ መጠየቂያ ፍርድ ቤት በሚወሰዱበት ጊዜ ያለውን አጋጣሚ በሚገባ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ በተለምዶ ፍርድቤት በፖሊስ የአያያዝ በደል ተፈጽሞብኛል ብሎ የሚያመለክት ሰው ከፍርድ ቤቱ መልስ ተመልሶ ማዕከላዊ እንደሚገባ ስለሚያውቅ የባሰአደጋ ለመቀነስ በሚል አቤቱታ ከማቅረብ ሊቆጠብ ይችላል፡፡ ነገር ግን አቤቱታውን አቀረበም አላቀረበም ሰብዓዊ መብቱን ከመረገጥአይድንም፡፡ ልዩነቱ የሚሆነው የፍርድ ቤቱ መዝገብ ላይ የመብት ጥሰቱ ተመዝግቧል ወይስ አልተመዘገበም የሚለው ነው፡፡
እዚህ ላይ የምመክራቸውን ነገሮች ያለማድረግ ቁጭት በእኔ ብቻ ሳይሆን ብዙ ታሳሪዎች ላይ ያስተዋልኩት ነው፡፡ ያላደረግሁትንአድርጉ ብሎ የመጠየቅ ይሉኝታም ጽሁፉን ልጻፍ ወይስ ይቅርብኝ ብዬ እንዳንገራግር አድርጎኝ ነበር፡፡ ውስጤ ከሚብላላ ግን ጽፌውአንብቦ ቢያንስ አንድ ሰው የተለየ መንገድ ተከትሎ ጉዳት ቢቀንስ የተሻለ ነው የሚለው ሀሳብ የተሻለ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ ሌሎቹምጓደኞቼ ተመሳሳይ መንገድ አልፈዋል፡፡ የነሱንም የምርመራ ሂደት ይጽፉታል የሚል እምነት አለኝ፡፡ እስከዛው ድረስ መታገስ ያልቻለየሀገር ውስጥ ነዋሪ ግን ወደ ቂሊንጦ ጎራ ብሎ ከራሳቸው አፍ ጠይቆ መረዳት ይችላል፡፡ እኔ ቀረኝ የምለው ነገር ካለኝ በሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ፡፡
ማስታወሻ፡-7. የማዕከላዊ ቤቶችን (ክፍሎች) ይተዋወቁ
ማዕከላዊማዕከላዊ
በግቢው ውስጥ ሶስት የእስረኛ ማቆያ ቦታዎች አሉ፡፡ በተለምዶ ጣውላ ቤት፣ ሳይቤሪያ እና ሸራተን በመባል ይታወቃሉ፡፡ጣውላ ቤት አምስት ክፍሎችን በተርታ የያዘ ሲሆን የምርመራ ቢሮዎች ያሉበት ህንጻ ጀርባ ምድር ላይ ያሉ ክፍሎች ናቸው፡፡ እኛ ማዕከላዊታስረን በነበርንበት ወቅት ሶስቱ ክፍሎች ለሴት ተጠርጣሪዎች ማቆያ ሲሆኑ ቆርቆሮ መከለያ ተደርጎለት፣ ደግሞ የተቀሩት ሁለቱ ምስክርለመሆን የተስማሙ ወንድ ተመርማሪዎች ማቆያ ነው፡፡ ማሂ እና ኤዶም ከሶስቱ ክፍሎች በአንደኛው ከሌላ ሴት ታሳሪዎች ጋር እንዳይገናኙሁለቱ ብቻ ተለይተው ነበር፡፡ ጣውላ ቤት ፊት ለፊት የክፍሎቹ ወለል ጣውላ መሆኑ ነው ጣውላ ቤት የሚል ስያሜ ያሰጠው፡፡ ይህንንማቆያ ቤት አልፎ አልፎ ሂልተን በማለት የሚጠሩት ሰዎች ገጥመውኛል፡፡
ሳይቤሪያ የሚባለው የእስረኛ ማቆያ በቅዝቃዜው ምክንያት ነው ስሙን ያገኘው፡፡ ይህ ባለአንድ ፎቅ ህንጻ ምድር ላይየሚገኘው ማቆያ ቦታ በረጅም ኮሪደር የተከፈለ ሲሆን በግራና በቀኝ ከ2 ቁጥር እስከ 10 ቁጥር የተለጠፈባቸው አምስት አምስት ክፍሎችአሉት፡፡ 8 ቁጥር ከተለጠፈበት ውጭ ሌሎቹ ወጥ ክፍሎች ሲሆኑ 8 ቁጥር የተለጠፈበትን በር ተከፍቶ ሲገባ ግን ሌሎች ራሳቸውን የቻሉአራት ክፍሎች አሉት፡፡ የበለጠ ቅጣት እንዲቀጣ የሚፈልጉት ተመርማሪ እነዚህ ሁለት ሜትር በሁለት ሜትር የሆነ ጨለማ ክፍል ውስጥያስሯቸዋል፡፡ ሳይቤሪያ የምርመራ ግለቱ እስኪሰክን ድረስ ተመርማሪዎች የሚቆዩበት ቦታ ሲሆን ሁሉም ክፍሎች ከኤሌክትሪክ መብራትውጭ ምንም አይነት ብርሃን አይደርሳቸውም፡፡ የክፍሎቹ ግድግዳዎች ወለሉና ጣራው ከኮንክሪት የተሰራ ነው፡፡ ቀኑን ሙሉ ከውጭ ተዘግቶየሚውለው ክፍል በቀን ለሶስት ጊዜ ያክል ይከፈታል፡፡
ሳይቤሪያ ውስጥ ያሉ ክፍሎች ጠዋትና ማታ በተራ በተራ እየተከፈቱ ተመርማሪዎች በጋራ ወደሚጠቀሙት ባለስድስት ክፍልሽንት ቤት እና መታጠቢያ ቤት እንዲሄዱና ተጠቅመው እንዲመለሱ ለደቂቃዎች ፈቃድ ያገኛሉ፡፡ ለሌሎች ጥቂት ደቂቃዎች ደግሞ የፀሐይብርሃን ለማግኘት ይፈቀድልን ነበር፡፡ ፀሐይ የምናገኘው በጣውላ ቤት እና በህክምና ክሊኒኩ መሐከል ባለ ክፍት ቦታ ላይ ነበር፡፡ጣውላ ቤት ያሉት ክፍሎች በር ክፍት ስለሚሆን ከማሂ እና ኤዶም ጋር በዓይን እና በምልክት ብቻ እናወራ ነበር፡፡ የሳይቤሪያ ክፍሎችበየተራ በሳምንት አንድ ቀን የሚጸዱ ሲሆን ባለችን መታጠቢያ ጊዜም የምናገኘው በነዚህ ቀናት ብቻ በሳምንት አንዴ ነው፡፡
ሸራተን ለ12 ሰዓት ፀሐይ የሚገኝበት፣ ቲቪ የሚታይበት እና የሽንት ቤት እና የመታጠብ ፍላጎት ያለው ሰው የፈለገውንማድረግ የሚችልበት ቦታ ነው፡፡ የምርመራው ሂደት ሲጠናቀቅ ቀለል ባለ ጉዳይ የሚመረመር ሰው ወይንም ደህና ባለስልጣን ዘመድ ያለውሰው ሸራተን ሆኖ የማዕከላዊ ቆይታውን ያጠናቅቃል፡፡
በመጨረሻም አንድ እብሪተኛ መርማሪ በተናገረኝ ንግግር ማስታወሻየን ላጠናቅቅ፡፡ እንዲህ ነበር ያለኝ፣ ‹‹መንግስትብዙ ዓይኖች እና ጆሮዎች አሉት፡፡ እናንተ ደግሞ ስታወሩ የነበረው በእኛው ስልክ፣ ከሀገር ስትወጡ የነበረው በእኛው በሀገራችን አየር መንገድ እና በቦሌ በኩል ነበር፡፡ እያንዳንዱ እንቅስቃሴያችሁን መረጃ አለን፡፡ አንተ አሁን እየደበቅህን ነው፡፡ ይህ ደግሞ ለአንተ አይጠቅምም፡፡ እኛ ምርጫ እንሰጥሃለን፡፡ ሕይወትህን ወደብርሃን መውሰድ የምትፈልግ ከሆነ ወደዚያው እንመራሃለን፡፡ አይ አልፈልግም የምትል ከሆነ ደግሞ መውጣት ወደማትችለው ድቅድቅ ጨለማ እንከትሃለን፡፡ ምርጫው የአንተ ነው፡፡››


Leave a Reply

Your email address will not be published.

9 + 2 =

ቅዳሜ 27 ጁን 2015

Mr. Obama’s visit to Ethiopia sends the wrong message on democracy

“AFRICA DOESN’T need strongmen, it needs strong institutions.” Those were President Obama’s words when he addressed Ghana’s parliament in July 2009, during his first trip to sub-Saharan Africa as president. The historic speech, watched around the globe, was an optimistic clarion call to the leaders on the continent from the son of a Kenyan. “First, we must support strong and sustainable democratic governments,” Mr. Obama said. http://www.satenaw.com/wp-content/uploads/2015/06/11204407_958639020821812_980497817893224664_n.jpg

The president seems to have forgotten that speech. Last week, the White House announced that, while traveling to Kenya next month, Mr. Obama also will stop in Ethiopia, the first such visit by a sitting U.S. president to the country of 94 million. It’s almost unfathomable that he would make time for an entrenched human rights abuser such as Ethi­o­pia while cold-shouldering the nation that just witnessed a historic, peaceful, democratic change of power: Nigeria.
Administration officials justify the trip by citing the United States’ long-standing cooperation with Ethi­o­pia on issues of regional security and the country’s accelerating economic growth. Ethi­o­pia is a major recipient of U.S. development assistance, and the African Union has its headquarters there. But it also stands out in Africa for its increasingly harsh repression and its escalating chokehold on independent media and political dissent. Since June 2014, 34 journalists have been forced to flee the country, according to the Committee to Protect Journalists. Ethi­o­pia is also one of the world’s leading jailers of journalists


The administration already undermined Ethiopia’s struggling journalists and democracy advocates in April, when Undersecretary of State Wendy Sherman said Ethi­o­pia has “moved forward in strengthening its democracy. Every time there is an election, it gets better and better.” Shortly after her statement, the ruling party held an election in which it secured 100 percent of the parliamentary seats. That was indeed an improvement upon its 2010 performance, when it won 99.6 percent of seats. In the months ahead of the May 24 polls, opposition party members and leaders were harassed and arrested. The Ethiopian government refused to allow independent election observers, except from the African Union. Since the election, two opposition members and one candidate have been murdered. The government has denied any responsibility for the killings.
Meanwhile, Nigeria, the continent’s most populous nation and the one with the largest economy, overcame risks of electoral violence and Boko Haram’s terrorism to manage a peaceful transfer of power to an opposition party for the first time since the country’s return to democracy in 1999. With numerous African countries facing elections in the next two years, a visit to Nigeria would have signaled U.S. commitment to partnering with governments that respect freedom, the rule of law and the will of their people. Snubbing Nigeria for a trip to Ethi­o­pia sends the opposite message, in essence validat ing Ethiopia’s sham elections and rewarding a regime that has shown no intent to reform. Six years after his idealistic speech in Ghana, Mr. Obama is sending a message to Africa that democracy isn’t all that important after all.
FRICA DOES
FRICA DOES
“AFRICA DOESN’T need strongmen, it needs strong institutions.” Those were President Obama’s words when he addressed Ghana’s parliament in July 2009, during his first trip to sub-Saharan Africa as president. The historic speech, watched around the globe, was an optimistic clarion call to the leaders on the continent from the son of a Kenyan. “First, we must support strong and sustainable democratic governments,” Mr. Obama said.
The president seems to have forgotten that speech. Last week, the White House announced that, while traveling to Kenya next month, Mr. Obama also will stop in Ethiopia, the first such visit by a sitting U.S. president to the country of 94 million. It’s almost unfathomable that he would make time for an entrenched human rights abuser such as Ethi­o­pia while cold-shouldering the nation that just witnessed a historic, peaceful, democratic change of power: Nigeria.
Mr. Obama’s visit to Ethiopia sends the wrong message on democracy
Mr. Obama’s visit to Ethiopia sends the wrong message on democracy
Administration officials justify the trip by citing the United States’ long-standing cooperation with Ethi­o­pia on issues of regional security and the country’s accelerating economic growth. Ethi­o­pia is a major recipient of U.S. development assistance, and the African Union has its headquarters there. But it also stands out in Africa for its increasingly harsh repression and its escalating chokehold on independent media and political dissent. Since June 2014, 34 journalists have been forced to flee the country, according to the Committee to Protect Journalists. Ethi­o­pia is also one of the world’s leading jailers of journalists.
The administration already undermined Ethiopia’s struggling journalists and democracy advocates in April, when Undersecretary of State Wendy Sherman said Ethi­o­pia has “moved forward in strengthening its democracy. Every time there is an election, it gets better and better.” Shortly after her statement, the ruling party held an election in which it secured 100 percent of the parliamentary seats. That was indeed an improvement upon its 2010 performance, when it won 99.6 percent of seats. In the months ahead of the May 24 polls, opposition party members and leaders were harassed and arrested. The Ethiopian government refused to allow independent election observers, except from the African Union. Since the election, two opposition members and one candidate have been murdered. The government has denied any responsibility for the killings.
Meanwhile, Nigeria, the continent’s most populous nation and the one with the largest economy, overcame risks of electoral violence and Boko Haram’s terrorism to manage a peaceful transfer of power to an opposition party for the first time since the country’s return to democracy in 1999. With numerous African countries facing elections in the next two years, a visit to Nigeria would have signaled U.S. commitment to partnering with governments that respect freedom, the rule of law and the will of their people. Snubbing Nigeria for a trip to Ethi­o­pia sends the opposite message, in essence validat ing Ethiopia’s sham elections and rewarding a regime that has shown no intent to reform. Six years after his idealistic speech in Ghana, Mr. Obama is sending a message to Africa that democracy isn’t all that important after all.
- See more at: http://www.satenaw.com/mr-obamas-visit-to-ethiopia-sends-the-wrong-message-on-democracy/#sthash.oSEuu3EO.dpuf
“AFRICA DOESN’T need strongmen, it needs strong institutions.” Those were President Obama’s words when he addressed Ghana’s parliament in July 2009, during his first trip to sub-Saharan Africa as president. The historic speech, watched around the globe, was an optimistic clarion call to the leaders on the continent from the son of a Kenyan. “First, we must support strong and sustainable democratic governments,” Mr. Obama said.
The president seems to have forgotten that speech. Last week, the White House announced that, while traveling to Kenya next month, Mr. Obama also will stop in Ethiopia, the first such visit by a sitting U.S. president to the country of 94 million. It’s almost unfathomable that he would make time for an entrenched human rights abuser such as Ethi­o­pia while cold-shouldering the nation that just witnessed a historic, peaceful, democratic change of power: Nigeria.
Mr. Obama’s visit to Ethiopia sends the wrong message on democracy
Mr. Obama’s visit to Ethiopia sends the wrong message on democracy
Administration officials justify the trip by citing the United States’ long-standing cooperation with Ethi­o­pia on issues of regional security and the country’s accelerating economic growth. Ethi­o­pia is a major recipient of U.S. development assistance, and the African Union has its headquarters there. But it also stands out in Africa for its increasingly harsh repression and its escalating chokehold on independent media and political dissent. Since June 2014, 34 journalists have been forced to flee the country, according to the Committee to Protect Journalists. Ethi­o­pia is also one of the world’s leading jailers of journalists.
The administration already undermined Ethiopia’s struggling journalists and democracy advocates in April, when Undersecretary of State Wendy Sherman said Ethi­o­pia has “moved forward in strengthening its democracy. Every time there is an election, it gets better and better.” Shortly after her statement, the ruling party held an election in which it secured 100 percent of the parliamentary seats. That was indeed an improvement upon its 2010 performance, when it won 99.6 percent of seats. In the months ahead of the May 24 polls, opposition party members and leaders were harassed and arrested. The Ethiopian government refused to allow independent election observers, except from the African Union. Since the election, two opposition members and one candidate have been murdered. The government has denied any responsibility for the killings.
Meanwhile, Nigeria, the continent’s most populous nation and the one with the largest economy, overcame risks of electoral violence and Boko Haram’s terrorism to manage a peaceful transfer of power to an opposition party for the first time since the country’s return to democracy in 1999. With numerous African countries facing elections in the next two years, a visit to Nigeria would have signaled U.S. commitment to partnering with governments that respect freedom, the rule of law and the will of their people. Snubbing Nigeria for a trip to Ethi­o­pia sends the opposite message, in essence validat ing Ethiopia’s sham elections and rewarding a regime that has shown no intent to reform. Six years after his idealistic speech in Ghana, Mr. Obama is sending a message to Africa that democracy isn’t all that important after all.
- See more at: http://www.satenaw.com/mr-obamas-visit-to-ethiopia-sends-the-wrong-message-on-democracy/#sthash.oSEuu3EO.dpuf
“AFRICA DOESN’T need strongmen, it needs strong institutions.” Those were President Obama’s words when he addressed Ghana’s parliament in July 2009, during his first trip to sub-Saharan Africa as president. The historic speech, watched around the globe, was an optimistic clarion call to the leaders on the continent from the son of a Kenyan. “First, we must support strong and sustainable democratic governments,” Mr. Obama said.
The president seems to have forgotten that speech. Last week, the White House announced that, while traveling to Kenya next month, Mr. Obama also will stop in Ethiopia, the first such visit by a sitting U.S. president to the country of 94 million. It’s almost unfathomable that he would make time for an entrenched human rights abuser such as Ethi­o­pia while cold-shouldering the nation that just witnessed a historic, peaceful, democratic change of power: Nigeria.
Mr. Obama’s visit to Ethiopia sends the wrong message on democracy
Mr. Obama’s visit to Ethiopia sends the wrong message on democracy
Administration officials justify the trip by citing the United States’ long-standing cooperation with Ethi­o­pia on issues of regional security and the country’s accelerating economic growth. Ethi­o­pia is a major recipient of U.S. development assistance, and the African Union has its headquarters there. But it also stands out in Africa for its increasingly harsh repression and its escalating chokehold on independent media and political dissent. Since June 2014, 34 journalists have been forced to flee the country, according to the Committee to Protect Journalists. Ethi­o­pia is also one of the world’s leading jailers of journalists.
The administration already undermined Ethiopia’s struggling journalists and democracy advocates in April, when Undersecretary of State Wendy Sherman said Ethi­o­pia has “moved forward in strengthening its democracy. Every time there is an election, it gets better and better.” Shortly after her statement, the ruling party held an election in which it secured 100 percent of the parliamentary seats. That was indeed an improvement upon its 2010 performance, when it won 99.6 percent of seats. In the months ahead of the May 24 polls, opposition party members and leaders were harassed and arrested. The Ethiopian government refused to allow independent election observers, except from the African Union. Since the election, two opposition members and one candidate have been murdered. The government has denied any responsibility for the killings.
Meanwhile, Nigeria, the continent’s most populous nation and the one with the largest economy, overcame risks of electoral violence and Boko Haram’s terrorism to manage a peaceful transfer of power to an opposition party for the first time since the country’s return to democracy in 1999. With numerous African countries facing elections in the next two years, a visit to Nigeria would have signaled U.S. commitment to partnering with governments that respect freedom, the rule of law and the will of their people. Snubbing Nigeria for a trip to Ethi­o­pia sends the opposite message, in essence validat ing Ethiopia’s sham elections and rewarding a regime that has shown no intent to reform. Six years after his idealistic speech in Ghana, Mr. Obama is sending a message to Africa that democracy isn’t all that important after all.
- See more at: http://www.satenaw.com/mr-obamas-visit-to-ethiopia-sends-the-wrong-message-on-democracy/#sthash.oSEuu3EO.dpuf

ቅዳሜ 20 ጁን 2015

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ( መኢአድ) አመራር እና አባላት ላይ እስራቱ ተባብሶ ቀጥሏል

እስራቱ ተባብሷል
/ ለገሰ ወ/ሃና/
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ( መኢአድ) አመራር እና አባላት ላይ እስራቱ ተባብሶ ቀጥሏል
በትላንትናው እለት ማለትም 12/10/2007 ዓም ከምሽቱ 2:30 አካባቢ ልዩ ቦታው ሜክሲኮ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ( መኢአድ ) የውጭ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አብርሃም ጌጡ ተይዞ ልደታ ፓሊስ መምሪያ ታስሯል በዛሬው እለት ከፓሊስ መምሪያ ወደ አምስተኛ ተዛውሯል ከአዲስ አበባ ውጭም አባላት እየታሰሩ እንደሆነ መረጃ ደርሶኛል የተጠናከረ መረጃ ሲደርሰኝ እመለስበታለሁ አሁን ወደተረጋገጠው ጉዳይ
አቶ አብርሃም ጌጡ ትግል የጀመረው ገና በለጋ እድሜው በ1989 ዓም ነው መኢአድ ካፈራቸው ምርጥ ታጋዮች ግንባር ቀደሙ ነው ከመአሕድ ጀምሮ በተለያዩ የሀላፊነት ቦታ ላይ የጎላ አስተዋጽኦ አበርክቷል በተለይ ከ2001 አስከ 2003 ዓም ሀገራቀፍ የወጣቶች ጉዳይ ሀላፊ ሆኖ በርካታ ወጣቶችን በማደራጀትና በሠላማዊ ትግል ላይ ስልጠና በመስጠት ብዙ ወጣቶችን አብቅቷል በ2002 ሀገራቀፍ ምርጫ በልደታ ክ/ከተማ ለተወካዮች ምክር ቤት ተወዳድሮ ነበር ምርጫው ነጻና ዲሞክራሲያዊ ቢሆን ኖሮ ባለው የህዝብ ፍቅርና መልካም ስነ ምግባሩ የህዝብ እንደራሴ መሆን ይችል ነበር
መኢአድ ታህሳስ 17 - 19 /2003 ዓም ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ ድርጅት ጉዳይ ሀላፊ ሆኖ ተመርጦ ነበር በጠቅላላ ጉባኤው ማግስት በወቅቱ መኢአድን በፕሬዝደንትነት የሚመሩት ኢንጂነር ሀይሉ በወሰዱት የተሳሳተ እርምጃ ምክንያት የተመረጠውን አመራር በማገድ እና በመክሰስ ከፅ/ቤት እንድንወጣ ሲደረግ ከተከሰሱት አመራሮች አንዱ ነበር ኢንጂነር ሀይሉ እየሄዱበት የነበረውን የተሳሳተ መንገድ እንዲተው ፊት ለፊት የሞገተ ቆራጥ ታጋይ ነው ሠሚ አጣ እንጂ
ከ2003 ዓም እስከ ጥቅምት 28 -30 2007 ዓም ጠቅላላ ጉባኤ ድረስ በህገወጥ መንገድ ከፅ/ቤት የወጣውን አባልና አመራር በአላማው አፀንቶ ለአሸናፊነት ያበቃው ዋናው ሰው አብርሃም ነው አብርሃም ልታይ ልታይ ማለት አይወድም የፓርቲ መሪ ከመሆን ይልቅ መሪ ሊሆኑ የሚችሉ ሰዎች ማብቃት ላይ ያተኩራል ከአብዛኛው የመኢአድ አመራር የሚልቅበት የወጣለት ዲፕሎማት መሆኑ ነው እጅግ አስተዋይ እና በሰላማው ትግል ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል በፅኑ የሚያምን ነው
ጥቅምት 28-30 በተደረገውጠቅላላ ጉባኤ መኢአድን ለመምራት ታጭቶ በአቶ ማሙሸት አማረ በጥቂት ድምፅ ተበልጦ የመኢአድ ፕሬዝደንት መሆን ባይችልም በአቶ ማሙሸት ካቢኔ ውስጥ ባለው ጠንካራ የዲፕሎማሲ ችሎታ እና በፓለቲካል ሳይንስና አለማቀፍ ግንኙነት የማስትሬት ድግሪ ያለው በመሆኑ የመኢአድ የውጭ ግንኙነት ሀላፊ ሆኖ ቢሰራ ትልቅ ስራ እንደሚሰራ በመታመኑ ሀላፊነቱ ተሰጥቶት በአጭር ጊዜ አስደናቂ ሥራ ሰርቷል
አንባገነኑ መንግስት በምርጫ ቦርድ በኩል በወሰደው እርምጃ የነ አብርሃም ጌጡ አመራር ከፅ /ቤት በፌደራል ፓሊስ እንዲወጣ ተደረገ እንጂ
በደረሱብን በርካታ ችግሮች ሳይደናገጥ መፍትሄ መሻትን የሚመርጠው ፍፁም መደናገጥ ውስጥ የማይገባው አብርሃም መውጫ ቀዳዳ የሌለው የሚመስለን ነገር በጥልቀት ካሰብን መውጫ አለው ይላል አብርሀም ምርጫ ቦርድ በአዋጅ ከተሰጠው ስልጣን ውጭ ድርጅታችንን በጠራራ ፀሀይ ተነጥቀን ዝም አንልም በማለት ከፕሬዝደንቱ ከአቶ ማሙሸት አማረ ጋር በመሆን ጉዳዩን ወደ ህግ በመውሰድ ምርጫ ቦርድን በመሞገት ትልቅ ስራ በመስራት ላይ እያለ ነው ተይዞ ለእስር የተዳረገው
ቀጣይ ክፍል ጊዜ ሲገኝ አመለስበታለሁ፡፡

የፓርቲው ዕጩ ተወዳዳሪ የነበረው ወጣት ሳሙኤል


ይህ የምታዩት የሰማያዊ ፓርቲ የምስራቅ ጎጃም ዞን ፀኃፊና በ2007 ዓ.ም ምርጫ የፓርቲው ዕጩ ተወዳዳሪ የነበረው ወጣት ሳሙኤል ፤ትናንት ሰኔ 8/2007 ዓ.ም ምሽት ላይ ወደ ቤቱ እየገባ በነበረበት ወቅት በሁለት ግለሰቦች ከፍተኛ ድብዳባ ከተፈፀመበት በኋላ ሆስፒታል ውስጥ ነፍሱ ማለፏን እየሰማን ነው።
ይህች አጭር ጽሁፍ ደግሞ ሳሙኤል ከመገደሉ በፊት በፌስቡክ ገጹ ያሰፈራት ነች ፦
“…ውድ የደብረማርቆስ ከተማ ኗሪዎች ፤ ሰማያዊ ፓርቲን የመረጣችሁ ከ25'0000 በላይ መራጮች(ኮረጆውን) እርሱት እና በተጨማሪም በ31 ዩኒቨርስቲ የምትገኙ ከ14,000 በላይ ሰማያዊ ፓርቲን የመረጣችሁ ሌሎች ደጋፊዎች እና የኢሕአዴግ አባላትም የማያፍረው ብአዴን / ኢሕአዴግ ድምፅ መቀማቱ ሳያንስ በ21/08/2007 ዓም አፍነው ደብድበው ከሞት መትረፌ ቆጭቷቸው እሰር ቤት ለመወርወር ያለመከሰስ መብቴን እንኳን ተዳፍረው የሀሰት ክሰ እየፈጠሩ ነው!!!" በስልኬ እደተደወለም ያለፍላጎቴ ደሕንነት እያስገደደኝ ይገኛል!!!!! ተገደልሁም ታሠርሁም ፤ ታፈንኩም ነፃነት አይቀርም እና ለማሰረጃነት የደሕንነቶችን ስም፤ ፎቶግራፍ ፤ እና አድራሻ እንዲሁም በሐሠት ምሰክርነት እና ከሳሽነት የተደራጁ አካላት እና ዋና ተወካዮች የደብረማርቆስ ከተማ 04 ቀበሌ አመራሮች እና ፖሊስ ለታሪክ አሰመዘግባለሁ ማንኛውም የምከፍለው ዋጋ ለሀገሬ እና ለነፃነት ነው ከታሠርሁም ሕሊናዬ አይታሰርም ከገደሉኝም ትግሌን አደራ በተለይ የኔ ትውልድ አደራ !!!!" አገራችን የወያኔ ዘረኞች ብቻ መፈንጫ መሆን የለባትም ትግላችን የነፃነት ጉዟችን ጎርባጣ መድረሻችን ነፃነት ታሪካችን ዘላለማዊ ነው!!!!”(ከሳሙኤል አወቀ ዓለም - የሰማያዊ ፓርቲ የደብረ ማርቆስ የሕዝብ ተወካዮች እጩ ተወዳዳሪ)

ሰኞ 8 ጁን 2015

ራቁታችንን ትግሪኛ ተናገሩ ተብለን ተገርፈናል


ማረሚያ ቤቶች ነው የሚሏቸው። ሆኖም የኢትዮጵያ እሥር ቤቶች በዜጎች ላይ ከፍተኛ ስቃይ፣ ድብደባ፣ ቶርቸር የሚፈጸምባቸው ናቸው። መጀመሪያው አብዛኛው ታሳሪ ባላጠፋው ጥፋት ነው “ሽብርተኛ” ተብሎ ወደ ወህኒ የሚወርደው። አገሩን እና ሕዝቡ በመዉደዱ፣ ፍርትህን ለመብት በመቆሙ። ያ ሳይንስ ደግሞ ህወሃቶች በ እስር ቤትም ከአዉሬ እንጂ ከሰው የማይጠበቅ ከፍተኛ ስቃይ እያደረሱባቸው ነው።
አቶ ዘመነ ምህረት የጎንደር ከተማ ነዋሪ፣ የመኢአድ ምክትል ፕሬዘዳንት ናቸው። እርሳቸውን እነ ሌሎች በርካታ የሰላማዊ ታጋዮች ሽብርተኞች ተብለው ታስረዋል።
“ራቁታችንን ትግሪኛ ተናገሩ ተብለነ ተገፈናል “ ሲሉ አቶ ዘመነ ምህረት በርሳቸው ላይ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ጓደኞቻቸው ላይ የደረሰውን ግፍ ለዳኛው ገልጸዋል።
ግንቦት 27 ቀን ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር። አቶ ለገሰ ወልደሃና የፍርድ ቤቱን ዉሎ እንድሚከተለው ነበር የዘገበው
የፍርድ ቤት ዉሎ -ለገሰ ወልደሃና
ግንቦት 27/09/2007 ዓም ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለሁለተኛ ጊዜ የቀረቡት የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት/መኢአድ/ አመራሮች ተከሳሾቾ እነ
1. ዘመነ ምህረት
2. መለሰ መንገሻ
3. ጌትነት ደርሶ
በ3:00 ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኘ ችሎት ተሠይመዋል። ከነሱ በፊት 7 የጋሞቤላ አካባቢ ተወላጅ የሚመስሉ ቀረቡ በመቀጠል 8 ሙስሊሞች በአንድ መዝገብ ቀረቡ
.............. እያለ ሁሉሞ ቀጠሮ እየተሠጣቸው ወጥተዋል መጨረሻ አካባቢ የታየው የነ ዘመነ ጉዳይ ነበረ ቀደም ሲል በቀረቡበት ጊዜ የክስ ቻርጅ ተነቦለቸው እንደነበር ዳኛው ጠይቋቸው አዎ ተነቦልናል ብለው መልሰዋል ፡፡
ቀደም ሲል እዚሁ ችሎት በቀረቡበት አለት ጠበቃ ማቆም ይችሉ እንደሆነ ተጠይቃችሁ ጠበቃ ተመካክራችሁ እንደምታቆሙ ነበር ምን አደረጋችሁ ሲል ዳኛ ጠይቋቸው ነበር የተለያየ ቦታ ስላለን መገናኘት እና መነጋገር ስላልቻልን ቤተሰብም በቅርብ ስለሌን ማድረግ አልቻልንም ብለው መልስ ሰጥተዋል።
ጌትነት ደርሶ ክሱም የሀሰት ስለሆነ ፍትህ አገኛለሁ ብየ ስለማላምን ጠበቃ ማቆም አያስፈልገኝም በማለት ተናግሯል ዳኛው ጌትነትን እንዲህ ብሎ መናገሩ ስህተት እንደሆነ በመገሰጽ አስቁሞዉታል።
ዘመነ ምህረት እና መለሰ መንገሻ ሁኔታዎች ምቹ ስላልሆነ ጠበቃ ማቆም የሚችል አቅም ሰለሌለን ጊዜያዊ የመንግስት ጠበቃ ይቁምልን ብለዋል።
ዘመነ ምህረት፣ ጓደኛየ ጌትነት የተናገረው የልቡን ነው። በምርመራ ወቅት ልብሳችንን አስወልቀው እራቁታችንን ትግሪኛ ተናገሩ እየተባልን ተደብድበናል። ጌትነት ብሶት ስላለበት ነው “በአማራነታችን ተደብድበናል” እያለ ሲናገር የነበረው ሲል፣ ፓሊሶቹም ከዳኛው ይልቅ ቀድመው ለማስቆም ሙከራ አድርገው የነበረ ቢሆንም፣ በኋላ ዳኛው ራሳቸው አቶ ዘመነ እንዳይናገር አስቁመዉታል። ዳኛው “እዛ የነበረውን ስሜት እዚህ አታንፀባርቁ። ለቀረበባችሁ ክስ ማስረጃ ከሌለ አይፈረድባችሁም። ፍረድ የምንሰጠው በማስረጃ ነው” በማለት እንዳይናገሩ ከልክሎ ሊያማክራችሁ የሚችል ጠበቃ ማረሚያ ቤት ድረስ መጥቶ ያማክራችኀል በማለት ቀጣይ ቀጠሮ ሰኔ 11/10/2007 እንዲቀርቡ በማዘዝ የእለቱ ችሎት ተዘግቷል ፡፡

“እንዳልወልድ የዘር ፍሬዬ ተኮላሽቷል” መቶ አለቃ ጌታቸው

“እንዳልወልድ የዘር ፍሬዬ ተኮላሽቷል” መቶ አለቃ ጌታቸው
አንበሳው ያንበሳ ዘር የመኢአዱ ጀግና መቶ አለቃ ጌታቸው መኮነን እና ተስፋየ ታሪኩ ሌሎች 16 የመኢአድ የቁርጥቀን ልጆች ልደታ ፍርድቤት 19ኛው የወንጀል ችሎት ቀረቡ
ግንቦት 28 ቀን 2007
መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን የደረሰበትን አስከፊ ወንጀል ለዳኛው ቢያቀርብም ተቀባይነት አላገኘም። አቶ ተስፋየ ታሪኩ እሱም እየተፈፀመበት ያለውን ግፍ ለመናገር ቢያስፈቅድም፣ ያቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት የለውም በማለት ዳኛው አስቁመዉታል። ዳኛው “የናንተ ጉዳይ ወደ እኛ ከመጣ በኋላ የተፈፀመውን ለማስተካከል እንሞክራለን። ማእከላዊ በነበራችሁበት ወቅት የተፈፀመውን የማየት ስልጣን የለንም” ብለዋል።
በመቶ አለቃ ጌታቸው ላይ የተፈፀመው ወንጀል እግሩን በመስበር “አማራን ማጥፋት አለብን” በማለት የዘር ፍሬውን በማኮላሸት እራሱን እንዳይተካ (እናዳይወልድ) ተደርጓል። ሕክምናም እንዳያገኝ ተደርጓል።
አቶ ተስፋየ ታሬኩ “ፍርድ ቤቱ ያቀረብነው አቤቱታ የማይሰማ ከሆነ፣ ምንም ጠበቃ አያስፈልገንም። ለፀረ ሺብር ህጉም ሆነ ለዚህ ፍርድ ቤት እውቅና አንሰጥም። ያሰረንም ያሳሰረንም የደበደበንም የሚያስደበድብንም የሚመሰክርብንም የሚያስመሰክርብንም የሚፈርድብንም ወያኔ ነው። እኛ ለግንቦት 7 እና ለአርበኞች ግንባር ያደረግነው ነገር የለም። እነሱም የሳላማዊ ትግሉ ሲዘጋ ነው ወደትግል የገቡት” ብለዋል።
ሁሉም የመኢአድ አመራሮች እና አባሎች 16ቱም የተከሰሱበት ክስ ግንቦት 7 አርበኞች ግንባር እና ያማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ አባሎች ናችሁ የሚል ነው።
ቀጠሮ ለሐምሌ 1 ተወስኖአል።