የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በዛሬው እለት ምርጫ ቦርድ በመኢአድ ላይ እየወሰደ ያለውን ህገወጥ አካሄድ መኢአድ እንደማቀበለው ገልፀዋል ኢቲቪ እና ፋና ሬዲዮ እያሠራጩ ያሉት ያለው የውስጥ ችግር የለም ፓርቲው አንዳችም ችግር ሳይኖርበት ችግር እንዳለ አድርጎ ማውራት ቅጥፈት ነው አንድ ግለሠብ የፓርቲ ማህተም ሠርቆ የወጣና ለጉባኤው ተራ አባል ሆኛለሁ ብሎ ደብዳቤ የፃፈን ግለሰብ ምርጫ ቦርድ አዝሎ ይዞራል ቀደም ሲል አበባው የሚባል ግለሰብን በመኢአድ ፕሬዝደንትን አላውቅም ያለውን ግለሠብ የፓርቲውን ማህተም ሠርቆ ሲወስድ ምርጫ ቦርድ እርምጃ መውሰድ ሲገባው ከሌባ ጋር የሚያደርገው ግንኙነት ወንጀል መሆኑን ገልፀዋል
ሌላው በመኢአድ ባላት ላይ እየደረሰ ያለው እስራት አፈና አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ገልፀዋል በ10/05/2007ዓም የፓርቲው ም/ል ፕሬዝደንትና የሠሜን ቀጠና ሀላፊ አቶ ዘመነ ምህረት አፊነው በመያዝ አዘዞ ጦር ካንፕ ከፍተኛ ድብደባ እየተፈፀመበት መሆኑን ማወቅ ተችሏል ሌላ የመኢአድን ጠቅላላ ጉባኤ ተካፍሎ ሲመለስ ተይዞ 3 አመት ከ7 ወር የተፈረደበት የማህበራውይ ጉዳይ ሀላፊ ኢያሱ ሁሴን በአሰቃቂ ሁኔታ ይገኛል
ሌሎች የማእከላውይ ም/ቤት አባላት
1, ተስፋየ ታሪኩ ከደጀን
2, መ/አ ጌታቸው መኮንን ከም/ጎጃም
3 , ጥላሁን አድማሴ ደ/ጎንደር ፀሀፊ 4, አቶ ታጀለ አለኸኝ አዊይ ዞን ከዳንግላ ወረዳ
5 , አቶ ዮሀንስ ገደቡ ከጫራ ወረዳ
6, አዝመራው ከፍአለ ወዘተ ታስረዋል አንዳንዶቹ ያሉበትም አልታወቀም
እየተደረገ ያለው አፈና ባስቸኳይ እንዲቆም የታሠረት አመራሮችና አባሎች ባስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቋል
ሌላው የገዥው ቀኝ እጅ መሆኑን ያረጋገጠው ምርጫ ቦርድ በመኢአድ ላይ እየሠራ ያለውን ደባ እንዲያቆም ወደ ህሊናው እንዲመለስ እናሳስባለን
1, ምርጫ ቦርድ በፓርቲዎች ላይ ያልተገባ አካሄዱን እንዲያስተካክል እናሳስባለን
2, የፓለቲካ ፓርቲዎች ከሠላማውይ ትግል ወደ ኋላ እንደማንል ቦርዱ ልብ ሊለው ይገባል
3, ምርጫ ቦርድ በመኢአድ ላይ ጣልቃ በመግባት የሚወስነው ውሳኔ ጥቅሙና ጉዳቱን ለይቶ ተጠንቅቆ የመኢአድን ህልውና እንዲያረጋጥ እናሳስባለን
ቦርድ ጣልቃ ገብነት ካላቆመ እስከመጨረሻው ድረስ አስፈላጊውን መስዋዕትነት በመክፈል በሠላማውይ መንገድ የምንታገለው መሆናችንን ለመላው ህዝብ እንገልፃለን
ህውሃት /ኢሃዴግ /በህዝብ ላይ የሚያደርሰውን ከፍተኛ ግፍ እና መከራ ማድረሱ መፍትሄ ስለማይሆን ባስቸኳይ ያቁም… …………………………………… ማንኛውም ኢትዮጵያውይ ከመኢአድ ጎን በመቆም አጋርነቱን እንዲያሳይ ጥሪ እናቀርባለን
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ