ረቡዕ 17 ፌብሩዋሪ 2016

መኢአድ ፓርቲ እርስ በርሱ ሲባላ በደቡብ የወያኔ-ደህንነት ቢሮ ሶስት የተቃዋሚ አመራሮችን አፍኗል::

  ‬

ወያኔ ሰላማዊ ፓርቲዎችን እና አመራሮችን ማሸበሩን ቀጥሏል::በኢንጂነር ሃይሉ ሻውል ፓርቲ መኢአድ ውስጥ በፕሬዚደንቱ አበባው መሃሪ እና በማእከላዊ ምክር ቤቱ መካከል በተነሳው አምባጓሮ ደክሞ የነበረው ፓርቲ ተሽመድምዶ እየሞተ ነው ሲሉ አባላቱ ማማረራቸው ሲታወቅ አቶ አበባ ያልታወቀ ሃይል መከታ በማድረግ የፍርድ ቤት ማገጃ በመጣስ ማህተሙን ለሕገወጥ ስራ እየተጠቀሙበት ነው ሲሉ አባላቱ ይናገራሉ::
አቶ አበባው መሃሪ በመኢአድ ማዕከላዊ ምክርቤት በጥር 15 ቀን, 2008 ዓ.ም ከፕሬዚዳንትነት ሃላፊነታቸው የማንሳቱን ውሳኔ እና በጥር 23 ቀን, 2008 ዓ.ም በፍርድቤት ተከሰው የድርጅቱን ማህተም እንዳይጠቀሙ መታገዳቸውን አምነው እና አክብረው ከተቀበሉ በኋላ ፤በህገወጥ መንገድ የፓርቲው ማዕከላዊ ምክር ቤትን ውሳኔ እና የፍርድቤት የዕግድ ትዕዛዝ በመጣስ የፓርቲውን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ እንድሪያስ ጨምሮ ሌሎች የላዕላይ ምክር ቤት አባላትን በግላቸው አግጃለው እያሉ ደብዳቤ እያሰራጩ መሆኑ ስለተደረሰባቸው ፓርቲው በማጭበርበር ወንጀል ሕግ ሊጠይቃቸው ነው ። ሲሉ አባላቱ ተናግረዋል::
ይህ በእንዲህ እንዳለ በደቡብ ክልል ሲዳማ አርነት ንቅናቄ አመራሮች ባለታወቀ ምክንያት ከያሉበት በደህንነት ሃይሎች ታፍነው መታሰራቸው ታውቋል።በዚህም መሰረት የታፈኑ አመራሮች
1ኛ ደሳለኝ ሜሳ(ሲአን ፖሊቲካ ዘርፍ ኃላፊ )
2ኛ ተሾመ ደበበ (የሲአን ወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ)
3ኛ ደበሳ ዳካ ( የሲአን ቱላ ዞን ሊቀመንበር) ሲሆኑ የደቡብ ክልል ደህነቶችና ፖሊሶች ተባብረው አመራሮቹ በማፈን ወደ ተለያዩ እስር ቤቶች መወሰዳቸው ታውቋል::

ሰማያዊና መድረክ ከስዊድን የፓርላማ አባላት ጋር ተወያዩ

Negere Ethiopia's photo.

የሰማያዊ እና የመድረክ ፓርቲዎች አመራሮች ከስዊድን የፓርላማ አባላት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ተናግረዋል፡፡
የፓርቲዎቹ አመራሮች የሆኑት ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ፣ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት እና ዶ/ር መረራ ጉዲና ከስዊድን ፓርላማ የውጭ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ልዑክ ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ዛሬ የካቲት 9/2008 ዓ.ም መወያየታቸው ታውቋል፡፡
የፓርቲ አመራሮቹ ከስዊድን ስድስት ፓርቲዎች ከተውጣጡ 11 የልዑካኑ አባላት ጋር በተወያዩበት ወቅት በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በኦሮሚያ በተቀሰቀሰው የህዝብ ተቃውሞ እና በጋምቤላ ክልል ስለነበረው ግጭት ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡
Negere Ethiopia's photo.
አመራሮቹ ለተቃውሞ አደባባይ በወጣው ህዝብ ላይ የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እየወሰዱት ያለውን እርምጃ በተመለከተም በውይይታቸው አንስተዋል፡፡
አሁን ላይ በኢትዮጵያ የተቃውሞ ድምጽ የሚያሰሙ የፓርቲ አባላትን እና በነጻነት ስራቸውን በሚያከናውኑ ጋዜጠኞች ላይ እንዲሁም በአጠቃላይ ተቃውሞ በሚያሰማው ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው አፈና እየጨመረ መሆኑንና በሀገሪቱ ፓርላማም አንድም ተቃዋሚ ድምጽ የማይሰማበት መሆኑን እንደገለጹላቸው ታውቋል፡፡
የስዊድን ፓርላማ አባላትም የተቃዋሚ ፓርቲዎች እያደረጉት ስላለው የፖለቲካ እንቅስቃሴና በጋራ ስለሚሰሩበት ጉዳይ ጥያቄ አንስተው በፓርቲዎች አመራሮች ገለጻ እንደተደረገላቸው ኢ/ር ይልቃል ተናግረዋል፡፡
የስዊድን የፓርላማ አባላት ጠ/ሚ ኃ/ማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ከተለያዩ የመንግስት አካላት ጋር እንደተወያዩም ለማወቅ ተችሏል፡፡

ረቡዕ 3 ፌብሩዋሪ 2016

በኦሮሚያ ክልል አዲስ የጸጥታና የደህንነት/ስለላ መዋቅር ሊዘረጋ ነው::በጋምቤላ የሕወሓት ባለስልጣናትና ቤተሰቦቻቸው ንብረት በታጠቁ የደቡብ ሱዳን ቅጥረኞች እና በአግአዚ ወታደሮች መጠበቅ ተጀምሯል::


ልዩነት ውበት ነው…ግን አልፈጠረብንም::መቻቻል ያልተጋባቸው ያልበሰሉ ጭፍኖች በ2 ጽንፍ ማሕበራዊ ድህረገጾችን ወረዋል:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎Gambella‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬
በኦሮሚያ ክልል አዲስ የጸጥታና የደህንነት/ስለላ መዋቅር ሊዘረጋ ነው::በጋምቤላ የሕወሓት ባለስልጣናትና ቤተሰቦቻቸው ንብረት በታጠቁ የደቡብ ሱዳን ቅጥረኞች እና በአግአዚ ወታደሮች መጠበቅ ተጀምሯል::
===========================================================
Minilik Salsawi – በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ አከባቢዎች አሁንም ውጥረት የነገሰ መሆኑን የደህንነት ቢሮ የሚደርሱ ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙ ለጉዳዩ ቅርበት ያላችው ወገኖች መረጃ ሰጥተዋል::በኦሮሚያ ክልል በጥሩ ክፍያ በፎቶግራፍ እና በቭድዮ ቀረጻ ላይ ተሰማርተው የነበሩ የኦሕደእድ ካድሬዎች እየተለቀሙ መሆኑ ታውቋል::የወያኔው ጁንታ አገዛዝ አስፈላጊውን ግድያና የጅምላ እስር ከፈጸመ በኋላ ለይስሙላ የመለሳለስ ባሕሪያ በማሳየት የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን አቆምኩት እንዲሁም የሕዝቡ ጥያቄ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ነው በሚል የሰራውን እኩይ ተግባር ለመሸፋፈን ቢዳክርም የሕዝቡ ተቃውሞ እያገረሸ ብሎም እንዳተኮሰ ይገኛል::መሰሪ እና ውሸታም የሆነው የወያኔ አስተዳደር ላይ ላዩን በመለሳለስ ውስጥ ውስጡን አዲስ የጸጥታ እና የደህንነት/ ስለላ መዋቅር ሊዘረጋ ሲሆን ሕዝቡ ግን አሁንም ለአንድ ለአምስት የአፈና መዋቅር ያልተበገረ ለአዲሱም የስለላ መዋቅር እንደሚያስቸውግር ስጋት መኖሩት የወያነ የደህንነት መረጃዎች ጠቁመዋል:: የመዋቅሩ አዘረጋግ በተመለከተ አስፈላጊው ስራ እየተሰራ ሲሆን ይህ መረጃ የደረሳችሁ ማንኛውም የሕዝብ አካላት የወያኔን መዋቅር በማፈራረስ ዳግም ለህዝባዊ እምቢተኝነት እንድትዘጋጁ ምንጮቹ አሳስበዋል::
በጋምቤላ ክልል አኙዋክ ብሄሮች ላይ ከቀያቸው አፈናቅሎ በሕወሓቶች ለመተካት በደቡብ ሱዳን ቅጥረኛ ኑዌሮች የተጀመረው ግድያ እና ማሳደድ የቀጠለ ሲሆን የሕወሓት ባለስልጣናትና ቤተሰቦቻቸው ንብረት በታጠቁ የደቡብ ሱዳን ቅጥረኞች እና በአግአዚ ወታደሮች መጠበቅ ተጀምሯል::በአኙዋክ ሕዝብ ላይ እጅግ አደገኛ የሚባልለት ይህ የዘር ማጽዳት ከዚህ ቀደም የተካሄደ ሲሆን ለም መሬቶችን ለመቀራመት ባሰፈሰፉ የሕወሓት ስዎች እና ጋሻጃግሬዎቻቸው የደቡብ ሱዳን ኑዌር ስደተኞችን በማስታጠቅ አከባቢው በደም እንዲጨቀይ አድርገዋል::በአለም አቀፉ እና በሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ጫና ግጭቱ ራሱ በከፈተው መንገድ ራሱ ያቀዘቀዘው ሕወሓት አሁንም በበቂ ሁኔታ ለመስፋፋት እና አዳዲስ ለም መሬቶችን ለመያዝ እንዳቀደ በስፋት እየተነገረ ይገኛል::በሃገሪቱ ከባድ እና አደገኛ ውጥረት በመጫር ዘእጎች በሞት እንዲያልኡ እያደረገ የሚገኘውን የሕወሓት አገዛዝ ከስሩ ነቅሎ ለመጣል ትግላችንን አጠናክረን መቀጠል እንዳለብን አሳስባለሁ:: ‬
Minilik Salsawi's photo.

ማክሰኞ 2 ፌብሩዋሪ 2016

የመኢአድ ላዕላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንቱን አገደ

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ላዕላይ ምክር ቤት ሰኞ ጥር 16 ቀን 2008 ዓ.ም. ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ፣ የፓርቲውን ፕሬዚዳንት አቶ አበባው መሐሪን አገደ፡፡ ቀጣዩ ጠቅላላ ጉባዔ እስከሚካሄድ ድረስም ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ እንድርያስ ኤሮ ፓርቲውን እንዲመሩ ወስኗል፡፡
‹‹ፕሬዚዳንቱ ስብሰባ እንዲጠሩንና ጠቅላላ ጉባዔ እንዲካሄድ በተደጋጋሚ ብንጠይቅም ፈቃደኛ ካለመሆን አልፈው፣ ወደ አምባጓሮ በመግባታቸው ይህን ለመወሰን ተገደናል፤›› ሲሉ ተቀዳሚ ፕሬዚዳንቱ አቶ እንድርያስ ለሪፖርተር አስታውቀዋል፡፡
ፓርቲው ከገዥው ፓርቲ የሚደርሱበት ጫናና ፈተናዎች እንደተጠበቁ ሆነው፣ ጥቂት የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች የውስጥ ችግሮችን ተወያይተው እንዳይፈቱ መሰናክል እየሆኑ ነው በማለት ገልጸው፣ ‹‹የፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ አበባው መሐሪ የላዕላይ ምክር ቤቱን በደንቡ መሠረት ስብሰባ ባለመጥራት፣ እንዲሁም የፓርቲውን ጠቅላላ ጉባዔ በወቅቱ እንዳይካሄድ በማድረግ ላይ ናቸው፤›› በማለት ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ስብሰባ እንዲጠሩ በተደጋጋሚ ጠይቀው እንደነበር የገለጹት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንቱ፣ ‹‹አቶ አበባው ይህን ማድረግ ባለመፈለጋቸው ከአንድ ሦስተኛ በላይ የምንሆን የምክር ቤቱ አባላት ተሰባስበን በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መክረን ፕሬዚዳንቱን ለማገድ ወስነናል፤›› በማለት አስረድተዋል፡፡
የፓርቲው ላዕላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንቱን በመተካት እስከ ቀጣይ ጠቅላላ ጉባዔ ድረስም በተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንቱ እየተመራ እንዲቆይም እንዲሁ ወስኗል፡፡
ቀጣይ የፓርቲው ጠቅላላ ጉባዔ መቼ እንደሚካሄድ ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ‹‹በመጪዎቹ ስድስት ወራት ውስጥ ይካሄዳል፤›› ሲሉ አቶ እንድሪያስ መልሰዋል፡፡
ከዚህ ውሳኔ በተጨማሪም የፓርቲው ላዕላይ ምክር ቤት ምንም እንኳን የፓርቲው ፕሬዚዳንት የሥልጣን ዘመናቸው የተጠናቀቀ ቢሆንም፣ በመጪው ጠቅላላ ጉባዔ የፓርቲውን ሙሉ ሪፖርት፣ የውስጥና የውጭ ኦዲተሮችን ሪፖርትን ያካተተ ሪፖርት ይዘው እንዲቀርቡም መወሰኑ ተሰምቷል፡፡
የላዕላይ ምክር ቤቱ አባላትም ባወጡት መግለጫ፣ ‹‹እኛ የመኢአድ የላዕላይ ምክር ቤት አባላት መጪው ጠቅላላ ጉባዔ እስኪደረግ ድረስ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንቱና አመራሩ የሚያወርደውን ማንኛውም የድርጅቱ ሥራዎችን ለማከናወን ዝግጁ መሆናችንን እናረጋግጣለን፤›› በማለት ለተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ይሁንታውን መግለጹን አስታውቋል፡፡
ምርጫ 2007 ከመከናወኑ ወራት በፊት መኢአድ ተመሳሳይ ችግር አጋጥሞት እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ በወቅቱ ፓርቲውን በፕሬዚዳንትነት ለመምራት በአቶ ማሙሸት አማረና በአቶ አበባው መሐሪ መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ ነበር፡፡
በወቅቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሰጠው ውሳኔ መሠረት አቶ አበባው የፓርቲው ፕሬዚዳንት ሆነው እንዲቀጥሉ መደረጉ የሚታወስ ነው፡፡
በመኢአድ ላዕላይ ምክር ቤት ከፕሬዚዳንትነት ሥልጣናቸው የታገዱትን አቶ አበባው በአካልም ሆነ በተንቀሳቃሽ ስልካቸው ለማግኘት የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡

እሑድ 31 ጃንዋሪ 2016

ኢንሳ የአየር ላይ ፎቶ በማንሳት ላይ የሚገኘው ለሱዳን ተሰጥቷል የሚባለውን አልፋሽጋ ተብሎ የሚጠራውን አካባቢ መሆኑ ታወቀ

ጥር ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ካለፈው ጥር ወር መግቢያ ጀምሮ የአየር ላይ ፎቶ እየተነሳ ያለው አካባቢ የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ” ኢትዮጵያ መሬቱ የእኛ መሆኑን እውቅና ሰጥታለች” በማለት ለአልጀዚራ የተናገሩት አልፋሽጋ እየተባለ የሚጠራው ቦታ መሆኑ ታውቋል።Ethiopian Border Affairs Committee
ትናንት ኢሳት የመረጃና ደህንነት ኢንፎረሜሽን ባለሙያ በማናገር በሰራው ዘገባ ላይ በአሁኑ ሰአት የአየር ላይ ፎቶ ለማንሳት ምልክቶችን መሬት ላይ የማስቀመጡ ስራ የሚከናወነው 365 ኪሜ ርዝመት ባለው ቦታ ላይ መሆኑን ቢዘግብም፣ ይህ ርቀት ግን የአየር ላይ ርቀትን የሚያመለክት እንጅ የመሬትን እርቀት የሚያመለክት ባለመሆኑ ማስተከከያ እንዲደረግበት ጠይቀዋል። በመጀመሪያው ሂደት ድንበር የማካለሉ ሂዳት የሚከናወነው 725 ኪሜ ርዝመት ላይ ባለው መሬት ላይ ሲሆን፣ ይህም አካባቢ ሱዳን የኢትዮጵያ መንግስት የእኔ መሬት መሆኑን አምኖልኛል በማለት የገለጸችው አልፋሽጋ እየተባለ የሚጠራውን ለም መሬት የሚያካትት ነው።
አልፋሽጋ የሚባለው ቦታ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ከመለየቷ በፊት ከራስካሳር እስከ አትባራ የሚደርሰውን ቦታ ያካልል እንደነበር የሚገልጹት ባለሙያዎች፣ የኢህአዴግ መንግስት ለማስረከብ እየተዘጋጀ ያለው ከሰቲት ወንዝ እስከ አትባራ ድረስ ያለውን 725 ኪሜ የሚደርስ ሰፊ መሬት ነው። አልፋሽጋ በደቡብ አጥባራ፣ በሰሜን ሰቲት ማሃል ላይ ባህረነጋሽ በተባለ ወንዝ የተከበበ በመሆኑ፣ መሬቱ ለእርሻ ስራ እጅግ ተስማሚ ነው።
በሁለተኛው ዙር መሬት የማካለል ስራ ከሁመራ ጫፍ እስከ ኤልሚ ወይም የሱዳን፣ ኬንያና ኢትዮጵያ መገናኛ ድንበር ድረስ እንደሚካሄድ ባለሙያዎች ገልጸዋል።
የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አልፋሽጋ ሱዳን መሆኑን ኢትዮጵያ ማረጋገጫ ሰጥታለች ቢሉም፣ በኢህአዴግ መንግስት በኩል እስካሁን ምንም አይነት ማስተባበያ አልተሰጠም። ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያምና ቃለአቀባዩ ጌታቸው ረዳ ከሱዳን ጋር ምንም አይነት የድንበር ማካለል ድርድር እየተካሄደ እንዳልሆነ ገልጸው ነበር።
ሱዳኖች በበኩላቸው የሁለቱ አገራት የድንበር ኮሚቴ ስራውን በማጠቃለል ላይ መሆኑንና የመጀመሪያው ድንበር የመለየት ስራ በቅርቡ እንደሚጀመር ገልጸዋል።
የኢህአዴግ መንግስት የድንበር ጉዳዩን ለህዝብ ለምን ግልጽ ማድረግ እንደተሳነው የታወቀ ነገር የለም። መሬቱን በድብቅ ለማስረከብ የሚደረገው ሂደት በሁለቱ አገራት መካከል ሰላም ያመጣል ተብሎ አይታመንም።
የአካባቢው ነዋሪዎች በእርሻ ማሳዎች ላይ የሚተከሉትን ምልክቶች በመንቀል ተቃውአቸውን እንዲገልጹ ባለሙያዎች ጥሪያቸውን በድጋሜ አቅርበዋል።

ዓርብ 8 ጃንዋሪ 2016

ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በዋሽንግተን ዲሲ የፊታችን ሰኞ ጃንዋሪ 25 / 2015 በኣሜሪካ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት

US Department of State
2201 C St NW
Washington, DC. 20520
Date and Time:
Monday 25th January 2016 at 9:00 AM
Dress code Black
Image
Organizers: Ethiopian Orthodox Religious Leaders, Ethiopian Muslim Leaders (First Higrah), Ethiopian Evangelical Religious Leaders, United OLF, Moresh Wegene, All Amhara Peoples Party, United Ethiopian Muslims Peaceful Movement Support Group, Patriotic Ginbot 7, EPRP, Shengo, AEDP Support Group, SMNE, DC Joint Task Force, Border Committee, SOCEPP, Netsanet Radio

ማክሰኞ 5 ጃንዋሪ 2016

በወቅታዊ የአገራችን አሳሳቢ ጉዳዮች ላይ ለመምከር የተዘጋጀ የዉይይት መድረክ — በዋሽንግተን ዲሲ


የኢትዮጵያ እና የህዝቦቿ የወደፊት እጣ ፈንታ አሳስበዎታል? ያገርዎ፣ የባህልዎ፣ የእምነትዎ ወዘተ ጉዳይ ያገባኛል ይላሉ? እዉነተኛ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር፣ የህግ የበላይነት፣  ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ስርዓት እንዲመጣ ይሻሉ? ለነዚህ እና ለመሳሰሉት አንገብጋቢ ጉዳዮች ገንቢ ሃሳብ ለመስማት እና የርስዎንም ለማካፈል እንዲሁም ባገር ዉስጥ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች እቅድ እና እንቅስቃሴን ለመረዳት በዚህ ዝግጅት ላይ ተካፋይ ይሁኑ!
ተጋባዥ እንግዶች:
(ከአዲስ አበባ)
ዶ/ር መረራ ጉዲና
ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት
አቶ ነጋሲ በየነ
(ከዋሺንግቶን ዲሲ)
አቶ ሀይለገብርኤል አያሌው
አቶ ሄኖክ ጋቢሳ
አወያይ:
አቶ ጥበበ ሳሙኤል
ቀን:       እሁድ Jan 10, 2016    ሰአት:  2pm
ቦታ: 7701 16th St NW, Washington DC, 20012
አዘጋጅ:     የሰማያዊ አንድነት ድጋፍ በሰሜን አሜሪካ
ለተጨማሪ መረጃ: ስልክ፥ (202) 556-3078
ኢሜል፥ info@semayawiusa.org
ድህረ ገጽ፥ www.semayawiusa.org
ይህ ዉይይት የሚካሄደው በአዲስ አበባ እና በዋሺንግቶን ዲሲ በቪዲዮ ግንኙነት ስለሆነ በሁለቱ ከተሞች መካከል ያለዉን የሰአታት ልዩነት ታሳቢ በማድረግ ፕሮግራሙ በሰአቱ የሚጀመር መሆኑን አዘጋጆች ማሳሳብ እንሻለን። እርስዎም ከጥሪው ሰአት ቀደም ብለዉ በመገኝት እንዲተባበሩን በማክበር እንጠይቃለን።