ሐሙስ 29 ጃንዋሪ 2015

ESAT Daily News Amsterdam January 29 2015 Ethiopia | ESATTUBE

ESAT Daily News Amsterdam January 29 2015 Ethiopia | ESATTUBE

BBC Is journalism a crime in Ethiopia Journalists in exile and governmen...

Ethiopian Government Intensifies Crackdown on Dissent

Ethiopia Crackdown on Dissent Intensifies(Human Rights Watch, Nairobi) – The Ethiopian government during 2014 intensified its campaign of arrests, prosecutions, and unlawful force to silence criticism, Human Rights Watch said today in its World Report 2015. The government responded to peaceful protests with harassment, threats, and arbitrary detention, and used draconian laws to further repress journalists, opposition activists, and critics.
“The Ethiopian government fell back on tried and true measures to muzzle any perceived dissent in 2014,” said Leslie Lefkow, deputy Africa director. “Journalists and dissenters suffered most, snuffing out any hope that the government would widen political space ahead of the May 2015 elections.”
In the 656-page world report, its 25th edition, Human Rights Watch reviews human rights practices in more than 90 countries. In his introductory essay, Executive Director Kenneth Roth urges governments to recognize that human rights offer an effective moral guide in turbulent times, and that violating rights can spark or aggravate serious security challenges. The short-term gains of undermining core values of freedom and non-discrimination are rarely worth the long-term price.
Ethiopia’s dismal rights record faced little criticism from donor countries in 2014. Throughout the year, state security forces harassed and detained leaders and supporters of Ethiopian opposition parties. Security personnel responded to protests in Oromia in April and May with excessive force, resulting in the deaths of at least several dozen people, and the arrests of hundreds more. The authorities regularly blocked the Semawayi (Blue) Party’s attempts to hold protests.
Media remain under a government stranglehold, with many journalists having to choose between self-censorship, harassment and arrest, and exile. In 2014, dozens of journalists fled the country following threats. In July, the government charged seven bloggers known as Zone 9 and three journalists under the abusive Anti-Terrorism Proclamation. In August, the owners of six private publications were charged under the criminal code following threats against their publications. The government blocks websites and blogs and regularly monitors and records telephone calls.
The authorities have been displacing indigenous populations without appropriate consultation or compensation in the lower Omo Valley to make way for the development of sugar plantations. Villagers and activists who have questioned the development plans face arrest and harassment.
The government showed no willingness to amend the Anti-Terrorism Law or the Charities and Societies Proclamation, despite increasing condemnation of these laws for violating basic rights. Authorities more rigorously enforced the Charities and Societies Proclamation, which bars organizations from working on human rights, good governance, conflict resolution, and advocacy on the rights of women, children, and people with disabilities if the organizations receive more than 10 percent of their funds from foreign sources.
“The government’s crackdown on free expression in 2014 is a bad sign for elections in 2015,” Lefkow said.

መኢአድ

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አገር አቀፍ የወጣቶች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ የማህበራዊ ጉዳይ ሃላፊ የሆነው ወጣት መለሰ መንገሻ ጎነደር የጥምቀትን በዓል ለማክበር ሄዶ በነበረት ተይዞ አሁን በማዕከላዊ እስር ቤት በስቃይ ላይ ይገኛል:

እሑድ 25 ጃንዋሪ 2015

የመኢአድ ምክትል ፕሬዝደንት አዘዞ ጦር ካምፕ መወሰዳቸው ተነገረ።

ጥር ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከቀናት በፊት በፖሊሶች ከፍተኛ ድብደ ተፈጽሞባቸው ወዳልታወቀ ስፍራ ስለመወሰዳቸው የተዘገበው የመላው ኢትዮጰያ አንድነት ድርጅት ምክትል ፕሬዚዳንት  አቶ ዘመነምህረት አዘዞ በሚገኘው መከላከያ ካምፕ መታየታቸውን ፓርቲያቸው ገለጸ።
መኢአድ ዛሬ በሰጠው መግለጫ የድርጅቱ  ምክትል ፕሬዝደንት እና የሰሜን ቀጠና ኃላፊ የሆኑት አቶ ዘመነ ምህረት የድርጅታቸውን ጠቅላላ ጉባኤ አድርገው ወደ መኖሪያቸው ጎንደር ከተማ ከተመለሱ በኋላ ከፍተኛ የደህንነት ክትትልና ጫና ይደረግባቸው እንደነበር ለፓርቲያቸው አሳውቀው እንደነበር አስታውሷል።
አቶ ዘመነ በ10/05/2007 ዓ.ም ጎንደር ከሚገኘው መኖሪያው ቤታቸው ከባቤታቸውና ከህጻን ልጃቸው ፊት የፖሊስ ልብስ በለበሱ አካላት ከፍተኛ ደብደባ ተፈጽሞባቸው ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዳቸውን ያወሳው መኢአድ ፤በአሁኑ ወቅት የፓርቲው አባላት ባደረጉት ክትትል  አዘዞ የሚገኘው የመከላከያ ካምፕ ውስጥ እንደሚኙ  መረጋገጡን  ገልጿል።
<<በአቶ ዘመነ ላይ  የደረሰባቸው ስቃይና እንግልት በሰው ልጅ ላይ ይፈጸማል ተብሎ ፈጽሞ የማይገመት ነው >>ብሏል-መኢአድ። ከአቶ ዘመነ በተጨማሪ ጠቅላላ ጉባኤውን ተሳትፈው የተመለሱት የፓርቲው የማህበራዊ ጉዳይ ኃላፊ አቶ እያሱ ሁሴን 3 አመት ተፈርዶባቸው እስር ቤት እንደሚገኙ እንዲሁም የፓርቲው አመራር አካላት የሆኑት  አቶ ተስፋዬ ታሪኩ፣ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንንና አቶ ጥላሁን አድማሴ   ታስረው እየተሰቃዩ እንደሚገኙ ገልጿል።
በሌላ በኩል  ምርጫ ቦርድ- መኢአድ በምርጫ 2007 እንዳይሳተፍ የኢህአዴግ ቀኝ እጅ ሆኖ በመስራት ላይ እንዳለ ያወሳው መግለጫው፤ ፓርቲው በምርጫው እንዳይሳተፍ ከተደረገ ሰላማዊ ትግሉን አጠናክሮ ይቀጥላል ብሏል፡፡
ምርጫ ቦርድና ኢህአዴግ በፓርቲው ላይ የሚፈጽሙትን በደል ለማስቆም በሚደርገው ትግልም ህዝቡ ከጎኑ እንዲቆም ጥሪ መኢአድ አቅርቧል።

ዓርብ 23 ጃንዋሪ 2015

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ጋዜጣውይ መግለጫ በከፊል


የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በዛሬው እለት ምርጫ ቦርድ በመኢአድ ላይ እየወሰደ ያለውን ህገወጥ አካሄድ መኢአድ እንደማቀበለው ገልፀዋል ኢቲቪ እና ፋና ሬዲዮ እያሠራጩ ያሉት ያለው የውስጥ ችግር የለም ፓርቲው አንዳችም ችግር ሳይኖርበት ችግር እንዳለ አድርጎ ማውራት ቅጥፈት ነው አንድ ግለሠብ የፓርቲ ማህተም ሠርቆ የወጣና ለጉባኤው ተራ አባል ሆኛለሁ ብሎ ደብዳቤ የፃፈን ግለሰብ ምርጫ ቦርድ አዝሎ ይዞራል ቀደም ሲል አበባው የሚባል ግለሰብን በመኢአድ ፕሬዝደንትን አላውቅም ያለውን ግለሠብ የፓርቲውን ማህተም ሠርቆ ሲወስድ ምርጫ ቦርድ እርምጃ መውሰድ ሲገባው ከሌባ ጋር የሚያደርገው ግንኙነት ወንጀል መሆኑን ገልፀዋል
ሌላው በመኢአድ ባላት ላይ እየደረሰ ያለው እስራት አፈና አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ገልፀዋል በ10/05/2007ዓም የፓርቲው ም/ል ፕሬዝደንትና የሠሜን ቀጠና ሀላፊ አቶ ዘመነ ምህረት አፊነው በመያዝ አዘዞ ጦር ካንፕ ከፍተኛ ድብደባ እየተፈፀመበት መሆኑን ማወቅ ተችሏል ሌላ የመኢአድን ጠቅላላ ጉባኤ ተካፍሎ ሲመለስ ተይዞ 3 አመት ከ7 ወር የተፈረደበት የማህበራውይ ጉዳይ ሀላፊ ኢያሱ ሁሴን በአሰቃቂ ሁኔታ ይገኛል
ሌሎች የማእከላውይ ም/ቤት አባላት
1, ተስፋየ ታሪኩ ከደጀን
2, መ/አ ጌታቸው መኮንን ከም/ጎጃም
3 , ጥላሁን አድማሴ ደ/ጎንደር ፀሀፊ 4, አቶ ታጀለ አለኸኝ አዊይ ዞን ከዳንግላ ወረዳ
5 , አቶ ዮሀንስ ገደቡ ከጫራ ወረዳ
6, አዝመራው ከፍአለ ወዘተ ታስረዋል አንዳንዶቹ ያሉበትም አልታወቀም
እየተደረገ ያለው አፈና ባስቸኳይ እንዲቆም የታሠረት አመራሮችና አባሎች ባስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቋል
ሌላው የገዥው ቀኝ እጅ መሆኑን ያረጋገጠው ምርጫ ቦርድ በመኢአድ ላይ እየሠራ ያለውን ደባ እንዲያቆም ወደ ህሊናው እንዲመለስ እናሳስባለን
1, ምርጫ ቦርድ በፓርቲዎች ላይ ያልተገባ አካሄዱን እንዲያስተካክል እናሳስባለን
2, የፓለቲካ ፓርቲዎች ከሠላማውይ ትግል ወደ ኋላ እንደማንል ቦርዱ ልብ ሊለው ይገባል
3, ምርጫ ቦርድ በመኢአድ ላይ ጣልቃ በመግባት የሚወስነው ውሳኔ ጥቅሙና ጉዳቱን ለይቶ ተጠንቅቆ የመኢአድን ህልውና እንዲያረጋጥ እናሳስባለን
ቦርድ ጣልቃ ገብነት ካላቆመ እስከመጨረሻው ድረስ አስፈላጊውን መስዋዕትነት በመክፈል በሠላማውይ መንገድ የምንታገለው መሆናችንን ለመላው ህዝብ እንገልፃለን
ህውሃት /ኢሃዴግ /በህዝብ ላይ የሚያደርሰውን ከፍተኛ ግፍ እና መከራ ማድረሱ መፍትሄ ስለማይሆን ባስቸኳይ ያቁም… …………………………………… ማንኛውም ኢትዮጵያውይ ከመኢአድ ጎን በመቆም አጋርነቱን እንዲያሳይ ጥሪ እናቀርባለን
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!

ረቡዕ 21 ጃንዋሪ 2015

Human Rights Watch released “Journalism is Not a Crime”:

Ethiopia’s government has systematically assaulted the country’s independent voices, treating the media as a threat rather than a valued source of information and analysis. Ethiopia’s media should be playing a crucial role in the May elections, but instead many journalists fear that their next article could get them thrown in jail. 
Leslie Lefkow, deputy Africa director
(Nairobi) – The Ethiopian government’s systematic repression of independent media has created a bleak landscape for free expression ahead of the May 2015 general elections, Human Rights Watch said in a report released today. In the past year, six privately owned publications closed after government harassment; at least 22 journalists, bloggers, and publishers were criminally charged, and more than 30 journalists fled the country in fear of being arrested under repressive laws.

The 76-page report, “‘Journalism is Not a Crime’: Violations of Media Freedom in Ethiopia,” details how the Ethiopian government has curtailed independent reporting since 2010. Human Rights Watch interviewed more than 70 current and exiled journalists between May 2013 and December 2014, and found patterns of government abuses against journalists that resulted in 19 being imprisoned for exercising their right to free expression, and that have forced at least 60 others into exile since 2010.

Ethiopia’s government has systematically assaulted the country’s independent voices, treating the media as a threat rather than a valued source of information and analysis,” said Leslie Lefkow, deputy Africa director. “Ethiopia’s media should be playing a crucial role in the May elections, but instead many journalists fear that their next article could get them thrown in jail.”

Most of Ethiopia’s print, television, and radio outlets are state-controlled, and the few private print media often self-censor their coverage of politically sensitive issues for fear of being shut down.

The six independent print publications that closed in 2014 did so after a lengthy campaign of intimidation that included documentaries on state-run television that alleged the publications were linked to terrorist groups. The intimidation also included harassment and threats against staff, pressure on printers and distributors, regulatory delays, and eventually criminal charges against the editors. Dozens of staff members went into exile. Three of the owners were convicted under the criminal code and sentenced in absentia to more than three years in prison. The evidence the prosecution presented against them consisted of articles that criticized government policies.



While the plight of a few high-profile Ethiopian journalists has become widely known, dozens more in Addis Ababa and in rural regions have suffered systematic abuses at the hands of security officials.

The threats against journalists often take a similar course. Journalists who publish a critical article might receive threatening telephone calls, text messages, and visits from security officials and ruling party cadres. Some said they received hundreds of these threats. If this does not silence them or intimidate them into self-censorship, then the threats intensify and arrests often follow. The courts have shown little or no independence in criminal cases against journalists who have been convicted after unfair trials and sentenced to lengthy prison terms, often on terrorism-related charges.

“Muzzling independent voices through trumped-up criminal charges and harassment is making Ethiopia one of the world’s biggest jailers of journalists,” Lefkow said. “The government should immediately release those wrongly imprisoned and reform laws to protect media freedom.”

Most radio and television stations in Ethiopia are government-affiliated, rarely stray from the government position, and tend to promote government policies and tout development successes. Control of radio is crucial politically given that more than 80 percent of Ethiopia’s population lives in rural areas, where the radio is still the main medium for news and information. The few private radio stations that cover political events are subjected to editing and approval requirements by local government officials. Broadcasters who deviate from approved content have been harassed, detained, and in many cases forced into exile.

The government has also frequently jammed broadcasts and blocked the websites of foreign and diaspora-based radio and television stations. Staff working for broadcasters face repeated threats and harassment, as well as intimidation of their sources or people interviewed on international media outlets. Even people watching or listening to these services have been arrested.

The government has also used a variety of more subtle but effective administrative and regulatory restrictions such as hampering efforts to form journalist associations, delaying permits and renewals of private publications, putting pressure on the few printing presses and distributors, and linking employment in state media to ruling party membership.

Social media are also heavily restricted, and many blog sites and websites run by Ethiopians in the diaspora are blocked inside Ethiopia. In April, the authorities arrested six people from Zone 9, a blogging collective that provides commentary on social, political, and other events of interest to young Ethiopians, and charged them under the country’s counterterrorism law and criminal code. Their trial, along with other media figures, has been fraught with various due process concerns. On January 14, 2015, it was adjourned for the 16th time and they have now been jailed for over 260 days. The arrest and prosecution of the Zone 9 bloggers has had a wider chilling effect on freedom of expression in Ethiopia, especially among critically minded bloggers and online activists.

The increased media repression will clearly affect the media landscape for the May elections,.

“The government still has time to make significant reforms that would improve media freedoms before the May elections,” Lefkow said. “Amending oppressive laws and freeing jailed journalists do not require significant time or resources, but only the political will for reform.” 

የመኢአድ አባላት በጅምላ እየታፈሱ ነው

ጥር ፲፫(አስራ ሦስት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል  የመላው ኢትዮጰያ አንድነት ድርጅት  አባላት በብዛት እየታሰሩ መሆናቸውን ከስፍራው  አንድ የመኢአድ  አመራር ገለጹ።
የድርጅቱ የ አዲስ አበባ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አወቀ አባተ  ለኢሳት እንደገለጹት፤በምራብ ጎጃም ዞን  በዳንግላ ወረዳ ጫራ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት የመኢአድ አባላት ወጣት ታጀለ አለኸኝ እና ወጣት የዋንስ ገደቡ፣ እንዲሁም የቡሬ ወረዳ  የ መ ኢአድ ወኪል የሆነው  አቶ አዝመራው ከፋለ  ሰሞኑን  በፖሊሶች ተይዘው ወዳልታወቀ ስፍራ ተወስደዋል።
እንዲሁም በጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 ነዋሪ የሆኑት የመኢአድ አባላት ወጣት ተስፋ አስማረና  ወጣት ችሎት ባዜ  በፌደራል ፖሊስ ተይዘው መወሰዳቸውንና  የደረሱበት አለመታወቁን የህዝብ ግንኙነት ሀላሰፊው ተናግረዋል።
በተመሳሳይ  በጃዊ ወረዳ  የመ ኢአድ አባላት የሆኑ በርካታ ወጣቶችም  በፌደራል ፖሊስ  ታፍሰው  የደረሱበት  መጥፋቱን  የገለጹት አቶ አወቀ፤ ስለጉዳዩ የወረዳው የፖሊስ አዛዥ ቢጠየቅም  <<የወሰዳቸው የፌድራል ፖሊስ ነው፤ እኛ የምናውቀው ነገር የለም>>” በማለት ምላሽ መስጠቱን ተናግረዋል።
“መኢአድን በማፈን ትግሉ ማቆም አይቻልም” ያሉት አቶ አወቀ፤  “ትግሉ በ እልህና በቁጭት ይበልጥ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ በርካታ የመኢአድ አመራሮች  በማእከላዊ ወንጀል ምርመራ ታስረው እየተሰቃዩ እንደሚገኙ በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወቃል

ከአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ /አንድነት/ የተሰጠ መግለጫ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)
በአንድነት ላይ የተቀነባበረው ዘመቻ በአስቸኳይ ይቁም!
ከአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ /አንድነት/
የተሰጠ መግለጫ

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ /አንድነት/ የ2007 አገር አቀፍ ምርጫን በአሸናፊነት ለመወጣት የተለየ ስትራቴጂ በመንደፍ በሙሉ ኃይሉ ወደ ሥራ ገብቷል፡፡ አንድነት የምርጫ ውድድር የይስሙላ ሳይሆን የምር መሬት ላይ በሚታይ ደረጃ መሆን እንዳለበት ወስኖ፤ የተንቀሳቀሰበት ሁኔታ በገዥው ፓርቲ የተወደደ ባለመሆኑ፤ በምርጫ ቦርድ፣ በሬዲዮ ፋና፣በቀድሞ ኢቲቪ በአሁኑ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬሽን እና የአንድነት አባል ነን በሚሉ በተግባር ለአፍራሽ ተልዕኮ በተሰለፉ ወገኖች የተቀነባበረ ዘመቻ ከተጀመረ ወራት ተቆጥረዋል፡፡ ዓላማው ግልፅ ነው፤ ህዝቡ በተቃዋሚዎች በተለይም በአንድነት ላይ እምነት እንዳይኖረው እና ተስፋ እንዲቆርጥ በማድረግ አሉታዊ የምርጫ ቅስቀሳ በፓርቲያችን ላይ በማሳደር ለገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ መንገድ እየጠረጉ ነው፡፡
አሁን ባለው ሁኔታ ከምንጊዜውም በላይ ባፈጠጠ እና ባገጠጠ መልኩ በኢትዮጵያ የመድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲ ፈተና ላይ ወድቋል፡፡ ሰላማዊ ትግሉ በሩ ሙሉ ለሙሉ እየተዘጋ መጥቷል፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ ሌሎች ትልልቅ በሮችን ይከፍታል፡፡ በዚህ መንገድ አገሪቱን ለከፋ ችግር እየተጋለጠች መሆኑ ግልፅ ጉዳይ ሆኗል፡፡ በፓርቲያችን በኩል ለሰላማዊ ትግል መጐልበት፤ ለዘላቂ ሰላምና መረጋጋት የቻልነውን ብናደርግም ህዝብ በሚከፍለው ታክስ የሚተዳደሩት የመገናኛ ብዙኃን እና የግል ተቋም ነኝ የሚለው፤ በተግባር ግን የገዥው ፓርቲ ልሳን የሆነው ሬዲዮ ፋና በፓርቲያችን ላይ ከምን ጊዜውም በላይ አፍራሽ ዘመቻቸውን አጠናክረው ገፍተውበታል፡፡ የዚሁ ተልዕኮ አካል የሆነ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ብሮድ ካስቲንግ ኮርፓሬሽን ከ3 ወር በፊት ያስተላለፈውን ፕሮግራም አቧራውን አራግፎ እንደ አዲስ ሐሙስ ጥር 14 ቀን 2007 ዓ.ም ምሽት ፕሮግራም እንዳዘጋጀ ተከታትለናል፡፡ በመሆኑም ሕዝቡ በቀድሞ ኢቲቪ በአሁኑ ኢቢሲ የሚተላለፉ ዘገባዎች ላይ ያለውን ዕምነት ብናውቅም ስለዚህ ፕሮግራም በፓርተያችን በኩል ማለት የምንፈልገው፤ የተለያዩ አካላት የፓርቲው አባላት ነን ከሚሉት ጋር በመሆን የተቀነባበር ቀጣይ አፍራሽ ድራማ መሆኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲረዳው ነው፡፡
በመጨረሻም የመንግስት ኃላፊነት እና ልዩ ልዩ ስልጣኖች ያልፋሉ አገር እና ሕዝብ ግን ህያው ናቸው፡፡ ዛሬ በአንድት ፓርቲ ላይ የተቀነባበረው ዘመቻ ለአባላቱና ለደጋፊው ጥንካሬን ይሰጠዋል “ታጋይና ምስማር ሲመቱት ይጠብቃል” እንደሚባለው ነው፡፡ ሕዝብ ደግሞ በግልፅ እየታዘበ ነው፡፡ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ሬዲዮ ፋና የቀድሞ ኢቲቪ የአሁኑ ኢብኮን ተባባሪዎቻቸውን ታሪክ እና ጊዜ ይፈረዳቸዋል፡፡ ፓርቲያችን አይጠፋም፡፡ ምንም ጥርጥር የለውም ሊያጠፉት የሚቅነዘነዙት ይጠፋሉ፡፡ የሕዝብ ፓርቲ ሁሌም ዘላለም ይኖራል፡፡
ድል የሕዝብ ነው!!
ጥር 14 ቀን 2007 ዓ.ም
አዲስ አበባ

ኢትዮጵያን እየመሩ ያሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት በሙሉ በጥቂት ቀናት ትምህርት ብቻ ከአንድ የውጪ ዩኒቨርሲቲ የማስተርስ ዲግሪ እንዲያገኙ መደረጋቸው ተመለከተ።


 ጥር ፲፫(አስራ ሦስት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሀገሪቱ
የምትመራበትን ፖሊሲ ከመጠምዘዝ ጀምሮ ድርጊቱ በሀገርና
በህዝብ ላይ የከፋ ተጽእኖ እንዳለው የተገነዘቡ ኢትዮጰያውያን
በዩኒቨርሲቲው ላይ የተቃውሞ ዘመቻ እያስተባበሩ ነው።
አዲስ አበባ የሚገኘው ኢንተርናሽናል ሊደር ሺፕ ኢንስቲትዩት
አማካይነት የሚቀርቡለትን ባለስልጣናት በአጭር ቀናት ኮርስ
በማስተርስ ዲግሪ እያንሸበሸ ያለው ፤በእንግሊዝ ሀገር የሚገኘው
የግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ ነው። በአይ ኤል አይ ድረገጽ
እንደተመለከተው ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝን
ጨምሮ ሁሉም የሀገሪቱ ባለስልጣናት በቀናት ኮርስ ከአንድ
ትምህርት ቤት ማለትም ከግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ የማስተርስ ዲግሪ
እንዲወስዱ ተደርገዋል።
እነሱም፦አፈ-ጉባኤ አባዱላ ገመዳ፣ የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ
ሚኒስትር አዲሱ ለገሰ፣የቀድሞው የኮሙኒኬሽን ሚኒስትርና የ
አሁኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲ አማካሪ በረከት
ስምኦን፣የሱማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ መሀመድ
ኡመር፣የቀድሞው የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር ጁነዲን ሳዶ፣
የቀድሞው የ አዲስ አበባ ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ፣የ ኦሮሚያ
ክልል ፕሬዚዳንት ሙክታር ከድር፣ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር
ዴኤታ ሸፈራው ተክለማርያም፤ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር
ሬድዋን ሁሴን፣ የትምርት ሚኒስትር ሽፈራው ሽጉጤ፣ የሲቪል
ሰርቪስ ምክትል ሚኒስትር አስቴር ማሞ፣ የቀድሞው መከላከያ
ሚኒስትርና የ አሁኑ የ አዲስ አበባ ከንቲባ ድሪባ ኩማ፣የሴቶች፣
የህጻናትና የወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትር ዘነቡ ታደሰ፣የፌዴሬሽን
ምክር ቤት አፈጉባ ኤ ካሳ ተክለብርሀን፣የሳይንስና ቴክኖሎጂ
ሚኒስትር ደሴ ዳልክዬ ዱካሞ፣የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት
ሚኒስትር ዴኤታ አብርሐም ተከስተመስቀል፣የቀድሞ መከላከያ
ሚኒስተርር ሲራጅ ፈርጌሳ፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ
ዳውድ መሀመድ አሊ፣የትራንስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ተከስተ ረባ
አያና፣በፌዴሬሽን ምክር ቤት የትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
ሰብሳቢ ሙፈሪያት ካሚል አህመድ እና በመከላከያ ሚኒስትር
የምእራብ እዝ አዛዥ ሜጀር ጀነራል ብርሀኑ ጁላ ጋላቻ ናቸው።
በኢንተርናሽናል ሊደር ሽፕ ኢንስቲትዩት ድረ-ገጽ ከተዘረዘሩት
ከነኚህ ባለስልጣናት ባሻገር የሀገሪቱ ጀነራሎችና የጦር አዛዦች
እንዲሆም የየዞኑ የቢሮ ሀላፊዎች በሙሉ በሶስትና አራት ቀናት
ኮርስ ከዚሁ ከግሪንዎች ዩኒቨርሲቲ የማስተርስ ዲግሪ መያዛቸውን
በአንድ ወቅት በዩኒቨርሲቲው መምህር የነበሩት ዶክተር ታደሰ ብሩ
ይናገራሉ።
የማስተርስ ዲግሪ ከወሰዱት ከነኚህ ሹመኞች መካከል በጣት
የሚቆጠሩ ጥቂቶች በራሳቸው የተማሩ ቢሆንም፤ በርካታዎቹ
የ2ለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሚገባ ስለማጠናቀቃቸው
ትክክለኛ ማረጋገጫ ማቅረብ አይቻልም። ከጠቅላይ ሚኒስትሩና
ከትምህርት ሚኒስትሩ ጀምሮ አሉ ለሚባሉ የሐገሪቱ ሹማምንት
ሁሉ የማስተርስ ዲግሪ በዚህ መልክ መታደሉ በሀገሪቱ
ፖሊሲዎችና የወደፊት አቅጣጫዎች ላይ ያለው ተጽ እኖ ከፍተኛ
እንደሆነ ዶክተር ታደሰ ያብራራሉ።
የግሪንዊች ዩኒቨርሲቲንም “ሀገሪቱን እጅ የጠመዘዘ፣ሀገሪቱን
እኪሱ ያስገባ ተቋም”ብለውታል ዶክተር ታደሰ። የትምህርት
ሚኒስትሩ ዕፈራው ሽጉጤ ከዚሁ ከግሪንዊች ተቋም መመረቃቸው
የሚፈጥረን የጥቅም ግጭት ዶክተር ታደሰ ሲያብራሩም፦ ይህ
ድርጊት ለዩኒቨርሲቲውም እፍረት ነው፤ለሀገራችንም ጉዳት ነው
ያሉት ዶክተር ታደሰ፤ የዩኒቨርሲቲውን ድርጊት ለመቃወም ፒቲሺን
ፈርሞ የማስገባት እንቅስቃሴ መጀመሩን በማውሳት፤
ኢትዮጰያውያን በተቃውሞ ዘመቻው እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል
ፍለጋው አልተሳካም
ቆራጡ የመኢአድ ከፍተኛ አመራር ዘመነ ምህረት ከተያዘበት እለት ጀምሮ ያለበትን ለማወቅ የተደረጉ ፍለጋዎች አልተሳኩም ዛሬም ፍለጋ ላይ የነበሩት የመኢአድ አባላትና ቤተሰቦቹ ከትላንቱ የተለየ ነገር እንደሌለ ገልፀውልኛል
ከ1ወር በፊት ከጎንደር ተሳዶ የመጣው የመኢአድ አባል ጌትነት ደሴ ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ፅ/ቤት እቃ ገዝቼ መጣሁ ብሎ እንደወጣ ሳይመለስ ቀርቷል እስከአሁን የት እንዳለ ማወቅ አልተቻለም

ሰኞ 19 ጃንዋሪ 2015

የመላው ኢትዮጲያ አንድነት ድርጂት (መኢአድ)
የቁርጥ ቀን ልጆቺ
የኛ ማንዴላወች
የመላው ኢትዮጲያ አንድነት ድርጂት ( መኢአድ )
የቁርጥ ቀን ልጆቺ
የኛ ማንዴላወች


ይች ለግላጋ ቆንጆ ትርሲት ውቤ ትባላለች፤
የጎንደር ከተማ ነዋሪ ስትሆን በቅርቡ
በፌደራሎች ታፍና ተወስዳ የት እንዳለች
ማወቅ አልተቻለም። የኢንተርኔት ካፌና
የፎቶ ኮፒ ንግድ ቤት ባለቤቷ ትርሲት ገዥው
ቡድን በአሰማራቸው አፋኞች የተወሰደችው
የተቃዋሚዎችን ፅሁፎችና መፈክሮች ኮፒ
እያደረግሽ ህገ መንግስቱን በሀይል ለመናድ
አሲረሻል በሚል ምክንያት እንደሆነ በወቅቱ
በሥራ ቦታዋ አካባቢ የነበሩ የአይን እማኞች
ተናግረዋል። ቤተሰቦቿ በተደጋጋሚ ወደ
ፖሊስ ጣብያ እየሄዱ ያለችበትን ለማወቅ
ያደረጉት ጥረት እስካሁን አልተሳካም።

በተቃዋሚዎች ላይ እየተፈጸመ ያለው በደል ተባብሶ ቀጥሏል

ጥር ፲፩(አስራ አንድ ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጎንደር ዙሪያ ወረዳ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ) አስተባባሪ  የሆነው ወጣት ዘመነ ምረተአብ ትናንት ጥር 10 ቀን  11:00  አካባቢ  በማክሰኝት ከከተራ በዓል ላይ ባልታወቁ ሰዎች ተወስዷል። አፋኞቹ ዘመነ ምረተአብን ወዴት እንደወሰዱትና በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ እስካሁን አልታወቀም።

ቀደም ሲል የታሰሩት  የመኢአድ የቀድሞ  ዋና ጸሃፊ አቶ ተስፋየ ታሪኩ፣ የድርጅቱ የደቡብ ጎንደር ዋና ጸሃፊ የሆነው አቶ ጥላሁን አድማሴ እና   የምራብ ጎጃም ዋና አደራጅ የሆነው መቶ አለቃ ጌታቸው  በማእከላዊ ወንጀል ምርመራ እየተገረፉና  እየተሰቃዩ እንደሚገኙ  ተመልክቷል።

<< የመኢአድን አመራሮችን በማሰር የኢትዮጲያን ትንሳኤ ማዳፈን አይቻልም፤ እንደውም እየደረሰብን ያለው ግፍ መኢአድ በበለጠ መልኩ  ያጠናክረዋል>>-ብለዋል የድርጅቱ  የአዲስ አበባ  ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አወቀ አባተ።

በተመሳሳይ በአንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምጽ አምደኛና የፓርቲው አባል  የሆነው  እስማኤል ዳውድ እንድሪስ ትናንት ማለዳ ከሌሊቱ 12   ላይ በሁለት ሲቪል በለበሱና በሁለት ታጣቂዎች ከመኖሪያ ቤቱ ተወስዷል።

እስማዔል በፖሊሶች ሊወሰድ ሲል ስልክ ደውሎለት እንደነበር የገለጸው ጓደኛውና የድርጅት አጋሩ አናንያ ሶሪ፤ በስፍራው ሲደርስ ወላጅ እናቱ እየተመለከቱ ፖሊሶች  ሲወስዱት ማየቱን ተናግሯል።

እስማ ኤል ወደተወሰደበት  ጃን ሜዳ ፖሊስ ጣቢያ ከሶስት ጓደኞቹ ጋር  መሄዳቸውን የገለጸው አናንያ፤  ፖሊሶች  እስማዔልን ወደ ፍርድ ቤት ሊወስዱት  መኪና ላይ ሲጭኑት ፎቶ በማንሳቱ  እሱንም  እንዳሰሩትና ቃሉን ከተቀበሉ በሁዋላ እንደለቀቁት ተናግሯል።

እስማዔል  በአሁኑ ወቅት የ 7 ቀን ቀጠሮ ተጠይቆበት በቀጨኔ ፖሊስ ጣቢያ ይገኛል።

ቀደም ሲል  የተገንጣዩ ቡድን አባል የነበረው መሳይ ትኩ፤ ሁዋላ ላይ ወደ ራሱ በመመለስ  የተገንጣዮቹን ሴራ በማጋለጡ፤ የቅድስት ማርያም ነዋሪ በሆነው እና ዳን ኤል ሙላት በተባለው አብሮ አደጉ መደብደቡን  ያወሳው አናንያ፤ በፓርቲያቸው አባላት ላይ እየደረሰ ያለው በደል እየከፋ መምጣቱን ተናግሯል።

ላለፉት ሶስት ዓመታት በጋዜጠኝነት ሲሰራ የቆየው አናንያ ሶሪ፤  ለመብትና ለነጻነት በሚደረገው ትግል የድርሻውን ለማበርከት  ከቀናት በፊት አንድነት ፓርቲን በይፋ እንደተቀላቀለ ማሳወቁ ይታወሳል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ   ትርሲት ውቤ የተባለች የጎንደር ከተማ ነዋሪ ወጣት  በቅርቡ በፌደራሎች ታፍና መወሰዳን እና እስካሁ  የት እንዳለች አለማመታወቁን ከስፍራው የደረሰን ዜና ያመለክታል።

የኢንተርኔት ካፌና የፎቶ ኮፒ ንግድ ቤት ባለቤት የሆነችው ወጣት ትርሲት በአፋኞች የተወሰደችው፤ የተቃዋሚዎችን ፅሁፎችና መፈክሮች ኮፒ እያደረግሽ ህገ መንግስቱን በሀይል ለመናድ አሲረሻል በሚል ምክንያት እንደሆነ በወቅቱ በሥራ ቦታዋ አካባቢ የነበሩ የአይን እማኞች ተናግረዋል። ቤተሰቦቿ በተደጋጋሚ ወደ ፖሊስ ጣብያ እየሄዱ ያለችበትን ለማወቅ ያደረጉት ጥረት እስካሁን አልተሳካም።

በሌላ በኩል  ወጣቶች በከተራ እና በጥምቀት በዓል ላይ ሰማያዊ ቲሸርት እንዳይለብሱ ፖሊስ ሲያስጠነቅቅ ቢቆይም፤ <<መንግስት በእምነታችን አያገባውም፤ልብሳችንንም  ሊመርጥልን አይችልም>> ያሉ ወጣቶች ሰማያዊ ቲሸርቶችን ለብሰው ወጥተዋል።

በየሰንበት ት/ቤቱ ሰማያዊ ቲሸርት እንዳይለብሱ ጥብቅ ትእዛዝ የተላለፈ ቢሆንም፤  በርካታዎቹ የሰንበት ተማሪ ወጣቶች የተሰጣቸውን ማስጠንቀቂያ ከምንም ሳይቆጥሩት  ከመቼውም ወቅት በላይ በሰማያዊ ቲሸርት አሸብርቀው ታይተዋል።

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወንድም በወታደሮች ተደበደበ

ጥር ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዝዋይ ወህኒ ቤት የሚገኘውን ወንድሙን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ለመጠየቅ ትናንት ማለዳ ወህኒ ቤቱ በራፍ ላይ የደረሰው ታሪኩ ደሳለኝ በወህኒ ቤቱ ሀላፊና ስምንት በሚደርሱ ወታደሮች ድብደባ እንደደረሰበት በፌስ ቡክ ገጹ ታሪኩ አስታውቋል፡፡ለተመስገን ይዞ የመጣውን ምግብ ወታደሮቹ መሬት ላይ ከመድፋታቸውም በላይ በኪሱ የያዘውን ገንዘብ ወስደውበታል፡፡ታሪኩ ከደረሰበት ድብደባ በላይ ወንድሙን ሳይጠይቅና የሚገኝበትን ሁኔታ ሳያጣራ መመለሱ ህመም እንደፈጠረበት አስታውቋል

ሐሙስ 15 ጃንዋሪ 2015

አንድነት ለፍትህኗ ለዲሞክራሲ ፓርቲ- ከመድረክ ጋር በትብብር ከመ ኢአድ እና ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ደግሞ ውህደት ፈጥሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ።

ጥር ፭(አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፍኖተ ነጻነት የፓርቲውን የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ አቶ ተክሌ በቀለን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ  ታህሳስ 25 ቀን 2007 ኣመተ ምህረት ባደረገው ስብሰባ  መጪውን ምርጫና ከምርጫው ጋር ተያይዘው ስለሚመጡ ጉዳዮች፤ እንዲሁም ከምርጫው በሁዋላ ፓርቲዎች ሊኖራቸው ስለሚገባው ትብብርና ውህደት የሚያመቻች ኮሚቴ ተቋቁሟል።
በስብሰባው፣ ፓርቲዎች በትብብርና በውህደት መስራት እንዳለባቸው ስራ አስፈጻሚው መምከሩን የተናገሩት አቶ ተክሌ ፤ ፓርቲያቸው ከመድረክ ጋር በትብብር ከሰማያዊና ከ መ ኢአድ ጋር ደግሞ ውህደት ፈጥሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አስታውቀዋል።
ተቃዋሚ ፓርቲዎች በገዥው ፓርቲ ላይ ጫና  በማሳደር አሁን ካሉበት ደረጃ  ወደፊት መሄድ  የሚችሉት ተባብረው አለያም ተዋህደው ሲሰሩ ብቻ ነው ብሎ ሚያምነው አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ፓርቲዎቹ እንዲዋሀዱ አለያም ተባብረው እንዲሰሩ ጥሪ እያደረገ ይገኛል።በተለይ በአሁኑ ወቅት ፓርቲዎቹ በምርጫ ቦርድ አማካይነት እያደረገባቸው ያለውን  ከበድ ያለ ጫና ለመቋቋም ቢያንስ ተባብሮ መስራት አስፈላጊ እንደሆነ የሚመክሩ በርካታዎች ናቸው።
በሌላ በኩል ምርጫው በተቃረበበት በአሁኑ ወቅት፡ከፓርቲዎች ጋር ውዝግብ ውስጥ ገባው ምርጫ ቦርድ አንድነትና መኢአድ በሁለት ሳምንት ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርጉ ውሳኔ ማሳለፉን እና ለሰማያዊ ፓርቲ ማስጠንቀቂያ ሰጥቻለሁ ማለቱን ነገረ-ኢትዮጵያ ዘግባል።
እንደ ጋዜጣው ዘገባ’፤የቦርዱን ስብሰባ ረግጦ ከመውጣትም በላይ ይቅርታ ለመጠ የቅ ፈቃደኛ አይደለም ላለው ሰማያዊ ፓርቲ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን የገለጸው ቦርዱ፤ ፓርቲው ማስጠንቀቂያውን የማያከብር ከሆነ ህጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ ሲል ዝቷል።

ሐሙስ 8 ጃንዋሪ 2015

ከትናን በስቲያ ሰኞ ታህሳስ 27 ቀን 2007 ዓመተ ምህረት በአዲስ አበባ ወሎ ሰፈር የሚገኙ የውስጥ መንገዶች  በግድግዳ ላይ ጽሁፎችና መፈክር በተጻፈባቸው ወረቀቶች አሸብርቀው ማደራቸውን ፍትህ ራዲዮ ዘገበ።


ታኀሳስ ፳፱(ሃያ ዘጠኖ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ራዲዮው  ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ የውሎ ሰፈር የውስጥ መንገዶች ግድግዳ ላይ የተጻፉት መፈክሮች-ህዝበ-ሙስሊሙ መብቱን ለማስከበር ያነሳቸውን ያቄዎች የሚያሰተጋቡና  መብታቸውን በመጠየቃቸው የታሰሩት የሙስሊም  መሪዎች እንዲፈቱ የሚጠይቁ ናቸው።
ከተለጠፉት መፈክሮች መካከል፦”አዐባሪዎች አይደለንም፣ የታሰሩት ሙስሊሞች ይፈቱ!ኮሚቴው ይፈታ!የሂጃብ ገፈፋው ይቁም! ትግሉ ይቀጥላል! እና ፍትህ ናፈቀን!”የሚሉት ይገኙበታል።
በግድግዳ ላይ ከተጻፉትና ከተለጠፉት ባሻገር ሙስሊሞች መብታቸውን ለማስከበር ያነሷቸውን ጥያቄዎች የሚያስተጋቡ በርካታ ወረቀቶችም መበተናቸው ታውቋል።

የህወሀት መስራችና የቀድሞ ሊቀ-መንበር የአቶ ስብሀት ነጋ ልጅ፤ ጎተራን ለአምሰት አመት ኮንትራት በ600 ሺህ ብር እንደወሰደው ፎርቹን ሳምንታዊ ጋዜጣ ዘገበ።

ታኀሳስ ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-እንደ ጋዜጣው ዘገባ የአክሊል ክሬቲቭ ኤጄንሲ ባለቤት የሆነው ተከስተ ስብሀት  ነጋ፤ በአካባቢው ያለን 4000 ስኩዌር ኪሎ ሜትር መሬትን ለተለያዩ መዝናኛዎች፣እንዲሁም  43 ትልልቅ ጎተራዎችን ለማስታወቂያ ስራ  ነው በ600 ሺህ ብር ለአምስት ዓመት ኮንትራት የወሰደው።
ለጥቂት ቀናት የሚለጠፍ አንድ ማስታወቂያ ብቻ ብዙ ሺህ ብር  በሚያስከፍልበት በአሁኑ ወቅት፤ ትልቅ አደባባይ የሆነውን የጎተራን አካባቢና ትላልቆቹን  43 ጎተራዎች በአንድ ዓመት በመቶ ሀያ ሺህ ብር ሂሳብ  ለአቶ ስብሀት ነጋ ልጅ መሰጠታቸው፤ ስርዓቱ  የተዘፈቀበትን  የሙስና ጥልቀት የሚያሳይ ነው ሲሉ የጋዜጣውን ዘገባ ያነበቡ ሰዎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ጋዜጣው በሌላ ዘገባው የሕወኃት ንብረት የሆኑትን ኤፈርትን እና መስፍን ኢንጂነሪንግን  ሲያስተዳድር የቆየው የቀድሞው  የአዲስ አበባ ከንቲባ የኣርከበ ዕቑባይ ወንድም  ጌታቸው ዕቑባይ በዚህ ሳምንት  የኢትዮጰያ የመንገዶች ባለስልጣንን በሀላፊነት እንደሚረከብ አስነብቧል።

ረቡዕ 7 ጃንዋሪ 2015

ምርጫ ቦርድ ፤አንድነትና መኢአድ በምርጫው ላይሳተፉ ይችላሉ አለ።



ታኀሳስ ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንድነት፤ ከምርጫው ከታገድኩ ውሳኔው ፖለቲካዊ ነው የሚሆነው አለ።
አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት)እና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የውስጥ ችግሮቻቸውን ካለፈቱ የምርጫውን ሂደት ላይሳተፉ ይችላሉ ሲል የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስጠነቀቀ።
የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ዶክተር አዲሱ ገብረ እግዚአብሄር ፦ሁለቱ ፓርቲዎች በውስጥ ህገ ደንባቸው ሊሄዱ እንዳልቻሉ በመጥቀስ፤ ይህንንም አስመልክቶ ቦርዱ ሊያወያያቸው ቢሞክርም ሊግባቡ አልቻሉም ብለዋል። በመሆኑም ቦርዱ በጉዳዩ ላይ በመጪው ማክሰኞ ውይይት እንደሚያደርግ ምክትል ሰብሳቢው ለድርጅት ብዙሀን መገናኛዎች ተናግረዋል።
ችግርን ለመፍታት እና ለህግ ተገዢ የመሆን ቁልፉ በፓርቲዎቹ እጅ ይገኛል ያሉት የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ፤ ፓርቲዎቹ ለህግ ተገዢ ሆነው በምርጫ የመወዳደር ዕድሉ አሁንም እንዳላቸውም ገልጸዋል። በፓርቲዎቹ የታዩ ችግሮችን በተመለከተ ቀደም ሲል በተደጋጋሚ መግለጫ ተሰጥቷል ያሉት ዶክተር አዲሱ፥ ችግሮቻቸውን በመተዳደሪያ ደንባቸው መሰረት መፍታት ካለቻሉ በመጪው ግንቦት የሚካሄደው ምርጫ ላይ እንደማይሳተፉ ተናግረዋል።
ኢሳት ከሁለት ሳምንት በፊት ስለፖለቲካ ፓርቲዎች እጩ ምዝገባ ባስተላለፈው ዜና አንድነትና መኢአድ ከምርጫ ቦርድ ጋር በተፈጠረ ውዝግብ በምርጫው የመሳተፋቸው ነገር አጠራጣሪ እንደሆነ መዘገቡ ይታወሳል።
ጉዳዩን አስመልክቶ የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ አመራር አቶ አስራት አብርሀ በሰጡት ምላሽ ፤ቦርዱ የሚሰበሰበው ገና ዛሬ ሆና ሳለ ፤ምክትል ሰብሳቢው ከአንድ ቀን በፊት በድርጅት ሚዲያ መግለጫ መስጠታቸው ስህተትና በቦርዱ ውሳኔ ላይ ተጽእኖ የሚፈጥር መሆኑን በመጥቀስ፤አንድነት መደረግ ያለባቸውን ነገሮች በሙሉ ማድረጉንና ያልፈታው ችግር እንደሌለ ገልጸዋል።
ቦርዱ አንድነት በምርጫው እንዳይሳተፍ ከወሰነ ፤ ሆን ተብሎ አንድነት በምርጫው እንዳይሳተፍ የማድረግ ፖለቲካዊ ነው የሚሆነው ያሉት የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አስራት አብርሐ ፤ያኔ አንድነትም ለዚህ ተመጣጣኝ የሆነ የራሱን ፖለቲካዊ ውሳኔ ይወስናል ብለዋል። ወደ ምርጫው ስንገባ እናሸንፋለን፤አናሸንፍም በሚል ስሌት ሳይሆን ህዝቡን በዚህ መልክ በማንቃት ለተሻለ ትግል የምናደራጀበትን መንገድ እንከፍታለን ብለን ነው ያሉት አቶ አስራት፤ “ቦርዱ እንዳንሳተፍ ከከለከለን ምንም የሚያደናገጠን ነገር የለም፤እንደውም ቀጥታ ህዝቡን ወደማደራጀትና ወደማታገል እንድንገባ መንገዱን ነው የሚያቀልልን ” ብለዋል።