ረቡዕ 16 ጁላይ 2014

የመኢአድና አንድነት ውህደት አመቻች ኮሚቴ የባንክ አካውንቱን ይፋ አደረገ


የመኢአድና አንድነት ውህደት አመቻች ኮሚቴ ስራውን በቅልጥፍና እና በትጋት እየተወጣ መሆኑን ለፍኖተ ነፃነት የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ በዚህም መሰረት ለጉባኤው መሳካት ይረዳ ዘንድ መላው ኢትዮጵያውያን እንዲተባበሩ ጥሪ በማድረግ የባንክ አካውንቱን ይፋ አድርጓል፡፡
የባንክ አካውንት ቁጥር አቢሲኒያ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ UDJ A/C 47
የባንክ አካውንት ቁጥር አቢሲኒያ ባንክ ቦሌ ቅርንጫፍ AEUP SP 235

ማክሰኞ 8 ጁላይ 2014

ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ለኢትዮጵያ ሕዝብ የቀረበ የሰላማዊ ትግል ጥሪ


“ኢትዮጵያን ለመታደግ በንቃት እንደራጅ!!

ዛሬ በረገፈ ዘውዱና በረገበ ዙፋኑ ላይ ያለ አቅሙና ያለ ህዝባዊ ይሁንታ የቆጥ ላይ እንቅልፍ የሆነበትን “ሥልጣን” የሙጥኝ ብሎ ያለው መካሪና ዘካሪ አልባው የህወሓት /ኢህአዴግ “መንግሥት” የሚንሊክ ቤተ-መንግሥትን ከተቆጣጠረ ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ የራሱን ስውር ደባ ለማስፈፀም በሚያመቸው መንገድ ጥንተ ገናናዋን፣ የዓለም የነፃነት ተምሳሌቷን፣ የጥበብና የሥልጣኔ ጮራዋን፣ የይሁዲ የክርስትና የእስልምና ማደሪያ የሆነች ምድረ ገነት የብዙሺህ ዓመት እመቤት ውዲት ሀገራችን ኢትዮጵያን ከፋሺስት ጣሊያን ተውሶ ባመጣው ሽንሸና በዘርና በቋንቋ አቧድኖ ላለፉት 22 ዓመታት በአሰቃቂ ጭቆና በግፍ ረግጦ ሲገዛህ ቆይቷል፤ ይህንን ህዝብን በሙልጭልጭ ሰንካላ ምክንያቶች በመከፋፈል /በመለያየት፣ በማባላት /በማናከስ፣ በመናቅ/ በማዋረድ፣ በማሸማቀቅ /አንገት በማስደፋት ለመዋሸት /በመቅጠፍ ላይ የተመሰረተ የእውር ድንብር አስተዳደሩን የሚቃወሙ ዜጎችን በማሳደድ፣ በመደብደብ፣ በመግደል፣ ከሥራና ከመኖሪያ በማፈናቀል፣ ያፈሩትን ሃብት በመዝረፍ፣ ከቤተሰብና ከትዳር በመለያየት፣ ዘብጥያ በማውረድ፣ በኃይማኖት ጣልቃ በመግባት ከፈጣሪያቸው በመለየት፣ ራሳቸውን እንዲያጠፉ በማድረግ፣ የገዛ ሃገራቸውን ጥለው እንዲሰደዱ ከፈተኛ ጫና በማድረግ “የነፍስ ውጪ የነፍስ ግቢ” የጣር እስትንፍሱን ለማራዘም ሲፍጨረጨር ቆይቷል እየተፍጨረጨረም ይገኛል፡፡
ህወሓት /ኢህአዴግ የአንባገነንነቱን በትር ከጨበጠበት እለት ጀምሮ ከራሱ መሰል ግለሰቦችና ተላላኪዎች በስተቀር ሌሎች ዜጐች በሀገራችን ባይተዋርና የበይ ተመልካች ሆነን ለአንዲት ቀን እንኳ ከኑሮ ግብግብ አፎይ ሳንል በምንጓዛት አንዲት እርምጃ ሁሉ እንቅፋት የተሞላው ድቅድቅ ጨለማ ሆኖብናል፡፡ በዚህም ምክንያት ቀደም የነበረን የውስጥ ደስታና የርስ በርስ ፍቅር አጥተን በአስከፊ ስቃይ ላይ እንገኛለን፡፡
የሀገሪቱ የፖለቲካ የኢኮኖሚና ማህበራዋ እንቅስቃሴ ፈፅሞ ፍትህ የጐደለው ከመሆኑ የተነሳ ጥቂት አፍቃሬ ህውሓት /ኢህአዴግ የሆኑ ግለሰቦች በአንድ ጀንበር ሚሊየኒየር ሲያደርግ አጠቃላይ ዜጐችን ደግሞ እያንደረደረ ወደ ድህነትና ድንቁርና የሲኦል አዘቅት ያለርህራሄ ይወረውራቸዋል፣ ከዚህም የተነሳ የመላ ሃገሪቱ አዛዥና ናዛዥ እነርሱ አንተ ደግሞ ሁሉ ነገርህን ተነጥቀህ ጭሰኛ ከሆንክ ሰነባብቷል፡፡
ይህንንም አገዛዝ ለማሰንበት ይቻለው ዘንድ የህወሓት /ኢህአዴግ አምባገነን “መንግሥት” በየጊዜው የሚያወጣቸውና የሚያፀድቃቸው ፌደራላዊም ሆነ ክልላዊ ፖሊሲዎች በሙሉ ለሀገርም ሆነ ለህዝብ ጥቅም ታስቦ ሳይሆን ለህወሓት /ኢህአዴግ የፖለቲካ ትርፍ እንዴት እንደሚያስገኙለት ታሳቢ በማድረግ ብቻ ነው፡፡ ይህ ሀገርንም ሆነ ህዝብን አጥፊ የሆነ ሒደት ተገቶ በአገራችን ኢትዮጵያ ለህዝብ ተጠያቂና ተገዢ፣ የሆነ መንግሥት ተቋቁሞ ዲሞክራሲ፣ መልካም አስተዳደር፣ ፍትሕ፣ ሰላምና ብልፅግና ማስፈን እንዲቻል መኢአድ “የስልጣን ምንጭ ሕዝብ ነውና!” ኑ! አብረን በሰላማዊ ትግል ህወሓት /ኢህአዴግን እናበርክከው እያለ ህዝባዊ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

የአንድነት ስራ አስፈፃሚ አስቸኳይ ስብሰባ ተጠራ

የአንድነት ስራ አስፈፃሚ አስቸኳይ ስብሰባ ተጠራ
**************************************************
የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊና የመኢአድ እና የአንድነት የውህደት ጉዳዮች አመቻች ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆነው ወጣቱ ፖለቲከኛና ደራሲ ሀብታሙ አያሌው ዛሬ ጠዋት በመንግስት የደህንነት ሀይሎች መታገቱን ተከትሎ ፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው በምን ሁኔታ እንደሚገኝ ለማጣራት ያደረገው ሙከራ ባለመሳካቱ ምክንያት ስራ አስፈፃሚውን አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቷል፡፡ ስራ አስፃሚው ከስብሰባው በኋላ ጠንከር ያለ ፖለቲካዊ አቋም ይይዛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የአንድነት ፓርቲ ወጣት አመራሮችን የመሰር ዘመቻው ቀጥሏል

የአንድነት ፓርቲ ወጣት አመራሮችን የመሰር ዘመቻው ቀጥሏል
------------------------
የአንድነት ፓርቲ ም/የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሺ ዛሬ ጠዋት ሜክሲኮ አካባቢ በመንግስት የፀጥታ ሀይሎች ከተያዘ በኋላ በአሁኑ ሰዓት አየርጤና አካባቢ የሚገኘው መኖሪያ ቤቱ እየተበረበረ እንደሆነ ለፍኖተ ነፃነት የደረሰው መረጃ አመልክቷል፡፡

አቶ ሀብታሙ አያሌው ተያዙ፤ እስካሁን ያሉበት ሁኔታም ሆነ ቦታ አልታወቀም

አቶ ሀብታሙ አያሌው ተያዙ፤ እስካሁን ያሉበት ሁኔታም ሆነ ቦታ አልታወቀም
+++++++++++++++++++++++++++++++
የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው በዛሬው እለት ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ላይ ወደ ቢሮአቸው በማምራት ላይ እንዳሉ ደንበል አካባቢ የፖሊስ የደንብ ልብስ በለበሱ አካላት መያዛቸውን ከስፍራው የነበሩ የዓይን እማኞች የገለፁ ስሆን እስካሁን የት አውንዳሉና በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ አልተቻለም፡፡

ቅዳሜ 5 ጁላይ 2014

የተቃዋሚ አባላትን ማሰር ማወከብና ማፈናቀሉ ቀጥሏል

--------------------------------------------------
በሰሜን ወሎ መቄት ወረዳ የሚኖሩ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አባሎች የሆኑት
- አቶ ሞላ ገረመው
- አቶ ብርሃኑ ገረመው
- አቶ ካሳሁን እንዳለ ከረቡዕ ሰኔ 18 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ የተቃዋሚ አባል
በመሆናቸው ብቻ የሚያርሱትን መሬት ቀምተው አሳርሰውባቸዋል፡፡ ለምን እንቀማለን ዜጎች አይደለንም ወይ ብለው ተቃውሞ
ሲያሰሙ ከፓርቲው ለቃችሁ ካልወጣችሁ መሬታችሁ አይመለስም በማለት የቀበሌው ሊቀመንበር አቶ ፀጋዬ ጎሹ አስፈራርተዋቸዋል፡፡
እንዲሁም በምዕራብ ጎጃም በይልማና ዴንሳ ወረዳ (አዴት) የሚገኙ የመኢአድ አባላት ላይ እስርና አፈና የተፈጸመ ሲሆን አቶ በቃሉ
ደፋሩ የተባሉ የወረዳው አባል ከሳምንት በፊት በፖሊስ ተይዘው እስካሁን ፍ/ቤት አልቀረቡም፡፡
በዚሁ ወረዳ - አቶ አትገኝ እምሬ እንዲሁም
- ቄስ ይሁን ዘለቀ ከሐሙስ ሰኔ 19ቀን 2006ዓ.ም ሌሊት ጀምሮ የደረሱበት አይታወቅም ሲሉ የመኢአድ
የህ/ግንኙነት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አለምነህ ለፍኖተ ነፃነት ዝግጅት ክፍል ገልጸዋል፡፡

የተቃዋሚ አባላትን ማሰር ማወከብና ማፈናቀሉ ቀጥሏል
---------------------------------------------------------------------
በሰሜን ወሎ መቄት ወረዳ የሚኖሩ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አባሎች የሆኑት
- አቶ ሞላ ገረመው
- አቶ ብርሃኑ ገረመው
- አቶ ካሳሁን እንዳለ ከረቡዕ ሰኔ 18 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ የተቃዋሚ አባል
በመሆናቸው ብቻ የሚያርሱትን መሬት ቀምተው አሳርሰውባቸዋል፡፡ ለምን እንቀማለን ዜጎች አይደለንም ወይ ብለው ተቃውሞ
ሲያሰሙ ከፓርቲው ለቃችሁ ካልወጣችሁ መሬታችሁ አይመለስም በማለት የቀበሌው ሊቀመንበር አቶ ፀጋዬ ጎሹ አስፈራርተዋቸዋል፡፡
እንዲሁም በምዕራብ ጎጃም በይልማና ዴንሳ ወረዳ (አዴት) የሚገኙ የመኢአድ አባላት ላይ እስርና አፈና የተፈጸመ ሲሆን አቶ በቃሉ
ደፋሩ የተባሉ የወረዳው አባል ከሳምንት በፊት በፖሊስ ተይዘው እስካሁን ፍ/ቤት አልቀረቡም፡፡
በዚሁ ወረዳ - አቶ አትገኝ እምሬ እንዲሁም
- ቄስ ይሁን ዘለቀ ከሐሙስ ሰኔ 19ቀን 2006ዓ.ም ሌሊት ጀምሮ የደረሱበት አይታወቅም ሲሉ የመኢአድ
የህ/ግንኙነት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አለምነህ ለፍኖተ ነፃነት ዝግጅት ክፍል ገልጸዋል፡፡

ከመኢአድ/አንድነት የውህደት አመቻች ኮሚቴ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ!!!

የኢትዮጵያን ህዝብ የለውጥ ፍላጎት እውን ለማድረግ የመኢአድ እና የአንድነት መዋሀድ ወሳኝ የፖለቲካ ምዕራፍ ነው!!!
*****************************************

የኢትዮጵያን ህዝብ የለውጥ ፋላጎት ዕውን ለማድረግ የተቃዋሚው ጎራ በመሰባሰብ አንድ ግዙፍ አማራጭ ኃይል ወደ መገንባት ሊሸጋገር እንደሚገባ መላው የአገራችን ህዝብ ለረጅም ግዜ ሲያሳስብ መቆየቱ የሚታወቅ ነው፡፡
በዚሁ መሰረትም ትግሉ የሚጠይቀውን የፖለቲካ ተክለ ቁመና ለመያዝ የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የደረሱበትን ወሳኝ የፖለቲካ ምዕራፍ እውን ለማድረግ ከሁለቱም ፓርቲዎች በእኩል ቁጥር የተቀወከሉ አሥር አባላት ያሉት የውህደት አመቻች ኮሚቴ ተቋቁሞ የውህዱን ጉባኤ በስኬት ለማጠናቀቅ በርካታ ተግባራት በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
የውህደት አመቻች ኮሚቴው ሁለቱ ታርቲዎች በተናጠል የሚያካሂዱት እና በጋራ ውህዱ ፓርቲ የሚያደርገው ጉባኤ በተያዘለት ግዜ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ተግባር በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ የሁለቱ ፓርቲዎች መዋሃድ ከፍተኛ ስጋት የፈጠረበት ገዥው ፓርቲም ሆነ ሌሎች አካላት በውህደቱ ሂደት ላይ ተግዳሮት ለመደቀን በርካታ ጥረት እያደረጉ እንደሆነም አስተውለናል፡፡
ስለሆነም መላው የሀገራችን ህዝብ ጉዳዩን በንቃት እንዲከታተልና ገዥው ፓርቲ ከፍተኛ በጀት በመመደብ ከግሉ ሚድያ ጋር ተመሳስለው አፍራሽ ተልእኮ እንዲፈጽሙ ባደራጃቸው አካላት እና ሚዲያዎች ሁለቱ ፓርቲዎች የህዝብ ጥያቄ ለመመለስ የሚያደርጉትን ጥረት በማጠልሸቱ ተግባር ላይ እንዲሰማሩ እየተደረገ ያለውን ስውር ሴራ በጥንቃቄ ማየት እንደሚገባ ለመጠቆም እንወዳለን፡፡
የሁለቱ ፓርቲዎች መዋቅርም ሆነ ዋነኛ ባለቤት የሆነው የውህደት አመቻች ኮሚቴው መረጃዎችን በጥንቃቄ እንደሚከታተል እና ይፋ እንደሚደረግ እየገለፅን በአጭር ጊዜ ውስጥ ውህደቱን በማጠናቀቅ ወደ ቀጣይ ምዕራፍ እንደምንሸጋገር ለመላው ህዝባችን እንገልጻለን፡፡ ስለሆነም በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ለውህደቱ መሳካት አስፈላጊውን የፋይናንስ፣ የማቴሪያል፣ የሞራልና የሀሳብ ድጋፍ በማድረግ ሀገራዊ ሃላፊነታችንን በጋራ እንድንወጣ ጥሪ እንቀርባለን፡፡
በ1997 ዓ.ም የታየውን የህዝብ የለውጥ ፋላጎት እና የፖለቲካ ተሳትፎ ዳግም ለመመለስ ሳንታክት እንሰራለን!!!
ከውህደት አመቻች ኮሚቴ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ
ሰኔ 26 ቀን 2006 ዓ.ም
አዲስ አበባ